St.Paul's Hospital Millennium Medical College
22.1K subscribers
3.67K photos
39 videos
23 files
583 links
St. Paul's is a leading public hospital and medical college in Addis Ababa, Ethiopia.
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የስኳር ህመም እና የኮቪድ-19 በሽታ
t.me/spmmc
አንድ ግለሰብ የስኳር ህመም ቢኖርበት በቀጥታ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ተጠቂ አይሆንም፣ ነገር ግን የስኳር ህመም በተለይም በቁጥጥር ስር ያልዋለ ከሆነ ለከፋ የኮሮና በሽታ ሊዳርግ ስለሚችል ታካሚዎች ተገቢውን ህክምናና ክትትል እንዲያደርጉ ይመከራል፡፡
በተለይም ከስኳር ህመም ጋር ተደራራቢ የጤና ችግር እንደልብ ህመም፣ደም ግፊት፣ አስም ያለባቸው ታካሚዎች ለከባድ ህመም ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡ የኮሮና ቫይረስ ህመም የስኳር ቁጥጥሩን ሊያውክ ይችላል፡፡
በተለይ በአይነት አንድ የስኳር ህሙማን ላይ መርዛማ አሲዶችን በመጨመር የሚከሰትን ድንገተኛ የስኳር መጨመር ሁኔታን (DKA) ሊያስከትል ይችላል፡፡ የኮሮና በሽታ ሲጠና በሰውነት ውስጥ የደም መርጋትና መዛባትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር እንደ አዲስ የስኳር ህመም የሚገኝባቸው ሰዎች እየጨመረ በመምጣቱ ምናልባት ቫይረሱ ኢንሱሊን የሚያመርቱ ቆሽት ውስጥ ያሉ ህዋሶች ሊያጠቃ ይችላል የሚሉ ሳይንሳዊ መላምቶች እየወጡ ይገኛሉ፡፡
አንድ የስኳር ታካሚ በኮሮና የተያዘ እንደሆነ ለቫይረሱ በሚመከረው መልኩ እራሱን ከመንከባከብ በተጨማሪ ስኳሩን መከታተል፣ መድሃኒቱን በአግባቡ መውሰድ፣ ሀኪሙን ማማከር እንደአስፈላጊነቱ የሚሰጡትን የመድሃኒት ማስተካከያና ምክር መተግበር አለበት፡፡
የከባድ የኮሮና ህመም ምልክቶች ትንፋሽ ማጠር፣ደረት መጫንና፣ ራስ መሳት ከታየ በአስቸኳይ በራስ ወይም በቤተሰብ አባል ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ የህክምና እርዳታ ማግኝት ያስፈልጋል፡፡
የኮቪድ-19 በሽታ በስኳር ህሙማን ላይ የሚያስከትለው የጤና እክል የጠነከረ ሊሆን ስለሚችልና በሽታውን የሚያድን እስከ አሁን የተረጋገጠ መድሃኒትም ስለሌለ አዘውትሮ እጅን በሳሙና ውሃ በመታጠብ፣ አልኮል ያላቸውን የጀርም ማፅጃ በመጠቀም፣የአፍና የአፍንጫ ጭንብሎችን በመጠቀም ርቀትን በመጠበቅ፣ ያለአስፈላጊ ጉዞዎችንና ንክኪዎችን በማስቀረትና፣ ተገቢውን ጥንቃቄዎች በሙሉ በማድረግ ከበሽታው ራስን፣ቤተሰብንና ማህበረሰብን ይጠብቁ፡፡
ለመሆኑ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ለምን ይጠቅማል?

ሰዎች በሚያስሉበት፣ በሚያስነጥሱበትና በሚያወሩበት ጊዜ ከአፍ የሚወጡ ፍንጣቂዎች በአየር ላይ ተለቀው በቅርበት ባለው ሰው አፍና አፍንጫ ያርፉና በመተንፈስ ሒደት ወደ ሳምባ ይገባሉ፡፡ ስለሆነም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ፡-

በዋነኝነት ከአፍ የሚወጡ ብናኞችን ወደ ሌላ ሰው እንዳያልፉ ስለሚገድባቸው፣ የኮሮና ቫይረስ ከትንፋሽ ጋር በሚወጡ ብናኞች ምክንያት የሚተላለፍበትን መንገድ ለመቀነስ ይጠቅማል፤
በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው ቫይረሱን ወደ ሌላ ሰው እንዳያስተላልፍ ይከላከላል፤
ቫይረሱ፣ ከአፍ በሚወጡ ብናኞች አማካይነት በቫይረሱ መያዛቸውን ካላወቁና ምልክቶችን ካላሳዩ ሰዎች ወደ ሌላው ሰው እንዳይዛመት ይከላከላል፤
በተለይ ደግሞ ሰዎች በሚበዙበትና ማኅበራዊ/አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በማይቻልበት ሁኔታ (በመገበያያ ሥፍራዎች፣ በሕዝብ ማመላለሻ መኪናዎች፣ ርቀትን ጠብቆ ለመሥራት የማያስችሉ የሥራ ቦታዎች) እጅግ ወሳኝ የሆነ የመከላከያ መንገድ ነው፡፡
ስለሆነም ጭምብል ማድረግ ቫይረሱ ከሌላ ሰው እንዳይተላለፍብን ራሳችንን ለመከላከል ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ለመጠበቅ ጭምር የምናከናውነው፣ ለሌሎች አሳቢ መሆናችን የሚገለጽበት የትብብር ድርጊት ነው፡፡
ነገር ግን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው እንዳይተላለፍ የሚረዱ ሌሎች ጥንቃቄዎችን በሙሉ ሊተካ አይችልም፡፡ የቫይረሱን መስፋፋት የሚቀንሰው ማኅበራዊ ርቀትን ከመጠበቅና ከሌሎች የተለያዩ የመከላከያ ተግባራት ጎን ለጎን ዘወትር ሲተገበር መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል፡፡

የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ የት የት መደረግ አለበት?

የኮሮና ቫይረስ ካለበት ሰው ከአፍ የሚወጡት ጠብታዎች በቅርበት (ከሁለት ሜትር ባነሰ ርቀት) ወዳለ ሰው ይገባሉ፡፡ ስለሆነም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ የሚገባን ሥፍራዎች የሚከተሉት ናቸው (የበሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል ሐምሌ 30 ቀን 2012)

ሕዝብ በሚበዛባቸው ሥፍራዎች ላይ ሲገኙ (የመገበያያ ሥፍራዎች፣ የሕዝብ ማመላለሻ መኪናዎች፣ ወዘተ…)፤
አብረዋቸው ከሚኖሩ የቤተሰብ አባላት ውጪ ከሆኑ ሰዎች ጋር ሲገናኙ፤
ማኅበራዊ ርቀትን ለመጠበቅ አስቸጋሪ በሚሆንበት ሁኔታ ላይ ሲሆኑ፤
የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አብዛኛዎቹ ኮቪድ-19 ያለባቸው ሰዎች የሕመሙ ምልክቶች የማይታዩባቸው በመሆናቸው ቫይረሱን በቀላሉ ወደ ሌላ ሰው ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ከቤት ውጭና ሕዝብ በሚበዛቸው ሥፍራዎች በምንሆንበት ጊዜ ሁሉ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የሥራቸው ሁኔታ (መመገቢያ ሥፍራዎች፣ ሱቆች፣ ወዘተ…) አብዛኛውን ጊዜ ከሰዎች ጋር የሚያገናኛቸው ሰዎችና በቫይረሱ ከተያዙ ለከፍተኛ ሕመም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች መሸፈኛውን ማድረግ አለባቸው፡፡
ለመሆኑ የማህፀን በር ካንሰር ምንድ ነው ?
t.me/spmmc
ይህ የካንሰር ዓይነት ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ በተሰኘ ረቂቅ ተህዋስ አማካኝነት የሚከሰት ነው፡፡
ተህዋሱ የማህፀን በር ህዋሳትን ጤናማ ያልሆነ ዕድገትና ብዜትን እያስከተለ ወደ ሌሎች የአካል ክፍሎች በመሰራጨት የሰውነትን ተለምዶአዊ ተግባር በማወክ የብዙ ሴቶችን ህይወት በመንጠቁ የታወቀ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በሽታው ስር ሳይሰድ በምርመራ ከተደረሰበት ታክሞ መዳን ይቻላል፡፡
ለማህፀን በር ካንሰር ተጋላጭ የሆኑት እነማን ናቸው ?
ማንኛውም የግብረ ስጋ ግንኙነት ፈፅማ የምታውቅ ሴት ለማህፀን በር ካንሰር ዋነኛ መንስኤ ለሆነው ሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ የመጋለጥ አጋጣሚ አላት፡፡
ይበልጥ ለችግሩ የሚጋለጡ ሴቶች፡
 በለጋነት ዕድሜ (ከሃያ ዓመት ዕድሜ በታች) የግብረ ስጋ ግንኙነት የጀመሩ ሴቶች፣
 ከተለያዩ ወንዶች ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሴቶች፣
 ከተለያዩ ሴቶች ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት የሚፈጽሙ የወንድ ጓደኞች ያላቸው ሴቶች፣
 በተለያዩ ምክንያቶች የሰውነት በሽታ የመቋቋም ሃይል መቀነስ ያጋጠማቸው ሴቶች (ለምሳሌ ኤች.አይ.ቪ በደማቸው ውስጥ ያለ፣የመከላከል ዓቅምን የሚቀንስ መድሃኒት የሚወስዱ፣ ወዘተ)፣
 በአባላዘር በሽታዎች የተያዙ ሴቶች እና፣
 ሲጋራ የሚያጤሱ ሴቶች
ምርመራና ህክምናውስ ?
የማህፀን በር ካንሰር የመስፋፋት ሂደቱ በጣም አዝጋሚ በመሆኑ ቅድመ ካንሰር ምርመራ በማድረግ፡ በሽታው ተባብሶ ለህይወት አስጊ ከመሆኑ በፊት ታክሞ መዳን ይችላል፡፡
የማህፀን በር ካንሰር መኖር ያለመኖሩ ለመለየት የተለያዩ ምርመራዎች ይደረጋሉ፡፡
የምርመራ ውጤቱ ለካንሰር የመጋለጥ ሁኔታን ካመላከተ ተገቢው ህክምና ተደርጎ ለመዳን ይችላል፡፡
በምርመራ ወቅት የቅድመ ካንሰር ምልክት ከታየ ክራዮቴራፒ ወይም ሊፕ የተባሉት ህክምናዎች በመውሰድ የማህፀን በር ካንሰርን ከ90 በመቶ በላይ መከላከል ይቻላል፡፡
የበሽታው ስሜቶችና ምልክቶች ?
የማህፀን በር ካንሰር ሥር እስኪሰድና እስኪባባስ ድረስ ምንም ዓይነት ስሜት ወይም ምልክት ሳይኖረው ከ15 እስከ 20 ዓመት ሊቆይ ይችላል፡፡
በሽታው እየተባባሰ ሲሄድ ግን የተለያዩ በማህፀን አካባቢ በሚከሰቱ የህመም ምልክቶች ችግሩ ይገለጣል፡፡

የማህፀን በር ካንሰር መከላከያና መቆጣጠሪያ ዘዴዎችስ ?

 ከሃያ ዓመት ዕድሜ በፊት የግብረ ስጋ ግንኙነት አለመፈጸም፡፡ ከሃያ ዓመት ዕድሜ በታች የሚገኙ ሴቶች የማህፀን በራቸው ያልዳበረና ለሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስ መስፋፋት አመቺ በመሆኑ ለችግሩ ተጋላጭችነታቸውን ከፍ ያደርጋል፡፡
 ኤች.ፒ.ቪ ክተባትን መከተብ፣
 አንድ ለአንድ መወሰን፣
 የአባላዘር በሽታዎችን መከላከል፣
 ሲጋራ ያለማጤስ፣
 አስፈላጊውን ምርመራ በየጊዜው ወደጤና ድርጅቶች ሄዶ ማድረግ፣
 ኮንዶምን በአግባቡ እና ሁልጊዜ መጠቀም፣ ሆኖም ግን ኮንዶም የኤች.አይ.ቪ መተላለፍን ሙሉ ለሙሉ እንደሚከላከለው ሁሉ የሂውማን ፓፒሎማ ቫይረስን መተላለፍ አይከላከለልም፡፡

ልብ ይበሉ!
የማህፀን በር ካንሰር በምርመራ ሊታወቅና ስር ሳይሰድ ከተደረሰበት በህክምና ሊድን ይችላል፡፡
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በዘር የሚተላለፈውን "የcystic fibrosis" በሽታ ምርመራ በቅርቡ ይጀምራል፡፡
ከወላጆች ወደ ልጆች የሚተላለፈው ይህ በሽታ በሣንባ ላይ ጉዳት በማድረስ የምግብ ማሣለጥ (መፍጨት) ሥርዓትን ያናጋል፡፡ አየር መተንፈሻ አካላትን የአየር ቧንቧ፣አንጀትን፣ ሆርሞን የሚያመነጩ ክፍሎችንም በእጅጉ ይጎዳል፡፡
በሃገራችን በሽታው ሊኖር እንደሚችል ቢታመንም አስከዛሬ የምርመራ መሣሪያ ባለመኖሩ የስርጭቱ መጠንን በውል ለማወቅ አልተቻለም፡፡
ኮሌጁ P’ cystic fibrosis በሽታ ምርመራ አገልግሎቱን ለመጀመር ያስቻለው፤ ከአንድ ዓለም አቀፍ ድርጅት 1.6 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መሣሪያ በማግኘቱ ነው፡፡
የሐዘን መግለጫ
t.me/spmmc
የኮሌጃችን ሲኒየር አንስቴቲስት የሆኑት ገብረሥላሴ አባዲ በኮቪድ ሕመም ሳቢያ በሞት ተለይተውናል። በቀድሞው የከፋ ክፍለ ሀገር በ1976 ዓ.ም በሙያቸው ሥራ የጀመሩ ሲሆን በቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ከ1987 ዓም ጀምሮ በተለያየ የሥራ ኃለፊነት ደረጃዎች አገልግለዋል። አቶ ገብረሥላሴ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ናቸው። የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ማሕበረሰብ ለቤተሰብ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መጽናናትን ይመኛል።
ለቅዱስ ጳውሎስ ማሕበረሰብ በሙሉ

ዛሬ 4:00 የአቶ ገብረሥላሴ አስከሬን ሽኝት ይደረጋል።
ስለዚህ 4:00 5ኛ በር እንድትገኙ ይሁን ።
መኪና የተዘጋጀ በመሆኑ ቀብር መሄድ ትችላላችሁ ።
የኢትዮጽያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮቪድ- 19 ምርመራ ማዕከላትን ይፋ አድርጓል። ምርመራ ማድረግ የሚፈልጉ በሚመቻቸውና በአቅራቢያቸው በሚገኙ የጤና ተቋማት አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ። ለአገልግሎቱም ነጻ ነው።( የማዕከላቱን አድራሻ ይመልከቱ)
በአገራችን ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ምን እንደሚመስል የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስትር ክብርት ሊያ ታደሰ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የእርሳቸውን መግለጫ እጥርጥሩን እንዲህ አቅርበናል፡፡
የኮቪድ ምርመራ
በአገራችን የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ አቅማችንን በየጊዜው በማሳደግ እስከአሁን ለ1,683,558 ዜጎች የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን 114,834 (6.8%) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል፤ ከነዚህ ውስጥም የ1,769 (1.5%) በበሽታው ሕይወታቸው አልፏል፡፡
የህሙማን ሁኔታ
በየቀኑ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ለሕክምና ክትትል ወደ ሕክምና ማዕከል ከሚገቡት ታማሚዎች ውስጥ በአማካይ 305 የሚሆኑት ጽኑ ህሙማን ሕክምና ክፍል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም ከ40 እስከ 45 የሚሆኑት ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሣሪያ (Mechanical Ventilator) የሚጠቀሙ ናቸው፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታ የጽኑ ሕክምና ክፍል ከገቡት ውስጥ 59 በመቶ ያህሉ ሕይወታቸው አልፏል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሕብረተሰባችን ውስጥ እየተስተዋለ ያለው ቸልተኝነትና በዚህ ከቀጠለ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ፣ እንደ ሀገር ካለን ውስን የጽኑ ህሙማን እንክብካቤ ከአቅም በላይ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ስጋት አለ፡፡
በአሁኑ ሰዓት የጽኑ ሕክምና አገልገሎት የሚፈልጉ የህሙማን ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ በመሆኑ ( በተለይ በአዲስ አበባ) ከጤና ተቋማት የመቀበል አቅም በላይ ሆኗል፡፡
የማስክ አጠቃቀም
የማስክ አጠቃቀምን በተመለከተ በየሳምንቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጥናት ያደርጋል፡፡ ጥናቱ እንደሚያመለክተው፡ በተለይ በአዲስ አበባ በሰኔና ሐምሌ በተጠናው ጥናት መሰረት አዲስ አበባ 75 በመቶ ህብረተሰቡ ማስክ ይጠቀም ነበር አሁን ላይ ግን ወደ 52 በመቶ ወርዷል። ይህ እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡

ለአገልግሎት ሠጪ ተቋማት ማሳሰቢያ

ሁሉም አገልግሎት ሰጭ ተቋማትና ግለሰቦች ሰራተኞቻቸውም ሆኑ ደንበኞቻቸው የቫይረሱ መከላከያ መንገዶችን መተግበራቸውን በመቆጣጠር ወረርሽኑን በመከላከል ስራ ላይ ያለመዘናጋትና ቸልተኝነት እንዲሰሩና በመመሪያ ቁጥር 30 የተቀመጡትን ግዴታዎች እንዲተገብሩ አደራ ብለዋል፡፡

የሚኒስትርዋ ተማጽዕኖ
ኮቪድ-19 እያደረሰብን እና ሊያስከትልብን የሚችለውን የሰብዓዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ-ልቦናዊ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን የመከላከል ስራ ለአፍታም ቢሆን ጊዜ የማይሰጠው እና ለተወሰኑ ተቋማት የማይተው በመሆኑ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ የሐይማኖት ተቋማት፣ የህብረተሰብ ክፍሎችና ፣ ልዩ ልዩ ማህበራት፣ ቤተሰቦች እና እያንዳንዱ ግለሰብ የመከላከያ መንገዶችን የዕለት ተዕለት የህይወት ተግባራቸው አድርገው እንዲቀጥሉ አሳስባዋል፡፡እማጸናለሁም ብለዋል፡፡
ማጠቃለያ
በዕለት ተዕለት ኑሮአችን እጆቻንን በአግባቡ በማጽዳት፣ በተለይ ደግሞ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በአግባቡ በመጠቀም፣ አካላዊ እርቀታችንን በመጠበቅ እና የሰዎችን በአንድ ቦታ መሰባሰብን የሚያስከትሉ ሁነቶችን በመቀነስ ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል፡፡
በእያንዳንዷ ደቂቃ የምናከናውነው ቅድመ ጥንቃቄ በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስ እና አርዓያነት ያለው ሊሆን እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ (ፎቶ፡ ጤና ሚኒስቴር)
የጡት ማጥባት 12 ጥቅሞች t.me/spmmc
የጡት ወተት ለህፃናት ከምግብነት ባለፈ የሚሰጠው ጥቅምና አንዲት እናት በማጥባቷ ብቻ የምታገኛቸውን ጥቅሞች እናያለን።
ጡት ማጥባት ለልጅሽ

1. ከብዙ ኢንፌክሽኖች ይከላከላል። ለምሳሌ; የሳንባና የጆሮ ኢንፌክሽን፣ የማጅራት ገትር፣ የሆድ ቫይረስ
2. ከአለረጂክ ይከላከላል።
3. ብሩህ አዕምሮ እዲኖራቸው ያደርጋል
4. ከመጠን በላይ ውፍረትን በመከላከል አስተማማኝ እድገት እንዲኖራቸው ያደርጋል
5. በህፃናት ላይ የሚከሰትን ካንሰር መጠንን ይቀንሳል
6. ድንገተኛ የሆነ የጨቅላ ህፃናትን ሞት ይቀንሳል

ጡት ማጥባት ላንቺ

7. በእርግዝና ወቅት ያደገው ማህጸን ቶሎ ወደቦታው ስለሚመለስ የሚፈሰው የደም መጠን ይቀንሳል
8. ከልጅሽ ጋር የሚኖረው ፍቅር ይጨምራል
9. ከወሊድ በኃላ ቶሎ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል
10. እድሜ ሲገፋ የሚፈጠረውን የስኳር በሽታ ይቀንሳል
11. ከጡት እና ከእንቁላል ማምረቻ ካንሰር ይከላከላል
12. ወጪ ቆጣቢ ነው።

(በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት)

ጽሑፉን ከወደዱት(Like) በማድረግ ለሌሎችም (share)ያድርጉት፡፡
Today is Universal Health Coverage Day!

Universal health coverage means that all people have access to the quality health services when and where they need them, including:

🔹Well-trained health workers👩‍⚕️👨‍⚕️
🔹Safe treatment
🔹Access to medicines 💊 and vaccines 💉

We know health for all is possible, let’s make it happen!
የአስም በሽታና እርግዝና

የአስም በሽታ በመላው ዓለም የሚታይ ሲሆን በአየር ብክለት ምክንያት መጠኑ እየጨመረ ይገኛል።
አስም ያለባት ሴት ማረወገዝ ትችላለች ወይ?
አዎን

እርግዝና በአስም ላይ የሚያመጣው ችግር

አስም ካለባቸው ነፍሰ-ጡሮች ውስጥ
· ሲሶዎቹ (1/3)- ከበፊቱ የተለየ ህመም አይታይባቸውም
· ሲሶዎቹ - ይሻላቸዋል
· ሲሶዎቹ - ደግሞ በጣም ይታመማሉ።
በዚህ ምክንያት አስም ያለባት እናት በእርግዝና ጊዜ መድኃኒቷን እንዳታቋርጥ ይመከራል።

አስም በእርግዝና ላይ የሚያመጣው ችግር

አስም ያለባት እናት ከጤነኛዋ በበለጠ
· ለደም ግፊት
· ያለጊዜው መውለድ
· ክብደቱ ትንሽ የሆነ ወይም በማህፀን ውስጥ የቀጨጨ ህፃን
· ሲወለዱ የመታመምና የመሞት እድላቸው ከፍ ያሉ ህፃናትን የመውለድ እድል አላት።

መፍትሄው ፦ አስሙን በተቻለ አቅም እየተቆጣጠሩ ጥሩ የሆነ የእርግዝና ክትትል ማድርግ ይኖርባታል።

ቸር እንሰንብት
በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት