The Ethiopian Economist View
29.3K subscribers
723 photos
4 videos
197 files
1.33K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
ኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ማኅበር (Ethio Telecom S.c) 10% በመቶ ድርሻውን መሸጥ የሚያስችለውን ሥርዓት (Mini App) በቴሌብር ሱፐር አፕ መተግበሪያው ላይ አካቷል።

ዜጎች ይህንን ሼር ከመግዛታቸው አስቀድሞ ስለ አጠቃላይ የሼር ሽያጭ የቀረበ ዝርዝር መረጃ (prospectus) አንብበው መስማማታቸውን መግለጽ ይኖርባቸዋል።

ይህ ዶክመንት ምን ይላል ?

ዶክመንቱ ፥ የሼር መጠን ፤ መግዛት ስለሚቻለው የሼር ብዛት፤ ስለ አክሲዮን ማኅበሩ ዳራ፤ የሂሳብ ሪፖርት መረጃዎችን፤ ቀነ ገደቦችን፤ ስጋቶችን፤ ለማመልከት የሚያስፈልጉ ዝርዝር ሂደቶችን፤ የሼር አከፋፈል ሥርዓቶችን በዝርዝር ያስቀመጠ ነው።

ሂደቶቹ ምን ይመስላሉ ?

ዜጎች በ prospectus ዶክመንቱ እንዲሁም ውል እና ሁኔታዎች (Terms and conditions) ከተስማሙ በኃላ መግዛት የሚፈልጉትን የሼር መጠን በመምረጥ ያመለክታሉ።

የመኖሪያ አድራሻ ፣ መታወቂያ ፣ ፎቶ ፣ ስልክ ቁጥር ጨምሮ ዝርዝር መረጃዎችን ከተሞላ በኋላ ሼር ለመግዛት ማመልከት ይቻላል። እነዚህን መረጃዎች ለማስተካከል እና ክፍያ ለመፈጸም 48 ሰዓት ተሰጥቷል።

ሼር ለመግዛት ካመለከቱ በኋላ ኢትዮ ቴሌኮም የክፍያ ሂደቱን እንዲሁም ያስገቡት ዝርዝር መረጃ የማጣራት ሂደት የሚያካሂድ ሲሆን ሂደቱን ካለፉ የተሳካ ማመልከቻ ዝርዝር ውስጥ ይካተታሉ። ሂደቱን ካላለፉ መሰረዞን የሚገልጽ መልዕክት ይደርሶታል።

(የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈበት መታወቂያ እንዲሁም ፎቶ ሲያነሱት በሚታይ መልኩ እንዲሆን ይመከራል)

ኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ማኅበር ካቀረበው በላይ ግዢ ከተፈጸመ ምን ይደረጋል ?

መሸጥ ከሚታሰበው በታች ሼር ከተሸጠ ሼር ለመግዛት ያመለከቱ በሙሉ የጠየቁትን የሼር መጠን የሚያገኙ ይሆናል።

ሆኖም የሼር ግዢ ጥያቄው ከተቀመጠው በላይ ከሆነ በprospectus ዶክመንቱ መሰረት የአክሲዮን ድልድል (Allotment of Shares) ይካሄዳል።

ይህም ሼር መሸጥ ከሚያበቃበት ታኅሣሥ 25 ጀምሮ የሚደረግ ይሆናል።

ይህ ድልድል በተመጣጣኝ ድርሻ ስሌት (Pro-rata Algorithm) የሚካሄድ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ በዲጂታል የሚከናወን ነው። ይህም እያንዳንዱ አመልካች ተመጣጣኝ ድርሻ እንዲደርሰው የሚያስችል ነው።

ለምሳሌ ፦  አንድ ሰው 100 ሼር ግዢ ለመፈጸም ጥያቄ አቀረበ። የተመጣጣኝ ድርሻ ስሌቱ (Pro-rata Algorithm) ሁሉም 70% እንዲደርሳቸው ቢወስን 100 ሼር ለመግዛት ጥያቄ ያቀረበው ሰው የሚደርሰው 70 ሼር ይሆናል ማለት ነው።

በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ድልድሉ ጥር 23/2017 ዓ.ም በይፋ ለህዝብ በይፋ ይገለጻል።

ተመላሽ ክፍያ በተመለከተ ?

አመልካቾች ድልድል ከተደረገ በኋላ የደረሳቸው የሼር መጠን ያክል ክፍያ ተቆርጦለት ቀሪው ገንዘብ ከአገልግሎት ክፍያው ጋር ተደምሮ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል።

ገንዘቡ ድልድሉ ይፋ በሆነ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረጋል። ዜጎች ሼር ለመግዛት ካመለከቱ እና ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ ድልድሉን አለመቀበል አይችሉም።

የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ማኅበር 10% ድርሻ ለኢትዮጵያውያን ብቻ የቀረበ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሽያጭ የሚደረግበት ይሆናል። በተጨማሪም ዜጎች ለራሳቸው እና ህጋዊ ውክልና ላላቸው ዜጋ ግዢውን መፈጸም ይችላሉ።

ከዚህ የሼር ሽያጭ ኢትዮ ቴሌኮም 30 ቢሊዮን ብር ገቢ የሚያገኝ ሲሆን። ከአገልግሎት ክፍያ ደግሞ 450 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ ገቢ ያገኛል። መንግሥት ሙሉ ለሙሉ የቀረበው ሼር ተሸጦ ካለቀ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ብቻ 67.5 ሚሊዮን ብር ያገኛል።

አክሲዮን ማኅበሩ፥ በኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬት ገበያ ዝርዝር ውስጥ ለመካተት (Listing) የሚያስችለውን ዝግጅት የሼር ሽያጩ ካበቃ በ12 ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዱን በዶክመንቱ ተገልጿል።
@tikvahethiopia
የጥቅምት ወር ደመወዝ ክፍያ በአዲሱ የተሻሻለው ስኬል መሆን ይጀምራል...

ከመስከረም ወር ጀምሮ የመጨረሻ ውሳኔ ሲጠብቅ የነበረው የመንግስት ሰራተኞች አዲሱ ደሞዝ ከጥቅምት ወር እንደሚጀምር የገንዘብ ሚኒስቴር (አቶ አህመድ ሽዴ) አሳውቋል።

ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ደመወዝ በካቢኔ ተወስኗል። ባለፉት ሳምንታት በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ቅድመ ዝግጅቱ አልቋል፤ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንም በኩል ቅድመ ዝግጅት አልቋል፤ የአፈጻጸም መመሪያ ተዘጋጅቷል" ብለዋል። የጥቅምት ወር ደመወዝ ክፍያም በአዲሱ ስኬል ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል።

"ዝቅተኛ ተከፋይ ለሆነው የመንግሥት ሰራተኞች፣ ለጸጥታ ተቋም አባላት፤ በየደረጃው ባሉ የመንግሥት ተቋማት በክልልም በፌዴራልም ተግባራዊ ማድረግ ይጀምራል" ብለዋል።

"ይሄ በመላው ሀገሪቱ የሚፈጸም ነው። ክልሎችም ለሰራተኞቻቸው / የደመወዝ ተከፋዮቻቸው የሚመጣውን ደመወዝ ከጥቅምት ወር ጀምሮ የክልል ድርሻ በፌዴራል መንግሥት የሚሸፈን ሆኖ በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ለክልሎች ይላካል" ሲሉ ገልጸዋል።

አዲሱ የጭማሪ መጠን፤ ከሰራተኛው የሚቆረጥ የግብር መጠን እና የጡረታ መዋጮ ተቀንሶ በእጁ የሚቀበለው የተጣራ ደሞዝ መጠን ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡https://youtu.be/1LEjbMptwms

#ማሳሰቢያ፦ ደሞዙ ላይ የቤት ኪራይ ድጎማ፤ የወንበር፤ የስልክ፤ የተለያዩ የአበል ክፍያዎች ካላችሁ መደመር ትችላላችሁ!
#ለመረጃ

ጅቡቲ ላይ የተከማቹ የነዳጅ ተሸከርካሪዎች እንዲገቡ ተፈቀደ!


የገንዘብ ሚኒስቴር ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር፣ በጅቡቲና ድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ላይ ተከማችተው የሚገኙ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ መፈቀዱ ተሰምቷል፡፡


አዲሱ መመሪያ፤ ከዚህ ቀደም እንዳይገቡ ታግደው የቆዩ ተሸከርካሪዎችን ጉዳይ መፍትሄ ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል፡፡


መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ከተለያዩ ኤጀንሲዎችና ከጉምሩክ ኮሚሽን ተውጣጥቶ የተቋቋመ ኮሚቴ፣ ዝርዝር ግምገማ  ማድረጉን ተከትሎ፣ በጥያቄ ውስጥ የነበሩ ተሽከርካሪዎች በተገዙበት ቀንና የጉምሩክ ምዝገባ መሰረት እንዲመደቡ ተደርጓል፡፡


መንግሥት በተለይም ከየካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የተገዙና በጉምሩክ ተገቢው ምዝገባ የተደረገላቸው ተሽከርካሪዎች፣ ወደ ድሬዳዋ ተጓጉዘው መንግሥት ተጨማሪ ውሳኔ እስከሚሰጥ ይጠበቃል ተብሏል (@አዲስ አድማስ)፡፡
IMF ለኢትዮጵያ የተራዘመ ብድር ለመልቀቅ ሲያደርግ የቆየውን ግምገማ ማጠናቀቁንና አገሪቱ የክፍያ ሚዛን ጉድለቷን ማስተካከል እንድትችል ባፋጣኝ 340.7 ሚሊዮን ዶላር ብድር እንዲለቀቅላት ከፍተኛ የሥራ አስፈጻሚ ቦርዱ መወሰኑን ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።


IMF የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም አንቀሳቃሽ በመሆኑ የሚያወጣቸው መግለጫዎች በሀገር ውስጥ የሚተገበሩ በመሆናቸው በትኩረት መከታተል በጣም ጠቃሚ በመሆኑ..


በመሆኑም ከግምገማው በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጣይ መከናወን አለባቸው በሚል ያቀረባቸውን 5 Statements በዝርዝር እንመለከታለን....https://youtu.be/q6Lpd_OwJrg
#ደመወዝ : የደመወዝ ጭማሪ ተፈቅዶና በጀቱም ጸድቆ ክፍያው ከጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም.  ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ዛሬ አሳውቋል።

ከገንዘብ ሚኒስቴር የተፈቀደው በጀት፣ የአፈጻጸም መመሪያውንና የክፍያ ትዕዛዙን ለ12ቱ ክልሎች፣ ለሁለቱ የከተማ አስተዳደሮችና ለፌደራል ተቋማት ዛሬ መተላለፉም ተገልጿል።

(ከጥቅምት ወር 2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው ይፋዊ (Gross Salary) የደመወዝ ስኬል ከላይ ተያይዟል)!

የተጣራ ደሞዝ ለማወቅ
👇
https://youtu.be/1LEjbMptwms
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአገልግሎት ክፍያ ላይ ጭማሪ አድርጓል። (ልክ ሳየው ከገረመኝ የታሪፍ ጭማሪዎች መካከል ነው!)....

ጊዜያዊ ዕውቅና ክፍያ ከ100ብር ወደ 15,000 ብር፤

የሙሉ ዕውቅና ክፍያ ከ200ብር ወደ 30,000 ብር፤

የሰነድ ማሻሻያ ክፍያ ከ30ብር ወደ 5,000 ብር ገብቷል።
ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ....

ኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ መከተሌን እቀጥላለሁ ሲል ዛሬ ገልጿል..... IMF የገንዘብ ፖሊሲችሁ መጥበቅ አለበት ብሎ በቅርቡ መክሯል።

ለመሆኑ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ (Tight Monetary Policy) ምን ማለት ነው? የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እየተከተለ ያለው ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ መገለጫምች ምንድን ናቸው? የገንዘብ ፖሊሲው ጥብቅ የመሆኑ እድል እና ስጋት ምንድን ነው?

እነዚህን እና የመሳሰሉትን መሰረታዊ ነጥቦች ተከታተሉ...https://youtu.be/PaPaufDSgf0
የBRICS አባል በመሆን የኢኮኖሚ ወይስ የፖለቲካ ተጠቃሚነት የሚረጋገጠው?


በማደግ ላይ ያሉ የዓለም ሀገራት ጥምረቱን ለመቀላቀል ከፍተኛ እርብርብ እያደረጉ ነው! አሜሪካ እና አውሮፓን እየሸሹ ወደ ራሽያ እና ቻይና እየተጠጉ ነው? ወይስ ተጨማሪ አማራጭ እየፈጠሩ ነው?


አብዛኞቹ አባል ሀገራት የIMF እና የWorld Bank ባለእዳዎች ሆነው ወደ BRICS ጥምረት መቀላቀላቸው የሚያመጣው አሉታዊ ጎን ምን ሊሆን ይችላል?


እነዚህን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ የባለሙያዎች ትንተናዎች እና ጥናታዊ መረጃዎችን ጨምሮ እንመለከታለን! ተከታተሉት..... https://youtu.be/5Fd-581QfDY

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ የBRICS አባል በመሆኗ ሊያጋጥሟት የሚችሉ እድሎች እና ስጋቶች ዙሪያ የተሰራውን ትንተና ለመመልከት...https://youtu.be/k_gJB3G2vM8
IMF ዛሬ ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራትን የዘንድሮ የ2024 እና የ2025 የGDP እድገት ትንበያ አቅርቧል! ደቡብ ሱዳን ዘንድሮ ከዜሮ በታች በ -26.4% እንደምታድግ ከገመተ በኋላ በቀጣይ ዓመት በ27.2% ታድጋለች እያለ ነው!

ደቡብ ሱዳን ምን ሊፈጠር ነው?
text (1).pdf
2.6 MB
IMF: Regional Economic Outlook 2024 ሙሉ ሰነድ ማንበብ ለምትፈልጉ።
IMF የ2024 እና የ2025 የሰብሰሃራ አፍሪካ ቀጠና ሀገራት የኢኮኖሚ ደረጃ ሪፖርት (Regional Economic Outlook 2024) አውጥቷል!

የሰብሰሃራ አፍሪካ ሀገራትን በ6 ቡድን የከፈለ ሲሆን ነዳጅ ያላቸው፤ ከነዳጅ ወጪ ከፍተኛ ነዳጅ ያላቸው፤ ማዕድን የሌላቸው፤ መካከለኛ ገቢ ያላቸው፤ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው እና በግጭት የሚታመሱ ናቸው...

የትንበያ ሰነዱ ኢትዮጵያን ዝቅተኛ ገቢ፤ አነስተኛ ማዕድን፤ በግጭት የታመሰ በሚል ቢመድብም በቀጣይ ዓመት 6.5% የኢኮኖሚ እድገት ታስመዘግባለች ይላል.....

የሰነዱን መሰረታዊ ነጥቦች እና የሰጠውን ትንበያ ለመመልከት...https://youtu.be/viXWTsWHv94
የከተማ_መሬትን_በሊዝ_ስለመያዝ_የወጣ_አዋጅ.pdf
638.2 KB
#ለመረጃ

ዛሬ ፓርላማው ረቂቁ ቀርቦለት ወደ ቋሚ ኮሚቴ የመራው  "የከተማ መሬትን በሊዝ ለመያዝ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ" በተለይ አዲሱን ሃሳብ ማለትም "በድርድር በሊዝ የከተማ መሬት ስለማግኘት" ማንበብ ለምትፈልጉ! https://t.me/WaseAlpha ላይ አስቀምጫለሁ።