The Ethiopian Economist View
29.2K subscribers
725 photos
4 videos
197 files
1.34K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
መቆጠብ ወይስ ኢንቨስት ማድረግ

በመቆጠብ እና ኢንቨስት በማድረግ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት! የገንዘብ ነጻነት እና የቀጣይ ህይወት መሰረት ላይ ወሳኝ ነው!

አንዳንዴ ተለዋዋጭ ተደርገው ይወሰዳሉ! ከተቆጠበ ኢንቨስት ይደረጋል! ኢንቨስት ተደርጎ ከተገኘው ይቆጠባል! (ፍጹም የተለያዩ መሆናቸው ማወቅ ግድ ነው!)

በግለሰብ ደረጃ ቁጠባ ምንድን ነው? ኢንቨስትመንት ምንድን ነው? የሁለቱም እድል እና ስጋት ምንድን ነው?

ቁጠባ ምንድን ነው?
ሰዎች ለ2 ምክንያት ገንዘብ ያስቀምጣሉ (የሆነ ነገር ለመግዛት ወይም ለማይታወቅ የአደጋ ጊዜ) ቁጠባ በቤት፤ በባንክ (በወለድ)፤
ቁጠባ ለአጭር ጊዜ ሸመታ ፍላጎት ጥሩ ነው (አልጋ ለመግዛት 4 መቆጠብ! እስከ 1 ዓመት)
ቁጠባ አደጋው ጠባብ! በቤት ከሆነ የወለድ ግኝት የለውም (የዋጋ ንረት ይንደዋል)

ለምሳሌ፡- የ10ሺ ብር አልጋ ለመግዛት ለ10 ወር በየወሩ 1ሺ ብር መቆጠብ! ወይም 10ሺ ብር ተበድሮ በየወሩ ለአበዳሪ 1ሺ ብር መክፈል (ከዘመድ፤ ከጓደኛ፤ ከቤተሰብ….ብድር)

የቁጠባ ጥቅም
በገቢ በአንዴ ለማይገዛ መግዣ ይሆናል
ድንገት ለሚስፈልግ ወጪ መሸፈኛ ይሆናል (ድንገት ሰው ቢታመም፤ ሞባይል ቢጠፋ….)
ከኪሳራ ለመዳን (ቁጠባው በባንክ ከሆነ ወለድ ካለው! ከኢንቨስትመንት አንጻር)

የቁጠባ አደጋ

አነስተኛ ትርፍ ያስገኛል (በባንክ ከሆነ ወለድ! መባዛት አይችልም!
በዋጋ ንረት ይበላል (በቤት ከተቆጠበ፤ በአነስተኛ ወለድ ከተቆጠበ!
ገንዘቡን ኢንቨስት ባለማድረጋችን የምናጣው ነገር (Opportunity costs)

ኢንቨስትመንት ምንድን ነው?
ያለንን ገንዘብ ወደ ሌላ ብር ወደሚመጣ ነገር የመለወጥ ሂደት (መነገድ፤ አክሲዮን፤ ገዝቶ መሸጥ (ወርቅ)፤ ትምህርት መማሪያ፤ የኪራይ ቅድመ ክፍያ መፈጸም፤ ….

ኢንቨስትመንት አደጋ ያለው ቢሆን የረጅም ጊዜ ትርፍ አለው (ለምሳሌ አክሲዮን የገዛ ሰው ድርጅቱ ሲከስር ይቀንሳል (መሸጥ) ሲጨምር ይጨምራል…..(ያልተጠና ቦታ እና አንድ/ ተመሳሳይ ቦታ ኢንቨስት ማድረግ ዋጋ ቢስ ነው!)

የኢንቨስትመንት እድል?
ከቁጠባ በላይ አትራፊ ነው!
የረጅም ጊዜ የፋይናንስ ምንጭ/መተማመኛ ይፈጥራል!
አሰባጥሮ እንቨስት ማድርግ አደጋን ይቀንሳል!

የኢንቨስትመንት አደጋ?

በተለይ ለአጭር ጊዜ የኪሳራ አደጋ (ስራ እስኪጀመር! ቁጠባ ቢሆን ወለድ)
ከፍተኛ ትጋት የሚፈልግ ተግባር መሆኑ (ጸጉር ቤት የከፈተ ተግቶ መስራት አለበት!)
ረጅም ጊዜ ሊያስጠብቅ ይችላል (አክሲዮን ቢሆን ዓመት ሙሉ ተጠብቆ ትርፍ)

መቼ መቆጠብ መቼ ኢንቨስት ማድረግ?
የዚህ ጥያቄ መልስ ከሰውየው የገንዘብ አቅም፤ ካስቀመጠው ዓላማ እና አደጋ ለመጋፈጥ ያለው አቅም ላይ ይመሰረታል!

ምን አልባት መጣት የሆነ ሰው፡ ትንሽ ገቢ እና ትንሽ ወጪ ስለሚኖረው ቁጠባ ላያሳስበው ይችላል (ወጣት አደጋ የመጋፈጥ እድል እና ጊዜ ስላለው ኢንቨስትመንት (መማር፤ መሰልጠን፤ መሞከር፤…

ምን አልባት ትልቅ የሆነ ሰው፡ አጭር ቀሪ ጊዜ ያለው (አደጋ ካለው ኢንቨስትመንት መካከል አክሲዮን ሊመከር ይችላል! ገንዘቡን በካሽ መያዝ ሊሆን ይችላል)፤

ኢንቨስት ከማድረግ በፊት በቂ መጠባበቂያ ቁጠባ (ቢያንስ ከ3-6 ወር ፍጆታ የሚበቃ) መኖሩን ማረጋገጥ ግድ ነው (ለቤት ኪራይ፤ ለወራዊ አስቤዛ፤ !

ለምን ብዙ ሰዎች ኢንቨስት ከማድረግ በላይ ቁጠባ ይመርጣሉ!

አደጋ ይኖራል የሚል ስጋት መኖር (በመጠባበቂያ መተማመን)
ብዙ የወጪ ምክንያቶች መኖር!
ቁጠባ ትጋት ስለማይጠይቅ!
ኢንቨስት በማድግ አስፈላጊነት በቂ ግንዛቤ አለመኖር (ምን ልስራ!)! በምን ያህል!
ኢንቨስት በማድረግ ወስጥ የሚኖርን አደጋ የመቋቋም አቅም አለመኖር (መፍራት!)
ቁጠባው ለየትኛውም ኢንቨስትመንት የማይበቃ ሲሆን (የቀጣይ ገቢ አነስተኛ መሆን!

ከቪዲዮው ላይ የተጻፈ (@MesBe)
ቆጥቦ በመግዛት እና ተበድሮ በመግዛት መካከል ያለ ልዩነት! ከማን መበደር ያዋጣል?

ማንኛውም ሰው መግዛት የሚፈልገውን ከቁጠባው አልያም ተበድሮ ሊገዛው ይችላል...

ከተለያየ ምንጭ ተበድሮ መግዛት በጣም የሚያዋጣበት ጊዜ እና ቆጥቦ መግዛት የሚያዋጣበት የሸመታ እና የቢዝነስ ውሳኔዎች....

ሰዎች የመበደር እድሉ ካላቸው መበደር የሚኖርባቸው ምንጮች ከዜሮ ወለድ እስከ ዋጋ ንረት ጣሪያ ድረስ በምሳሌ እንመልከት....https://youtu.be/1A7AGcuKyYk
IMF ለኢትዮጵያ 251 ሚሊየን ዶላር ሊለቅ ነው!

IMF ለኢትዮጵያ በ4 ዓመታት ውስጥ ሊሰጥ ካሰበው ብድር ውስጥ በ1ኛ ዙር ከለቀቀው 345 ሚሊየን ዶላር በኋላ የ2ኛ ዙር ግምገማ (በ3 ወር ውስጥ) በማድረግ 251 ሚሊየን ዶላር ሊለቅ መሆኑን ገልጿል።

እንደ IMF ግምገማ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም አፈፃፀም ጥሩ መሆኑን ገልጿል!

IMF ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ የተመለከተው ጥሩ ጎኖች ምንድን ናቸው?

የ3ኛ ዙር የIMF ግምገማ ከ6 ወር በኋላ ይደረጋል የተባለው ለምንድን ነው?

የሚከተለውን መረጃ ተመልከቱ...https://youtu.be/ZsahDfvh1aI
የIMF_የ2ኛ_ዙር_የባለሙያ_ግምገማ_ሪፖርት.pdf
144.5 KB
IMF በ2ኛ ዙር በኢትዮጲያ ያደረገው የባለሙያ ግምገማ ውጤት መግለጫ!
በ100% ዋጋ ጭማሪ Survive ያደርጋል?

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ ላይ 100% ጭማሪ አደረገ። አሁን አገልግሎት እየተሰጠበት ያለው 10 ብር ሲሆን ወደ 20 ብር ጭማሪ ተደርጓል።
እንደ ኢኮኖሚስት አስቡ (Think Like an Economist)!

እመኑኝ እንደ ኢኮኖሚስት ማሰብ ስትጀምሩ በስራ ቦታዎ፣ በቤትዎ እና በማህበረሰብ ውስጥ የተሻሉ ውሳኔዎችን እንዲወስኑ የሚያስችልዎትን አቅም በማግኘት የተለየ ዓለምን በግልፅ ያያሉ!

እንደ ኢኮኖሚስት የማሰብን መሰረታዊ ነጥቦች ላጋራችሁ! እይታዎ ላይ ለውጥ ያመጣሉ!

ለእይታው...https://youtu.be/HKkEZcw0gjU
ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል (Minimum Wage)! በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል! ለኑሮ በቂ የሆነ ዝቅተኛ ክፍያ በሰዓት ስንት ነው?

ለሰራተኞች ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ይቀመጣል! (Minimum Wage)....

በዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ላይ ከፍተኛ ክርክር አለ! ዝቅተኛ የክፍያ ወለል በመንግስት እና በግል ሰራተኞች ላይ ከፍ እንዲል መደረጉ የዋጋ ንረት እና ስራ አጥነትን ሊያባብስ ወይም የደሞዝተኞች ገቢ ማደጉ ኢኮኖሚን ሊያነቃቃ ይችላል...

በኢትዮጵያ አሳማኝ ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ለመወሰን ተፅዕኖ ያላቸው ጉዳዮች....

እነዚህ ወሳኝ ነጥቦች በምሳሌ ተመልከቱ....https://youtu.be/Sglp7fXTBmk
ትራምፕ ለብሪክስ አባል ሀገራት #ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ሰጡ!

የብሪክስ አባል ሀገራት ከአሜሪካ ዶላር ውጪ ለመገበያየት የራሳቸውን ገንዘብ ለመፍጠር እየሞከሩ ነው!

የብሪክስ አባል ሀገራት አዲስ መገበያያው ገንዘብ (ከዶላር ውጪ) መጠቀም የሚጀምሩ ከሆነ በአሜሪካ ገበያ ካለመግባት እስከ 100% ታሪፍ እንዲጣልባቸው ይደረጋል (ዶናልድ ትራምፕ)!

የብሪክስ አባል ሀገራት ማስተካካያ የማያደርጉ ከሆነ እና የትራምፕ ውሳኔ የሚተገበር ከሆነ ኢትዮጵያ የሚደርስ ተፅኖ አለው!

ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ትንታኔ ተመልከቱ...https://youtu.be/ZYcn7D644ZQ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ #የፋይናንስ_መረጋጋት ሪፖርት ይፋ አደረገ!

ሪፖርቱ የኢኮኖሚ እድገት ማሳያዎችን፤ የዋጋ ንረት ሁኔታን፤ የባንክ ዘርፉ ያለበትን ሁኔታ፤ በዋናነት የተተገበሩ የፖለሲ አማራጮችን፤…. የ5 ዓመት በንጽጽር አቅርቧል (ከሃምሌ 2016 እስከ ህዳር 2017 እንዲሁም የቀጣይ ዓመት ትንበያን ጨምሮ በትኩረት አቅርቧል)....

የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ የገጠሙትን 3 ዋና ዋና  አደጋዎች እና ስጋቶች (Risks) አምኖ አቅርቧል!

ይህንን የሪፖርት ትንተና ይመልከቱ...https://youtu.be/Z2lQT6tUmZc
#ለመረጃ: የሲሚንቶ ዋጋ በሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎች እንዲወሰን ተደረገ!

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለሲሚንቶ ፋብሪካ ድርጅቶች በጻፈው ደብዳቤ ከጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ  ምርታቸውን በፍትሃዊ ዋጋ እንዲያቀርቡ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም የሲሚንቶ ምርት የፋብሪካ መሸጫ ዋጋ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተወሰነ ለገበያ ሲሰራጭ የቆየ ቢሆንም በአዲሱ የአሰራር ሂደት ግን አምራች ፋብሪካዎች ሙሉ ሀላፊነቱን በመውሰድ በነጻነት ምርታቸውን ለገበያ እንዲያቀርቡ እና ገበያውን እንዲያረጋጉ ሃላፊነት መስጠቱን ሚኒስቴሩ እውቁልኝ ብሏል፡፡

የሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ የተሰጣቸውን ሀላፊነት በተጠያቂነት ስሜት እና በፍትሃዊ የዋጋ ተመን ማህበረሰቡን እንዲያገለግሉም መወሰኑን ገልጾ ከዚህ ቀደም አገልግሎት ላይ ይውል የነበረውን መመሪያ 940/2015 ማንሳቱን ይፋ አድርጓል (አዲስ ማለዳ)።
ገቢ እና ወጪን እንዴት እናስተዳድር? (የምኖረውን ልምዴን ልንገራችሁ)!

በህይወት እስካለን ድረስ ስለ ገቢያችንም ሆነ ስለወጪያችን ሁኔታ መስተካከልም ሆነ መበላሸት ዋናው ተጠያቂዎች እኛው ነን!

ገቢያችንን እና ወጪያችንን በምክንያታዊነት እንዴት መምራት እንደምንችል እና የፋይናንስ ነፃነትን ማረጋገጥ የሚቻልበትን ዘዴ ከተጠቀምኩበት ልምድ በመነሳት ላጋራችሁ!

የፋይናንስ ነፃነት ላይ መድረስ የምትፈልጉ እና የኑሮ ጫናን ለመቋቋም ለምትፈልጉ የሚከተለው ሃሳብ በትክክል ያግዛችኋል! ልታመሰግኑኝ ትችላላችሁ!https://youtu.be/ubMsX455BQA
የሪል_ስቴት_ልማት_እና_የማይንቀሳቀስ_ንብረት_ግብይትና_ግመታ_አዋጅ_1.pdf
1.7 MB
የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ።
ማንበብ ለምትፈልጉ!
ዘንድሮ የባንኮች የትርፍ ክፍያ ለምን ቀነሰ?

ባንኮች የ2016 ጠቅላላ ጉባኤ እያካሄዱ ነው። የብዙ ባንኮች የሂሳብ ሪፖርት የሚያሳየው የአክሲዮን የትርፍ ክፍፍል መጠን መቀነስ እና ጭራሽ አለመክፈል እየተገለፀ ነው።

ብዙ ባንኮች የሚጋሩት የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ እንዲሁም የአስተዳደር ችግሮች መኖራቸው ከሚወጡ ሪፖርቶች አሉ!

ንብ ባንክ በዚህ ዓመት የሚከፋፈል የትርፍ ድርሻ እንደሌለው አሳውቋል! ከተመሰረተ የቆየ ባንክ በ2015 የትርፍ ክፍፍል መስጠት ባለመቻሉ ይቅርታ ሲጠይቅ ነበር!

የንግድ ባንኮች የትርፍ መጠናቸው ከፍ ማለቱን እየገለፁ የትርፍ ክፍፍል ለባለአክሲዮኖች መክፈል ያልቻሉት ወይም ይከፍሉ ከነበረው የቀነሰ የትርፍ ድርሻ እየደለደሉ ያሉት ለምንድን ነው?

የባንኮች የትርፍ ክፍፍል ሁኔታ ለባለአክሲዮኖች ያለው ተፅዕኖ ምን ሊሆን ይችላል?

ከላይ የተዘረዘሩትን ጉዳዮች በመረጃ እንመልከት https://youtu.be/oP9JjPlJSTc
በትዳር ውስጥ የሚተገበሩ Economic Theories! ኢኮኖሚ የትዳር አለመመስረት፤ የትዳር መመስረት እና የትዳር መፍረስ አመክንዮዎች.....

ማንኛውም ባለትዳሮች ህይወት ውስጥ በየዕለቱ የሚተገበሩ የኢኮኖሚ አመክንዮዎች (Economic Theories) አሉ....

ትዳር በኢኮኖሚ አመክንዮ ውስጥ አዎንታዊ እና አሉታዊ ትርጓሜ የተሰጠው ለምንድን ነው?

የሚከተለውን ድንቅ የማህበራዊ ኢኮኖሚ ትንታኔ ተመልከቱ....https://youtu.be/wpC8G2gba0M
በትዳር ውስጥ የሚተገበሩ Economic Theories! ኢኮኖሚ የትዳር አለመመስረት፤ የትዳር መመስረት እና የትዳር መፍረስ አመክንዮዎች.....

ማንኛውም ባለትዳሮች ህይወት ውስጥ በየዕለቱ የሚተገበሩ የኢኮኖሚ አመክንዮዎች (Economic Theories) አሉ....

ትዳር በኢኮኖሚ አመክንዮ ውስጥ አዎንታዊ እና አሉታዊ ትርጓሜ የተሰጠው ለምንድን ነው?

የሚከተለውን ድንቅ የማህበራዊ ኢኮኖሚ ትንታኔ ተመልከቱ....https://youtu.be/wpC8G2gba0M
#Significant

በዩኒቨርስቲ የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ላይ ማሻሻያ ተደርጓል። በነፍስ ወከፍ ለአንድ ተማሪ በቀን ከነበረው 22 ብር ወደ 100 ብር አድጓል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ካሽ ቀንሷል! የኢኮኖሚ ቀውስ ወይስ የፖሊሲ ውጤት?

ብዙዎቻችሁ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ባላችሁ ተሳትፎ የካሽ (ጥሬ ብር) የመቀነስ ሁኔታን መመልከታችሁ አይቀርም!

የካሽ እጥረት (Liquidity Criss) ስለመፈጠሩ የሚያሳዩ ምልክቶች....

የካሽ እጥረት እንዲፈጠር የሆነባቸው ምክንያቶች....

የካሽ እጥረት መኖር ኢኮኖሚው ላይ እየፈጠረ ያለው ስጋት....

የካሽ እጥረቱ በቀጣይ ሊቀረፍ የሚችልበት ሁኔታ....

ከላይ ለተዘረዘሩ ኢኮኖሚያዊ ነጥቦች ምላሽ እንስጥ!https://youtu.be/Q-D0RLb9jDU
Channel photo updated
#ለመረጃ!

ግብር ከፋዮች በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት #ብቻ የታተመ የእጅ በእጅ (ማኑዋል) ደረሰኝ መጠቀም እንዳለባቸው ተወሰነ!

ግብር ከፋዮች ከየካቲት 1 ጀምሮ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ብቻ የታተመ የማንዋል ደረሰኝ መጠቀም እንዳለባቸው ተወሰነ።

የገቢዎች ሚኒስቴር ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ጋር ሃሰተኛ ደረሰኞችን ለመከላከል በደረሰኞች ላይ ልዩ መለያ ኮድ (QR-Code) አካቶ ማተም በሚያስችል አሰራር ዙሪያ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

ስምምነቱ የህትመት ጥያቄ መቀበል እንዲሁም ከታተመ በኋላ የስርጭት እና የቁጥጥር ሥርዓትን ማስፈን በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ መስራት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ደረሰኝ እንዲታተም ፍቃድ ከመስጠት ጀምሮ ያሉ አገልግሎቶችን ማስተናገድ እንዲቻል የራሱ የሆነ ዲጂታል ፕላትፎርም የተዘጋጀ በመሆኑን፤ ደረሰኝ የሚያሳትም ማንኛውም ግብር ከፋይ በዚሁ መንገድ መስተናገድ የሚችል መሆኑን መስሪያ ቤቱ አስታውቋል ።

ከታህሳስ 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ ማንዋል ደረሰኝ የማሳተም ጥያቄ ማቅረብ የሚቻል ሲሆን ከየካቲት 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ብቻ የታተመ የማንዋል ደረሰኝ መጠቀም እንደሚገባ ሚንስትር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።