The Ethiopian Economist View
29.3K subscribers
724 photos
4 videos
197 files
1.34K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
በትዳር ውስጥ የሚተገበሩ Economic Theories! ኢኮኖሚ የትዳር አለመመስረት፤ የትዳር መመስረት እና የትዳር መፍረስ አመክንዮዎች.....

ማንኛውም ባለትዳሮች ህይወት ውስጥ በየዕለቱ የሚተገበሩ የኢኮኖሚ አመክንዮዎች (Economic Theories) አሉ....

ትዳር በኢኮኖሚ አመክንዮ ውስጥ አዎንታዊ እና አሉታዊ ትርጓሜ የተሰጠው ለምንድን ነው?

የሚከተለውን ድንቅ የማህበራዊ ኢኮኖሚ ትንታኔ ተመልከቱ....https://youtu.be/wpC8G2gba0M
#Significant

በዩኒቨርስቲ የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ላይ ማሻሻያ ተደርጓል። በነፍስ ወከፍ ለአንድ ተማሪ በቀን ከነበረው 22 ብር ወደ 100 ብር አድጓል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ካሽ ቀንሷል! የኢኮኖሚ ቀውስ ወይስ የፖሊሲ ውጤት?

ብዙዎቻችሁ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ባላችሁ ተሳትፎ የካሽ (ጥሬ ብር) የመቀነስ ሁኔታን መመልከታችሁ አይቀርም!

የካሽ እጥረት (Liquidity Criss) ስለመፈጠሩ የሚያሳዩ ምልክቶች....

የካሽ እጥረት እንዲፈጠር የሆነባቸው ምክንያቶች....

የካሽ እጥረት መኖር ኢኮኖሚው ላይ እየፈጠረ ያለው ስጋት....

የካሽ እጥረቱ በቀጣይ ሊቀረፍ የሚችልበት ሁኔታ....

ከላይ ለተዘረዘሩ ኢኮኖሚያዊ ነጥቦች ምላሽ እንስጥ!https://youtu.be/Q-D0RLb9jDU
Channel photo updated
#ለመረጃ!

ግብር ከፋዮች በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት #ብቻ የታተመ የእጅ በእጅ (ማኑዋል) ደረሰኝ መጠቀም እንዳለባቸው ተወሰነ!

ግብር ከፋዮች ከየካቲት 1 ጀምሮ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ብቻ የታተመ የማንዋል ደረሰኝ መጠቀም እንዳለባቸው ተወሰነ።

የገቢዎች ሚኒስቴር ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ጋር ሃሰተኛ ደረሰኞችን ለመከላከል በደረሰኞች ላይ ልዩ መለያ ኮድ (QR-Code) አካቶ ማተም በሚያስችል አሰራር ዙሪያ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

ስምምነቱ የህትመት ጥያቄ መቀበል እንዲሁም ከታተመ በኋላ የስርጭት እና የቁጥጥር ሥርዓትን ማስፈን በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ መስራት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ደረሰኝ እንዲታተም ፍቃድ ከመስጠት ጀምሮ ያሉ አገልግሎቶችን ማስተናገድ እንዲቻል የራሱ የሆነ ዲጂታል ፕላትፎርም የተዘጋጀ በመሆኑን፤ ደረሰኝ የሚያሳትም ማንኛውም ግብር ከፋይ በዚሁ መንገድ መስተናገድ የሚችል መሆኑን መስሪያ ቤቱ አስታውቋል ።

ከታህሳስ 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ ማንዋል ደረሰኝ የማሳተም ጥያቄ ማቅረብ የሚቻል ሲሆን ከየካቲት 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ብቻ የታተመ የማንዋል ደረሰኝ መጠቀም እንደሚገባ ሚንስትር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ከመደበኛ ገበያ ወደ ጥቁር ገበያ የገቡ ምርቶች!

ኢትዮጵያ ውስጥ በመደበኛ ገበያ በነፃነት መገኘት የነበረባቸው ምርቶች በኢኮኖሚ መዳከም፤ በተሳሳተ ፖሊሲ እና ጤነኛ ባልሆነ የቁጥጥር ስርዓት ወደ ጥቁር ገበያ እና ወደ ግራጫ የገበያ ስርዓት የወረዱ ምርቶች ብዙ ናቸው......

ኢትዮጵያ ውስጥ በስህተት መሰረታዊ የገበያ ባህሪያቸውን የለወጡ ምርቶች፤ ምክንያት እና መወሰድ የነበረባቸው የመፍትሔ ሃሳቦች እንመልከት....https://youtu.be/w8nRSPgUozs
#ለመረጃ (ፌስታል ያስቀጣል!)

በኢትዮጵያ የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም፣ ማምረት እና ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት በገንዘብ እና በእስራት የሚያስቀጣ ድንጋጌ የተካተተበት ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።

በረቂቅ አዋጁ መሠረት የፕላስቲክ ከረጢት የተጠቀመ ወይም ለመጠቀም ይዞ የተገኘ ማንኛውም ሰው ከ5 እስከ 10 ሺህ ብር ገንዘብ ይቀጣል።

በተመሳሳይ የፕላስቲክ ከረጢት ማምረት፣ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት፣ ለገበያ ማቅረብ፣ መሸጥ ወይም ለንግድ ዓላማ ማከማች *ከሃምሳ እስከ መቶ ሺህ ብር ያስቀጣል።* ከዚህ በተጨማሪም ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ ረቂቁ ላይ ሰፍሯል።

አነዚህን "የወንጀል ድርጊቶች" የፈጸመው ሕጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት በሚሆንበት ጊዜ ቅጣቱ ሦስት እጥፍ እንደሚሆን ረቂቁ ያትታል።
#ለመረጃ፡ የኢትዮጵያ የቀረጥና ታክስ ሕጎች በቀላሉ የሚገኙበት የኦንላይን ድረ ገጽ ይፋ ሆኗል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ድረ ገጽ፡ ከ300 በላይ የታክስ ሕጎች በአማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተቀመጡበት ነው።

ድህረገጹን ለምትፈልጉ https://ethiopia.mylexisnexis.co.za/#/navigation-view;listCode=LNSA

ድረገፁ የገንዘብ ሚኒስቴር “ከሌክሲስ ኔክሲስ ሩል ኦፍ ሎው ፋዌንዴሽን” ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው።
የዓለማችን 10 ሃብታሞች! The 10 Richest People in the World (Forbes 2024)!

ፎርብስ በ2024 የቢሊየነሮች ቁጥር 2,781 መድረሱን አሳውቋል፡፡ የባለሃብቶቹ ድርጅቶች 1% ድርሻ የብዙ ሀገራትን ጠቅላላ የምርት መጠን (GDP) በብዙ እጥፍ ይበልጣል.....

ለምሳሌ….

1. የኢለን መስክ ሃብት የኢትዮጲያ GDP እጥፍ ነው!

2. የAmazon ካምፓኒ 10% ድርሻ ከኢትዮጲያ ጠቅላላ (GDP) ይበልጣል!

ሃብታሞች የዓለምን የኢኮኖሚ፤ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ድጋፍ አቅጣጫ የመወሰን አቅም አላቸው፡፡

የሃብት መጠናቸውን እና የቢዝነስ ዘርፍ እና ስልት በዝርዝር እንመልከት! https://youtu.be/4_1T1A1xcDU
ገቢዎች ቢሮ ድርጅቶች ሊኖራቸው የሚገባውን የሰራተኞችን ቁጥር እና ሊከፈል የሚገባውን ዝቅተኛ ደመወዝ ወለል ወሰነ!

በዚህ ውሳኔ በሆቴሎች እና ሌሎች የንግድ ዘርፎች ላይ አሰሪዎች ለሰራተኞቻቸው የደሞዝ ጭማሪ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ተመን ይሆናል።

ከአስተናጋጅ፣ ጥበቃና የፅዳት ሙያ ውጭ ላሉ ሰራተኞች ትንሹ የሚከፍሉት ደመወዝ 5,000 ብር ሆኖ ተተምኗል።

በዚህም የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በግብር  ሂደት  ውስጥ የሚፈጠሩ ማጭበርበሮችን ለመቀነስ ዓላማው ያደረገ ለሆቴሎች፣ ለስጋ ቤቶች፣ ለመጠጥ ቤቶች እና ለተለያዩ የተመረጡ የንግድ ዘርፎች ለሰራተኞቻቸው አነስተኛ የደመወዝ ወለል እና የሰራተኞችን ብዛት የሚተምን ተመን ይፋ አድርጓል።

በዚህ ውሳኔ ዝቅተኛ የደሞዝ መጠን እና ዝቅተኛ የሰራተኛ ብዛት የተቀመጠውን እና የውሳኔውን ተፅኖ እና ደካማ ምክንያታዊነት እንመልከት....https://youtu.be/6kxo14riypA
ገቢዎች ቢሮ ድርጅቶች ሊኖራቸው የሚገባውን የሰራተኞችን ቁጥር እና ሊከፈል የሚገባውን ዝቅተኛ ደመወዝ ወለል ወሰነ!

በዚህ ውሳኔ በሆቴሎች እና ሌሎች የንግድ ዘርፎች ላይ አሰሪዎች ለሰራተኞቻቸው የደሞዝ ጭማሪ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ ተመን ይሆናል።

ከአስተናጋጅ፣ ጥበቃና የፅዳት ሙያ ውጭ ላሉ ሰራተኞች ትንሹ የሚከፍሉት ደመወዝ 5,000 ብር ሆኖ ተተምኗል።

በዚህም የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በግብር  ሂደት  ውስጥ የሚፈጠሩ ማጭበርበሮችን ለመቀነስ ዓላማው ያደረገ ለሆቴሎች፣ ለስጋ ቤቶች፣ ለመጠጥ ቤቶች እና ለተለያዩ የተመረጡ የንግድ ዘርፎች ለሰራተኞቻቸው አነስተኛ የደመወዝ ወለል እና የሰራተኞችን ብዛት የሚተምን ተመን ይፋ አድርጓል።

በዚህ ውሳኔ ዝቅተኛ የደሞዝ መጠን እና ዝቅተኛ የሰራተኛ ብዛት የተቀመጠውን እና የውሳኔውን ተፅኖ እና ደካማ ምክንያታዊነት እንመልከት....https://youtu.be/6kxo14riypA
በዋና መንገዶች ላይ የንግድ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3:30 አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ባካሄደበት ቀን "በሁሉም የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ያሉ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ" የሚል ውሳኔ አስተላልፏል!

ውሳኔው ሰው ሰራሽ የአካባቢ ዋጋ ሊፈጥር ይችላል!

የዚህ ውሳኔ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ምክንያታዊነት የተመጣጠነ ስለመሆኑ እንመልከት!https://youtu.be/AV5QYFpjj1w
#ለመረጃ (የሚገርም!) ለህዝብ ተወካዮች የቀረበው አጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅ

አንድ የግል ትምህርት ቤት በገበያው ለመቆየት "የትምህርት ቤቱን መምህራንና ሌሎች ሰራተኞች የ6 ወር ደመወዝ ክፍያ ለመሸፈን የሚችል በዝግ የባንክ ሂሳብ የተቀመጠ እና በባንኩ የተረጋገጠ ሂሳብ" ያስፈልጋል ይላል።

ለተቃራኒ ውጤት የተጋለጠ ረቂቅ!
የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ .pdf
498.2 KB
አጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ገቢ ለማመንጨት ሲል እየተጨነቀ ነው!

የኢትዮጵያ መንግስት በ2017 የ1.5 ትሪሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል! ይህንን የገቢ እቅድ ለማሳካት ሲባል በፌደራል እና በክልል ደረጃ የሚወሰዱ እርምጃዎች ኢኮኖሚውን እያስጨነቁት ነው።

የሚወሰዱ እርምጃዎች እየፈጠሩ ያሉት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር "The Cobra Effect" እንዳያመጣ ያሰጋል!

በዝርዝር እንመልከተው https://youtu.be/UiaO3c58NtQ
#በጣም_ጥሩ_መረጃ፡ የኢትዮጲያ ሰነደመዋለንዋይ ገበያ #ዲጂታል_አካዳሚ መጀመሩን በይፋ አብስሯል።

የኢትዮጲያ ሰነደመዋለንዋይ ገበያ "ESX Academy" የተሰኘውን የመማሪያ ፕላትፎርም ያስተዋወቀ ሲሆን ይህም ከFSD Ethiopia ጋር በመተባበር የተሰራ ፕሮጀክት ነው።

ፕላትፎርሙ የተለያዩ ኮርሶችን አንድ ላይ የያዘ ሲሆን ከነዚህም፡
1. ካፒታል ገበያ እንዴት ነው የሚሰራው?
2. ኢንቨስትመንት ስትራቴጂ
3. ሻሪያን ስላገናዘቡ ምርቶች
4. የኢትዮጲያ ሰነደመዋለንዋይ ገበያ በኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ላይ ስላለው ሚናና ያካትታል።

ኮርሶቹን esxacademy.com ላይ ገብተው መውሰድ ይችላሉ።
ኮርሱን ያጠናቀቁ ሰዎች በስራ አስፈጻሚው የተፈረመ ሰርተፊኬት በኢሜላቸው ይደርሳቸዋል!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲሱ አዋጅ 5 ዋና ዋና ለውጦች! የውጪ ባንኮች የሚገቡባቸው 4 ዘዴዎች! ለዲያስፖራው የተመለሰው የኢንቨስትመንት እድል....

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዲስ አዋጅ ፀድቆለታል! በዚህ አዋጅ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚን መወሰን የሚችሉ ዋና ዋና ማሻሻያዎች ተካተውበታል!

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩትን የአዋጁን 5 ዋና ዋና ድንጋጌዎች በዝርዝር እንመልከት...https://youtu.be/vjOrIxpyLPY