The Ethiopian Economist View
29.3K subscribers
724 photos
4 videos
197 files
1.34K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
በኢትዮጵያ #ተደራራቢ የግብር ጫና እየተፈጠረ ነው። መንግስት ከግብር ገቢ ውጪ የገቢ እቅዱን ማሳካት የሚችልበት አማራጭ የለውም?

የሚከተለውን ትንታኔ እንመልከት.....https://youtu.be/Cyyc2ZYb3iA
"ከገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያው በፊት የምርትና ምርታማነት እጥረት እንዲሁም የዋጋ ንረት ሀገሪቱን ሲፈትናት ነበር፤ ከማሻሻያው በኋላ ግን የዋጋ ንረቱ ከነበረበት 30% አሁን ላይ ወደ 16% ዝቅ ብሏል" የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ።

ይህ ቁጥር በነዋሪው #መደበኛ ገበያ እንዴት ይገለፃል?https://youtu.be/X7mv7D41TFU
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች በሚሰጡት የብድር ጣሪያ ላይ አስቀምጦት የነበረው የ14% ገደብ ወደ 18% እንዲያድግ ወስኗል!

ንግድ ባንኮች ከብሔራዊ ባንክ የሚበደሩበት የፖሊሲ የብድር ጣሪያ በነበረበት 15% ይቀጥላል ተብሏል!

ይህ ውሳኔ በብዙ መለኪያ ተፅዕኖ ያለው ስለመሆኑ የሚከተለውን መረጃ ተመልከቱ....https://youtu.be/VMnfTXXZ8UE
#ለመረጃ፦ "በ2017 በጀት ዓመት አምስት ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን" የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
የብድር ወለድ ሊጨምር ነው!

በኢትዮጵያ የሚገኙ ባንኮች ከቀናት በኋላ #በነባሩም (ከዚህ በፊት ተበድረው እዳ እየከፈሉ ያሉ) ሆነ #አዳዲስ (አዲስ ተበዳሪዎች) የብድር ወለድን ከ3 እስከ 5 በመቶ ከፍ ሊያደርጉ በዝግጅት ላይ ናቸው!

የባንኮች ምክንያታዊነት፤ በገበያው የሚፈጥረው አደጋ፤ ብሄራዊ ባንክ በቀጣይ ሊያደርግ ስለሚችለው እርምጃ የሚከተለውን ትንታኔ እንመልከት....https://youtu.be/S04hJoL7PRA
#ለመረጃ፦ ብሄራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሬ ግብይት መሠማራት ለሚፈልጉ የግል የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች ለጊዜው ፍቃድ መስጠት አቁሟል።

ባንኩ ለግል የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች ፍቃድ መስጠት ያቆመው፣ ካሁን ቀደም ፍቃድ የወሰዱ አምስት ቢሮዎችን የሥራ አፈጻጸም በቅድሚያ መገምገም ስለፈለገ መሆኑ ታውቋል።
ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ! እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና) አደረሳችሁ። መልካም በዓል ይሁንላችሁ!
#ለመረጃ፦ ከዛሬ ታህሳስ 29 ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ቤንዚን  በሊትር 101.47 ብር ሲገባ ናፍጣ በሊትር 98.98 ብር ሆኗል።
የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ጠቅላላ ኢኮኖሚው ላይ ታሪፍ መጨመር ነው!

መኪና እያለው ካሽ የሌለውን የፈጠረው ኢኮኖሚው ነው!

ነዳጅ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ያለውን ተፅዕኖ እንመልከት!https://youtu.be/w2uHmOPd8_k
#ለመረጃ፦ የኢትዮጵያ ሰነድ ሙዓለ ገበያ (Ethiopia Security Exchange -ESX ) ግብይት በይፋ ተጀመረ- ደወሉ ተደወለ!!

በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ 50 ያህል ኩባንያዎች በአዲሱ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ላይ የአክሲዮን ድርሻዎችን ለግብይት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።
የነፍስ ወከፍ ገቢ ንፅፅር #ፖለቲካ!

የሀገራችን የነፍስ ወከፍ ገቢ የህዝቡን ህይወት አይወክልም!

ነገር ግን...በመንግስት እና በኢኮኖሚስቶች እንዲሁም የሚዲያ ሰዎች መካከል ኢትዮጵያ የምትወስደው የማክሮ ፖሊሲ የዋጋ ጭማሪ መነፃፀር ያለበት በሀገራት መካከል ባለ የነፍስ ወከፍ ገቢ ነው የሚል ጠንካራ ክርክር አለ!

ይህንን ትክክለኛ የህዝቦችን ህይወት የማይለካ የዋጋ መጨመሪያ መከራከሪያ በተለየ መንገድ እንመልከተው!https://youtu.be/BRMmHlkP21o
693,000 ብር ብቻ በመክፈል መሃል ፒያሳ አፓርታማ ይኑሮት |  Apartment price in addis ababa | Apartment in Addis https://youtu.be/gcDmPJJCubU
እንኳን ለጥምቀት በአል አደረሳችሁ!
#መልካም_በዓል!
በኢትዮጵያ አዲሱ የ Property Tax አሰራር! የተወሰነባችሁን የንብረት ታክስ ትክክል መሆኑን እንዴት ታውቃላችሁ?

ኢትዮጵያ ውስጥ የንብረት (Property) ታክስ መከፈል እንዳለበት ተወስኗል።

የንብረታችሁ ወቅታዊ ዋጋ እንዴት ይሰላል? የንብረታችሁ ወቅታዊ ዋጋ በምን ምክንያት ሊለዋወጥ ይችላል?

የአካባቢ መሰረተ ልማት በተለወጠ ቁጥር የንብረት ታክስ መጠን ይለወጣል!

ባላችሁ ንብረት ማለትም #ቦታ እና #ቤት (ኮንደሚኒየምን ጨምሮ) በየዓመቱ መከፈል ያለበት የንብረት ታክስ ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ስንት እንደሆነ በቀላሉ በምሳሌ ተመልከቱ!https://youtu.be/tONUIGIdp0s
የኢትዮጵያ GDP በወራት ውስጥ ከ207 ቢሊየን ዶላር ወደ 100 ቢሊየን ዶላር ወርዷል!

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከሃምሌ 2016 ወዲህ በወሰደው የኢኮኖሚ ሪፎርም ጠቅላላ ሀገራዊ ምርቱ (GDP) ሲቀንስ የመንግስት የእዳ መጠን እና ከድህነት ወለል በታች የሚኖረው ህዝብ ቁጥር ጨምሯል።

ኢትዮጵያ በ207 ቢሊየን ዶላር GDP በአፍሪካ ከነበረችበት የ5ኛነት ደረጃ አሁን ላይ የGDP መጠኗ 100 ቢሊየን ዶላር በመውረዱ ከደረጃዋ ወርዳለች።

ገንዘብ ከዶላር አንፃር እየፈጠረ ያለው ልዩነት በጠቅላላ ኢኮኖሚው ውስጥ እንዴት እንደሚገለጽ በምሳሌ እንመልከት https://youtu.be/ArxEV6VWjEs