The Ethiopian Economist View
29.2K subscribers
726 photos
4 videos
198 files
1.34K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
2015 የስኬታችን ዓመት ይሁን!
መልካም አዲስ ዓመት!
በኑሮ ውድነት ወቅት ወጪያችንን እንዴት ማስተካከል እንደምንችል ያቀረብኩላችሁን https://www.youtube.com/watch?v=_S2pGFeLZrkeLZrk ተመልከቱ!
አዲስ አበባ ውስጥ #ባስ በመጠበቅ ከሚጠፋው ጊዜ በላይ #ባስ_ውስጥ ሆኖ በመንገድ መዘጋጋት የሚጠፋው ጊዜ እየበለጠ ነው!


የትራንስፖርት ሁኔታ የሰዎች መጓጓዝ ማለት ብቻ ሳይሆን የገንዘብ እና ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ፍጥነትን ይወስናል። ሰዎች በመንገድ መጨናነቅ መንገድ ላይ ዋሉ ማለት ከምርት ስርዓት ተቀነሱ ማለት ነው።


#ለምሳሌ፦ በአንድ ከተማ ውስጥ የመንገድ እንቅስቃሴን ለማስተካከል የትራንስፖርት አማራጮችን መጨመር፤  የመንገድ አማራጮችን ማስፋት ወይም የመንገድ እና የትራንስፖርት አጠቃቀም እና ስምሪትን ማስተካከል በተናጥል ወይም በአንድ ላይ ሊተገበሩ ይችላሉ።


ሁሉም አማራጮች ተገቢ ቢሆኑም በጣም የሚያዋጣውን መምረጥ ደግሞ ግድ ነው (Mitigate opportunity Cost)!


#ለምሳሌ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 110 አዳዲስ የአንበሳ አውቶቢሶችን 16.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ በማድረግ  ሥራ አስጀመረ እንዲሁም በሚቀጥሉት ሦስት ወራት 250 አዳዲስ አውቶቢሶች ወደ አገልግሎት የሚገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል (ወጪው የአስተዳደሩ በጀት እና የዓለም ባንክ  ድጋፍ ነው)።


በርግጥ ከአገልግሎት እየወጡ ያሉ በርካታ አሮጌ ባሶች ያሉበት ከተማ በመሆኑ አዳዲስ ባሶች ግዢ መደረጉ መጥፎ አይደለም! ለጉዳዩ ትኩረት ለመስጠት እና ለመወያየት ያህል የሚከተለው ጥያቄ ቢነሳ....


#ጥያቄው! ለአዲስ አበባ ከተማ ለትራንስፖርት ሁኔታው ተቀዳሚ መፍትሄው ተጨማሪ 360 ባስ ነው? ወይስ የተለዋጭ መንገድ ማስፋፋት እና የመንገድ አጠቃቀም ስርዓት ማበጀት? የሚለው ነው።


360ዎቹ ባሶች የመንገድ መስፋፋት ሳይኖር እና የመንገድ እና የትራንስፖርት አጠቃቀም እና ስምሪት ላይ ሳይሰራ ወደ ስምሪት ሲገቡ ተጨማሪ Opportunity Cost አለመፍጠራቸውን ማረጋገጥ ተገቢ ነው።


የበጀት እና የውጪ ምንዛሬ እጥረት ባለበት ኢኮኖሚ ውስጥ ወሳኙ ነጥብ የሚከናወኑ ስራዎች የሚኖራቸው ፋይዳ በጣም አሳማኝ እና ተቀዳሚ (Significant) መሆናቸውን ማረጋገጥ ነው።
#መረጃ

"ለግል መገልገያ እንዲውሉ ወደ ሀገር የሚገቡ/የሚወጡ ዕቃዎች ሁኔታን የሚወስነው በሥራ ላይ ያለው መመሪያ (መመሪያ ቁጥር 51/2010) ለሕገ ወጥ ንግድ በር የከፈተ እና አገልግሎት አሰጣጡ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደረ በመሆኑ ዓለምአቀፍ አሠራሮችን በተከተለ አኳኋን መመሪያውን አሻሽል ማውጣት በማስፈለጉ" በሚል ምክንያት ለግል መገልገያ እንዲውሉ ወደ አገር የሚገቡ ወይም ከአገር የሚወጡ ዕቃዎችን ለመወሰን መመሪያ ቁጥር 923/2014 ከነሀሴ 12/2014 ጀምሮ ተፈፃሚ እንዲሆን በገንዘብ ሚኒስቴር የተሻሻለው መመሪያ ይፋ ወጥቷል፡፡

በቀደመው መመሪያ በርካታ የቁሳቁስ አይነቶች ወደ ሀገር ውስጥ ከቀረጥ ነጻ ለማስገባት የሚፈቅደው መመሪያ በተሻሻለው አዲሱ መመሪያ መጠኑን ወደሚከተለው ሰንጠረዥ አሳጥሯል፡፡ ሙሉ መመሪያውን ማንበብ ለምትፈልጉ ከታች አስቀምጫለሁ!
ዋጋ ንረት ከፍተኛ ሲሆን የገንዘብ የመግዛት አቅም ስለሚዳከም ሰዎች ገንዘባቸውን ምን ላይ ቢያውሉት ከቁጥጥራቸው ወጪ የሆነውን የዋጋ ንረት ችግር መቋቋም ይችላሉ?


ገንዘብ በዋለበት ቦታ ዋጋውን የመወሰን አቅም አለው! ስለዚህ ሁኔታ የሰራሁትን ትንተና https://www.youtube.com/watch?v=1QHW-A5KXdU ተመልከቱ!



ገንዘብ በቤት ሲቀመጥ፤ በባንክ ሲቀመጥ፤ አክሲዮን/ቦንድ ሲገዛበት፤ ወርቅ ሲገዛበት፤ የውጪ ምንዛሬ ሲገዛበት እና ንግድ ሲጀመርበት ሊኖረው የሚችለውን ልዩነት ተመልከቱ!
መንግስት በየተቋማቱ #የመጨረሻዎቹን መሪዎች ማስቀመጥ አለበት!


ቢሮ ተቀምጠው ባለጉዳይ የሚያስተናግዱ የመንግስት ሰራተኞች እና ሃላፊዎች በሀገሪቷ ኢኮኖሚ ምርት እና ምርታማነት ላይ ተዘዋዋሪ ተጽኖ እንዳላቸው ሊረዱ ይገባል፡፡


#ለምሳሌ፡- ተቋማቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ ወይም የንግድ ፍቃድ ሂደቶች ላይ ፈጣን ምላሽ በመስጠታቸው በፍጥነት ስራ እንዲጀመር እና ምርት እንዲጨምር እንዲሁም የመንግስት ገቢ እንዲያድግ ማድረግ ይችላሉ፡፡


የተሾሙበትን ተቋም ራዕይ፤ ተልዕኮ እና ተግባር በመረዳት በእውቀት እና በድፍረት ሃላፊነት ወስደው የሚወስኑ የሚያሰሩ እና የሚሰሩ ሃላፊዎች ያሉበትን ያህል በየተቋሙ #አይሆንም፤ #አይቻልም እና #አይፈቀድም የሚል መልስ በግላቸው የሚሰጡ #ይሆናል የሚል መልስ ለመስጠት የመጨረሻ ሰው አለመሆናቸው የሚያሳዩ ብዙዎች ናቸው፡፡


#ለምሳሌ፡- በተቋማት የሆነ ጥያቄ እና አቤቱታ ይዞ ለሄደ ሰው ሃላፊዎች/ሰራተኞች ማንንም ሳያማክሩ #እንደማይቻል ሊናገሩ ይችላሉ! ስለዚህ የተቋሙ የመጨረሻ ሰው ማነው? ብላችሁ ስትሄዱ እሱም ለመወሰን እንዳልቻለ በኮሚቴ ወይም ከበላይ አካሎች ጋር አውርቼበት ምላሽ እሰጣለሁ ይላል፡፡


ማንንም ማማከር፤ ኮሚቴ ማዋቀር እና ከበላዮቹ ጋር ማውራት ሳያስፈልገው #አይሆንም! ያለ ሰው ይሆናል ወይም የማይሆነው በዚህ ምክንያት ነው ለማለት እንደመጨረሻ ሰው ሚና መውሰድ መከራ ነው፡፡


ለአንድ ጉዳይ ለዓመታት በተቋም የሚመላለሱ ሰዎች የመጨረሻ የሚባለውን ሰው ማግኘት ባለመቻላቸው ይቸገራሉ! ወረዳ መልስ አጥተው ክፍለ ከተማ የሄዱ፡ ክፍለ ከተማ መልስ አጥተው ከተማ የሄዱ፡ ሰዎችን ብትጠይቁ በየተቋሙ የመጨረሻ መሆን የነበረባቸው የተቋም ሃላፊዎች አግኝተዋቸዋል! ነገር ግን በውሳኔ እና ሃላፊነት በመውሰድ ረገድ የመጨረሻው ሰው መሆን ባለመቻላቸው የስራ ጫና/ተጠቃሚነት አንድ ቦታ እና ጥቂት ሰዎች ላይ እንዲጠራቀም ያደርጋል፡፡


በብዙ ተቋማት ለተለያዩ ጉዳዮች የመሄድ ልምድ አለኝ! በአብዛኛው ተቋማት ተቋማዊ አሰራር የመገንባት ልምምድ ብዙ ነው የሚቀረው፡፡ አንድ ሃገር ከድህነት ለመውጣት የመጀመሪያ የምትመከረው ተቋማዊ አሰራሮችን (Institutionalization) ለመገንባት እንድትሞክር ነው፡፡


ለአንድ ተቋም የሚያሰራ አዋጅ፤ ደንብ እና መመሪያ ከተዘጋጀ እሱን ተከትሎ የማስፈጸም እና የመፈጸም ሃላፊነት በየተቋሙ ያሉ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች ድርሻ ነው፡፡ አንዳንዶች "ተገልጋይ መመሪያውን አያውቀውም" በሚል መነሻ አብዛኛውን የሚቻል ጉዳይ ቅንነት በማጣታቸው፤ ለሙስና እና በአቅም ማነስ ምክንያት "መመሪያው አይፈቅድም" በሚል ጥቅል መልስ ለረጅም ጊዜ ድህነት ቅነሳ ስርዓት ላይ የሚተኙ አሉ፡፡


#ለምሳሌ፡- በተቋማቸው ላይ ሃላፊ ሆነው እንደተወካይ ወይም ከላይ ላለው መዋቅር መልክተኛ ይመስል ተራ
ጉዳይ ሲቀርብላቸው ቆይ ከላይ ጉዳዩን ማብራሪያ ልጠይቅበት የሚሉ ብዙ ናቸው፡፡


አንዳንዶች አይሆንም ለሚል መልስ የተቀመጡ ይመስል ንግግራቸውን አይሆንም ከሚል ነው የሚጀምሩት #ለምሳሌ፡- ባለሙያ መልስ መስጠት ካልቻለ ቡድን መሪ፤ ቡድን መሪ መልስ ካልሰጠ ዳይሬክተር፤ ዳይሬክተር መልስ መስጠት ከተቸገረ የመጨረሻው በስልጣን ተዋረድ ሃላፊው ጋር ቀርቦለት መመለስ እንደማይችል በተለያየ ምክንያት ካሳየ በለውጥ ጥናቶች ስራን እና ሃላፊነትን ወደታች ማውረድ የሚለው የ Decentralization መርህ ዋጋ አጥቷል ማለት ነው፡፡


አንዳንድ ሰዎች በየተቋሙ "ሃላፊውን አሳዩኝ" ይላሉ ነገር ግን ሃላፊውም በተለያዩ ምክንቶች ለብቻው ምላሽ መስጠት እንደማይችል ያሳያል (ተገልጋዮች የየተቋማቱ ሃላፊዎች የመጨረሻ ሰዎች እንደሆኑ ያምናሉ፡ የየተቋማቱ ሃላፊዎች የመጨረሻዎቹ ሰዎች እንደሆኑ ቢያምኑም በተግባር ግን የመጨረሻ አይደሉም)፡፡


#ለምሳሌ፡- ከተማ ያሉ ሃላፊዎች ክፍለ ከተሞች መጨረስ የነበረባቸውን አለመጨረሳቸውን ይታዘባሉ! ክፍለ ከተሞች ወረዳ በራሱ አቅም መወሰን አለመቻሉን ይታዘባሉ! የሚገርመው ወረዳ ያሉ ተገልጋዮች ክፍለ ከተማ ቢሄዱ የተሻለ ምላሽ እንደሚያገኙ ይሰማቸዋል! ከተማ ቢሄዱ ደግሞ የተሻለ እንዲሁም ፈጣን ምላሽ እንደሚያገኙ ያምናሉ፡፡


ይህ ሁሉ የሚያሳየው በየተቋሙ ጉዳዮቻችንን የምንነግራቸው ሃላፊዎች የመጨረሻዎቹ ሰዎች መሆናቸውን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? በተመሳሳይ መንግስት በየተዋረድ ያስቀመጣቸው የስራ ሃላፊዎች በተቋማቸው የመጨረሻዎቹ ሰዎች ለመሆን በእውቀት እና በነጻነት ብቁ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለበት፡፡


በርግጥ አይሆንም መልስ ነው! ነገር ግን ጉዳዩን በአግባቡ ሳይረዱ ለአይሆንም መልስ መዘጋጀት ባለጉዳዮች ረጅም ጥበቃ በማድረግ ጊዚያቸውን እና መተማመናቸውን እንዲያጡ በማድረግ ድህነት ቅነሳን ያስተጓጉላል፡፡


#ማስታወሻ፦ አንዳንዶች ርዕስ ብቻ ያነባሉ፤ አንዳንዶች ምሳሌውን ብቻ ያነባሉ፤ ሌሎች ገረፍ አርገው በማንበብ ጀጅ ያረጋሉ፤ አንዳንዶች የላቀ ተጨማሪ ምልከታ ይሰጡኛል። እኔ የምመክረው የፅሁፉን Context በመረዳት Rational የሆነ ውይይት ብናካሂድ ነው።
የውጪ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ በመግባታቸው የሀገር ውስጥ ባንኮች ደንበኞቻቸውን ያጣሉ?


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የውጪ ባንኮች ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መታሰቡን ተከትሎ ብዙ ሰዎች የሀገር ውስጥ ባንኮች ህልውና አሉታዊ ተጽኖ እንደሚደርስበት ያስባሉ! የሀገር ውስጥ ባንኮች ደንበኞቻቸውን ሊያጡ ስለሚችሉ ይጎዳሉ የሚል መከራከሪያ ያነሳሉ!


በመጪው ጊዚያት ውስን የሀገር ውስጥ ባንኮች ሊጎዱ ይችላሉ! ነገር ግን የሚጎዱት የውጪ ባንኮች ስለሚገቡ ወይም መሰረታዊ ደንበኞቻቸውን ስለሚያጡ ነው ብዬ አላስብም!


ለዚህ ውይይት እንዲረዳን የፋይናንስ ገበያውን ባህል እንመልከት! የቆጣቢው ህዝብ ብዛት፤ ሰዎች የሚቆጥቡበት/የባንክ ደብተር የሚከፍቱበት ምክንያት እና አማካይ ሰዎች በየባንክ አካውንታቸው እየቆጠቡ ያሉት የቁጠባ መጠን፤ ወዘተ፡፡


በተመሳሳይ የውጪ ባንኮች መሰረታዊ ትኩረት ቁጠባን በማሰባሰብ ለብድር ማቅረብ ሳይሆን ከተከማቸ ካፒታል ብድር በማቅረብ ከከፍተኛ የብድር ወለድ ትርፍ መሰብሰብ ነው፡፡ ስለዚህ የሀገር ውስጥ ባንኮች ሰፊ የቁጠባ ስርዓት ላይ መሳተፋቸውን ከቀጠሉ ለብድር ሊያቀርቡት የሚችሉት ካፒታል ተቀማጭ ገንዘብ ሳያጡ በገበያው ሊቆዩ ይችላሉ፡፡


#ለምሳሌ፡- የውጪ ባንኮች በሀገር ውስጥ የማህበራዊ ተሳትፏቸው ደካማ ነው! እንዲሁም ዋና መስሪያ ቤት ላይገነቡም ይችላሉ! ምን ማለት ነው በተዘዋዋሪ በተደረገላቸው ጥበቃ ወይም ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት በከፍተኛ ሁኔታ ወጪ በማውጣት የሚሳተፉ የሀገር ውስጥ ባንኮች በተወሰነ መልኩ ከተሳትፏቸው ሊቀንሱ ይችላሉ! ነገር ግን ከጠቅላላ ኢኮኖሚው ፋይዳ አንጻር የሚቻቻል ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡


ልብ በሉ አሁንም የውጪ ባንክ ሳይገባም የባንክ ሴክተሩን ፉክክር መቋቋም ያቃታቸው የሀገር ወስጥ ባንኮች አሉ! በተመሳሳይ ከ5 ዓመት በኋላ (ለአዳዲስ ባንኮች እስከ 7 ዓመት) መሟላት የሚገባው የ5 ቢሊየን ብር ተቀማጭ ካፒታል ለሟሟላት ብዙ የሚቀራቸው ባንኮች ብዙ ናቸው፡፡


በርካታ ሃብቶቻቸውን ዋስትና በማስያዝ በቢሊየን እና በመቶ ሚሊየን ብድር ውስጥ ያሉ ደንበኞች እስከ 30 ዓመት የሚቆይ የእዳ ዋስትና ውስጥ በመሆናቸው በቀላሉ ከነባር የሀገር ውስጥ ባንኮች በመላቀቅ ከውጪ ባንኮች ዋስትና አስይዘው ብድር ለመውሰድ የሚያስችል አቅም ሊኖራቸው ስለማይችል የሀገር ውስጥ ባንኮች ከፍተኛ ተበዳሪ ደንበኞቻቸው እንደያዙ በገበያው ትርፋማነታቸውን ይዘው የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡


የውጪ ባንኮች መግባት ከፍተኛ መጠን ያለው ብድር ለማቅረብ ድፍረት ወይም አሰራር ሊኖራቸው ስለማይችል ወደ ተለያዩ ታዳጊ ሀገራት ገበያ ሲገቡ ዝቅተኛ ብድሮች ላይ የመሳተፍ ልምድ ስላላቸው የሀገር ውስጥ ባንኮች ከፍተኛ የብድር ጥያቄዎችን በማስተናገድ በገበያው ሊፎካከሩ መቻላቸው አይቀርም፡፡


ባንኮች ያለባቸው አደጋ የውጪ ባንኮች ከመግባታቸው በፊትም ለረጅም ዓመታት ለባለሃብቶች/ድርጅቶች ያቀረቡትን ብድር ወለድ እንጂ ዋናውን በመሰብሰብ የተመዘገበ ትርፋቸው ዝቅተኛ በመሆኑ የመጪው ጊዜ ስጋታቸው ከውጪ ባንኮች ጋር ከመፎካከር በላይ እስካሁን ሲያቀርቡ የኖሩትን ዋናውን/Principal ብድር ማስመለስ ላይ ነው (ሁሉም ብድር በበቂ ዋስትና የቀረበ ነው ብሎ ማሰብ ጤነኛ አይደለም)፡፡


በባንኮች የቁጠባ ታሪክ ውስጥ ብዙ የባንክ ደብተር የሚከፍቱ ሰዎች እና በምክንያት ሳይሆን በሰዎች ጉትጎታ ብዙ አካውንት የሚከፍቱ ሰዎች በአካውንቶቻቸው የሚያንቀሳቅሱት ገንዘብ ከፍተኛ ባለመሆኑ አዳዲስ የውጪ ባንኮች በገቡበት ቅስፈት ብዙ ሰዎች ተጨማሪ አካውንት ከውጪ ባንኮች ቢያወጡ ከፍተኛ ቁጠባ ወደ ውጪ ባንኮች የሚዛወር እና ከፍተኛ ቁጠባ ከሃገር ውስጥ ባንኮች የሚወጣ ሊሆን ይችላል ብዬ አላስብም፡፡


#ለምሳሌ፡- የሰዎች ልምድ በመሆኑ የመጀመሪያ ወራቶች ላይ የውጪ ባንክ አካውንት የሚኖራቸው ሰዎች ቁጥር እንደወረት መጨመሩ አይቀርም! በተመሳሳይ የሳፋሪኮም 07 መነሻ ሲም ካርድ የሚያወጣ ሰው ቁጥር ቀላል ሊሆን አይችልም፡፡


መደበኛ የሀገር ውስጥ ባንኮች ገጠሩን ሲነኩ ስላልኖሩ እና የገጠሩ ክፍለ ኢኮኖሚ የፋይናንስ አቅርቦት እየተሸፈነ ያለው በመደበኛ የዋስትና ማስያዣ ባለመሆኑ አደጋ በመጋራት የብድር እና ቁጠባ ተቋማት ህልውና የውጪ ባንኮች በመግባታቸው ይበልጥ የሚፈተን ሊሆን ይችላል፡፡


ነገር ግን የገጠሩ ማህበረሰብ ንቃተ ህሊና እና ለአዳዲስ አሰራሮች የሚኖራቸው ተሳትፎ ፈጣን ባለመሆኑ ከተለመደው የብድር እና ቁጠባ የደንበኝነት መዝገቦቻቸው ወደ አዳዲሶቹ የውጪ ባንኮች ደንበኛ ለመሆን ፈጣን ምላሽ ይሰጣሉ ለማለት እንደሚያስቸግር ይሰማኛል፡፡


#ለምሳሌ፡- አዳዲስ የግብርና አሰራር (ምርጥ ዘር፤ መስኖ/ውሃ ማቆር፤ ኩታ ገጠም፤ የመኖ ዝርያ፤ ወዘተ) ለማስተዋወቅ በጣም ከፍተኛ ተግዳሮት የሚኖረው ከተለመደው የወጡ ልምዶችን ቶሎ ያለመቀበል ባህሪ በብዛት ስላል ነው)፡፡


የውጪ ባንኮች ባይመጡም ወደፊት ሁሉም የሀገር ውስጥ ባንኮች የተለመደውን ትርፋቸውን ይዘው ሊቀጥሉ አይችሉም! ውስን ባንኮች አሁንም በተሻሉ ባንኮች እየተዋጡ ነው፡፡ የስራ ማስኬጃ ወጪያቸውን እስከሸፈኑ ድረስ እንዳልወደቁ የሚያስቡ እንዲሁም ለባለአክሲዮን የትርፍ ክፍፍል መስጠት ተቸግረው/ዝቅተኛ መጠን የትርፍ ክፍፍል በተደጋጋሚ እያቀረቡ ያሉ ባንኮችን ታዘቡ፡፡


#ለምሳሌ፡- አንድ ባንክ በበቂ ሁኔታ ከፍተኛ ደሞዝ ለሃላፊዎቹ፤ ለሰራተኞቹ እና አበል ለቦርዶቹ እስከከፈለ እና የስራ ማስኬጃ ወጪውን እስከሸፈነ ድረስ አክሲዬን የገዙ ደንበኞች ምንም ትርፍ አላገኙም በሚል የሚጨነቅበት ደረጃ ምን ያህል ነው? በተመሳሳይ የባንከ ባለአክሲዮኖች  ባንካችን የትርፍ ክፍፍል እየሰጠን አይደለም ስለዚህ ይቅርብን ቢሉ! ለሶስተኛ ወገን ከስረው ካላስተላለፉ በቀር አሰራሩ ቀላል ነው?


የውጪ ባንኮች ቢገቡም ባይገቡም ወደ ፊት የካፒታል ገበያው ሲከፈት አሁን ካለው በተሻለ የነባር/ውጤታማ ባንኮች አክሲሆን ለገበያ በሰፊው ሊዘዋወር ስለሚችል ባለአክሲዮኖቻቸውን እያጡ የሚመጡ ባንኮች እንዲሁም አዳዲስ ባንኮች ለመክፈት ለገበያ ለሚቀርብ አክሲዬን ለመግዛት ፍላጎቶቻቸው የሚቀንስ ትርፍ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ስለሚመጣ አሁን ላይ ደካማ ባንኮች እስከ ጥምረት የደረሰ ስትራቴጂ ማሰብ መጀመር አለባቸው (ጠቅላላ ጉባዬ ላይ ባለአክሲዬኖች ይህንን የመፍትሄ ሃሳብ ቢያነሱ ስህተት ነው?)፡፡


በተቃራኒው የውጪ ባንኮች መግባትን እንደ እድል በመቁጠር በቴክኖሎጂ፤ በዘርፉ በሰለጠነ የሰው ሃይል፤ በቀልጣፋ አሰራር፤ በደህንነት አመራር፤ በጥምረት ብድር የማቅረብ አሰራር፤ ወዘተ ላይ ማሻሻያዎችን በማድረግ በጋራ ለማደግ ቀዳዳዎችን መፍጠር የሚችሉ የሀገር ውስጥ ባንኮች ለውጡን በብዙ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡
የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም እና በመጪው ጊዜ ይህ ሁኔታ በፍጥነት ላይቀረፍ ይችላል በሚል Uncertainty ሰዎች ያላቸው ገንዘብ ወደ ቋሚ ንብረት ለመለወጥ ካላቸው ፍላጎት በመነሳት የመሬት፤ የቤት እና የመኪና ዋጋ እየበረረ ነው።፡


የባንኮች የቋሚ ንብረት ብድር ስርዓትን ተከትሎ 30% ቅድመ ክፍያ መሸፈን የቻሉ ሰዎች ብራቸው ዋጋ እያጣ መምጣቱን ተከትሎ ወደ መኪና እና ቤት ሸመታ እየገቡ በመሆኑ ገበያው በጣም እየናረ ነው።


#ለምሳሌ፦ ላለፉት 3 ዓመታት ኮቪድን ተከትሎ የዓለም አቀፍ ንግድ መቀዛቀዝን ተከትሎ ለጊዜው ከገበያ የወጡ ገንዘቦች በአዲስ አበባ ከተማ ቤት እና መሬት ግዢ ላይ ውለዋል! በተመሳሳይ በተለያዩ አካባቢዎች የፀጥታ ሁኔታው በፈጠረው Uncertainty ሃብትን ወደ ቤት እና መሬት ማዞር የፈለጉ ሰዎች በአዲስ ከበባ የቋሚ ንብረት ገበያ ውስጥ ያላቸው ፍላጎት ቀላል አይደለም።


በቋሚ ንብረት ሸመታ ላይ እየተረባረቡ ያሉ የመካከለኛ እና ከፍተኛ ገቢ ባለቤቶች ተሳትፎ አብዛኛውን ኢ-መደበኛ ሴክተር ተሳታፊዎችን እና የዝቅተኛ ገቢ ባለቤቶችን ስለሚነካ ኢኮኖሚው ምን አገባኝ የሚለው ተፅዕኖ ስላልሆነ የመንግስትን ፈጣን እርምጃ ይፈልጋል (በመረረ የገበያ መዛነፍ ላይ የመንግስት ጣልቃ ገብነት ምክንያታዊ ነው)።


#ለምሳሌ፦ ከውጭ የሚገቡ ሆነ ሀገር ውስጥ የሚመረቱ #የኤሌክትሪክ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፣ የቤት አውቶሞቢሎችና የእቃ መጫኛ ተሽከርካሪዎች ላይ ዝቅተኛ የጉምሩክ ታሪፍ የሚጣልባቸው ሲሆን ከተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከኤክሳይዝ ታክስና ከሱር ታክስ #ነፃ መደረጋቸውን ገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።
Channel photo updated
ዘንድሮ ትምህርት ቤት የሚሄዱ #መካከለኛ_ገቢ ያላቸው ወላጆች ተበድረውም ይሁን ኖሯቸው የሚያሰተምሯቸው ህፃናት!

የ1000ብር ምሳ እቃ ከነምሳው (የመጀመሪያ ቀን ስለሆነ ምሳው እጅ ማስቆርጠሙ አይቀርም)።

የ1000ብር ደብተር (ራዲካል 850ብር ሲሆን ስኴር ደብተር፣ double line..ያካትታል)።

የ1700ብር ዩኒፎርም የህፃን/የህፃን የሚለው ላይ እናሰምራለን/ ።

ጫማ 1000ብር ተጠርቶ በስንት ጉንጭ አልፋ ክርክር 980 ብር የተገዛ።

የ1200 ብር ቦርሳ /በሌለ መንገድ የሚጎተተውን ቦርሳ ከገዙ 3400ብር/።

የ700 ብር ከለር/አርሳስ/ስዕል ደብተር/pencil case.....የመሳሰሉትን ይይዛሉ።

አዳዲስ ፓካውት፣ ካልሲ፣ የውስጥ ሱሪ ትምህርት ቤት የተከፈለላቸው እና የታክሲ/የሰርቪስ አልተካተቱም!

አንድ የሀረር ክላስሜቴ አጋርታው ያየሁት ነው! የቤተሰብ ትልቁ አስቤዛ የልጆች ትምህርት ወጪ ሆኗል (እኔም ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ልጄን ትምህርት ቤት ስለላኩ ይህንን ታዝቢያለሁ!)።
#ጥቂትነት! የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ችግር ነው!

ኢትዮጲያ ውስጥ መሰረታዊ የሚባሉ ቁሳቁሶች ከውጪ ሸምተው የሚያስገቡ ባለሃብቶች ጥቂት ናቸው! ይህ ማለት በቀላሉ ዋጋ የመወሰን፤ መረጃ የመለዋወጥ እና የመደራደር አቅም እንዲኖራቸው በማድረጉ በሰዓታት እና በቀናት ልዩነት ዋጋን፤ አቅርቦትን እና የውጪ ምንዛሬ ተመንን ይወስናሉ፡፡ በዚህ ሃሳብ ዙሪያ ይህንን ቪዲዮ ተመልከቱ https://www.youtube.com/watch?v=F79k8LG-7oY
#ጥቂትነት! የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ችግር ነው!

ኢትዮጲያ ውስጥ መሰረታዊ የሚባሉ ቁሳቁሶች ከውጪ ሸምተው የሚያስገቡ ባለሃብቶች ጥቂት ናቸው! ይህ ማለት በቀላሉ ዋጋ የመወሰን፤ መረጃ የመለዋወጥ እና የመደራደር አቅም እንዲኖራቸው በማድረጉ በሰዓታት እና በቀናት ልዩነት ዋጋን፤ አቅርቦትን እና የውጪ ምንዛሬ ተመንን ይወስናሉ፡፡

ከባንክ ከፍተኛ መጠን ብድር በህጋዊም ሆነ በአጠራጣሪው የወሰዱት ጥቂቶች ናቸው (የመንግስት እና የግል ባንኮች ብዙ ቢሊየኖች በብድር መልክ በጥቂት ሰዎች እጅ እንደሆነ ስውር መረጃ አይደለም)፡፡

#ለምሳሌ፡- በአንድ ወቅት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የፓልም ዘይት የሚያስገቡ አስመጪዎችን ሰብስበው "እናንተ ጥቂቶች ናችሁ በገበያው እየተጫወታችሁ ያላችሁት!" በሚል ማስጠንቀቂያ እና ተማጽኖ በማድረግ የፓልም ዘይት የመሸጫ ዋጋ ተመን ተቀምጦ ነበር! ነገር ግን በተቀመጠው የመሸጫ ዋጋ ምክንያት ካደሙ አስመጪዎች መካከል ለመንግስት ለዘብ ያሉት አስመጪዎች በወቅቱ ሁኔታዎችን ሲለውጡ አስተውለን ነበር፡፡

በኢኮኖሚ የገበያ ስርዓት ውስጥ ጤነኛ ካልሆኑ ስርዓቶች መካከል ብቸኝነት (Monopoly) ወይም ጥቂትነት (Oligopoly) ናቸው! ምክንያቱም እነዚህ የገበያ ስርዓቶች ዋጋን በመወሰን የገበያ ጤናማ ስርዓት ስለሚያዛቡ ነው፡፡

#ብቸኝነት (Monopoly)፡- አንድ ብቸኛ አምራች/አስመጪ ያለበት ገበያ ሲሆን አምራቹ ወይም አስመጪው አብዛኛው ፈላጊ ምርጫ ስለሌለው "ሸማች ቁሱን እስከፈለገው እና ገቢው እስከፈቀደ ድረስ ይሸምታል!" ስለሚል የቁሱን ዋጋ የመወሰን መብት አለው፡፡

#ለምሳሌ፡- በኢትዮጲያ ሳፋሪኮም እስኪመጣ ላለፉት 128 ዓመታት የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት የሚሰጠው ኢትዮ-ቴሌኮም ነው! ስለዚህ የአየር ሰዓት ዋጋን ካለተፎካካሪ ያዋጣኛል ያለውን ሲወስን ኖሯል፡፡ የዚህ አይነቱ ብቸኛ አቅራቢነት በመንግስትም ሆነ በግል ተቋማት ባይፈጠር የሚወደድ ነው! ነገር ግን የሚከለከል ስርዓት አይደለም! በዓለም ላይ ማይክሮሶፍት አቅሙ ኖሮት በብቸኝነት ማምረት እና መጠበቅ እስከቻለ ድረስ ቢልጌት ብቸኛ የዓለም አቅራቢ ሆኖ ሊቀጥል ይችላል (በቅርብ መረጃ ማይክሮሶፍት በአለም ላይ 90ከመቶ የኮምፕዪተር ኦፕሬቲንግ ሲስተምን የሚያቀርብ ድርጅት ነው)፡

#ጥቂትነት (Oligopoly):- ጥቂት አምራች፤ አስመጪ እና አገልግሎት አቅራቢ ኖሮ የፈላጊው ህዝብ ቁጥር ከፍተኛ ሲሆን ማለት ነው! በዚህ ስርዓት ውስጥ ጥቂቶች አቅርቦትን ከከፍተኛው ፍላጎት አንጻር ማዳረስ ስለሚቸገሩ እጥረቱን ተከትለው በጥቂት ፉክክር ዋጋን ይወስናሉ፡፡

#ለምሳሌ፡- ኢትዮጲያ ውስጥ የሲሚንቶ እና የብረት አምራች እና አስመጪዎች ግብይት የዚህ አይነት ባህሪ አለው! ትንሽ ሲያኮርፉ እጥረት ይፈጥራሉ! መንግስትን ምክንያት ደርድረው ይደራደራሉ! የራሳቸውን ዋጋ ይተምናሉ! (ለዚህ ነው የሲሚንቶ የመሸጫ ዋጋ ተመን መንግስት ሲያወጣ የሚስተዋለው)፡፡

ልብ በሉ! በኢትዮጲያ ቸርቻሪው ነው እንጂ አስመጪዎች እና አምራቾች ጥቂት ናቸው! ቸርቻሪ ዋጋን በመሰረታዊነት የመወሰን አቅም የለውም! #ለምሳሌ፡- መኪና የሚያስመጡ ጥቂቶቹት አስመጪዎች ተደዋውለው ተመሳሳይ የዕለቱን የመኪና ዋጋ የመወሰን አቅም ሊፈጥሩ ይችላሉ! ነገር ግን በመቶ ሺ የሚቆጠር የመኪና ፈላጊ/ሸማች መረጃ በመለዋወጥ ሻጮች መኪና ካስወደዱ "ለጊዚው አንግዛቸው" የሚል ውሳኔ ለመወሰን የመረጃ ተደራሽነት ችግር (Information Asymmetry) አለበት፡፡

#ለምሳሌ፡- "በአለፈው አንድ ወር ውስጥ ብቻ የተሽከርካሪ ዋጋ እጅግ እስደንጋጭ በሆነ ፍጥነት በአማካይ ከ300ሺ እስከ 700ሺ ብር ጭማሪ አሳይቷል"። በቅርቡ ያየሁት መረጃ ነው፡፡

#ለምሳሌ፡- 10 የምግብ ዘይት አስመጪ ነጋዴዎች ቢኖሩ ቡና እየጠጡ ገበያው ላይ ጫና ለመፍጠር ሊወስኑ ይችላሉ! አቅርቦት ደካማ መሆኑን ተረድተው የትርፍ ድርሻ ስሌታቸውን ለማሳደግ ሊወስኑ ይችላሉ፡፡ በሆነ አንድ ምክንያት 10ሩም ቢያኮርፉ (የወጡ አዳዲስ መመሪያዎች ላይ ደስተኛ ባይሆኑ) ወይ መንግስት ዘይቱን በራሱ መስመር ያስመጣዋል አልያም ህዝቡ የዘይት ያለ ይላል፡፡

በኢትዮጰያ እንግዳው ነገር ብቸኝነት እና ጥቂተኝነት በማምረት የሚፈጠር ሳይሆን ከውጪ በማስመጣት የሚፈጠር መሆኑ ነው፡፡ በሀገር ውስጥ የማምረቻ ወጪ ከፍተኛ መሆን፤ በአምራቾች እና በአስመጪዎች መካከል የተዘረጋው ማበረታቻ በአግባቡ ስላልተለጠጠ፤ የጥቁር ገበያ መጠንከር፤ ደካማ የገበያ ጣልቃ ገብነት አካሄድ መኖር፤ ወዘተ አስመጪዎችን የጥቂተኝነት ጉልበት እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች ገበያው በበቂ ማምረት ያልቻላቸው ቁሶች ሲበራከቱ፤ በገበያው ባለው የቆየ አሻጥር የተገደበው የንግዱ ተዋናዬች ቁጥር መጨመር ካልቻለ፤ የጥቁር ገበያው አዋጪነቱን ካላቆመ እና የመረጃ ተደራሽነት/ምክንያታዊ የሸመታ ውሳኔ እየተለመደ ካልመጣ! መንግስት በፖሊሲ/በመመሪያ የገበያ ጣልቃ ገብነት እና የተጠና ገደብ ማስቀመጥ አለበት፡፡

ፈጣን እና ሰፊ መሰረት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ለመፍጠር የግል ሴክተሩ የላቀ ተሳትፎ በገበያው እንዲኖረው ማድረግ ተገቢ ነው! ነገር ግን የግል ሴክተሩ በተለያዩ ምክንያቶች ውስን ቁጥር ያላቸውን የቀደሙ ተዋናዮች ብቻ ይዞ ከቀጠለ ከአመክንዬ የወጣ የገበያ ቅርጽ እንዲኖር ያደርጋል፡፡

ስለዚህ የግል ሴክተሩ በሀገር ውስጥ የማምረት አቅሙ እንዲያድግ የእጥረት ዘርፎችን ለይቶ ማበረታታት፤ የፋይናንስ አቅርቦት አሰራር ማሻሻያ ማድረግ፤ የባላሃብቶችን ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ በመርህ ላይ እንዲመሰረት ማድረግ (ባለሃብቶች ላይ የተጣበቀም ሆነ ባላሃብቶችን ትኩረት የነሳ የመንግስት ግንኙነት አመክንዮያዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መሰረቱን ይለቃል!)፡፡

በጥቂቶች የገበያ አሻጥር እየተፈተነ ያለ ኢኮኖሚ/መንግስት ምክንያታዊ ወዳልሆነ ቁጥጥር አልያም በገበያው የአስመጪነት እና የቸርቻሪነት ሚና እራሱ እንዲረከብ በማድረግ የውጤታማነት ማነስ እና የወጪ መብዛት ውስጥ ገብቶ ከመሰረታዊ መፍትሄ ይልቅ ለጊዚያዊ ማስታገሻዎች ትኩረት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡
የዛሬ 40 ዓመት ጥርስ የሚነቀልበት ሂደት ብዙም ሳይለወጥ ጥርስ የማስነቂያ ዋጋ አሁን ላይ እጅግ ውድ የሆነው ለምን ይመስላችኋል? የ1980ዎቹ ክትፎ ከዘንድሮው ክትፎ ምንም ለውጥ ሳይጨመርበት በዋጋ ረገድ ውድ የሆነበት ምክንያት ምን ይመስላቸኋል? በትምህርት ጥራት እየቀነሱ ነገር ግን በዋጋ ውድ እየሆኑ ያሉ ኮሌጅ እና ዩኒቨርስቲዎች ምክንያታቸው ምን ይመስላችኋል?

ከ1970ዎቹ እስከ 2014 ድረስ ተመሳሳይ ዘፈን በየመድረኩ የዘፈነ ዘፋኝ ተመሳሳይ ስራ እየሰራ የሚከፈለው ክፍያ ለምን የጨመረ ይመስላችኋል? የዛሬ 25 ዓመት በተመሳሳይ የሰርግ ዘፈን የዳረ ዘፋኝ ዘንድሮ ያንኑ ዘፍኖ በብዙ እጥፍ ክፈሉኝ ለምን የሚል ይመስላችኋል? የዛሬ 20 ዓመት የነበሩ የግል ትምህርት ቤቶች የማስተማሪያ ዘዲያቸው ብዙም ሳይለውጡ እና ነባር አስተማሪዎቻቸው እየተጠቀሙ የዛሬ 20 ዓመት ከሚጠይቁት ክፍያ በከፍተኛ ሁኔታ ያስወደዱት ለምን ይመስላችኋል?

በጥራትም ሆነ በአዋጪነት ደካማ መሆናቸው እየታወቀ ለትምህርት ሴክተር፤ ለጤናው ሴክተር፤ ለደህንንት ተቋማት፤ ወዘተ ለምን ከፍተኛውን የመንግስታትን በጀት ድርሻ የሚወስዱ ይመስላችኋል?

ከላይ በዘመናት መካከል የአገልግሎት ዋጋዎች በከፍተኛ ደረጃ እየጨመሩ የመጡበትን ምክንያት እኔም እናንተ ልትገምቱ ከምትችሉት የዘለለ ምክንያት አላቸው ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ ነገር ግን የአሜሪካዊውን ኢኮኖሚስት William Baumol ወሳኝ አርቲክል ማለትም #Cost_Disease (Baumol effect) የሚለውን ሳነብ በቀጣይ የአለም የኢኮኖሚ አካሄድ ባህሪ ልብ ሳይባል እየተለወጠ መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡

William Baumol በ1960ዎቹ የሚሰሩ ሙዚቀኞች የተለየ ፈጠራን ሳይጨምሩ (Low productivity) ተመሳሳይ ስራዎች በመስራት የሚያገኙት ገቢ ግን በፍጥነት እያደገ መሄዱን አየ! ከዛ የ100 ዓመት መረጃዎችን (1865 እስከ 1965) ሲያጠና ተጨማሪ ፈጠራ ሳይኖራቸው ዘፋኞች በየመድረኩ የሚያስከፍሉት ክፍያ እየጨመረ ነበር፡፡

ስለዚህ "ሁለት አይነት ሴክተር በኢኮኖሚ ውስጥ አለ" አለ! በጣም የቴክኖሎጂ ፈጠራቸው እያደግ ያሉ እና በተጨማሪ የማምረት አቅም (Productivity) የደረጁት የአምራች/Manufacture ክፍሉ እና ብዙም የተለየ ፈጠራ እና የማምረት አቅማቸው እያደገ ያልሆኑት (Stagnant productivity) የአገልግሎት/Service ክፍል ናቸው ይላል፡፡

#ለምሳሌ፡- ከደርግ ዘመን ጀምሮ የቆዳ ጫማ የምርት ስርዓት ለማደግ የለፋውን ያህል ከደርግ ጊዜ ጀምሮ በተመሳሳይ ጣባ የሚቀርበው ክትፎን ማወዳደር ማለት ነው (ከያኔው አንጻር አሁን ላይ የቂቤው ጥራት ቀንሶ ሊሆንም ይችላል!) ስለዚህ የአንድ ጫማ ዋጋ ጫማውን ለማምረት በየዘመኑ የተፈጠሩ የጫማ ቴክኖሎጂ እና ማሽኖችን መሰረት በማድረግ ውስን የዋጋ ጭማሪ ሊኖረው ቢችልም ምንም የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና የአመራረት ሂደት የሌለው ክትፎ በየሬስቶራንቱ የሚጠየቅበት ዋጋ ከያኔው አንጻር ከፍተኛ ነው፡፡

ከታች ያለውን ግራፍ ተመልከቱት በአሜሪካ የ20ዓመት መረጃ ተወስዶ የአምራች ክፍሉ ዋጋ እና የአገልግሎት ክፍሉ ዋጋ ያላቸው ልዩነት ከፍተኛ ነው! የጫማ ዋጋ ከሚጨምረው በላይ የትምህርት ቤት ክፍያ ያድጋል፤ የአዳዲስ ዘመናዊ መኪኖች ዋጋ ከሚጨምረው በላይ ለህክምና የሚጠየቀው ዋጋ ውድ ነው፤ በየዘመኑ ለመጡ ለፈርኒቸር ውጤቶች ከሚጠየቀው ዋጋ በላይ ልጅ ለማስተማር የሚጠየቀው ዋጋ ውድ ነው፤ ወዘተ፡፡

በአምራች ክፍሉ ያለው ምርታማነት ማደግ ሰዎች ከፍተኛ ገቢ እንዲያገኙ ስለሚያደርግ የመክፈል አቅም አላቸው (This is because the economy's constantly growing productivity simultaneously increases the community's overall purchasing power) የሚለው እሳቤ ለአገልግሎት የሚቀርቡ ሰዎችን ዋጋ እያናረው መጥቷል እንዲሁም ሰዎች በተቻለ መጠን ወደ አምራች ክፍሉ የስራ ዘርፍ ሊኖራቸው የሚችልን መዛወር ለመቋቋም በአገልግሎቱ ሴክተር ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን እዳይለቁ ለማባበል ሲባል የሚከፈላቸው ክፍያ እያደገ ሲሄድ ለአገልግሎቱ የሚያስከፍሉት እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

በሀገራችን ከሆቴል ማናጀር ወይም ዋና ሼፍ እና ከጫማ ፋብሪካ ማናጀር በደሞዝ የሚሻለው ማን ነው?

William Baumol የመኪና አምራች ክፍሉ በጣም ዘመናዊ መኪኖችን እያመረተ ነው! ስለዚህ ፈጠራው ጨምሮ በሹፍርና ዘርፍ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰዎች በራሱ መንቀሳቀስ የሚችል (Automated) መኪና ሲፈጠር ስራቸውን ያጣሉ! ነገር ግን ምንም ዘመናዊነት ቢያድግ ሰዎች ሃኪም፤ አስተማሪ እና ጸጉር ቆራጮችን በማሽን ሊተኳቸው አልያም እነዚህ የአገልግሎት ሴክተር ሰራተኞች ስራችንን ልናጣ እንችላለን ስለማይሉ የአገልግሎት ሴክተሩ ተሳትፎ እያደገ ይሄዳል ይላል፡፡

ረቦቶች/ማሽኖች እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች እያደጉ መምጣታቸውን ተከትሎ በማምረቻ ተቋማት ያለው የሰራተኛ ቁጥር የመጨመር ሳይሆን የመቀነስ አዝማሚያ እያሳየ ነው፡፡ ነገር ግን በአገልግሎት ሴክተሩ ያለው ሰራተኛ በእጅጉ እያደገ ነው፡፡ ምን ማለት ነው? በቀጣይ የዓለም ኢኮኖሚ ከአምራች ወደ አገልግሎት ሴክተር እየተዛወረ መሄዱ ጤነኛ የሚባል አይሆንም ይላል ምክንያቱም በአገልግሎት ሴክተሩ የሚከፈለው ከፍተኛ ክፍያ በአምራች ዘርፉ ያሉ ሰራተኞችን ማስኮብለሉ አይቀርም ነው፡፡

የመንግስታት የጤና እና የትምህርት ወጪ/በጀት እያደገ ሲሄድ ለሴክተሩ በተሰጠ ትኩረት ብቻ ይመስላቸዋል! ነገር ግን ሴክተሩ የሚጠይቀው ዋጋ እና ወጪ በፍጥነት እየጨመረ በመምጣቱ ነው፡፡

ከፍተኛ የማምረት አቅም ያላቸው የአምራች ክፍሎች/ፋብሪካዎች የሚጠቀሟቸው ማሽኖች የምርትን ጠቅላላ ወጪ ስለቀነሱት የምርቶች ዋጋ መቀነስ እያሳየ ነው ነገር ግን ከፍተኛ የማምረት አቅም የማይስተዋልበት የአገልግሎት ዘርፉ ከፍተኛ ፈላጊ በመያዝ የአገልግሎት ወጪውም ክፍያውም ውድ እየሆነ ነው፡፡

#ለምሳሌ፡- ደሞዝ በማይከፈላቸው ረቦቶች የሚያመርት ካምፓኒ የማምረቻ ወጪው በሂደት እየቀነሰለት ነው የሚሄደው ስለዚህ የምርቱ ዋጋ እየቀነሰ ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ቀጥታ ተሳትፎ የሚያደርጉበት ሴክተር (labor-intensive services) ውድ መሆናቸው ቀጥለዋል፡፡

ነገር ግን በሀገራችን ሁኔታው ይህንን ባህሪ ይይዛል ለማለት ከባድ ነው፡፡ የማምረቻ ዘርፉ የምርታማነት መጠን በሚፈለገው ልክ ሳያድግ/ኢኮኖሚው በአብዛኛው ለፍጆታው የሚያስፈልገውን የኢንዱስትሪ ውጤቶች ከውጪ ሸምቶ አስገቢ ሆኖ/ የግል ሴክተሩ ለትምህርት፤ ለጤና፤ ወዘተ የሚጠየቀው ክፍያ William Baumol በሚለው በተመሳሳዩ እያደገ ነው! ስለዚህ ኢኮኖሚያዊ መሰረት ጠንካራ መሆን የሚገባው በአምራች እና በአገልግሎት ሴክተሩ መካከል ሊኖር የሚገባው እሽቅድድም ጤነኛ ሲያረግ ነው፡፡

የኢኮኖሚክስ ትምህርት እንዲወደድ የሚያደርገው ዋናው ምክንያት አለማለቁ ነው! ሁሌም ከሁኔታዎች አንጻር አመክንዮዎቹ ይቀነሳሉ! ይጨመራሉ! ዛሬ ላቀርብላችሁ የሞከርኩት ሃሳብ ትንሽ ግር የሚል ቢመስልም ዓለም ምርጥ የሚለው የኢኮኖሚክስ ሃሳብ ነው! በጽሁፍ ለመግለጽ የማያመቹ ቢሆኑም የተወሰነ ሞክሪያለሁ ተጨማሪ በማንበብ በደንብ መረዳት አልያም ማዳበር የምትፈልጉ ሰዎች ልትጨምሩበት ትችላላችሁ፡፡
በቅርቡ ድሬዳዋ እና ሀረር ሄጄ ስመለከት!


#በድሬዳዋ ባጃጆች የቀን እና የምሽት የሚል ክፍፍል አላቸው። #በሀረር ዛሬ የሚሰሩ ባጃጆች በቀጣዩ ቀን መስራት አይችሉም! (በታርጋቸው የመጨረሻ ቁጥር ሙሉ እና ጎዶሎ በሚለው አሰራር ኮቪድን ተከትሎ የተጀመረ ቢሆንም ስምሪቱን ለማቃለል በሚል ቀጥሏል)።


የባጃጆች ቁጥር ከመንገዱ እና ከተገልጋዩ አንፃር ከፍተኛ በመሆኑ የተወሰደ መፍትሄ ቢሆንም! በመርህ ደረጃ መንግስት በገበያው ያለውን ውድድር በመመሪያ እየመራው ነው።


አሽከርካሪዎች በውሳኔው ብዙም አልተከፉም! ምክንያቱም የፈረቃ ስራ ተጠቃሚውን ለከፍተኛ ክፍያ ቢዳርገውም አሽከርካሪዎች ወደ #ማካካስ ስርዓት እንዲመጡ አድርጓል። በተጨማሪም ሁሉም ባጃጅ አንድ ላይ ቢሰማራ ሽሚያው ዝቅተኛ የሚባለውን ገቢ መግኘትን ከባድ እንደሚያረገው አውቀዋል።


ከ300ሺ ብር በላይ መነሻ ካፒታል የሚጠይቀው የባጃጅ ስራን ሰዎች ከሌሎች አዋጪ መካከለኛ የቢዝነስ ስራዎች ጋር እንዲያወዳድሩ እድሉን መንግስት መክፈት አለበት (የባጃጅ ስራ ትምህርት ካቋረጠ ወጣት እስከ የመንግስት ስራ አያዋጣም እስካለው  ወጣት በሙሉ የሚመካበት ስራ ሆኗል)።


ለወጣቶች ስራ ማለት አዋዋል እና ወጪን ከማስተካከያ መንገዶች ውስጥ ዋነኛው ነው። ጥቂቶች በስራ ቀን ያገኙትን ገንዘብ በቀጣይ ቀኑ እረፍት ሲሆኑ እንዲያባክኑት ሙሉ ፍቃድ የመስጠት ያህል ሊሆን ይችላል።


በከተሞቹ ባጃጆች ቁጥራቸው ብዙ በመሆኑ በነዳጅ ግብይት ላይ የሚኖራቸው ሽሚያ እና ቆይታ ከመጨመሩ የተነሳ ነዳጅ በጥቁር ገበያ እንዲሸጥም የሚያስገድድበት ወቅት አለ።


በመመሪያ ተገድቦ በወር 15 ቀን ብቻ ለመስራት የሚወስን ወጣት የሙሉ ጊዜ ውጤታማ ስራ እንዲሰራ ከተሞች እና ክለሎች ቀድመው ወጣቱ ወደ Productivity ሴክተር ገንዘብ፤ ጉልበቱን እና ያለውን እውቀት ይዞ እንዲገባ ምርጫ ማዘጋጀት ግድ ነው።


ከወጣቶች እይታ አንፃር ወር ሙሉ ስራ ፈት ከመሆን በወር ውስጥ 15 ቀን ስራ መስራት መጥፎ አይደለም! ለመንግስት ደግሞ ጠንካራ ወጣቶች ከነመነሻ ካፒታላቸው በወር 15 ቀን ሙሉ በቤታቸው መቀመጣቸውን ለማስቀረት ቢያስብ መጥፎ አይደለም።
የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ችግር ከአቅርቦት ማነስ ወይስ ከፍላጎት ማደግ የመነጨ ነው?


በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ የብዙ ሀገራት ችግር ለዜጎቻቸው በቂ የሆነ የቁሳቁስ፤ የአገልግሎት እና የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት ማዳረስ ነው፡፡


በተመሳሳይ የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ከፍተኛ ፍላጎት ያለበት ቢሆንም አቅርቦትን በተመለከተ የባለብዙ ክፍተት ነው፡፡


ፍላጎት እና አቅርቦት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና የኢትዮጲያ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ችግር የአቅርቦት በየጊዜው ማደግ ወይስ ተፈላጊው አቅርቦት ያለመጨመር?


በምሳሌ በማስደገፍ ይህንን ቪዲዮhttps://www.youtube.com/watch?v=TQ0HscndAgQ&t=38s አቅርቤላችኋለሁ እስከ መጨረሻው ተከታተሉ፡፡
የንግድ እና ቀጠናዊ ሚኒስትር፦ "በነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ምክንያት የሸቀጦችን ዋጋ የሚጨምሩት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ!"።


መንግስት መሸከም ያቃተውን የነዳጅ ወጪ ሸማች እንዲሸከም እያደረጉ ያሉትን ነጋዴዎች በተመሳሳይ #ዛቻ ብቻ ማስታገስ ይቻላል?
የኢትዮጵያ የዋጋ ንረት አስፈሪው Hyperinflation ደረጃ ላይ ደርሷል?


የኑሮ ውድነቱን ጣራ ያደረሰው የዋጋ ንረት ምክንያት እና ያለበት ደረጃ ከዓለም ሀገራት አንፃር ምን ይመስላል? በዚህ ዙሪያ ይህንን https://youtu.be/0gEbN0kzeP0 ትንታኔ ተመልከቱ።
መሰረታዊ የኢኮኖሚ ችግር የሆነውን የዋጋ ንረትን በደንብ መረዳት ተገቢ ነው! የዋጋ ንረት ማለት በተደጋጋሚ የቁሳቁስም ሆነ የአገልግሎት ዋጋ መጨመር ሲከሰት እና እሱን ተከትሎ የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም ሲጀምር ነው። በቀላል ቋንቋ ብዙ ገንዘብ ይዞ ጥቂት ብቻ መሸመት መቻል ማለት ነው!


የዋጋ ንረት አሁን ላይ በሀገራችን የደረሰበት ደረጃ ላይ ለመድረስ የተጓዘባቸውን እና ወደፊት የሚጓዝባቸውን ደረጃዎች እንመልከት! የዋጋ ንረት አይነት እና ደረጃዎች......


#Creeping_Inflation፦ የዋጋ ንረት መሆን የሚገባው ተፈጥሯዊ ደረጃ አለ እሱም በዓመት ዋጋ ከ3% ባልበለጠ መልኩ በዝግታ እየጨመረ ሲሄድ የአምራች ክፍሉ ስለሚበረታታ ጤነኛ የዋጋ ንረት (Moderate Inflation) ደረጃ ይባላል።


#ለምሳሌ፦ የዛሬ አመት መስከረም ወር 100 ብር ይሸጥ የነበረ ቁስ ዘንድሮ በመስከረም ወር ቢያንስ አማካይ ዋጋው እስከ 3 ብር ጨምሮ 103 ብር ቢሸጥ እንደማለት ነው።


#Walking_Inflation፦ ጤነኛ የነበረው የዋጋ መጨመር በሂደት ከፍ እያለ በዓመት በአማካኝ ቢያንስ ከ3% እስከ 9% በዝግመት መጨመር ሲጀምር የዋጋ ግሽበት ጥንቃቄ መደሚፈልግበት ደረጃ ደርሷል ይባላል።


#ለምሳሌ፦ የዛሬ አመት መስከረም ወር 100 ብር ይሸጥ የነበረ ቁስ ዘንድሮ በመስከረም ወር ቢያንስ አማካይ ዋጋው በ9 ብር ጨምሮ 109 ብር ቢሸጥ እንደማለት ነው።


#Running_Inflation፦ የዋጋ ንረት ፈጠን ያለ ዝግመት በጀመረበት ወቅት ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ ባለማድረግ ሁኔታው እየተባባሰ ከመጣ የዋጋ ጭማሪ ወደ ሩጫ ይዘዋወራል። ማለትም በዓመት ቢያንስ ከ10% እስከ 20% ሲጨምር ማለት ነው። የዋጋ ንረት ከወጣ በኋላ ለመቆጣጠር ከመሞከር ይልቅ መጀመሪያ አካባቢ የሚታዩ የዋጋ መጨመርን በጥንቃቄ መቆጣጠር ካልተቻለ የዋጋ ንረት በፍጥነት ከጨመረ በኋላ ዝቅ ማድረግ አስቸጋሪ እና ፈታኝ ነው።


#ለምሳሌ፦ የዛሬ አመት መስከረም ወር 100 ብር ይሸጥ የነበረ ቁስ ዘንድሮ በመስከረም ወር ቢያንስ አማካይ ዋጋው 20 ብር ጨምሮ 120 ብር ቢሸጥ እንደማለት ነው።


#Hyper_inflation፦ የዋጋ ንረት የመጨረሻ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ እና ኢኮኖሚውን በሚያሽመደምድ ደረጃ ላይ ሲደርስ ማለት ሲሆን በዚህ ወቅት የቁሳቁስም ሆነ የአገልግሎት ዋጋ አማካይ ወራዊ ጭማሪ ከ50% በላይ ሲደርስ ነው።


#ለምሳሌ፦ የዛሬ አመት መስከረም ወር 100 ብር ይሸጥ የነበረ ቁስ ዘንድሮ በመስከረም ወር ቢያንስ ከ50 ብር በላይ ጨምሮ ከ150 ብር በላይ ቢሸጥ እንደማለት ነው። ሀገራችን በተለይ በውስን ቁሶች ለዚህ አይነቱ የዋጋ ንረት እየተቃረበች ነው።


በዓለም ላይ ከተከሰቱ ከፍተኛ የዋጋ ንረቶች የምንማረው! አብዛኛው ከፍተኛ የዋጋ ንረት Hyperinflation ተፈጥሮባቸው የነበሩ ሀገራት ስንመለከት በጦርነት ወቅት እና ከጦርነት ማግስት ባሉት የመጀመሪያዎቹ 3 ዓመታት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አስተናግደው ነበር! ምክንያቱም ከጦርነት ለማገገም ከፍተኛ የበጀት ጉድለቱ የሚሞላበት መንገድ ዋጋ ንረትን አቀጣጣይ በመሆኑ ነው፡፡


#ለምሳሌ፡- በዓለም ላይ ከተከሰቱ ከፍተኛ የዋጋ ንረቶች መካከል…..


#ሀንጋሪ፦ 1946 (የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማለቂያ ላይ) የዋጋ ንረቱ በወር 41.9 ኳድሪሊየን % የነበረ ሲሆን (41,900,000,000,000,000%) በየ15 ሰዓቱ የዋጋ ንረቱ ራሱን እጥፍ ያደርግ ነበር።


#ዝምባዋብዌ፦ 2008 (የዓለም የፋይናንስ ቀውስ በተፈጠረበት እና የነጮችን መሬት በመቀማት ለጥቁሮች ማደል በተጀመሩበት ወቅት) የዋጋ ንረቱ በወር 79 ቢሊየን ወይም 79,600,000,000%% የነበረ ሲሆን በየ 24 ሰዓቱ የዋጋ ንረቱ ራሱን እጥፍ ያደርግ ነበር።


በዚህ ወቅት ዜጎች ቁሳቁስ ለመግዛት ገንዘብ መሸከም ዋጋ ቢስ ከመሆኑ የተነሳ በአንድ ወረቀት እስከ 100ትሪሊን ኖት ለማተም ተገደው የነበረ ሲሆን በመጨረሻ መገበያያ ገንዘባቸውን ወደ አሜሪካ ዶላር ለውጠው ነበር።


#ይጎዝላቪያ፦ 1994 (ጦርነት እና መከፋፈልን በነበረበት ወቅት) የዋጋ ንረቱ በወር 313 ሚሊየን % የነበረ ሲሆን በየ 1 ቀን ከግማሽ የዋጋ ንረቱ ራሱን እጥፍ ያደርግ ነበር (ዓመታዊ የዋጋ ንረቱ 116 ትርሊዮን ወይም 116,545,906,563,330% ደርሶ ነበር)።


#ጀርመን፦ 1923 (የአንደኛው የዓለም ጦርነት በ1918 ከተጠናቀቀ በኋላ) የዋጋ ንረቱ በወር 29ሺ% የነበረ ሲሆን በየ3 ቀን የዋጋ ንረቱ ራሱን እጥፍ ያደርግ ነበር።


#ግሪክ፦ 1944 (በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት) የዋጋ ንረቱ በወር 14ሺ% የነበረ ሲሆን በየ4 ቀኑ የዋጋ ንረቱ ራሱን እጥፍ ያደርግ ነበር።


በ2022 በዓለማችን ከፍተኛ የዋጋ ንረት ካላባቸው 10 ሃገራት መካከል ኢትዮጲያ አንዷ ነች (ቬንዙዬላ በ1200% ዓመታዊ የዋጋ ንረት ቀዳሚዋ ሀገር ነች)፡፡


#ማሳሰቢያ፦ የዋጋ ንረቱ መነሻ የፍላጎት መናር (Demand-Pull Inflation) ወይም የማምረቻ ወጪ በመጨመሩ (Cost-Push Inflation) ምክንያት ሊሆን ይችላል። አማካይ የዋጋ ንረት የሚሰላው የብዙ ቁሶች የመሸጫ ዋጋ ይሰበሰብ እና ለእያንዳንዱ ቁሳቁስ ከተሰጠው ክብደት አንፃር ተሰልቶ የሚሰራ ስለሚሆን በገበያው ከተቀመጠው ዋጋ የሚጨምርም የሚቀንስም ይኖራል።


#ለምሳሌ፦ የዋጋ ንረት 20% ሆኗል ሲባል ሁሉም ቁሳቁስ የጨመረው 20% ብቻ ነው ማለት ሳይሆን የተወሰኑት ከ20% በታች የተወሰኑት ከ50% በላይ ጨምረው ሊሆን ይችላል።


በሀገራችን ያለው የዋጋ ንረት ተደራራቢ ነባር እና አዳዲስ ምክንያቶችን እየጨመረ የሚሄድ በመሆኑ ለአጭር ጊዜ ከውጪ አጋር ሀገራት የፍጆታ ብድርችን በማፈላለግ መሰረታዊ ቁሶች ሸመታ ማከናወን (መሰረታዊ ቁሶች ላይ የተፈቀደው የፍራንኮ ቫሎታ እድል የግንባታ ቁሶችን ቢያጠቃልል መጥፎ አይደለም!)፤ በድጎማ የሚገቡ ምርቶችን የገበያ ስርጭትን መከታተል፤ የምርት ስራዎች ላይ ርብርብ ማድረግ፤ ከውጪ በሚገቡ ምርቶች ላይ ቁጥጥር እና ክልከላ ማካሄድ፤ አዳዲስ ብር ማተምን ማቆም ወይም መቀነስ………..


የመንግስት የገቢ አማራጮችን ማስፋት (መሬቶች፤ ቤቶች፤ ማዕድኖች፤ ወዘተ ለሽያጭ ማቅረብ ሊሆን ይችላል!) ግብር ከፋዩ ቀድሞ የሚከፍል ከሆነ አበረታች የግብር ቅናሽ በማቅረብ አሁን ላይ የመንግስት ገቢን ማሳደግ፤ #ለምሳሌ፦ በዓመት 100 ሚሊየን ብር ግብር የሚከፍል ተቋም ቀድሞ 85 ሚሊየን ብር ቢከፍል እና የ15 ሚሊየን ብር ቅናሽ እንደሚያገኝ ድርድር ቢፈጠር ያልተለመደ ወይም የማይሰራ አካሄድ አይደለም!፤ የመንግስትን ወጪ ምክንያታዊ ማድረግ እንዲሁም ከሁሉም በላይ #የጸጥታ ሁኔታውን ማረጋጋት ለውጥ ያመጣሉ ብዬ አስባለሁ፡፡