The Ethiopian Economist View
29.2K subscribers
725 photos
4 videos
198 files
1.34K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
SPSS ላይ ዳታ እንዴት ማስገባት ይቻላል?

ጥናት ለማካሄድ የተሰበሰበ መረጃ ወደ ሶፍትዌር መግባት እንዳለበት ይታወቃል፡፡

ስለዚህ....

1. ወደ SPSS እንዴት ዳታ ማስገባት እንደሚቻል፤

2. ከExcel እና ከStata እንዴት ዳታና ወደ SPSS ማምጣት እንደሚቻል፤

3. ከSPSS ወደ Excel እና Stata ዳታን ማዛወር/ Export እንደሚቻል፤

ጠቃሚ ቪዲዮ ጭኛለሁ! እስከመጨረሻው በመመልከት ጥናቶን በቀላል የመስሪያ ግንዛቤ ያግኙ!
https://www.youtube.com/watch?v=IXTlP1SRIvQ
ናይጄሪያ የባለ 200,500 እና 1,000 የገንዘብ ኖቷን/ናይራ ልትለውጥ ነው። ምክንያቱ 85% የሚሆነው ብሯ (ከጠቅላላው ካላት 3.23 ትሪሊዮን ናይራ መካከል 2.73 ትሪሊዮን  ናይራ)ከባንክ ስርዓት ውጪ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ በመታወቁ ነው!


ናይጄሪያ ላለፉት 20 ዓመታት ተመሳሳይ የገንዘብ ኖት ነው የምትጠቀመው። ትልልቅ መጠን ያላቸው የብር ኖቶች በሰዎች እጅ በጣም ተፈላጊ እና ለስወራ ስለሚቀሉ ተመራጭ ናቸው! ለዚህም ሲባል ሀገራት ባለ ትልቅ ኖት ብር ለማሳተም ፍላጎት አያሳዩም!


በኢትዮጵያ ብር ሲለወጥ አንዱ ምክንያት ከ113ቢሊየን ብር በላይ ከባንክ ስርዓት ውጪ በመኖሩ ነበር! አሁን ላይ ብር ከተለወጠ ረጅም ጊዜ ባይሆንም ጥሬ ገንዘብ የሚወደው ገበያ ምን ያህሉን ብር ከባንክ ያስወጣው ይመስላችኋል?


ሀገራት ተመሳሳይ የገንዘብ ኖቶችን ሳይለውጡ ከ10 ዓመት በላይ እንዳይቆዩ ይመከራል።
የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ላለፉት ሁለት ዓመታት ለሶስተኛ ዙር ጦርነት ውስጥ ነው፡፡ የጦርነቱ ባህሪ በአንድ ሀገር ውስጥ ከመከናወኑ በተጨማሪ ሰፊ ቦታን የሸፈነ ነው፡፡ ሰፊ ቦታን የሸፈነ ማለት ብዙ ሞት፤ ብዙ መፈናቀል፤ ብዙ መሰረተ ልማት መውደም፤ ብዙ ወጪ፤ ብዙ እዳ፤ ብዙ ጫና ያለበት ነው ማለት ነው፡፡

በየትም ሀገር ጦርነት ለኢኮኖሚ ጫናው ከባድ ነው፡፡ በተለይ ለእንደኛ ዓይነቱ ድሃ ሃገር ጫናው ከሃገር ውስጥ ወደ ውጪም የሚዘልቅ ነው፡፡ ለዚህ ማሳያ ከአግዋ ከመሰረዝ እስከ የውጪ እርዳታ እና ብድር መቀነስ እና ዲፕሎማሲያዊ ጫናን ጨምሯል፡፡

ጦርነት በቀጥታ ከሚታዩ የወጪ መጠን ብዛት እና የመሰረተ ልማት ውድመት በተጨማሪ የዜጎች በኢኮኖሚው ላይ ያላቸው መተማመን/Public Confidence ይሸረሽራል፡፡ ምክንያቱም ጦርነት በረዘመ ቁጥር ብርም ዶላርም መብላቱ ስለማይቀር በማዕከላዊ ባንክ የሚኖርን የውጪ ምንዛሬ መንካቱ ስለማይቀር የጥቁር ገበያው ከፍተኛ ሸማቾች እንዲኖሩት ያደርጋል፡፡ የዜጎች መተማመን መቀነስ ኢኮኖሚውን ከቤተሰብ እስከ ጠቅላላ ኢኮኖሚ ድረስ ተጽኖ እንዲፈጠርበት ያደርጋል፡፡


#ለምሳሌ፡- የኢኮኖሚክ ትሬዲንግ መረጃ ብንመለከት ላለፉት አራት ወራት የዋጋ ንረቱ በሰኔ ወር 38.1%፤ በሃምሌ ወር 35.5%፤ በነሃሴ ወር 32.5%፤ በመስከረም/ጥቅምት ወር ወደ 30.7% ከመቶ ዝቅ ብሏል (ከአፍሪካ ሃገራት ኢትዮጲያ ዝምባብዌ፤ ሱዳን እና ጋናን በመከተል አራተኛዋ ባለከፍተኛ የዋጋ ንረት ሀገር ነች)! ለማነጻጸር ያህል የዓለም የገንዘብ ድርጅት ትንበያ የሚያሳየው ኢትዮጲያ ውስጥ ጠቅላላ የዓመቱ የዋጋ ንረት በቀጣይ ዓመት ወደ 28.6% ዝቅ ሊል ይችላል የሚል ትንበያ ሰጥቷል (የሰላም ስምምነቱን ሳያውቅ በፊት የሰጠው ትንበያ ነው ደምሩ ቀንሱበት!)፡፡

ስለዚህ በአንጻራዊነት በሂደት እየወረደ ያለ የዋጋ ንረት ባለበት የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ውስጥ የጥቁር ገበያ የውጪ ምንዛሬ ፍላጎት እና የቋሚ ቁሶች (መሬት እና ቤት) ግዢ ፍላጎት የሚንረው ዜጎች የገንዘብን የመግዛት አቅም በቀጣይ ይቀዛቀዛል የሚለው ግምታቸው ጠንካራ በመሆኑ ብራቸውን ወደ ንብረት ለማዞር ከመፈለግ ስጋት ጋር የተገናኘ ነው (ስጋትን ከሚፈጥረው መሰረታዊ ምክንያት አንዱ ጦርነት ነው)፡፡

የውጪ ምንዛሬ አጠቃቀም መመሪያ እና የውጪ ምንዛሬ ጥያቄ ላልተወሰነ ጊዜ በተወሰኑ ቁሶች ላይ ክልከላ መደረግ (የዓለም የገንዘብ ድርጅት በዚህ ወቅት የኢትዮጲያ የውጪ ምንዛሬ ክምችት ለ21 ቀን የሚያሸምት ነው የሚለው ሪፖርት) የሚያሳዩት የውጪ ምንዛሬ ወጪ ሰፊ እንደነበር እና የውጪ ምንዛሬ አቅርቦት መሳሳት ምክንያት መካከል ቀጥታ ጦርነት እና ጦርነቱን ምክንያት በማድረግ ያሉ ዓለም አቀፍ ጫናዎች የታከሉበት መሆኑ አይቀርም፡፡

በሀገራችን ያለው ጦርነት ባህሪ ለየት ያለ ኢኮኖሚዊ ተጽኖ ያለበት ነው! አንዴት? ለጦርነት የሚሆነው ወጪም ሆነ በጦርነት የወደሙትን መሰረተ ልማቶች የመገንባት ወጪም ከአንድ የኢኮኖሚ ቋት ላይ መሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ ኢኮኖሚው ሲዋጋም ያወደመውን መልሶ ሲገነባም ባለ ብዙ ወጪ መሆኑ አይቀርም፡፡

ጦርነቱ የምርት ሁኔታን መጉዳቱ፤ አምራች ክፍሉን ለሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት መዳረጉ፤ የቱሪዝም ሴክተሩን ማዳከሙ፤ የማህበራዊ እና የገንዘብ እንቅስቃሴን መቀነሱ (በመብራት፤ በቴሌኮም፤ በመንገድ፤ ወዘተ ሊጠቀስ ይችላል)፤ መሰረተ ልማቶችን ማውደሙ፤ የመንግስት እና የማህበረሰብ ወጪን ምርታም ላልሆነ ሴክተር/ጦርነት ማስወጣቱ፤ ወዘተ የታወቀ ነው፡፡

ስለዚህ በዚህ ወቅት በመርህ ደረጃ ሰላም ለማውረድ የተደረገው ስምምነት በራሱ ሊኖረው የሚችለው እድል ምንድን ነው? እንዲሁም የሰላም ስምምነቱን በአግባቡ ወደ መሬት በማውረድ ሲተገበር በኢኮኖሚው ላይ ሊኖረው የሚችለው እድል ምንድን ነው?

በመጀመሪያ ጦርነት አውዳሚ ከሆነ ሰላም መጥፎ ሊሆን አይችልም! ስለዚህ ሰላም ለማውረድ የተጀመረ የመጀመሪያ ስምምነት በጣም ጥሩ ነው! እኔ የሰላም ስምምነት መደረጉ ብቻ በመጀመሪያው ደረጃ ለኢኮኖሚው የሚከተሉት ዋና ዋና ጠቀሜታዎች ሊኖሩት እንደሚችሉ ይሰማኛል፡፡

1. በተወሰነ መልኩ በቀጥታ ለጦርነት የሚደረጉ ወጪዎች እንዲቀንሱ ሊያግዝ ይችላል፡፡ እንዲሁም በቀጣይ የሚጠበቀው የሰብዓዊ እና የመልሶ ግንባታ ወጪዎች ማደጋቸው ባይቀርም የረጅም ጊዜ ውጤቶችን መሰረት በማድረግ የማህበረሰብ ተሳትፎ እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ትብብርን መሰረት በማድረግ ወደ ተረጋጋ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ክልሎችን (በዋናነት ትግራይ፤ አፋር እና አማራ) ወደ ተሻለ ሁኔታ ለመመለስ እድል ሊሰጥ ይችላል፡፡

2. የማህበረሰብ መተማመን/Public Confidence እንዲሻሻል ሊያደርግ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ጦርነት የመጪው ጊዚያት ላይ ያለን መተማመን ካጠፋ፡ የሰላም አዝማሚያ ደግሞ ሰዎች በመጪው ጊዜ ላይ የሚኖራቸው መተማመን እንዲጠናከር ያደርጋል (የስልክ፤ የመብራት እና የባንክ አገልግሎት መጀመር ብቻውን ለዜጎች ብዙ ማለት ነው!) የማምረት እና የመሸመት (ማከማቸትን ጨምሮ) ውሳኔ ከመጪው ጊዜ ሀኔታ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው! ስለዚህ ሰላም ይወርዳል የሚለው ስሜት ዜጎች የተረጋጉ ጊዜዎች እና ገበያዎች ሊኖሩ ይችላሉ በሚል ትንበያ በተወሰነ መልኩ የተረጋጋ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ሊያደርግ ይችላል፡፡

3. የውጪ ሀገራት እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ጫና በተወሰነ መልኩ ሊላላ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ጦርነቱን ተከትሎ የውጪ ሃገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ኢኮኖሚያዊ ጫና ቀላል አልነበረም! ስለዚህ የሰላም አዝማሚያን ተከትሎ የኢኮኖሚ ጫና መቀነስ (ብድር እና እርዳታን ጨምሮ) እንዲሁም የሰብዓዊ ድጋፍ መጨመር ሊኖር ስለሚችል የተሻለ የውጪ ንግድ እና የውጪ ምንዛሬ ምንጮችን ለመፍጠር ያግዛል ብዬ አስባለሁ፡፡

በቀጣይ ሁኔታዎችን በአንጻራዊነት ወደ ተረጋጋ ሁኔታ ማምጣት ከተቻለ የግብርና፤ የኢንዱስትሪ፤ የቱሪዝም ሴክተሮች መነቃቃት፤ የሰዎች እንቅስቃሴ ከገደብ መውጣት፤ የገቢ መጠን መሻሻል፤ የስራ እድል መነቃቃት፤ የልማት ትኩረት መሻሻል፤ ወዘተ ሊኖር መቻሉ አይቀርም! ነገር ግን ይህ ሁሉ የሚኖረው አብዛኛውን ያስማማ እና ዘላቂነት ያለው ሰላም የማስፈን ፍላጎት እና ተግባር ሲኖር ነው፡፡


https://youtu.be/TgB7brBVrV4
ዛሬ ሽንኩርት ለመግዛት ትልቅ አትክልት ቤት ቆሜ ስመለከት 2 አይነት ሽንኩርት ተቀምጧል ዋጋቸው በኪሎ 25ብር እና 40ብር ነው።

የሁለቱን ሽንኩርት ልዩነት ንገረኝ አልኩት! "ብዙም ልዩነት የላቸውም" አለኝ። ነገር ግን የተወሰኑ ሰዎች ከተለጠፈው ዋጋ አንፃር ከ40 ብሩ አድርግልኝ እያሉ ሲወስዱ አየሁ።

ለምን የ15 ብር ልዩነት ያለውን ተመሳሳይ ምርት በ25ብር መውሰድ ትታችሁ በ40ብር ትገዛላችሁ ስላቸው! "መጠኑ ትንሽ ተለቅ ስለሚል እና ዋጋው ጥራቱን ያሳያል ብለን ነው!" የሚል አይነት መልስ ሰጡኝ።

ሻጩን ለምን የሁለቱ ሽንኩርቶች ዋጋ ተለያየ? ስለው "ባለ 40ብሩ ሽንኩርት ከሩቅ ቦታ ስለሚመጣ ነው! የተወደደው" አለኝ።

ዋጋ የሚወሰነው በምርት ወቅት የነበረው የግብዓት ወጪ መጠን እና ወደ ገበያ የሚመጣበት የትራንስፖርት ወጪ እንዲሁም የሚሸጥበት ቦታ ሁኔታ (ውድ የኪራይ ቦታ ከሆነ ዋጋ ላይ ሊደመር ይችላል!) ተደማምረው ነው።

በተወሰነ መልኩ ሁለቱ ሽንኩርቶች ለመመረት ያለባቸው የግብዓት ወጪ ተቀራራቢ ነው የሚሆነው! ስለዚህ የምርቱ የትራንስፖርት ወጪ ነው ዋጋው ላይ ልዩነት የፈጠረው።

በሀገራችን ውድ ነገር ጥሩ ነው የሚል ልምድ አለ! ነገር ግን ተመሳሳይ ነገር ለመግዛት የዋጋ ልዩነት ሲገጥማችሁ የተፈጠረው የዋጋ ልዩነት ምክንያታዊ መሆኑን ማረጋገጥ ግድ ነው።

ተመሳሳይ ምርት ከሩቅ ስለመጣ ውድ ሆነ ማለት በሸማች አስተሳሰብ በዋጋ ውድ የሆነው የተሻለ ቢሆን ነው በሚል ነባር የሸመታ ልምድ መሸመት እንደመሸወድ ነው የሚቆጠረው።

እኔ ለሸመታው ምክንያታዊ ለመሆን ሻጩንም ሲሸምቱ የነበሩ ሰዎችን ጠየኩ በቂ መረጃ የሌለው ሸማች ሊያደርግ እንደሚችለው ሸማች አወዳደርኩ እና ባለ 25ብሩ ሽንኩርት ገዛሁ።

#ለምሳሌ፦ በተለያዩ ሽንኩርቶች መካከል የአይነት መሰረታዊ ልዩነት ሊኖር ይችላል! የሚጣፍጥ፤ ቶሎ የሚበስል፤ ሳይበላሽ የሚቆይ፤ ወዘተ ነገር ግን እኔ በተገኘሁበት የነበረው ምርት ይህ ልዩነት እንዳለው ሻጭም ሸማቾችም አላወቁም ግን ውዱን መግዛት መርጠዋል።

ዋጋ ብቻውን የጥራት ማሳያ አይደለም! ለምትከፍሉት የዋጋ ልዩነት ተጨማሪ ምክንያት መፈለግ መለመድ አለበት።
ዳታ በቀላሉ በStata እንዴት ይተነተናል ?/ How to interpret descriptive data results in Stata?

ከዚህ በፊት ዳታ ወደ SPSS እንዴት ማስገባት እንደሚቻል፤ እንዴት መተንተን እንደሚቻል እና እንዴት ቻርት ማውጣት እንደሚቻል አቅርቤላችሁ የነበረ ቢሆንም ዛሬ በቀላሉ በStata እንዴት Descriptive ውጤት እና ግራፍ ማውጣት እንደሚቻል ይህንን https://youtu.be/1irwoamoZKc አጭር ቪዲዮ ሰርቻለሁ፡፡

የዚህ ቪዲዮ ዓላማ ሰዎች እንደመነሻ እንዲወስዱት እና ተጨማሪ ሌሎች መጽሃፍትን እና ቪዲዮችን በመመልከት ጥናታቸውን በቀላሉ በአቅማቸው ልክ መስራት እንደሚችሉ ለማስረዳት ያህል ነው፡፡ ከዚህ በፊት በSPSS እንዴት ዳታ ማስገባት እና መተንተን እንደሚቻል የሰራሁትን ቪዲዮ ለምትፈልጉ ከታች ያለው ሊንክ ተጠቀሙ፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=wV4_BIKl0cA
https://www.youtube.com/watch?v=IXTlP1SRIvQ
https://www.youtube.com/watch?v=X5mwTniLNN8
በኢኮኖሚክስ #ፍፁም ትክክል የሚባል ሃሳብ የለም!

#ቀላል_ምሳሌ፦ የዋጋ ንረት የመፍትሄ ሃሳቦች የተለያዩ ናቸው! ለአንዱ ሀገር የሰራ የመፍትሄ ሃሳብ ለሌላ ሀገር የዋጋ ንረት አባባሽ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ተመሳሳይ የዋጋ ንረት የመነሻ ምክንያት (ከፍላጎት መጨመር/Demand Pull አልያም የማምረት ወጪ መጨመር/Cost Push) ቢፈጠር እና የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እውቀት ያላቸው ሰዎች የሚከተለውን ምክር ቢለግሱ.......

#የምጣኔ_ሃብት_ባለሙያ1፦ "በገበያ የገንዘብ ስርጭት እንዲጨምር ማድረግ #ከፍላጎት በሚነሳ ምክንያት አንፃር የዋጋ ንረትን ያባባብሳል! ስለዚህ የገንዘብ አቅርቦትን በመቀነስ የዋጋ ንረቱን መቀነስ ይቻላል" የሚል ምክረ ሃሳብ ቢያቀርብ።

#የምጣኔ_ሃብት_ባለሙያ2፦ በተቃራኒው "ለአምራች ሃይሉ የገንዘብ አቅርቦትን በማሳደግ #የማምረት አቅም/የግብዓት አቅርቦት እንዲሻሻል በማድረግ አቅርቦትን በመጨመር የዋጋ ንረት እንዲቀንስ ማድረግ ይቻላል" የሚል ምክረ ሃሳብ ቢያቀርብ።

የሁለቱም ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ በመርህ ደረጃ ስህተት የለበትም! ማንኛቸውም ባለሙያ የሰጠሁት የመፍትሔ ሃሳብ ፍፁም ትክክለኛውን ነው በሚል መኩራራትም አይችልም! የመፍትሔ ሃሳቦች ሲተገበሩ የመንሻፈፍ አጋጣሚዎቻቸው ብዙ ናቸው። ለዚህ ነው ታዋቂ የኢኮኖሚክስ Assumption መላምቶች (Other Things Remaining Constant) በሚል የሚጀምሩት።

#ለምሳሌ፦ በ1930 በአሜሪካ የተከሰተው ኢኮኖሚያዊ ቀውስ (Great Depression) በዋናነት መነሻው ምክንያት የአምራች ክፍሉ ያመረተውን ከፍተኛ መጠን ምርት መግዛት የሚገባው የሸማች ክፍሉ በበቂ ሁኔታ መሸመት ባለመቻሉ አምራቾች የተመረቱ ምርቶች ገበያ ካጡ ተጨማሪ ምርት ከማምረት በመቆጠብ ሰራተኛ በማሰናበታቸው በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛው የስራ አጥነት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል።

#ለምሳሌ፦ በአሜሪካ በ1929 ስራ አጥነቱ 3.2% ነበር፤ በዓመቱ  6 ሚሊየን አሜሪካዊያን ስራ በማጣታቸው በ1930 የስራ አጥነቱ ቁጥር 19.4% ደረሰ በ1933 ስራ አጥነቱ 25% አልፎ ነበር፡፡

ይህ ችግር እንዲቀረፍ ብዙ ኢኮኖሚስቶች ተሞክረው በመጨረሻ እንግሊዛዊው ኢኮኖሚስት ጆን ሜሬድ ኬነስ "የገንዘብ አቅርቦትን ባለመቀነስ የሸማች ክፍሉን አቅም በማሳደግ ችግሩን መቅረፍ ይቻላል" የሚለው ሃሳብ በLogic አደገኛ በመሆኑ ከብዙ ክርክር በኋላ "እስቲ ይሞከር!" በሚል ነበር የተተገበረው! ነገር ግን ችግሩ ለመቀረፍ 10ዓመት ቢፈጅም ምክረ ሃሳቡ መፍትሄ መሆን በመቻሉ መማሪያ ሆኖ Keynesian Theory በሚል ተመዝግቧል።

በወቅቱ ከኬይነስ በፊት ከቀረቡ የመፍትሄ ሃሳቦች መካከል "የሰራተኛውን ክፍያን በመቀነስ እና የአምራች ክፍሉ የሚከፍለውን የወለድ መጠን በመቀነስ ወጪን በመቆጠብ ስራ አጥነቱ እናዲቃለል ማድረግ ይቻላል" የሚለው ሲሆን ኬይነስ በበኩሉ "የሰራተኛውን ክፍያ ከመቀነሰ ይልቅ የሰራተኛው ክፍል የመሸመት አቅም እንዲጨምር በማድረግ ሸማች እንዲሆን ማድረግ ይቻላል"፤ ይህንን ተከትሎ የአምራች ክፍሉ የማምረት መጠን እየጨመረ ይሄዳል የሚል ነበር፡፡ በተግባርም አስተሳሰቡ ውጤት አምጥቷል፡፡

በሀገራችን ኢኮኖሚክስን የተማሩ ሰዎች በአብዛኛው ለጊዚያዊ ችግሮች የመፍትሄ ሃሳብ እና የኢኮኖሚያዊ ችግሮች መነሻ ምክንያትን ሲያስቀምጡ ሃሳቦቹ የተለያዩ ናቸው። ይህ ማለት ባለሙያዎቹ ሙሉ ለሙሉ ስህተቶች ናቸው እና ትክክለኛው መፍትሄ እና ምክንያት የቱ እንደሆነ አልታወቀም አያስብልም።

አስር የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ኢትዮጵያ ለምን የከፋ ድህነት ውስጥ ለመኖር ተገደደች? ተብለው ቢጠየቁ። ስምንት አልያም አስር የተለያዩ ምክንያቶችን ሊያቀርቡ ይችላሉ። ስለዚህ ኢትዮጵያ ከድህነት እንድትወጣ ምን ይደረግ? ቢባሉም ስምንት አልያም አስር የተለያዩ ከችግር መውጫ መንገዶችን በምክንያትነት ሊያቀርቡ ይችላሉ።

ለዚህ አይነቱ ችግር የባለሙያዎች ስብስብ በመፍጠር የሃሳቦችን እድል እና ስጋት በመወያየት ወደ ዋና መሰረታዊ (Significant) ነጥብ እንዲደርሱ ማድረግ ይቻላል! ደግሞም መንግስታት ይህንን ዘዴ ይጠቀማሉ።

#ለምሳሌ፦ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ቤት ውስጥ ያሉ ኢኮኖሚስቶች የጥሬ ገንዘብ ገደብ ይቀመጥ! የሚለው ውሳኔ ላይ በተናጥል የተለያየ ምልከታ እንደሚኖራቸው እገምታለሁ። ነገር ግን እንደማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳዳሪነታቸው በጋራ ከየልዩነታቸው ወደ ተመሳሳይ ውሳኔ እንደደረሱ መገመት ይቻላል። በተመሳሳይ የገንዘብ ሚኒስትር፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ አማካሪ ቡድኑ፤ ወዘተ ውስጥ በምክንያት እና መፍትሄ ላይ የሚኖረው ሁኔታ በተናጥል እና በቡድን ሃሳቦቻቸው የተለያዩ ነው የሚሆኑት።

በሀገራችን ብዙ ሰዎች ኢኮኖሚክስን በብዙ ጥልቀት በትምህርት እና በስራ ልምድ እንደሚያውቁት ግልፅ ነው! ስለዚህ የሚሰማቸውን ስሜት ለማጋራት ግዴታ ጥቂት ሰዎች ብቻ በየቀኑ የሚያቀርቡትን ሚዲያዎች መፈለግ አይጠበቅባቸውም፤ ሃሳቦቻቸው ለፖሊሲ አውጪዎች እንዲደርስ መፈለግ የለባቸውም፤ ሃሳቦች ትክክል እና ስህተት መሆናቸውን የሚመዝን አካል ስለመኖሩ ማሰብ የለባቸውም፤ ወዘተ። ስለዚህ የተማሩትን እና የሚያውቁትን ብቻ ያንጸባርቃሉ፡፡

#ለምሳሌ፦ በሀገራችንን የምጣኔ ሃብት ዙሪያ አስተያየት ለመስጠት በተለያዩ ሚዲያዎች የሚቀርቡት እንዲሁም ሚዲያዎች የሚያቀርቧቸው ሰዎች ጥቂት እና ተመሳሳይ ናቸው (ከጥቂት ጊዚያት ወዲህ እኔንም ይጨምራል!) ይህ ሁኔታ የሃሳብ ተዋፅኦን ይቀንሳል!

ኢኮኖሚክስን የተማረ ሰው ልኩን ብቻ ሳይሆን ልክ ነው ብሎ የሚያምንበትን እና የሚያውቀውን ሃሳብ ነው ማጋራት ያለበት! (ለብዙ ጉዳዬች ፍፁም ልክ የሚል ሳይሆን የመሳካት እድላቸው ከፍ ያለ ሃሳቦች ናቸው የኢኮኖሚክስ አስተምሮትን የሞሉት)።


#ለምሳሌ፦ ከውጪ ለሚገቡ ውስን ምርቶች የLC ክልከላ መደረግ ልክ የሚሆነውም ልክ የማይሆነውም በሚቀርቡት አመክንዮ ብዛት እና ጥንካሬ እንጂ በደፈናው መከልከሉ ፍፁም ትክክል ወይም አለመከልከል ለቀጣይ ኢኮኖሚው ፍፁም ወሳኝ ነው የሚባል አይሆንም። ምክንያቱም ኢኮኖሚክስ ያላለቀ እና ከተለዋዋጭ ነባሪያዊ ሁኔታዎች ጋር ጥገኛ ነው።

ስለዚህ ሀገር ኢኮኖሚክስን ያስተማረቻቸውን እንዲሁም በራሳቸው ያዳበሩትን እውቀት ባገኙት አጋጣሚ (በማህበራዊ ሚዲያ፤ በህትመት ሚዲያ፤ በራዲዮ፤ በቲቪ፤ ወዘተ) ማጋራት ተገቢ ነው። ኢኮኖሚያዊ መረጃ እና ሃሳብ ለመንግስት፤ ለሚዲያዎች፤ ለተማሪዎች፤ ለመደበኛው ሰው፤ ወዘተ በጣም አስፈላጊ ነው።


YouTube፦ https://youtube.com/channel/UCzc8ISpZJ6RskJmd_DEx7WQ
Channel photo updated
የኢኮኖሚክስ ትምህርት በሁለት ይከፈላል። Static Economics (የማይለዋወጥ ኦኮኖሚ) እና Dynamic Economics (ተለዋዋጭ ወይም ተራማጅ ኢኮኖሚክስ) በመባል ይታወቃል።

ታድያ ብዙ ጊዜ በአንድ ኢኮኖሚያዊ አጀንዳ ላይ ፍፁም የሆነ መደምደሚያ ላይ መድረስ የማንችለው እነዚህን ሁለት ኢኮኖሚክስ ክፍሎች በቅጡ ስለማናጤንና አንዳንዴም ከግምት ውስጥ ሳናስገባ ስንቀር ነው።

የሁለቱን የኢኮኖሚክስ ፅንሰ ሃሳቦች በአጭሩ ለመረዳት ያክል……

በማንኛውም ጊዜ የሚፈጠር ኢኮኖሚያዊ ክስተት በአንድና ከዛ በላይ በሆኑ ተፅዕኖ ፈጣሪ ምክንያቶች ሊፈጠር ይችላል። ለምሳሌ የዋጋ ግሽበት/ መናር ቢፈጠር ምክንያቶቹ አንድ ወይም ከዛ በላይ ሊሆኑ ይችላሉ። የዋጋ መናሩን ያመጡት የሸማቹ አቅም ወይም ቁጥር መጨመር፣ የአቅርቦት ማነስ፣ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት መጨመር እና ሌሎች ፖለቲካዊና ድንገቴ ክስተቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ታዲያ ነጥቡ እዚህ ላይ ነው። የዋጋ መናሩን ካመጡት ውስጥ አንዱን ወይም የተወሰኑትን ነጥሎ የሚያጠናው የኢኮኖሚክስ ዘርፍ (Static Economics) ይባላል። ሌሎች ተፅዕኖ ፈጣሪ ጉዳዮችን (Economic Factors) "Other Things Remaining Constant" በሚል ያልፋቸዋል።

ሌላኛው ደግሞ ሁሉንም ተፅዕኖ ፈጣሪ ክስተቶች ፈልፍሎ አውጥቶ የሚያጠናው ዘርፍ ደግሞ Dynamic Economics ይባላል። ስለዚህ የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች የሀሳብ ልዩነትም ከዚህ አንፃር የሚከሰት ነው። እናም መፍትሄው አንደኛ በሙያው ላይ ጥርስ የነቀሉ ባለሙያዎችን አማካሪም ተንታኝም እንዲሆኑ ማሳተፍ ሲሆን። ሁለተኛው ደግሞ ብዙ አይነት አመለካከት ያላቸውን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ወደውይይትና አለፍ ሲልም ወደ ክርክር ማምጣት ነው። ይህ በስተመጨረሻ የተሻለ መፍትሄ የማምጣት እድሉ የሰፋ ነው (Abu Fawzan) ።
መሰረታዊ የሆኑ 5 የኢኮኖሚክስ ትምህርት መነሻ ሃሳቦች!

የኢኮኖሚክስ ትምህርት መሰረት ምርጫን የመወሰን ጉዳይ ነው! ስለዚህ ኢኮኖሚክስን በተረዳችሁ ቁጥር ለምታደርጉት ማንኛውም ውሳኔ ምክንያታዊነት እድትፈጥሩ ለማድረግ ነው ትምህርቱ የተቋቋመው፡፡

#እጥረት፡- አብዛኞቹ በዙሪያችን ያሉ ሃብቶች እና የሰዎች ፍላጎት መካከል ከፍተኛ አለመጣጣም አለ፡፡ ለምን? ምክንያቱም ሃብቶች (የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ) ውስን በመሆናቸው እና የሰዎች ፍላጎት በሂደት እያደገ በመሆኑ ያልተገደበውን የሰዎች ፍላጎት ማሟላት የሚችል ሃብት ሊኖር አለመቻሉ ይታወቃል፡፡

#ለምሳሌ፡- በአዲስ አበባ ተሰርተው በሚቀርቡ ቤቶች እና ሰዎች ለቤቶች ያላቸው ፍላጎት መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ! ስለዚህ ኢኮኖሚክስ በተለያዩ ዘዴዎች ይህንን የሰዎች የቤት ፍላጎት እንዴት ማሟላት አንደሚቻል የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባል (በግል ሴክተሩ መገንባት፤ መሬት ከሊዝ ነጻ ማቅረብ፤ የማህበራ የቤት ስርዓት ማዘጋጀት፤ ነባር አነስተኛ የመንግስት ቤቶችን በርካታ ሰው በሚይዙ ህንጻዎች መለወጥ፤ የመንግስት እና የግል ተቋማት ትብብር ማሳደግ፤ በቤት ልማት የውጪ ባለሃብት መጋበዝ፤ በአነስተኛ ወጪ የቤት አሰራር ቴክኖሎጂ መፍጠር፤ የቤት አልሚዎችን መቆጣጠር፤ የመሬትን ባለቤትነት ፖሊሲ ማሻሻል፤ ወዘተ)፡፡

በሀገራችንም የሃይል፤ የመንገድ፤ የውጪ ምንዛሬ፤ የትራንስፖርት፤ የነዳጅ፤ የበጀት፤ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ፤ ቤተመጽሃፍት፤ የመስኖ፤ የአፈር ማዳበሪያ፤ የደህንነት ዋስትና፤ ወዘተ የእጥረት ማሳያ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ኢኮኖሚክሰ ትምህርትን የፈጠረው የአቅርቦት እጥረትን ከአዳጊው ፍላጎት ጋር ስለማጣጣም ሲባል ነው፡፡

#አቅርቦት እና #ፍላጎት፡- እጥረት በባህሪው ሰዎች ተጨማሪ እንዲያመርቱ፤ እንዲሸጡ እና እንዲገዙ ወደሚፈልጉበት ስርዓት ይከታል፡፡ ስለዚህ የሰዎች ፍላጎት (የቁሳቁስ፤ የአገልግሎት እና የውጪ ምንዛሬ) በገበያው ካለው አቅርቦት (የቁሳቁስ፤ የአገልግሎት እና የውጪ ምንዛሬ) ከበለጠ እጥረት አለ ማለት ነው! ኢኮኖሚክስ ይህ ሁኔታ የሚስተካከልበትን ዘዴ ይፈልጋል፡፡ አቅርቦቶችን ከማሳደግ እስከ ፍላጎቶችን መገደብ ድረስ በአቅርቦት እና ፍላጎት መካከል የሚኖርን ክፍተት ለመሙላት የሚደረጉ የኢኮኖሚክስ መላዎች ናቸው፡፡

#ፉክክር፡- የእጥረት መከሰት በገበያ የሚኖርን ፉክክር ያሳድጋል፡፡ ለምሳሌ፡- የውጪ ምንዛሬ እጥረት ሰዎችን በጥቁር ገበያ ያላቸውን የመሸመት ፍላጎት በማሳደጉ ወደ ፉክክር ደረጃ ከቶታል፡፡ በገበያው የሚፈጠርን ጤነኛም ሆነ ጤነኛ ያልሆነ ፉክክር ስርዓት የማስያዝ ሃላፊነትን ኢኮኖሚክስ ይወጣል! እንዴት? የውጪ ምንዛሬ ፉክክሩ የመነጨው ከእጥረት ከሆነ የውጪ ምንዛሬ የሚገኝባቸው አማራጮች፤ የውጪ ምንዛሬ አጠቃቀም እና የውጪ ምንዛሬ የሚያስወጡ ምርቶች የመተካት አማራጭ ለገበያው ይሰጣል እንደማለት ነው፡፡

#ዋጋ_ንረት፡- በኢኮኖሚ ውስጥ በተከታታይ የቁሳቁስ እና የአገልግሎት ዋጋ እየጨመረ መምጣት የአንድ ኢኮኖሚ አደጋ ሲሆን ይህንን ሁኔታ ለማስተካካል ኢኮኖሚክስ የገንዘብ አቅርቦት እና ስርጭት ቁጥጥር፤ የማምረቻ ግብዓት አቅርቦት፤ የምርት እና የምርታማነት መጠን፤ የበጀት አጠቃቀም፤ የፕሮጀክቶች አይነት፤ የገበያ ቁጥጥር፤ የኮታ ስርጭት፤ የቀረጥ መጠን፤ የወለድ መጠን፤ የብድር አቅርቦት፤ ወዘተ እየተለዋወጡ እንዲተገበሩ የሚያደርገው ኢኮኖሚክስ ነው፡፡

#የንግድ_ጉድለት፡- አንድ ሃገር ከውጪ ለምታስገባቸው ምርቶች እና አገልግሎቶች የምታወጣው ወጪ ወደ ውጪ ምርት እና አገልግሎት ልካ ከምታገኘው ገቢ የበለጠ ሲሆን ኢኮኖሚክሱ ለውጪ ንግድ የሚቀርቡ ምርቶች ምርታማነት እና አይነት መጨመር፤ የገበያ አማራጭ መለየት፤ የሃገር ውስጥ አምራቾችን የማሳደግ፤ መሰረታዊ የማይባሉ ምርቶች ማገድ፤ የውጪ ምንዛሬ ምንጭ ማስፋት፤ ወዘተ ሊያደርግ ይችላል፡፡

አብዛኞቹ የኢኮኖሚክስ አስተምሮቶች ከላይ ከተጠቀሱ መሰረታዊ መነሻዎች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- ስራ አጥነት የኢኮኖሚው ችግር ቢሆንም በምርት ስርዓት አቅርቦት ሲያድግ፤ የዋጋ ንረት ሲረጋጋ፤ የውጪ ንግድ ጤነኛ ሲሆን፤ ወዘተ መልስ እያገኘ የሚሄድ ነው፡፡ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱ ስርዓቶች በሙሉ ብቸኛ ምርጫ ስለሌላቸው ጠንካራ የሚባለውን አማራጭ ለመምረጥ እንዲረዳ የተለያዩ የኢኮኖሚክስ አስተምሮቶች/Theories ይቀረጻሉ፡፡

መቀሌ እያለን የመጀመሪያ ድግሪ ስንማር የኢኮኖሚክስ ትምህርት ብዙ በመሆኑ የዕለት ውሏችን በአብዛኛው ተመሳሳይ ነበር! መብላት፤ ማጥናት እና ከእኩለ ለሊት በኋላ መተኛት! ነገር ግን ከምንማራቸው እና ከምናነባቸው በላይ ብዙ ያልሰማናቸው የኢኮኖሚክስ አስተምሮቶች እንዳሉ ይሰማን ነበር፡፡ አሁንም በተቻለ መጠን የተወሰኑ የኢኮኖሚክስ አርቲክሎች ማንበብ መለማመድ እና አለመሰልቸት ተገቢ ነው፡፡



Subscribe      
                                                             
🙏🙏🙏🙏

YouTube፦ https://youtube.com/channel/UCzc8ISpZJ6RskJmd_DEx7WQ
ጥሩ እና በተደጋጋሚ ያልተሰራ የጥናት ርዕስ ለማግኘት የብዙ ተመራቂዎች ጭንቀት ነው። ስለዚህ በቀላሉ አዲስ፤ መረጃ ያለው እና አቅምን ያገናዘበ የመመረቂያ የድግሪ እና የማስተርስ ርዕስ ማገኘት እንደሚቻል ይህንን ምክረ ሃሳብ አቅርበናል ተጠቀሙበት።

https://youtu.be/X4jlW1cp6Qo
በተቻላችሁ አቅም ተመሳሳይ የኑሮ እንቅስቃሴ እንዳይኖራችሁ ለማድረግ ሞክሩ!

ከሰኞ እስከ አርብ ተመሳሳይ ስራ፤ ተመሳሳይ ገቢ፤ ተመሳሳይ ማህበራዊ ግንኙነት ከሆነ ያላችሁ እንዲሁም  በተመሳሳይ ቅዳሜ እና እሁዳችሁ ተመሳሳይ የውሎ ዘይቤ ካለው ህይወታችሁ ወጥ/ልዩነት የሌለው ይሆናል።


ወጥ ህይወት ወጥ ለውጥ ነው ያለው፤ ወጥ ስራ ወጥ ገቢ ነው የሚኖረው፤ ወጥ ግንኙነት አዳዲስ ሃሳብ ለማመንጨት የሚቸገር ነው የሚሆነው፤ ወዘተ።


ለብዙ ሰዎች ከሰኞ እስከ አርብ የስራ እና የገቢ ምንጭ ነው! ነገር ግን የተሻለ ኑሮ ለመኖር እና የህይወት ጣዕም ከሚያሳጣው ተገማች እና ወጥ የሆነ ሳምንታዊ እንቅስቃሴ ለመላቀቅ ቅዳሜ እና እሁድን ውጤታማ ለማድረግ መሞከር ተገቢ ነው። ብዙ ነገሮችን ለመለወጥ ቅዳሜ እና እሁድ ነፃነት ይሰጣል።


ቅዳሜ እና እሁድ ወሳኝ ገቢ የሚገኝበት፤ ዋጋው የሚታወቅ ማህበራዊ ግንኙነት የሚደረግበት፤ አዲስ ነገር የሚታወቅበት፤ ጤና የሚጠበቅበት/ስፖርት የሚሰራበት፤ ልጆች የሚታነፁበት፤ ወዘተ መሆን አለበት።


በተለይ በጣም ትርፋማ ያልሆነ ከሰኞ እስከ አርብ ላሳለፈ ሰው ቅዳሜ እና እሁድ ማካካሻ መሆን አለበት (ደሞዜ/ገቢዬ ልፋቴን እና እውቀቴን አይመጥንም የሚሉ ብዙ ናቸው)።


ቅዳሜ እና እሁድ ለሁላችንም የእረፍት ቀን መሆን አለበት ብዬ አላምንም!


የአስቤዛ ወጪ መሸፈን የተቸገረውም፤ የቤት ኪራይ ወጪ የተጫነውም፤ ተጨማሪ ካልሲ ለመግዛት ማጠራቀም ያለበትም፤ የስልክ ካርድ መሙላት ቀላል ለማይሆንለትም፤ ሰራተኛ ሆኖ ከቤተሰብ ጥገኝነት ለመላቀቅ ፈተና የሆነበትም፤ ወዘተ።


ቅዳሜ እና እሁድ ተኝቼ ቴሌቪዥን ማየት ነው ልምዴ ምክንያቱም የእረፍ ቀኔ ነው ቢል ከኑሮ ውድነት የማያድን ባዶ መብት እንዳለው ነው የምቆጥረው።


እና ምን ልስራ? አደለም ቅዳሜ እና እሁድ ከሰኞ እስከ አርብ የምሰራው የለኝም የሚል ምክንያት መደርደር ይቻላል! ነገር ግን ለዚህ ጉዳይ መልስ መስጠት ያለበት ምክንያት ደርዳሪው ነው ብዬ አምናለሁ! እድል፦ የጥረት፤ የመረጃ እና የውሳኔ ውጤት ነው!


የኑኖ ወጪ ነፃነት ለማግኘት የእረፍት ነፃነት በተወሰነ መልኩ መላላት አለበት! ስለዚህ የምትችሉ እና መለወጥ በራሳችሁ ጉልበት፤ ፍላጎት እና ጥረት እንደሚመጣ የምታምኑ ቅዳሜ እና እሁዳችሁን ወደሚታይ ዋጋ ለውጡ! (እኔ በግሌ ቅዳሜ እና እሁድ ከሰኞ እስከ አርብ ከሚኖረኝ በላይ ነው)።


Subscribe      
                                                             
🙏🙏🙏🙏

YouTube፦ https://youtube.com/channel/UCzc8ISpZJ6RskJmd_DEx7WQ
ስንዴን በብዛት ማምረት ማለት #በምግብ እራስን መቻል ማለት ሳይሆን #በስንዴ_ምግብ እራስን መቻል ማለት ብቻ ነው!


የቤተሰቦች ገበታ ዋስትናው ተጠበቀ የሚባለው ጤፍ፤ ስንዴ፤ ዘይት፤ ሽንኩርት፤ ቲማቲም፤ ወዘተ ሲሟላ ነው። በተመሳሳይ እንደሀገር በምግብ እራስን የመቻል ደረጃ ማለት መሰረታዊዎቹን የምግብ ግብዓቶች ለዜጎች ማቅረብ ማለት ነው።


ስለዚህ ስንዴ አንዱ እና ከበጣም አስፈላጊዎቹ የምግብ ግብዓት መካከል እንጂ ብቸኛ አይደለም። በምግብ እራስን ለመቻል ሁሉንም ማምረት ግዴታ አይደለም! ለሀገር ውስጥ ፍጆታ በሚበቃ መጠን በበቂ ሁኔታ ከሌሎች ሀገራት ሸምቶ ማቅረብ የሚችል ኢኮኖሚያዊ አቅም መፍጠርንም ይጨምራል።


ስንዴን በብዛት ማምረት መቻል ትልቁን የቤተሰብ ፍጆታ ዋጋ ማረጋጋት እንዲቻል፤ ለውጪ ንግድ በማቅረብ የውጪ ምንዛሬ ለማግኘት እና የውጪ ሀገር እና ተቋማት ምልከታን ሊያስተካክል ይችላል።


ነገር ግን ስንዴን ለውጪ ንግድ ማቅረብ ቀጥተኛ #በምግብ_እራስን የመቻል ምልክት የሚያስመስሉ ንግግሮች በተደጋጋሚ ይታያል (ባለስልጣናት እና ዘጋቢዎችን ጨምሮ)። በስንዴ ምርት ፍላጎትን ማሟላት ማለት የሌሎች የምግብ አይነት ፍላጎቶችን ማሟላት ማለት አይደለም።


ስለዚህ የስንዴ ውጤታማነት በሌሎች መሰረታዊ የምግብ ምርቶች ላይ መድገም ሲቻል የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ በምግብ እራስን መቻል ላይ ሊደረስ ይችላል።


Subscribe      
                                                             
🙏🙏🙏🙏

YouTube፦ https://youtube.com/channel/UCzc8ISpZJ6RskJmd_DEx7WQ
እሸቱ ብዙ የሚያስተምረን ድንቅ ወጣት ነው! ስራ ፈጣሪ (Content creator)፤ ትጉ (ለ20 ሰዓት ያለማረፍ ሲሰራ አየሁት) እና ቅን ነው። በርታ ወንድሜ!
#ጠቅላይ_ሚኒስትር?፡- በኢትዮጲያ የህዝብ ቁጥሩ ነው? የነፍስ ወከፍ ገቢው ነው? የኢትዮጲያ የመረጃ ስርዓት ነው? ወይስ የአለም ባንክ መረጃ ነው? መታረም ያለበት?


ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጲያ የነፍስ ወከፍ ገቢ 1,212 ዶላር ደርሷል ብለዋል (ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት 126.9 ቢሊየን ዶላር)፡፡ በአለም ባንክ መረጃ የኢትዮጲያ GDP አሁን ላይ 112.2 ቢሊየን ዶላር ደርሷል ብሏል፡፡ ይህንን ሁለት መረጃ ይዘን የሚከተለውን እንጠይቅ…..


የነፍስ ወከፍ ገቢ የሚሰላው GDP ሲካፈል ለጠቅላላ ህዝብ ነው፡፡ ስለዚህ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ስሌት የኢትዮጲያ ህዝብ አሁን ላይ ከ102 ሚሊየን አይበልጥም ምክንያቱም 126.9 ቢሊየን ዶላር GDP ሲካፈል 102 ሚሊየን የኢትዮጲያ ህዝብ የነፍስ ወከፍ ገቢ 1,232 ዶላር ይሆናል (ቁጥሩ ተጠጋግቶ ነው)፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጲያ ጠቅላላ ምርት/GDP ከሰሃራ በታች ሶስተኛው ግዙፉ ነው የሚለውን ሲገልጹ የአለም ባንክ መረጃ ማለትም 111.2 ቢሊየን ዶላር (111,271,112.33) ደርሷል የሚለውን ወስደው ነው የሚሆነው (አለም ባንክ የናይጄርያ 440.7 ቢልዮን ዶላር፤ የደቡብ አፍሪካ 419.9 ቢልዮን ዶላር እንዲሁም የኢትዮጵያ 111.2 ቢልዮን ዶላር ደርሷል ይላል)፡፡


የአለም ባንክ የኢትዮጲያ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከ944 አይበልጥም ይላል! ምን ማለት ነው? ምክንያቱም 111.2 ቢሊየን ዶላር GDP ሲካፈል ለ118 ሚሊየን የኢትዮጲያ ህዝብ የነፍስ ወከፍ ገቢ 942 ዶላር ይሆናል እንደማለት ነው (የህዝብ ቆጠራ ከተደረገ 10ዓመት ስላለፈ የኢትዮጲያ ህዝብ አሁን ላይ 117 ሚሊየን ይደርሳል የሚል የአለም ባንክ ግምት አለ)፡፡


#ለምሳሌ፡- የናይጄሪያ ጠቅላላ ምርት 440.7 ቢልዮን ዶላር እና ለጠቅላላ 211.4 ሚሊየን የናይጄሪያ ህዝብ ሲካፈል የነፍስ ወከፍ ገቢ 2,085 ዶላር ይመጣል፤ በተመሳሳይ የደቡብ አፍሪካ ጠቅላላ ምርት 419.9 ቢልዮን ዶላር እና ለጠቅላላ 60.04 ሚሊየን የደቡብ አፍሪካ ህዝብ ሲካፈል የነፍስ ወከፍ ገቢ 6,993 ዶላር ይመጣል (ጉግል ቢደረግ ይህ ቁጥር መዛነፍ የለውም)፡፡


ታዲያ! በኢትዮጲያ የህዝብ ቁጥሩ ነው? የነፍስ ወከፍ ገቢው ነው? የኢትዮጲያ የመረጃ ስርዓት ነው? ወይስ የአለም ባንክ መረጃ ነው? መታረም ያለበት?

የአለም ባንክን መረጃ https://data.worldbank.org/indicator/NY.GDP.PCAP.CD ማግኘት ይቻላል።