The Ethiopian Economist View
29.2K subscribers
724 photos
4 videos
197 files
1.34K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
ጤነኛ የሚባለው የወጪ ዝርዝር ቀመር (The Golden Rule of Budgeting!)

ሰዎች ከገቢዎቻቸው ላይ የሚያወጡት ወጪ በዘፈቀደ ሳይሆን በስሌት መሆን አለበት! (በ50/30/20 ወይም በ30/30/30/10 ወይም በ80/20 ቀመር መሰረት) ስለሆነም ከወጪያችሁ ለመሰረታዊው (Need) እና ለፍላጎቶቻችሁ (Want) ምን ያህል ድርሻ መስጠት አለባችሁ? እንዲሁም ምን ያህል መቆጠብ መቻል ነው ጤነኛ በሆነው የወጪ ዝርዝር ውስጥ እንዳላችሁ የሚያሳየው?

በአዲስ አበባ በተደረገ የቀደመ ጥናት ሰዎች ከ50/30/20 ወርቃማው የወጪ ዝርዝር ህግ አንጻር ያሉበትን ደረጃ ቪዲዮው https://youtu.be/0oZakptRZ0E ላይ በመመልከት እናንተ ደግሞ ያለባችሁበትን ደረጃ በማስላት ተጠቃሚ ይሁኑ!

Subscribe በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ Share ያድርጉት!
ጤነኛ የሚባለው የወጪ ዝርዝር ቀመር (The Golden Rule of Budgeting!)

ሰዎች ከገቢዎቻቸው ላይ የሚያወጡት ወጪ በዘፈቀደ ሳይሆን በስሌት መሆን አለበት! (በ50/30/20 ወይም በ30/30/30/10 ወይም በ80/20 ቀመር መሰረት) ስለሆነም ከወጪያችሁ ለመሰረታዊው (Need) እና ለፍላጎቶቻችሁ (Want) ምን ያህል ድርሻ መስጠት አለባችሁ? እንዲሁም ምን ያህል መቆጠብ መቻል ነው ጤነኛ በሆነው የወጪ ዝርዝር ውስጥ እንዳላችሁ የሚያሳየው?

በአዲስ አበባ በተደረገ የቀደመ ጥናት ሰዎች ከ50/30/20 ወርቃማው የወጪ ዝርዝር ህግ አንጻር ያሉበትን ደረጃ ቪዲዮው https://youtu.be/0oZakptRZ0E ላይ በመመልከት እናንተ ደግሞ ያለባችሁበትን ደረጃ በማስላት ተጠቃሚ ይሁኑ!

Subscribe በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ Share ያድርጉት!
መሰረታዊ የሚባሉት የኢኮኖሚ መሳሪያዎች በሁለት ይከፈላሉ፦ እነሱም የሞንተሪ/Monetary ፖሊሲ (የገንዘብ ስርጭት ቁጥጥር፤ የወለድ ተመን፤ የውጪ ምንዛሬ ተመን እና የፋይናንስ ተቋማት ቁጥጥር) እና የፊስካል/Fiscal ፖሊሲ (የግብር፤ የቀረጥ እና የበጀት) ናቸው።


ከሁለቱ የፖሊሲ አማራጮች የኢኮኖሚ እድገት ለመፍጠር፤ የዋጋ ንረት እና ስራ አጥነትን ለመቀነስ ውጤታማው የትኛው ነው? በሁለቱ ፖሊሲዎች መካከል በጥምረት መስራት ላይ ችግር የሚሆነው ምክንያት ምንድን ነው?


በኢትዮጵያ ሁለቱን ፖሊሲዎች የሚመሩት ተቋማት የትኞቹ ናቸው? ከላይ ከተዘረዘሩት ጥያቄዎች በተጨማሪ ሰፊ ማብራሪያ ያለበትን ቪዲዮ https://youtu.be/l_oCHVqlxe4 ተመልከቱ ለሌሎችም ግንዛቤ እንዲያገኙበት አጋሩት።
የአንዱ ሴክተር ወይም ሀገር መዳከም አልያም መነቃቃት ለሌላው ሴክተር ወይም ሀገር ላይ ያለው ቀጥተኛ ወይም ተዘዋዋሪ ተጽኖ/Spillover Effect ይባላል፡፡ በተለምዶ Spillover Effect ለአሉታዊ ተጽኖ (Negative Spillover Effect) መግለጫ ሆኖ የሚቀርብ ቢሆንም ለአዎንታዊ ተጽኖም (Positive Spillover Effect) መገለጫ ይሆናል፡፡

#ለምሳሌ፡- ራሽያ እና ዩክሬን በዓለም ገበያ ላይ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ጦርነት ውስጥ በመግባታቸው እና ማዕቀብ ውስጥ በመግባታቸው በዓለም ውስጥ ያላቸው ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ በመቀነሱ በዋናነት ሰፊ የንግድ አጋርነት ያላቸው ሀገራት ተጽኖ ውስጥ ገብተዋል፡፡ የዚህ አይነቱ ሁኔታ ሌሎች ሀገራት በሁለቱ ሀገራት ጦርነት ምክንያት Negative Spillover Effect ደረሰባቸው ይባላል፡፡

#ለምሳሌ፡- ራሽያ የዓለም ማዕቀብ ስለተጣለባት ህንድን አጋር ሀገር በማለት በርካሽ ነዳጅ ብታቀርብላት እና የህንድ ኢኮኖሚ መነቃቃት ቢያሳይ በራሽያ ጦርነት ሰበብ ህንድ Positive Spillover Effect ደረሰባት ሊባል ይችላል (ናይጄሪያ ጦርነቱን ተከትሎ የነዳጅ ገበያዋ ደርቷል ይህም በተመሳሳይ አወንታዊ ተጽኖ ሊባል ይችላል!)፡፡

ቀጥተኛ የትርፍም ሆነ የኪሳራ ተካፋይ የማይሆን ነገር ግን ተዘዋዋሪ ተጽኖ የሚጋሩ የኢኮኖሚ ክፍሎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ #ለምሳሌ፡- ራሽያ እና ዩክሬን ጦርነት ውስጥ መግባታቸውን መሰረት በማድረግ ራሽያ ላይ ማዕቀብ በመጣሉ በሶስተኛ ሀገራት ላይ የሚፈጠር ከራሽያ መሸመት ያለመቻል ችግር Externalities Spillover Effect ሊባል ይችላል፡፡

#ለምሳሌ፡- የአትክልት ማሳዎች ምርታምነት ቢሻሻል ለአግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፍ አወንታዊ ተጽኖ ሊፈጠርለት ይችላል፤ አፋር ክልል ችግር ውስጥ ቢገባ ሌላው ክልል በጨው አቅርቦት እጥረት አሉታዊ ተጽኖ ሊፈጠርበት ይችላል፤ በሀገር ውስጥ ለቻይና ተቋራጭ ፕሮጀክት መስጠት የእውቀት ሽግግር ቢፈጠር አዎንታዊ ተጽኖ ሊፈጠር ይችላል፤ የሶሻል ሚዲያ መምጣት ለጥቂቶች ገንዘብ መስሪያ ለብዙዎች የወጪ ምክንያት ሆኗል! ወዘተ ማለት ነው፡፡

በዚህ ወቅት የዓለም ሀገራት ኢኮኖሚ በጣም የተሳሰረ ከመሆኑ የተነሳ የአንዱ ሀገር ኢኮኖሚያዊ መቀዛቀዝም ሆነ በፍጥነት ማደግ ሌሎች ሀገራት ላይ ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ተጽኖ መፍጠሩ አይቀርም ይሁ ሁሉ Spillover Effect ይባላል፡፡
የተሟላ ምርጥ የጥናት ፕሮፖዛል አዘገጃጀት (ከሀ እስከ ፐ) (How to Write an Excellent Research Proposal?) የተሟላ የጥናት ፕሮፖዛል ለማዘጋጀት በመሰረታዊነት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ መከተል ያለባችሁ መስፈርቶች እና ጠለቅ ያለ መግለጫ/ትንታኔ የያዘ ቪዲዮ https://youtu.be/nNgAqBe1jFg አዘጋጅቻለሁ ስለዚህ #የምትፈልጉ ሰዎች ተጠቀሙበት ሌሎች መጠቀም ለሚፈልጉ ሰዎችም እዲማሩበት አጋሩት!
የጥናት ፕሮፖዛል (Research Proposal) መስፈርቶች

1. Title

2. Summary/Abstract

3. Introduction

4. Background

5. Statement of the Problem

6. Conceptual Framework

7. Research Objectives (Main and Specific)

8. Research Questions/Research Hypotheses

9. Significance

10. Scope, Thematic

11. Description of the Study Area

12. Research Methods and Procedures (Research Design (Research Paradigm)

#Research Approach (Deductive, Inductive, Exploratory, Explanatory, Qualitative, Quantitative, Mixed).

#Research Type (Descriptive, Analytical, Evaluative, etc.)

#Research Strategy (Experiment, Survey, Case Study, Grounded Theory, Ethnography, Action Research, etc.)

#Time Dimension (Cross sectional, Longitudinal (time series), panel) 

#Method of Data Collection (Type of Data, Instrumentation (Questionnaire, Interview, Focus Group Discussion, Document Review, Observation Etc.)

#Sampling Methods (Sampling Technique, target population, Sampling Frame, Sampling Unit, Sample Size)

#Operationalization Framework (Variables and Description, Measurement Type, Expected Sign etc.). 

#Method of Data Analysis: Data quality assurance (Validity, Reliability, etc.)

13. Limitations

14. Ethical Considerations

15. Organization of the Paper

16. Work Plan 

17. Budget

18. References

19. Appendices (Questionnaire, Schedule of Interview, FGD questions for etc.)


በቪዲዮ በዝርዝር ከነምሳሌው ለምትፈልጉ https://youtu.be/nNgAqBe1jFg
የኢኮኖሚክስ አስተምሮት በሁለት መሰረታዊ አመክንዮዎች የተከፈለ ነው፦ እነሱም በ18ኛው እና በ19ኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ አካባቢ የተጀመረው የክላሲካል(Classical Economics) እና ከ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ  ጀምሮ አዳዲስ ልምዶች እና ሃሳቦች በተጨመሩበት የኒዮክላሲካል (Neoclassical Economics) እውነቶች ነው።


የሁለቱ አስተምሮቶች ምንድን ነው? ልዩነታቸው የሚመነጨው ከየትኛው እውነት ተነስቶ ነው? አሁን ላይ የዓለም ሀገራት ከሁለቱም አስተምሮቶች እየቀላቀሉ የሚጠቀሙባቸው የትኞቹን ነው?


የትኛውም ሀገር ከሁለቱ አስተምሮቶች ውጪ አይደለም! ለምን? የሚከተለውን ቪዲዮ https://youtu.be/KQJ0UWkLklw ተመልከቱ ኢኮኖሚክስ ይበልጥ በማወቅ በእውነታዎቹ ይገረሙ።
የኢኮኖሚክስ አስተምሮት በሁለት መሰረታዊ አመክንዮዎች የተከፈለ ነው፦ እነሱም በ18ኛው እና በ19ኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ አካባቢ የተጀመረው የክላሲካል(Classical Economics) እና ከ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ  ጀምሮ አዳዲስ ልምዶች እና ሃሳቦች በተጨመሩበት የኒዮክላሲካል (Neoclassical Economics) እውነቶች ነው።


የሁለቱ አስተምሮቶች ምንድን ነው? ልዩነታቸው የሚመነጨው ከየትኛው እውነት ተነስቶ ነው? አሁን ላይ የዓለም ሀገራት ከሁለቱም አስተምሮቶች እየቀላቀሉ የሚጠቀሙባቸው የትኞቹን ነው?


የትኛውም ሀገር ከሁለቱ አስተምሮቶች ውጪ አይደለም! ለምን? የሚከተለውን ቪዲዮ https://youtu.be/KQJ0UWkLklw ተመልከቱ ኢኮኖሚክስ ይበልጥ በማወቅ በእውነታዎቹ ይገረሙ።
ወቅት እየጠበቁ እስከ 30% ቅናሽ አድርገናል የሚሉ አምራቾች እና ሻጮች እውነታቸውን ከሆነ ከዚህ በፊት የነበራቸው የትርፍ ጣሪያ/Profit Margin ስንት ይሆን?
አምራቾች፤ ነጋዴዎች፤ የቢዝነስ አዋጪነት ጥናት አዘጋጆች እና የቢዝነስ ፕላን ጥናት ገምጋሚዎች የመሸጫ እና የአገልግሎት መስጫ ዋጋ ለማውጣት የሚከተሉትን መስፈርቶች መከተል ተገቢ ነው...

1. ምርቱ ለመመረት ያስወጣውን ጠቅላላ ወጪ (Variable Costs)
2. ለቋሚ ንብረቶች የወጣ ወጪ (Fixed Costs)
3. የትርፍ ጣሪያ (Profit Margin)

ሸማች ለሚሸምተው ነገር በአብዛኛው በቂ መረጃ አለው ተብሎ ይታሰባል! ስለዚህ ጊዜው እና ገንዘቡ የሚመጥነውን ዋጋ በራሱ በማስላት እርካታውን ለመጠበቅ ይጥራል፡፡ ስለዚህ አምራቾች እና ሻጮች ትክክለኛውን ሸማች ማወቅ እና ለሚያቀርቡት ምርት እስከ ስንት ድረስ የመክፈል ፍላጎት እንዳለው (Willing to Pay) ለማወቅ፤ የወሰኑት ዋጋ ቢዝነሳቸው በትርፋማነት ለረጅም ጊዜ እንዲዘልቅ የሚያደርግ ዋጋ መሆኑን ለማወቅ በሳይንስ (Pricing Strategy) መመራት ያለበት የገበያ ጥናት አካል ነው፡፡

ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን ቪዲዮ https://youtu.be/h0KT3GE5rz0 ተመልከቱ፤ ተጠቀሙበት እና ለሌሎች እንዲጠቀሙበት አጋሩት፡፡
#ዋጋ_እንዴት_ይወጣል?


ቢዝነስ ለመጀመርም ሆነ በቢዝነስ ውስጥ ለመቆየት አስቸጋሪ ከሆኑ ነገሮች መካከል ዋነኛው ለሚያቀርቡት ምርት ትክክለኛውን ዋጋ እንዴት ማስቀመጥ እንደሚቻል አለማወቅ ነው፡፡ ትክክለኛውን መስፈርት ጠብቆ ዋጋን መተመን አለመቻል ጠቅላላ የቢዝነስ እንቅስቃሴን ህልውና ያናጋል፡፡


የዋጋ ተመን የሸማችን ሁኔታ በቀጥታ ይነካል፤ ምክንያቱም ሸማች ከምንም በላይ ለሸመታ ውሳኔው ዋጋን በተመለከተ ስሜታዊ ነው (Price Sensitivity) ይህ ሁኔታ ደግሞ አምራች እና ሻጮችን ስለ ዋጋ ሁኔታ እንቅልፍ እንዲያጡ ያደርጋል (የእኛ ሃገርን ሁኔን ገላጭ ባይሆንም)፡፡ የምርትም ሆነ የአገልግሎት ዋጋ በተለመደ መልኩ ወይም ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ሊወሰን ይችላል፡፡ ነገር ግን ዋጋን ለመወሰን ውስጣዊ እና ውጫዊ ምክንያቶች መሰረታዊ መስፈርቶች ናቸው፡፡


ሸማች ለሚሸምተው ነገር በአብዛኛው በቂ መረጃ አለው ተብሎ ይታሰባል! ስለዚህ ጊዜው እና ገንዘቡ የሚመጥነውን ዋጋ በራሱ በማስላት እርካታውን ለመጠበቅ ይጥራል፡፡ ስለዚህ አምራቾች እና ሻጮች ትክክለኛውን ሸማች ማወቅ እና ለሚያቀርቡት ምርት እስከ ስንት ድረስ የመክፈል ፍላጎት እንዳለው (Willing to Pay) ማወቅ በሳይንስ (Pricing Strategy) መመራት ያለበት የገበያ ጥናት አካል ነው፡፡


የዋጋ ሁኔታን ለመወሰን ከቢዝነሱ አይነት (ኢንዱስትሪ፤ ግብርና፤ አገልግሎት፤ ቴክኖሎጂ፤ ወዘተ)፤ ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ከሚሸምተው እና ከሚጠቀመው ደንበኛ አንጻር (Ideal Target Customers)፤ ምርቱ ወይም አገልግሎቱ ካስወጣው ወጪ አንጻር እንዲሁም ከተመሳሳይ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ካላቸው የዋጋ ንጽጽር አንጻር (Competitive Markets/Pricing) ከግምት መከተት አለባቸው፡፡


#ለምሳሌ፡ የችርቻሮ ሻጮች የዋጋ ተመን ከአምራቾች እኩል አሳሳቢ እና ሳይንሳዊ ለመሆን ላይገደድ ይችላል፡፡


አንድ ምርት ለመመረት ያስወጣውን ወጪ በጠቅላላ ደምሮ ይገባኛል የሚሉትን የትርፍ መጠን (Profit Margin) ጨምሮ ዋጋ ማውጣት በጣም ቀላሉ ነው (Cost-Plus Pricing):: ነገር ግን አምራቾችም ሆኑ ሻጮች ዋጋን አንዴ የሚወስኑት ጉዳይ ብቻ መሆን አይችልም! ምክንያቱም የሚያስቀምጡት ዋጋ የቢዝነሳቸውን ዘላቂነት የሚነካ መሆኑን ማወቅ ግድ ነው፡፡


#ለምሳሌ፡- የሚቀመጠው ዋጋ ወድ ሆኖ ሸማቾች የሚችሉት/የሚመርጡት ካልሆነ ከገበያ መውጣት ሊከሰት ይችላል በተቃራኒው ከመሰረታዊ ወጪ በታች ዝቅተኛ ዋጋ በማስቀመጥም በገበያው በቀጣይ ለመቆየት መቸገር ሊመጣ ይችላል፡፡ በርግጥ ሸማችን እና በገበያው የሚኖርን ዘለቄታዊ ቆይታ በማሰብ በውስን ክስረት መሸጥ ሊኖር ይችላል ግን ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ አካሄድ ነው፡፡


አንዳንዴ አምራቾች ነባር ደንበኞቻቸውን መሰረት በማድረግ የተጨማሪን ዋጋ ሁኔታ መመርመር ይቻላሉ! ይህ የሸማችን የመግዛት አቅም እና ምክንያታዊነት ለማወቅ ይረዳል፡፡


ዋጋ ለማስቀመጥ የሚከተሉትን መስፈርቶች መከተል ተገቢ ነው እነሱም…..


1. ምርቱ ለመመረት ያስወጣውን ጠቅላላ ወጪ ማወቅ (Variable Costs)፡- አምራች ከሆኑ ለማምረት ያወጡት የግብዓት ወጪ፤ የሰራተኛ ወጪ፤ የማጓጓዝ ወጪ እና የስራ ማስኬጃ ወጪዎችን በመውሰድ እና የምርቱን መጠን ደምሮ ማስላት ማለት ነው:: እያንዳንዱ ምርት ተመርቶ ለመውጣት የፈጀው ሰዓት እንደወጪ ዝርዝር ይካተታል፡፡


#ለምሳሌ፡- አንድ ኪሎ ቲማቲም ለማምረት የግብዓት ወጪ 10 ብር ቢሆን፤ ለማምረት የፈጀው ጊዜ ወደ ገንዘብ ሲቀየር በኪሎ 2 ቢሆን፤ ተለቅሞ የሚሰበሰብበትን ሳጥን ለመግዛት የወጣው ወጪ በኪሎ 2 ብር ቢሆን፤ ምንአልባት ለማስተዋወቅ (ባነርም ቢሆን) ያስወጣው ወጪ በኪሎ 1ብር ቢደርስ፤ ቲማቲሙን ወደ ገበያ ለማድረስ ያስወጣው ወጪ በኪሎ 3 ብር ቢደርስ፤ ጫኝና አውራጆች የሚጠይቁት በኪሎ 1 ብር ቢደርስ፤ (ህጋዊም ሆነ ህገወጥ ቀረጥ እና ግብር ኖሮ) 1 ብር ቢያስወጣ……..አንድ ኪሎ ቲማቲም ገበያ ለመድረስ ያስወጣው ወጪ (Per-Product Cost) 20 ብር ደረሰ ማለት ነው፡፡


2.ቋሚ ወጪዎችን ማጠቃለል (Fixed Costs)፡- በማምረት ወቅት የቋሚ ንብረቶች ወጪ መታሰብ አለበት (የመሬት፤ የግንባታ፤ የማሽኖች፤ የመኪኖች፤ ወዘተ) ምክንያቱም ግንባታ ገንብቶ እና ማሽን ገዝቶ የሚያመርት አምራች በሂደት ወጪውን ማካካስ የሚችለው ከሚሸጠው ምርት ነው፡፡


#ለምሳሌ፡- በ10 ሚሊየን ብር ግንባታ ሰርቶ ቲማቲም ለማምረት ቢዝነስ የጀመረ አምራች የሚሸጡ ቲማቲሞች ላይ የቋሚ ንብረቶችን ወጪ መደመር አለበት ነገር ግን በነጠላ እያንዳንዱ ቲማቲም ላይ ለመደመር ሊያስቸግር ይችላል (ዋጋ ሳይንስ ነው የሚባለው ለዚህ ነው! ከጠቅላላው 10 ሚሊየን ብር ውስጥ አንዷ ቲማቲም ምን ያህል ብር ድርሻ ትያዝ?)


3.የትርፍ ጣሪያ (Profit Margin)፡- አምራች ማትረፍ የሚፈልገውን የትርፍ መጠን ለማስላት ሁለት ነገር ታሳቢ ማድረግ አለበት፡፡ የመጀመሪያው ለቋሚ ንብረቶች (የመሬት፤ የግንባታ፤ የማሽኖች፤ የመኪኖች፤ ወዘተ) ያወጣው ወጪ እዚህ ላይ መደመር የለበትም ሁለተኛው የሚያጠቃልለው የትርፍ ጣሪያ ጭማሪ ምርቱ መጨረሻ ላይ ሲሸጥ ተቀባይነት ከሚኖራቸው ዋጋዎች በጣም የራቀ እንዳያደርገው መጠንቀቅ አለበት፡፡


#ለምሳሌ፡ ጠቅላላ የምርት ወጪው እና ለቋሚ ንብረት የወጣበት ወጪ ተደምር አንድ ምርት ገበያ ለመድረስ 20 ብር ቢያስወጣ እና አምራቹ የትርፍ መጠኑ 20%  እዲሆን ቢወስን በቀላል ስሌት/Profit Margin Calculator (20 ብር/1-20% (0.2) = 20/0.8 = 25 ብር ሊሸጥ ይችላል) ስለዚህ ምርቱ ያስወጣው ወጪ 20 ብር ሆኖ የምርቱ የመሸጫ ዋጋ 25ብር ደረሰ ማለት ሲሆን የአምራቹ ትርፍ ደግሞ 5 ብር ሆነ ማለት ነው፡፡


ከላይ የተጠቀሱ ሶስቱም መስፈርቶች በሙሉ ታሳቢ ቢደረጉም በመጨረሻ ግን ሸማች ለመሸመት የሚፈቅድበት የዋጋ መጠን (Willing to Pay) ከግምት ካልገባ ዋጋ የለውም፡፡
ማለፍ ለሚችል ፍላጎት/ፍጆታ ብላችሁ ብድር ውስጥ ላለመግባት ሞክሩ! የዚህ አይነት ልምድ ከፋይናንስ ነፃነት ማጣት እስከ ነባር ልምዶችን መቀየር የደረሰ ውሳኔን የሚጠይቅ ነው።
ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳዔ በዓል አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!
ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በራሳቸው ገንዘብ (ከዶላር ውጪ) ቢገበያዩ ማን ተጠቃሚ ይሆናል?


በዓለም ላይ በሀገራት መካከል ግብይት የሚከናወነው በአብዛኛው በዶላር ነው። ነገር ግን በተለያዩ አስገዳጅ ምክንያቶች ሀገራት የየራሳቸውን ገንዘብ የእርስበርስ ግብይት አድርገው ሊጠቀሙ ይችላሉ።


በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለ ጥምረት ለኢኮኖሚዊ ህልውና ወሳኝ ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያ ከጅቡቲ ጋር በጅቡቲ ፍራንክ እንዲሁም ጅቡቲ ከኢትዮጵያ ጋር በኢትዮጵያ ብር ሸመታ እና ሽያጭ ቢያከናውኑ ተጠቃሚው ማነው?


በረጅም ጊዜ ጅቡቲ በአጭር ጊዜ ኢትዮጵያ በዚህ የንግድ ስምምነት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስባለሁ! እንዴት እንደሆነ ይህንን https://youtu.be/E01n3QjMHu8 ሰፊ በመረጃ የተደገፈ ትንታኔ ተመልከቱ።