The Ethiopian Economist View
29.3K subscribers
724 photos
4 videos
197 files
1.34K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
በቅርቡ የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ኢትዮጲያን በጎበኙ በጥቂት ቀናት ውስጥ የኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ የፖሊሲ ማሻሻያ ስለማድረጉ መግለጫ ለመስጠት ሲዘጋጅ ብዙዎች በቀጥታ ከገንዘብ የመግዛት አቅም ሊዳከም (Devaluation) ይችላል ከሚለው ግምት ጋር አገናኝተውት ነበር! (የኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንኩ ገዢ በቀደመ ስራቸው ከዓለም ባንክ ጋር ነበር)፡፡


ለብዙዎች የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም ጉዳይ ለምን መሰረታዊ ስጋታቸው ሆነ? የዓለም ባንክ ኢትዮጲያ ገንዘቧን ከዶላር አንጻር እንድታዳክም ለምን ይጓጓል?


የዓለም ባንክን ፕሬዝደንት የመሾም ስልጣን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት መሆኑን ታውቃላችሁ? ምንም እንኳን የዓለም ባንክ ዓለም አቀፍ ድርጅት ቢሆንም የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የዓለም ባንክን መሪ ይመርጣል:: ይህ የሆነበት ምክንያት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ጀምሮ ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ኃያላን ሁለት የፋይናንስ ተቋማትን በ Bretton Woods ስምምነት ማለትም የዓለም ባንክ (World Bank) እና የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) ሲፈጥሩ በተደረገው ስምምነት አማካኝነት ነው። (ባንኩ ዋና መቀመጫው በአሜሪካ ያደረገ ቢሆንም ከ130 በላይ አገሮች ውስጥ ቢሮዎች አሉት)።


ከግንቦት ወር 2023 ጀምሮ አሜሪካዊው #አጃይ_ባንጋ (በትውልድ ህንዳዊ ቢሆንም ከ2007 ጀምሮ አሜሪካዊ ሆኗል) በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ተሹሞ እየሰራ ነው፡፡


የዓለም ባንክ እና የዓለም የገንዘብ ድርጅቶች ዋና ዓላማ የአባል ሀገራቶቻቸውን (በተለይ የምዕራባውያን) ፍላጎት ማሳካት በመሆኑ ነፃ የገንዘብ ዓለም አቀፍ ዝውውር እንዲፈጠር ካላቸው/ካለባቸው ዓላማ/ግፊት አንፃር ሃገራቶች የገንዘቦቻቸውን የምንዛሬ ገበያ በነፃ ህግ (Floating Exchange Rate) እንዲመራ ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ ጫና ይፈጥራሉ።


ከፊት ለፊት የሚቀርበው መነሻ ምክንያታቸው ሃገራት ጠንካራ ኢኮኖሚ እንዲኖራቸው በማሰብ መሆኑን ቢጠቅሱም የዓለምን ነፃ የገንዘብ እና የሪሶርስ ዝውውር ቀላል በማድረግ የግዙፍነት እድል (በተለይ ከደካማው የታዳጊ ሃገራት ሃብት) ለመውሰድ ነው።


የኢትዮጵያ ገንዘብ (ብር) በብዙ መለኪያ ከሚገባው በላይ አቅም ይዟል! ስለዚህ እራሱን ይበልጥ አዳክሞ በውጪ ምንዛሬ ግኝት እና በውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት የሚገኙ ትሩፋቶችን ለመጠቀም ቢሞክር መጥፎ ምክረ ሃሳብ አይሆንም።


የውጪ ምንዛሬ ፖሊሲ ከሌሎች የገንዘብ እና የፊስካል ፖሊሲ አፈፃፀሞች ጋር ካልተናበበ አደጋው ብዙ ነው።


ለምሳሌ፦ አንድ ዶላር በባንኮች በ80ብር እንዲመነዘር ማሻሻያ ተደርጎ ከውጪ የሚገቡ ምርቶች በፍጥነት ከሚፈጥሩት የዋጋ መናር ጋር መገዳደር የሚችል የሀገር ውስጥ ምርታማነት ስራ ካልተሰራ ችግር ነው!


ወይም ገንዘብ ተዳክሞ ሊፈጠር ለሚችለው የዓለም አቀፍ የገበያ እድል በቂ የሆነ የውጪ ገበያ የሚቀርብ ምርት መጠን እና እሴት ካልጨመረ አልያም በገንዘብ ድክመት ምክንያት የሚፈጠር የውጪ ምንዛሬ ግኝት አጠቃቀም ከCapital Goods (የምርት ግብዓት) በተፃፃሪ የፍጆታ ምርት ከሆነ ማሻሻያውን አደጋ ያደርገዋል።


እንደ ሀገር የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም እንደስጋት እንዲታይ ያደረገው ከፖሊሲው በላይ በፖሊሲ አተገባበር እና በእድል አጠቃቀም ላይ ኢኮኖሚው አወንታዊ ለውጥ በፍጥነት ሲመለከት ስላልኖረ ነው።


የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ደካማ አቅም ያለው ነው! ያሉበት ችግሮች ደግሞ ባህሪያቸው ከኢኮኖሚ ተቋማት ድክመት ብቻ የሚነሳ አይደለም! ስለዚህ አለም አቀፍ ሰፊ መደገፍ ውስጥ ያለ ኢኮኖሚ በመሆኑ የዓለም አቀፊ መልቲ ላተራል ተቋማት ጫና ኢኮኖሚያዊ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊም ጭምር በመሆኑ የዓለም ባንክን ጫና ቸል የማለት ሳይሆን በሂደት አያለሳለሱ የመጠቀም አዝማሚያ ውስጥ እንደሆነ ይሰማኛል።


ስለሆነም ዜሮ አደጋ የሆነ ፖሊሲ ያለመኖሩን በማወቅ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያ ለማድረግ የሃገር ውስጥ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲም ሆነ የፖለቲካ ስርዓት አስፈፃሚ ተቋማትን አቅም ማጠናከር ለማይቀረው ፈተና እንደመከላከያ መቁጠር ያዋጣዋል።
ኢትዮጲያ BRICSን መቀላቀሏ ሊኖረው የሚችለው ጥቅም እና ጉዳት ምንድን ነው?


በመጀመሪያ አባል በመኮኑ ማታሰብ ያለባቸው መሰረታዊ ነጥቦች ተግባራዊ ስጋቶች ከአሜሪካ እና ከምዕራቡ ዓለም በምላሽ መልክ መምጣቱን ማሰብ፤ ስለ አዲስ ህብረቶች ሁኔታ መዘጋጀት እና BRICSን የመቀላቀል ጥቅሞች እና BRICS በመቀላቀል የሚመጡ አደጋዎችን ማመዛዘን ይገባል፡፡ ስለሆነም የሚከተለውን ትንታኔ ይመልከቱ https://youtu.be/k_gJB3G2vM8
ኢትዮጲያ BRICSን መቀላቀሏ ሊኖረው የሚችለው ጥቅም እና ጉዳት ምንድን ነው?


በመጀመሪያ አባል በመኮኑ ማታሰብ ያለባቸው መሰረታዊ ነጥቦች ተግባራዊ ስጋቶች ከአሜሪካ እና ከምዕራቡ ዓለም በምላሽ መልክ መምጣቱን ማሰብ፤ ስለ አዲስ ህብረቶች ሁኔታ መዘጋጀት እና BRICSን የመቀላቀል ጥቅሞች እና BRICS በመቀላቀል የሚመጡ አደጋዎችን ማመዛዘን ይገባል፡፡ ስለሆነም የሚከተለውን ትንታኔ ይመልከቱ https://youtu.be/k_gJB3G2vM8
ኢትዮጲያ #BRICSን የመቀላቀሏ ጥቅም እና ጉዳት ምን ሊሆን ይችላል?

በ2001 ብራዚል (Brazil)፤ ሩስያ (Russia)፤ ህንድ (India) እና ቻይና (China) የስማቸውን የመጀመሪያ ፊደል በመውሰድ BRIC የተባለ አጋርነት መሰረቱ በ2010 ደቡብ አፍሪካን (South Africa) አካተው BRICS ተብለው ላለፉት 22 ዓመታት የቆየ የኢኮኖሚ አጋርነት ቢሆንም በ2023 ጉባዬ የአባላቶቻቸውን ቁጥር ወደ 11 ለማሳደግ ወስነዋል (የተጨመሩት ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፤ ኢራን፣ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና አርጀንቲናን ናቸው)። የወቅቱ ሊቀመንበር ደቡብ አፍሪካ ስትሆን BRICS ዋና መቀመጫውን በቻይና ሸንጋይ አድርጓል፡፡

BRICS የምዕራባውያን ተፅእኖን ለመፎካከር የተመሰረተ የኢኮኖሚ አጋርነት ነው። በመጀመሪያውም አባል ሀገራቱ የሽርክና ቡድኑ ዓላማ ብዝሃነት ያለው አዲስ የዓለም የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ስርዓት እንዲፈጠር መሆኑን ያስረዳሉ! በተጨማሪነትም የዓለም የጂዎ ፖለቲክስ ሚዛንን ለመጠበቅ፤ የዓለም አቀፍ ተቋማት በተለይ (የዓለም ባንክ እና የዓለም የገንዘብ ድርጅት) ጫናን ለመቋቋም፤ ታዳጊ ሃገራትን ከምዕራባዊያን ፍታዊ ያልሆነ ጫና ለመጠበቅ ያለመ አይነት ነው፡፡ የዓለም ንግድ ከዶላር ውጪ ተጨማሪ መገበያያ ገንዘብ እንደሚያስፈልገውም ይስማማሉ።


አምስቱ የBRICS አባል ሀገራት ብቻቸውን 3.77 ቢሊዮን የዓለም የህዝብ ብዛት አላቸው! ቻይና 1.412 ቢሊየን፤ ህንድ 1.408 ቢሊየን፤ ብራዚል 214.3 ሚሊየን፤ ራሽያ 143.4 ሚሊየን እና ደቡብ አፍሪካ 59.39 ሚሊየን (የተጨመሩት 6 አዲስ አባል ሀገራት በጠቅላላ 410 ሚሊየን ህዝብ ያላቸው በመሆኑ የአባል ሃገራት ህዝብ ብዛትን ወደ 4.2 ቢሊየን ያደርሱታል)። ነባር አባል ሀገራቱ ያላቸው ጠቅላላ የምርት መጠን (GDP) 26 ትሪሊዮን ዶላር ይደርሳል (ከዓለም ጠቅላላ ምርት መጠን ውስጥ 26 ከመቶ ነው)።

ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ጀምሮ እስከ ቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት ድረስ የነበረው የዓለም ሀገራት በርዕዩተ ዓለም የመቧደን አይነት አዝማሚያ ያለው የሚመስል ሆኖ አባል ሀገራቱ በዚህ ወቅት ዓለም በጥቂት ሀገራት የበላይነት መመራቷ ማብቃት አለበት ሲሉ ይሞግታሉ።

በተለይ ኢትዮጲያ BRICS የመቀላቀሏ ጥቅም እና ጉዳት ምንድን ሊሆን ይችላል?

በመጀመሪያ አባል በመኮኑ ማታሰብ ያለባቸው መሰረታዊ ነጥቦች ተግባራዊ ስጋቶች ከአሜሪካ እና ከምዕራቡ ዓለም በምላሽ መልክ መምጣቱት ማሰብ፤ ስለ አዲስ ህብረቶች ሁኔታ መዘጋጀት እና BRICSን የመቀላቀል ጥቅሞች እና BRICS በመቀላቀል የሚመጡ አደጋዎችን ማመዛዘን ይገባል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን ታሳብ ጥቅሞች እና ጉዳቶችን ማሰብ ይቻላል……

እድሎች

የተሻሻለ የኢኮኖሚ ትብብር ሊፈጠር ይችላል፡ ለኢትዮጲያ ዓለም አቀፍ ንግድን፣ የውጪ ኢንቨስትመንትን እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማጎልበት ኢኮኖሚያዊ ትብብር እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል። ይህ አጋርነት ቀጣይነት ያለው የኢንዱስትሪ ልማትን ማበረታታት፣ የስራ እድል መፍጠር እና ፈጠራን ማጎልበት በመጨረሻም የረዥም ጊዜ የኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅዖ ሊያደርግ ይችላል።

የመሠረተ ልማት ግንባታ ተስፋዎች ሊኖሩት ይችላል፡ የቀደሙ የBRICS አባል ሀገራት (አዲስ የቀላቀሉትንም ጨምሮ) በመሠረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ከፍተኛ እውቀት እና ሀብቶች አሏቸው። ኢትዮጲያ ህብረቱን በመቀላቀሏ ከፍተኛ የመሠረተ ልማት ጉድለትን ለመፍታት ወሳኝ የሆነውን እውቀት እና ልምድ ልታገኝ ትችላለች። ከአዲሱ የBRICS ልማት ባንክ (New Development Bank) የገንዘብ ድጋፍ በማግኘት የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ለማፋጠን አስደሳች ዕድል ሊፈጥርላት ይችላል።

ለምሳሌ፡- የኢትዮጲያ ከዓለም ባንክ ብድር እና ድጋፍ ስታገኝ የኖረች ቢሆንም ጠንካራ ቅድመ ሁኔታ ያለው ብድር ከመሆኑ በተጨማሪ የበለጸጉት ሃገራት ብድሩን እንደ ርዕዩተ ዓለም ማስፈጸሚያ እና ጫና መፍጠሪያ አድርገው ይጠቀማሉ፡፡ ለነገሩ ረዘም ላሉ ዓመታት የብድር ፍላጎቶቿ/እድሎቿ ወደ ቻይና ዞረዋል (የብዙ አፍሪካ ሀገራት አጋርነት ወደ ቻይና የመዞር በቻይና አፍሪካ ጉባዬ እና በዩኤስ አፍሪካ ጉዳኤ ላይ በተደጋጋሚ የሚነሳ ጉዳይ ነው)፡፡


ይህ የተቀመጠ እድል ወደ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጠቀሜታ እንዲለወጥ በሀገር ውስጥ ጠንካ እና ተፎካከሪ የኢኮኖሚ እና የማምረት አቅም መፍጠር የማይቻል ከሆነ ምንም ፋይዳ ላይኖረው ይችላል፡፡

ስጋቶች

የምዕራባውያን ውጪ ባሉ ሀገሮች ላይ ተመሳሳይ ጥገኝነት መፍጠር፡ አባልነትን ተከትሎ የምዕራብ ሃገራትም ሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማት በውሳኔው ደስተኛ ያለመሆን አዝማማያ ሊኖራቸው ስለሚችል (ቅታቸውን ብድር እና እርዳታ ወደ መከልከል የሚያዞሩት ከሆነ) ኢትዮጲያ ወደ ሌሎቹ የBRICS አባል ሀገራት ይበልጥ ጥገኝነቷን ማዞር ልትጀምር ትችላለች (በተለይ ወደ ቻይና! ይህ አዝማሚያ የBRICS አባል ከመሆንም በፊት እየታየ የመጣ ነው)፡፡


የንግድ ግንኙነት መዳረሻዎች መለውጥ፡ BRICSን መቀላቀል የንግድ መዳረሻዎችን ወደ አባል ሀገራት ገበያዎች አቅጣጫ እንዲቀይር ሊያደርግ ይችላል። ይህ ለረጂም ጊዜ የቆየውን የኢትዮጲያ እና የምዕራባውያን እና የአሜሪካ የንግድ ግንኙነቶችን ሊያደናቅፍ ይችላል፡፡ ነገር ግን ኢትዮጲያ የውጪ ገበያ መዳረሻዎቿን በማስፋት የንግድ ልውውጥ እንዲጨምር እና በነጠላ የንግድ አጋሮች ላይ ያላትን ነባር ጥገኝነት እንዲቀንስ አዳዲስ ዕድሎችን ሊከፍትላትም ይችላል።


የመገለል ስጋት፡- BRICSን መቀላቀል እንደ የአለም ባንክ እና የአለም የገንዘብ ድርጅት ካሉ ምዕራባውያን ተቋማት ሊያስገልል እንደሚችል ማሰብ ይቻላል። ይሁን እንጂ በBRICS ውስጥ የተመሰረተው አዲስ የልማት ባንክ (New Development Bank) ያሉ አማራጭ የፋይናንስ ዘዴዎች መፈጠራቸው እነዚህን ሥጋቶች ለመፍታት እና ለኢትዮጲያ ለመሠረተ ልማትና ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በጣም አስፈላጊ የሆነውን ካፒታል (የውጪ ምንዛሬ) እንድታገኝ ሊያግዛትም ይችላል።

ከዚህ ቀደም ዩናይትድ ስቴትስ እና አንዳንድ ምዕራባውያን ኃያላን የአፍሪካ ሀገራት ከBRICS ጋር መስማማታቸው ስጋታቸው መሆኑን ገልጸዋል። የBRICS ታዋቂነት እያደገ በመምጣቱ ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ ላይ ያላት ተጽእኖ እየቀነሰ እንዳይሄድ ትሰጋለች። ስለሆነም አጋርነትን ማጠናከር፣ የእርዳታ ፖሊሲዎቻቸውን ማሻሻል ወይም ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ ጫና ፈጣሪ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይችላሉ።
በቡድን 7 (G7)፤ በቡድን 8 G8)፤ በቡድን 20(G20) እና በBRICS የዓለም ሀገራት የሚደራጁበት ምክንያት እና በሁሉም ቡድኖች መካከል ያለ ልዩነት ምንድን ነው!


ቡድኖቹ የበለፀጉ ሀገራት ቢሆንም በየዓመቱ የስብሰባ ውሳኔዎቻቸውን በጉጉት የሚጠብቁት ደግሞ ያላደጉት ድሃ ሃገራት ናቸው።


https://youtu.be/ZY2EB3EI2Y0
በቡድን 7 (G7)፤ በቡድን 8 G8)፤ በቡድን 20(G20) እና በBRICS የዓለም ሀገራት የሚደራጁበት ምክንያት እና በሁሉም ቡድኖች መካከል ያለ ልዩነት ምንድን ነው!


ቡድኖቹ የበለፀጉ ሀገራት ቢሆንም በየዓመቱ የስብሰባ ውሳኔዎቻቸውን በጉጉት የሚጠብቁት ደግሞ ያላደጉት ድሃ ሃገራት ናቸው።


https://youtu.be/ZY2EB3EI2Y0
የዓለም የኢኮኖሚ ህብረቶች (ቡድን 7፤ ቡድን 8 እና ቡድን 20) ምክንያት እና ልዩነት!

የቡድን 7
የቡድን 7 ሀገራት (ካናዳ፤ ፈረንሳይ፤ ጀርመን፤ ጣልያን፤ ጃፓን፤ አንግሊዝ እና አሜሪካ በተጨማሪም የአውሮፓ ህብረት (እንደ ተቋም ያለ ግን የማይቆጠር) ናቸው፡፡ በኢ-መደበኛ አደረጃጀት ደረጃ ያለ በፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ጉዳዮች አባል ሀገራት ውይይት የሚያደርጉበት የውይይት ህብረት ሲሆን የተመረተው 1975 በወቅቱ በዓለም ላይ ከነበረው የነዳጅ ቀውስ ማግስት ሲሆን በመጀመሪያ በአውሮፓ ህብረት ውስጥ ሰፊ ህዝብ እና የድምጽ ሽፋን ያላቸው 6 ሃገራት ማለትም ፈረንሳይ፤ ጀርመን፤ ጣልያን፤ ጃፓን፤ አንግሊዝ እና ፖላንድ ሆነው የሊበራል ህብረት በሚል ነው፡፡

አባል ሃገራቱን ለተመለከተ በዓለም ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ዲፕሎማሲያዊ እንዲሁም የሚሊተሪ ዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ላይ የጎላ ተሳትፎ እና ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ ተትኖ ያላቸው ናቸው፡፡ የዓለም የገንዘብ ድርጅት ላይ ሰፊ ድርሻ፤ የዓለም ግማሽ ሃብት መጠን (ከ200 ትሪሊየን ዶላር በላይ)፤ ከ40 ከመቶ በላይ የዓለም የኢኮኖሚ ምርት መጠን GDP፤ 10 ከመቶ የዓለም ህዝብ፡፡ ዓመታዊ ስብሰባቸው በጉጉት የሚጠበቅ እና የተሻለ መግባባት ያለበት ህብረት እንደሆነ ይታወቃል፡፡

አባል ሀገራቱ ከ1997 አንደእንግዳ በጉባያቸው ላይ ይጋብዟት የነበረችውን ራሽያ ክርሚያን ወረሻል በሚል ምክንያት ከ2014 በኋላ እስኪያባርሯት የቡድን ስምንት መባል ጀምረው ነበር፡፡ በርግጥ የቡድን 7 ቋሚ ጸሃፊም ሆነ ቢሮ የሌለው ቢሆንም የአባል ሀገራቱ መሪዎች በዙር እየተለዋወጡ በፕሬዝደንትነት ዓመታዊ ስብሰባውን ይመሩታል (የ2023 ተረኛ ፕሬዝደንት ጃፓን ነች)፡፡

ቡድኑ በዓለም ላይ ኤች አይ ቪ ኤድስን በመዋጋት፤ ለታዳጊ ሃገራት የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ (የእዳ ስረዛ እና የእዳ ክፍያ ወቅት ማራዘምን ጨምሮ) እና የአካባቢ ጥበቃ ላይ ተጽኖዎችን ፈጥሯል፡፡ ነገር ግን ቡድኑ ጊዜ ያለፈበት እና ውስን አባልነት ያለው፣ ጠባብ የዓለም ውክልና እና በሚጠበቀው ልክ ውጤታማ ባለመሆኑ ይወቀሳል።

የቡድን 8
በ1975 የተቋቋመው የቡድን ሰባት ሀገራት ከ1997 እስከ 2014 ድረስ ማለትም ራሽያን በፖለቲካዊ ውሳኔ እስኪቀንሱ ድረስ የቡድን ስምንት ተብለው ይጠሩ ነበር (ማለትም ካናዳ፤ ፈረንሳይ፤ ጀርመን፤ ጣልያን፤ ጃፓን፤ አንግሊዝ፤ ራሽያ እና አሜሪካ)፡፡ ነገር ግን ራሽያ በ2014 የክርሚያ ወረራ ማግስት በማባረራቸው ወደቀደመ ስማቸው ማለትም ቡድን 7 በመባል እስካሁን ቀጥለዋል፡፡

በ2005 እንግሊዝ በቡድን ስምንት ሃገራት ላይ ተጨማሪ አምስት ሀገራት እንዲቀላቀሉ ሃሳብ በማምጣት G8+5 ሊደመሩ የታሰቡት ብራዚል፤ ህንድ፤ ቻይና፤ ሜክሲኮ እና ደቡብ አፍሪካ ነበሩ)፡፡ የቡድን 8 ሀገራት በተለይ ከ2009 በኋላ ወደ 93 ከመቶ ፈንዶቻቸውን የዓለም የምግብ አቅርቦት ድጋፍ እና ዘላቂ የግብርና ምርት እድገት ላይ ለማድረግ ወጥነው እየሰሩ ነው፡፡

የቡድን 20
የቡድን 20 የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ 19 ሀገራት (አውስትራሊያ፤ ካናዳ፤ ህንድ፤ ራሽያ፤ ተርኪዬ፤ ጣልያን፤ ሜክሲኮ፤ ጀርመን፤ ፈረንሳይ፤ ቻይና፤ አሜሪካ፤ ብራዚል፤ ጃፓን፤ አርጀንቲና፤ ደቡብ አፍሪካ፤ ኢንዶኒዠያ፤ ደቡብ ኮርያ፤ ሳውዲአረቢያ እና እንግሊዝ) በዋናነት ከ2009 ጀምሮ (ከ2008ቱ የዓለም የፋይናንስ ቀውስ ማግስት ታስቦ) የተቋቋመ ህብረት ነው፡፡ በዓላማ ደረጃ የዓለም የፋይናንስ እንቅስቃሴ ጤነኛ እንዲሆን፤ የዓለም አካባቢ ጥበቃን ለማጠናከር እና ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት መፍጠርን ያለመ ነው፡፡

ከ80 ከመቶ በላይ የዓለም ሃብትከ 75 ከመቶ በላይ የዓለም የንግድ ልውውጥ ድርሻ፤ የዓለም 2/3ኛ ህዝብ ቁጥር እና ከ60 ከመቶ በላይ የዓለም ቆዳ ስፋትን ይዘዋል፡፡ በየዓመቱ የአባል ሀገራቱ ፕሬዝደንት/ጠቅላይ ሚኒስቴር፤ የፋይናንስ ሚኒስትሮች/ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች በየደረጃቸው በዓመት ሁለቴ በሚቀረጹ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋሉ፡፡

በርግጥ የቡድን 20 ቋሚ ጸሃፊም ሆነ ቢሮ የሌለው ቢሆንም የአባል ሀገራቱ መሪዎች በዙር እየተለዋወጡ በፕሬዝደንትነት ዓመታዊ ስብሰባውን ይመሩታል (የ2023 ተረኛ ፕሬዝደንት ህንድ ነች)፡፡

ልብ ካላችሁ የBRICS አባል ሀገራት በሙሉ የቡድን 20 አባል ሀገራት ናቸው! መሰረታዊ ልዩነቱ ተቋም BRICS ቋሚ ጽ/ቤት ያለው ተቋም ሲሆን ከላይ የተዘረዘሩት ህብረቶች በሙሉ ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ናቸው (ቋሚ ጽ/ቤት የሌላቸው) ማለት ነው፡፡
#ለመረጃ

አሜሪካ የዛሬ ሁለት አመት (Sep 17, 2021) ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ጋር በተያያዘ ጥላው የነበረው ማዕቀብ እንዲቀጥል (ለሁለተኛ ጊዜ) ፕሬዝደንት ባይደን በትናንትናው እለት ወስነዋል።
#በዓል_እና_የዋጋ_ንረት!


የበዓላት ወቅቶችን ተከትለው ለተለያዩ ቁሳቁሶች እና አገልግሎቶች የሚጠየቀው ዋጋ በተለየ መልኩ ከፍተኛ ነው! ለመሆኑ የተለያዩ በዓላትን ተከትሎ የዋጋ መናር በጣም የተለመደ ነገር የሆነው ለምንድን ነው?……


1. ለዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ምክንያቱ በዋናነት በፍላጎት ማደግ (Demand Side) ነው ብዬ አስባለሁ፤ ይህም ማለት ለበዓላት አብዛኞቹ ኢትዮጲያዊያን የበዓላትን አከባበር በእምነት በመያዝ መስፈርት አውጥተው ያከብራሉ፤ እነሱም የቻለ በግ በማረድ፤ ቅርጫ በመግባት፤ ዶሮ በማረድ፤ ጠጅ በመጣል፤ ጠላ በመጥመቅ፤ አዳዲስ ልብስ በመግዛት፤ ቤት በማደስ፤ የቤት እቃ በመለወጥ፤ ቅቤ በመግዛት፤ እንቁላል በመግዛት፤ የስንዴ ዱቄት በመግዛት ወዘተ እነዚህ የበዓል ግብዓቶች እንደሆኑ ሸማችም አቅራቢም በደንብ ተረድተዋል፤ ስለዚህ ነጋዴዎች ከተቀመጠው መስፈርት ላለማነስ የሸማች ቤተሰቦች በጨመረው ዋጋ መሸመት ግዴታ ውስጥ መሆናቸውን በመረዳት ዋጋን ይሰቅላሉ፡፡


2. ''ለበዓላት የሁሉም ነገር ዋጋ በሻጭ እና በአምራች ይወሰናል'' ምክንያቱም ከአቅርቦት እጅግ የበለጠ የድሃውም የሃብታሙም የህብረተሰብ ክፍል ፍላጎት በመኖሩ ወቅቱን ተከትሎ ሻጭም አምራችም ዋጋ ይጨምራሉ፡፡


3. ምርጥ ምርጡን ለበዓል! (ለበዓል ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ!!) የሚል አስተሳሰብ ሸማች ስላለው በውድ ዋጋ የመግዛት ግዴታ ውስጥ መግባቱ የተለመደ ነው፤ ይህም ውድ ዋጋ መጥራትን (Psychological Price) ልምድ እንዲሆን አድርጓል!


4. በበዓላት ወቅት የጨመረውን የፍላጎት መጠን የሚመጥን አቅርቦት አለመኖርም አንዱ ችግር ነው፤ በተለይ አብዛኛዎቹ ለበዓላት ለምግብነት የሚቀርቡ ቁሳቁሶች የሀገር ውስጥ ምርት መሆናቸው ችግሩን ያባብሰዋል ለምሳሌ፡- በሬ፤ በግ፤ ፍየል፤ ዶሮ፤ እንቁላል፤ ቅቤ፤ በርበሬ ወዘተ….


አሁን ላይ የደረስንበት የኢኮኖሚ ሁኔታ ምንም ነገር ያልጎደለበት የበዓል ፕሮግራም ለማዘጋጀት የሚያስችል ባለመሆኑ ሸማቾች ከአቅማቸው በላይ የሆነ እና ቁጠባቸውን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያናጋ የበዓላት ወጪ ከማድረግ ቢቆጠቡ፤ ሁሉም የሚኖረው የዘንድሮ አቅሙን ያህል ብቻ መሆኑን ማመን፤ የዋጋ ንረት ከሚባባስበት ወቅት ቀደም አድርጎ መሸመት፤ የዋጋ ንረት ያልተባባሰበት ቦታ በግሩፕ ሆኖ መሸመት፤ ወዘተ በማድረግ እንኳን በዓል ሆኖ እንዲሁም እየተባበሰ ያለውን የዋጋ ንረት በጥቂቱ በቤተሰብ ደረጃ ለመቀነስ ያግዛል፡፡


መንግስትም ከላይ የተዘረዘሩትን አባባሽ ምክንያቶች ለመከላከል ጣልቃ ገብ የአቅርቦት ስራ እና የገበያ ራሽናሊቲ ለመጠበቅ የሚያግዙ የቁጥጥር ስራ በመስራት ችግሩን ለማቃለል ቢሞክር ጥሩ ነው፡፡


በሀገራችን የህዝባችን ፍላጎት እንዲያድግ ተደረገ እንጂ ግዚያዊ (ወቅቶችን) ሳይጠብቅ Consumption ላይ በሰፊው እንዲሳተፍ አልተደረገም፤ ለዚህም ይመስላል ዓመታዊ ከፍተኛ Consumption ወይም ቁጠባውን የበዓላትን ግዚያት አስታኮ ሲጠቀም የምንመለከተው! ጠቅላላ ሀገራዊ ምርት በወቅቶች ተከፋፍሎ ቢሰላ የኢትዮጲያ GDP ከፍ የሚለው በበዓላት ወቅት ባለ ግብይት ነው፡፡
ቡድን 20 "#ታሪካዊ_ነው" በተባለ ውሳኔ የአፍሪካ ኅብረትን አባል አድርጎ ተቀበለ።


በቡድን 7 (G7)፤ በቡድን 8 G8)፤ በቡድን 20(G20) እና በBRICS የዓለም ሀገራት የሚደራጁበት ምክንያት እና በሁሉም ቡድኖች መካከል ያለ ልዩነት ምንድን ነው!


ቡድኖቹ የበለፀጉ ሀገራት ቢሆንም በየዓመቱ የስብሰባ ውሳኔዎቻቸውን በጉጉት የሚጠብቁት ደግሞ ያላደጉት ድሃ ሃገራት ናቸው።


https://youtu.be/ZY2EB3EI2Y0
2016 ዓ.ም ውጤታማ ዓመታችሁ ይሁን!
በሀገር ውስጥ በህገወጥ (Fake) ብር እና ዶላር መታተሙ ያለው ስጋት ምንድን ነው?


ዶላር የአሜሪካ ህጋዊ ገንዘብ ነው! የመጠቀም መብት ብቻ ባላት ኢትዮጵያ ውስጥ በህገወጥ መንገድ መታቱሙ ስጋቱ ለማን ነው?


ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን https://www.youtube.com/watch?v=HlYmsqvabGA ትንታኔ ይመልከቱ!
የዛሬ 10 ዓመት 250ሺ ብር የተገዛ መኪና አሁን ላይ ስንት ብር ቢሸጥ ያዋጣል? በኢኮኖሚክስ አመክንዮ ካሰብነው በ150,000ብር መሸጥ ነበረበት! ነገር ግን ከወቅታዊ የዋጋ ንረት አንፃር ካሰብነው ቢያንስ 1,547,766 ብር ቢሸጥ ክስረት አይደለም! እንዴት እንደሚሰላ እንመልከት? https://youtu.be/teYYG3AGgEE
ጠያቂ፦ " ዋስይሁን የዛሬ 10 ዓመት 250ሺ ብር የተገዛዋትን Dx መኪና በዚህ ወር 1.2 ሚሊየን ብር ሸጥኳት! ከስሪያለሁ ወይስ አልከሰርኩም? ስንት ብር ብትሸጥ ያዋጣ ነበር?"

ያገለገለ እቃ ለመሸጥ ዋጋ እንዴት እንደሚሰላ እንመልከት? https://youtu.be/teYYG3AGgEE
አንድ ዶላር በአንድ ብር እንዲመነዘር ቢወሰን የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ በወራት ውስጥ ምን ያስተናግዳል?


በስልጣን ደረጃ የኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ (መንግስት) ከዛሬ ጀምሮ አንድ ብር ከአንድ ዶላር ጋር እኩል ነው ብሎ መወሰን ይችላል!


ምን አልባት (በኢኮኖሚክሰኛ Let Assume ተብሎ እንደሚጀመረው) በውሳኔ (Artificial Exchange Rate) ተጠቅሞ መንግስት አንድ ዶላርን ከአንድ ብር ጋር እኩል ቢያደርግ ሊገጥሙት የሚችሉት ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊ፤ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ችግሮች ምንድን ናቸው ?


https://youtu.be/Xg8JMetAv5E
እንኳን ለኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ! መልካም በዓል ይሁንላችሁ!
የዘንድሮ 2023ዓ/ም በኢኮኖሚክስ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት አሜሪካዊቷ ኢኮኖሚስት #ክላውዲያ_ጎልዲን አሸናፊ መሆኗ ታውቋል (በ56ዓመት ታሪክ ውስጥ ሶስተኛዋ ኖቤል አሸናፊ ሴት ኢኮኖሚስት ሆናለች በ2008 ኤልኖር ኦስትሮም እና በ2019 ዱፍሎ መውሰዳቸው ይታወቃል)፡፡

ለመመረጥ ያስቻላት ተግባር ሴቶች በሰራተኛ ገበያው ውስጥ የተሳትፏቸውን ያህል ተከፋይ አለመሆናቸው ለማረጋገጥ ከ200ዓመታት በላይ የተከማቹ መረጃዎችን/ዳታ በመመርመር የክፍያ ስርዓቶች እየተለወጡም ቢሆንም ሴቶች ከወንዶች አንጻር በሰራተኛ ገበያ ውስጥ አነስተኛ ክፍያ ሲያገኙ መኖራቸውን እና ምክንያቶቹን በጥናት በማሳየቷ የ‘for having advanced our understanding of women’s labor market outcomes‘ ነው፡፡

የኖቤል ሽልማት ከ1901 እስከ 2023 ለ122ዓመታት የተሰጠ ሲሆን፤ እውቅናው ከተጀመረ ጀምሮ በአምስት ዘርፎች (በኬሚስትሪ፤ በስነ-ጽሁፍ፤ በሰላም፤ በፊዚክስ፤ በህክምና) በየዓመቱ የተለያዩ ሽልማቶች ሲሰጥ ቆይቶ፤ ከ1969 ጀምሮ የኢኮኖሚክስ ዘርፍን አካቶ እስከ ዘንድሮ ዓመት ድረስ በ56 ጊዜ ውስጥ ለ93 ኢኮኖሚስቶች የኖቤል ሽልማት ተበርክቷል፡፡

ከ1969-2023ዓ/ም ድረስ ለ56 ጊዜ በኢኮኖሚክስ ዘርፍ ኖቤል ተሰጥቷል፤ 93 ኢኮኖሚስቶች ኖቤል ተቀብለዋል (ባለፉት ቀናት በ5ቱ ዘርፎች ተሸላሚዎች የታወቁ ሲሆነ በመጨረሻ የሚገለጸው የኢኮኖሚክስ ዘርፍ በመሆኑ ዛሬ አሸናፊዋ ታውቃለች)፤ ዘንድሮ 999,137ዶላር፤ ዲፕሎማ እና የወርቅ ሜዳልያ በሽልማትነት ይሰጣል፡፡ የሽልማት ፕሮግራሙ በቀጣይ ወር (December 10, 2023) ይካሄዳል፡፡
በየዓመቱ ሀገራት የጠቅላላ ሀገራዊ ምርት መጠን (GDP) እድገትን ሪፖርት ያደርጋሉ! እንዴት ይሰላል? በኢትዮጵያ የGDP አድገት ቁጥር  ክርክር አያጣውም!


በቀላል ለመረዳት የሚከተለውን https://youtu.be/f8MZGRpyfpA በምሳሌ የተቀመጠ ቀመር ተመልከቱ።
ወደብ ጠቃሚ ሆኖ አንገብጋቢ የማይሆንበት ወቅት ይኖራል! የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ያለ ወደብ ባለቤትነት በጠቅላላ ሀገራዊ ምርት መጠን (GDP) ደካማ የሚባል አይደለም! (በአፍሪካ ከ100ቢሊዮን ዶላር በላይ GDP ካላቸው ጥቂቶች መካከል አንዱ ነው (የIMF ሪፖርት ዋቢ ከተደረገ!)። ይህ ቁጥር ሰፋፊ ወደብ ካላቸው የምስራቅ እና የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር ግዙፍ ነው።

በዓለም ላይ 44 ሀገራት የወደብ ባለቤትነት የላቸውም! ከአፍሪካ 16 ሀገራት፤ ከአውሮፓ 16 ሀገራት (የበለጸጉትን ሉግዘምበርግ፤ ኦስትሪያ እና ሲዊዘርላንድን ጨምሮ) እና ከላቲን አሜሪካ 2 ሀገራት (ቦሊቪያ እና ፓራጓይ)፡፡ በዓለም ላይ ካዛኪስታን እና ኢትዮጲያ ግዙፍ ቆዳ ስፋት ይዘው ወደብ አልባ ከሚባሉት ሀገራት መካከል ናቸው፡፡

በዓለም ላይ ጎረቤቶቻቸው ሳይቀር ወደብ አልባ የሆኑ ሀገራት (Double Landlocked Countries) ሁለት ሲሆኑ፡ Liechtenstein (ጎረቤቶቿ ኦስትሪያ እና ሲዊዘርላንድን ሲሆኑ ወደብ የላቸውም) እና Uzbekistan (በአምስት ወደብ አልባ ሀገራት ተከባለች) ናቸው፡፡

ብዙ ድሃ ሀገራት ወደብ ቢኖራቸውም በየብስ ከጎረቤቶቻቸው ጋር የንግድ ግንኙነት በማድረግ ከወደብ የሚገኝን እድል ያልተጠቀሙ አሉ (ደካማ የውጪ ንግድ ተሳትፎ አላቸው)፡፡ የሱዳን፤ የጅቡቲ፤ የኤርትራ፤ የሴራሊዮን፤ የላይቤሪያ፤ የጊኒ፤ የቡርኪና ፋሶ፤ በአፍሪካ የግዙፍ ወደብ ባለቤቶች መካከል ሞዛምቢክ እና ማዳጋስካር፤ ወዘተ ኢኮኖሚ ከወደብ ጋር በጣም ደካማ ነው፡፡

ወደብ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚ የውጪ ንግድን ከማሳደግ ጀምሮ የውጪ ባለሃብቶችን እስከመሳብ የደረሰ ሰፊ እድል ይሰጣል፡፡ በፖለቲካል ሪፎርም የተነሳ ወደብ አልባ ቢሆኑም ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ያሉት ቦትስዋና እና ሩዋንዳ ደግሞ ከወደብ ውጪ ኢኮኖሚ ሪፎርም ሊደረግ እንደሚችል ያሳያሉ፡፡

ኢኮኖሚ ከወደብ ሊያስቀድመው የሚችለው አንገብጋቢ ችግር ሊኖርበት ይችላል! በብዙ የአፍሪካ ሃገራት ፖለቲካል አለመረጋጋት ኢኮኖሚውን ወደብ ከማጣቱ በተጨማሪ ይፈትነዋል፡፡ ለምሳሌ፡ ባለፉት 3 ዓመታት ማሊ፤ ሱዳን፤ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር በድምሩ ወደ 7 ጊዜ በመፈንቅለ መንግስት ድርጊት እና ሙከራ ኢኮኖሚያቸው ይንገዳገዳል)፡፡

ኢትዮጲያ 9 የየብስ የወደብ በሮች ሲኖራት 95 ከመቶ የውጪ ንግዷን በጅቡቲ ወደብ በመጠቀም ከቢሊየን ዶላር በላይ በዓመት ታወጣለች፡፡ የወደብ ባለቤት ሆና ቢሆን ኖሮ የውጪ ንግድ መጠኗን ከማሳደጓ በተጨማሪ የወደብ ክፍያን በማስቀረት በዓለም ገበያ በቀነሰ የትራንስፖርት ዋጋ በሚቀርብ ምርት የገበያ ተፎካካሪነቷን ማሳደግ ትችል ነበር፡፡

ነገር ግን አሁን ላይ ፖለቲካሊ በነበረ ሂደት ወደብ በኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ውስጥ የለም! ወደብ አስፈላጊ ቢሆንም በወቅታዊ ሁኔታ አንገብጋቢው የውስጥ ፖለቲካል አለመረጋጋት እና የምርት አቅም መዳከም ነው፡፡ ፖለቲካል አለመረጋጋት የወደብም ሆነ የከፍተኛ ማዕድን ባለቤት ለሆኑ የአፍሪካ ሀገራት እያመጣ ያለው መከራ ከባድ ነው፡፡

ኢትዮጲያ በሊበራላይዜሽን መርህ Comparative Advantage የያዘችባቸውን ሴክተሮች (በጋራ ተጠቃሚነት ስልት) ኢኮኖሚያዊ እድል በምታገኝባቸው የውጪ ኢንቨስትመንቶች ላይ በመሳተፍ ወደብ ለማግኘት ብትችል መጥፎ አይሆንም፡፡ ነገር ግን ወደብ ለማግኘት ሰፊ Opportunity Cost ያለውን አይነት መንገድ (ጦርነት ተያይዞም ዓለም አቀፍ ውግዘት) ከተከተለች ግን ኢኮኖሚው ይበልጥ ፈተና እንዳያገኘው ያሰጋል፡፡