The Ethiopian Economist View
29.3K subscribers
723 photos
4 videos
197 files
1.33K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
ለአንድ ትሪሊዮን ብር የቀረበው የ2017 በጀት ጉዳይ!

የ2016 በጀት 801 ቢሊየን ብር ላይ 169 ቢሊየን ብር በመጨመር 971 ቢሊየን ብር ለ2017 የኢትዮጵያ በጀት ሆኖ ቀርቧል!

የ2017 በጀት ከ2016 አንፃር የ21 ከመቶ ብልጫ አለው! ለአንድ ትሪሊዮን ብር የቀረበ በጀት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ መሸከም ይችላል?

የበጀቱ ከፍተኛ ጭማሪ መሰረታዊ ምክንያቶች ምንድን ሊሆኑ ይችላሉ? የበጀቱ መጠን ስጋት እና እድል ምን ሊሆን ይችላል?

https://youtu.be/kAJnEEwYt7U
የዋጋ ንረት፤ የGDP እድገት፤ የበጀት ጉድለት እና የሃገር ውስጥ ዕዳ ክፍያ ስልት ላይ አስተያያት ለመስጠት ያህል!

#መንግስት፡- የዋጋ ዕድገት በ2017ዓ/ም ዘንድሮ ካለበት 27.4% ወደ 12% ዝቅ እንደሚል ታሳቢ ተደርጓል!

#አስተያየት፡- በኢትዮጲያ የዋጋ ንረቱ በተለያዩ ምክንያቶች ላለፉት አምስት ዓመታት 2012 (20.3%)፣ 2013 (26.8%)፣ 2014 (33.9%)፣ 2015 (30.5%)፣ 2016 (27.5%) ይህ መረጃ የሚያሳየው የዋጋ ንረቱ ከ2012-2014 በየዓመት ቢያንስ በ6 ከመቶ የመጨመር እና ከ2014-2017 ደግሞ በየዓመቱ በ3 ከመቶ ባልበለጠ የመቀነስ ልምድ ነው ያለው! በዕቅድ ደረጃ በየዓመቱ የዋጋ ንረቱን ወደ ነጠላ አሃዝ ለማውረድ ይታቀዳል!

ነገር ግን ከተሞክሮ እና ከሚገመቱ እድሎች በመነሳት ለቀጣይ 2017 በዓመት ውስጥ ከእጥፍ በላይ የዋጋ ንረቱ ሊቀንስ ይችላል ማለት ከባድ ነው (በርግጥ የዓለም የገንዘብ ድርጅት ትንበያ በቀጣይ ዓመት የዋጋ ንረቱ ወደ 18ከመቶ ዝቅ የማለት እድል ሊኖረው እንደሚችል ይተነብያል!)፡፡

#መንግስት፡- በ2016 በጀት ዓመት የ7.9 በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዘግብ ተገምቷል። በ2017 በጀት ዓመት ኢኮኖሚው የ8.4 በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዝግብ ተተንብዮአል፡፡

#አስተያየት፡- የዓለም የገንዘብ ድርጅትም ሆነ የአፍሪካ ልማት ባንክ ትንበያ ከ6 እስከ 6.5በመቶ የጠቅላላ ሃገራዊ ምርት መጠን ሊኖር እንደሚችል ያመላክታል! ስለዚህ ተጨማሪ የመንግስት የወጪ መጠን መጨመር አገራዊ ምርትን ማሳደጉ ስለማይቀር እስከ 7 ከመቶ የጠቅላላ ሃገራዊ ምርት መጠን (GDP) እድገት ሊመጣ ይችላል፡፡ መሰረታዊው ነጥብ GDP የሚጨምረው ከመንግስት ወጪ መጠን ከመነሳት ይልቅ የዜጎች የመሸመት አቅም መሻሻል (Consumption) እና የግል ዘርፉ የማልማት አቅም ማደግን (Investment) ተከትሎ መሆኑን ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡

#መንግስት፡- የበጀት ጉድለቱ ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ 2.1 በመቶ ነው፡፡

#አስተያየት፡- በ2017 በጀት ዓመት ጠቅላላ የፌዴራል መንግሥት ገቢ የውጭ ርዳታን ጨምሮ ብር 612.7 ቢሊዮን እንደሚሆን ተግምቷል! ስለዚህ ሊያወጣ ካቀደው 971 ቢሊየን ብር መካከል የ358.5 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ የበጀት ጉድለት ታይቷል። የኢትዮጲያ GDP መጠን የመጨረሻ የዓለም የገንዘብ ድርጅት ትንበያ ብንመለከት 205 ቢሊየን ዶላር (11 ትሪሊየን ብር) ቢሆን 358 ቢሊየን ብር/11ትሪሊየን ብር 3 ከመቶ የበጀት ጉድለት ይኖረዋል! ይህ ቁጥር መጥፎ የሚባል አይደለም!

#መንግስት፡- ለመደበኛ ወጪ ከተደለደለው በጀት ለዕዳ ክፍያ የተያዘው በጀት ብር 139.3 ቢሊየን ብር:: ለዕዳ ክፍያ ከተያዘው በጀት ውስጥ 54.8 በመቶ ለሀገር ውስጥ ዕዳ ክፍያ እንዲሁም ቀሪ 45.2 በመቶ ደግሞ ለውጭ ሀገር ዕዳ ክፍያ የሚውል ነው።

#አስተያየት፡- ይህ ኢኮኖሚ ሌላ ስልት ካላዘጋጀ በስተቀር ያለበትን የበጀት ጉድለት ለመሙላት ያቀደው የመንግስት የግምጃ ቤት ሰነድ በመሸጥ እና የመካከለኛ ረጅም ጊዜ ቦንድ ለሽያጭ በማቅረብ ነው! ነገር ግን የሃገር ውስጥ እዳን ለማቃለል እየሞከረ ተጨማሪ ሰፊ የብር መጠን ለመበደር እያሰብ መሆኑ ወደ ፊት ተንከባላይ የሀገር ውስጥ እዳን እንዳያከማች የሚያሰጋ ነው!
Budget1.pdf
570.3 KB
2017 Budget Speech!
ስለ ኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ update ለሚፈልጉ እና ወደፊት በካፒታል ገበያው ለመሳተፍ ለሚያስቡ ስለ ኢንቨስትመንት ባንኮች እንቅስቃሴ እድል እና ውስን ስጋት ዙሪያ መረጃ ለማግኘት የሚረዳ ጥሩ ቪዲዮ!
https://youtu.be/LdhfvBSoui8?si=0W8sULTm6rFFdDT5
የኢኮኖሚ እድገት (GDP) እና የዋጋ ንረት ያላቸው ግንኙነት ቀጥተኛ ወይስ ተዘዋዋሪ?

የኢኮኖሚ እድገት አለ ከተባለ ዜጎች ለምን በዋጋ ንረት ይፈተናሉ?

የኢኮኖሚ እድገት እያለ የዋጋ ንረት ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል! ለምን?

በኢትዮጵያ ከ6 ከመቶ በላይ የGDP እድገት ቢኖርም የዋጋ ንረት በተመሳሳይ ከፍተኛ ነው! ለምን?

በምሳሌ፦ የህንድ፤ የግብፅ፤ የኬንያ እና የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት እና የዋጋ ንረት Trends ምን እንደሚመስል ከIMF መረጃ በመነሳት እናነፃፅር!

የተጠቀሱትን ሃሳቦች ትንታኔ ለመመልከት
https://youtu.be/gEXCjOYmtr4?si=9APK0RhkBW5kwg1o
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ እህት/ወንድሞቻችን፣ እንኳን ለኢድ አል‐አድሀ በዓል አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!
የፌደራል_መንግስት_ሠራተኞች_ረቂቅ_አዋጅ_አጭር_ማብራሪያ_1.pdf
468.8 KB
የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅ ማብራሪያ።
የኢኮኖሚ እድገት (GDP) እና የዋጋ ንረት ያላቸው ግንኙነት ቀጥተኛ ወይስ ተዘዋዋሪ?

የኢኮኖሚ እድገት አለ ከተባለ ዜጎች ለምን በዋጋ ንረት ይፈተናሉ?

የኢኮኖሚ እድገት እያለ የዋጋ ንረት ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል! ለምን?

በኢትዮጵያ ከ6 ከመቶ በላይ የGDP እድገት ቢኖርም የዋጋ ንረት በተመሳሳይ ከፍተኛ ነው! ለምን?

በምሳሌ፦ የህንድ፤ የግብፅ፤ የኬንያ እና የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት እና የዋጋ ንረት Trends ምን እንደሚመስል ከIMF መረጃ በመነሳት እናነፃፅር!

የተጠቀሱትን ሃሳቦች ትንታኔ ለመመልከት
https://youtu.be/gEXCjOYmtr4?si=9APK0RhkBW5kwg1o
ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን #ደረሰኝ ያላቀረበ ንብረቱ እንዲወረስ የሚደነግግ አዋጅ ቀረበ!

የዚህ ረቂቅ አዋጅ አመክንዮ በመጪው ጊዜ የዲያስፖራው የኢንቨስትመንት ውሳኔ ላይ ተፅዕኖ ሊያመጣ ይችላል!

ረቂቅ አዋጁ ለተላከ የውጪ ምንዛሬ ደረሰኝ ያለማቅረብ ገፊ ምክንያት፤ በቀጣይ የፍጆታ የውጪ ምንዛሬ አጠቃቀም ማደግ እና ከማስተማር ለማትረፍ በትናንት ስህተት ዛሬ ያለመጠየቅ ሁኔታ ላይ ማተኮር ሊኖርበት ይገባል! https://youtu.be/vO4SPPHxzUg

ረቂቅ አዋጁን እና የረቂቅ አዋጁን ማብራሪያ ለምትፈልጉ ቴሌግራም https://t.me/WaseAlpha አለ።

ጥናት ስትሰሩ ማመን ያለባችሁ ማንን ነው (የጥናት ሳይንሱን፤ Advisor ወይስ Examiner?

ለመመረቂያ ጥናት የምትሰሩ ሰዎች የጥናት ሳይንስን ተከትሎ በመስራት፤ Advisor የሚሰጠውን አቅጣጫ ተከትሎ በመስራት እና በመጨረሻ ሰዓት Examiner ሊያምንበት ይችላል ብሎ አስቦ በመስራት መካከል መጨነቅ አለ!

ስለዚህ ሳይንሱንም (Research Methodology)፤ አማካሪውን (Advisor) እና የመጨረሻ ገምጋሚውን (Examiner) ባስማማ መልኩ ጥሩ ጥናት እንዴት ልትሰሩ እንደምትችሉ እንመልከት! https://youtu.be/xQasy9NF6ec

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ሴክተር #የውጪ_ባንኮች እንዲገቡ ተፈቅዷል......

1. ለምን የውጪ ባንኮች እንዲገቡ ተፈቀደ (የሀገር ውስጥ ባንኮች ያሏቸው ባህሪያት)?

2. የትኖቹ የውጪ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ይችላሉ? ምክንያቶቿቸው ምን ሊሆኑ ይችላሉ? ላለመግባት ሊያደርጓቸው የሚችሉ ስጋቶችስ?

3. የውጪ ባንኮች የመግባታቸው ኢኮኖሚያዊ እድሎች (ለህዝብ፤ ለባላሃብት፤ ለሀገር ውስጥ ባንኮች እና ለመንግስት)?

4. የውጪ ባንኮች በመግባታቸው ሊፈጠሩ የሚችሉ ስጋቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

5. የውጪ ባንኮች በመግባታቸው የሀገር ውስጥ ባንኮች የቀጣይ እጣፈንታ ምን ሊሆን ይችላል?

ይህንን ሰፊ ትንታኔ ለመመልከት https://youtu.be/DXlPXzdlHcQ

በኢትዮጲያ የምንዛሬ ተመን ደረጃ ከብር አንጻር የአሜሪካን ዶላር 5ኛ ነው! የኩዌት ዲናር (1ኛ)፤ የእንግሊዝ ፓውንድ (2ኛ)፤ ይሮ (3ኛ) እና የሲዊዝ ፍራንክ (4ኛ) መንግስት ይህንን የምንዛሬ ተመን ለምን ይወስናል?

በ2024 በዓለም ላይ 10 ጠንካራ የተባሉ ገንዘቦች ዝርዝር ወጥቷል! The Highest-Valued Currencies in the World in 2024 (#የአሜሪካ_ዶላር 10ኛ ደረጃ ላይ ነው! ለምን?)

በውሳኔ ጠንካራ ከሆነው የኩዌት ዲናር እና ፍጹም የተረጋጋ ምንዛሬ እንደሆነ ከሚታመንበት የሲዊዝ ፍራንክ እስከ የዓለም ተጽኖ ፈጣሪው የአሜሪካ ዶላር የምንዛሬውን ሁኔታ ብንመለከት የኢኮኖሚ እድገት ደረጃ፤ የፖለቲካ መረጋጋት፤ የተፈጥሮ ሃብት (መጠቀም)፤ የዓለም አቀፉ ገበያ ለምንዛሬዎቹ ያላቸው ፍላጎት የየሀገራቱን ገንዘብ አቅም እና ደረጃ ይወስናል፡፡

የዚህን ዝርዝር ለመመልከት https://youtu.be/rpko9lC_m5g

የተባበሩት መንግስታት በዓለም ላይ ለ180 ሀገራት ገንዘቦች እውቅና ሰጥቷል፡፡ ገንዘብ አንድን ቁስ ለመግዛት ያለው አቅም እና ሌሎች ምንዛሬዎች ለሱ ያላቸው ፍላጎት ጠንካራ እና ደካማ ሊያስብለው ይችላል፡፡ በተጨማሪም በአንድ ሀገር ውስጥ ያለው የውጪ ምንዛሬ ክምችት፤ የዋጋ ንረት፤ የወለድ ምጣኔ፤ የኢኮኖሚ እድገት እና የማዕከላዊ ባንኮች የፖሊሲ ሁኔታ ምንዛሬውን ጠንካራ አልያም ደካማ ተብሎ እንዲፈረጅ ሊያደርገው ይችላል፡፡

10 የዓለማችን ጠንካራ ምንዛሬዎች!

ከአሜሪካ ዶላር አንጻር ያላቸውን ዓለም አቀፍ የምንዛሬ መጠን በመመልከት ለመለካት ያህል….

10ኛ. የአሜሪካ ዶላር (ጠንካራ የመገበያያ እና የውጪ ምንዛሬ ክምችት ገንዘብ ነው)

9ኛ. ይሮ (አንድ ይሮ በ1.08 ዶላር ይመነዘራል! የዓለም ሁለተኛው ግዙፍ መገበያያ እና የውጪ ምንዛሬ ክምችት የ19 አባል ሀገራት መገበያያ ገንዘብ ነው)

8ኛ. የሲዊዝ ፍራንክ (አንድየሲዊዝ ፍራንክ በ1.10 ዶላር ይመነዘራል! የተረጋጋ ምንዛሬ ከሚባሉት መካከል ሲሆን! የሲዊዘርላንድ እና ሊቺተንስቲን ገንዘብ ነው)

7ኛ. Cayman Islands (ካሪቢያን ደሴት) አንድ የካይማን ደሴት ዶላር በ1.20 ዶላር ይመነዘራል!) 68ሺ ነዋሪ ያለባት የእንግዚዝ ቅኝ ግዛት ነች!

6ኛ. ጅብራአልታር ፓውንድ (አንድ የጅብራአልታር ፓውንድ በ1.26 ዶላር ይመነዘራል!) 32ሺ ነዋሪ ያለባት የእንግዚዝ ቅኝ ግዛት ነች!

5ኛ. የእንግሊዝ ፓውንድ (አንድ የእንግሊዝ ፓውንድ በ1.26 ዶላር ይመነዘራል!)

4ኛ. የጆርዳን ዲናር (አንድ የጆርዳን ዲናር በ1.41 ዶላር ይመነዘራል!) የጆርዳን ዲናር በ1950 የፓለስቲን ፓውንድን ከለወጠ ጀምሮ በመንግስት ውሳኔ ምንዛሬውን ያስተዳድራል!

3ኛ. የኦማን ሪያል (አንድ የኦማን ሪያል በ2.60 ዶላር ይመነዘራል!) የኦማን ሪያል የህንድን ሩፒ መገበያያ አድርጎ ይጠቀም ነበር ነገር ግን ከፍተኛ የነዳጅ ሃብትን ተከትሎ ከለወጠ ጀምሮ በመንግስት ውሳኔ ምንዛሬውን ያስተዳድራል!

2ኛ. የባህሪን ዲናር (አንድ የባህሪን ዲናር በ2.65 ዶላር ይመነዘራል!) የባህሪን ዲናር የአሜሪከ ዶላርን ተጨማሪ መገበያያ አድርጎ ይጠቀም ነበር ነገር ግን ከፍተኛ የነዳጅ ሃብትን ተከትሎ ከለወጠ ጀምሮ በመንግስት ውሳኔ ምንዛሬውን ያስተዳድራል!

1ኛ. የኪዌት ዲናር (አንድ የኩዌት ዲናር በ3.25 ዶላር ይመነዘራል!) የኪዌት ዲናር በ1960 ከተዋወቀ ጀምሮ ሀገሪቷ ካላት ከፍተኛ የነዳጅ ሃብት ጠንካራ ኢኮኖሚ እና ከታክስ ጫና የሆነ የንግድ አማራጭ ከመሆኑ በተጨማሪ መንግስት በውሳኔ ምንዛሬውን ያስተዳድራል!

በውሳኔ ጠንካራ ከሆነው #የኪዌት_ዲናር እና ፍጹም የተረጋጋ ምንዛሬ ከሆነው #የሲዊዝ_ፍራንክ እስከ የዓለም ተጽኖ ፈጣሪው #የአሜሪካ_ዶላር የምንዛሬውን ሁኔታ ብንመለከት የኢኮኖሚ እድገት ደረጃ፤ የፖለቲካ መረጋጋት፤ የተፈጥሮ ሃብት (መጠቀም)፤ የዓለም አቀፉ ገበያ ለምንዛሬዎቹ ያላቸው ፍላጎት የየሀገራቱን ገንዘብ አቅም እና ደረጃ ይወስናል፡፡