The Ethiopian Economist View
29.3K subscribers
723 photos
4 videos
197 files
1.33K links
Wase.belay12@gmail.com(0913243956)
Download Telegram
#ለመረጃ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከሚሰጡ አገልግሎቶች የክፍያ ታሪፍ ማሻሻያ የተደረገባቸው ጠቅላላ ዝርዝር።
ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ከግል ሴክተሩ ሲጠበቅ ከመንግስት መጣ....

ከIMF ጋር የተደረገው የኢኮኖሚ ሪፎርም የሀገር ውስጥ ገቢ ማሳደግ እና የመንግስት ተቋማትን የፋይናንስ አቅም ማሳደግ የሚል ስምምነት አለበት።

የዚህን ስምምነት መሰረት ባደረገ መልኩ መንግስት የተቋማቱን የአገልግሎት ክፍያ እና ታሪፍ እያሻሻለ (ጭማሪ እያደረገ) ነው።

ለምሳሌ በሁለት ቀን ውስጥ.....

#ተሽከርካሪ (ከመስከረም 20 ጀምሮ)

#ኢትዮቴሌኮም (ከመስከረም 21 ጀምሮ)

#CBE ተጨማሪ እሴት ታክስ (ከመስከረም 21 ጀምሮ)

ከሪፎርም በኋላ የታሪፍ ጭማሪ የሚጠበቅ ቢሆንም በተከታታይ እና በከፍተኛ መጠን መሆኑ ያለውን አሉታዊ ጫና እንመልከት.....https://youtu.be/3dkRSrPslJs
Channel photo updated
#ለመረጃ

የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ዛሬ ጠዋት ተሰብስቦ ነበር። በቅርብ የተደረገውን የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎች አፈፃፀም መገምገሙም ተሰምቷል።

ይህን ተከትሎ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፥ "ፖሊሲው ተፈፃሚ በሆነባቸው ሁለት ወራት የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ከባቢን መመልከት ችለናል" ሲሉ ገልጸዋል።

"በተመሳሳይ የገቢ ግባችን የተቀመጠለትን ግብ በመምታት በታለመለት መንገድ ላይ ይገኛል" ብለዋል።

"በአጠቃላይ ያለፉት ሁለት ወራት ፖሊሲው በስኬታማ አፈፃፀም ላይ መሆኑን አሳይተዋል" ሲሉ ገልጸዋል።
#ለመረጃ

በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሕግ መሰረት ባንኮች በሚሰጧቸው  አገልግሎቶች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲጥሉ ታውጇል፡፡

ስለሆነም የመንግሥት እና የግል ባንኮች ከመስከረም 21 ቀን 2017 ዓ. ም ጀምሮ በባንክ አገልግሎቶች ላይ በሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ታሪፍ ጨምረዋል።
#መረጃ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች (Forex Bureau) የስራ ፈቃድ ሰጠ!
የውጪ ምንዛሬ ቢሮዎቹ…

ዶላር #መግዛት የሚችሉት (ብር ሰጥተው ዶላር የሚቀበሉት)….

ከማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት እስከ 10ሺ ዶላር!

የጉምሩክ ዲክላራሲዮን (ከውጪ በካሽ ይዘው የገቡትን ዶላር የተመዘገበበትን ማረጋገጫ ከሚያቀርቡ) የቻሉትን ያህል ዶላር መግዛት ይችላሉ!

ዶላር #መሸጥ የሚችሉት (ብር ተቀብለው ዶላር የሚሰጡት)

ወደውጪ ለመሄድ አስፈላጊውን የጉዞ ሰነድ ለሚያቀርቡ የግል ተጓዦች (ለምሳሌ ቪዛ) እስከ 5ሺ ዶላር ሊሸጡ ይችላሉ!

ለንግድ ስራ ተጓዦች (አስመጪ ሊሆን ይችላል) እስከ 10ሺ ዶላር ሊሸጡ ይችላሉ!
#ለማስታወስ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችን (Forex Bureau) ለመክፈት የሥራ ፈቃድ መስፈርት...


የግል የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎችን (Forex Bureau) ምን ማለት ነው?

ፍቃድ ለማውጣት መስፈርቱ ምንድን ነው?

ቢሮዎቹ እንዴት ይሰራሉ?

ቢሮዎቹ ከጥቁር ገበያ እና ከንግድ ባንኮች ምን ይለያቸዋል?

የኢትዮጵያ የፍቃድ መስፈርት ከጎረቤት ሀገራት በምን ይለያል?

ይህንን በተመለከተ የሚከተለውን መረጃ አዘጋጅቻለሁ....https://youtu.be/9TmBUDGcwug
"በባንኮች ያለው የውጭ ምንዛሬ ክምችት በ80 በመቶ ጨምሯል" የብሔራዊ ባንክ ገዥ!

#ትዝብት፦ ባንኮቹ የሰበሰቡትን የውጪ ምንዛሬ LC ከፍተው ካልሰጡትም መከማቸቱ አይቀርም (በዚህ 2 ወር ባንኮች የመግዣ እና የመሸጫ ላይ ትርፍ ለመሰብሰብ ሲሉ LC ያለመክፈት ልምምድ ውስጥ ነበሩ)!
ኢትዮጲያ እና የግብጽ ግንኙነት ጤነኛ አይደለም! ግብፅ ከአባይ ወንዝ ኢትዮጵያን አግልላ ብዙ ተጠቅማለች! እነዚህ ሁለት ባላንጣ ሀገራት ያሉበት የኢኮኖሚ ሁኔታ ከአባይ ወንዝ ጋር መገናኘቱ ምን አስመስሎታል?


ኢትዮጲያ እና ግብጽን በኢኮኖሚ መለኪያዎችን በህዝብ ቁጥር፤ በተማረ ሰው ሃይል ብዛት፤ በከተሜነት ስፋት፤  በGDP፤ በነፍስ ወከፍ ገቢ መጠን፤ በዋጋ ንረት፤ በስራ አጥነት (በሰራተኛ ሃይል)፤ በውጪ ንግድ መጠን (Import እና Export)፤ በውጪ እዳ መጠን (እዳ በመክፈል አቅም)፤ በFDI፤ በውጪ ምንዛሬ ክምችት፤ ከውጪ በሚላክ ሃዋላ መጠን (Remittance)፤ በኢኮኖሚ ሴክተር፤ በንግድ አጋራት፤ በምንዛሬ አቅም፤ በመሰረተ ልማት፤ በሚታረስ መሬት መጠን፤ በማዕድን፤ በድህነት መለኪያ፤ በHDI፤ ወዘተ በመውሰድ ሁለቱን ሀገራት ስናነጻጽር ፍጹም ልትገምቱ የማትችሉትን ልዩነት እንመለከታለን…….https://youtu.be/ZDlwHSoc2A8
መንግስት (የማክሮ ኮሚቴ) በኢትዮጵያ የማክሮ ሪፎርም በተደረገበት በዚህ 2 ወር ምሳሌ የሚሆን አመርቂ ውጤት ተመዝግቧል ሲል አቅርቧል።


የተረጋጋና የምንዛሬ ሁኔታ እና የገቢ መሰብሰብ አቅም አዝማሚያን አሳይቷል ሲሉ የብሄራዊ ባንክ እና የገንዘብ ሚኒስትር የግምገማ ሪፖርት አቅርበዋል።


በውጪ ንግድ፤ በውጪ ምንዛሬ ክምችት፤ የምንዛሬ ተመን መቀራረብ ላይ ከተጠበቀው በላይ ውጤት አስመዝግቧል ተብሏል።


ነገርግን ኮሚቴው የሪፎርሙ አዘጋጅ በመሆኑ ያልጠቀሳቸው የኢኮኖሚውን እና የህዝብን ኑሮ እየፈተኑ ያሉ የሪፎርሙ ሌላኛውን ጎን ለመመልከት እንሞክር...https://youtu.be/_pDrSxJx6gM
መልካም የኢሬቻ በዓል ይሁንላችሁ! "Baga Ayyaana Irreechaa Nagaan Geessan!"
የሰራተኞች ደሞዝ ደረጃ እና የድህነት ድንበር! ሰራተኛው ብቻውን፤ ሲያገባ እና ሲወልድ....


ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ለማስላት ዝቅተኛ የኑሮ ወጪ የሚሸፍን ክፍያ ማለት ነው! ይህ ዝቅተኛ የክፍያ ወለል ከቤተሰብ ብዛት እና ከመኖሪያ አካባቢ ጋር ትስስር አለው።


በዚህ ቪዲዮ የደሞዝተኛ መሪር የድህነት ወለል፤ መደበኛ የድህነት ወለል እና ልዝብ የድህነት ወለል ለማስላት የቤተሰቡ ገቢ እና በገቢው ይመገባል ተብሎ የሚጠበቀው የካሎሪ መጠን እንዴት ሊሰላ እንደቻለ እንመለከታለን....https://youtu.be/OGsZGInVY34
በዓለም ላይ 2 እና በአፍሪካ 5 ሀገራት 50% የደረሰ GDP ጠቅልለው ይዘዋል።


አፍሪካ ውስጥ 54 ሀገራት አሉ። የአፍሪካ ጥቅል ምርት (GDP) ከሁሉም ሀገራት ተደምሮ በ2024 የ2.8 ትሪሊዮን ዶላር አቅም አለው።

ከጠቅላላው የ2.8 ትሪሊዮን ዶላር ውስጥ ከ51 ከመቶ በላይ የተያዘው በ5 ሀገራት ነው።

እነሱም....

ደቡብ አፍሪካ (በ373 ቢሊየን ዶላር 13.2% ድርሻ)፤

ግብፅ (በ347 ቢሊየን ዶላር 12.3% ድርሻ)፤

አልጄሪያ (በ266 ቢሊየን ዶላር 9.5% ድርሻ)፤

ናይጄሪያ (በ252 ቢሊየን ዶላር 9% ድርሻ)፤

ኢትዮጵያ (በ205 ቢሊየን ዶላር 7.3% ድርሻ) አላቸው።

የሚገርመው አፍሪካ 54 ሀገራት ይዛ ያላት የ2.8 ትሪሊየን ዶላር GDP ከፈረንሳይ የ3 ትሪሊየን GDP ያንሳል።

በዓለም ላይ እውቅና ያልተሰጣቸውን ጨምሮ የ203 ሀገራት ድምር GDP በ2024 ላይ የደረሰው 110 ትሪሊየን ዶላር ነው። ከጠቅላላው ከ42 ከመቶ በላዩ የተያዘው በሁለት ሀገራት ብቻ ነው። እነሱም...

አሜሪካ 29 ትሪሊየን ዶላር (26% ድርሻ) እና ቻይና 18 ትሪሊየን ዶላር (16% ድርሻ) ይዘዋል።


ምክንያቱ ምንም ይሁን ምንም ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እና የዓለም ተጠቃሚነት የፍታዊነት ጉድለት ያለበት ነው።
Paid Promotion!

ተራራ ህትመት እና ማስታወቂያ ሥራ

ማስታወቂያ እና ሕትመት ሥራ

የኛ ልዩነታችን :-

# ልብዎ የተመኘውን : ሰው እንዲያውቅልዎ የፈለጉትን ሃሳብ ንድፍ (design ) ከማውጣት ጀምሮ ታትሞ እስኪያዩት ድረስ በአርክቴክት ባለሙያዎች ፕሮፌሽናል ሥራ መስራታችን

# ያዘዙንን ሥራ በፍጥነት ሰርተን ያሉበት መጥተን ማስረከባችን ( free delivery )

# ገበያው ላይ ካለው ዋጋ በቅናሽ መስራታችን ( ዋጋ matters 😁)

# ስራችንን የምንሰራው outsource አድርገን ሳይሆን በዉድ ዋጋ በገዛናቸው በራሳችን ማሽኖች ስለሆነ በጥራት እና በቅናሽ መስራታችን ላዘዙን ሥራ እንጨነቃለን ::

# እናማክርዎታለን!!! ሥራዎን : ንግድዎን : ሃሳብዎን ለሕዝብ ለማስተዋወቅ ፈልገው ነገር ግን
      > የት ማስተዋወቅ እንዳለብዎ ካላወቁ
      >ምን አይነት ማስታወቂያ ማሰራት እንዳለብዎ ካላወቁ
      > ማንን ማናገር እንዳለብዎ ካላወቁ :- እኛ እናማክርዎታለን : እንመራዎታለን ::

****
ልብስ ላይ ህትመት :-


=ቲሸርት
=አንፀባራቂ
=ሁዲ
=ባንዲራ (ለድርጅት እና መሰል )
=ጃኬቶች
=የስራ ልብሶች
=የስፖርት ማልያዎች እና ትጥቆች

ወረቀቶች

=በራሪ ወረቀት
=የሰርግ ካርድ
=ቢዝነስ ካርድ
=ፖስት ካርድ
=ደረሰኝ
=የሃኪም ቤት እና መሰል ካርዶች
=መፅሄት
=መፅሐፍ
=ተለጣፊ ወረቀቶች
=ትኬቶች
=የሃዘን ካርዶች
=ለድርጅትዎ ፖስታዎች ወዘተ

ሌሎች

=ባነር
=ማግ
=ሾፒንግ ባግ
=ሕጋዊ ማህተሞች
=ላይት ቦክስ
=ማይካ
=ድጅታል መታወቂያ እናትምልዎታለን
=እስክርቢቶዎች
=ለኮምፕዩተርዎ ማዉዝ ፓድ
=የድርጅትዎ የቁልፍ መያዣዎች
= የድርጅትዎን አርማ የያዙ ማስታወሻዎች (note book)
= ወዘተ

ተራራ ህትመት እና ማስታወቂያ ሥራ

PRINT $ INSPIRE $ REPEAT

0927361854
0799100230
0985257938

👇
https://vm.tiktok.com/ZMrtqxR5U/

👇
https://t.me/Teraraprinting1

👇
https://www.facebook.com/share/aCdm9rvi7Mnx4Fo1/?mibextid=qi2Omg

ሎኬሽን
👇https://maps.app.goo.gl/heRTnskHQDUj2jgQ9
የመንግስት የ2016 የኢኮኖሚ ሪፖርት እና የ2017 ቀጣይ ትኩረት (Summary)!Export በ31%፤ FDI በ28%፤ የሀገር ወስጥ የገቢ መጠን በእጥፍ እንዴት ያድጋል?

ዛሬ በአዲሱ የኢፌድሪ ፕሬዝደንት የኢትዮጲያ የ2016 የኢኮኖሚ ሪፖርት እና በ2017 በኢኮኖሚ ዘርፍ ትኩረት የሚደረግባቸው ነጥቦች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡ የ2016 የኢኮኖሚ ሪፖርት እና የ2017 የትኩረት ነጥቦች .... https://youtu.be/icEAuJFYeZU
The Ethiopian Economist View pinned «Paid Promotion! ተራራ ህትመት እና ማስታወቂያ ሥራ ማስታወቂያ እና ሕትመት ሥራ የኛ ልዩነታችን :- # ልብዎ የተመኘውን : ሰው እንዲያውቅልዎ የፈለጉትን ሃሳብ ንድፍ (design ) ከማውጣት ጀምሮ ታትሞ እስኪያዩት ድረስ በአርክቴክት ባለሙያዎች ፕሮፌሽናል ሥራ መስራታችን # ያዘዙንን ሥራ በፍጥነት ሰርተን ያሉበት መጥተን ማስረከባችን ( free delivery ) # ገበያው ላይ ካለው…»