Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
AB PHOTOGRAY
😔😔🤦‍♂🤦‍♂
SAMISHO(DOC)
I FEEL SAD FOR YOU BRO😔
Phenomenal pictures & graphic design
AB PHOTOGRAY 😔😔🤦‍♂🤦‍♂ SAMISHO(DOC) I FEEL SAD FOR YOU BRO😔
ሳሚ(DOC SHOESHINE) ይባላል ትውውቃችን የዛሬ አምስት አመት ምኒልክ ትምህርት ቤት የ11ኛ ክፍል ተማሪ ሳለሁ ነው፡፡ ምኒሊክ የተማሩ አብዛኞቹ ያቁታል ይህ ትሁት የፍቅር ሰው ጫማ በማሳመር ሙያ የሚተዳደር ወንድማችን ነው፡፡

ሳሚሻ ይናገራል "አብዬ ያው ድሮ ታቃለህ እናንተም፣ የዩኒቨርስቲው ተማሪም፣ አስተማሪዎችም እዚሁ ስራ ያላቸውም አላፊ አግዳሚውም ነበር ጥሩ እሰራነበር.....አሁን አስቸጋሪው ጊዜ ላይ ነኝ ስራ አልወጣም እንዳይባል ብቻ ነው የምመጣው መጥቼ ቁጭ ነው፡፡ ምንም ስራ የለም ካልተሰራ በምን ይበላል የቤት ኪራይ🤦‍♂አለ ሚገርምህ ባለፈውም ደውዬ ነግሬኻለሁ ትምህርት ነፃ ነው.....ምናምን ሲባል ደጉ ጊዜ ብዬ የመጀመሪያ ልጄን እዚሁ እንዲማር አምጥቼዋለሁ ስራ በነበረ ሰዓት እንደነገሩ አሳልፈናል አሁን ግን የእውነት አብዬ ከብዶኛል ጨንቆኛል አስተምራለሁ ብዬ አምጥቼ ይህ መጥፎ በሽታ እንዳይነጥቀኝ ፈራሁ ሀገራችን እናቱ ጋር እልከዋለሁ ብዬ ነበር ድንገት መንገድ ተዘጋ ስራም የለም ምን እንደሚሻል አላቅም የኔንም ስራ ታቀዋለህ ከብዙ ሰው ያገናኛል ለራሴም ባይሆን ለሱ ፈራሁ ድንገት እኔን ከያዘኝ እሱ ላይ አጋባበት ይሆን እያልኩ በሰቀቀኝ አለኩ ስራውን እንዳላቆም ሌላ ምን እሰራለሁ🤷‍♂ ብቻ ግራ ያጋባል".....አለኝ እዝን ባለ ድምፅ

የተዘጋጀሁበትን ትንሿን ነገር አቀበልኩት አለቀሰ በእውነት አዘንኩ በጣም አዘንኩ ወደላይ ቀና ብዬ አምላካችን እባክህ ለእነዚ ምስኪኖች ስትል በሽታውን ከሀገራችንም ከአለምም አጥፋልን አልኩኝ ከልብ ተሰማኝ ምን ማድረግ እችል ይሆን ስል አሰብኩ....🤔እናም ታሪኩን ለናንተ አካፍዬ የተቻለንን ብናረግ ብዬ አሰብኩ የተቻለንን አቅማችን ሚችለውን እናደርግ ዘንድ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

ማንኛውምን አይነት እርዳታ ማድረግ የሚፈልግ ሰው በ+251973068982 በመደወል እና ከእኔ ጋር በመገናኘት ወንድማችንን በአካል አግኝቶ መርዳት ይቻላል።

😍😍😍 ኢትዮጵያዊነት ደግነት😍😍😍

ይሄን ክፉ ቀን በፍቅር ተደጋግፈን እንለፈው!

ለአስተያየታችሁ @jahABP
AB PHOTOGRAPY
በጠዋት ስትኀሳ ተፈጥሮ እራሷ ታስገርምኅለች
Wallpaper 😍
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPY
"ዋናው ልብ ነው! ልባችንን ንፁህ ካደረግን ኢኒሻ አላህ! መድሃኒቱ ይገኛል"
መልካሙን ሁሉ የምንሰማበት የተቀደሰ ቀን ይሁንልን! መልካም ጁሙአ
ማህበራዊ እርቀታችንን እንጠብቅ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
ፈገግ ሳቃችንን ቀምተውን

ሁልጊዜ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት እነሳና እማረራለሁ፡፡ እናቴ ደግሞ በዚህ እኔን ማየቱ በራሱ ያስቃታል፡፡ ያሳቃት ጉዳይ ቢያበሳጨኘም ሳቋ ስለሚያስቀኘ እየሳኩ እናደዳለሁ፡፡ እናቴ ስትስቅ ማንም አለመሳቅ አይችልም፡፡ዓይኖቿ ይጨፈኑና እንባዋ ጠብ እስኪል ረዥምና በየመሃሉ እፎይ ወይም 'ውይ' የሚሉ እረፍቶች የተካተቱበት ሳቅ......

አባቴ ኮስታራ ነው፡፡ እናቴ ፊት ሲሆን ምንጊዜም ላለመሳቅ ይታገላል፡፡ በሳቅና በመኮሳተር መካከል ላይ የቆመ ፊት ያለው አባት ደሞ ያስቃል፡፡ "ውይ ስቀህ ብታርፈው ምናለ እንዳልዬ
፣ እንዲህ ግራ የገባው አንበሳ ከምትመስል ሃሃሃሃሃሃሃሃ .... ውይ .... ሂሂሂሂሂሂሂሂ ፊትህ እኮ ሲያስቅ ህህህህህህህህ ... በቃ እናቴ አታቆምም .......

አንዳንዴ ብቻዋን ሆና በሳቅ ፍርስርስ ስትል እደርስና ፣ "ኧረ ማሚ ሰው ጉድ ይልሻል" እላታለሁ፡፡

"ውይ በስማም እቴ ስትገባ እንኳን አታንኳኳም ... ሆሆ አስደነገጥከኘ እኮ ጥላ ቢስ" ትልና በሳቅ ፍርስርስስ......
አታየውም ሁለቱ ድመቶች ተጣልተው የኩሽናውን እቃ ጨረሱት .... ስኳር ነሽ ፣ ሽሮ ፣ በርበሬ ድፍትፍት ሃሃሃሃሃሃሃሃ .... ወይጉድ ጦርሜዳ ትላለች የተደፋፋውን እያፈሰች፡፡ በቃ እናቴ እንዲህ ናት - ሳቅ የተመረቀላት ....

ዛሬም ታዲያ ገና በጠዋቱ ሳቋን ጀመረችው፡፡

አብርሽ ደህና አደርክ....ክ ኪኪኪኪኪኪ !!ሳቋ ለሰላምታ እንኳን ፋታ አልሰጣትም፡፡ ፊቷን እየታጠበች ትስቃለች ፣ ቁርስ እየሰራች ብቅ እያለች ትስቃለች ፣ መናገርማ አትችልም - ሳቋ ስለሚቀድማት መናገር አትችልም፡፡

አብርሽ...ቁርስ ደርሷል ህህህህህህ ... ሃሃሃሃሃሃ ... ሁሁሁሁሁሁ ፎይ ... ትስቃለች፡፡ ሰሃኑ ከእጇ ሊያመልጣት እስኪደርስ ትስቃለች፡፡ እያንዳንዷ ቃሏ ረዥም የሳቅ ጅራት አለው...

"ኧረ ማሚ አይደብርሽም እንዴ... እላታለሁ ብስጭት ብዬ፡፡

"አይ ..እኔ እኮ ሆሆሆሆሆ.. ያ..ሳቀኘ...ህህህህ ..አብርሽዬ" ....እያቀራረበች አይኗቿ የሞላው እንባ በክንዷ ትጠርጋለች - በጠዋቱ ይሄን የሚያህል ሳቅ ....!!

አባቴ ያንኑ ግራ የሚያጋባ አንበሳ የመሰለ ፊቱ ይዞ ከመኘታ ቤት ብቅ ይላል፡፡ አሁን ማሚ በእጇ የያዘችውን የሻይ ማንቆርቆሪያ እስኪያመልጣት ሳቋ ወሰኑን አልፎ ይንፎለፎላል ...ወደ አባቴ እያየች ...

"ዛሬም እየጠበቀው ነው..." ይላል ወገቡን ይዞ..

"በደንብ ነዋ....ሃሃሃሃሃሃ" ትመልሳለች እናቴ፡፡

ጎረቤታችን አቶ ይፍሩ የሚባሉ ሰውዬ አሉ፡፡ መኪና አለቻቸው(ካለመኖር የማትሻል ) ክርክስ ያለች ዲኤክስ፡፡ ጠዋት ወደ ትምህርት ቤት ስሔድ እቺን መኪና የመግፋት ጎረቤታዊ ግዴታ አለብኘ፡፡ ደሞ ክብደቷ ፣ ባቡር የምገፋ ነው ሚመስለኘ፡፡ አንንንንን ካካካካ ትልና ዝም!! እንደገና እንገፋለን፡፡ በዋናነት እኔ ፣ ኤልያስና ፍቅሩ ነን ነን የምንገፋው፡፡ አቶ ይፍሩ በራቸው ላይ ይቆሙና የትም አለም ተሰርቶ የማያውቅ 'ስፖርት' (መወራጨት) እየሰሩ ሦስታችንን ይጠብቁናል፡፡ ዋና ስራቸው እያን መጠበቅ ነው፡፡ ትምህርት ቤት ለመሔድ በእርሳቸው በር ማለፍ ግዴታ ስለሆነ የትም አናመልጥም፡፡

ከዛ ከቤት ስንወጣ ፣ ወጣት የነብር ጣት መጣችሁ ..እስኪ እቺን ነገር እናስነሳት ... ይሉና ወደ ግቢያቸው እየመሩ ያስገቡናል፡፡ መግፋፍ ነው የመኪና (የመኪና ስም አይገዛ) "ግፉ ግፉ ግፋ..." አንንንንንንንንነ ..ዝም ! ተግተግተግተግተግተግ..ዝም! "በሉ ግፉ አብርሃም ዛሬ ደከም ብለሃል ግፉ እንጂ..ግፋ ግፋ..ተርርርርርርርርርር ፈትለክ...አንዳንዴ መኪናዋ ስትፈተለክ በደረታችን መሬቱ ላይ እንለሸሻለን፡፡ አስፓልቱ ላይ እንደተለሸሽን በጉያችን እናያታለን፡፡ እየተንተፋተፈች ከሩቅ በኢብሩ ሱቅ ፦ትታጠፍ ከወደቅንበት ተነስተን በእፎይታ እጃችንንና ልብሳችን እያረጋገፍን መንገዳችንን እንቀጥልና በኢሩብ ሱቅ እጥፍ ስንል ያውም አቀበቱ ላይ ቆሞ ትጠብቀናለች፡፡

"ዛሬ ሰይጣኗ መጥቷል...ወደዛ ሸጬ ካላረፍኩ" እያሉ ይጠብቁናል፡፡ ሁልጊዜ ነው የሚሉት፡፡ ማነው ያበደ እቺን የሚገዛ፣ አብሮ እኛን ካልገዛ በስተቀር፡፡
...ግፉ ...ግፉ...ተግተግ....ተግትግተግትግትግግ..ዝም!!

እናቴ ታዲያ የሚያስቃት ይሔ ነው፡፡ ቀስ ብላ የቤታችንን መጋረጃ ገለጥ አድርጋ ቀሳቅ ፍርፍር እያለች፣ "የዛሬው ስፖርት ደግሞ ይለያል" ትላለች፡፡ ከዛም፣ "አብርሽዬ ስፖርቱ እኮ ለናንተም ሳይጠቅም" ትልና ፍርስስስስስስ በሳቅ!

ትላንት ማታ ታዲያ አባቴ እንዳለ ይሄን ነገር ሰማና ተቆጣ....

በቃ ከአሁን በኀላ እቸኩላለሁ ይቅርታ ብለህ እለፍ!! መኪና በመግፋት የተዳከመ ሰውነት ይዞ ትምህርት ቤት ለምን ይሔዳል...እንዳትገፋ...እንደ ጎረቤት አንድ ሁለት ቀን መተባበር አንድ ነገር ነው÷ ሦስት ወር ሙሉ...ለምን አያሰራም..እንዴዴዴዴዴዴ...አያስቅም!! አለ እናቴን እያየ፡፡ እናቴ ወደ ውስጥ ገባች ልትስቅ እኮ ነው- አታበሳጭም? አባቴ ከልቡ በነገሩ ተቆጥቶ ነበር፣ "እንዴ በሌሊቱ የማንንም ቆርቆሮ..."

"አብርሃም"

"አቤት አባባ"

"ስትገፋ ባይህ ውርድ ከራሴ ፣ ቸኩያለሁ ብለህ እለፍ...እ"

"እሺ"
"አዎ...ይሉኘታ አያስፈልግም፡፡ አንዳንዴም እንደ ፈረንጅ ማሰብ ጥሩ ነው፡፡ ማንም የወዘፈውን ስንገፋ ነው እድሜዳችን የገፋው፡፡ ሲቆም ደሃው ይገፋል ÷ ሲነሳ የሚንፈላሰስበት ሌላ-እንዳትገፋ-.....!!

ጅልና ወረቀት የያዘውን አይለቅ፣ አባቴ እንደመከረኘ አቶ ይፍሩን፣ ይቅርታ ፈተና ስላለብኘ ዛሬ አልገፋልዎትም ብዬ በቀጣዩ ቀን አለፍኳቸው፡፡ ጓደኞቼም በየራሳቸው ምክንያት አንገፋልዎትም ብለዋቸዋል ኖሯል...."

ይቀጥላል......................
...ማታ ወደ ቤት ስመለስ ማሚ ገና ስታየኝ ሆዷን ይዛ ሶፋው ላይ ቁጭ ብላ በሳቅ ፍርፍርርርርርርር አለች፡፡

የዛሬው ይለያል....

ጉዳዩ እንዲህ ነው፡- እኔ አቶ ይፍሩ ጋር ስነጋገር አባቴና እናቴ በመስኮቱ መጋረጃ ተከልለው እያዩ ነበር፡፡

"እንቢ ብዬ ሳልፍ አባቴ በልጁ ኮራ፡፡ "ጎበዝ የኔ አንበሳ እንዲህ ነው...! በዚህ እድሜው በይሉኝታ ከተሸበሸበ የማንም መጫወቻ ነው የሚሆነው... አለና ፣ አሁን አንቺም እስኪወጣልሽ ሳቂ" አላት እናቴን፡፡ እንኳን ተፈቅዶላት እንደውም እንዲያው ናት፡፡ አባቴም ሳይስቅ አልቀረም እንደውም ሳይጎነታተሉ አይቀሩም እናቴና አባቴ፡፡
"ውይ እንዳልዬ የጣድኩት እንቁላል አረረ... "እያለች እየሳቁ እየተጎነታተሉ እያለ፣

በር ተንኳኳ....

"ማነው" አለ አባቴ

"እንደምን አደራቹ..."

አባቴ በሩን ከፈተ አቶ ይፍሩ ነበሩ፡፡ ስሞታ ሊናገሩ ነው ብለው እናትና አባቴ ሲጠብቁ ፣

"እንዳለ እባክህ እቺ መኪናዬ ትንሽ አስቸግራኝ የሚገፋልኝ ሰው አጣሁ - ይቅርተታ ትተባበረኝ.."
ብለውት እርፍ፡፡ 'የልጅ እዳ ላባት' ተረቷ ተገልብጣ!!

"መጣሁ መጣሁ ምን ችግር አለ ደሞ ለጎረቤት..." ሲል እናቴ መኝታ ቤት ገብታ እስከ ምሳ ሰዓት ሳቀች....

ይሔን ስትነግረኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእናቴ ጋር በሳቅ ተወዳደርኩ፡፡

ማታ አባቴ እንዲህ አለኝ
"አብርሽ ክላስ እንዴት ነው...?"

"ጥሩ ነው"

"እእ ዛሬ ቢሮ ተቀምጬሳስበው...ማታ የመከርኩህ ነገር..ልክ አልመሰለኝም-ሶሪ"

"የትኛው ጉዳይ አባባ"
"የአቶ ይፍሩ መኪና ጉዳይ"
"አየህ ትልቅ ሰው ናቸው፡፡ በዛ ላይ ልጆቻቸው ውጪ ሃገር ነው ያሉት፡፡ ብቸኝነቱ.... አለ በባህላችንም ጎረቤት መርዳት ጥሩ ነው፡፡ እግዚአብሔርም በመጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ...ቁጥር... "ልጄ ሆይ ታላላቆችህን አክብር፤ አንተም ባረጀህ ጊዜ ትከበራለህና ይላል፤ እና እስኪያስተካክሏት ድረስ መኪናቸውን ብትገፋላቸው ምንም ማለት አይደለም...ለአንተም ስፖርት ነው" አለኝ ኮስተር ብሎ፡፡

ማሚ የሆነውን ሁሉ እንደነገረችኝ አልጠረጠረም ነበር፡፡ አይ አባባ በሱ ቤት 'አሪፍ' መሆኑ ነው፡፡

በኋላ መኝታ ቤት ሆኜ ማሚ እየሳቀች፣ "አንተ ፖለቲከኛ መሰልክ እኮ...ሃሃሃሃሃሃሃ..." ስትል ሰማኋት ለአባቴ፡፡ አብረው በሳቅ ፍርስስስስስ....፡፡ አባባ እዳውን ለኔ ወርውሮ መሳቅ ጀመረ......እኔም ለንቦጬን ጣልኩ፡፡

አባቶቻችን በተሰላቸ ምክር ፣ በተሽሞነሞነች ተረት እነሱ መግፋት ያልቻሏትን ስንት ጣጣ 'በፍቅር' አውርሰውናል!! ማሚ እንዳለችውም ፖለቲከኞች እንዲህ ይሆን እጥፍ ብለው በቲቪ ፈገግ ሲሉ የምናያቸው፡፡ የማሚ ሳቅ ይሰማል ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ እፎይ ሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂ ምስኪን አብርሽ.....

አሌክስ አብርሃም፡- ዙቤይዳ 2007

ለአስተያየታችሁ፡- @jahABP
ቤታችን እንሁን እናንብብ
ከቤተሰቦቻችን ጋር ጥሩ ጊዜን እናሳልፍ
ሁላችንም በሀይማኖታችን ስለሀገራችን ስለዓለም እንፀልይ
AB PHOTOGRAPY
In front of s.t estifanos church 😱😂
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
✨በቀጣይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
🤲🤲
እንድንፀልይ የፈቀደልን አምላክ የተመሰገነ
ይሁን!

ሰው ወደ እግዚአብሔር መቅረብና መነጋገር የሚችልበት የመጀመሪያ መንፈሳዊ መንገድ ጸሎት ነው፡፡

ጸሎት እግዚአብሔር እና ሰዎች የሚገናኙበት ድልድይ ነው፡፡ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ እንዳየው መሰላል ከሰማይ እስከምድር የሚደርስ መወጣጫ ነው፡፡

ጸሎት ከውስጥ የሚመነጭ የልብ መቃተት ስለሆነ ቃላት ብቻ ሊገልፁት አቅም የላቸውም። በተመስጦ ልብ፣ በመንፈሳዊ ሀሳብ፣ በተሰቀለ ሕሊና ወደ አምላካችን የምንነጠቅበትና ከፈጣሪያችን ጋር የምንነጋገርበት ስለሆነ ጸሎት ከቃላትም በላይ ነው፡፡ በዝምታ እያለን በህሊና ልንመሰጥ እንችላለን፡፡ ጸሎት እግዚአብሔር የናፈቀ ልብ ሲቃ ነውና ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ይለካበታል፡፡ሰውና እግዚአብሔርን ማገናኘት የሚችለው በዚህ ዓይነት ከልብ ፈንቅሎ የሚወጣ ጸሎት ስለሆነ ከዚህ መንፈሳዊ ሕብረት ውጪ ሆኖ የሚጮህ ጩኸት ረብ የለሽ የቃላት ጋጋታ ነው፡፡

ለጸሎት በተነሳህበት ጊዜ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንደቆምክ አስብ፡፡ "ዋላ ወደ ውሃ ምንጮች እንደሚናፍቅ አቤቱ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች፣ ነፍሴ ወደ ህያው አምላክ ተጠማች፡፡ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?(መዝ 41÷2)። በእውነት ዝናምን እንደምትናፍቅ ደረቅ መሬት እግዚአብሔርን መናፈቅና መጠማት ይህ አይደለምን?

እግዚአብሔር የሚቀበለው ጸሎት በንጹህና በተሰበረ ልብ የሚቀርበውን ብቻ ነው፡፡ "የኃጥአን መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፣ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው፡፡" ምሳ.15÷8) ስለዚህ ኃጢአት የከበደው የተጨነቀ ሰው ምን ማድረግ አለበት? "መልሰኝ እኔም እመለሳለሁ" ይበል(ኤር 31÷18)።

አንተም ዛሬ መጸለይ ያለብህ ጸሎት ይህ ነው። ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ ከኃጥያቴም አንጻኝ እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፡፡" (መዝ 50÷2)

ጸሎት የአንደበትን፣ የሃሳብን፣ የነፍስን መስዋዕት ማቅረቢያ ነው፡፡ከእግዚአብሔር ጋር የተጣላ ሊያነጋግረው ስለማይችል ጸሎት ደግሞ የመታረቂያ መንገድ ነው፡፡ ተሰሚነት ያለው መልካም ጸሎት ለመጸለይ ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖርህና ስለእርሱም በቂ እውቀት ለመጨበጥ እንድትችል መጣር አለብህ፡፡ የማይጸልይ ሰው እግዚአብሔርን አላወቀውም፡፡ የሚጸልይ ግን ከእግዚአብሔርን ጋር መታረቅ የፈለገና የቀደመ ክፉ ስራውን እንየታወሰው በትህትና የተሰበረ ልብ ያለው ነው፡፡ ሰው ወደ ጤናማ ክርስቲያናዊ ሕይወት ምልክት ወደ ትህትና ደረጃ መድረስ የሚችለው በጸሎት ነው፡፡ የጥሩ መንፈሳዊ ሕይወት ፍሬ ትሕትና ነውና፡፡

ጸሎት ክፉ ሀሳብ ከውስጣችን የሚወገድበት ነው፡፡ ከጨለማ ኃይላት ርቆ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መግባት የሚቻለው በጸሎት ነው፡፡
ጸሎት አጋንት የሚፈሩትና የሚንቀጠቀጡበት መንፈሳዊ መሳሪያ ነው፡፡ ከወጥመዱ ያመለጠ ጸሎተኛን ዲያብሎስ ይፈራዋል፡፡ "ይህ ሰው በጸሎቱ ኃይል እያገኘ ነው፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወቱ እየጠነከረ ነው፡፡ ስለዚህ እኔን ሊዋጋኝ ይነሳል እያለ ይርዳል ይንቀጠቀጣል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር በጸሎት የሚፈጠረውንም ጥልቅ ግንኙነት እርሱ አስቀድሞ ያጣው ነውና ይቀናበታል ይመቀኘዋል፡፡ ስለዚህ ዲያብሎስ በሚችለው አቅም ሁሉ ጸሎትህን ለማስተው ይጥራል፡፡ ጊዜ እንደሌለህ፣ እንደተጣበብክ፣ እንደደከመህና፣ እረፍት እንደሚያስፈልግህ እያሳሰበ ጸሎትህን ለማስቆም ይታገላል፡፡ በጸሎትህ የምትታመን የምትተጋ ብትሆንበትም ከመንገድህ ለማስነሳት ሀሳብህን ለመበተን ሰይጣን የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡

ጌታ ሆይ የውስጤን የሚረዳልኝ እንዳንተ ያለማንንም አላገኝም፣ ከአንተ ጋር ስሆን ብቻ ደህንነት ስለሚሰማኝ ለአንተ ለአምላኬ ልቤን ከፍቼ ምስጥሬን አዋይሃለሁ፡፡ ቃልህን የምሰማ ነገር ግን የማላስተውል ደካማ ነኝና፣ ናፍቆቴን ቢገልፅልኝ እንባዬን በፊትህ አፈሰዋለሁ፡፡ይህ አይነት ጸሎት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን በደረጃው ከፍ ያለ እና በእግዚአብሔር ፍቅር ያደገ ነው፡፡

ታላቁ አባት ቅዱስ ባስልዮስ "ጸሎታችሁን በጥያቄ አትጀምሩ" እንዳለው የእግዚአብሔርን ዕጹብ ድንቅ ባህሪያት አውቀህ በተመስጦ የምትፀልይና የምትጠቀም ሁን፡፡

"ለፀሎት ጊዜ የለኝም" ማለት እጅግ አስፀያፊና ዘግናኝ ኃጢያት ነው፡፡ አንድ አገልጋይ(ባሪያ) "ጌታዬን የማነጋግርበት ጊዜ የለኝም" ቢል እንዴት ያለ ድፍረት ይሆን? ፍጡሩስ ከፈጣሪው ጋር ለመነጋገር "ጊዜ የለኝም" ቢል ምን ይደንቅ! ዋጋ ቢስ ለሆኑ በርካታ ነገሮች ጊዜ ታገኛለህ፡፡ ምንም ረብ ለሌላቸው ንትርኮች ከበቂ በላይ ጊዜ አለህ። ምነው ታዲያ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እንደጊዜ ማባከን ቆጠርከው? ነብዩ ቅዱስ ዳዊት ከታላቅ ቤተሰብ ጋር ሕዝብን፣ አገርን የሚመራ፣ የሚያስተዳድር፣ መሪ፣ መስፍን፣ ፈራጅ ንጉስ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ዳዊትን የምንሰማው እንዲህ ሲል ነው፡፡ "ስለጽድቅህ ፍርድ ሰባት ጊዜ በቀን አመሰግንሃለሁ" (መዝ 118÷164) ከዚህ የምንረዳው ችግሩ የጊዜ ሳይሆን የፍላጎት እንደሆነ ነው፡፡

ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ እንዳለው "ጸሎት ከሕመም የመፈወሻ መንፈሳዊ መንገድ ነውና ላለመፀለይ በሽታን እንኳን ምክንያት አታድርግ"።

ማርይስሐቅም "ንጹህ ጸሎት ለመፀለይ በጀመርክበት ጊዜ ለሚመጣው ነገር ዝግጁ ሆነህ ጠብቅ፡፡" ይሉናል ማለትም ከጸሎት ሊያደናቅፍህ ዲያቢሎስ ለሚከፍትብህ ጦርነት የተዘጋጀህ ሁን ማለታቸው ነው፡፡

እግዚብሔር የለመንከውን እንደሚሰማህ፣ ይወድሃልና መልስ እንደሚሰጥህ፣ መልካሙን ሁሉ ለአንተ እንደሚመርጥልህ በፍፁም ልብህ እመን(ማቴ 21÷22) ይህ እምነት ባይኖርህ እንኳን "ጌታ ሆይ አለማመኔን እርዳው" እያልክ ጸልይ (ማር 9÷24 ) ደግሞም እንደሐዋርያት እምነት እንዲጨመርልህ ለም'ን (ሉቃ 17÷5 ) ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል የሚለውን ድንቅ ቃልኪዳንም አትርሳ(ማር 9÷23)።

እምነት ለጸሎተኛው ጽናትን የሚሰጥ ታላቅ ኃይል ነው፡፡ ጸሎትም እምነት ያሳድጋል፡፡ አንድ ነገር እንዲሆንልህ ጠይቀህ፡፡ ለምላሹ ጌታን ጠብቅ እንጂ ያን ቶሎ ለማግኘት አትቸኩል፡፡ ምንም እግዚአብሔር የሚዘገይ ቢመስልህም፣ የረሳህ ያህል ቢሰማህም፣ እርሱ ግን የራሱ ጊዜ አለውና ጥያቄህን እንደሚመልስ እርግጠኛ ሁን፡፡

ለመጸለይ የምትጠቀመው ማንኛውም ቃልና እንቅስቃሴ በማስተዋል መሆን አለበት። ምክንያቱም ጸሎት በቀጥታ ከእግዚአብሔር ጋር የምታደርገው ግንኙነትና ውይይት ነው፡፡ ስለዚህ የእያንዳንዷ የፀሎት ቃል ጣዕሟን ማጣጣም ስለቻልክ ማቋረጥ አያሰኝህም፡፡ አባቶች ቅዱሳንም በአፋቸው ውስጥ ካለው የጸሎት ጣዕም የተነሳ ጸሎትን አቋርጠው ሌላ ነገር ለመናገር አይፈቅዱም ነበር፡፡ አንተም በዚህ ስጋዊ ዐይን በማያየው ልዩ የጸጋ መንገድህ ወደ ፈጣሪህ ገሥግስና ችግርህን፣ ደስታህን፣ ሁለንተናህን አዋየው፡፡ ጉድለትህን እንዲሞላ ባለማቋረጥ ጠይቀው፣ የምትሻውን እንደፈቃዱ የጠየከውን ሁሉ ይዘህ ትገኛለህ።

እንድንፀልይ የፈቀደልን አምላክ የተመሰገነ
ይሁን!!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

ጉዞ ወደእግዚአብሔር (the spiritual means)
ተርጓሚ:- ዲያቆን ግርማ ባቱ
ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ
በኃይማኖታችን ስለሀገራችን ስለአለም እንፀልይ
ለአስተያየታችሁ @jahABP
እየሩሳሌም ሆይ ምስጋናን ጀምሪ

መለከትን ንፊ ነጋሪት ጎስሚ

ሰላምሽ ታውጇል መዳንሽም ቀርቧል

ጌታ ሊጎበኘሽ ከበራፍሽ ቆሟል

መልካም የሆሳዕና በአል🙏
AB PHOTOGRAPY

ብታምኑም ባታምኑም የዛሬ ለሊት ጨረቃ ነች😍😍😱😱
መልካም ቀን
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
በቀጣይ ልደቱን እያከበረ የሚገኘው

በሚገርም የብዕር አጣጣሉ ሁሉንም ያስገረመው ቃላቶቹ ስዕል መስለው እንድንዳስሳቸው እያንዳንዱ ስሜቶች እንዲሰሙን ድርሰቱ ላይ ያሉት እያንዳንዱ ገፀባህሪያት ከአይምሮአችን እንዳይጠፉ አድርጎ በተለየ የመፅሐፍ ችሎታው አንቱታን ያተረፈው
አለማየሁ ገላጋይ(አሌክሶ)
መልካም ልደት ብዙ አስገራሚ ስራዎችን ካንተ እንጠብቃለን፡፡ ረጅም አመት ከጤና ጋር ተመኘን
😍🙏👏
ተፈነከትኩ÷ለመጀመሪያ ጊዜ ደሜ ፈሰሰ፡፡ የግንባሬን አካፋይ ወደቀኘ ትቶ ከፍ ካለው ቦታ የእሳት ፍንጣሪ ከመሰለ ፍንክት የሚጎርፈው ደም ግራ አይኔን አስጨፍኖ ወደ አገጬ ወረደ፡፡

ግር አለኘ፡፡ ተገረምኩ፡፡ ነፍስ ካወኩ ወዲህ ከመፈንከት ጋር ስተዋወቅ የመጀመሪያዬ ነው፡፡
የበኸር ፍንክቴ ልበለው? ከዚ ቀደም ሰው ተፈንክቶ ስመለከት የደም አወራረድ እንዲህ ፀጥተኛና ሰላማዊ አይመስለኘም ነበር፡፡ እንደ እሳት ጅረት ያረፈበትን ቆዳ እየለበሰና እያኮማተረ የሚወርድ ፈሳሽ ስቃይ ይመስለኘ ነበር፡፡ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ አናታችን ላይ እንደተከለበሰ ሙቅ ውሃ ዝም ብሎ ይወርዳል፡፡ አካላችን ውስጥ እንዳልነበር፣ የእኛ እንዳልሆነ ባዕድነት ዝም ብሎ መንዠቅዠቁ አስገረመኘ፡፡ ደም ለተመልካች የሚከብደውን ያህል ለተፈንካቹ ሥቃይ አይደለም፡፡

ስለተጠራጠርኩ ዳግመኛ በጣቶቼ ነካ አደረኩት፡፡ አለላ የመሰለ አስደንጋጭ ነገር አይኔ ተጋፈጠው፡፡ ደሜን ስመለከት አደጋ ላይ እንዳለሁ ተሰማኘ እንጂ እንደውም ሲወርድ እንደወጠረ ሽንት እፎይታ አለው፡፡

"ና! ና ወዳጄ

ጎንበስ ብዬ እጄን አየሁት፡፡ ደሜ እጄ ላይ ደርቆ መሰነጣጠቅ ጀምሮ ነበር፡፡ ከመቼው? አሁን መገረም ቃጣኘ፡፡ ታዲያ ጓደኞቼ ካንዴም ሁለት ሦስቴ ተፈንክተው ለምን እንደዚህ ለደም ይሽቆጠቆጣሉ? ስንተኛው ፍንክታቸው ላይ ደምን ይንቁታል? ጋሙዳ ሦስቴ ተፈንክቷል፣ ሙቄ አራቴ ደርሶታል፣ ቀጮ ሁለቴ ቀምሷል፣ ሴንጢም ቁጥሩን የማላቀው ያህል ተቀንድቧል፡፡
በፍንክት የተፈተፈተ ቅንድቁን እያዩ ትግራዩ የሚሉትም አሉ፡፡ ያልፈነከትነው እኔና አሰፋ ጠሪራ ብቻ ነበርነ፡፡ አሰፋ ጢሪራ ካልደረሱበት የማይደርስ ስለሆነ ነው፡፡ ከደረሱበት ሦስት ቀንም ቢሆን እየተከታተለ ይነጫነጫል እንጂ ልማታ አይልም፡፡ እኔ ደግሞ ዛሬ ቀመስኩ፡፡

ጓደኞቼ የመፈንከት ቆሌያቸው ስላልተገፈፈ ወይም የሞትኩ ያህል ስለቆጠሩኘ እንደ አስክሬን ተሸከሙኘ፡፡ ከሚጢጢ እጆቻቸው የተበጀ ርብራብ ቃሬዛ ላይ አንጋለሉኘ፡፡ ሰውነቴ ዘና ብሎ የመንሳፈፍ መንፈስ ተሰማኘ፡፡ አሁንም ፈንካቼ እየተግለበለበ ወደ ሰማየ-ሰማያት የሚሮጥ መሰለኘ፡፡ የጉም ችፍርጉን እየጣሰ ወደ ላይ....

......ከተንጋለልኩበት እንደምንም አንገቴን አቅንቼ በአንድ አይኔ ወደ ፊት አየሁ፡፡ ጋሙዳው እጆቹን ሰቅስቆ ወገቤ ስር ከትቶ ብቻውን የተሸከመ የሚመስለው ድርሻ ወስዷል፡፡ ቀጮ የያዘችው ቂርጭምጪሚቴን ነው፡፡ ሙቄ ትንሽ ከፍ ብሎ ባቴ ላይ እጁን አጋድሟል፡፡ የተረፉት በአንፋሽ አከንፋሽነት ፊት ፊት ይላሉ፡፡

"መንገድ! መንገድ!"

እንደ ጓደኞቼ እጅ የሚያንፈላስስ የሸለብታ እቅፍ ውስጥ ሆኜ የሚያስተጋቡ ድምፆች ይሰሙኛል፡፡

-ምን ሆኖ ነው?

-ጋንጩር ፈንክቶት፡፡

-እሱ ልጅ ምን ይሻላል ይኼን ድንጋይ መወርወር? አበስኩ ገበርኩ! ደሙ ማለቁ አይደለም እንዴ?

በድምፃቸው የጋሙዳ እናት መሆናቸውን አውቄያለሁ፡፡ ታችኛው ሰፈር ደርሰናል ማለት ነው፡፡ ሜዳውን ካቋረጥን እቤት፡፡በዚህ መካከል ይጋርዱ ቂጦ ድምፅ እያስገመገመ ከበበኘ፡፡

-እንዴ እንዴ መቼም ያ ጋንጩር ነው፡፡ ቆም አድርጋችሁ ደቃቅ አፈር ነስንሱበት እንጂ ደሙ እንዲያቆሙለት፡፡

ይጋርዱ ቂጦ ተፈጥሮ ሚዛኗን ስታ በተካሰረችበት አንድ ወቅት የተፈጠሩ ይመስለኛል፡ ቀጭን ወገብ፣ ጠባብ ትከሻና ትንሽ ፊት ከትልልቅ ቂጥ ጋር አላቸው፡፡
የእኛ ሰፈር ወንዶች ይጋርዱ ቂጦን ሲያዩ የሚያንኾልላቸው አንዳች ሚስጥር እንዳለ ይሰማኛል፡፡ አንድ ቀን እኔ÷ አባቴና እናቴ ከሆነ ቦታ ስንመለስ አባቴ ተገርሞ እንዲህ አለ፡፡

"የእኚህ ሴት 'ነገር' ምን ያህላል? የጤና ብለሽ?"

"ምን አሳየሽ?" ሦስት ቀን ተኳረፉ፡፡ በሦስተኛው ቀን "እውነት ምን አሳየኘ ሠይጣን ካልሆነ በቀር? አለ አባቴ፡፡

ይቅርታ ተደረገለት፡፡

ይጋርዱ ቂጦ "አይ ያቺ እናቱ፣ አሁን ስታየው እንግዲህ....." አሉ በሚያስተጋባ ቀጭን ድምፃቸው፡፡

የእናቴ ነገር ሲነሳ የሞት መቀስቀሻ ወስፌ ሆነብኘ፡፡ ሸለብታይ ጠፋ፡፡ ፍፁም ንቁ ሆንኩ፡፡ የታች ሰፈርን ጨርሰን ጨርሰን የጉድጓዱን ውሃ እንዳሳለፍን ላይኛው ሰፈር እንደርሳለን፡፡ ለስሙ ላይ ሰፈር ይባላል እንጂ ያሉት ሁለት ቤቶች ናቸው፡፡ የእኛና የነ ጋንጩር ቤቶች፡፡ ስንደርስ ምጥ ምጥ አለኘ፡፡ እናቴን ለወይን ጠጅ የቀረበ ጥቁር ፊት ብዙ ቋንቋ አለው፡፡

የእነ ጋንጩር ቤት በኮሸለለ ቅጠል ስለሚታጠር እንደ ፀናፅል እየተንሿሿ ተቀበለን፡፡

"ያ የእኔ ጉድ ነው እንዲህ ያደረገው? ምነው ሞቼ ባረፍኩት" አሉ የጋንጩር እናት፡፡ ድምፃቸውን በማድመጥ ብቻ ገጣጣ ጥርስ እንዳላቸው ያስታውቃል ብዬ አስባለሁ፡፡ እንዴት? እንጃ!

የእናቴ ድምፅ አልተሰማም፡፡ የቤተክርስቲያን ደጃፍ እንደሚሳለም አስክሬን የእኛን ቤቴ አሳይተው መለሱኘ፡፡ እነ ጋሙዳ እየደከማቸው ስለሄደ ከመንፈላሰስ ወደመንዘላዘል ተሸጋገርኩ፡፡ ሚስማር ፋብሪካ መዳረሻ ላይ ያሉት የመንደር ሐኪም ገበያ ይዘንላቸው እንዳልሔድን ሁሉ እየተነጫነጩ አንድ መርፌ ወጉኘ፡፡ ፕላስተር ደራርበው ግንባሬ ላይ የበቀለ የነጭ ቀንድ አጎጠጎጤ አስመሰሉት፡፡

አለማየሁ ገላጋይ:- የብርሃን ፈለጎች

ይሔን ምርጥ ስራ ታነቡት ዘንድ ስጋብዛችሁ በደስታ ነው፡፡ ትገረሙበታላቹ፡፡
ብዙ ነገር ትቀስሙቀታላቹ

ቤታችን እንሁን🏠🏠

እናንብብ📚📚

ለአስተያየታችሁ @jahABP
AB PHOTOGRAPY
ቦሌ መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ያለ ዛፍ ላይ የተቀረፀ አለማድነቅ አልቻልኩም፡፡

መልካም ቀን መልካም የፀሎት ጊዜ
ሁላችንም በኃይማኖታችን ስለሀገራችን ስለዓለም እንፀልይ መልካም የህማማት ሳምንት
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

በቀጣይ ስለማቀርበው መፅሐፍ ፀኃፊ አንድ ጓደኛዬ የሆነ ጊዜ ላይ ያካፈለኘን ጀባ ልበላችሁ

"ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ ይባላል። የእመጓ፣ የዝጎራና መርበብት መፃሕፍት ደራሲ ነው። የሚኖረውን የሚያስተምር ብርቱ ሰው ነው።

ስለሱ የሰማሁትን እውነታዎች ልንገራችሁ...

➊. በሚሰራበት መስሪያቤት <<ጠንካራ ስራ አስኪያጅ ስለሆንክ ደመወዝህን በእጥፍ አሳድገንልሀል>> ተብሎ በቦርድ የተወሰነለትን ደመወዝ አልቀበልም ብሎ በደብዳቤ መልሷል።

➋. ከአንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ ለስራ ተወዳድሮ ካለፈ በኋላ፣ ደመወዙ ስለበዛ ቅጥሩን ሰርዞ ያውቃል(80,000 ብር)።

➌ ከወር የቤትና የራሱ ወጪ ውጪ ያለውን የባንክ ገንዘቡን በየወሩ ለነዳያንና ለገዳማት ይሰጣል።

የዶክተር አለማየሁ መርህ ምን መሰላችሁ? የራሱንና የቤተሰቡን ኑሮ ስታንዳርድ አበጅቷል።

"ቤት አለኝ" ይልህና፤ "የቤቴን አይነት ግን አትጠይቁኝ" ይልሀል።

"መኪና አለኝ" ይልህና፣ "የመኪናዬን አይነት ግን አትጠይቁኝ" ይልሃል።

"የምኖረው ከተማ ነው" ይልህና፣ "የት ከተማ ግን እንዳትለኝ" ይልሀል።
ምክንያቱም ይላል "ከቤት በላይ ቤት፣ ከመኪና በላይ መኪና፣ ከከተማ በላይ ከተማ አለ፤ ከቀበቶ በላይ እንኳን ቀበቶ አለ፣ የቀበቶ ስራው ግን ሱሪ እንዳይወልቅ ማድረግ ነው።" ይላል።

ባጠቃላይ ዶክተር አለማየሁ ምኞትን በጥልቅ ጉድጓድ ቆፍሮ የቀበረ፣ የገንዘብን አቅም ያሰነሰ ምርጥ ሰው ነው። ሲናገር እና ሲያስተምር ደግሞ አዝናኝ ነው። የፃፋቸው አስደማሚ መፃሕፍት የሱን ህይወት ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ።"



@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD