Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
የናንተን ምርጥ ምረጡ ፲፪-፲፪-፲፪

ኑ የንጉሱን ልደት እናክብር
AB PHOTOGRAPHY
መልካም ልደት ንጉሱ😍💪💪👑🌕🌎✨💥🎂🎂🍭🍮🍩🏹🏇🏇🏆🥇🥈🎼🚗🚞🚉🚦🏠🏗☎️📺📻📡💡🕯🔧🔨⚖⚖⚖⛓🏺⚱🔬🚪🗝📈🗒📚📖🔓🔓🔓🔓🔓🔓

"ሚኒልክን ልትጠላው ትችላለህ፤ ደግሞም ልትወደው ትችላለህ። ነገር ግን ሚኒልክ ተራ ስብዕና እንዳልነበረ ለመረዳት አይከብድም። ሚኒልክ ውስብስብ ሰው ነው። ረቂቅ ነው። ደግሞ አድማጭ ነው። ሚኒልክ እንደ ገሞራ እሳት የሚፋጅ ነው። ደግሞ እንደ ምንጭ ውኃ ገር ነው። ሚኒልክ ሀገር መመስረት፣ ግዛት ማስተዳደር ያውቃል። ተራ የታሪክ ሰው አይደለም። ጉልህ ነው። የሚኒልክን ነገር ለማጉላት ብዬ ከሌሎች ማወዳደር አልፈልግም። ዳግሞም ማሳነስ ሊሆን ይችላል። "
@jahABP ነኘ #፲፪-፲፪-፲፪
AB PHOTOGRAPHY

መልካም የቡሄ በዓል ተመኘቻለሁ

ማህበረ ጎዶልያስ ዘ-ዑራኤል😍🙏😍
"ማንኛውም ሰው በያዘው መሪ ለተመሪው መሪ ነው"

መልካም አዳር
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ሁለት ወንድ

"ፍቅረኛዬን ለምን አናገርካት"

ገጭ!

"ፍቅረኛዬ ላይ ምን ታፈጣለህ"

ገጭ.....ገጭ!!

ማንንም አይፈራም፡፡ እሷ ግን ትሸማቀቃለች፡፡

እሷን አቅፎ አይኑ ወደሷ የሚወሰልተውን ይፈልጋል ገጭ!...ገጭ!..ገጭ!

አንዳንዱ ጎረምሳ ዱቄት ተነፍቶበት ከወደ ሽንትቤት ከመጣ እንደታሸ ታውቃለች፡፡ አንዳንዱ የፊቱ ሚዛን ተዛብቶ ብቅ ይላል፡፡

የመጨረሻውን ወንድ እፊቷ ሲመታው እሷ ብሳ ቱግ አለች፡፡

"አየሽ!"

"አላየኘም"

"አይቶሻል እኮ!"

"ቢያየኘስ"

የተመታው ይገላግላቸው ጀመር፡፡

"ካየኹም ይቅርታ ብሎ" ጉልበት ሊስም አጎበደደ
አንዳንዱ ወንድ ምኑ ታይቶ ነው ወንድ የሚባለው? አንድ አይኑ ተለስኗል፡፡
ይህን ስትመለከት ቅልብሽ አላት፡፡

"አሳፈርከኘ" በፍቅረኛዋ እየተለመነች እንቢ ብላ ስትሔድ....

የተደበደበው ለመናት "በእኔ ሰበብ አትጣሉ"

እንቢ ብላ ሔደች የአንዳንዱ ሰው ፍርሃት እየገረማት፡፡

ጠዋት ፍቅረኛዋ ደወለላት፡፡ "ምንድነው??"

"እስኪ ነይ"

"የት ነህ"

"እቤቴ"

"ስራህስ"

"ቀረሁ"

"ለምን"

ኦ!.....ኦ!...ነይ"

ንዴቷን ለመበቀል ጭምር ሔደች ተኘቷል፡፡ ሁለት አይኖቹ አብጠዋል፡፡ ግራ እጁ ከክርኑከፍ ብሎ ፋሻ ተጠምጥሟል፡፡


"ምንድነው??"

"እ!"

"አንቺ ስትሔጂ እሷ ፊት አላዋርድህም ብዬ ነው፡፡ በልና ይዋጣልን.....ብሎ ወንድ ነው!!
መላልሼ ብገጥመውም መላልሶ አሸነፈኘ፡፡ወንድ ነው!! አጋጣሚ ከመሰለህ ሲሻልህ ደውልልኘ ብሎ ስልኩን ሰጥቶኘ ታክሲ አሳፈረኘ፡፡

እ....በህይወቴ ሁለት ወንድ አውቃለሁ፡፡

#እሱ እና #እኔ፡፡

አለማየሁ ገላጋይ :- ውልብታ

🙏😂😂መልካም ቀን 😂😂🙏

አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኘ😊🙏
AB PHOTOGRAPHY

ድንግል ሆይ ሞትሽ ሞታችን ትንሳኤሽ ትንሳኤአችን ነው፡፡😍🙏😍

ምህረትሽ ቸርነትሽ የበዛ መዓትሽ የራቀ ትዕግስትሽ የሰፋ የመልካም የአሳቤ ፈፃሚ የምኞቴ መሉላት ስምሽ ድንቅ የሆነ የጌታዬ እናት ሆይ አመሰግንሻለሁ፡፡

በድካሜ ብርታትሽን ትገልጫለሽ በሞኘነቴ ትጠበቢያለሽ ማንነቴ አይገርምሽም አፅድተሽ የክብር ዕቃ ታደርጊኛለሽ፡፡

ይቅርታሽ እንደ ቀስተደመና ከቦኛል፡፡
በኔ ላይ ስራሽ ከትላንት ዛሬ ያስገርመኛል፡፡

የኑሮዬ ድምቀት ፣ የቋንቋዬ ጥራት፣ የመኖሬ ትርፍ የመንገዴ መጨረሻ አንቺ ነሽ፡፡

🙏እንኳን አደረሳችሁ፡፡😍
አብይ አንዷለም(የማርያም ልጅ)
😢😭😭😭💔💔🤦‍♂🙇

አስሳውሳለሁ የዛሬ ሦስት አመት ነው ትውውቃችን ከወንድሜ ጋር አንድ ክፍል ነበሩ የአርት ሰው ስለነበረች ወንድሜ እንድተዋወቃት ጋበዘኘ ገራሚ ገራሚ ግጥሞችን የምትፅፍ ግጥሞቿን አድናቂ እንደሆንኩ እና እንደምናሳትማቸው እምነት ነበረኘ ቃላቶቿ ሃይል ነበራቸው እሷ ስታነባቸው ግጥሞቿ በእውቅ ደራሲ የተፃፉ ይመስላሉ፡፡


ደስ ምትል ሳቂታ ተጫዋች ልጅ ነች ግን ብዙ ሃላፊነት የተሸከመች በብዙ ሃሳቦች የተወጠረች ልጅ ናት ሃሳቧ እሩቅ ህልሟ ትልቅ ነው...ለቤተሰቦቿ ስትል መስራት ያለባትን ብቻ ሳይሆን ከዛም በላይ ሆናለች፡፡ ጥንካሬዋ ይገርመኘ ነበር እራሴን ዞር ብዬ እንዳይ ያደርገኘ ነበር፡፡

ግራፊክስ ዲዛይን ትምርት የጀመርኩበት አመት ነበርና....እንዲህ አልኳት ግራፊክስ ትምህርት ጀምሬያለሁ አልኳት ተደሰተች.....እኔም ቃል እገባልሻለሁ የዛሬ ሦስት አመት ስትመረቂ thank you card እኔ ነኘ ምሰራልሽ አልኳት አብዬ አመሰግናለሁ የዛ ሰው ይበለን አለችኘ አሜን አሜን ተባባልን በትምህርቷ ጠንካራ ነበረች ብዙ ነገሮችን አውርተናል ስለሷ ብዙ አውቃለሁ እንገናኛለን ተባብለን በኔም በሷ የስራና የትምር ውጥረት ሳንገናኘ ቀርተናል ዘንድሮ የዛኔ ያልነው ሦስተኛ አመት ደርሶ ኮሮና አስቀረውና ለመስከረም በተሸጋገረው ምርቃታቸው እንደወንድምነቴ ቃሌን ልፈፅም thank you card እና የፎቶግራፊውንም ስራ ነገር ግዴታዬን ልወጣ ቀናትን ስንጠብቅ፡፡

ትላንት አስደንጋጭ መርዶ ለወንድሜ ደረሰው ፂዮን አርፋለች አሉት ደውለው በጣም አዘነ በጣም ለኔም ነገረኘ በጣም አዘንኩ ከልቤ😱😢😢😢😢😢😭😭💔💔💔
ማርያምን ከልቤ አዘንኩ በዚ ሰዓት መሞት አልነበረባትም ወንድሜ ለማረጋጋት አይ ሁለት ፂዮኖች ነው ያሉት አላጣራሁም አለኘ ቆይቼ አጨናነኩት እሱም እያዘነ እሷ ነች አለኘ ይበልጥ ልቤ ደማ አለም ከንቱ ሁሌም ለለፋላት የማትሆን ወጣቷ በአጭር ተቀጨች ስንት ጠንካራ ራዕይ የነበራት ፂዮን አጣናት ምርጥ ጓደኛዬን አጣኀት በጣም አዘንኩ ሁሌም በልቤ በልባችን ትኖሪያለሽ ፂዮንዬ አምላክ ነፍስሽን በአፀደ ገነት ያኑረው 💔😔😢😢😭😭 የምቶጃት እመብርሃን ከደጋጎቹ ጎን ታኑርሽ የውስጥሽን እሷው ታውቃለችና፡፡

እኔ ግን የልቤ ሀዘን ጥልቅ ነው፡፡

ልቀብራት እንኳን አልቻልኩም ምክንያቱም የተነገረን የሰልስቷ ጊዜ ነው፡፡
ይቅርታሽን እንደምትሰጪኘ እምነቴ ነው፡፡ እወድሻለሁ በኡነት እወድሻለሁ ልቤ ተሰብሯል ማመን አቅቶኛል

የተለየሽን ምክንያቱን ባላቅም

በተደጋጋሚ እንደሚያምሽ ነግረሽኘ ነበር
ያንቺን ህመም መከታተል የኔም የወንድምነቴ ድርሻ ነበር እኔ ግን ከንቱ ከማውራት ውጪ ምንም ላመጣ አልቻልኩም ይቅርታ አድርጊልኘ😢🙏...ፂ ይቅርታ አድርጊልኘ😢😢😢ሃዘኔ ጥልቅ ነው፡፡ ማርያምን ሃዘኔ ጥልቅ ነው፡፡😢😢😢😢😭😭😭😭😭😭😭😭