አላህ አለሙን ፈጠራና ቀጥሎ እሷን ለመፍጠር አሰበ ልክ ስትታይ የምታስደነግጥ የምትስብ ሁሉ የተሟላላት አጃኢብ ቱቱቱ ማሻ አላህ ከአይን ያውጣሽ የተባለላት ሴት ለመፍጠር አሰበ
ሲሞክር ሳይሳካለት ሲቀር ሲሞክር ስትበላሽበት ሲሞክር አንዱ ነገሯ ያስጠላ ሲሆንበት ሲሞክር የሆነ ነገር ሲጎላት ሲሞክር እንደፈለገው አልሆን ሲለው ቆንጆ አልሆንም ስትለው እውቀቷ ሲያንስ ሲሞክር......ሲሞክር ሲሞክር ሲሞክር..........
ይሔ ሁሉ ሴት የተፈጠረው እኮ አላህ እሷን ለመፍጠር ባደረገው ሙከራዎች ነው
ከዛ ልክ የዛሬ......21 አመት እሷን ፈጠራት ተሳካለት እሱ እራሱ ወደዳት እጄ ይባረክ አለ......ይቺ ልጅ ሀይማኖቷን አክባሪ ናት የቤተሰቧን የሀገሯን ስም ታስጠራለች እውቀቷ ብዙ ነው አለ፡፡
አብረን ስንማር እብድ
ውጤት ላይ አንደኛ ይሔማ ልትሳሳት ማይገባህ ጥያቄ ነው ባለፈው አስረድቼህ ትለኘ ነበር
ብዙ ተፎካክረን አንደኛ ግን እሷ ናት
አሁንደሞ ሐረማያ ዩኒቨርስቲ አሉኘ ከሚላቸው ተማሪዎች አንዷ ክቡራንና ክቡራት እኔ ደሞ ጓደኛዬ ይቅርታ ጓደኛ ብቻ ሳትሆን እህቴ መካሪዬ ሁሉ ነገሬ በመሆኗ በጣም ምኮራባት ውዷ ራኑ(ሩታዬ) ልደቷ ነው.....
ኧረ ለኔ ስትይ እንኳን ተወለድሽልኘ ሩታዬ መልካም ልደት ከረጅም እድሜና ጤና ጋር
አኩርተሽኛል ወደፊትም እንደምታኮሪኘ አልጠራጠርም፡፡
😘😍😘😘👏👏🤪🤪👑🎂🎂🎂🍩🍩

AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
እኛም ተረኞች ነን.....🏃♂😢😔
ዓለማችን መገፋፋት መጠላላት የበዛበት ዓለም ነው፡፡
ሕፃን ልጅ በእጁ ባለው ከመደሰት በሰው እጅ ባለው እንደሚያለቅስ እንዲሁ ሁሉን ለእኔ በሚል አመል ራሳቸውን የሚያውኩ ጥቂት አይደሉም፡፡
የሌላውን ነገር መመኘት ስንጀምር መገፋፋት ይከሰታል፡፡
ሁላችንም እኩል እንውደቅ ካላልን በቀር የሌላው የእኛ ሊሆን አይችልም፡፡
መስመር ጠብቀን ከመሮጥ የቀደመንን ጠልፈን መጣል በሐሜትና በነቀፋ ከአገር ማባረር አንዱ የመኖራችን እሴት ስርዓት ሆኗል፡፡
ስለዚህ የምንጓዘው ጉዞ የመጠባበቅ ጉዞ ነው፡፡
ጅብ ፊትና ኀላ ሆኖ አይሔድም ይባላል፡፡
ምክንያቱም አንዱ ከፊት ሲሔድ ታፋው ያምረውና የኀልኛውን ሊገምጠው ይችላል፡፡
ስለዚህ ጅብ በመጠባበቅ ነው የሚሔደው፡፡
ዛሬም የሰው ጉዞ ሳይሆን የጅብ ጉዞ የምንጓዝ መሆናችን ያሳዝናል፡፡
በማንኛውም የሕይወት አንጻር ወረፋ ቆመናል፡
ለመልካሙም ለክፉውም ወረፋ ላይ ነን፡፡
ሕይወት በዙር የምትሔድ ጽዋ ናት፡፡
በወረፋ ከዓለም ከፊት ያለው ሲጠራ ተረኛ እኛ ነን፡፡
ስለዚህ ከፊታችን ያለው መልካም ዕድል ሲያገኘ አንድ ችግረኛ ከመቀነሱም ባላይ ቀጥሎ እኛ ነንና ደስ ሊለን ይገባል፡፡
እንዲሁም ዓለም ወረፋ ነውና ከፊታችን ያለው በሞት ሲቀጣ ቀጥሎ እኛ በመሆናችን መዘጋጀት ይገባናል፡፡
ከወላጆቻችን እየተማርን ያደግነው ነገር በትምህርትና በብዙ ጥረት እንኳን መላቀቅ አይቻለንም፡፡ አልቻልንምም፡፡
በወላጆቻችን እቅፍ ሳለን ምግብ ሲያበሉን ምግቡ ጣፋጭ ነው ምግቡ ጠቃሚ ነው እያሉ አላሳደጉንም፡፡
"እገሌ ሊበላብህ ነው" እያሉ ነው ያሳደጉን፡፡
ስለዚህ ከማንኪያ ጋር የጠቀጠቁብንን አመለካከት ዲግሪ እያሳዘነው እንቀጥላለን እንጂ መተው አልቻልንም፡፡
#የሁልጊዜ ኑሮአችን እገሌ #እንዳይበላብህ ከጥጋብ በላይ መብላት ሆኗል፡፡
በዘመናችን ያለው ትልቁ የሕዝባችን ውድቀት ምንድነው? ስንል ውሸት ነው፡፡
ውሸት ዘመናዊነት የኑሮ ስልት ሆኗል፡፡
በውሸት ብዙ ነገር ሊሰበሰብ ይችላል፡፡
ነገር ግን ሰላም የለውም፡፡
ለሰዎች የምናሳየው የማታለል ጎዳና ለዘላለም አያገናኘንም እና እንጠንቀቅ፡፡
ትልቁ መባረክ በፈጣሪ ማረፍ ነው፡፡
ትልቁ ቁም ነገር ኑሮን መቀበል ነው፡፡
ትልቁ ጥበብ አሁን በሆነው መደሰት ነው፡፡
"የኑሮ መድህን"
ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንደቀነጨብኩት፡፡
እኛም ተረኞች ነንና ኑሮ ላይ ባናተርፍ እንኳን መክሰር የለብንም ባይ ነኘ
@jahABP ነኘ 😊😍🙏
🙏መልካም ጊዜ ተመኘሁ🙏
@ABPHD @ABPGD @ABPGD

ሴቶች አላቹቹቹቹቹ😃😃😃😃😃
ኑ......................ነይ
ቆየት ካለው በወቅቱ ብዙ ከተባለላቸው በደንብ ከተደመጡ አልበሞች አንዱ ከሆነው በተለይ በአሁን ሰዓት መሰማት አለባቸው ብዬ ከማስበው ዘፈኖቾ መካከል ይህ ዘፈን አንዱን ነው፡፡
መርጬላችኀለሁ ጀባ ልላቹ እፈልጋለሁ.....በደንብ ስሙት መስማት ብቻ ሳይሆን አዳምጡት.....በመጀመሪያ እራስሽን ቀጥሎ ሌሎችን እይበት....በዚህ ዘፈን ውስጥ እራስሽን ፈልጊበት፡፡
ወንዶችም አድምጡት የተዘፈነው ለሴት ስለሆነና ጊዜውን ሚዋጀው በሴቶች ጉዳዬ ላይ ነው ብዬ እንጂ እራሳችንንም እንፈትሽበታለን፡፡
ያማለት የዘፈኑ ተቃራኒ ወይም አድራጊዎች እኛው ወንዶች ነንና እኛን ይኮንናል ከገባን ነው ግን.....
አስተያየታቹን እቀበላለሁ😊😍🙏፡፡
ነገ ጠብቁኘ🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂
@jahABP ነኘ 😊🙏😊

ውድ ነሽ (Wudinesh)
ሐይሌ ሩትስ(ሐይለሚካኤል ጌትነት)
ሐይሌ ሩትስ( ሐይለሚካኤል ጌትነት)
ውድ ነሽ
ማንነትሽን ገንዘብ ላይተካው
ለምን ማንም ክብርሽን ይንካው
አንቺም ለፍተሽ ላታንሺ ከሱ
ለምን ይግዛሽ ሌላው በኪሱ
👏👏👏👏👏👏
አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኘ
መልካም ቀን ተመኘሁ
ውድ ነሽ
ማንነትሽን ገንዘብ ላይተካው
ለምን ማንም ክብርሽን ይንካው
አንቺም ለፍተሽ ላታንሺ ከሱ
ለምን ይግዛሽ ሌላው በኪሱ
👏👏👏👏👏👏
አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኘ
መልካም ቀን ተመኘሁ
ቀጣዩን ፅሁፍ እባካቹ ሁላቹም እንድታነቡት እፈልጋለሁ.............እንዳተኙ
አስተያየታችሁንም እጠብቃለሁ
ጠብቁኘ 🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂
አስተያየታችሁንም እጠብቃለሁ
ጠብቁኘ 🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
" "እኔ ለአንተአንተ ለእኔ"
የተለያየ ድርሻ መያዛችን ሕይወትን የተሟላች ያደርጋታል፡፡
ሰዎች እንደ እኛ ካላሰቡ የተሳሳቱ ፣ እንደ እኛ ካልተናገሩ ቋንቋ ያበላሹ ፣ እንደ እኛ ካልኖሩ የሞቱ ፣ እንደ እኛ ካልሰሩ ሥራ የፈቱ አይደሉም፡፡
ሌሎች አስፈላጊያችን የሚሆኑት እኛ የማንችለውን ሲያውቁና ሲያደርጉ ነው፡፡
ሁሉም ሰው ዶክተር ቢሆን ያለገበሬ ምን ይመገባል?? ዶክተሩ በእውቀቱ ተመክቶ ገበሬውን አንተ አታስፈልገኘም ቢለው ይሞኛል፡፡
የላይኛው ከታችኛው የግድ የሚፈላለግ የተለያየ ተሰጦ ተቀብለናል፡፡
ስለዚህ አንዱ አንዱን አታስፈልገኘም ሊለውና ሕይወትን ብቻውን ሊመራ አይቻለውም፡፡
ትልቁ የኑሮ የኑሮ ሚስጢር
" እኔ ለአንተ ፣ አንተ ለእኔ" የሚል ነው፡፡
የጥቁሮች መብት ታጋይ የነበረው ማርቲን ሉተር ኪንግ፡-
"በአላባማ እያለሁ ጫማዩን የሚጠርግልኘ አንዲት ሊስትሮ ነበር፡፡
ይህን ሊስትሮ ስመለከት ወደ አእምሮዬ የሚመጣ ነገር ቢኖር የቱንም ያህል ጫማዬን ብጠርገው እንደእርሱ አድርጌ ላሳምረው አለመቻሌ ነው፡፡
ስለዚህምይህ ልጅ በጫማ ማሳመር የዶክትሬት ዲግሪ አለው ብዬ ተቀበልኩ፡፡
ከኔም የተሻለ ስለሆነ አከበርኩት" ብሏል፡፡
የትኛውም እውቀታችን አዋቂ የሚያሰኘን ላላወቁት በምናደርገው መንገድ ብቻ ነው፡፡
ምክንያቱም እውነተኛ እውቀት የአገልጋይነት እንጂ የጌትነት መንፈስ የለውምና፡፡
የእኛ እውቀት አስፈላጊ የሚሆነው የማያውቁ ስላሉ ነው፡፡
ሁሉም ቢያውቅ እውቀታቸው አለማወቅ ይሆናል
ስለዚህ የማያውቁትን አክብረን ማገልገል ይኖርብናል፡፡
የትኛውም ሀብታችን ባለጠጋ የሚያሰኘን በችግር ለሚያቃስቱት ባፈሰስነው ልክ ነው፡፡
ራሱን የቻለ ባለጠጋ አይባልም፡፡
ለሌሎች የተረፈ ግን ባለጠጋ ይባላል፡፡
ስኬታችን የሚለካው ራሳችንን በረዳንበት መጠን ሳይሆን በሌሎች በተረፍንበት መጠን ነው፡፡
ዛሬ ኑሮአችንንና ሕይወታችንን እንዲገዛው የፈቀድንለት ነገር ቢኖር ንቀት ነው፡፡
ሌሎች እንዲያከብሩን እንፈልጋለን ፣ እኛ ግን ሌሎችን መናቅ እንሻለን፡፡
ሌሎችን መናቅ በአዋጅ የተፈቀደልን ሥልጣን ይመስለናል፡፡
ሌሎችን በንቀት ዝቅ ካላደረግን የተስተካከልናቸው አይመስለንም፡፡
ስለዚህ የበላይነት ስሜታችን የበታችነት መንፈስ የወለደብን ነው፡፡
የምንኖረው ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ለመቀበልም ነውና ሌሎችን...ማክበር ደግሞም ፈጣሪ የምንሰጠውን አስታቅፎ ወደ ዓለም ልኮናልና አደራችንን ማድረስ ይገባናል፡፡
በቤታችን ፣ በሥራ ቦታችን ፣ በአገልግሎታችን እየሰራን ያለን እኛ ብቻ መስሎ ከተሰማን ሌሎች የሠሩት አይታየንም፡፡
ሌሎችን መውደድ ያቅተናል፡፡
ሥራችንም ከጥቅሙ ኩራቱ እየገነነ ይመጣል፡፡
በሌሎች ላይም እምነት እያጣንም የርክክብን ሥርዓት እናፈርሳለን፡፡
ራሳችን አልሚ ሌሎችን አጥፊ ሆነው እየታዩን ነቃፊ ብቻ እንሆናለን፡፡
የዓለማችን ትልቁ የኢኮኖሚ አቅም ፣ የሰላም መሰረት ግብረ ገብነት ወይም የሞራል ሕግ ነው፡፡ የሥነምግባር መሰረቱ ሃይማኖት ነውና ሃይማኖትን መጥላት ተገቢ አይደለም፡፡
ሰዎችን ከሕግ ፣ ከፍልስፍና ይልቅ ሃይማኖት የመግዛት አቅም አለው፡፡
ብዙ ባለ ራዕዯች ነን የሚሉ ሃይማኖትን በቀና መንፈስ አያዩትም፡፡
ሃይማኖት ግን የልምድ ሳይሆን የተፈጥሮ መሻት ነው፡፡
መስራት ፣ መማር ፣ መልፋት ፣ መትጋት ብቻውን በቂ አይደለም ሃይማኖት ያስፈልጋል፡፡
ዓለም ድፍርስ ውሃ ነው፡፡
ስለዚህ ማንነትን አያሳይም፡፡
እንደውም እውነትን የሚሸፍን በመሆኑ ምንመ ያልበራለትን የብርሃናት አለቃ ፣ ሰነፉን የትጉሃን አለቃ እያለ ያሞካሻል፡፡
ዓለሙ የሽንገላ ፣ የመዳለል አለም ነው፡፡
ሰዎች መንፈሳዊ መፅሐፍትን የሚጠሉት እውነት ስላልሆነ ሳይሆን ኃጢአጣቸውን ስለሚነግራቸው ነው፡፡
ዓለሙ የንግግር መክፈቻው "አንተ ለአንተ" ወይም "ሀይልህን አውጣ" የሚል ነው፡፡
ዛሬ የሰው ልጆች ሌላውን እንጂ ራሳቸውን ማየት አልቻሉም፡፡
ተራችንን ጠብቀን መቆም ፣ ቀጥሎ መመልከት ከዚያም መጠየቅ በመጨረሻም መጓዝ ነው፡፡
ካልቆምን መመልከት ፣ ካልተመለከትን መጠየቅ ፣ ካልጠየቅንም መጓዝ አንችልም፡፡
መቆም ለቀጣዩ ጊዜ ያዘጋጃል ፣ ለቀጣዩ ጉዞም ኃይል ይሰጣል፡፡
በክፉ ጎዳና የሚጓዝ መቆም ያስፈልገዋል፡፡
የመጣበትንና የሚሔድበትን የሚያየው በመቆም ብቻ ነው፡፡
በመቆም በፀጥታ ውስጥ ሆኖ ራስን መገምገም ፣ ከዚያም መመልከት ቀጥሎም መጠየቅ በመጨረሻም ዕረፍት ወዳለበት ደሴት መጓዝ፡፡"
ራዕይ ያለው ትውልድ
ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንደቀነጨብኩት
መቆም.... ራስን ማየት ...ከኛ የተሻሉ ሰዎች እንዳሉ ማመን፡፡
ከትላንት የተሻልን ብቻ ሳይሆን የበለጠ ለመሆን መሞከር፡፡
ማርቲን ሉተር ኪንግ ግን ሳሚሻን(DOC SHOESHINE) አስታውሶኛል 11-12 እስካሁንም ድረስ ሚኒልክ ትምህርትቤት ደጅ😍🙏😊 ሳሚሾዬ
ተስፋ አለን እንደርሳለን ለዛሬ ብቻ አይደለም ነገንም ለማየትም ነው ከትላንት ያለፍነው፡፡
😍መልካም አዳር😊
@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD

ያኔ ማስታወሻዬ ላይ እንደዚህ ብዬ ፅፌ ነበር......
በጣም ደስ ይላል ንፋሱ አየሩ መንፈስን ያድሳል ብቻዬን ሆንኩ እንጂ🤦♂😔
እዚ ቦታ መምጣት ከምቶዳቸው ጓደኞችህ ጋር ቀጥሎ ከፍቅረኛህ ጋር ከዛ ደሞ ከቤተሰብህ ጋር....በእርግጠኘነት ያበደ ጊዜን ነው ምታሳልፈው ኡፍ AM IN LOP WITH ሃዋሳዬ😍😍😍😘😘 እንግዲህ ካልኳቸው ሰዎች ጋር ለመምጣት እግዚአብሔር ያብቃኘ ደሞ አይቀርም💪💪🙏፡፡
ተፃፈ 10:59 ሃዋሳ ሌዊ ሪዞርት
ጥር 2012

የቀጣዩ ፅሁፍ
ፀሀፊው፡- ሙሀዘጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ነው፡፡
እኔ በጣም ተመችቶኛል ወድጄዋለሁ
ጠብቁኘ🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂
ፀሀፊው፡- ሙሀዘጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ነው፡፡
እኔ በጣም ተመችቶኛል ወድጄዋለሁ
ጠብቁኘ🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂
AB PHOTOGRAPHY GRAPHIC DESIGN
🤔መንገድ ያለው ከውጪ አይደለም🤔
ሁለት ወንድማማቾች እናታቸው ስታርፍ በቤት ውስጥ ያገኙት ትልቅ ገመድ ብቻ ነበር፡፡
ታላቁ ልጅ እጅግ በመበሳጨቱ ገመዱን ጠቅልሎ ጣራ ላዬ ወረወረውና ከቤት ወጥቶ ሔደ ፡፡
ታናሹ ግን ምንም ቢሆን ገመዱ የእናቱ ማስታወሻ ቅርስ ነውና እንደምንም ብሎ ጣራ ላይ ወጥቶ አወረደው፡፡
ከባዱ ጥያቄ ግን ከዚህ በኀላ ያለውን ኑሮ እንዴት ነው መግፋት ይችላል? የሚለው ነው ነበር፡፡
ለብዙ ሰዓታት ተቀምጦ አሰበበት ምንም ነገር ግን ሊታየው አልቻለም መንገዱ ሁሉ በግንብ የታጠረነው አስቦ አስቦ ወደ አንድ ጠቢብ ዘንድ ሔደ፡፡
ጠቢቡ ሰው እንዳገኘውም የጠየቀው ጥያቄ "ምን አለህ" የሚል ነበር፡፡
መልሱም ቀላል ሆነ "ምንም"
ጠቢቡም ሰውም "በዓለም ላይ ምንም የሌለው ሰው የለም፡፡ ምናልባት ግን ጥቂት ብቻ ያለው ሰው ሊኖር ይችላል፡፡
ለምሳሌ:- አንተ ከወንድምህ በተለየ ጥበብ አለህ ይህም ጥበብ ነው ወደ ጠቢቡ ያመጣህ አለው"
ልጁ ግን በእርግጠኘነት እየማለ ምንም እንደሌለው ተናገረ፡፡
ጠቢቡም "ይህ ፈፅሞ ሊሆን የማይችል ነው፡፡ ሰው ሆኖ ምንም የሌለው የለም፡፡ ረስተኸው ነው እንጂ አንዳች ነገር አለህ" አለው፡፡
ልጁ ቢያወጣና ቢያወርድ ያለውን ነገር ሊያገኘው አልቻለም፡፡
የሚያውቀው ምንም እንደሌለው ብቻ ነው፡፡
ያን ጊዜ ጠቢቡ ልጁን ይዞት ወደ አንድ ክፍል ገባ፡፡ ክፍሉ ሊዳሰስ በሚችል ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ የተሞላ ነው፡፡
ጨለማው አይን ሊወጋ ይደርሳል፡፡
ከጠቢቡም ጋር በዚያ ክፍል እንደገቡም
"ምን ይታይሃል?"አለና ጠየቀው ልጁም ወዲያውኑ ነው መልሱን ያገኘው "ጨለማ"
ጠቢቡ ግን እንደገና ጠየቀው፡፡ "ሌላነገር አለ ፈልገው" ዘወር ዘወር አለ ምንም ግን ምንም የለም ጠቢቡ እንዲህ አለው "ና አብረን ቁጭ እንበልና ጊዜ ወስደህ ተመልከት"
ተቀመጡም ልጁ በግራና በቀኘ በፊትና በኀላ ማየት ጀመረ፡፡ ለብዙ ደቂቃዎች አየ በመካከልም ላይ "አሃ" የሚል ድምፅ ከልጁ ሲወጣ ተሰማ .............ይቀጥላል
ጠብቁኘ🏃♂🏃♂🏃♂ ገራሚ ታሪክ ነው🏃♂🏃♂

ልጁ በግራና በቀኘ በፊትና በኀላ ማየት ጀመረ፡፡ ለብዙ ደቂቃዎች አየ በመካከልም ላይ "አሃ' የሚል ድምፅ ከልጁ ሲወጣ ተሰማ፡፡
ጠቢቡም " እሺ ምን ተገኘ" አለው
"በዚያ በኩል ባለው ቀዳዳ ብርሃን ነገር ይታየኛል" አለው
ጠቢቡም አቀፈው
"አሁን አይምሮህን መጠቀም ጀመርክ፡፡ አእምሮን መጠቀም ማለት ከአይነ ስጋ ይልቅ በዓይነ ልቡና ማየት መቻል ከእዝነ ልቡና መስማት መቻል ማለት ነው፡፡ "ልብ ካላየ አይን አያይም" ሲባል አልሰማህም አእምሮን የሚጠቀም ሰው ሁሉ የሚያየውን ብቻ ሳይሆን የማያየውንም ያያል፡፡
ለዚህ ነው አእምሮ ያለው ሰው ተስፋ የማይቆርጠው፡፡ አእምሮ ያለው ሰው በግንብ መካከል በር ፣ በጨለማ መካከል ብርሃን ፣ በተራራ መካከል ፣ ሕይወት ይታየዋል፡፡
መንገድ ያለው ከውጪ አይደለም፡፡
መንገድ ያለው ከውስጥ ነው፡፡
የውጪው መንገድ እግር ነው የሚሔድበት፡፡
የውስጡ መንገድ ግን ልቡና ነው የሚጓዝበት፡፡
በልቦናቸው የሔዱ ሰዎች ናቸው በእግራቸው ለመሔድ ፈልገው የእግሩን መንገድ የሰሩት፡፡
ከእነርሱ በኀላ ግን ብዙዋች በልቡናቸው ሳያዩ ይጓዙበታል፡፡
መጀመሪያ በልቦናቸው የበረሩ ሰዎች ናቸው አውሮፕላንን የፈጠሩት መጀመሪያ በልቡናቸው የተገናኙ ሰዎች ናቸው ስልክን የሰሩት እናመ መንገድ ያለው ውስጥህ ነው፡፡
አንተ ውስጥ መንገድ አለ፡፡
ምን አልባት ያ መንገድ #አልተጠረገ ከሆነ #ጥረገው #ተጎድቶ ከሆነ #ጠግነው #አርጅቶ ከሆነ #አድሰው ከዚያ በኀላ ሁሉም ነገር ቀላል ነው፡፡
ጊዜ ውሰድ፡፡
ለማየት ጊዜ ውሰድ፡፡
ወሳኙ የጨለማው መጠን አይደለም ወሳኙ አንተ የሰጠኸው ጊዜ መጠን ነው፡፡ ለማሰብ የምትወስደው ጊዜህና የምታስብበት መንገድ ነው፡፡
ጊዜህን ወስደህ ባሰብክ ቁጥር ያለኸው ጨለማ ውስጥ አመሆኑን ታውቀዋለህ፡፡ እስኪ ትንሽ ጊዜ እንውሰድ"
ሁለቱም ጥቂት ጊዜ ተቀመጡ
ያልጅም ማየት ጀመረ....
እስከዚያም በዓለም ላይ ታዋቂ የሆነውን
"የተጠማውን ቁራ ታሪክ" ልንገርህ
ቁራው ውሃ ጠማውና በአካባቢው ወዲያና ወዲህ እያለ መፈለግ ጀመረ፡፡ ግን አላገኘም፡፡ በመጨረሻም በውሃ ጥም ወደቀ፡፡ ነገር ግን ተስፋ ለመቁረጥ አልፈለገምና እንደምንም ብሎ ተነስቶ አካባቢውን ማማተር ጀመረ፡፡በሩቁም አንድ ገንቦ አየ ወድቆ እየተነሳ ገንቦው ጋር ደረሰ ሲያይ ጥቂት ውሃ ውስጡ አለ፡፡
ማንቁርቱን አስገብቶ ሊጠጣ ሲሞክርየገንቦው አንገት ጠባብ ስለነበር አልቻለም፡፡ገንቦውን ሊያዘነብለው ሲገፉውም ዐቅሙ ተዳክሞ ነበርና ያንን ከባድ ገንቦ መግፋት አልተቻለውም፡፡
"ማሰብ ጀመረ፡፡ መንገድ ከውስጥ ነውና ውስጡ መንገድ ፈለገ መንገዱንም አገኘው፡፡
በአካባቢው ያሉትን ጠጠሮች እየለቀመ ወደ ገንቦው ውስጥ መጣል ጀመረ ለብዙ ጊዜ ሲጥል ገንቦው በጠጠር እየተሞላ ውሃውም ወደላይ እየወጣ መጣ፡፡ በመጨረሻም የገንቦውን ታችኛውን ክፍል ሞላውና ውሃው ወደ ገንቦው አፍ ደረሰ ቁራውም ጠጣ፡፡"
በታሪኩ ትረካ መካከል ልጁ አንዳች ቅርፅ ያለው ነገር ተመለከተ፡፡ መሥመር ያለው ነገር ከወለሉ ጀምሮ ወደ ጣራው የተሰመረ፡፡ አይኑን ከታች ወደ ላይ እያንከባለለ ተከተለው፡፡ አንዳች የብርሃን ቀጭን መሥመር ከታች ወደላይ ሄደና እንደገና ወደ ግራ ዞረ ተከተለው፡፡ ከግራ ደግሞ ወደ ታች ተጠመዘዘ አብሮትም ሔደ፡፡ ከዚያም ተመልሶ ወለል ላይ ደረሰ፡፡
"ያ የብርሃን መስመር ምንድነው አለው ጠቢቡን"
"ጠጋ ብለህ እየው"
ፈራ
"አትፍራ ጨለማውን ሳትፈራ እንዴት ብርሃኑን ተፈራለህ፡፡ ምንጊዜም የማያቁት ነገር ያስፈራል ሂድ ተጠጋ፡፡"
ሄደና ተጠጋ፡፡ የጣውላ በር በሚመስለው ነገር ዙሪያ የሚገባ ብርሃን ነው፡፡
"እስኪ ንካው" አለው ጠቢቡ እየፈራ እየደፈረ ነካ አደረገው፡፡ ጣውላ ነገር ነው፡፡
"በምትችለው አቅም ሙሉ ግፋው" አለው ላቡ ጠብ እስኪል ገፋው፡፡ ሲጢጢጢ እያለ በመጨረሻ ያ ጣውላ የመሰለ በር ነገር ወደ ኀላ ወደቀ፡፡ ያን ጊዜ በውጪ ያለው ብርሃን ፏ ብሎ ገባ፡፡ ዓይኑን ጨፈን አድርጎ ሲገልጠው በበሩ ፊት ለፊት ሰፊ መንገድ አለ፡፡
"በሕይወትህ ለመለወጥ ከፈለክ ሦስቱን መሰረታዊ ነገሮች አሁን ተምረሃል" አለው፡፡
ምንድናቸው??
"መጀመሪያ እምነት ነው፡፡ ምንግዜም መንገድ አለ፡፡ ሊዘጋ ሊታጠር የማይችል መንገድ አለ፡፡ እርሱም አንተ ውስጥ ነው፡፡ ጊዜ ስጥ ለማሰብ ጊዜ ይኑርህ ምንጊዜም በፍለጋ ላይ ሁን፡፡
አሁን ያልታየህ ቆይቶ ይታይሃል ነገር ለመቁረጥ እንጂ ተስፋ ለመቁረጥ አትቸኩል፡፡ "ገና አላገኘሁትም እንጂ የለም አትበል"፡፡
አለ ግን አልደረስክበትም፡፡
#መድረስ "ጊዜና "ጥረት ይጠይቃል፡፡
ሦስተኛ ያገኘኸው ነገር ያገኘኸው አጋጣሚን ንካው፡፡
ካልነካኸው በሩ ግድግዳ እንደሆነ ይቀራል፡፡
ከነካኸው ግን በሩ መንገድ ይሆናል፡፡
ብርሃን ማየትህ ብቻ ዋጋ የለውም ብርሃኑ እንዳይገባ ያደረገውን ነገር መንካት አለብህ እክ?ኪወድቅ ብርሃኑ በሚገባ እስኪገባ መንገዱ ወለል እስኪል መግፋት፡፡
"ሳይነኩት በምኞት ብቻ የሚወገድ ችግር የለም የሚከፈትም በር የለም አየህ ማሰብ የብርሃን ጭላንጭልን አሳየህ ጊዜ ሰጥቶ ማስተዋል ይህንን በርገለጠልህ መንካት ደግሞ መንገዱን
አሳየህ፡፡ አሁን አይበቃህም??"
"ይበቃኛል"
"ታዲያስአሁን ምን አለህ"
"ገመድ አለኘ"
ሂድ ጊዜ ሰጥተህ ፣ መጣፍ አገላብጠህ ፣ ዐዋቂ ጠይቀህ ፣ ግራ ቀኙን አስብ፡፡
ይህች ገመድ ህይወትህን የመለወጫ ምክንያት ትሆንሃለች የባለፀጋነት መጀመሪያ የሥልጣን እርከን የሊቅነት ፋና ፣ የጀግንነት መንስኤ ትሆንሃለች፡፡
ያለበለዚያ ደግሞ #የመታነቂያህ መሳሪያ ትሆናለች ሁለቱም በእጅህ ነው፡፡"
ብሎ አሰናበተውና...........ሔደ
ዕንቁ መፅሔት ግንጣይ ገፅ ጥቅምት 2005
ሙሃዘ ጥበባህ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
ማልዋኪ ፣ ዊስኮንሲን
እኛስ ያለን ምንድነው??
ባለን ነገር ምንፈልገው ነገር ማምጣት አንችልም??
በደንብ እንችላለን....
የዛሬ መጨለም አይደለም ጨለማው ላይ መንገድ እንዳለ ማመን ነው💪እምነት ሁሉንም ይፈታዋል፡፡
ተስፋ ማድረግ ነው፡፡
ጊዜ ወስዶ ማሰብ ነው ከራስ ጋር ማውራት ነው
ችግር ላይ ስትሆን ከማማረር መፍትሔ መፈለግ ነው፡፡
ይሔን አስታውሱ አለም ላይ ምንም የሌለው ሰው የለም የሆነ ነገር አለን ዋናው ነገር አውጥቶ መጠቀሙ ላይ ነው፡፡
ፍርሃትን እናሶግድ
ምንግዜም መንገድ አለ......
እንበርታ እንጠንክር ፈጣሪ ወደ አለም አስታቅፎ የላከንን ተሰጦ አውጥተን እራሳችንንም ሌሎችንም እንጥቀም እንርዳ
አእምሮአችንን ለበጎ ነገር እንጠቀምበት
ዛሬ እዚህ ደርሰናል ሩጫችን ነገ ላይ ዛሬን ላለመድገም ይሁን
ጊዜ ሁሉን ይፈታል ከጣርን ሁሉም ይሳካል፡፡
@jahABP ነኘ

የዛኔ አልበሟ እንደወጣ ሊያስጠኑን ልናጠና በሚል ሰበብ እንሰበሰብ ነበር ከዛ በ90ዎቹ ራዲዮ😍ድምፁን ቀንሰን የሷን ዘፈኖች መኮምኮም ነው፡፡
በደንብ ሰምተናታል የዛኔ ትንሽ ልጆች ብኖንም ብዙ ባናስተውልም ዘፈኖቹ ስለማይሰለቹም እስካሁንም ስለምንሰማው መልክቶቹ ሀይል አላቸው........እናም አንዱ ዘፈኗ በዚህ ጊዜ መደመጥ አለበት አልኩና ልጋብዛችሁ ፈለኩ
ወይ ኤልያስ መልካ ያስገርመኛል በኡነት ምን አይነት ሰው ነው ብዬ ሁሌም እራሴን እጠይቃለሁ ብሶታችንን ያወጣዋል መናገር ማለት ምንፈልገውን በድንቅ አእምሮው ወረቀት ላይ ያሰፍረዋል ምርጥ ግጥም አድርጎ ግጥሙን የሚያጎላ ዜማ ፈጥሮለት ከሚገርም ቅንብሩ ጋር እንካቹ ይለናል እኛም እንደነቃለን ውስጣችን ያለው ሀሳብ ነውና ተደስተን እንቀበላለን ኡነቱን እኮ ነው ግን እንላለን እኛም እንፈላሰፋለን ቆም ብለን እንጠይቃለን..........
ታላቁ ኤልያስ መልካ😍😔😢
አንተ ትለያለህ ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን🙏
ከፈጣሪ ጋርም በሷ ድንቅ ድምፅ እንዲህ እያለ ሙግት ይገጥማል
ዘፈን ብቻ ሳይሆን ፍልሰፍና ነው፡፡
ጥያቄ ነው ጥያቄው ለሰው አይደለም ለሱ ለፈጣሪ ነው..........
ምን እያለ??🏃♂🏃♂🏃♂
ነገ ጠዋት ጠብቁኘ🏃♂🏃♂🏃♂
ተስፋ አለን እንደርሳለን ለዛሬ ብቻ አይደለም ነገንም ለማየት ነው ከትላንት ያለፍነው...... 🏃♂
@jahABP ነኘ
😊መልካም አዳር🙏

Track 7
Zeritu
ዘሪቱ ከበደ😍😘
"Track 7" የእኔም አይን አይቷል
አንዱን ሊያደድነው አንዱን ሊያሞኘው
ከአንዱ በፈሰሰ አንዱን ሊያርሰው
ላዘነው ሰው ምነው ቢያካፍለው ቢያቻችለው
ለዘረፈው ምነው በቃህ ቢለው
ይብቃህ ቢለው
አንዱ በዝቶበቶ ሲቸገር መምረጥ
ሌላው ምንም አጥቶ ላይ ታች ሲሮጥ
ላዘነው ሰው ምነው ቢያካፍለው ቢያቻችለው
ለተረፈው ምነው በቃኸ ቢለው
ይብቃህ ቢለው
ለመኖር ሲጓጓ ለማየት የፊቱን
ግን ሳይወድ ይሔዳል ሳይደርስ ምኞቱ
ሌላው ተዘጋጅቶ ሲጠባበቅ ቀኑን
ከርሞ ይበተናል እያለ በሞትኩኘ
ኦ ምን አለፋኘ መልሱ ከጠፋኘ
እሱ አይሳሳት ሁሉም በምክንያት
የኔም አይን አይቷል እሱ ያበራው
ሰሪ አይበልጥም ወይ ከተሰራው
ሰርቆ ለበላ ይበዛለታል
የታመነ አጥቶ ይንከራተታል
ለሚገባው ምነው ቢሆንለት ቢሳካለት
ለሚያምታታው ምነው ቢታይበት ቢቀጣበት
በፅናት ሲታገል ልልፋ እስኪያልፍ እያለ
ሳያልፍለት ያልፋል እንደተቃጠለ
ሌላው ግን ሳይለፋ ሳይጥር እንደደላው
ተስማምቶት ይኖራል አንድ ቀን ሳይከፋ
ኦ ምንአለፋኘ መልሱ ከጠፋኘ
እሱ አይሳሳት ሁሉም በምክንያት
የእኔም አይን አይቷል እሱ ያበራው
ሰሪው አይበልጥም ወይ ከተሰራው
ግጥም....ዜማ.....ቅንብር ታላቁ ኤልያስ መልካ
😍🙏🙏😘😘😔😢😢😭😭
👏👏👏👏እነቱን እኮ ነው እሱ ፈጣሪ አይሳሳት ሁሉንም በምክንያት ነው ሚያደርገው🤷♂🤷♂🤷♂🤷♂🤷♂
ኤላ አንተ ትለያለህ🙏🙏🙏
መልካም ዕለተ ቅዳሜ ተመኘሁ @jahABP ነኘ

ሁሌም ከፊት ለፊት በኢትዮጽያ ሙዚቃ
ጥበብ እሱ እራሱ ስሙ ኤልያስ መልካ፡፡
ገጠምኩ ወይስ ተቀኘሁ
ኤልያስ መልካን ካጣነው ድፍን አንድ አመት ሞላን 😭😢😭
በከተማ መመነን እንደሚቻል ያሳየ ክፋትን በስራዎቹ የተጠየፈ ፍቅርን የሰበከ ፍቅርን ሆኖ በተግባር ያሳየ ሳይሞት ስለራሱ የዘፈነ ሁሉም ነገር ከፈጣሪ እንደሆነ የሚያምን......በፈጣሪ ትልቅ ዕምነት የነበረው ኤልያስ መልካ፡፡
ነበር ብሎ ማውራት ምንኛ ያማል😔😢😭😭🙇በቀጣይ ስለ ኤላ ከአንድ ታሪክ ጋር ልመለስ
1ኛ አመት መታሰቢያ🙏🙏

ስለ ኤልያስ መልካ ህይወት ሳስብ አንድ ታሪክ ትዝ ይለኛል....
አስታውሳለሁ በአባቴ ቤት ካሳንችስ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ፀሎቴን አድርሼ ቦታዬ ላይ ተቀምጫለሁ አንድ አባት እያስተማሩ ነው........ ድምፃቸው በደንብ ይሰማኛል
...........እግዚአብሔር አይሳሳትም ሁሌም ትክክል ነው ይላሉ.........
እኔም እውነት ነው እሱ አይሳሳት ሁሉም በምክንያት እላለሁ.....
ከዛ አንድ ትምህርት ጀመሩ
እኔም በጥሞና ተከታተልኩ......እንዲህ ይላል.....
አንድ ሰውዬ ከብዙ ጊዜያት የንግድ ጉዞ በኀላ ወደ ሀገሩ ይመለሳል...... ከቀዬው እንደደረሰም ድል ያለ ድግስ ያያል....ተገርሞ ምንድነው ብሎ አጠገቡ ያገኘውን ሰው ይጠይቃል......
ሰውዬውም አይ የሀገሩ ንጉስ አርፈው ነው ይላል
እንዴ ይህ ንጉስ ህዝቡን ሲበድል ያለውን ሲቀማ አባቶችን ያለ ክፍያ ሲያስለፋ
እናቶችን ሲያስለቅስ
ወጣቶችን ሲገል....ሲያሳድድ አይደለም እንዴ የኖረው.......ይኸው እኔም በሱ የመጣ አይደል ከሀገሬ ተሰድጄ በሰው ሀገር ስሰቃይ የኖርኩት
እንዴት እንዲህ ድል ተደርጎ ይደገሳል ሰርግም አይደል ሞት ይላል..... በአካባቢውም የነበሩት ጥለውት ይሸሻሉ........እሱም እጅግ እየተበሳጨ
ከራሱ ጋር እያወራ ወደ ቤቱ መንገዱን ይቀጥላል
🤦♂🚶♂🚶♂
ከግማሽ ሰዓት ጉዞ በኀላ ወደ ቤቱ እንደመድረስ ሲል ከሩቅ ከሰፈራቸው ደብር አካባቢ በጫካው ውስጥ የተሰበሰቡ ሰዎች ያያል ምን ሆነ ወይ ጉዴ ማን አረፈ ይሆን ብሎ ርምጃ ሳይሆን እንደ ሩጫ ወደ ቤተክርስቲያኗ ነጎደ.........ሲደርስም ምን ተፈጠረ ማን ምን ሆነ አለ አለ በድንጋጤ ሚሆነውን አቷል
ሰዎችም ለማረጋጋት እየሞከሩ የቤተክርስቲያኑ እጅግ የተወደዱ ቄስ እከሌ ናቸው...... አሉት ኮትኩተው አሳድገውታልና ክፉኛ አለቀሰ ወደሳቸው ወደ ሬሳቸው ቀርቦ ሲመለከት ይባስ ብሎ የሞቱት በጅብ ተበልተው ነው......ከቅድሙ ይቀልጥ እየጮኸ አለቀሰ....
ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ....ወይኔ አባቴን.....አባቴን.....ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ....
ለያዣ አስቸገረ...... ለምን እኮ ለምን እያለ እያለቀሰ እየጮኸ ወደ ቤተክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ
ገባ........
በትልቁ የመድኃኒዓለም ስነስዕል ፊት እየጮኸ ተንበረከከ ለምን ለምን አንተ ኡነተኛ ፈራጅ ሆነህ ሳለ ለምነ ወይስ አይደለኸም??
ለምን እንዲህ ታረጋለህ መልስልኘ ለምን......ለምንንንን???
ስንት ሰው ሲበድል የነበረውን የስንት ሰው ሞት ተጠያቂ የሆነውን የስንት ሰው እንባ ያለበትን ሰውዬ ሞቱን ድል አድርገኸ ደግሰህ ሞቱን እየሸኘህ.........
ለስምህ ሲሉ ደፋ ቀና ያሉ ሌት ተቀን ሲያገለግሉህ ህዝቡን ወደ ንሰሃ እያሉ ከደጀ ሰላሙ እንዳንጠፋ ያደረጉ ህፃናት ሀ...ሁ...አቦጊዳ የመገቡ ስንት ዲያቆናትን ያወጡ ስለስምህ መከራን የተቀበሉ ገደልክ.....እሱስ ይቅር እሱስ ይቅር እንዴት አሟሟታቸውን እንኳን ምናለ ብታሳምረው ይሔ ልክ ነውውውውውውው ይሔሔሔ ልክ ነው መልስልኘ በጅብ በጅብ አስበልተኸ ትገላቸዋለህ ምን አይነት ጨካኘ ነህ ኡኡኡኡሐ ለምን መልስልኘ እያለ ያለማቋረጥ ይጮኻል......
እግዚአብሔርም አምላክም ድምፁን አሰማ እንዲህም አለ.....
ልጄ ሆይ ስማኘ ማዘንህን አይቻለሁ ለቅሶህን ሰምቻለሁ እንባህም እኔ ጋር ደርሷል ግን ልጄ ምክንያቴን ግን ልብ ብለህ አድምጠኘ
ያንጉስ የሰራውን ሀጢያት ረስቼ ወይም ዝም ልል ፈልጌ አይደለም እኛ ካህን ያደረጉትን ፅድቅ ጠፍቶኘ አይደለም እኔ ልብና ኩላሊትን ምመረምር አምላክ መሆኔም አትዘንጋ.....ግን ምክንያቴ ይህ ነው..........
ንጉስ ብዙ ሀጢያቶችን ሰርቷል ይህ ሚደበቅ አይደለም ግን ንጉስ በምድር ህይወቱ የሰራቸው ትንንሽ ደግ ነገሮች ነበሩ እነሱን በማሰብ ሰማይ ቤት ሊቀጣ የሀጢያት መዝገቡ ሲገለጥ ከንቱ የሆነ አስቧቸው ያልሰራቸውን ትንንሽ ደጋግ ስራዎች እንዳያነሳ እዛው ምድር ላይ በትንሹ እየከፈልኩት ነው.........
እኛ ፃድቅ አባትም በምድር ላይ ሲኖሩ የሰሩት ትንሽዬ ክፉ ስራ ነበራቸውና የፅድቅ መዝገባቸው ሲከፈት ጥንት ጠላታችን ዲያቢሎስ ሆን አስበው አቅደው ያልፈፀሙትን ሀጢያት እንዳይናገር እዚሁ ቀጥቻቸው ሰማይ ቤት ነፃ እንዲሆኑ ነው አለው፡፡
ይህን ታሪክ ወደ ታላቁ ኤልያስ መልካ አዙሬ አሰብኩት....
ማቆ ጠቁሮ ከስቶ መልኩ ጠፍቶ የነበረው
አለበት የተባሉት በሽታዎች እንዳለ የምድር ትንንሽ ሀጢያቱ ሰማይ ቤት እንዳይጠየቅበት የተቀበላቸው አይመስላችሁም ለኔ በደንብ ይመስለኛል፡፡
😍ነፍስህን በአፀደገነት ያኑርልን🙏
እሱ አይሳሳት ሁሉም በምክንያት
😢😢😢😢😭😭😭😍🙏🙏🙏