AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
ዛሬ ካላንደር ዝግ ነውና እቤቴ ቁጭ ብዬ ወትሮ የማደርገውን ተግባር ለመከወን የመፅሐፍ መደርድርያ ላይ ከተቀመጡ መፅሐፎቼ ውስጥ በዲ/ን አሸናፊ የተፃፈው መፅሐፍ ቀልቤን ገዝቶኝ ነበረና አንስቼ ገፁን እየገለጥኩ ማንበብ ጀመርኩ እስካሁን በውስጤ የሚመላለሰውን ጥያቄ ያዘለች የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ ቁልጭ አድርጋ የምታሳይ ሀሳብ አገኘውና ለውድ ቤተሰቦቼ የዝህ ቻናል ተከታይ ለሆናችሁ ማካፈል ወደድኩ፡፡ ከታች ፅሁፉን አስፍርያለሁ እስቲ እንደ ዜጋ የሚሰማችሁን ሀሳብ አጋሩ፡፡
.......ከሁለም በላይ ኢትዮፕያዊነት መጠን ሳይለካ ተፈረንጅ የፖለቲካ ቀሚስ ለሀገሬ ላልብሳት በሚል ፈሊጥ የመጣ ዕልቂት ነው፡፡ በዚህም ነጭና ቀይ ሽብር በማለት ገዳይም ሟችም ሁሉም የሚያፍሩባት እልቂት ተፈፅሟል፡፡ ንጉሳዊ ሥርዓትን ገርስሶ ሥልጣኑን ወታደራዊ መንግሥት ሲይዝ በደጅ ደሞ ኢሕአፓ ፣ መኢሶን ፣ ሰደድ ፣ የአብዮትቱ ጥበቃ፣.........እየተባለ እርስ በርሱ ተላለቀ፡፡
የእኛን እየተወን ኢትዮፕያዊነት ቋሚ ሆኖ ግዛት ግን እየጠበበ እዚህ ደርሰናል፡
ለረጅም ዘመናት የወንድሟሟቾች እልቂት አስተናግደናል፡፡ ያለፋት አርባ አመታት ለውጥ ፈላጊው ትውልድ ለውጡን በሚያስተናግድበት መድረክ መርሐ ግብር ተጣልቶ ጦር ተማዟል፡፡ እናሸንፋለን እናሸንፋለን ትልቅ ርዕስ ሁኖ አፋጅቷል፡፡ "ወዝ አደር" እና " ላብ አደር" የሚለው ሰፊ ጠብ አስነስቷል፡፡ ወዝ የደላው ነው ፣ ላብ ግን የከርታታ ነው ተብሏል፡፡ ከአንድ ንጉስ ጥሎ አርባ ነገስታትን ዳኞችን ምኞት ያፈራ ነው ፣ የሀሳብ ልዩነት ማስተናገድ ያልቻለው የአርባ አመቱ ጉዞ የትውልድ ክፍተት እስኪፈጠር አንድ ትውልድ አሳጥቶናል፡፡ የተረፈውም ተምሮ እንዳይደገም በማለት የድንበር የድንበር ድንጋይ በማስቀመጥ ገና በጥፋት እየፀናና እየተፅናና ይገኛል፡፡ ወንድምን ገድሎ ጠላትን ደመሰስኩ ማለት የተለመደ ንግግራችን ሁኗል፡፡ ጣልያንን ካሸነፍንበት ድል ወንድምን የገደልንበት ድል ለማድመቅ ፈልገናል፡፡ በደም ተጀምሮ በደም የሚየሚጠናቀቀው ጉዞአችን አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡
በክፋት የምንወዳደር ፣ እንደ ጴጥሮስ ዘቅዝቀን ክቡር ሰውን የምንሰቅል ገድለን የማንረካ የሆንነው ለምንድነው? በብዙ መንገድ ስነልቦናችን መጠናት አለበት፡፡ ለምን ወደዚህ ገባን? እንግዳ ተቀባይ ህዝብ እራሱን ለምን ማስወጣት ጀመረ? የተማሪ ዕዳ የሁለም ነው ብሎ ለዘመናት ወጪን ሲጋራ የኖረ ማህበረሰብ "በእንተ ስሟ ለማርያም" ለሚለው ተሜ ሲቆርስ የነበረ ለምን ተማሪዎችን ማርከስ ፈቀደ? ከወለደው ልጅ አልፎ ጉድፍቻ የሚወስድ ዛሬ አንተ ከሰሜን ፣ አንተ ከደቡብ...፣ ለመባባል እንዴት ደረሰ? ለውጥ የሚመስሉ ነውጦች ከሁሉም በላይ የጎዱት እናቶችን ነው፡፡ ሁሉም እናቱን ይወዳል የእናቱን ስቃይ ለመቀነስ ግን የሚሰራ አልተገኘም፡፡.....
ዲ/ን አሸናፊ መኮንን የደስታ ቋጠሮ ለንባብ እንዲመች አድርጌ የወሰድኩት
አስተያየታቹን በ @JahABP አድርሱኘ
SHARE FOR YOUR FRIENDS
@ABPGD @ABPGD @ABPGD