................ለእነዚህ መነኮሳት ያለኘ አድናቆት እያንሰላሰልኩ ትንሽ እንደተጓዝን በክረምት የውኃ መውረጃ የሚመስል አንድ ፈፋ አካባቢ ስንደርስ የትራክተሩ ጎማ ምልክት ጨርሶ ጠፋ፡፡ በቅርብም በርቀትም በዚያ በአግባቡ በተያዘ ጫካ ውስጥ የሚታይ መንገድ ነገር የለም፡፡ ተስፋ ወደመቁረጡ ተቃረብን፡፡
"በቃ ጠፍተናል!" አለ አንድኛው ባለሙያ፡፡
ወዲያው አንድ ሀሳብ ብልጭ አለልኘ፡፡ ይህ የውኃ መውረጃ ፈፉ የገዳሙ ዋናው ቤተክርስቲያን ከሚገኘበት ተራራ አካባቢ እንደሚነሳ መገመት ይቻላል፡፡ፈፉውን ብንከተል የሚያቋርጥ መንገድ እናገኘ ይሆናል አለበለዚያም ወደ ተራራው በወጣን ቁጥር ሕንፃ ቤተክርስቲያኑን ልናይ የምንችልበት አካባቢ መድረስ ያስችለናል፡፡ ይህ ጥሩ ጂኦግራፊያዊ አመንክዮ ነው አልኩና አብረውኘ ላሉት ሐሳቤን አካፈልኳቸው፡፡
ቄስ ገዳሙ ሐሳቤ አልተዋጠላቸውም፡፡ ምክንያታቸውን ስጠይቃቸው እንዲህ አሉ:-
"አሁን ሰሁን ሰዓቱ ቀትር ነው፡፡ ይህ ፈፉ ደግሞ ዐልፎ አልፎ ውኃ ሊኖረው ይችላል ወይም ቀዝቃዛ አሸዋ ይኖረዋል..." ሲሉ አቋርጬ
"ታዲያ ያማ ለጉዞአችን ጥሩ ነው" አልኳቸው
"አይ በዚህ ሰዓት ዘንዶው ወደ ፈፉው ሊመጣ ይችላል ብዬ ነው" አሉን በስጋት፡፡
'ዘንዶ' ሲባል አብረውኝ ያሉት ሁሉም ደነገጡ፡፡ ዘንዶ መርዝ የለውም፡፡ ሊያደርግ የሚችለው በጅረቱ ጠልፎ በመጠምጠም አጥንትና ጡንቻን በማጨማደድና በመሰባበርበ መጨረሻም በአፉ ውስጥ አስገብቶ በማፈን መዋጥ ነው፡፡ ይህነ ለማድረግ ጊዜ ይወስድበታል፡፡ በዚህ የተነሳ ሁለት ሦስተት የሆኑሰዎችን ለማጥቃት እንደሚቸገር ስለማውቅ:-
"በርከት ያልን በመሆናችን ስጋት አይግባችሁ፡፡ አይደፍረንም በዛ ላይ " አልኩና በመስክ ስራ የማትለየኘ ተስፈንጣሪ ስለታማ ሰንጢ እንዲሁም በትልቅ ፍንዳታ እሳት የሚተፋ የእሳት መለኮሻ(LIGHTER) አሳየኀቸውና አደፋፈርኳቸው፡፡ በዚህም መሰረት መኪናዋን ፈፉው ውስጥ አስገብተን ከተጠፈጠፈ ዐለት ላይ አቆምን፡፡ ይህ ቦታ እሳት ቢነሳ መኪናዋ የመቃጠል ዕድሏ አነስተኛ ሲሆን ተመልሰን የቆምንበትንም ለማግኘት ፈፉውን በመከተል መመለስ እንደምንችል ሁላችንም ተግባባን፡፡
መኪናዋን ቆላልፈን ፈፉውን ተከትለን በስተደቡብ ወደ ተራራው አቅጣጫ መጓዝ ጀመርን፡፡ አንድ ሁለት ኪሎ ሜትሮችን ዳዋ እየጣስን እንደተጓዝን የትራክተሩ ጎማ ፈፉውን የሚያቋርጥበት ግልፅ ቦታ ደረስን፡፡ የጉዞ መላምታችን በትክክል መሆኑን ስላረጋገጥን በጣም ተደሰትን፡፡ ስለሆነም ፈፉውን ለቀን ወደ ደቡብ ምስራቅ ታጥፈን የትራክተሩን ጎማ ተከትለን እንደገና ተጓዘን፡፡ የገዳሚ እንስሳት የሰፈሩበት አካባቢ ደረስን፡፡ ትልቅ እፎይታ ነበር፡፡
ከዚህ በፊት በሆላንድ ሜዳዎች ላይ ንፅህናቸው የተጠበቀ ነጭና ጥቁር ቀለም ያለባቸው ላሞች ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይ ቀንቼ ነበር፡፡ የማኅበረ ስላሴ ገዳምን ላሞችና ወይፈኖች ባየሁ ጊዜ ግን በቀላዋጭነቴ ፈጣሪ እንዳይፈርድብኘ ፈራሁ ፡፡ እጅግ ንፁህ ፣ መልካቸው ያማረ ፣ ሰውነታቸው የሞላ ፣ ዥርጋዳ አቋም ያላቸው ፣ ለብቻ መንገድ ሰርተው የሚጠቀቁት እምቦሶቻቸው ደግሞ እንደ ሕፃን ልጅ አንስቶ አቅፎ ለመሳም የሚገፋፋ ናቸው፡፡
አብረውኘ ከነቀሩት ባለሙያዎች አንዱ እጅግ መመሰጤን ሲያይ በአድናቆት "ያስጎመጃሉ አይደል?" አለኘ፡፡
"የየመንደሩ አድባር ፣ የዐባይ ቆሌ ፣ የዘንገናው ጋኔል ፣ የቢሾፍቱ ቆሪጥ ፣ የገናሌው ሞቴ ፣ የጁሩዋ አተቴ ፣ የዱበርቲ መጀን ሰራን ወይም ሶለላ ዶሮ ፣ ነጭ ወይም ዳንግሌ በግ ካላመጣህ እንጀራህን አልሰጥህም ፣ ጤናህን አልመልስም ፣ አዱኛልን አልከፍትም እያሉ የሚያስደነድራቸው አማኞቻቸውን እነዚህን ጊደሮችና ወይፈኖች አይተው ቢሆን ኖሮ 'ተማህበረ ስላሴ የከብት መንጋ ÷ ሻኛው የቆመውን ወይፈን ወይም አለላ የመሰለች ጊደር አምጣ ባሉ ነበር' አልኩ"፡፡
እነዚህ በሬዎች ፣ ወይፈኖች ፣ ላሞችና ጊደሮች እንዲሁም ጥጃዋችና እንቦሶች ከውበታቸው በተጨማሪ እንደመናንያኑ በጥብቅ ስርዓት የታነጹ መሆናቸውን መስማት ለእኔ ቢጤ ሰውነ ለማመን ይከብድ ይሆናል፡፡ በአካባቢው ያገኘናቸው ጠባቂ ሲያስረዱን:-
"ማታ ማታ ላይ ጥጃዎችና ላሞች ከተጣቡ በኀላ 'ወገን ወገን' እያልን ስናጨበጭብ ጥጆቹ ከእናቶቻቸው ተለይተው የራሳቸውን መንጋ ይሰራሉ፡፡ ወዲያው ደግሞ ' አጎድ አጎድ' ተብሎ ሲጨበጨብ ሁሉም ወደ ማደሪያቸው ይገባሉ፡፡ የገዳሙ ሳር በስርዓት ለማስጋጥ ሲባል እንስሳቶቹ በተወሰኑ ቀናት ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ እንዲሰፍሩ ይደረጋል፡፡ ታዲያ ጠባቂያቸው 'ጉዞ ጉዞ' ብሎ ሲያጨበጭብ ሁሉሞ ተከትለውት ወደ ሚመራቸው ይጓዛሉ፡፡ ከሚፈለገው ስፍራ ሲደርስ 'ሰፈር ሰፈር' ብሎ ሲያጨበጭብ አዲስ የግጦሽ አካባቢያቸው መሆኑን ተረድው ለግጦሽ ይሰማራሉ አሉ፡፡
የእነዚህ የከብቶች ዝርያና ዘረመል ምንነት በሀገራችን ባለሙያዎች መጠናታቸውን እጠራጠራለሁ፡፡ በገዳሙ ቆይታዬ የተረዳሁት ግን ከአውስትሪያ ዩኒኒቨርስቲዎች የእንስሳት ሳይንስ ተመራማሪዎች በተደጋጋሚ እየመጡ ጥናት እንደሚያደርጉ ነው፡፡ ንብ የአበባ መገኛን ፣ዝንብም የቆሻሻን ስፍራን አስሰው እንደሚያገኙት ሁሉ ምዕራባዊያን የሀብትና የብልፅግና መገኛ አካባቢ ማነፍነፍ የእድገታቸው አንዱ ሚስጢር ነውና፡፡..........
አለማየሁ ዋሴ እሸቴ :- ዝጎራ 2008 ዓ.ም
ይህን መፅሐፍ ሳነብ የተሰማኘ ነገር ኢትዮጵያኖች በእውቀታችን እንዳልተጠቀምንበት
አሁን ከለም ላይ ምንገረምበት እያንዳንዷ ነገር ከእኛው ከጉያችን የተወሰዱ መሆናቸው መጠየቅን አለመውደዳችን ለሀይማኖት አባቶች ክብር እንደሌለን ታሪካዊ ቦታዎችን መጎብኘት አለመቻላችን ታሪክን ለማወቅ አለመጣራችንን.....ሌላም ብዙ ብዙ....
ብቻ እኛ ከሌለን ነገር ያለን ይበልጣል ይለናል ዝጎራ መፅሐፍ፡፡
ይህን ከገፅ ገፅ ልብ አንጠልጣይ መፅሐፍ በዚ በእረፍት ጊዜ ታነቡት ዘንድ ስጋብዛችሁ በደስታ ነው፡፡
ቤታችን እንሁን🏡🏘🏠
እናንብብ📚📚
ለአስተያየታችሁ :- @jahABP

AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
ህክምና መታደል ነው፡፡ በየትኛውም አጋጣሚ ከታመመ ሰው ፊት ስትቆሙ ምን ያህል የታደላችሁ መሆናችሁን አትርሱ የታመማችሁት እናንተ ባለመሆናችሁ ብቻ ሳይሆን ለመፍትሔ የተመረጣችሁ እናንተ ስለሆናችሁ እንጂ.......
ህክምና መስዋዕትነት ነው፡፡ ጓደኛ ብለህ የማትሸሸው፣ ከፋኘ ብለህ የማትተወዉ ተቸገርኩ ብለህ የማትሸጠው፣ ምክንያት የለሽ መስዋዕትነት ነው፡፡ ንፁህ መስዋዕትነት፣ በጎ ስለሆነ ብቻ የምታደርገው፡፡
ህክምና መጠራትና መመረጥ ነው፡፡ በሰው መኖርና አለመኖር መሃል፣ ከውልደት እስከ ሞት ÷በደስታ እና በመከራ በተሞላው ሕይወት ውስጥ የፈጣሪን የመፍጠር ፣ የማኖር የማሳመንና የማጥፋት ፍላጎቶች ተባባሪ መሆን ነው፡፡
ከዚህም በላይ ብዙ ነገር ነው!!!
አለመኖር፡- በዶ/ር ዳዊት ወንድም አገኘ 2009
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD

ሳሚሻ ስቋል ከልቡም ደስ ብሎታል
መርዳት መቻል እድል ነውና እንጠቀምበት ምክንያቱም እግዚአብሔር ዛሬ እኛን ሰጪ አድርጎናል ይሔን እድል ካልተጠቀምንበት ምናልባት ነገ ደሞ እኛም የሰው ጠባቂ ልንሆን እንችላለን ስለዚህ ዛሬ በተሰጠን ባገኘነው እድል መርዳት አለብን ዛሬ ያደረግነው መልካም ነገር ነገ ተመልሶ እኛኑ ይጠቅመናልና ለድሃ የሚሰጥ ለእግዚአብሔር ያበድራል ነውና፡፡ እውነተኛ ስጦታ ደግሞ ከተረፈን ላይ ሳይሆን ካለን ላይ ነው፡፡
ይኸው የሳሚሻን ታሪክ ለሁላችሁም ካጋራሁ በኀላ ከናንተው ያሰባሰብኳትን ትንሿን ነገር ዛሬ ነበር ይዤለት ልሔድ የነበረው......
ሳሚሻ ጋር ደወልኩለት የለመድኳት የትህትና ድምፅ ተቀበለችኘ ዛሬ ስቅለት ስለሆነ እንደማይሰራ ነገረኘ ግን....መምጣት አትችልም ስለው ቤላ ነው እኮ ቤቴ መጣሁ እሺ ጠብቅኃለሁ አፍጥነው ሳሚሻዬ ብዬው ስልኩን ዘጋሁ በምኖዳት 4ኪሎ የድሮ ትውስታዎቼን እያስታወስኩ ወደዛሬ አምስት አመት ተጓዝኩ...ስንቱን አሰብኩት መሰላቹ ከሐሳቤ የመኪኖች ጩኸት አነቃኘ፡፡
ትንሽ ቆይቶም ሳሚሻ መጣ ብዙ ተጨዋወትን ልጅህን ላከው አልኩት አይ አብይ ገንዘቡም እጥፍ ሆነ በዛ ላይ ሲሔድ ለቤተሰብም ገንዘብ መላክ አለ...እጄም ላይ ብር ስለሌለ መቆየቱ ግድ ሆኗል ወንድሜም እዚሁ ቢቆይ ይሻላል አለ፡፡
አይ ጥሩ አድርገኸል አልኩት በቃ ሳሚሻ ስግደትም ስላለ እንሒድ አልኩት ያቺ ደስ ምትል ፈገግታውን እያሳየ እኔም ቸርች ልሔድ ነበር አለኘ
እ......ሳሚሻ ይሔ ባለፈው አንተን ካገኘሁ በኀላ ለሰዎች ስላንተ ነግሬያቸው ሁሉም የተቻላቸውን አድርገው ይሔን ልከውልኻል ሁሉንም አመስግናቸው አልኩት፡፡
ረጅም ሰዓት ዝምታ......................
ቀጠለ እግዚአብሔር አምላክ ይባርካችሁ እኔ ምንም የለኘም ምንም ልሰጣችሁ አልችልም ግን እሱ የፍጥረታት ጌታ ሀሳባችሁን ሙሉ ያድርገው አብዝቶ ይስጣችሁ ለኔ እንደደረሳችሁ ለናንተም አለሁ ይበላችሁ፡፡ ሊያቅፈኘም ፈለገ ግን ጊዜው አጉል ነውና ፈራ ለመሔድ ተነሳን ምስጋናው እንደቀጠለ ነው፡፡ መጨረሻ ቻው ስንባባል ግን አንተን ባይሆንም ብሎ የያዝኩትነ ቦርሳ ጭምቅ አድርጎ አቅፎ አመሰግናለሁ አብዬ አለኘ ከልቤ አዘንኩ ማርያምን ውስጤን የሆነ ነገር ወረረኘ እንባ ዳዳኘ...
ምን ማለት እንዳለብኘ ግራ ገባኘ
ቻው ሳሚሻ ችግር ካለ ደውልልኘ አቅመ በተቻለ መጠን ሁሌም አለን አልኩት እሱ አሁንም እያመሰገነ አስፓልቱን ተሻግሬ ሔድኩኘ፡፡
እቤት እንደደረስኩም ስልኬ ጮኸ ሳሚሻ ነበር እቃዎቹን ከፍቶ አይቶ ኖሮ ለካ ከቅድሙ የባሰ የምስጋና ቃል ይሰማኘ ጀመር.....ሲጨርስም አትጨናነቅ ሳሚሾ ይህ ግዴታችን ነው አልኩትና ዝልኩን ዘጋሁ፡፡
የሳሚሾ የደስታ ፊት አሁንም ይታየኛል ጥቂት ሆነን ይህን ካደረግን ብዙ ስንሆን ደግም ብዙ የደስታ ፊቶችን ማየት እንችላለን፡፡
ይህን ክፋ ጊዜ በፍቅር ተደጋግፈን እንለፈው
እጃችሁን ለዘረጋችሁልን ግለሰቦች ሁሉ ልዑል እግዚአብሔር ያሰባችሁትን ያሳካላችሁ፡፡
መርዳት ፈልጋችሁም 'ቤታችን እንሁን' በcovid-19 ምክንያት ነውና ያልተሳካላችሁ ፈጣሪ የልብን ያያል እና ልታዝኑ አይገባም፡፡
ያሁኑ ያመለጣችሁ ደግሞ ለሌላ ጊዜ ተዘጋጁ፡፡
መርዳት እድል ነውና እንጠቀምበት
@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ

AB PHOTOGRAPHY
የፒኮክ ሰፈር ወጣቶች ክብር ይገባችኀል
ለአቅመ ደካሞች እና ለአረጋውያን የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም
CANON 4000D
የፒኮክ ሰፈር ወጣቶች ክብር ይገባችኀል
ለአቅመ ደካሞች እና ለአረጋውያን የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም
CANON 4000D