Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
AB PHOTOGRAPHY


መልካሙን የምንሰማበት የተቀደሰ ቀን ይሁንልን
መርካቶ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሀይማኖት

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB graphic design

Hulk bog down in the coffee😂😂😂
stay home stay safe😊🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY


ረጅሙ ፋፋቴ ደብረ ሊባኖስ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

DEADPOOL 3
TRIP TO HAWASSA

RUN DEADPOOL RUN RUN

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Ab photography & graphic design

ከምንም ነገር በላይ ማንበብ የሰው ልጅን ህይወት ይቀይራል፡፡ በህይወት አጋጣሚ ህይወትህ የሚለወጥበት እና ተነሳሽነትህን የሚጨምሩ ነገሮች ሊያጋጥሙህ ይችላሉ። በአጋጣሚ ያገኘኻቸው ሰዎች፣ ድንገት ያየኸው ፊልም፣ ድንገት የሰማኸው ዘፈን ወይም ታሪክ አንተነትህ ላይ ተፅኖ ያሳድራል ወደ ህልምህ፣ ወደ ተሰጦህ እና መሆን ወደምትፈልገው ነገር ሁሉ ተስፋ ሳትቆርጥ እንድትጓዝ ያደርጉኻል፡፡

እኔም ባገኘኋቸው አጋጣሚዎች ከላይ ከጠቀስኳቸው ነገሮች ወደ ህልሜ የማደርገውን ሩጫ እንዳላቆም የሚያደርጉ አያሌ ተሞክሮዎችን እና ተነሳሽነትን አግኝቻለሁ፡፡

እንደእኔ አስተሳሰብ ዋነኛ አለምን የሚለውጡ ሰዎች አንባቢዎች ናቸው፡፡ ጨጓራችን የሚፈጨው ምግብ እንደሚፈልግ ሁሉ አይምሮአችንም የሚያወጣውና የሚያወርደው ሀሳብ ያስፈልገዋል አለምን በተለያየ አቅጣጫ ለማየት ደግሞ ዋነኞቹ አቅጣጫ ጠቋሚዎች መጽሐፍት ናቸው፡፡

አውቃለሁ ጎበዝ አንባቢ አይደለሁም ግን በተቻለኝ አቅም መጽሐፍትን ለማንበብ እጥራለሁ፤ የለውጡ አካል መሆን እፈልጋለሁ። እኔ ከመጽሐፍት ላይ ያገኘኋቸው እውቀቶች አያሌ ናቸው፡፡ ካነበብኳቸው መጽሐፍቶች ደግሞ እኔ በህይወቴ ትልቅ ቦታ የሰጠኋቸው 3 መጽሀፎች አሉ። እነዚህን መጽሐፍቶች አንብቤ ብቻ አልተውኳቸውም እየኖርኳቸውም ጭምር ነው። ድሮ እኔን የሚያውቁኝ ሰዎች "አንተ እኮ እንዲህ አልነበርክም በጣም ተለውጠሀል" ይሉኛል፤ አሁን የሚያውቁኝ ደግሞ ጥሩ ሰው እንደሆንኩ ይነግሩኛል (ጥሩ ነኝ ለማለት ባልደፍርም)፡፡

እውነታው ግን ለእኔ መለወጥ የእነዚህ መጽሐፍት ሚና እጅጉን ላቅ ያለ ነው እውነት ለመናገር መጽሐፍቶቹን ከማንበቤ በፊት እና ካነበብኩ በኋላ የተለየሁ ሰው ሆኛለሁ፤ ለእራሴ እስኪደንቀኝ እራሴን ተለውጦ አግኝቼዋለሁ። ያሉኝ ጥቂት መጽሐፍት ባለችኝ ትንሽዬ መሳቢያ ስር ተደርድረው ይቀመጣሉ። እነዚህ ሶስቱ መጽሐፎች ግን ሁሌም አልጋዬ ትራሴ አጠገብ ይቀመጣሉ። ሁል ጊዜም እንደ አዲስ አንስቼ አነባቸዋለሁ፤ ሁልጊዜም ለኔ ቅርብ እንዲሆኑ አደርጋለሁ ጉዞ ስሄድ ከተቻለ ሶስቱንም ካልተቻለ አንዱን ይዤ መሄዴ የማይቀር ጉዳይ ነው።

ብዙ ጊዜ በኑሮዬም ሆነ በንግግሬም ላይ ከእነዚህ መጽሐፍት ያገኘኋቸው እውቀቶች ነፀብራቅ ይታያል። የፈጣሪን ትልቅነት፣ የተረጋጋ ሰው መሆንን፣ ለሰው ችግር መድረስን፣ ሰውን ካለበት አለማዊ ሀሳብ ማንቃትን፣ ያለውን የውስጥ ችሎታ አውጥቶ እንዲጠቀም ማድረግን፣ ያላስተዋላቸው የህይወት መርሆችን መጠቆምን፣ ችግርን ከስር መሰረት መቅረፍን፣ ተስፋ አለመቁረጥን፣ ታጋሽነት፣ ለማንኛውም ችግራችን መጀመሪያ እራስን ተጠያቂ ማድረግን፣ ለፍርድ አለመቸኮልን፣ በፍቅር ሁሉንም ማሸነፍን፣ ሰላም ለማምጣት ዝቅ ማለትን፣ ሰዎች መጥፎ ሲያደርጉብን ምላሻችን ሁሌም መልካም መሆን እንዳለበት፣ ራዕይ ያለን ልንሆን እንደሚገባ፣ አመሰግንሃለሁ/ እግዚአብሔር ይስጥልኝ ማለትን፣ ለጥፋታችን ቶሎ ይቅርታ መጠየቅን፣ በእያንዳንዱ ውድቀታችን መማር መቻልን፣ ከምንም ተነስተን ትልቅ ደረጃ መድረስ እንደምንችል፣ የምንፈልገውን ነገር ተስፋ እስካልቆረጥን ድረስ ማሳካት እንደምንችል፣ በህይወት አጋጣሚ የምናገኛቸው ሰዎች ለእኛ መማሪያዎቻችን መሆናቸውን፣ የምናደርገው መልካም ነገር በቀጥታ ባይሆንም በተዘዋዋሪ እኛኑ መጥቀሙ የማይቀር መሆኑን፣ ደስታ ከመቀበል ይልቅ በመስጠት ላይ መሆኑን፣ እውተኛ ስጦታም ከተረፈን ላይ ሳይሆን ካለን ላይ መሆኑ፣ ዛሬን ከትላንት የተሻለ አዲስ እና የተሻለ ማድረግ እንዳለብን እና እንደምንችልም ............. ብቻ ብዙ ብዙ ነገሮችን አስተምረውኛል ያስተምሩኛልም። ያስተምሩኛል የምላችሁ ሁልጊዜም ሳነባቸው አዲስ ነገር ስለማገኝባቸው ነው፡፡

ሶስቱን መጽሐፍ አንብቤ በጨረስኩበት ወቅት ይህን የፎቶግራፊ ቻናል አልከፈትኩም ነበር። ነገር ግን ለራሴ እንዲህ ብዬ ነግሬው ነበር ቻናል ሲኖረኝ ሰዎች እነዚህን መጽሐፍት እንዲያነቡ እጋብዛለሁ ብዬ ነበር....ገና ቻናል ሳልከፍት..... አሁን ግን 3.1k ሰዎች ያሉበት ቻናል ላይ ስለነዚህ መጽሐፍት እየተናገርኩ ነው። ራዕይ ነበረኝ አሳካሁት ማለትም አይደል? ነገም ደግሞ ከዚህ የበለጠ ሰዎች ፊት ስለነዚህ መፅሐፍት እናገራለሁ። ነገ በትልልቅ ሚዲያዎች ላይ ስለነዚህ መጽሐፍት አወራለሁ። ደራሲዎቹን በደንብ አድርጌ አመሰግናቸዋለሁ.... እኔ እነዚህን መፅሐፍት እየኖርኳቸው ነው፡፡ በእውነት እላችኋለሁ ጥሩ ሰው እንድሆን አድርገውኛል፣ በጥሩ አንፀውኛል፤ እናም እነዚህን መጽሐፍት እንድናነባቸው ለጻፉልን ጸሐፊዎች በእናንተ ስም እጅግ እጅግ ታላቅ የሆነውን ፍቅርና አክብሮቴን ላደርስ እወዳለሁ፡፡

እነዚህን መጽሐፍት እንዲያነቡ የጋበዝኳቸው ሰዎች አባቴን አቶ አንዷለምን ጨምሮ ለሰጠኋቸው መጽሐፍት አድናቆታቸው ላቅ ያለ ነበር። እንዲያነቡት ስለጋበዝኳቸውም ለእኔም ምስጋናቸውን ችረውኛ።

የመጽሐፍቶቹ ርዕስ ምንድነው???

ደራሲዎቹስ እነማን ናቸው???

በመጀመሪያ የመጽሐፉን ርዕስና የደራሲውን ማንነት ሳልጠቅስ ከሶስቱም መጽሐፍ የተወሰነ ቀንጭቤ ለንባብ አቀርባለሁ ከዛም መጽሐፍቶቹንም የደራሲዎቹንም ስም እለጥፋለሁ፡፡

@jahABP ነኝ አስተያየታችሁን አድርሱኝ፡፡

ቤታችን እንሁን!
እናንብብ!
ቤተሰብን አካባቢን ሀገርን እንዲሁም አለምን እንለውጥ!!! ❤️❤️❤️
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY


አንቺ ጨረቃ ታምሪያለሽ በጣም😍😍😱😱

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
Phenomenal pictures & graphic design pinned «Ab photography & graphic design ከምንም ነገር በላይ ማንበብ የሰው ልጅን ህይወት ይቀይራል፡፡ በህይወት አጋጣሚ ህይወትህ የሚለወጥበት እና ተነሳሽነትህን የሚጨምሩ ነገሮች ሊያጋጥሙህ ይችላሉ። በአጋጣሚ ያገኘኻቸው ሰዎች፣ ድንገት ያየኸው ፊልም፣ ድንገት የሰማኸው ዘፈን ወይም ታሪክ አንተነትህ ላይ ተፅኖ ያሳድራል ወደ ህልምህ፣ ወደ ተሰጦህ እና መሆን ወደምትፈልገው ነገር ሁሉ ተስፋ ሳትቆርጥ…»
በቀጣይ ከሦስቱ መፅሐፎች ከአንዱ ቀንጨብ እናድርግ
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ተጨማሪ ሙከራ

ትዕግሥት ማለት ያልተሸበረ መንፈስና የማይበርድ ተስፋ ነው፡፡ ትዕግስት ከዚህም ያለፈ ትርጉም አለው፡፡ "ተጨማሪ ሙከራ ማድረግ ነው፡፡" ትዕግሥት እጅና እግርን አጣጥፎ ጊዜን ወይንም እግዚአብሔርን መጠበቅ ማለት አይደለም፡፡ ትዕግሥት እንቅስቃሴ ነው፡፡ ሁላችንም እንደሚገባን የወደቀ ሰው ዳግመኛ ለመነሳት የሚያደርገው መፍጨርጨር ፣ የከሰረው ሰው እንደገና ውጤታማ ለመሆን የሚያደርገው ሩጫ ትዕግሥት ወይም ውስጣዊ ብርታት ነው፡፡

ብዙዎቻችን ተጨማሪ ሙከራ ማድረግን አንፈልግም፡፡ ለሰበባችን አንድ ነገር እንድናደርግ በቃ አልሆነም ምንም ማድረግ አልችልም እንላለን፡፡ ራሱ ማድረግ የማይፈልግ ሰው ግን ሌሎቹ እንዲያደርጉለት ይሻል፡፡ በሌሎች ልፋት መብላት ፣ በሌሎች መጋፈጥ ተጋርዶ መኖር ይሻል፡፡ ይህ ግን ራስን ለማኝና አካለ ስንኩል ማድረግ በራስ ላይም ውድቀትን መፍረድ ነው። የምንኖርበት ዓለም የሙከራ ዓለም ነው፡፡ ጠዋት የሚጎርፈው ሠራተኛ ሁሉን ማግኘት ተስፋ አድርጎ ብቻ ሳይሆን ከትላንቱ ዛሬ እንደሚሻል አምኖ ይወጣል፡፡ ይህንንም ባያምንም የቀኑን ፀሀይ እንኳን ለማየት ባልደፈረ ነበር፡፡ ዛሬ ባይሳካም ነገ ደግሞ በማለዳ ለመውጣት ያስባል፡፡ ሙከራዎች ከስኬት ላይ ያደርሳሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ የመኖር ፍላጎት ይጨምራሉ፡፡ ሙከራዎች ከጠራ ነገር ያደርሳሉ፡፡

እንዳንሞክር ፈተና የሚሆንብን..... የመውደቅ ፍርሃት ፣ የትላንት ክፉ ገጠመኝ ፣ ተስፋ መቁረጥ ናቸው፡፡ ሕፃን ልጅ በእግሩ ፀንቶ የሚቆመው ብዙ መውደቅ መነሳትን በማየትና ተስፋ ባለመቁረጥ ነው፡፡ ከዚያም ደጋፊዎችን በመያዝ መንገዱን ይለማመዳል፡፡ በሁለት እግር የሚሔድ ሰው ልምምድ ያስፈልገዋል፡፡ በአራት እግር የሚሔዱ እንስሳት ግን በተወለዱ ቀን ይቆማሉ፡፡ በሁለት እግር በኩራት መሔድ ከባድ ነው፡፡ ከልምምድና ከሙከራ በኀላ ግን በሁለት እግር መሔድና መሮጥ ይቻላል፡፡ ዓላማችን መቆም ከሆነ እስክንቆም ድረስ መሞከር አለብን። ዓላማችን ውድቀት ከሆነ ግን አለመሞከር እንችላለን፡፡ መሞከር ብቻ ሳይሆን በመራመድ የቀደሙን መያዝ ወይንም ምክራቸውን መቀበል ያስፈልገናል፡፡ በመራመድ የቀደሙን ሰዎች በአካል ብቻ ሳይሆን በመፅሐፋቸውና በምክራቸው ይደግፉናል፡፡ በእውቀት ለመቆም አዋቂዎችን በትሕትና መቅረብ ፣ በሀብት ለመቆም አዛዦቻችንን በአክብሮት ማገልገል ይገባናል። አዋቂዎችን የምንፈልገው ባወቅነው ላይ ማገልገል ይገባናል፡፡ አዋቂዎችን የምንፈልገው ባወቅነው ላይ ጨምረው እንዲነግሩን ከሆነ ምንም አናገኝም፡፡ ራሳችንን ባዶ አድርገን ካልቀረብን አዋቂዎች ሊቀርቡን አይችሉም፡፡ እኛም የሚነግሩንን ልንይዝ አንችልም፡፡ እንዲሁም መታዘዝን ያላወቀ አዛዥ መሆኖ አይችልም፡፡

ዕለቱን ተወልዶ ዕለቱን ብቁ የሚሆን ተግባር የለም፡፡ የተፈጥሮ ጊዜውን ሲጠብቅ ግን ደስታው እንደ ፀሀይ ብርሃን እየፈካ ይመጣል፡፡ መሠረት ያለው በመሆኑ ፀንቶ ይቆያል፡፡ ደክመንበታል ደስ ያሰኛል፡፡ ተአምር ናፋቂዎች ብንሆንም ተፈጥሮም የተአምራት አካል ነውና ሂደትን ማክበር ይገባናል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀስ በቀስ አደገ እንጂ አምላክ ነኝ ብሎ ዕለቱን አላደገም፡፡ የተፈጥሮን እድገት ሥርዓት ጠበቀ፡፡ ቀስ በቀስ ማደግ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡

ብዙ ትልልቅ ሰዎች ለደረሱበት ከፍታ የበቁት ከብዙ ትዕግስት ወይም ሙከራ በኋላ ነው፡፡ ከብዙ ሙከራ በኋላ ትልቅ የሆኑ ሰዎች ፣ ጊዜ ካነሳቸው ደግሞም ገጠመኝ ካገነናቸው ዝነኞች ይልቅ ክብራቸውን እንደጠበቁ ማለፍ ችለዋል፡፡ ለትዕግሥተኞች የዛሬ አለመሆን ሌላ አቅጣጫ እንዲያዩ ማስተዋላቸውን ያድሰዋል እንጂ መሬት ላይ ተቀምጠው ስለ ውድቀታቸው እንዲተክዙ አያደርጋቸውም፡፡ የአብርሃም ሊንከንን ታሪክ ብንመለከት ትዕግስት ብዙ መከራ እንደሆነ በመጨረሻም ድልን እንደሚያተርፍ ያስተምረናል፡፡ ስለአብርሃን ሊንከን ያነበብኩትና አሁንም ድረስ የሚመስጠኝ ታሪክ አለ፡፡

አብርሃም ሊንከን፡-

በ32 ዓመቱ ለፓርላማ ምርጫ ተወዳድሮ ወደቀ፡፡
በ35 ዓመቱ ፍቅረኛው ከዚህ አለም በሞት ተለየችው፡፡
በ36 ዓመቱ በነርቭ በሽታ ተያዘ፡፡
በ38 ዓመቱ ለአስመራጭነት ተወዳድሮ ወደቀ፡፡
በ40 ዓመቱ ለምርጫ ቀርቦ ሳይሳካለት ቀረ፡፡
በ48 ዓመቱ በኮንግረስ ምርጫ ተወዳድሮ ወደቀ፡፡
በ50 ዓመቱ ለሕግ መወሰኛ ም/ቤት ተወዳድሮ ወደቀ፡፡
በ56 ዓመቱ ለምክትል ፕሬዝዳንትነት ተወዳድሮ ወደቀ፡፡
በ58 ዓመቱ እንደገና ለህግ መወሰኛ ምክር ቤት ተወዳድሮ ወደቀ፡፡
ተስፋ ሳይቆርጥ ታግሦ በመጨረሻ በ1860 ለፕሬዝዳንትነት ተወዳድሮ ተመረጠ፡፡ የጥቁሮችን መብት ያስከበረና አሜሪካን አንድ ያደረገ ትልቅ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነ፡፡ አብርሃም ሊንከን በ32 ዓመቱ ለፓርላማ ምርጫ ተወዳድሮ እንደ ወደቀ በቃኝ ለእኔ ያልተሰጠ ነው ማለት ይችል ነበር፡፡ የሚወዳት አፍቃሪው በሞት ስትለየው ዓለም ለምኔ ብሎ ሁሉን ነገር መተው ይችል ነበር ፡፡ በአደባባይ የሚታወቁ ዘጠኝ ሙከራዎቹ መልሳቸው ውድቀት ነበር፡፡ በዐስረኛው ሙከራ ግን ከአሰበው ላይ ደረሰ፡፡ ለእነዚያ መከረኛ ጥቁሮች መብት ቆመ፡፡ የእርሱ ጅምር ዛሬ ከፍፃሜ ላይ ደርሶ አሜሪካ በማይታመን መልኩ በጥቁር ለመመራት በቃች፡፡

ወድቆ ለመቅረት ካለን ምክንያት ለመነሳት ያለን ምክንያት ይበልጣል፡፡ እግዚአብሔርና ደጋግ ሰዎች እየጠበቁን ነውና፡፡

ትዕግስት..... ተጨማሪ ሙከራ...... ወድቆ መነሳትን መልመድ...

የመጀመሪያው መጽሐፍ ይሄ ነው!

ይህችን እያነበባችሁ በህይወታችሁ ለመኖር መንገድ ጀምሩ እንደመጽሐፉ እየኖራችሁ ያላችሁም በርቱልኝ...
@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አይለየኘ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY &GRAPHIC DESIGN

R......for......reflection

Which one is the reflection??🤔🤔😳😳


@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
በቀጣይ ከትላንቱ መፅሐፍ ትንሽ እንቆንጥር🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🙏🙏

ቀጥታ ከመፅሐፉ ስለምወስደው እባካችሁ
እግዚአብሔር የሚለውን ቃል ፈጣሪ ወይም አላህ .....ብላችሁ እንድታነቡት እመክራለሁ የመፅሐፉ ዋና አላማ ህይወትን መቀየር ነውና፡፡
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
ይችለናል

ቀላል ሰው የሰማውን እስኪናገር ምጥ ይይዘዋል። የእግዚአብሔር ሰው ግን የእግዚአብሔርን ባህርይ ስለሚካፈል ያየውን ክፉ የማያሳይ ፣ የሰማውን ክፉ የማያሰማ ፣ መልካሙን እንጂ ክፉውን የማያውጅ ፣ የበደለውን ወንድሙን በር ዘግቶ የሚወቅስ ፣ ጥቅምን ሳይሆን ፍቅርን የሚያስብ ፣ ጭካኔ ድል ነስቶ ርህራሄን ገንዘብ ያደረገ ነው፡፡ ይህን መስፈርት የሚያሟላ የእግዚአብሔር ሰው ያለ ባይመስለን እንኳን እግዚአብሔር ግን አለ፡፡ ዛሬ ለክፋት የጨከኑ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ ለበጎ ነገርም የጨከኑ የእግዚአብሔር ሰዎች አሉ፡፡ ምናልባት በአደባባይ ሳይሆን በእልፍኝ በከተማ ሳይሆን በገዳም ስላሉ እነዚህን ሰዎች ማየት እንቸገር ይሆናል፡፡ የእግዚአብሔር ሐሳብ ግን መልካም ሰዎችን እንድንፈልግ ብቻ ሳይሆን መልካም ሰው እንድንሆንም ነው፡፡ ሰዎች በስብዕና የሚያደርጉትን እኛ በመንፈሳዊነት ማድረግ ካልቻልን ቆም ብለን እራሳችንን መመርመር ያስፈልገናል፡፡ እግዚአብሔር ግን የሰማውን የማያሰማብን ፣ የነገርነውን ምስጢር የማይዘራብን እውነተኛ አባት ነው፡፡ ዛሬ የሰው ነውር ዜና ተብሎ ብዙህ ሺህ ብር ከሚሸጥበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ የሚደብቅንል ሰው የምንደብቅለትም ወዳጅ የሌለበት የመካሰስ ዘመን ላይ ነን፡፡

የምንባረከው በመሸፋፈን እንጂ በመገላለጥ አይደለም፡፡ የወዳጃችንን ሐፍረት ከሌሎች እየሰወርን ለመለወጡ ግን ተግተን መምከር አለብን፡፡ እኛ ያየነውንም ያላየነውንም እናወራለን። እግዚአብሔር ግን ከመነሻው እስከ ፍፃሜ ያለውን ታሪክ እያወቀ ዝም ይላል፡፡ አንዳንዴም ሰውየው ንስሐ የገባበትን በደል ሳይቀር እናወራለን፡፡ ሰይጣን እንኳን በደልን በመመዝገብ ትጋቱ ንሰሐ የተገባበትን ኃጢያት ሲፅፍ አይውልም፡፡ እኛ ግን እንዲህ ስናደርግ ከሰይጣን መባሳችንን አንረዳም፡፡

እኛ ምህረትን በመስጠት መአትን ማውረድ አንችልም፡፡ ሁላችንም በታላቅ ችሎት ፊት አንድ ቀን እንቆማለን፡፡ እግዚአብሔር መዓቱም ምህረቱም በእጁ ሆኖ ይታገሰናል፡፡ ዛሬ አብረን እየበላንና እየጠጣን የወዳጃችንን ወንጀል ለአንድ ቀን እናጠራቅማለን፡፡ ይልቁኑም ሥልጣን ያላቸውን ሰዎች ለማዋረድ ስንት ፋይል ከፍተን እናሰባስባለን፡፡ አላወቅነውም እንጂ የወንድማችን ውርደት የኛም ውርደት ነው፡፡

እግዚአብሔር ለሁሉም እንደስራው ይሰጠዋል፡፡ እርሱ ሲፈርድ የእኛን ሰነድና ምስክርነት አይፈልግም፡፡ የሁሉም ጥፋት ከየግንባሩ ላይ ያነበዋል፡፡ በክርስቶስ ፊት ስንቆም የራሳችን እንጂ የሌሎች በደል አይታየንም፡፡እግዚአብሔር ቢቀጣን ምክንያታዊ ነው፤ ኃጢያተኞች ነንና፡፡ ነገር ግን የመዳን ምክንያት እንዲሆነን ምህረቱን አቁሞልናል፡፡ ሁላችንም "የአንድ ቀን ሥልጣን ቢኖረኝ" እንላለን በአንድ ቀን ሥልጣናችን ያንን ሁሉ ክፉ ሃሳባችንን ለመፈጸም ፤ በዘላለም ሥልጣኑ እኛን የሚያኖር ጌታ ትዕግስቱ እንዴት ሰፊ ነው!! እግዚአብሔር በፀጋው ስለሚያስተዳድረን ይኸው "አለን" ለማለት በቅተናል፡፡

እግዚአብሔር ያየብንን ቢያሳይብን ፣ የሰማብንን ቢያሰማብን ኖሮ እንደ ሰው እንኳን የማንቆጠር ፣ አንድም ቀን ለማደር የማይፈቀድልን ሰዎች በሆንን ነበር፡፡ የህሊናችንን ቁልፍ በራሱና በእኛ እጅ ስላደረገው እንኳን ልናመሰግነው ይገባል፡፡ የምናስበው ሁሉ ቢገለጥ ከማን ጋር እንኖር ነበር??? እግዚአብሔር ብቻ ይችለናል የእኛ ነገር የማይገርመው እርሱ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ የነገርነውን ሌላ ሰው ጋር አናገኘውም፡፡ ሰዎች የምንናገረውን በማዳመጥ ይወዱናል፡፡ የምናስበውም ግን አያውቁም፡፡ ቢያውቁ ሊጠሉን ይችላሉ፡፡ አውቆ የሚወደን ግን እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ የቀደሙ አባቶች እንደሚሉት "እርሱ ልብ ያወጣውን ኩላሊት ያጤሰውን ያውቃል" ይህ አምላክ አንድ አላማችን ፣ አንድ አይናችን ፣ አንድ ተስፋችን ነውና ተጠንቅቀን ልንይዘው ይገባል፡፡ ከሰው የታጣ በእርሱ ይሞላል፡፡ ከእርሱ የጎደለ ግን በማን ይሞላል??? ሰው ቢሸሸን እግዚአብሔር ዘመድ ይሆነናል÷እግዚአብሔር ቢርቀን ግን ማን ዘመድ ይሆነናል???

ሰዎች ፍቅራችንን ቢችሉት በደላችንን ግን መቻል አይሆንላቸውም፡፡ መስጠታችንን ቢወዱትም ሁልጊዜ ተቀባይ መሆናችንን ግን አይፈልጉትም እግዚአብሔር በኃጢያታችነ በፍላጎታችን ይችለናል፡፡ እርሱ እንዳየ ሰዎች ቢያዩን እርሱ እንደሰማ ሰዎች ቢሰሙን እንደ እኛ ክፉ ፍጥረት ባልነበረ፡፡ እርሱ ግን እንደኃጢአታችን አላደረገብንም እንደበደላችንመ አልከፈለንም፡፡

ያለንበት ዘመን ለእውነት ተቆርቋሪ የሚመስለውም ሆነ በአቋም የሚዋሸው ሁሉም አንድ የሆነበት ዘመን ይመስላል፡፡ የእግዚአብሔር ሰዎች ደግሞ በራቸውን ዘግተው የመጣውን መዓት እስኪያልፍ አቤቱ አቤቱ እያሉ ነው፡፡ በዛሬው ዘመን ያለው እውነተኝነት በእውነት ተከልሎ የጠሉትን ለማጥቃት እንጂ የጠፋውን ለመመለስ አለመሆኑ ያሳዝናል፡፡ ለዚህም ድራማችን እግዚአብሔር በቅርብ ጊዜ ድንበር ይሰጠዋል፡፡ ጥበብም ፣ ሃብትም የማያልፈው ቁርጥ ቀን ቀርቧል፡፡ ይችህ ቀን የምታልፈው ያለ ግብዝነት የምትቀርብ ፀሎትና እውነተኛ ንስሐ ብቻ ናት፡፡

ከእርሱ ጋር ያለነው በአንድ እድል ቢሆን ኖሮ ሰው ለመሆን ባልበቃን ነበር፡፡ "ከሎሌ ጥፋት ከጌታ ምህረት" እንዲሉ እኛ ከመበደል እግዚአብሔር ይቅር ከማለት ያረፍንበት ዘመን የለም። እግዚአብሔር ለመጨረሻ ጊዜ ነው ምቀበላችሁ ቢለን ምን እንሆን ነበር??? እርሱ ከእንግዲህ ወዲህ በቃኝ ቢለንስ ማን ይሸከመናል???

የማይለወጥ ፍቅሩ፣
የማይናወጥ ባሕርዪ፣
የማያልቅ ቸርነቱ፣
የማይሰለች ምህረቱ፣
የማይወሰን ይቅርታው፣
የማይጠብ ትዕግስቱ.......
ከኛ ያላራቀ የተባረከና የተመሰገነ ይሁን

ከመጀመሪያው መፅሐፍ ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተቀነጨበ፡፡

ይችህን እያነበባችሁ በህይወታችሁ ለመኖር መንገጅ ጀምሩ እንደመጽሐፉም እየኖራችሁ ያላችሁ በርቱልኝ.....

አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኘ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB GRAPHIC DESIGN
🙏🙏😍😍🙏🙏😍😍🙏🙏😍😍
ድንግል ሆይ ልደትሽ ልደታችን ነው፡፡
ከቀኖች ሁሉ አንቺን ያገኘንበት ቀን ምንኛ የተባረከች ናት፡፡ የዓለም ሁሉ መዳኛ ክብር እና ልዕልናሽን ለመናገር ቃላቶች አይበቁንም
እንዳንጠፋ አንቺን የሰጠን የተመሰገነ ይሁን!!
እንኳን አደረሳችሁ መልካም በዓል
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB GRAPHIC DESIGN

ሃና እና እያቄም በፀሎት ቢተጉም በፈጣሪያቸው ፊት መልካሙን ቢያደርጉም
በቅዱስ ጋብቻ ፀንተው ቢራመዱም
የአምላክን እናት ድንግልን ወለዱ፡፡
ሀና እና ኢያቄም ሰማይን ወለዱልን
ሰማያቸው ደግሞ ፀሀይን ወለደች

ክብር እና ምስጋና
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
በቀጣይ ከመጀመሪያው መፅሐፍ የመጨረሻ ፖስት፡፡
ትንሽ ረዘም ስለሚል ሁለት ቦታ ከፍለን እናቀርባለን፡፡ በመጨረሻም ፖስት ላይም የመፅሐፉን ርዕስና የደራሲውን ስም ምናሳውቅ ይሆናል፡፡
😊🙏😍🙏 ቤታችን እንሁን
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ይቅር ባይ እንሁን

የሀሳብ መለያየት ተፈጥሮ ነው፡፡ ተፈጥሮን መሻር አይቻልም፡፡ ተፈጥሮ ግን በመወያየት ይታረቃል፡፡ ባል እና ሚስት እኮ የሚያዋህዳቸው የተፈጥሮ ልዩነታቸው እንጂ አንድነታቸው አይደለም፡፡ ጾታቸው የተለያየ ነው፡፡ ልዩነቱ ግን የአንድነት ምክንያት ነው፡፡ ልዩነት ወደ አንድነት ያመጣል፡፡ ፍቅር ነው፡፡

የሀሳብ መለያየት እንደጠላት እያስተያየ ማጋደሉ ዛሬም ድረስ ዘልቋል፡፡ ቀይ ሽብርና ነጭ ሽብር እየተባባሉ በጎዳና ሲቀላሉ የኖሩ የአንድ እናት ልጆች አመለካከትን ማስታረቅ አቅቷቸው ነው፡፡ የአሳብ ልዩነትን እንደጠላት ማስተያየቱ አሳዛኝና ኀላ ቀርነትም ነው፡፡

በግጭቶች ውስጥ አንዱ ትዕግስት ያጣና ክፋ ቃል ይናገራል ፣ ክፉ እርምጃ ይወስዳል፡፡ እርሱ ጀምሮታል ብለውም ሁለኛውን ክፋት ብዙዎች ይቀጥላሉ፡፡ አንተ ትዕግስት የምታጣው ወገን አንድ ክፉ ነገር ስትናገር ሁለት ክፉ ትሰማለህ፡፡

የዘራኸውን ስድብ አትረፍርፈህ ታመርታለህ፡፡ አንተ ክፉ ምላሽ የምትሰጥ እርሱ በጀመረው ላይ ስለቀጠልክ የማትጠየቅ እንዳይመስልህ የሚያስጠይቀው ቅደም ተከተሉ ሳይሆን ክፉ ማድረጉ ነው፡፡ ይልቁንም እረሱ ሲያደርገው የጠላኸው እንዴት እንዲጠጋህና እንዲገዛህ ትፈቅዳለህ? ለክፉ ክፉ ስትመልስ የተንኮል ደቀመዝሙር እየሆንክ ለክፋት ሠራዊት ተጨማሪ ወታደር እንደሆንክ ማሰብ አለብህ፡፡ እርሱ በእጁ ያለውን ድንጋይ ይወርውር ባንተ እጅ ያለውን ብርቱካን ወርውርለት፡፡ ድንጋዩ ሲያልቅበት መልሶ ብርቱካኑን ይወረውርልሃል፡፡ ክፉ ነገር ያልቃል ፣ መልካም ነገር ግን አያልቅም፡፡ ብዙ ሀይለኞች ዛሬ ደክሟቸው የትንንሽ ልጆች መጫወቻ ሆነዋል የእግዚአብሔር ሰራዊቶች ግን በዓመታት ውስጥ አይደክሙም፡፡

አንድ ታዋቂ መሪጌታ ነበሩ፡፡ እኚህ መሪጌታ ክፉ ነገር ከአፋቸው ተሰምቶ አይታወቅም። ታዲያ አንድ ቀን ሰዎች፡- "እርሶ ግን መቼ ነው ተሳስተው ክፉ ነገር የሚናገሩት?" ቢሏቸው :- "መልካሙ መቼ አልቆብኝ ነው ክፉ ምናገረው" አሉ ይባላል፡፡

ለብዙዎቻችን ጠላታችንን ይቅር ከማለት ወዳጃችንን ይቅር ማለት ይከብደናል፡፡ የመዋደዳችን ፍፃሜ መጠላላት ለምን ሆነ? ከመጀመሪያው ፍቅር የኋላው ይቅርታ ይሻላል፡፡ አዎ "የሰዎችን በደል ሲረገጥ በሚጠፋው ፣ ነፋስ በሚሸፍነው አሸዋ ላይ መጽሐፍ ይገባናል። መልካምነታቸውን ግን በማይጠፋው ዓለት ላይ በልባችን ላይ መቅረፅ ይገባናል፡፡"

እኛ ግን የምናደርገው በተቃራኒ ነው፡፡ አንገት የተሰጠን ለጌጥ አይደለም ፣ ዞር ብለን ለማየትም ነው፡፡ ስለዚህ ያለፈውን መልካም ጊዜ ዞር ብለን ማየት አለብን፡፡ ለክፋት ሳይሆን ለመልካም ነገር ዋጋ መስጠት አለብን፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ የሰናፍጭ ቅንጣት እምነት ፣ የእሳት ፍንጣሪ የምታህል ምግባር ዋጋ አላት፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ የመልካም ነገር ዋጋው ብዙ ሲሆን በሰው ዘንድ ግን የክፉ ነገር ሚዛኑ ከፍ ያለ ነው፡፡

የራሳችንን ደካማነት ስንረዳ የሌሎቹን ደካማነት ለመረዳትና ይቅርታ ለማድረግ ዝግጁ እንሆናለን፡፡ ሰው ማነው? ለሚለውን ጥያቄ ምላሽ ካገኘን ይቅርታ የማይከብደን ሰዎች እንሆናለን፡፡ እውነተኛ ፍቅርም በክፋት ተሸንፎ ቂመኛና በቀለኛ የሚሆን ሳይሆን በመልካም አሸንፎ በዳዩን ሰው ለንሰሐ የሚጋብዝ ነው፡፡ በዓለም ላይ ከሰዎች ጋር የማንነካካበት ኑሮ ስለሌለን አስተውለን ካየነው የብዙ ሁከታችን ምንጩ የይቅርታ ሕይወት ማጣት ነው፡፡ ይቅርታ የከበደው ልብ ሁሉም ነገር ይከብደዋል፡፡

ሰዎችን ከማኩረፍና ከመሸሽ በላይ የምናስተምራቸው በይቅርታ ነው፡፡ ይቅርታ ማድረግ የወደቀው እንዲነሳ እድል መስጠት ነው፡፡ በአለም ላይ ትልልቅ ስራ የሚሰራው ከተዓምራት ይልቅ በይቅር ባይነት ነው፡፡ በክፋት እየመረረች ያለችው አለማችንን የሚያጣፍጡ ይቅር ባይና አፍቃሪ ሰዎች ከሌሉ የሰው ሕይወት ፈፅሞ ተስፋ የሌለው ይሆናል፡፡ ስለዚህ ይቅር ባይ እንሁን!! ይቅር ያልናቸው ሰዎች ከበደሉን በላይ ይክሱናል፡፡ ይቅርታ ሰው ያበላሸውን እንዲያስተካክል ዕድል መስጠት ነው፡፡

ህፃን ልጅ ወድቆ የሚነሳው ዙሪያውን አይቶ የሚጠብቁት ሰዎች ድጋፍ ከሰጡት በኋላ ነው፡፡ ተስፋ የሚያደርገውሰው ከሌለ ለመነሳት አያስብም፡፡ እዚያው እንቅልፍ ይይዘዋል። ሰዎችም ከስህተታቸው የሚመለሱት የወዳጆቻቸውን ይቅርታ ሲያገኙ ነው፡፡ አሊያ እንደወደቁ ይቀራሉ፡፡ ሌባ የሚባሉት የሚሰርቁትን ንብረት ጠብቁ ስንላቸው ከደህነኛ ሰው በላይ ይጠብቃሉ፡፡ ፀጥታ ሲጠፋ የበጥባጮቹን አለቃ አደራው ላንተ ነው ሲባል ሌት ተቀን ተግቶ ሰላምታን ያስከብራል፡፡ ሰዎች ባመናቸው መጠን ይታመኑልናል፡፡ ይቅርታ የወደቁትን ሰዎች እንዲነሱ እድል መስጠት ነው፡፡

አንድ አባት "ልጄ በአንድ አፍ ውስጥ የሚኖሩትን ጥርስና ምላስ አስታውስ፡፡ እነዚህ አካላት ተፈጥሮአቸው የተለያየ ነው፡፡ ጥርስ ነጭ ነው ፣ ምላስ ቀይ ናት፡፡ ጥርስ ጠንካራ ስለታም ነው፡፡
ምላስ በጣም ለስላሳ ናት፡፡ አፍ ሲከፈትላት ምላስ ትወጣለች፡፡ ሲከደን በገዛ ጎረቤቷ ላለመጎዳት ትሸሻለች፡፡ ጥርስ ያደማውን እጅ ምላስ ትልጣለች፡፡ ጥርስ ሲያኘክ ምላስ ታርስለታለች፡፡ የፊት ጥርስ ማኘክ ሲከብደው ወደመንጋጋው እህሉን በመውሰድ ትራዳለች፡፡ ግን በአንድ ቤት ይኖራሉ፡፡ እኛም መልካችን ፣ አቅማችን ፣ የሥራ ድርሻችን የተለያየ ፣ አንዳችን ስለታም አንዳችን ለስላሳ ብንሆንም ተቻችለን መኖር ይገባናል " አሉኝ። አዎ እሾህ ያላቸው ጃርቶች ተጣብቀው ይሔዳሉ፡፡ አንዱ ያንዱን ሙቀት ለማግኘትና ብርዱን ለመከላከል መወጋጋታቸውን ይችላሉ፡፡ እኛም ባልተለወጠ ማንነት ውስጥ እንደመኖራችን ሁላችንም ያልተነቀለ እሾህ አለን፡፡ ተገልለን ለመቀመጥ የዓለሙ ብርድ ይገድላል፡፡ ከመሞት መቁሰል የተሻለ ነውና ልንጠጋጋ ይገባናል፡፡ ድካማችንን እንደ አደጋ ከመቁጠር ተፈጥሮ መሆኑን ማሰብ ያበረታናል፡፡ ክፉ ጠባይ ባለቤቱም እየጠላው አብሮት ይቆያል፡፡ እግዚአብሔር ግን ይለውጣል፡፡ ተሰርተን እስከምናልቅ መሸካከም ይገባናል፡፡

.....ይቀጥላል....
AB PHOTOGRAPHY &GRAPHIC DESIGN

ቀዝቀዝ ለማለት😀😀😀

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
በቀጣይ

ከመጀመሪያው መፅሐፍ ቀሪውንና የመጨረሻውን ክፍል ይዘን እንቀርባለን መፅሐፉን ገዝታችሁ እንደምታነቡት ባለሙሉ ተስፋ ነኘ፡፡ አስተያየታችሁን እየሰጣችሁኘ ስላላችሁም ደስተኛ ነኘ አሁንም ይቀጥል እላለሁ፡፡
ቤታችን እንሁን እናንብብ
ቀጣይ እና የመጨረሻ ክፍል

.....ይቅርታ በነበረን ታሪክ ላይ ያልነበረንን አዲስ ታሪክ በህይወታችን ላይ ይጨምርልናል፡፡ የበደለንን ብናስፈርድበት ይህ ለዓለም አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ይቅር ብንለው ግን አዲስ ታሪክ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም በይቅርታ ሊማሩ የማይፈልጉ ሰዎችን እናስተምርበታለን፡፡ በእውነት የሚከብደን ይቅር ማለት ብቻ ሳይሆን ይቅርታም መቀበልም ይከብደናል እግዚአብሔር ይጎብኘን፡፡

አዎ እግዚአብሔር በኃጢያታችንና በድካማችን ተሸክሞናል፡፡ ራርቶም ይቅር ብሎናል፡፡ ይህ ትዕግስቱ ከማረከን እኛም ይቅር ባዮች ልንሆን ይገባል፡፡ እግዚአብሔር በድካማችን ብቻ ሳይሆን በፍላጎታችንም ተሸክሞናል፡፡ እኛም የሰዎችን በደላቸውን ብቻ ሳይሆን ፍላጎታቸውንም በትዕግስት ልናሟላላቸው ይገባናል፡፡

አንድ ሰው፡- "በዚህ ዓለም ላይ ያለኝ ወዳጄ ልብስ ሰፊዬ ነው፡፡ እርሱ ብቻ በትላንቱ አይለካኝም" ብሏል ልብስ ሰፊ ትላንት ለክቶን እንደሆነ ዛሬም ስንሔድ ይለካናል እንጂ በትላንቱ ልኬት ተረጋግቶ አይቀመጥም፡፡ እውነተኛ ወዳጅም በትላንትናው ማንነት የማይለካ ዛሬም በመለወጣችን የሚያምንብን ነው፡፡ የአገራችን ሰው፡- "አንዴ ሌባ ካሏት ብትቆርብም አያምኗት" እንደሚል የአንድ ቀን ስህተት የሁልጊዜ ስህተት ፣ የአንድ ቀን ጥፋት የሁልጊዜ ጥፋተኘነት አድርገን መውሰድ በእውነት ሀጢያት ነው፡፡ ሰው ይለወጣል ሰው እንደሚለወጥ ካላመንን ሰውነታችንን እያጣን ነው፡፡ እኛም እንደቀድሞው አይደለንም፡፡ ሰዎችም እንደቀድሞ አይሆኑም፡፡ ይህ ዓለም በየዕለቱ ትምህርት አለውና፡፡

የሰዎችን የቀደሙ ስህተታቸውን ልንረሳላቸው አልቻልንም፡፡ ንሰሐ ገብተውበት ይሆናል፡፡ እኛ ግን ይቅርታውን ሳይሆን ስህተቱን ስናወድስ እንኖራለን፡፡ ታላላቅ ሰዎችም ቢሳሳቱ ሊገርመን አይገባም፡፡ ታላቅነታቸው ሰው መሆናቸውን አያስቀረውምና፡፡ ደካማ ሰዎች ግን በታላላቆቹ ስህተት ሲሳለቁ ይኖራሉ፡፡ ቃሉም "እንደ ቆመ የሚመስለው ቢኖር እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ" ይለናል፡፡

ሰዎች የጣሉትን ሸክም እኛ ተሸክመንላቸው እየተበሳጨን እንዳይሆን እግዚአብሔር ይግለጥልን፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ይቅር እንባባል፡፡ እናቶቻችን የቂም ሙዳዮች ፣ እንዳይበሰብስ የሚጠብቁት ናቸው፡፡ እገሌን በዓይኔ አያሳየኝ የሚሉት ምክንያቱ ምንድነው??? ብንላቸው በመንግስቱ ንዋይ ግርግር ጊዜ እንዲህ አድርጋኝ ነበር ይላሉ፡፡ እስከዛሬ በዚያ ክስተት ይበሳጫሉ፡፡ በደሉ የተፈፀመው ግን 1953 ዓ.ም ነው፡፡ ቂምን መንከባከብ አረም ስንዴ ላይሆን መልፋት ነው። ይልቁንም በዛሬው ዘመን የሀይማኖት ሰዎችን ከማስታረቅ ዓለማውያንን ማስታረቅ እስኪቀል ድረስ መራሮች ሆነናል ይቅር እንባባል፡፡

በእውነት ትዕግሥትን ገንዘብ በማድረግ ይቅር ባይ እንሁን፡፡

የመፅሐፍ ርዕስ:- የእግዚአብሔር ትዕግስት

በዲ/ን አሸናፊ መኮንን
2002ዓ.ም

ከመጀመሪያው መፅሐፍ የመጨረሻ ፅሁፍ

ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ
ከጻፍኩት ያልጻፍኳቸው አያሌ ምክሮች አሉበትና ገዝታቹ ታነቡት ዘንድ ስጋብዛችሁ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ በእውነት አብዝታችሁ ታተርፉበታላችሁ ትለወጡበታላችሁም ህይወታችሁን አንድ ደረጃ ከፍ ታደርጉታላችሁ ትዕግስተኛ እና የይቅርታ ሰው ትሆኑበታላችሁ .....በእርግጠኝነት ከራሳችሁ አልፎ የሌላ ሰውንም ህይወት ትቀይሩበታላችሁ፡፡

መጽሐፉን አንብባችሁ በህይወታችሁ ለመኖር መንገድ ጀምሩ እንደመጽሐፉ እየኖራችሁ ያላችሁ በርቱልኝ

አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኝ

ጊዜዋን አጣባ የኔን አያሌ ስህተቶች ሳትሰለች አርማ እናንተ ጋር በአማረ መልኩ እንዲደርስ ለረዳችኘ ለትዙ ላቅ ያለ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ፡፡ አክብሮቴ ላቅ ያለ ነው፡፡
😍🙏😍🙏😘
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD