Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
AB PHOTOGRAPHY &GRAPHIC DESIGN

ስራን ከጥንቃቄ ጋር👏👌👌

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

እንደ መግቢያ

በሰማይ ላይ የሚበሩ አእዋፋት መልካቸውና ተፈጥሮአቸው እንዲሁም የአኗኗር ዘይቤያቸው የተለያየ ነው፡፡ ከእነዚህ አእዋፋት መካከል በV ቅርፅ የሚበሩት አእዋፋት ልዩ የሆነ የበረራ ሥነስርዓት አላቸው፡፡ ይህ በተፈጥሮ የታደሉት የበረራ ሥርዓት ለበረራው ሳይንስም ትልቅ መነሻ በመሆኑም አገልግሏል፡፡ በV ቅርፅ የሚበሩ ሁሉም አእዋፋት ሳይሆኑ ውስኖቹ ናቸው። ተመሳሳይ ቀለም ያላቸው በV ቅርፅ የሚበሩበት አእዋፋት እግዚአብሔር እንድንማርባቸው ያስቀመጠልን ተጓዥ ሰሌዳዎች ናቸው፡፡ ወደ ታላቅ መንፈሳዊ ተመስጦ የምንገባው የእግዚአብሔርን ቃል በማጥናትና ተፈጥሮን በማስተዋል ነው፡፡ በተፈጥሮ ውስጥ የፈጠረውን ጌታ የምናደንቅበት ጥበብ ተቀምጧል፡፡ እኛንም የሚያስተምር እውቀት ተስሏል፡፡

በV ቅርፅየሚበሩ አእዋፋት የበረራ ሥነስርዓታቸው የብዙ ተመራማሪዎችን ቀልብ የሳበና ናሳ የተባለውንም የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ማዕከል ሳይቀር ትኩረት አድርጎ የሚያጠናው ነው፡፡ ሰው ከሰው ብቻ ሳይሆን ሰው ከአእዋፋትም የሚማረው ትምህርት አለው። ከትምህርት ውጪ የሆነ አንዳች ፍጥረት ስለሌለ የሰው ልጅ በትህትና መማር ይገባዋል፡፡

እነዚህ አእዋፋት በV ቅርፅ መብረራቸው ራሱን የቻለ ጥቅም አለው፡፡ ይህ እውቀትም ከእግዚአብሔር የታደሉትና ለሰው ትልቅ አብነት የሚሆን ነው፡፡

አእዋፋቱ የሚበሩት ቅርፅ ከፊት ጉልበተኛ የሆነው ወፍ የመጀመሪያው መስመር ሲይዝ ከመጀመሪያው መሪ በመቀጠል ሰልፉ ለሁለት መስመር ወደኀላ እየሰፋ ይሔዳል፡፡ ከፊት ያለው መሪ ጉልበተኛ መሆኑ የአየር ግፊት የሚጋፈጠው እርሱ ስለሆነ ነው፡፡ መስመሩ በሁለት እረድፍ እየሰፋ ሲሔድ ሁሉም በራሪ አካል መሪውንና የበረራ ጓዱን በቀላሉ ለመመልከት ይረዳዋል፡፡

ከሰልፉ የወጣ ካለም ራሱን በሰልፉ መስመር ውስጥ ለማስተካከል የሚችልበት መልካም መንገድ እይታን ይፈጥርለታል፡፡ ከፍታቸውም የሁሉም እኩልነት አይደለም፡፡ ርቀቱን እየጠበቀ ደረጃው ወረድ ወረድ እያለ ያንን የV ቅርፅ ይጠብቃል፡፡ ደረጃውን እየቀነሰ መብረራቸው የአየር ግፊት ለመሰንጠቅ ይረዳቸዋል፡፡

ከፊት ያለው መሪውን ከታች ያለውን ግፊት ታግሎ ሲሰነጥቅ ከኋላ ለሚከተለው ወፍ ወደታች የሚገፋው ሀይል አቅጣጫው ተቀይሮለት ወደላይ የሚገፋ ሀይል ይሆንለታል፡፡ ስለሆነም ከፊት የሚቀድመው ወፍ ወደላይ ሊያንሳፍፍ የሚችል የአየር ሁኔታ ስለሚያጋጥመው ከኋላ የሚከተለው ወፍ ክንፉን በጉልበት ማርገብከብ ሳያስፈልገው ባነሰ ጉልበት በፍጥነት መብረር ያስችለዋል፡፡

እነዚህ በV ቅርፅ የሚበሩ አእዋፋት ብዙ ጊዜ ቡድናቸው 25 አባላት ያሉት እንደሆነ ተደርሶበታል። እነዚህ በV ቅርፅ የሚበሩ ወፎች ብቻቸውን ከሚበሩ ወፎች ይልቅ ሰባ በመቶ የተሻለ እንደሚበሩ ታውቋል፡፡ በረራቸውም አንዳቸው ከአንዳቸውን ያለውን ርቀትን በመጠበቅና በመቆጣጠር የሚከናወን ነው፡፡

በV ቅርፅ የሆነው ይህ በረራ መስመሩን የጠበቀ ደረጃ አለው፡፡ ደረጃውም የላይኛው የታችኞቹን የሚስብ የላይኞቹ ደግሞ እንዲንሳፈፉ የሚያደርጋቸው ነው፡፡ ይህ የበረራ ስልት ጠቃሚ ቢሆንም ከፊት የሚቀድመው ወፍ ግን አስቸጋሪው ኃላፊነትን የሚወጣ መሆን አለበት፡፡ ታዲያ ይህ ወፍ በሚደክምበት ጊዜ ከV ቅርፅ የአንዱን ጎን በመያዝ ወደኋላ ሲል ቀጣዩ ደግሞ የመሪነቱን ስፍራ ይጎናፀፋል፡፡

መተካካቱ ስላለ የሰልፉ ሥርዓት በቅፅበት ውስጥ ተስተካክሎ ይቀጥላል፡፡አሁን የተተካውም ሲደክመው ከመሐል ካሉት አንዱ በፍጥነት በመሔድ የመሪነቱን ድርሻ ይወጣል፡፡ ይህ አድካሚውን የመሪነትን ቦታ የመጨበጥ ድርሻ ሁለም በየተራ ይካፈሉታል፡፡ ሁሉም ኃላፊነትና ድርሻን በመከፋፈል በረራውን ወደ ግቡ በፍጥነትና በጥራት እንዲጓዝ ያደርጉታል፡፡

በV ቅርፅ በሰልፍ መብረር ወፎቹ በቀላሉ ግንኙነት እንዲያደርጉ ይረዳቸዋል፡፡ መልካም መተያየትን ስለሚፈጥርላቸው ሳይነጣጠሉ እስከመጨረሻው እንዲበሩ ይረዳቸዋል፡፡ መተያየት ተጣጥሎ መግባትን የሚያስቀር የኅብረት ኃይል እንደሆነ እንረዳለን፡፡ የጦር ጄት አብራሪዎች ይህንን የተፈጥሮ ትምርህርት በመቅሰም ለተመሳሳይ አላማ ይጠቀሙበታል፡፡

ከፍተኛ ጫና ያለው በመሪው ላይ መሆኑ እርሱ አየሩን በጉልበት ሲሰነጥቅላቸው ተከታዮቹ የመንሳፈፍ ያህል በቀላሉ ይጓዛሉ፡፡ ከእርሱ ጉልበት አነስ የሚሉት የመሪነቱን ስፍራ ለመረከብ ተከታይ ሆነው ይጠብቃሉ፡፡ ከፊት ያለውና ተከታዮቹ ቡድኑን ሲመሩ ከኃላ የሚሰማው ድምፅም ለፊተኞቹ ፍጥነታቸውን እንዲጨምሩ ጉልበት የመስጠት አቅም አለው፡፡

አንዱ የቡድኑ አባል ከሰልፉ ወጥቶ ብቻውን እንደሚጓዝ የሚረዳው ቅድም ያላየው የአየር ግፊትና ጫና ሲገጥመው ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ፈጥኖ ወደ ሰልፉ በመመለስ በሰልፉ ብቻ የሚያገኘውን ያለ ድካም የመንሳፈፍ ኃይል ያገኛል፡፡

ከሰልፈኞቹ መካከል አንዱ በሕመም ፣ በአዳኞች ጥይት ቢመታ ወይም ከሰልፉ ውጪ ባሉ በራሪ ነፍሳት ቢጠቃና ወደ ፊት ከመሔድ ይልቅ ወደ ታች መውረድ ቢጀምር ከሰልፈኞቺ ሁለቱ ከሰልፉ በመውጣት የተጎዳውን ወገናቸውን ይረዱታል፡፡ ከተጨማሪም ጥቃት ይከላከሉታል፡፡ የተጎዳውም ወፍ ከዛፍ ላይ ወይም ከመሬት ላይ ቢያርፍ መብረር እስኪችል ወይም እስኪሞት ድረስ ሁለቱ ወገኖች አብረውት ይቆያሉ፡፡ በመጨረሻም ከራሳቸው ቡድን ጋር እስኪቀላቀሉ ከሌሎች ሰልፈኞች ጋር ጉዞአቸውን ይቀጥላሉ፡፡ በረራው ግን ምን ጊዜም አይስተጓጎልም፡፡ የደከመውንም ጥለውና ረስተው አይሔዱም፡፡ ደካማው ዋስትና አለው፡፡

የጠነከሩት ወፎች ሰልፉን ይመራሉ፡፡ የጠነከሩት ሁልጊዜ ስለማይመሩ ለተከታዩ ስፍራን ስለሚለቁ በሥራ ብዛት ጫና ወይም በድካም የሚታገል መሪ አይኖርም፡፡ የተለየ ጉልበትና ችሎታ ያላቸው ወፎች በተመሳሳይ ፍጥነት በጋራ መብረራቸው አስገራሚ ነገር ነው፡፡

ቡድኑ የብርቱዎች ስብስብ ሳይሆን ብርቱዎች እየቀደሙ ሌሎችን የሚያበረቱበት ፣ ከቡድኑ በአደጋ የተለየው መብረር እስኪችል ድረስ በውድቀቱ ስፍራ ወድቀው የሚረዱበት ፣ እርዳታው እየተከናወነ ሰልፉ ግን የሚቀጥልቀበት መሆኑ ይገርማል፡፡

ከሁለተኛ መጽሐፍ የመጀመሪያ ፅሁፍ
ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ

አስተያየታችሁ @jahABP ላይ አድርሱኝ

ቤታችን እንሁን እናንብብ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY &GRAPHIC DESIGN

Ma little angle eye😍😍

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN


.....እግዚአብሔር አምላክ በእያንዳንዱ ተፈጥሮ ላይ ለእኛ ያስቀመጠውን ትምህርት የምናገኘው በጽሞና ነው፡፡ እግዚአብሔር በትንሽ ክፍል ውስጥ በአንድ መምህር ብቻ የሚናገር አምላክ አይደለም፡፡ መላው አለም ለእግዚአብሔር ማስተማሪያው ክፍሉ ነው፡፡ ሁሉም ለጥቅማችንና ለትምህርታችን ተፈጥሯል፡፡ አርኪ ጥቅም ያለው በመማር ውስጥ ነው፡፡ እነዚህ አእዋፋት ከህይወታችን ጋር ምንም ተዛምዶ የሌላቸው ይመስለናል፡፡ ይህንን መምሰል ግን የሚሽረው መመርመር ነው፡፡ እነርሱም እኛን እንዲናገሩን ሆነው ተፈጥረዋል፡፡ ይህን ትምህርት ግን የምናገኘው ከግርግር ይልቅ በጽሞና ፣ ከመናገር ይልቅ በማዳመጥ ውስጥ ነው፡፡ ግርግርና ልፍለፋ የዕውቀት ጠላቶች ናቸውና፡፡

እግዚአብሔር ሁሉን በወገኑ ፈጥሯል፡፡ ሁሉም በወገኑ ይጓዛል ፣ ይበራል፡፡ የሰው ወገን ደግሞ ሰው ነው፡፡ ስለዚህ ሰው ከሌላኛው ወገኑ ጋር አብሮ ሊጓዝ ፣ ተባብሮ ሊሰራ ይገባዋል፡፡

እግዚአብሔር የሰጠን አለም በኅብረት የምትገነባ አንዲት ቤት ናት፡፡ እንኳን ሰፊው አለም አንድ ህንፃ ብንመለከት በውስጡ ዲዛይን ካደረገው አንስቶ ብዙ ባለሞያዎችን እናገኛለን፡፡በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ያለው ህንፃ ብዙ ሰዎች የሚያሳትፍ ከሆነ ዓለምማ የብዙኃን ትብብር ይጠይቃል፡፡

በዓለም ላይ የሚገኙ ሰዎች በሦስት ከፍለን ብናያቸው:-
* ኅብረት ወዳጆች:- ለብዙኃን ጥቅም የሚኖሩ
* ራስ ወዳዶች:- ብዙኃን ለኔ ይኑሩ የሚሉ
* ገለልተኞች:- ተሸፍነው ለማለፍ የሚፈልጉ ናቸው፡፡

ገለልተኝነት ለሌሎች ብቻ ሳይሆን ራስንም የማይጠቅም ቃጠሎ የበዛበት ደሴት ነው፡፡ ራስ ወዳድነት በመጨረሻ ራስን ለማጥፋት ወንጀል የሚዳርግ ነው፡፡ ኅብረትን ፈላጊነት ግን ለብዙዎች ጥቅም ልኑር የሚል መንፈስ ነው። የቤተክርስቲያንን አባቶች እንዲሁም የሀገር ባለስልጣናትና መሪዎችን ስንነቅፍ ከግላችን ጥቅም አንፃር ነው ወይንስ ከብዙኃን ጥቅም አንፃር ነው??? ብለን መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡

ከራሳችን አንፃር የምንሰጠው ድጋፍም ሆነ ተቃውሞ ፍትሐዊ አያደርገንም፡፡ ለብዙኃን እንድንኖር የተፈጥሮ ግባችንን አሳክተን እንድናልፍ የሚያደርገን ራዕይ ብቻ ነው፡፡ ራዕይ ሁሉን ሰው እንደ ጠቃሚው እንደ ለውጥ አጋሩ ያየዋል። ክፉውንም ሰው ሳይቀር ይጥፋ ብሎ አይበይንበትም፡፡

ዐፄ ቴዎድሮስ እንዲህ አሉ ይባላል፡-
"ጋረድ ይሙት ብሎ ማነው የመከረ፣
ክፉ ለክፉ ቀን ይሆን የነበረ፣" ብለዋል

ቀድመው ያዩ ፣ የማስተባበርና የብዙኃንን ልብ በቀላሉ ማግኘት የሚችሉ ፣ ውስጣዊ ጀግንነት ያላቸው እንዲመሩን እንፍቀድ፡፡ ሁላችንም መሪ ከሆንን ብዙ ግቦች ይኖሩናል፡፡ ይህ የተፈጥሮ ህግ ነው፡፡ ይህ የሥልጣኔም መለኪያ ነው። ቦታ ሊያሳየን ከፊት የሚቀድመውን ሰው እናስብ፡፡ ሊመራን የሚችለው ቀድሞ ያየ በመሆኑ ነው፡፡ አስቀድሞ መጥቷል ፣ አሊያም የመንገዱ ምልክት ገብቶታል፡፡ ሆነም ሳይሆን የማየት ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ራዕይ ነው፡፡

ከአገር አገር በግልና በኅብረት ስንጓዝ ወጪውና እርካታው ልዩነት አለው፡፡ በኅብረት ስንሆን በአነስተኛ ወጪ ብዙ እንረካለን በግላችን ስንሆን ግን በብዙ ወጪ እንኳን ትንሽ መርካት ያቅተናል፡፡ በኅብረት መጓዙ በማንኛውም ገጽታ ጉልበት ይቀንሳል ፤ እርካታውም ይበዛል፡፡

እኛ በኑሮአችን የጋራ ስህተትን ስንመኝ የግል ሽልማት ደግሞ እንፈልጋለን፡፡ ነገር ግን ስህተትም እርምት የሚያገኘው በኅብረት ውስጥ ነው፡፡

በማንኛውም የሕይወት ዘርፍ ከኋላ ሆነን ለመሪዎቻችን የምናሰማው ድምፅ የሚያበረታታ አይደለም፡፡ ጓደኛ ለጓደኛው ፣ ሚስት ለባሏ፣ ምእመናን ለቀሳውስት፣ ዜጎች ለመንግስታት ፣ አንባብያን ለደራሲያን.....የሚያሰሙት ድምፅ መልካም ስላልሆነ ጉዞው መዘግየት ይገጥመዋል፡፡

እነዚያ አእዋፋት ግን የብርታት ጩኸትን ያሰማሉ፡፡ ጩኸቱ ሲሰማ ሩጫው ይፈጥናል፡፡ ቡድኑ በአንድነት እንዳለ ይገልፃል፡፡ የፊት መሪው የኋላውን የሚያየው በጆሮው ነው፡፡ በብርታት ጩኸት!

መሪዎች በቃኝ ሲሉ ሳይሆን በጉልበታቸው ልንተካላቸው ያስፈልገናል "መልካም ባልንጀራ ማር ነው ፣ ነገርግን ጨርሰህ አትላሰው" ይባላል፡፡ ጉልበቱን ጨርሶ የሚያገለግለን መሪ ደክሞት የወረደ ቀን ደስታ የለውም፡፡ የሠራውን እያየ እንዲደሰት ፣ አማካሪ ሆኖ ተተኪውን እንዲያሰለጥን በጉልበቱ ሳለ ልንተካው ያስፈልጋል፡፡ ሰልፉ ሳይቆም መተካካት መልካም ነው፡፡ ሰልፉ ከቆመ በኋላ መተካካት ግን ሁልጊዜም ጀማሪ ፣ ሁልጊዜም ሕግ አርቃቂ መሆን ነው፡፡

መንግስት ለሰራተኛው ደሞዝ ብቻ ሳይሆን ጡረታም ይሰጣል፡፡ ደሞዝ መስራት ለቻለበት ዘመን የሚከፈል የጉልበት ዕዳ ነው፡፡ ጡረታ ደግሞ መስራት በማይችልበት ዘመን የሚሰጥ የአገልግሎቱ መታሰቢያ ነው፡፡ ለድክመቱ የምናደርገው ምንድነው??? በሕመም ፣ በጠላት ጥይት ተጎድተው ከሰልፋ ለወጡት የወፎቹን ያህል እንኳን ማድረግ ችለናል??? ሰው ማለት ተጠቅመን የምንጥለው ዕቃ አይደለም ቢደክምም እንደገና ኃይሉን አድሶ የሚነሳ ነው፡፡ ለደከሙት በጀት አለን? የሰሩትን ሥራ ብቻ ሳይሆን ሰዎቹንም ማክበር ይገባናል፡፡ ሠራተኛ በሌለበት ሥራ የለምና፡፡ የራዕይ ቤት በእነዚህ ሁሉ ሐቆች የተዋቀረ ነው፡፡

ዕድሜ የገፉ ፣ ብዙ ትግሎችን አይተው በአቅም ገዳቢነት የተቀመጡ ለአዲሶቹ ስልጠና መስጠት ይገባቸዋል፡፡ የእነርሱ ስራ በሌሎች ከተሰራ ዛሬም እየሰሩ እንደሆነ እየተሰማቸው ሊደሰቱ ይገባቸዋል፡፡

ሁልጊዜ በጉልበትና በብርታት መሆን አይቻልም ዓለም እራሷ በልደትና በሞት ሕግ የተያዘች ናት ስለዚህ መተካካቱ ሊያምኑበት ይገባል፡፡ አዲሱን ትውልድ እንደ አውዳሚ ከማየት መንገዱን ማሳየት ይገባል፡፡ ሳያስተምሩ መውቀስ፣ መልካሙን መልካም ሳይሉ ስህተቱን ስህተት ማለት አይቻልም፡፡ አይገባምም፡፡

እነዚህ አእዋፋት ስለ ራዕይ ብዙ ትምህርት ያዘሉ የመልካም መጋቢነት/አስተዳዳሪነት ወግ የሚያስተምሩ ናቸው፡፡ በራዕይ ውስጥ ከግል ይልቅ የራ ሩጫ የሚፈለግ ነው፡፡ በራዕይ ውስጥ መሪነትን ማየት እንጂ ሹመት አይደለም፡፡ በራዕይ ውስጥ ተነጣጥሎ መግባት የለም፡፡ በራዕይ ውስጥ የዛሬው ጎበዝ ብቻ ሳይሆን የትላንትም ጎበዝ ዋስትና አለው፡፡ በራዕይ ውስጥ አቅም ሳለ ሩጫ አቅም የሌለቀን ደግሞ ታዳጊዎችን ማሰልጠን አለ፡፡ ስለዚህ እነዚህ አእዋፋት ራዕይን የሚገልጡ በራሪ ሰሌዳዎች ናቸው ማለት ይቻላል፡፡

ወቅታዊ መነቃቃቶችን ብዙ ጊዜ እናያለን የአገር ድንበር ሲደፈር የቤታችንን አጥር ማጠባቀቅ እንጀምራለን፡፡ የጽዳት ዘመቻ ሲጀመር በራችንን ለማፅዳት እንሮጣለን፡፡ ሯጮች አሸነፉ ሲባል በየማለዳው መሮጥ እንጀምራለን፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን እንረሳዋለን፡፡ ራዕይ ግን እንዲህ አይደለም፡፡ የምንኖርለት አላማ ፣ ለዓለም የምናደርሰው የተፈጥሮ መልዕክት ነው፡፡

ከሁለተኛው መፅሐፍ ሁለተኛ ፅሁፍ

ይቀጥላል........

ቤታችን እንሁን እናንብብ
አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኝ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY &GRAPHIC DESIGN

መልካም ቅዳሜ ኢትዮጵያዬ😍😍

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

........በአጋጣሚ የምናገኛቸው ነገሮች አባካኝ ወይንም ደስታ የለሽ ፣ አሊያም እብዶች ያደርጉና፡፡ እንዲሁም ራዕይ የሌለበት ስኬት እርካታ የለውም፡፡ ሕይወት በመለኮታዊ እቅድ ያገኘናት በመሆኗ እንዲሁ የምንገፋት አይደለችም፡፡ እንኳን ያለ ራዕይ በራሳችን እቅድ እንኳን የምትገፋ አይደለችም፡፡ በመለኮታዊ እቅድ የተገኘች ሕይወት የምትመራውም በመለኮታዊ እቅድ ነው፡፡ ስለዚህ በአጋጣሚ ያልተገኘውን ህይወት በአጋጣሚ መኖር ከባድና ውስብስብ ነው፡፡

እግዚአብሔር በእያንዳንዳችን ላይ አላማ አለው፡፡ የዓለም መሪዎች አላማቸው በሕዝቡ ላይ ሊሆን ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ግን በእያንዳችን ላይ ዓላማ አለው፡፡ መንግስታት በብዙኀኑ ላይ ያላቸው አላማ ግለሰቦችን ላያይና ላይነካ ይችላል። ተዋረዱም/ፍሰቱም/ ከታች ወደላይ ነው። እግዚአብሔር ግን በእያንዳችን ላይ ያለው አላማ በህዝቡ ላይ ያለውን አላማ ይገልጣል፡፡ ተዋረዱም ከታች ወደላይ ነው፡፡ የእኛ ማንነትና የእኛ አቅም ግን ይህን አይ'ረዳውም፡፡ አጥንቱ የተሰበረ ሰው ለመጠገን አቅሙን ትቶ ለጠጋኙ ሐኪም ራሱን ማላላት አለበት፡፡ ከአሁን ሀይሉ ይልቅ ከመዳን በኋላ ያለው ብርታቱ ጠቃሚ ነው። እግዚአብሔርም ሕፃናትን ፣ ድሆችንና ስም የሌላቸውን ይጠራቸዋል፡፡ ከዛሬው አቅማችን እግዚአብሔር ባለ ዓላማ ሲያደርገን ያለን አቅም ይበልጣል፡፡

አንድ እቃ ስንገዛ አጠቃቀሙን የሚገልጥ ጽሁፍ ይሰጠናል፡፡ ጽሁፉን እያነበብን ዕቃውን በተሳካ ሁኔታ መጠቀም እንችላለን፡፡ እንዲሁም እግዚአብሔር ሕይወትን ሲሰጠን ለአጠቃቀሙ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን ሰጥቶናል። የእግዚአብሔር ቃል ያለው ህይወትን አቻችሎ መኖር ይችላል፡፡

ለብዙ ሰዎች ለምን እኖራለሁ? የሚለው ጥያቄ ከባድ ጥያቄ ነው፡፡ የምንኖርበት ምክንያት እግዚአብሔር ሲመልስልን ብቻ መኖር እንችላለን፡፡ አንድ ሰው፡- "ዓላማን በመፈለግ ዓላማ አይገኝም፡፡ እግዚአብሔር በእኔ ላይ ያለው አላማ ምንድነው? በማለት ግን ዓላማን ማግኘት ይቻላል" ብሏል፡፡

እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሚሰጠው ስጦታ አንዱ ራዕይ ነው፡፡ እርሱ የራዕይ አምላክ ነው፡፡ ራዕይ በእግዚአብሔር ይጀመራል ፣ በእግዚአብሔር ይከናወናል ፣ በእግዚአብሔር ፣ ይፈፀማል፡፡

ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በናይን አንድ ለእናቱ የነበረውንና የሞተውን ሬሳ አገኘ፡፡ ሁሉም ተስፋ ቆርጠው አፈር ሊጭኑበት እየተጓዙ ነው፡፡ እናቲቱም እንዲቀበር ወስናለች፡፡ እምቢ የምትለው ለማልቀስ እንጂ እንዳይቀበር አልነበረም፡፡ ከዚህ በኋላ መውለድ የማትችል መበለት ናት፡፡ ከእርሷ በኋላ የተገኘው ልጅ ከእርሷ በፊት ሲሔድ አይታ አዝናለች፡፡ ጌታ ግን በመንገድ ላይ አገኛቸው፡፡ አብሮ አላለቀሰም፡፡ የሞት መድኃኒትነቱን መግለጥ ፈለገ፡፡ ቃሬዛውን የተሸከሙትን ቁሙ አላቸው፡፡ እናቲቱንም አታልቅሺ አላት፡፡ ለሞተውም ሰው በፍቅር ቃና "አንተ ጎበዝ እልሃለሁ ተነሳ" አለው፡፡ የሞተውም ቀና አለ ለመጀመሪያ ጊዜ ሬሳ ለቅሶውን ሳይሰማ፡- "አንተ ጎበዝ" የሚለውን ድምፅ ሰማ፡፡ ሙትን ጎበዝ በሚል ስም መጥራት ያልተለመደ ነው፡፡ የሞተ ሰው ወዲያውኑ ስሙ ይሻራል ፤ ሬሳ ይባላል፡፡ ጌታ ግን በመቃብር አፋፍ ላይ፡- "አንተ ጎበዝ እልሃለሁ ተነሳ" አለው፡፡

አሁን ላይ ብዙ ወጣቶች ተስፋ በመቁረጥ ውስጣቸው ሞቷል፡፡ ሳይቀበሩ ጉዞ አቁመዋል፡፡ ቤተሰብ ያዝናል፡፡ አካባቢው ቃሬዛ አሰናድቶ ሊቀብራቸው ይፈልጋል፡፡ ጌታ ግን በእነርሱ ውስጥ ያየው ነገር ስላለ፡- "አንተ ጎበዝ እልሃለሁ ተነሳ" ይላቸዋል፡፡ እነርሱን በዛሬ ሳኦልነታቸው ሳይሆን በነገ ጳውሎስነታቸው የሚያይ ወዳጃችን ነው፡፡ እግዚአብሔር በአለቀ ነገር መጀመር የሚችል ጉልበታም ፣ ከብሮም የሚያስከብር ንጉሥ ነው፡፡

ሰዎችን ከተኙበት ነገር የመቀስቀሻ ዘዴዎች በዘመናት የተለያየ ቅርፅ አላቸው፡፡ ይህንን በሦስት ዘመን ብናየው፡፡

1) ባለፉት ዘመናት አንድ መንፈሰ ደካማን ወጣት ለመቀስቀስ ደደብ ፣ የማትረባ.....የሚለው ቃል ያነቃው ነበር፡፡

2) በቅርብ ዘመናት እነ እገሌን አታይም የሚለው ማወዳደሪያ ቃል ያነቃዋል ተብሎ ይታሰብ ነበር፡፡

3) አሁን ግን ገና ነው ፣ ትችላለህ ፣ በርታ የሚለው ድምጽ ያነቃዋል፡፡ ይባላል ስለዚህ ጌታ ያለው የዚህንም ዘመን ማንቂያ ነው፡፡ "አንተ ጎበዝ እልሃለሁ ተነሳ"፡፡

ሚካኤል አንጀሎ አናጢዎች የጣሉትን ድንጋይ አንስቶ ሲቀጠቅጥ ጓደኛው ተመልክቶ ምን ይወጣዋል? ብለህ ነው የምትጠርበው ቢለው፡- "ውብ መልአክ አያለሁ" አለው፡፡ በብዙ ድካም ከቀረፀ በኋላ ያማረ መልአክ ቅርፅ ወጣ፡፡ ከመጥረብ በፊት ማየት ያስፈልጋል፡፡ ትልቁ ዋጋ ያለውም በማየት ውስጥ ነው፡፡ ያየ ሰው ድካሙን አይቆጥርም፡፡ ያየው ጋር እስኪደርስ ዕረፍት የለውም፡፡ ያየውን ለማየት ከሚደክመው ድካም ፣ ያየውን ታግሶ የሚቀመጠው ይከብድበታል፡፡ በመንገድ ስንሄድ ከሚታይ ቅርብ መንገድ ይልቅ የሚታየን ሩቁ መንገድ አጭር ነው፡፡

ዛሬ ብዙ ወጣቶች ኃይል አላቸው ራዕይ ግን የላቸውም፡፡ ኃይል ከአራዊትም ብዙዎቹ አላቸው፡፡ ራዕይ ግን ስለሌላቸው በቀጣይ ዘመን አይታወሱም፡፡ የጋራ ስም እንጂ የተለየ የዝና ስም የላቸውም፡፡ ታሪክ በተጠና ቁጥር በዚያ ዘመን እነማን ነበሩ ለሚለው መልስ የሚሰጡ የዚያ ዘመን ባለ ራዕዮች ናቸው፡፡

ብዙ ወጣቶች መጀመር ይፈራሉ፡፡ ያለቀ ነገር ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ የድል ደስታን ስለማያገኙ ሕይወትን ይሰለቻሉ፡፡ ያለ ትግል ድልን ይመኛሉ መንፈሳቸውን ቀዝቃዛ ያደርጉታል በጅምሩም ፍፁም ነገርን በመፈለግ ራሳቸውን ከተፈጥሮ ግጭት ውስት ይከቱታል፡፡ ብዙ ወጣቶች ከትልቅ ቤተሰብ መወለድን ዳግመኛም ከጥበብ ጋር መወለድን ይመኛሉ ለራዕይ ግን የሚመቸው ከተስተካከለው የተዘበራረቀው ነው፡፡

ቀዳማዊ ኃይለስላሴ፡- "ከትንሽ ወይም ከትልቅ መወለድ ሙያ አይደለም፡፡ ራስን ከትልቅ ሙያ መውለድ ግን እውነተኛ ሙያ ነው" ብለዋል፡፡

"ጎበዞቻችሁም ራዕይ ያያሉ" የሚለው ቃል ማራኪ ነው፡፡ ለጎበዝ የሚያስፈልገው ኃይል ሳይሆን ራዕይ ነው፡፡ ራዕይ የሌለበት ጉብዝና ከንቱ ጉብዝና ነው፡፡ መኪና ሀይል አለው፡፡ ኃይሉ ጠቃሚ የሚያደርገው መሪው ነው፡፡ ለትልቁ መኪና ፍፃሜውን የሚወስንለት መሪው እንጂ ኃይሉ አይደለም፡፡ ዛሬም ለትውልዳችን መልካም ግብ ከኃይል ይልቅ ራዕይ አስፈላጊ ነው፡፡

ከሁለተኛ መፅሐፍ ሦስተኛ ፅሁፍ

ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ

ሁሌም ይሔን ፅሁፍ ሳነብ አንዳች ኃይል ውስጤ ይሞላል፡፡

ቤታችን እንሁን እናንብብ ያነበብነውን ተግባር ላይ አውለን እራሳችንን ብሎም ሌሎችን እንለውጥ፡፡

@jahABP ነኝ

ማንኛውንም አስተያየታችሁን አድርሱኝ፡፡

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY &GRAPHIC DESIGN

መልካም ዕለተ ሰንበት

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY &GRAPHIC DESIGN

እርቀትህነ ትጠብቃለህ ትማራለህ
መልካም የስራ ቀን ምርጦች

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

??????

ሰዎች ራዕያቸውን እንዲገነዘቡ ለመርዳት አንድ ምሳሌ ይነገራል፡፡

በአሁኗ ሰዓት ልክ እንደሞትን አድርገን ራሳችንን እንቁጠረው፡፡ የቀብር ሥርዓታችን ሊፈፀም የቀረው ጥቂት ሰዓት ነው፡፡ ባለጠጎች ሞትን በቅርበት ማሰብ አይፈልጉምና ራቅ ራቅ ብለው ቆመዋል፡፡ ቆንጆዎች የለቅሶ ፉሽን የሆነው ጥቁር ልብሳቸውን ለብሰው ፣ አስለቃሽ ሰዎች እንባቸውን ካስመጡት ለመገደብ በተጠንቀቅ መሐረብ ይዘዋል፡፡ ዋዘኞች እያለቀሱ የለቅሶ ቄንጥ ያወጣሉ፡፡ ወረኞች ለመንደሩ ሪፖርት ይዞ ለመመለስ እያንዳንዷን ነገር በጥንቃቄ ይመለከታሉ ጓዴ ጓዴ ምትለዋን የድሮ ሚስቱ ትሆን?... እያሉ የሰውን ልብ በወሬ ያጠፋሉ፡፡ ሊቃውንቱም፡- ስለ ሞታችን ሳይሆን ስለ አኗኗራችን ብላሽነት ያዝናሉ፡፡ ቤተሰቦቻችኝ የሚሆኑት ጠፍቷቸዋል፡፡

ስርዓተ ቀብራችን ተፈፅሞ ቀባሪው ወደ ዐውደ ምህረቱ ሰበሰብ ስራ የበዛባቸው ቀሳውስት ቆም ቆም እንዳሉ አንድ ሰው የህይወት ታሪካችንን ሊናገር ድምፁን ሞረደ ፣ ሁሉም ሰው ፀጥ ረጭ አለ፡፡ የራቀውም ለመስማት ቀረበ የህይወት ታሪካችን መናገር ጀመረ፡፡

ታዲያ በዚህ ሰዓት እንዲነገርልን የምንፈልገው የህይወት ታሪክ ምንድነው??

"ቅንነት የተሞላበት ፣ ሁሉን ወዳጅ የነበረ ፣ ለሙት ልጆች ወላጅ የሆነ ፣ *ለሰፈር ሰው ታዛዥ የነበረ ፣ ለሰው ችግር ቶሎ ደራሽ የነበረ ፣ በፍቅር የሚያምን ትህትና የሞላው ፣ ሰው ላይ ደርሶ የማያውቅ፡፡ ሁሉን በፍቅር የሚያሸንፍ ሀይማኖቱን ፣ ልጆቹንና ቤተሰቡን አክባሪ ፣ አክብሮም የሚያስከብር ፣ ሀገር ወዳድ ፣ ስራ ፈጣሪ ፣ ባለው ነገር ደስተኛ*.....ወይስ በተቃራኒው *ቲክቶክ ተጠቃሚ ነበር instagram ላይ ብዙ ተከታይ ነበረው ብዙ የዘመኑን ወጣት የሚስብ ብዙ ፎቶዎች ነበሩት.......እስኪ ምን ተብሎ እንዲነገርልን ነው የምንፈልገው ይኼን አስበነው እናውቃለን??.......በየትኛው ነው ህይወታችን እየሔደ ያለው??* የትኛው ነው እንዲነገርልን የምንፈልገው?????

ይህ ምሳሌ ራዕይን ለማግኘት የሁል ጊዜ መለኪያ አይደለም፡፡ ራዕዬ ምንድነው? ለሚለውና ጭልም ላለበት አእምሮ ትንሽ ብርሃን ይሰጣል፡፡ በቀብራችን ሰዓት ብቻ አይደለም በቁማችንም እንዲነገርልን የምንፈልገው መልካም ነገር አይደለምን?? መልካም ናቸው እንዲባልልን እንሻለን፡፡ ነገር ግን መልካም ናቸው ከመባል መልካም መስራት ይሻላል ፣ ይቀላል ያስደስታልም፡፡

ራዕይ ምንድነው? ራዕይ ያልሆነው አይተናል፡፡ ራዕይ የሆነው ምንድነው? ጠቅለል ባለ ቋንቋ ብንገልጠው ራዕይ ግብ ነው፡፡ ግብ ሁሉ ራዕይ ላይሆን ይችላል፡፡ የተጠበቀ ግብ ግን ራዕይ ነው፡፡ ያለ ራዕይ ብዙ ስኬቶች ሊመጡ ይችላሉ፡፡በኑሮ ውስጥ የሚሰጠን መኖር በቅቶኛል ብለን እንድንረካ የሚያደርገን ራዕይ ነው፡፡ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ "ሰው የሚፈልገውን ካየ የሚጠብቀው ሞቱን ነው" ይሉ ነበር፡፡ ሰው መኖር ከብዶት ምቱን ሊመን ይችላል፡፡ ረክቶና ሰማይ ናፍቆትም ሞቱን ሊመኝ ይችላል፡፡

መኖርና መሔድን ዋጋውን እኩል የሚያደርግልን ራዕይ ብቻ ነው፡፡ ሰው የሚኖርበት በቂ ምክንያት ከሌለው መኖሩ ጣፋጭ አይሆንለትም መኖርን ጣፋጭ ከሚያደርጉት አንዱ ራዕይ ነው፡፡ እውነተኛ ራዕይ ግብ አለው፡፡ ራዕይ ግብ ከሆነ ደርሰን የምናውቀው ሳይሆን በእምነት መነፅር አይተን የምንጓዘው ነው፡፡

በመጀመሪያው እና በመጨረሻው መካከል ብዙ ሸለቆዎች/ጉድለቶች/ ብዙ ተራራዎች (ተገዳዳሪዎች) ቢኖሩም ባለ ራዕዩ ግን ወዳየው ፍጻሜ ይገሰግሳል፡፡ የሰው ልጅ "መጨረሻዬን አሳምርልኝ" ብሎ ይፀልያል፡፡ መጨረሻችን ከሚያምርበት ነገር አንዱ ራዕይ ነው፡፡ ሰለሞን እንደ ገለጠው ከመጀመሪያው የመጨረሻው ይሻላል፡፡ የተሻለው መጨረሻ ግን በራዕይ ስንጓዝ ነው፡

አንድ ሰው መጨረሻዬ እንዲህ ነው ብሎ የወሰነው ነገር ራዕዩ ይሆናል፡፡ እኛም እንደ ውሳኔያችን ነን፡፡ የምንሆነው ያሰብነውን ነው፡፡ ውጫዊ ኑሮአችን የውስጣዊ ትራፊክ ነው፡፡ የሚታዩ ተግባሮቻችን የአስተሳሰባችን ውጤቶች ናቸው፡፡ ራሳችንን እንዳዘጋጀነው ነን፡፡ ብንፈልግ አስጨናቂ ሰዎች መሆን እንችላለን ብንፈልግ አሳራፊ ሰዎች መሆን እንችላለን፡፡ ብንፈልግ ብዙዎችን ለማጥፋት የሚችል ማንነት አለን፡፡ ብንፈልግ ብዙዎችን ለማዳን ኃይል ተሰቶናል፡፡ በአንድ ኦሳማን ቢላደን አለም ተጨንቋል ፣ በአንዲት እማሆይ ትሬዛ ብዙዎች ድነዋል፡፡

እግዚአብሔር የሰጠን ነገር አለ ፣ ነፃ ፈቃዱ ግን የእኛ ነው፡፡ የአስተሳሰብ ኃይል በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ካልዋለ የጥፋት ፎርሙላ ነው፡፡ ልብ የተባለው ግዙፉ ተፈጥሮ ሳይሆን የሰው የሕይወቱ ማዕከል የሆነው አስተሳሰቡ ነው፡፡ ምነጩ ከደፈረሰ ወራጁ እንደማይጠራ አስተሳሰቡ የተበላሸም ከተግባሩ አይፀዳም፡፡ ልብ በደከመት ነገር አካል ሳይሰራ እንደሚደክመው ሁሉ ልብ ደስ ባለው ነገርም ሥጋ አይደክመውም፡፡

አስተሳሰባችን ቅዱስ ከሆነ መልካም ጌታ ሆኗል ማለት ነው፡፡ ያሉን ነገሮች ሁሉም መልካም ሎሌዎች ይሆናሉ፡፡ ወታደር የራሱ ጠብ የለውም፡፡ራሱን ለማስከበር ጦር አያንቀሳቅስም፡፡
የመንግስቱ ጠብ የእርሱ ጠብ ነው፡፡ መንግስቱ የወደደውን ይቀበላል፡፡ አስተሳሰባችንም እንዲሁ ለአካላችን ለንብረታችን መንግስት ነው፡፡ አካላችን ንብረታችን ውስጣችን የገፋውን ይገፋል ፣ የተቀበለውንም ያገለግላል፡፡

ኒውክለር ቦንብ ለመስራት ኒውክለር ቦንቡን ማግኘት አይጠቅምም፡፡ ረቂቁን ፎርሙላ ግን ኒውክለር ቦንቡን ይሰራል፡፡ ረቂቁ የአለም መሰረት ፣ ረቂቁ የግዙፉ ነገር ገዢ ፣ ረቂቁ የታመቀ ሀይል ነው፡፡

መኖር የሚለካው ኖረን ካበቃን በኋላ አይደለም፡፡ የምንኖራት ሕይወት ምንነቷ የማይታወቅ ስንደርስ ብቻ እንድናውቃት ሆና የተዋቀረች አይደለችም፡፡ የምትለካ ሕይወትን ተቀብለናል፡፡ አውሮፕላን ማረፊያ ሔደን አንዱን መንገደኛ የት ነው የምትሔደው?? ብንለው:-"አላውቀውም ስደርስ ነው ማውቀው" ይለናል? በፍፁም አይለንም፡፡ መድረሻውን ካላወቀ መነሳት አይችልም፡፡ መድረሻውን የማያውቅ መንገደኛ ሳይሆን ተንከራታች ነው፡፡ መንገደኛ ሁሉ "የምሔደው እዚህ ሀገር ነው ፣ እግዚአብሔር ከፈቀደ በዚህ ሰዓት እደርሳለሁ" ብሎ ቦታውን ጠቅሶ ፣ ሰዓቱን ቆርጦ የሚናገር ነው፡፡ ሕይወት መንገድ ናት፡፡ የሕይወት መንገደኛም መድረሻውን ወይም ግቡን ወስኖ የሚናገር ነው፡፡ ወስኖ የሚያናግረንም ራዕይ ነው፡፡

ከቤት ስንወጣ የት እንደምንሔድ ወስነን ነው የምንወጣው ስለዚህ ጊዜአችንን ፣ ገንዘባችንን ፣ ጉልበታችንን ሳናባክን ካሰብንበት በቀላሉ እንደርሳለን የት እንደምንሔድ ሳንወስን ብንወጣ ግን በመንቀዋለል ሰዓቱ ያልቃል ፣ ገንዘብ ይባክናል ፣ ጉልበት ይዝላል፡፡ የት ልሒድ? ብሎ እንደመንቀዋለል የሚያስጨንቅ ነገር የለም፡፡ ራዕዬም ግቤም ይህ ነው ብለን የምናስቀምጠው መዳረሻ ነው፡፡በጉዞ፡መጀመሪያ ላይም አይታይም ጉዞአችንን በገፋን ቁጥር ግን የታየን ነገር መግዘፍ ይጀምራል፡፡

ይቀጥላል......

ከሁለተኛ መጽሐፍ አራተኛ ፅሁፍ

ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ

መልካም ሰዎች እንሁን እኛን አይተው ሌሎችም መልካም ይሆናሉና!

ቤታችን እንሁን እናንብብ!!!

* ምልክት ያለበት እኔው እንደጨመርኩት ልብ ይባልልኝ
@jahABP ነኝ
ማንኛውም አስተያየታችሁን አድርሱኘ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY &GRAPHIC DESIGN

ብዙም አትፈላሰፉ የውሃ ጠብታ በኮዳ ውስጥ ነው፡፡😜😜😜

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY &GRAPHIC DESIGN

WALLPAPER እዮባዬዬዬ😍😍🙏🙏😔😔

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY &GRAPHIC DESIGN

የስራ ተምሳሌቷ በስራ ላይ😱😱😍😍😍

ለማነሳት እንዴት እነደተቸገርኩ ብታቁ ሳለነደፍ አገኘኀት

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

አብይ ወንድሜ የምትፅፋቸው ነገሮች በጣም ደስ የሚሉ ናቸው፡፡ በኡነት ደስ ይላል ጎበዝ በርታ ያነበብከውን እያካፈልከን ስለሆነ እናመሰግናለን ያነበብነውን መርሳት የለብንም አንተም እንዳትረሳቸው ብሎ በጣም ማከብረው ሰው ከወደ አሜሪካ ለኢንተርኔትህ ይሆን ዘንድ ብታንስም ብሎ የካርድ ብር ልኮልኛል፡፡

ለተደረገልኘ ነገር በጣም በጣም አመስግኛለሁ እንዲህ አይነት ቀና ሰው ሲገኘ ፈጣሪ አብዝቶ እንዲሰጠው መፀለይ ነው፡፡ ወንድሜ ከልብ አመስግኛለሁ😊🙏 ይኸ ስጦታ እንድጠነክር ያግዘኛል ሳትሰለች ስራዎቼንና ፅሑፎቹን ስለምታነብ አስተያየትም ስለምትሰጠኘ ትልቅ የሆነውን ፍቅርና አክብሮቴን ልገልፅ እወዳለሁ😍🙏


ቀጣዩ ፖስት በስፖንሰር ሆነ ማለት ነው😜😜👍
AB PHOTOGRAPHY &GRAPHIC DESIGN

ይሔን ታሪካዊ ህንጣ ምናል እኸተማው ላይ ቢያንጡልን ጃል

50 ብር ቻሌንጅ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ወዴት ነህ?

በአሜሪካ አገር አንዲት ወጣት በደረሰባት የሞተር ሳይክል አደጋ እግሯን አጣች፡፡ እጅግ ውብ አስተዋይ የነበረችው እና በቤተሰቧ ትልቅ ተስፋ የተጣለባት ልጅ በዐሥራ ሰባት ዓመቷ የደረሰባትን ጉዳት ረስታ ትኖራለች ብሎ ማንም አልገመተም ነበር፡፡ ወደ በመንፈሳዊው ዓለም ያነቋት ቤተሰቦቿም ከእንባቸው ወጥተው የልጃቸውን ጉዳት ለእግዚአብሔር ክብር ይሆናል ብለው አልገመቱም ነበር፡፡ ያች ልጅ ግን ከጉዳቷ በፊት የሰማችው የእግዚአብሔር ፍቅር ሁሉን አስረሳት፡፡ ልጅነቷ እንዴት እንደሚሄዱ በሚጨነቁ ወጣቶች ቄንጥ የተሳበ ነበር፡፡ አሁን ግን ወዴት እንደምትሄድ ያለው ተስፋዋ ብቻ ቀረላት ፤ በማንጎራጎር ጉዳቷን መለወጥ እንደማትችል ገባት፡፡ የቀናት መለዋወጥ ፣ የሁኔታዎች መደፍረስ የማይቀንሰው በሸክላ ልቧ ውስጥ የተቀመጠው የእግዚአብሔር ፍቅር ለትልቅ ዓላማ ቀሰቀሳት፡፡

አንድ ቀን ሰዎች ልዩ ችሎታቸውን በሚያሳዩበት መድረክ ላይ እርሷም በድንገት ተነስታ ቆመች፡፡ ምን ታሳየናለች? ብለው ሲጠብቁ እርሷም ከሁሉም ስለሚበልጠውን ችሎታ መናገር ጀመረች፡፡ "ከሁሉ የሚበልጠው ችሎታ ምን እንደሆነ እንኳን አላውቅም ግን ይህን አጋጣሚ በመጠቀም አንድ ነገር ልነግራችሁ ፈለግሁ፡፡ በደረሰብኝ የሞተር ሳይክል አደጋ አንድ እግሬን ባጣም ዶክተሮች ለሰባት ወራት ባደረጉልኝ ልዩ እንክብካቤ ልተርፍ ችያለሁ፡፡

በዚህ እድሜዬ የተማርኩት አንድ ልዩ ችሎታ አለኝ፡፡ አደጋው በደረሰብኝ ጊዜ እምነቴ በይበልጥ እየጨመረ ሄደ፡፡ ብዙዎቻችሁ በነፃነት ስትራመዱ አያችኋለሁ፡፡ እኔም እንደ እናንተ ልራመድ ብችል ደስ ይለኝ ነበር ነገር ግን ሁኔታዎች ተቀይረዋል። ዋናው ነገር እንዴት እንደምትራመዱ ማወቅ አይደለም፡፡ ከማን ጋር እንደምትራመዱና ማን አብሯችሁ እንዳለ ማወቅ ነው፡፡

እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው ፤ አብሮኝ ይራመዳል ፣ ያወራኛል ፣ እኔም የእርሱ እንደሆንኩ ይነግረኛል፡፡ ወዴት እንደምትሄዱ ባወቃችሁ ጊዜ እግር ምንም ማለት እንዳልሆነ ትረዱታላችሁ" በማለት ስትናገር ሁሉም በእንባ ማዕበል ተመቱ። እንዴት እንደሚራመዱ የሚጨነቁ ሁሉም ወዴት እንደሚሄዱ ማሰብ ጀመሩ፡፡ "ትልቁን ችሎታ ተረዱ"፡፡

ዘመናዊነት ሁሉ እንዴት እንደምንራመድ የሚያግዝ ነው፡፡ ወዴት እንደምንሄድ የሚያሳውቀን ራዕይ ግን እየጠፋ ነው። እንዴት እንደሚራመዱ ይጨነቁ የነበሩ ዛሬ በትልቅ የሕይወት ኪሳራ ውስጥ ናቸው ፤ ደስታቸው ጊዜያዊ ፣ ዓለምን ያልጠገቡ ፣ ታሪክን ያልተመራመሩ ፣ አዲስ ግልብጦች ናቸው፡፡

ልጅ እንደ ልጅ ሲያስብ ወጉ ቢሆንም አዋቂ ግን እንደልጅ ሲያስብ ውርደቱ ነው፡፡ "ከአካሄድ ቄንጥ ያማረ ፍፃሜ የተሻለ ነው"፡፡ ትልቁ ችሎታ የአለባበስ ፣ የአነጋገር ፣ የአረማመድ ቄንጥ አይደለም፡፡ ትልቁ ችሎታ መድረሻን ተምኖ ጉዞን መጀመር ነው፡፡ ሰዎች ስለ ቁንጅና ፣ ስለ ልብስ ፣ ስለስፖርት ፣ *ስለዝሙት ለመናገር በሚጣደፉበት ዓለም ላይ ከጥበብ የሚበልጠውን ጥበብ ክርስቶስን እና ራዕይን የሚገልጥ ማን ይሆን? ዓላማውን አይቶ ዓላማን የሚያሳይ የታደለ ነው፡፡

መልካም ነገር እና እውነተኛ አኗኗር ዋጋ የረከሰበት በሚመስልበት በዚህ ዘመን ራዕይን ማስተማር ትውልድን እንደገና መፍጠር ነው፡፡ የተፈጠሩ ጫካዎች ለማረፊያነት ማስተካከልና ማስዋብ እንደገና መፍጠር እንደሆነ ሁሉ እንደ ሰው ተፈጥሮ እደሰው መኖር ያልቻለውን ፣ ለሆድ ደሞዝ ብቻ እንደ ውሻ የሚኖረውን ትውልድ ባለ ራዕይ ማድረግ ትልቅ አባትነት ነው፡፡ ዓላማን ለማወቅ ግን ሁልጊዜ ከጉዳት እና ከኪሳራ መማር አያስፈልገንም፡፡

የእግዚአብሔር ቀጥተኛ የማስተማሪያው ዘዴው ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ቢሆንም እግራችንን አጥተን እንኳን ዓላማን ማግኘት የተሻለ ነው፡፡ ከባለ እግር ይልቅ ባለ ራዕይ ያደርሳልና፡፡ እግር ማድረስ እንጂ መድረሻውን መወሰን የእርሱ ስልጣን አይደለም፡፡ ሎሌው እግር በመራን መራመድ ለአሽከር መገዛት ነው፡፡ ያሰብነው ጋር መራመድና ፣ የተራመድነበትን ማሰብ የተለያየ ነገር ነው፡፡ ያሰቡት ጋር መሄድ ባለ ራዕይነት ነው፡፡ የሄዱትን ማሰብ ግን መባነን ነው፡፡

የሕይወትን ሩጫ ያስጀመረ እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር የሕይወት ባለቤትም ነው፡፡ እውነተኛው የሕይወት መምህር እርሱ ነው፡፡ እርሱ በቃሉ የእርሱ መሆናችንን ነግሮናል። በሕይወት በረሃ አብሮን የሚጓዝ የምድር በዳ ጓደኛችን ነው፡፡

ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ ጥቂት ነገሮች ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን በኑሮ ውስጥ ብዙ ነገሮችን ያስተምረናል፡፡ የእርሱ ትምህርት በልብ እንጂ በጆሮ የምንሰማው ስላልሆነ ማስተዋል ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሔር በየዕለቱ እያስተማረ የክፉ ነገርን ዋጋ እየከፈለ ነው፡፡ ግን የሚያስተውል የለም፡፡ በሕይወት መንገድ ላይ እግዚአብሔር አብሮን አለ፡፡ እርሱ ይመራናል፡፡ መልካም ፍፃሜም ከእርሱ ነውና ይሰጠናል፡፡

እንዴት እንደምንሄድ ያለን ጭንቀት ሲያበቃ ወዴት እንደምንሄድ ማሰብ እንጀምራለን፡፡ ማድረግ የማንችለው ነገር ሲገጥመን ማድረግ የምንችለውን ማሰብ ትልቅ ነገር ነው።

ሰዎች ከሚተርኩልን ታሪክ ይልቅ መልካም ውሳኔያችን የበለጠ እርካታ አለው፡፡ ትልቁ ችሎታ ሕይወትን በራዕይ መምራት ነው፡፡ ለሚማር ሰው ሕይወት በትምህርት ቤቶች የተሞላች ናት፡፡ ከጉዳታችን ውስጥ ወደ መጎዳት የሚሄዱትን የሚመልስ ብርሃን ሊወጣ ይገባዋል፡፡

ሰዎች ወድቀው ይማሩ ማለት ትልቅ ጭካኔ ነው፡፡ በእኔ ይብቃ ማለት የዓለምን ስቃይ ይቀንሳል፡፡ ደስታችን የግላችን ሊሆን ይችላል ፣ መከራችን ግን የጋራ ነው፡፡ የሌላው ጉዳት በግድ ሳይነካን አይቀርምና መምከር ይገባናል፡፡ ሰው ስለገደልን ብቻ ሳይሆን ሲገደል ስላየንም በየፍርድ ቤቱ እንከረተታለን፡፡ በታወሰን ቁጥር እናዝናለን፡፡

ከጉዳታችን ስንማር፡- "ከደረሰብኝ ነገር የደረሰልኝ እግዚአብሔር ይበልጣል" ማለት እንጀምራለን፡፡ የላይ ችሎታዎቻችን ሲወሰዱ ፣ ሀብታችንና ጉልበታችን ሲያልቅ ፣ የውስጡ ሰውነታችን እየጠነከረ ይመጣል፡፡ መከራዎች መካሪ ሆነው ራዕይ ያስጨብጡናል፡፡ ተምሮ መቅረት ብቻ ሳይሆን ተምሮ ለተግባር መነሣትን ያድሉናል፡፡
ስለ እውነት የሚመጣ መከራ ዕውነተኛ ማንነትን ያጎናፅፈናል፡፡

ከጎኔ ያለው ማነው ማለት ተገቢ ነው። እግዚአብሔር ነው ብለን ለራሳችን መመለስ ከቻልን ሺህ ሠራዊት ከከበበን በላይ ድፍረት ይሰጠናል፡፡ እኔስ ከማን ጋር ነኝ? ማለት ትልቅ ምርምር ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር መሆናችንን ለራሳችን መናገር ከቻልን ራዕይ ይታየናል፡፡ ያየነውንም እንወርሳለን፡፡

★ ትልቁ ችሎታ የቀና አካሄድ ሳይሆን የቀና ፍፃሜ ነው፡፡

★ትልቁ ችሎታ የቁንጅና አሸናፊነት ሳይሆን የግብረገብ ውበት ነው፡፡

★ትልቁ ችሎታ የገመድ ዝላይ ፣ የጦር ውርወራ ሳይሆን ከእኔ የሚጠበቀው ምንድነው ማለት ነው፡፡

★ትልቁ ችሎታ ማስተማር ሳይሆን የተናገሩትን መኖር ነው፡፡

★ትልቁ ችሎታ ሌሎች ማጋለጥ ሳይሆን ራስን መመርመር ነው፡፡

★ትልቁ ችሎታ የሌሎችን ታሪክ መቁጠር ሳይሆን ታሪክ መሥራት ነው፡፡

ከሁለተኛ መፅሐፍ አምስተኛ ጽሁፍ
ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ

እናንብብ እንለወጥ ለሌሎች መለወጥ ምክንያት እንሁን!
@jahABP ነኝ ማንኛውም አስተያየታችሁን አድርሱኝ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY &GRAPHIC DESIGN

Feeling sad😔😔😢😢
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
በእያንዳንዷ ምሽት በፍፁም ለስላሳና ለጆሮ በሚስብ ድምፅ የሚጀመረው መዝሙር ወይም ቅዳሴ በየዋሻውና ቀየቋጥኙ ስር ፣ በየጥሻው ውስጥ ያለው በመቶሺህ የሚቆጠረው ሸካራው የወንዶች ድምፅ ይቀበልና ሲደግመው ፣ ከነሱ ተቀብሎ የገደል ማሚቶው በጣም ሩቅ ላሉት ሲያስተጋባው ፣ ይህ ነው ተብሎ መግለፅ የማይቻል ፍፁም ልብን የሚነካ ፣ ሰውነት የሚያንቀጠቅጥ ስሜት ይሰማል፡፡

የሀበሻ ጀብዱ፡- አዶልፍ ፓርስለሳክ
ተርጓሚ:- ተጫኔ ጆብሬ መኮንን
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD

VOICE BY @jahABP
AB PHOTOGRAPHY &GRAPHIC DESIGN

ምርጦች
እንኳን ለ1ሺህ አራት መቶ አርባ አንድደኛው
ኢድ አልፈር በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ
በዓሉን ስናከብር ፍፁም ጥንቃቄ በተሞላበት ይሁን!!
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD