AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
??????
ሰዎች ራዕያቸውን እንዲገነዘቡ ለመርዳት አንድ ምሳሌ ይነገራል፡፡
በአሁኗ ሰዓት ልክ እንደሞትን አድርገን ራሳችንን እንቁጠረው፡፡ የቀብር ሥርዓታችን ሊፈፀም የቀረው ጥቂት ሰዓት ነው፡፡ ባለጠጎች ሞትን በቅርበት ማሰብ አይፈልጉምና ራቅ ራቅ ብለው ቆመዋል፡፡ ቆንጆዎች የለቅሶ ፉሽን የሆነው ጥቁር ልብሳቸውን ለብሰው ፣ አስለቃሽ ሰዎች እንባቸውን ካስመጡት ለመገደብ በተጠንቀቅ መሐረብ ይዘዋል፡፡ ዋዘኞች እያለቀሱ የለቅሶ ቄንጥ ያወጣሉ፡፡ ወረኞች ለመንደሩ ሪፖርት ይዞ ለመመለስ እያንዳንዷን ነገር በጥንቃቄ ይመለከታሉ ጓዴ ጓዴ ምትለዋን የድሮ ሚስቱ ትሆን?... እያሉ የሰውን ልብ በወሬ ያጠፋሉ፡፡ ሊቃውንቱም፡- ስለ ሞታችን ሳይሆን ስለ አኗኗራችን ብላሽነት ያዝናሉ፡፡ ቤተሰቦቻችኝ የሚሆኑት ጠፍቷቸዋል፡፡
ስርዓተ ቀብራችን ተፈፅሞ ቀባሪው ወደ ዐውደ ምህረቱ ሰበሰብ ስራ የበዛባቸው ቀሳውስት ቆም ቆም እንዳሉ አንድ ሰው የህይወት ታሪካችንን ሊናገር ድምፁን ሞረደ ፣ ሁሉም ሰው ፀጥ ረጭ አለ፡፡ የራቀውም ለመስማት ቀረበ የህይወት ታሪካችን መናገር ጀመረ፡፡
ታዲያ በዚህ ሰዓት እንዲነገርልን የምንፈልገው የህይወት ታሪክ ምንድነው??
"ቅንነት የተሞላበት ፣ ሁሉን ወዳጅ የነበረ ፣ ለሙት ልጆች ወላጅ የሆነ ፣ *ለሰፈር ሰው ታዛዥ የነበረ ፣ ለሰው ችግር ቶሎ ደራሽ የነበረ ፣ በፍቅር የሚያምን ትህትና የሞላው ፣ ሰው ላይ ደርሶ የማያውቅ፡፡ ሁሉን በፍቅር የሚያሸንፍ ሀይማኖቱን ፣ ልጆቹንና ቤተሰቡን አክባሪ ፣ አክብሮም የሚያስከብር ፣ ሀገር ወዳድ ፣ ስራ ፈጣሪ ፣ ባለው ነገር ደስተኛ*.....ወይስ በተቃራኒው *ቲክቶክ ተጠቃሚ ነበር instagram ላይ ብዙ ተከታይ ነበረው ብዙ የዘመኑን ወጣት የሚስብ ብዙ ፎቶዎች ነበሩት.......እስኪ ምን ተብሎ እንዲነገርልን ነው የምንፈልገው ይኼን አስበነው እናውቃለን??.......በየትኛው ነው ህይወታችን እየሔደ ያለው??* የትኛው ነው እንዲነገርልን የምንፈልገው?????
ይህ ምሳሌ ራዕይን ለማግኘት የሁል ጊዜ መለኪያ አይደለም፡፡ ራዕዬ ምንድነው? ለሚለውና ጭልም ላለበት አእምሮ ትንሽ ብርሃን ይሰጣል፡፡ በቀብራችን ሰዓት ብቻ አይደለም በቁማችንም እንዲነገርልን የምንፈልገው መልካም ነገር አይደለምን?? መልካም ናቸው እንዲባልልን እንሻለን፡፡ ነገር ግን መልካም ናቸው ከመባል መልካም መስራት ይሻላል ፣ ይቀላል ያስደስታልም፡፡
ራዕይ ምንድነው? ራዕይ ያልሆነው አይተናል፡፡ ራዕይ የሆነው ምንድነው? ጠቅለል ባለ ቋንቋ ብንገልጠው ራዕይ ግብ ነው፡፡ ግብ ሁሉ ራዕይ ላይሆን ይችላል፡፡ የተጠበቀ ግብ ግን ራዕይ ነው፡፡ ያለ ራዕይ ብዙ ስኬቶች ሊመጡ ይችላሉ፡፡በኑሮ ውስጥ የሚሰጠን መኖር በቅቶኛል ብለን እንድንረካ የሚያደርገን ራዕይ ነው፡፡ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ "ሰው የሚፈልገውን ካየ የሚጠብቀው ሞቱን ነው" ይሉ ነበር፡፡ ሰው መኖር ከብዶት ምቱን ሊመን ይችላል፡፡ ረክቶና ሰማይ ናፍቆትም ሞቱን ሊመኝ ይችላል፡፡
መኖርና መሔድን ዋጋውን እኩል የሚያደርግልን ራዕይ ብቻ ነው፡፡ ሰው የሚኖርበት በቂ ምክንያት ከሌለው መኖሩ ጣፋጭ አይሆንለትም መኖርን ጣፋጭ ከሚያደርጉት አንዱ ራዕይ ነው፡፡ እውነተኛ ራዕይ ግብ አለው፡፡ ራዕይ ግብ ከሆነ ደርሰን የምናውቀው ሳይሆን በእምነት መነፅር አይተን የምንጓዘው ነው፡፡
በመጀመሪያው እና በመጨረሻው መካከል ብዙ ሸለቆዎች/ጉድለቶች/ ብዙ ተራራዎች (ተገዳዳሪዎች) ቢኖሩም ባለ ራዕዩ ግን ወዳየው ፍጻሜ ይገሰግሳል፡፡ የሰው ልጅ "መጨረሻዬን አሳምርልኝ" ብሎ ይፀልያል፡፡ መጨረሻችን ከሚያምርበት ነገር አንዱ ራዕይ ነው፡፡ ሰለሞን እንደ ገለጠው ከመጀመሪያው የመጨረሻው ይሻላል፡፡ የተሻለው መጨረሻ ግን በራዕይ ስንጓዝ ነው፡
አንድ ሰው መጨረሻዬ እንዲህ ነው ብሎ የወሰነው ነገር ራዕዩ ይሆናል፡፡ እኛም እንደ ውሳኔያችን ነን፡፡ የምንሆነው ያሰብነውን ነው፡፡ ውጫዊ ኑሮአችን የውስጣዊ ትራፊክ ነው፡፡ የሚታዩ ተግባሮቻችን የአስተሳሰባችን ውጤቶች ናቸው፡፡ ራሳችንን እንዳዘጋጀነው ነን፡፡ ብንፈልግ አስጨናቂ ሰዎች መሆን እንችላለን ብንፈልግ አሳራፊ ሰዎች መሆን እንችላለን፡፡ ብንፈልግ ብዙዎችን ለማጥፋት የሚችል ማንነት አለን፡፡ ብንፈልግ ብዙዎችን ለማዳን ኃይል ተሰቶናል፡፡ በአንድ ኦሳማን ቢላደን አለም ተጨንቋል ፣ በአንዲት እማሆይ ትሬዛ ብዙዎች ድነዋል፡፡
እግዚአብሔር የሰጠን ነገር አለ ፣ ነፃ ፈቃዱ ግን የእኛ ነው፡፡ የአስተሳሰብ ኃይል በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ሥር ካልዋለ የጥፋት ፎርሙላ ነው፡፡ ልብ የተባለው ግዙፉ ተፈጥሮ ሳይሆን የሰው የሕይወቱ ማዕከል የሆነው አስተሳሰቡ ነው፡፡ ምነጩ ከደፈረሰ ወራጁ እንደማይጠራ አስተሳሰቡ የተበላሸም ከተግባሩ አይፀዳም፡፡ ልብ በደከመት ነገር አካል ሳይሰራ እንደሚደክመው ሁሉ ልብ ደስ ባለው ነገርም ሥጋ አይደክመውም፡፡
አስተሳሰባችን ቅዱስ ከሆነ መልካም ጌታ ሆኗል ማለት ነው፡፡ ያሉን ነገሮች ሁሉም መልካም ሎሌዎች ይሆናሉ፡፡ ወታደር የራሱ ጠብ የለውም፡፡ራሱን ለማስከበር ጦር አያንቀሳቅስም፡፡
የመንግስቱ ጠብ የእርሱ ጠብ ነው፡፡ መንግስቱ የወደደውን ይቀበላል፡፡ አስተሳሰባችንም እንዲሁ ለአካላችን ለንብረታችን መንግስት ነው፡፡ አካላችን ንብረታችን ውስጣችን የገፋውን ይገፋል ፣ የተቀበለውንም ያገለግላል፡፡
ኒውክለር ቦንብ ለመስራት ኒውክለር ቦንቡን ማግኘት አይጠቅምም፡፡ ረቂቁን ፎርሙላ ግን ኒውክለር ቦንቡን ይሰራል፡፡ ረቂቁ የአለም መሰረት ፣ ረቂቁ የግዙፉ ነገር ገዢ ፣ ረቂቁ የታመቀ ሀይል ነው፡፡
መኖር የሚለካው ኖረን ካበቃን በኋላ አይደለም፡፡ የምንኖራት ሕይወት ምንነቷ የማይታወቅ ስንደርስ ብቻ እንድናውቃት ሆና የተዋቀረች አይደለችም፡፡ የምትለካ ሕይወትን ተቀብለናል፡፡ አውሮፕላን ማረፊያ ሔደን አንዱን መንገደኛ የት ነው የምትሔደው?? ብንለው:-"አላውቀውም ስደርስ ነው ማውቀው" ይለናል? በፍፁም አይለንም፡፡ መድረሻውን ካላወቀ መነሳት አይችልም፡፡ መድረሻውን የማያውቅ መንገደኛ ሳይሆን ተንከራታች ነው፡፡ መንገደኛ ሁሉ "የምሔደው እዚህ ሀገር ነው ፣ እግዚአብሔር ከፈቀደ በዚህ ሰዓት እደርሳለሁ" ብሎ ቦታውን ጠቅሶ ፣ ሰዓቱን ቆርጦ የሚናገር ነው፡፡ ሕይወት መንገድ ናት፡፡ የሕይወት መንገደኛም መድረሻውን ወይም ግቡን ወስኖ የሚናገር ነው፡፡ ወስኖ የሚያናግረንም ራዕይ ነው፡፡
ከቤት ስንወጣ የት እንደምንሔድ ወስነን ነው የምንወጣው ስለዚህ ጊዜአችንን ፣ ገንዘባችንን ፣ ጉልበታችንን ሳናባክን ካሰብንበት በቀላሉ እንደርሳለን የት እንደምንሔድ ሳንወስን ብንወጣ ግን በመንቀዋለል ሰዓቱ ያልቃል ፣ ገንዘብ ይባክናል ፣ ጉልበት ይዝላል፡፡ የት ልሒድ? ብሎ እንደመንቀዋለል የሚያስጨንቅ ነገር የለም፡፡ ራዕዬም ግቤም ይህ ነው ብለን የምናስቀምጠው መዳረሻ ነው፡፡በጉዞ፡መጀመሪያ ላይም አይታይም ጉዞአችንን በገፋን ቁጥር ግን የታየን ነገር መግዘፍ ይጀምራል፡፡
ይቀጥላል......
ከሁለተኛ መጽሐፍ አራተኛ ፅሁፍ
ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ
መልካም ሰዎች እንሁን እኛን አይተው ሌሎችም መልካም ይሆናሉና!
ቤታችን እንሁን እናንብብ!!!
* ምልክት ያለበት እኔው እንደጨመርኩት ልብ ይባልልኝ
@jahABP ነኝ
ማንኛውም አስተያየታችሁን አድርሱኘ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD

አብይ ወንድሜ የምትፅፋቸው ነገሮች በጣም ደስ የሚሉ ናቸው፡፡ በኡነት ደስ ይላል ጎበዝ በርታ ያነበብከውን እያካፈልከን ስለሆነ እናመሰግናለን ያነበብነውን መርሳት የለብንም አንተም እንዳትረሳቸው ብሎ በጣም ማከብረው ሰው ከወደ አሜሪካ ለኢንተርኔትህ ይሆን ዘንድ ብታንስም ብሎ የካርድ ብር ልኮልኛል፡፡
ለተደረገልኘ ነገር በጣም በጣም አመስግኛለሁ እንዲህ አይነት ቀና ሰው ሲገኘ ፈጣሪ አብዝቶ እንዲሰጠው መፀለይ ነው፡፡ ወንድሜ ከልብ አመስግኛለሁ😊🙏 ይኸ ስጦታ እንድጠነክር ያግዘኛል ሳትሰለች ስራዎቼንና ፅሑፎቹን ስለምታነብ አስተያየትም ስለምትሰጠኘ ትልቅ የሆነውን ፍቅርና አክብሮቴን ልገልፅ እወዳለሁ😍🙏
ቀጣዩ ፖስት በስፖንሰር ሆነ ማለት ነው😜😜👍

ወዴት ነህ?
በአሜሪካ አገር አንዲት ወጣት በደረሰባት የሞተር ሳይክል አደጋ እግሯን አጣች፡፡ እጅግ ውብ አስተዋይ የነበረችው እና በቤተሰቧ ትልቅ ተስፋ የተጣለባት ልጅ በዐሥራ ሰባት ዓመቷ የደረሰባትን ጉዳት ረስታ ትኖራለች ብሎ ማንም አልገመተም ነበር፡፡ ወደ በመንፈሳዊው ዓለም ያነቋት ቤተሰቦቿም ከእንባቸው ወጥተው የልጃቸውን ጉዳት ለእግዚአብሔር ክብር ይሆናል ብለው አልገመቱም ነበር፡፡ ያች ልጅ ግን ከጉዳቷ በፊት የሰማችው የእግዚአብሔር ፍቅር ሁሉን አስረሳት፡፡ ልጅነቷ እንዴት እንደሚሄዱ በሚጨነቁ ወጣቶች ቄንጥ የተሳበ ነበር፡፡ አሁን ግን ወዴት እንደምትሄድ ያለው ተስፋዋ ብቻ ቀረላት ፤ በማንጎራጎር ጉዳቷን መለወጥ እንደማትችል ገባት፡፡ የቀናት መለዋወጥ ፣ የሁኔታዎች መደፍረስ የማይቀንሰው በሸክላ ልቧ ውስጥ የተቀመጠው የእግዚአብሔር ፍቅር ለትልቅ ዓላማ ቀሰቀሳት፡፡
አንድ ቀን ሰዎች ልዩ ችሎታቸውን በሚያሳዩበት መድረክ ላይ እርሷም በድንገት ተነስታ ቆመች፡፡ ምን ታሳየናለች? ብለው ሲጠብቁ እርሷም ከሁሉም ስለሚበልጠውን ችሎታ መናገር ጀመረች፡፡ "ከሁሉ የሚበልጠው ችሎታ ምን እንደሆነ እንኳን አላውቅም ግን ይህን አጋጣሚ በመጠቀም አንድ ነገር ልነግራችሁ ፈለግሁ፡፡ በደረሰብኝ የሞተር ሳይክል አደጋ አንድ እግሬን ባጣም ዶክተሮች ለሰባት ወራት ባደረጉልኝ ልዩ እንክብካቤ ልተርፍ ችያለሁ፡፡
በዚህ እድሜዬ የተማርኩት አንድ ልዩ ችሎታ አለኝ፡፡ አደጋው በደረሰብኝ ጊዜ እምነቴ በይበልጥ እየጨመረ ሄደ፡፡ ብዙዎቻችሁ በነፃነት ስትራመዱ አያችኋለሁ፡፡ እኔም እንደ እናንተ ልራመድ ብችል ደስ ይለኝ ነበር ነገር ግን ሁኔታዎች ተቀይረዋል። ዋናው ነገር እንዴት እንደምትራመዱ ማወቅ አይደለም፡፡ ከማን ጋር እንደምትራመዱና ማን አብሯችሁ እንዳለ ማወቅ ነው፡፡
እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው ፤ አብሮኝ ይራመዳል ፣ ያወራኛል ፣ እኔም የእርሱ እንደሆንኩ ይነግረኛል፡፡ ወዴት እንደምትሄዱ ባወቃችሁ ጊዜ እግር ምንም ማለት እንዳልሆነ ትረዱታላችሁ" በማለት ስትናገር ሁሉም በእንባ ማዕበል ተመቱ። እንዴት እንደሚራመዱ የሚጨነቁ ሁሉም ወዴት እንደሚሄዱ ማሰብ ጀመሩ፡፡ "ትልቁን ችሎታ ተረዱ"፡፡
ዘመናዊነት ሁሉ እንዴት እንደምንራመድ የሚያግዝ ነው፡፡ ወዴት እንደምንሄድ የሚያሳውቀን ራዕይ ግን እየጠፋ ነው። እንዴት እንደሚራመዱ ይጨነቁ የነበሩ ዛሬ በትልቅ የሕይወት ኪሳራ ውስጥ ናቸው ፤ ደስታቸው ጊዜያዊ ፣ ዓለምን ያልጠገቡ ፣ ታሪክን ያልተመራመሩ ፣ አዲስ ግልብጦች ናቸው፡፡
ልጅ እንደ ልጅ ሲያስብ ወጉ ቢሆንም አዋቂ ግን እንደልጅ ሲያስብ ውርደቱ ነው፡፡ "ከአካሄድ ቄንጥ ያማረ ፍፃሜ የተሻለ ነው"፡፡ ትልቁ ችሎታ የአለባበስ ፣ የአነጋገር ፣ የአረማመድ ቄንጥ አይደለም፡፡ ትልቁ ችሎታ መድረሻን ተምኖ ጉዞን መጀመር ነው፡፡ ሰዎች ስለ ቁንጅና ፣ ስለ ልብስ ፣ ስለስፖርት ፣ *ስለዝሙት ለመናገር በሚጣደፉበት ዓለም ላይ ከጥበብ የሚበልጠውን ጥበብ ክርስቶስን እና ራዕይን የሚገልጥ ማን ይሆን? ዓላማውን አይቶ ዓላማን የሚያሳይ የታደለ ነው፡፡
መልካም ነገር እና እውነተኛ አኗኗር ዋጋ የረከሰበት በሚመስልበት በዚህ ዘመን ራዕይን ማስተማር ትውልድን እንደገና መፍጠር ነው፡፡ የተፈጠሩ ጫካዎች ለማረፊያነት ማስተካከልና ማስዋብ እንደገና መፍጠር እንደሆነ ሁሉ እንደ ሰው ተፈጥሮ እደሰው መኖር ያልቻለውን ፣ ለሆድ ደሞዝ ብቻ እንደ ውሻ የሚኖረውን ትውልድ ባለ ራዕይ ማድረግ ትልቅ አባትነት ነው፡፡ ዓላማን ለማወቅ ግን ሁልጊዜ ከጉዳት እና ከኪሳራ መማር አያስፈልገንም፡፡
የእግዚአብሔር ቀጥተኛ የማስተማሪያው ዘዴው ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ቢሆንም እግራችንን አጥተን እንኳን ዓላማን ማግኘት የተሻለ ነው፡፡ ከባለ እግር ይልቅ ባለ ራዕይ ያደርሳልና፡፡ እግር ማድረስ እንጂ መድረሻውን መወሰን የእርሱ ስልጣን አይደለም፡፡ ሎሌው እግር በመራን መራመድ ለአሽከር መገዛት ነው፡፡ ያሰብነው ጋር መራመድና ፣ የተራመድነበትን ማሰብ የተለያየ ነገር ነው፡፡ ያሰቡት ጋር መሄድ ባለ ራዕይነት ነው፡፡ የሄዱትን ማሰብ ግን መባነን ነው፡፡
የሕይወትን ሩጫ ያስጀመረ እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር የሕይወት ባለቤትም ነው፡፡ እውነተኛው የሕይወት መምህር እርሱ ነው፡፡ እርሱ በቃሉ የእርሱ መሆናችንን ነግሮናል። በሕይወት በረሃ አብሮን የሚጓዝ የምድር በዳ ጓደኛችን ነው፡፡
ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ ጥቂት ነገሮች ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን በኑሮ ውስጥ ብዙ ነገሮችን ያስተምረናል፡፡ የእርሱ ትምህርት በልብ እንጂ በጆሮ የምንሰማው ስላልሆነ ማስተዋል ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሔር በየዕለቱ እያስተማረ የክፉ ነገርን ዋጋ እየከፈለ ነው፡፡ ግን የሚያስተውል የለም፡፡ በሕይወት መንገድ ላይ እግዚአብሔር አብሮን አለ፡፡ እርሱ ይመራናል፡፡ መልካም ፍፃሜም ከእርሱ ነውና ይሰጠናል፡፡
እንዴት እንደምንሄድ ያለን ጭንቀት ሲያበቃ ወዴት እንደምንሄድ ማሰብ እንጀምራለን፡፡ ማድረግ የማንችለው ነገር ሲገጥመን ማድረግ የምንችለውን ማሰብ ትልቅ ነገር ነው።
ሰዎች ከሚተርኩልን ታሪክ ይልቅ መልካም ውሳኔያችን የበለጠ እርካታ አለው፡፡ ትልቁ ችሎታ ሕይወትን በራዕይ መምራት ነው፡፡ ለሚማር ሰው ሕይወት በትምህርት ቤቶች የተሞላች ናት፡፡ ከጉዳታችን ውስጥ ወደ መጎዳት የሚሄዱትን የሚመልስ ብርሃን ሊወጣ ይገባዋል፡፡
ሰዎች ወድቀው ይማሩ ማለት ትልቅ ጭካኔ ነው፡፡ በእኔ ይብቃ ማለት የዓለምን ስቃይ ይቀንሳል፡፡ ደስታችን የግላችን ሊሆን ይችላል ፣ መከራችን ግን የጋራ ነው፡፡ የሌላው ጉዳት በግድ ሳይነካን አይቀርምና መምከር ይገባናል፡፡ ሰው ስለገደልን ብቻ ሳይሆን ሲገደል ስላየንም በየፍርድ ቤቱ እንከረተታለን፡፡ በታወሰን ቁጥር እናዝናለን፡፡
ከጉዳታችን ስንማር፡- "ከደረሰብኝ ነገር የደረሰልኝ እግዚአብሔር ይበልጣል" ማለት እንጀምራለን፡፡ የላይ ችሎታዎቻችን ሲወሰዱ ፣ ሀብታችንና ጉልበታችን ሲያልቅ ፣ የውስጡ ሰውነታችን እየጠነከረ ይመጣል፡፡ መከራዎች መካሪ ሆነው ራዕይ ያስጨብጡናል፡፡ ተምሮ መቅረት ብቻ ሳይሆን ተምሮ ለተግባር መነሣትን ያድሉናል፡፡
ስለ እውነት የሚመጣ መከራ ዕውነተኛ ማንነትን ያጎናፅፈናል፡፡
ከጎኔ ያለው ማነው ማለት ተገቢ ነው። እግዚአብሔር ነው ብለን ለራሳችን መመለስ ከቻልን ሺህ ሠራዊት ከከበበን በላይ ድፍረት ይሰጠናል፡፡ እኔስ ከማን ጋር ነኝ? ማለት ትልቅ ምርምር ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር መሆናችንን ለራሳችን መናገር ከቻልን ራዕይ ይታየናል፡፡ ያየነውንም እንወርሳለን፡፡
★ ትልቁ ችሎታ የቀና አካሄድ ሳይሆን የቀና ፍፃሜ ነው፡፡
★ትልቁ ችሎታ የቁንጅና አሸናፊነት ሳይሆን የግብረገብ ውበት ነው፡፡
★ትልቁ ችሎታ የገመድ ዝላይ ፣ የጦር ውርወራ ሳይሆን ከእኔ የሚጠበቀው ምንድነው ማለት ነው፡፡
★ትልቁ ችሎታ ማስተማር ሳይሆን የተናገሩትን መኖር ነው፡፡
★ትልቁ ችሎታ ሌሎች ማጋለጥ ሳይሆን ራስን መመርመር ነው፡፡
★ትልቁ ችሎታ የሌሎችን ታሪክ መቁጠር ሳይሆን ታሪክ መሥራት ነው፡፡
ከሁለተኛ መፅሐፍ አምስተኛ ጽሁፍ
ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ
እናንብብ እንለወጥ ለሌሎች መለወጥ ምክንያት እንሁን!
@jahABP ነኝ ማንኛውም አስተያየታችሁን አድርሱኝ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD

በእያንዳንዷ ምሽት በፍፁም ለስላሳና ለጆሮ በሚስብ ድምፅ የሚጀመረው መዝሙር ወይም ቅዳሴ በየዋሻውና ቀየቋጥኙ ስር ፣ በየጥሻው ውስጥ ያለው በመቶሺህ የሚቆጠረው ሸካራው የወንዶች ድምፅ ይቀበልና ሲደግመው ፣ ከነሱ ተቀብሎ የገደል ማሚቶው በጣም ሩቅ ላሉት ሲያስተጋባው ፣ ይህ ነው ተብሎ መግለፅ የማይቻል ፍፁም ልብን የሚነካ ፣ ሰውነት የሚያንቀጠቅጥ ስሜት ይሰማል፡፡
የሀበሻ ጀብዱ፡- አዶልፍ ፓርስለሳክ
ተርጓሚ:- ተጫኔ ጆብሬ መኮንን
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
VOICE BY @jahABP
የሀበሻ ጀብዱ፡- አዶልፍ ፓርስለሳክ
ተርጓሚ:- ተጫኔ ጆብሬ መኮንን
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
VOICE BY @jahABP
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
✝ ቻይ እና ትዕግስተኛ የሆነ ሰው ይጸልያል ስለሚሰጠውም የእግዚአብሔር መልስ አይጨነቅም ።
እግዚአብሔር ጸሎቱን እንደሚሰማው እርግጠኛ ነው ። ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ጥበብና ፈቃድ እንደሚሆን በተገቢው ጊዜና መንገድ መልስ እንደሚሰጠው በማመን ለእግዚአብሔር ፍቅር ይተዋል ። አንዳንድ ሰዎች ይህ መሰል ትዕግሥት የላቸውም ።
እግዚአብሔርን መውቀስ እና ከእርሱ ስሕተት መፈለግ እንጂ መጠባበቅ አይችሉም ። እርሱን ይወነጅሉታል እርሱ ግን እጅግ ይታገሳቸዋል ወቀሳቸውንም ይሸከማል ። እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔር ለእነርሱ እንደሚሰራ ማመን አለባቸው ።
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

አንድ ልምድ አለኘ ይቅርታ ግን ይህ የኔ ልምድ ነው ለብዙ ሰው ላይመች ይችላል👊👊...ሊመችም ይችላል 😍🙏ብቻ አላቅም🤷♂
ምን መሰላችሁ አዲስ ነገር በጣም ደስ ይለኛል፡፡
😃እና አዲስ ሰው ስተዋወቅ በተለይ ውይይት ከሆነ በሆነ አጋጣሚ ክርክር ከተነሳ አብሶ እኔ ስለማላቀው አዲስ ነገር ከሆነ🕺🕺....ደስታዬ ነው፡፡ ለነገሩ የማቀውም ነገር ቢሆን ከኔ የተሻለ ዕውቀት አላቸው ብዬ ካሰብኩ ያን ማድረጌ አይቀርም፡፡ ቲያትር እና ፊልሞች ሳይስ ብትሉ አይፋታኘም እኮ.....😂😂ለማየት ነው ለመፃፍ ምገባው አትሉኘም😝
ይህ ልምዴ ምን መሰላችሁ ከሰው ጋር ያወራነውን ቶሎ ብሎ መፃፍ ነው እና voice record ማድረግ ነው፡፡😂😜👊
የሆነ ሰዓት ላይ በምን እንደሆን አላቅም ድብር ሲለኘ ወይ ስለዛ ስላወራነው ነገር ደግሜ ሳስብ ወይም ማወቅ ስፈልግ ለሰው መናገር ስፈልግ ማስታወስ ካለብኘ ወደፃፍኩበት ማስታወሻ ስልኬ ላይ ሊሆን ይችላል ወይም openvoice🏃♂🏃♂........እናም ደጋግሜ እሰማዋለሁ record እንኳን ባላደርግ ደጋግሜ አነበዋለሁ አስበዋለሁ፡፡
ህግ ይፈቅዳል?? እኔንጃ አላቅም ብቻ እኔን ጠቅሞኛል ጥሩ ስለሆነም ሌሎችን ለማስተማር እጠቀምበታለሁ በመሐልም ሚጎዳ ያለ አይመስለኘም፡፡የህግ ሰዎች🙈🙈🙊🙊ምን ትላላቹ??
እናም ሁለተኛውን መፅሐፍ ከመጨረሳችን በፊት ከነዚህ አንዱን ላጋራቹ ወደድኩ...ኤጭ አበዛኸው እንዳትሉኘ፡፡😔😔🙏🙏
አንድ የሰፈራችን አብሮ አደጋችን ሰርግ👫 💑 ላይ በነገራችን ላይ ሶስት ሰርጎች በክብር የተጠራሁ ሰው ነኘ🤟🤘📱✉️✉️ከራሳቸው ከሙሽሮች፡፡ እና እዛ ሰርግ ላይ ሱፌን ለብሼ ዝንጥ ብዬ ሔድኩላችሁ🎀፡፡
ያው በሀገራችን ሙሽራ....ማርፈድ ልማዱ አይደል እስኪመጣ ብለን አንድ ሁለት🍻🍺🍻 ልንል እዛው በነበረ የቀበሌ መዝናኛ ጎራ አልን በነገራችን ላይ የመጠጥ አድናቂ አይደለሁም ግን ያው ወጣት አደለሁ እጠጣለሁ፡፡ወጣት ሁሉ ግን ይጠጣል ማለቴ አይደለም🙏
ከዛ ቁጭ ብለን እየጠጣን አጠገባችን ካለ በሌላ ጠረቤዛ ላይ የተቀመጠ ወጣት ልጅ እናንተ ሰዎች ትገርሙኛላችሁ ብሎ ወሬውን ጀመረ፡፡ ሳናውቀው ከማንአጠገብ ነው የተቀመጥነው ደሞ😳🤔 እናንተ ሰዎች😂😂 ሃሃሃሃሂሂሂሂ ምን ማለት ነው፡፡ ምንስ ለማለት ፈልጎ ነው እሱ ምንድንነው??🤔 ይሔንማ በደንብ፡ማወቅ አለብኘ ተገኘቶ ነው፡፡
ሰርገኞች በናታቹ ቆዩ ስል በልቤ ተመኘሁ ታዲያ እኔስ ምኔ ሞኘ ነው voice record ክፍት ወንበሬን ስቤ ምን ለማለት ፈልገህ ነው ብዬ ወሬውን ጀመርኩ ......ምን አለኘ ምን አወራን😃🤔🤔ነገ ነገ
ነገ እጨርስላችኀለው፡፡ ዝናብ እየመጣ🏃♂ነው፡፡ እደሩልኘ😍🙏
አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኘ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD