Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
AB POHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

የሚመስል ነገር

የሰው እድሜን በከንቱ የሚጨርስ ፣ ብልጥ ነኝ ብሎ የሚያስበውን ሳይቀር የሚያታልል ፣ አለሁ አለሁ፦እያለ የማይኖር ፣ መጣሁ መጣሁ እያለ የሚቀር ፣ ዝናብ የሌለው ደመና ፣ የሚያስፈራራ የጉም ጋሬጣ ፣ የማይቆይ የአመዳይ ምንጣፍ ቢኖር የሚመስል ነገር ነው፡፡

ፀሀይን የሚጋርዱ ፣ የነጋዴውን ምንጣፍ የሚያሳጥፉ ፣ ገበያተኛውን የሚበትኑ ፣ የደመቀውን ጭር የሚያደርጉ የረጋውን ግብይት የሚደባልቁ መንገደኛውን በማስቸኮል ልቡን የሚያስደልቁ ፣ ውሃ የተጠማውን የሚያጓጉ ፣ ታይተው የሚጠፉ ፣ ድምፅ አሰምተው የሚሞቱ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች አሉ፡፡

ሳይዘንቡ ፀሐይን የሚከልሉ ፣ ላያርሱ ጨለማ የሚያለብሱ ፣ ላይደርሱ የቀረበውን የሚያርቁ ፣ ላይወርዱ የተዘረጋውን የሚያጥፉ ፣ ቀስ ብሎ የሚያርሰውን የሚያስጋልቡ ፣ መጣሁ እያሉ የሚቀሩ ፣ የተጠማውን መቅጃ የማይሞሉ ፣ የተማመነባቸውን የሚያሳፍሩ ፣ ቀጠሮ አስይዘው የማይገኙ ፣ ብዙ በሽተኞችን አሳምመው ፣ ስሜትን አጨፍግገው በመዝነብ ያረኩናል ሲባሉ በሩቁ ታይተው የሚቀሩ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች አሉ፡፡ ከጥቁረታቸው ማስፈራራት የተነሳ ሁሉን ትተው ሲጠብቋቸው የሚቀሩ ፣ ፎክረው ሳይዘንቡ የሚመለሱ ፣ ነፋስ የሚበትናቸው ውስጠ ባዶ ደመናዎች አሉ፡፡ የሚመስል ነገር ዝናብ የሌለው ደመና ነው፡፡

በጋውን ክረምት የሚያስመስሉ ፣ በብርሃን መካከል ገብተው የሚያጨልሙ ፣ ሰላማዊ ግብይትን የሚያደፈርሱ ፣ በግርግራቸው ብዙ ንብረት የሚዘርፉ ፣ ዝናብ የሌላቸው ባለራዕዮች አሉ፡፡ ሲያንዣብቡ በረከት ያዘሉ የሚመስሉ ፣ ሲጠቋቁሩ የሚያረኩ የሚመስሉ ፣ ጥቁረታቸውን ታግሶ ዝናብ ለጠበቀባቸው እልም ብለው የሚቀሩ ባለዕራይዎች አሉ፡፡

ፈጣንነታቸውና ፣ ቡድን አሳዳሚነታቸውን ታግሰን መልካም ነገር ይወጣቸዋል ስንል ተስፋችንን አሳፍፈው የሚመልሱ ዛሬም አሉ፡፡ እንደእባብ እየተለሳለሱ አካልን እየዳሰሱ የሚነድፉ ፣ እያሰከሩ የሚሰርቁ ፣ እያደነዘዙ የሚያራግፉ ፣ የመንጋውን ልብ በቅብ ፍቅር የሚያሸፍቱ ዛሬም አሉ፡፡

ጭር ሲል የማይወዱ ፣ ማስመሰል አገልግሎቴ ፣ መበጥበጥ ራዕዬ ያሉ ፣ ያነደዱት እሳት ሌላው ሲያቃጥል እነርሱ ለመሞቅ የሚሹ ፣ ይህንንም አገልግሎት ብለው የያዙ ብዙዎች ናቸው፡፡ ከባል የሚያፋቱ ውሽሞች ፣ ከበግ ጋር የተሰማሩ ተኩላዎች ፣ በበግ እርምጃ እየተራመዱ ራሳቸውን የሚሰውሩ ፣ ሥጋ በል ሳሉ ለዓላማቸው ሣር ለመብላት የጨከኑ ፣ የእረኛው ልብ ከወደቀላቸው በኋላ ምልመላ የሚጀምሩ ፣ ባለራዕዩ እስኪጠላ በሌሊት ሳይቀር መንጋው የሚጎበኙ ፣ መንጋውን ከእረኛው ከለዩ በኋላ ትተው የሚሰወሩ ፣ ነገር ግን ባለ ራዕይ የሆኑ የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው፡፡

ከራዕይ እንቅፋቶች አንዱ የሚመስል ነገር ነው፡፡

የዘመናችን ሰው እውነተኛ ለመሆን አሳብ እንኳን የሌለው ራሱን በሚመስል ነገር አስሮ የሚኖር ነው፡፡ መልካም ተግባርን በጥሩ ንግግር ተክቶ የሚናገር ከእውነተኛም ጋርም ላለመገናኘት ተጠንቅቆ የሚጓዝ ነው፡፡ እውነት ያልሆኑ ፣ ነገር ግን እውነት እንዲመስሉ የተለፋባቸው ሐሰቶች በዝተዋል፡፡ እውነተኝነትን ደረቅነት ፣ አስመሳይነት ዘመናይነት የሆነበት ዘመን ነው፡፡

"እብድ እውነት ይናገራል" እያልን የጤነኝነት መገለጫው ውሸት ሐሰት መሆኑን ያመንበት ይመስላል፡፡ እኛን የማይገልጡ ቃሎችና አለባበሶች ተግባራችንን ለመሸፈን ብናውላቸውም መሸፈኛዎች ሁሉ የመሸፈን አቅም አጥተዋል፡፡ ጊዜውም ከዋሸህ ከተነቃብህ ጨምርበት ፣ ብዙኃን የተስማማበት ሐሰት ከእውነት ይቆጠራል የሚል ነው፡፡ የዚህ የማስመሰል አብዮት አራማጆች ብዙዎቹ የኃይማኖት ሰዎች ናቸው፡፡

እነዚህ በገንዘብና በሆዳቸው ፍቅር የሰከሩ ሲሆኑ መንገድ በማሳት የአገር መሪዎችን እንኳን ሲያስቱ የሚታዩ ናቸው፡፡ ዘወትር በውዳሴ ከንቱና በመወዳደስ ሕይወት ስለሚኖሩ ብርሃኑ ጨለማ ፣ ጨለማውን ብርሃን በማለት ምድሪቱን በብሩቱ ስቃይ ሲወጓት እየተመለከትን ነው፡፡

በሚመስል ነገር መያዝ ብርቱ እስር ቤት ነው፡፡ በሲኦል ውስጥ ከሚገኙ ዘጠና ዘጠኝ በመቶ የሚሆኑት ነፍሶች በሚመስል ነገር ተይዘው ዕድሜያቸውን ያባከኑ ብዙዎቹ በሃይማኖት ካባ ተደብቀው እራሳቸውን ያታልላሉ፡፡ በሕሊናቸው ፊት ሳይሆን በሰው ፊት እውነተኛ ለመሆን ይጥራሉ፡፡ ውሸታምን ያደናቀፈ ዕድሜ የለውምና እነዚህ ሰዎች ውሸታቸውን የነካባቸውን እንደ እርግጠኛ ጠላታቸው በማየት ለማጥፋት እንኳን ወደኋላ አይሉም፡፡

ሌባ ብርሃን አይወድምና የፈጣሪን ቃል ሲሰሙ ይበሳጫሉ፡፡ሰባኪውን ስም ይሰጡታል፡፡ ቅዱስ የሚሏቸውን የራሳቸውን መምህራን ያከማቻሉ፡፡ በአገር ደረጃም አገር እወዳለሁ እያሉ ህዝብን የሚፈጁ ፣ የወደቀ ዜጋ አልፈው እየሔዱ ሰውዬውን የወከለውን ባንዲራ የሚስሙ ብዙ ግለሰቦች አሉ፡፡

በራዕይ ውስጥ በሚመስል ነገር የተያዙ አያሌ ናቸው፡፡ ራዕይ ማለት ቶሎ ቶሎ መራመድ በተወጠረ ስሜት መስራት ትንፋሽ ለመዋጥ ጊዜ ማጣት የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው፡፡
እነዚህ ሰዎች ራዕይን ለመገምገም ፣ ትርፍና ኪሳራቸውን ለመመልከት ጊዜ የላቸውም፡፡ የሚያባክኑት ኃይል እውነተኞቹ ባለ ራዕዮች የሚያወጡት ሃይል በመሆኑ ያለ ዋጋ እንዳይቀሩ ቆም ቢሉ መልካም ነው፡፡

"ለስሟ ማስጠሪያ ቁና ሰፋች" እንደሚባለው አንዷን ተግባር ለዘለዓለም የሚያወሩ ለመጣ ለሔደው ያችኑ የሚደጋግሙ ከመጠን በላይ አጋነው የሚያወሩ ፣ የሰውን ቀልብ መሳብ ሥራቸው ያደረጉ ሰዎች በሚመስል ነገር የተያዙ ናቸው፡፡ በራዕያችን የምንሰራው የሰራን በማይመስለን ጊዜ ነው፡፡

እንደሰራን ካሰብን ቆመናል ማለት ነው፡፡ የሚሰራ በሰራው ረክቶ አይቀመጥም፡፡ የሚሰራ አይረካም፡፡ ሌሎችም ገድላቸው ተፅፎ እንዲኖር ታሪካቸው በወርቅ ቀለም እንዲሰፍር ይፈልጋሉ፡፡ ለዛሬ ትውልድ ጠቃሚ ሳይሆኑ ለሚቀጥለው ትውልድ ታሪክ ለመሆን ይጨነቃሉ፡፡ ብዙ ነገስታት መሳፍንታት ፣ እንኳን ኖረው ሞተው እንኳን ደምቀው እንዲታዩ ብዙ ለፍተዋል፡፡ ዛሬ ግን ከመደነቅ ይወቀሳሉ፡፡ ሁሉም ነገር እኛ እንዳሰብነው አይሆንም፡፡

ዛሬን ጠቃሚ ሰው ሆነን ለመዋል መጣር ብቻ ህሊናን ነፃ ያደርገዋል፡፡

በራዕይ ውስጥ ትዕግስት ከሚመስል ስንፍና ፣ ትጋት ከሚመስል መክነፍ መጠንቀቅ ይገባል፡፡

እናስተውል.....

★ ትዕቢተኛ የራሱን ትልቅነት የሚቀበለው የሌሎችን ትንሽነት በማመን ነው፡፡

★የሚያስፈራውን አምላክ ካልፈራን ፈሪ የሆኑትን የሰው ልጆች መፍራታችን አይቀርም፡፡

★ እግዚአብሔር ከችሎታችን ጋር ሳይሆን ከእሺታችን ጋር ኅብረት አለው፡፡

★ ምንም እንሁን ባለንበት ሁኔታ እግዚአብሔር ጠቃሚ ሊያደርገን ይችላል፡፡

★እኛም ፍፁም አለመሆናችን መረዳት ለፍፁምነት መነሻ ትልቅ መልስ ነው፡፡

★ የምንችለውን ማድረግ የማንችለውን ወደ ማድረግ አቅም ይመራናል፡፡

★ ሥር ያልሰደዱ ሁሉ ቢያምሩም በውበታቸው አይቆዩም፡፡

★ ራዕይ እየገፋ እንጂ እየጠፋ አይመጣም፡፡

★ ራዕይ እኛ ብናልፍም የሚቀጥል እንጂ ከእኛ ጋር የሚያልፍ አይደለም፡፡

ከሁለተኛ መጽሐፍ ስድስተኛ ፅሁፍ


ቤታችን እንሁን እና ንብብ
ለመልካም ነገር የፈጠንን እንሁን


ለአስተያየታችሁ @jahABP ነኝ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN




ውቢቷ ሐዋሳ ላይ እንደመጥለቅ
😍😘😘
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

😊እንዴት ዋላችሁ😍

"ትውልድን ለመታደግ ሁላችንም ግዴታ አለብን::
ምናልባት ለእኛ መለወጥ የደከመልን ላይኖር ይችል ይሆናል፡፡ ፈጣሪንና እራሳችንን ካወቅን ግን ያልተቀበልነውን ለመስጠት መነሳሳት አለብን፡፡ ሰው ወደመልካም ነገር እንዲመጣ ወደ መጥፎ የሚሔደውን መጀመሪያ ማስቆም አለብን፡፡ ወደ መጥፎ የሚሔደውን ካስቆምን በጥፋት ስፍራ ያለው ይለወጣል፡፡በሸለቆ ውስጥ የወደቀ ሰው አለ፡፡ ወደ ሸለቆው የሚወርደው ሰው ከበዛ ለመውጣት መንገዱ ዝግ ነው፡፡ ስለዚሁም ወደ ጥፋት የሚያወርደው መጀመሪያ መገደብ አለብን፡፡ አሊያ ይህ ትውልድ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ዕጣ ያሳስባል፡፡

ወንጀልም በሕግ ከለላ ያገኛል፡፡
ነውሩም ክብር ሆኖ ይፀድቃል፡፡

ትውልዳችን ስናይ የምናስተውላቸው ችግሮች አሉ፡፡ ችግሮቹን የምንጠቅሰው ያለፈውን መልካም ጊዜ ለማወደስ ዛሬን ለመርገም ሳይሆን የተሻለ ቀን ለማየት ነው፡፡ በዚህ ችግር የሚያልፉ ቆም ብለው እንዲያስቡ ፣ ትውልድን ለመታደግ አሳብ ላላቸው ችግሩን እንዲያዩ ለማድረግ ነው፡፡

ትውልዳችን እነዚህ ችግሮች አሉበት ይላል" ፡-

ምን ምን ከሁለተኛ መፅሐፍ ሰባተኛ ፅሁፍ ይቀጥላል፡፡

እኔ ይሔን ፅሁፍ ሳነብ ሁሌም እራሴን ከበኩርኩም እንደተመታ ኩም እላለሁ፡፡
የዚህ ትውልድ አካል ነኘና ችግሮቹ በእኔም ህይወት ላይ አሉ ሁሌም እሩጫዬ ከነዚህ ፍላፃዎች እራሴን ማውጣት ነው፡፡ ከዛ ሌሎችንም ለዛም ነው ላካፍላችሁ የወደድኩት፡፡


ሁላችንም ይህንን ፅሁፍ ማንበብ አለብን ከዛ እራሳችንንም ቆም ብለን መመልከት እራሳችንን መለወጥ ከዛ ሌሎች እንዲለወጡ ምክንያት መሆን፡፡

እንቀጥላለን🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

ቆዩልኘ፡፡
@jahABP ነኘ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ትውልዳችን፡-

1) መዳረሻውን ያላየ ነው

ከትውልዳችን አብዛኛውን የመጨረሻ ግቡ ገንዘብ ማግኘት ወይም ዝነኛ መሆን ነው፡፡ እነዚህ ነገሮች የተጠሉና የማያስፈልጉም ባይሆኑም ራዕይ ግን አይደሉም፡፡ ትውልዳችን የተሻለ ኑሮ እፈልጋለሁ ይላል ፣ ለእርሱ የተሻለው ቤትና መኪና ነው፡፡ ሰውን ለሚያህል ትልቅ ፍጡር ግን እነዚህ ቁሳቁሶች ግብ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ መንገዳችን ላይ ከምናገኛቸው በረከቶች ውስጥ ይመደባሉ። ግባችን ግን ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ሰው ከበሬ ለተሻለ ነገር መኖር አለበት፡፡ በሬ ቀኑን በሙሉ ላቡን ጠብ አድርጎ ይሰራል ፤ እኛም እንሰራለን ፤ በሬ ከስራ መልስ ላም አለችው እኛም ትዳር አለን፡፡ በሬ ጥጆች አሉት እኛም ልጆች አሉን፡፡ ከዚህ ያለፈ ነገር ከሌለን እየኖርን ያለነው እንደ በሬ ነው ለማለት ነው፡፡ ስለዚህ ደስተኛ ባንሆን ምን ይደንቃል፡፡

ወደላቀው የኑሮ ደረጃ ፣ እግዚአብሔር ወዳየልን ከፍታ መድረስ አለብን፡፡ እርሱም በራዕይ መገለጥ ነው፡፡ ከሕይወት ጥያቄዎች አንዱ "ወዴት ነው የምሄደው?" የሚል ነው፡፡ ሰው መዳረሻውን ካላወቀ በኑሮው ድፍረት አይሰማውም፡፡

ትውልዳችን ላይ በአብዛኛው የምናየው ለዛሬ መሙላት ብቻ መኖር ፣ ለራስ ብቻም ማሰብ ፣ ሁሉንም ሰው የጥቅሙ ገባር አድርጎ መፈለግን ነው፡፡ ለወገኔ የሚል ስሜቱ እየተሟጠጠ ነው፡፡ ለዚህ ትልቁ ችግር በእግዚአብሔር የለሽ አስተሳሰብ መበከሉ ነው፡፡ ፈጣሪ የለሽ ሥርዓት ከአደባባይ ቢወድቅም ከሰው ልብ ግን አልወደቀም፡፡

በየትምህርት ቤቱ ይሰጡ የነበሩ የግብረ ገብ ትምህርቶች በአዋጅ መከልከላቸው ከዚያ በኋላ ያተረፍነው ትውልድ ብኩን ትውልድ ነው፡፡ ትዕግስት የጎደለው ፣ ራዕይ አልባ ፣ መረን ትውልድ ለማፍራት ተገደናል፡፡

2) ውለታቢስነት ተቆራኝቶታል

አይሁዶች:- "ተቀብሎ የማያመሰግን ከቀማኛ ይቆጠራል" ይላሉ አብዛኛው ትውልዳችን ከእግዚአብሔር ፣ ከቤተሰቡ ፣ ከሀገሩ ከመምህራኖቹ ተቀብሎ ፣ እንደ ጩልፊት ነጥቆ የሚሮጥ እንጂ ለምስጋና የሚመለስ አይደለም፡፡ ውለታቢስነት ተቆራኝቶታል፡፡

ሰዎች እንዲያደርጉለት እንጂ እርሱ ለማንም በጎ ለማድረግ አይሻም፡፡ የሚያስፈልገውን ነገር ያደረጉለትን ሰዎች እንደሞኝ ያያል እንጂ ፍቅራቸውን እንኳን መረዳት አይሆንለትም፡፡ ሁሉንም ሰው ወላጆቹን እንኳን ሳይቀር ለጥቅሙ መሟላት ያፈላልጋል፡፡ ጥቅሙን የሚያሟላለት ከመሰለው ምንም ከመሆን ፣ ከመጣመር ወደኋላ አይልም፡፡

ፍላጎቱ ጣዖት ሆኖበታል፡፡ ጥቅሙን የሚያሟሉለት ከሆነ የራሱን ሰዎች እንኳን ይጠላል፡፡ አንዳንዴም ይተናኮላል፡፡ ያስተማረችውን አገሩን ለማገልገል አይፈልግም፡፡
ሁሉም ነገር ተመቻችቶለት መቀመጥ እንጂ ተግዳሮትን በፍጹም አይፈልግም፡፡ ቀለል ያለውን በመምረጥ ሲጓዝ ቀለል ያለ መስሎ የሚገኝለት ሱስና ሀጢያት ሆኖ ይቀዘፋል፡፡

ትውልዳችን አብዛኛው ወላጆቹን ለመርዳት ፣ ለማመስገን እንኳን ፈቃደኛ አይደለም፡፡ እራሴን መቻሌ የመርዳት ያህል ነው ብሎ በአፉ ይናገራል፡፡ ወላጆቹ የልጆቻቸውን ስጦታ ሲያጡ "ራሱን መቻሉ ጥሩ ነው" ብለው የሚጽናኑበትን ቃል እርሱ መኩሪያ አድርጎ መጠቀሙ ያሳፍራል፡፡
ገንዘብ ይበትናል እንጂ ጥሩ እርሻ ላይ አይዘራውም፡፡ ለአዝማሪና ለዝሙት ይበትነዋል፡፡ ደስታው ለራሱ ፣ መከራውን ለወላጆቹ መመደቡ በጣም አሳዛኝ አድርጎታል፡፡

ትውልዳችን ያስተማሩትን መምህራኑን የማያከብር ፣ ለራሱ መስፍን ሆኖ ንጉስ አልባ የሆነ ትውልድ ነው፡፡ የሌሎች ውለታ መመለስ መቻል የሰውነት ክብር ነው፡፡ ውለታን ማሰብ እንኳ አለመፈለግ ግን ከሰውነት ተራ የሚያወጣ ነው፡፡ በፈረንጆች አገር የእናቶች ቀን የመምህራን ቀን እያሉ ፍቅርን በዓል ያደረጉት በትውልዱ ውለታ ቢስነት ነው፡፡

3) ራሱን የማያከብር ነው

ራስን መሆን ለአእምር ጤንነት ፣ ለኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ ነው፡፡ ራሱን ያልሆነም እራሱንም ያጣል፡፡ ሌሎች ሊያከብሩት የሚችሉት መጀመሪያ እራሳችንን ስናከብር ነው፡፡ ራቁታችንን በራሳችን ሸማ ብንሸፍነውም እንሰወራለን ፤ በሌሎችም ልብስ ግን ሐፍረታችን አይሸፈንም፡፡

ትውልዳችንን ስናየው ገና በአእምሮ ቅኝ ግዛት የተያዘ ፣ እራሱን የማያከብር ፣ ከራሱ መልካም የሌሎችን ክፉ እንደ መልካም የተቀበለ ትውልድ ነው፡፡ ስለዚህ የረጋ ማንነት የለውም፡፡ ሕይወቱን የሚመራው ዘመናዊነት እንጂ ቋሚ እውነት አይደለም ፤ በሳምንቱን ምርጥ ፊልም ሳምንቱን ይመራዋል፡፡ መረጃዎቹን ለመስማት ሳይሆን ለመሆን ስለሚፈልግ በብዙ ጠፍቷል፡፡ ስለ ሌሎች ሲያወራ ስለ ኳስ ተጫዋቾች ደሞዝ ሲጨቃጨቅ ይውላል፡፡ አንድ አባባል አለ፡-

"ትልልቅ ጭንቅላቶች ስለ አሳብ ያወራሉ ፣ መካከለኛ ጭንቅላቶቹ ስለ ሁኔታ ያወራሉ ፣ ትንንሽ ጭንቅላቶች ሁሌም ስለ ሰው ያወራሉ"

እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው የሰጠው ማንነት አለ፡፡ ያ ማንነት የተለያየ ቢሆንም እግዚአብሔር ከሰማይ ወደምድር ሲመለከት የተለያየ ቀለምን የሚያሳይ ኪነ ጥበብ ነው፡፡ ራሳችንን ስንሆን እግዚአብሔር ሊያይ የፈለገውን ሥዕል እናሟላለን፡፡ ከሌሎች መማር አስፈላጊ ቢሆንም የምንቆምበት መሠረት ግን ያስፈልገናል፡፡ መሠረቱን ለቆ ዕቃ ላውርድ የሚል ዕቃውን ይዞ እንደሚወድቅ እንዲሁ ማንነቱን ጥሎ ከሌሎቹ ልማር የሚል ትምህርቱ ለመቆም አይረዳውም፡፡

ትውልዳችን እንደሌሎቹ መናገር ፣ እንደሌሎቹ መራመድ ፣ እንደሌልቹ መልበስ የሚያረካው የራሱ ነገር በጣም የሚያሳፍረው ነው፡፡
የገንዘብ ባሪያ ሆኖም ገንዘብን ለማግኘት ምንም መሆን የማይቆጨው ፣ ሰውነቱን አርክሶ ገንዘብ መሰብሰብ የሚያስደስተው ነው፡፡ ብዙ ወጣት ሴቶች ስናይ ገንዘብ ካዩ ምንም ዓይነት ክፉ ግብዣን እምቢ የማይሉ ፣ በባዕድ አገር ጭምር አገራቸውን የሚሰድቡ ክብር የለሽ ሆነዋል። ትውልዱን ራሱን አለማክበር ብቻ ሳይሆን ታላላቆቹን በመናቅ ትልቅ የሚሆን ይመስለዋል፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
4) ከስህተቱ መማር አይፈልግም

የስህተት ማካካሻው ትምህርት ነው፡፡ ካለፈው መማር ያለ መበደል ያህል ነው፡፡ ስህተትን እንዳልተሰራ ማድረግ አይቻልም፡፡ የሰውነት ክብር ግን ከትላንቱ መማር ነው፡፡ ትውልዳችን ግን ከትላንቱ የሚማር አይደለም፡፡ ሰው በሁለት ነገር ሊማር ይችላል፡፡

ከስህተት በፊት በመስማት ይማራል ÷ ከስህተት በኋላ ደግሞ ከውድቀት ይማራል፡፡ ትውልዳችን ግን ከስህተት በፊት ለመማር መስማት አይፈልግም፡፡ የቁም ነገር ሃሳብ ሲነሳበት እየሰለቸ ፣ ለፌዝ ተሰጥቶ ይታያል፡፡ ከውድቀት በኋላ ላለመማሩ ምክንያቱ ቶሎ ተስፋ መቁረጡና እግዚአብሔር የእንደገና አምላክ መሆኑን መዘንጋቱ ነው፡፡ ትውልዱ መስማት አይፈልግም፡፡

አክራሪነትን የወለደው ድንቁርና ነው፡፡ ማወቅ የሚመጣው ከመስማት ነው፡፡ አስተማሪዎቻችንን በመጀመሪያ ሰምተናቸዋል፡፡ ከዚያ የዕውቀት ባለቤት ሆነናል፡፡ የማወቅ መሰረቱ መስማት ነው፡፡ ትውልዳችን ግን ማወቅና መፍትሔ ላይ መድረስ አይፈልግም፡፡ ያለበትን ህይወት እንደመጨረሻ መፍትሔ ተቀብሎታል። ችግሩ በፈጠረው አስተሳሰብ ውስጥ ችግሩን መፍታት አይቻልም፡፡ አስተሳሰቡ መለወጥ አለበት፡፡

በትውልዳችን ላይ የምናየው ትልቅ ችግር የራሱን አመለካከት አለመኖር የሌሎችን አመለካከት አለማክበር ነው፡፡ ብዙ የተዋቡ ቃላት በቃሉ ያጠናል ፣ የመናገር አምሮት ስላለበት ይናገራል፡፡ በተግባሩ ግን የተበላሸ ነው፡፡ በተግባር የሌለበት የቃላት ኑሮ በመጨረሻም ብቸኛ ያደርጋል ፣ ተስፋ በመቁረጥም ወደ ሞት ያደርሳል፡፡ ስለዚህ ቃል ብቻ ከመሆን መዳን ያስፈልጋል፡፡

አሳባችንን ለመፈፀም በዋናነት የሚያስፈልገን ባለ አደራነት ወይም የቃል ኪዳን ልብ መሆኑን ማሰብ አለብን፡፡ ትውልዳችን ግን ዋናውን ነገር ገንዘብ ነው ብሎ ያስባል፡፡
ከበደ ሚካኤልም እንዲህ ብለዋል:-
"በዓለም አይገኝም ቢፈልጉ ዞሮ፣
መስማት ከማይፈልግ የባሰ ደንቆሮ"

5) ቦታውን ይለቃል

ትውልዳችን ተጓዥ ነው፡፡ አንድ ነገር ያልሆነ ከመሰለው ለዘወትር የማይሆን ነው ብሎ ስለሚያስብ እንደገና የመሞከር ትዕግስት የለውም፡፡ ከጓደኛው ጋር ቢጣላ ሌላ ጓደኛ ይፈልጋል እንጂ ከዚህ ውስጥ የምማረው ትምህርት ፣ ክፉ ከመሰለው ነገር ውስጥ የሚወጣው መልካም ነገር ምንድን ነው?
ለማለት ፍላጎትም ብስለትም የለውም፡፡

ተጓዥ በመሆኑም ሃይማኖቱን ሳይቀር ሲለዋውጥ ይኖራል፡፡ የአዲስ ሃይማኖት አድናቂ ሆኖ ዘመኑን በቅልውጥና ይጨርሳል፡፡ ኑሮው ሁሉ ወጥ ቀማሽነት እየሆነ ፣ በሰማበት ጣዱኝ እያለ የሚንከራተት ይሆናል፡፡ መሠረት ስለ ሌለው ሁሉንም ነገር የሚሰማው ቦታውን ለቅቆ ነው፡፡ ስለዝሙት ሲያነብ ማመንዘር ይፈልጋል ፤ ስለ ክህደት ሲያነብ ክዶ ይሰነብታል ፤ የቤተክርስቲያን ጉባኤ ሲሰማ አማኝ ይሆናል፡፡ አድራሻ አጥቶ የሚንከራተት ትውልድ እያስተዋልን ነው፡፡

ይህን የምጽፈው ትውልዱን በሙሉ ለመኮነን አይደለም፡፡ ችግሩን ማወቅ በራሱ ግማሽ መፍትሔ መሆኑን በማመን ነው፡፡ በጦር ሜዳ ቦታን አለመልቀቅ ለድል ያበቃል፡፡ ማፈግፈግ ግዛትን ለጠላት በፍቃድ ራስን አሳልፎ እንደ መስጠት ነው፡፡

ትውልዳችን በብዙ መከራዎች የታጀበ ፣ የጀመረውን ነገር ለመፈጸም እልህ የሚያንሰው ነው፡፡ እቅዱ ስለሚበዛም ውጤቱ ያንሳል፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን መንገድ መሪ አለማግኘቱ የበለጠ ጉዳት ነው፡፡

ሌሎች አምስት ይቀራሉ ይቀጥላል

ከሁለተኛ መፅሐፍ ሰባተኛ ፅሁፍ

እኔ ፣ አንተ ፣ አንቺ ፣ የእኛ ትውልድ በትንሽዬ
መጽሐፍ ያስገርማል፡፡

አስተያየታችሁን አድርሱኝ @jahABP ነኝ

ይቀጥላል🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
Forwarded from MiKiiĩ {MK} Art Studio
የተለያዩ ዲዛይንና ኳሊቲ ህትመት ያላቸውን የሰርግ ካርዶችን ይዘዙን በፍጥነት እና በጥራት እናደርሳለን
ይደውሉ:- 0920888649 ሊንኩን ተጭነው ይቀላቀሉንhttps://t.me/joinchat/AAAAAEhVLV9cI9xT3fq73g
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN



መልካም ዕለተ ሰንበት
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ሌሎች አምስቱን እንቀጥላለን......

እንዲህ ይላል "ትውልዳችን በአብዛኛውኝ ስንመለከተው ያልሆነውን ለመምሰል ደፋር ነው፡፡
የማያውቀውን አውቃለሁ ለማለት የቴክኖሎጂ እውቀትን እንደሕይወት እውቀት ለመቁጠር ፣ የማይወደውን ሰው እወድሃለሁ ብሎ ለመጥለፍ ፣ ያልገባውን እንደገባው ለመምሰል ፣ የጠራን ነገር ሳይዝ ለአስተማሪነት ለመነሳት ፣ የሚሔድበት ሳይገባው ልምራ ለማለት ፣ በእልፍኘ ሳይሰራ(ሳይታነፅ) በአደባባይ ለመታየት ፣ ትንሹን ብዙ ብሎ ለማውራት ፣ በማጋነን እውቀትን ለማቀጨጭ......ደፋር ነው፡፡ እያለ ይቀጥላል......ነገ እንቀጥለዋለን

መነበብ አለበት

ነገ ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂
አሁንም አስተያየታችሁ አይለየኘ @jahABP

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN


Wallpaper

ሲንጠባጠብ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
6) ሁሉንም ልሞክር ይላል

ትውልዳችን በአብዛኛው ስንመለከተው ክፉ ፣ ክፉ እንደሆነ የሚያውቀው ሲደርስበት ነው፡፡ እሳት ማቃጠሉን ለመረዳት እሳትን መንካት አያስፈልግም፡፡ እሳትን እንደሚያቃጥል ሲነግረን ተቀብለናል፡፡ የተቃጠሉ ሰዎችንም በማየት እሳትን መጠንቀቅ እንደሚገባን ተምረናል፡፡ ሁሉን በሕይወቴ ላረጋግጥ ፣ ሁሉን ቀምሼ ልወቅ ፣ ሁሉን ሞክሬ ልመለስ ማለት መንገዱን መሔጃ እንጂ መመለሻ የለውም፡፡

ሁሉን በዕድሜያችን ለማረጋገጥ ብንፈልግ ዕድሜያችንም አይበቃም፡፡ ነፃ የትምህርት ዕድልና የክፍያ ትምህርት ልዩነት አላቸው፡፡ ነፃ የትምህርት ዕድልያገኘ ሰው ትምህርቱን በደስታ የሚማር ሲሆን በክፍያ የሚማረው ግን የሚከፍለውን ለማግኘት የሚጥር ነው፡፡ እግዚግብሔር በቃሉ አማካኘነት ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጥቶናል፡፡ ትዕዛዙን በመፈፀም በነፃ እንማራለን፡፡
እምቢ ካልን ግን በዋጋ እንማራለን፡፡
በዋጋ መማር በስህተት ፣ በውድቀት መማር በመሆኑ ከባድ ነው፡፡

ትውልዳችን ስናይ ከጥፋት መንገዱ በምክር መቆም አይፈልግም፡፡ ፍሬኑ እንደተበጠሰበት መኪና ሲጋጭ ወይም ሲገለበጥ ለመቆም የሚነጉድ ነው፡፡ በወኅኒ ቤት የሚማቅቁ ፣ በበሽታ የተጎሳቆሉ ብዙ ወጣቶችን ስናይ ምክርን በመናቅ በግትርነት የገብበት ነው፡፡

7) ደፋር ነው፡፡

ትውልዳችን በአብዛኛውኝ ስንመለከተው ያልሆነውን ለመምሰል ደፋር ነው፡፡
የማያውቀውን አውቃለሁ ለማለት የቴክኖሎጂ እውቀትን እንደሕይወት እውቀት ለመቁጠር ፣ የማይወደውን ሰው እወድሃለሁ ብሎ ለመጥለፍ ፣ ያልገባውን እንደገባው ለመምሰል ፣ የጠራን ነገር ሳይዝ ለአስተማሪነት ለመነሳት ፣ የሚሔድበት ሳይገባው ልምራ ለማለት ፣ በእልፍኘ ሳይሰራ(ሳይታነፅ) በአደባባይ ለመታየት ፣ ትንሹን ብዙ ብሎ ለማውራት ፣ በማጋነን እውቀትን ለማቀጨጭ......ደፋር ነው፡፡

ከእኔ የተሻሉ ሰዎች አሉ ብሎ አይቀበልም፡፡ እነ እገሌ ያርሙኘ ለማለት ፈቃደኛ አይደለም፡፡ በቀዳዳ ያየውን በሰማይ መስክ ላይ እንደታየው አድርጎ ያወራል፡፡ የሞቀ አፍ እንጂ የሞቀ እውነት የለውም፡፡ ትውልዳችን ለመስረቅ ፣ ለመግደል ፣ ራሱን ለማጥፋት ደፋር ነው፡፡ የሰውነቱን ክብር ንቋል፡፡ ሁሉንም አድርጎ ለመደሰት ይፈልጋል፡፡

ያልታየውን እንደታየው አድርጎ የሚተርክ ባለ ራዕይ መሳይ ፣ ያልተሰማውን እንደተሰማው አድርጎ የሚያወራ ሩህሩህ መሳይ ፣ እደርስላችኀለሁ እያለ በተቀመጠበት የሚፎክር ታዳጊ መሳይ ነው፡፡ የሚናገረውን ቃል የማይረዳ ጥሬ ቃል ይዞ የሚሮጥ ፈ ተግዳሮት የሚያደናግር ፣ አፍ እንጂ ጆሮ የሌለው እንደ አመንዝራ በቁንጅናው በርን ሁሉ ለማስከፈት የሚሻ ደፋር ነው፡፡

ቋንቋን እውቀት አድርገው የሚኖሩ ብዙዎችን እየወለድን ነው፡፡

ብዙ አስተዋይ ሰዎች በራቸውን ዘግተው ተቀምጠዋል፡፡ ሰሚ ያጡ ሊቃውንት እንደ አላዋቂ ዱዳ ሆነዋል፡፡ ትልቅ ድንቁርና አለመማር ሳይሆን መማር አለመፈለግ ነው፡፡
አላዋቂነትን እንደ እውቀት በመቁጠር መንጎማለል ነው፡፡ ለማያፍሩ የሚያፍሩ ፣ ለማይፈሩ የሚፈሩ ብዙ አስተዋዮች ይህንን የሚቸኩል ዘመን ጥግ ይዘው እያዩት ነው፡፡

የዚህ ሁሉ ችግር ትውልዱ ለዕድገቴ ሌሎች ያስፈልጉኛል ፣ ለዕውቀቴ ስፋት መጠየቅ ያሻኛል ብሎ አለ ማሰቡ ነው፡፡ የዚህ ትውልድ አባላትም የቤተክርስቲያን መሪዎች ፣ የግዛት አስተዳዳሪዎች እየሆኑ ነውና ችግሩ አሳሳቢ ነው፡፡

8) በምኞት የሰከረ ነው

ትውልዳችን አብዛኛው በምኞት የሰከረ ነው፡፡
ትውልዳችን የምኞት እሳት አንድዶ የሚሞቅ ፣ ትንሽ ፈገግ እያለ ከራሱ ጋር የሚያወጋ ፣ ተግባር የሌለበት ምኞቱ በኩራት የሚናገር ፣ ባልተጨበጠ ነገር ከሰው የሚጣላ ፣ ምኞቱ እየራቀ ሲመጣ ደግሞ ቀቶሎ የሚረበሽ ፣ ተስፋ ለመቁረጥም የሚዳረግ ነው፡፡

ሰው በብዙ ነገሮች ሊያብድ ይችላል፡፡ በቁጣ ያብዳል ፣ በምኞት ያብዳል፡፡ የዕብደት አይነቱ ብዙ ነው፡፡ ሔዋን በምኞት አበደች፡፡ ስለዚህ ያላትን ብዙ ሳይሆን የሌላትን ትንሽ ነገር ነገር መፈለግ ጀመረች፡፡ ውጤቱ ግን የቆጡን አውርድ ብላ እንደሚባለው ተረት ሆነባት፡፡ ትውልዳችን በሰው እጅ ያለው የሚያምረው ፣ የራሱን የማይወድ ፣ በተሰጠው የማይረካ ነው፡፡

ብዙ ትውልዳችን በምኞት አብዷል፡፡ ይህንን ባደርግ ይህ ቢደረግልኘ ፣ ይህ ቢሆንልኘ በሚል መጎምጀዠት ተይዛል፡፡ በሕይወቱ አንድ ትልቅ ነገር ለማድረግ ይመኛል፡፡ በሕይወት ላይ ግን አንድ ጊዜ አንድ ትልቅ ነገር ማድረግ አይቻልም፡፡ በዙሪያችን የከበበን ትንንሽ ነገር ነው፡፡ በዕየለቱ ትንንሽ ጉዳዮችን ስንፈፅም ትልልቅ ተግባር ይሆናሉ፡፡ መመኘት ክፉ አይደለም፡፡ ምኞት ብቻ ግን ክፉ ነው፡፡ ያልሆኑትን ነገሮች እንደሆኑ አድርጎ መጣላት ከትውልዳችን ላይ ይንፀባረቃል፡፡

የተዘረጋን ድልድይን መፈለግ ሳይሆን ድልድይን መዘርጋት ፣ ድልድይ መሆን ይገባል፡፡ ትውልዳችን ላይ ግን ያንን አናይም፡፡

9) ራስ ወዳድ ነው

ትውልዳችን በአብዛኛው በዓለም ያለው እርሱ ብቻ ሆኖ የሚታየው ፣ ሁሉንም ሰው ለእርሱ እንዲኖርለት የሚፈልግ ፣ መስዋት መክፈል የማይወድ ፣ እኔን ብቻ ይድላኘ የሚል ራስ ወዳድ ነው፡፡ ራስወዳድነት ዘውድ ጭኖ እየገዛን ነው፡፡
"ከራስ በላይ ንፋስ"እንደሚባለው ለራስ ወዳዶች ከበላያቸው ነፋስ እንጂ እግዚአብሔር መኖሩን የማያምኑ ናቸው፡፡

ራስወዳድ ትውልድ ለክህደት ቅርብ የሆነ ትውልድ ነው፡፡ ቴክኖሎጂው ለራስ ወዳድነት ፣ በር ዘግቶ ለመኖር ምቹ ሆኗል፡፡ ሁሉም ሰው የራሱ የግል ስልክ ፣ የራሱ የኢሜል አድራሻ ፣ የኣሱ መኖሪያ ቤት...እንዲኖረው የሚጥር ነው፡፡ ስለዚህ ትውልዳችን የእኛ ለሚል ነገር ደስታ የለውም ፣ የእኔ ለሚል ነገር የተሰጠ ነው፡፡

ትውልዳችን ምን አገባኘ ማለት የሚወድ ፣ እኔን ካልነካኘ የፈለገው ነገር ይሁን የሚል ፣ ጓደኛውንም እንደ ባላንጣው የሚያይ ትውልድ ነው፡፡ ራስ ወዳድነት ሌላውን ሰው እንዳናይ ያደርገናል ፣ የጊዜያዊ የፍቅርና የጊዜያዊ ልስላሴ ባለቤቶች ያደርገናል፡፡ ጥቅማችን እስኪሟላ አፍቃሪ መሳይ እንድንሆን ፣ የምንሻውን እስክናገኘ በሰው ፊት ለፊት ያለማቋረጥ እንድንቆም ፣ ጥቅማችን ከተሟላ በኀላ ጀርባችንን እንድንሰጥ ያደርገናል፡፡ ራስ ወዳድነት ይሉኘታን እንኳን የሚያሳጣ ፣ የጥቅም አምልኮ ነው፡፡

ራስ ወዳድ እግዚአብሔር ማምለክና ባለ ራዕይ መሆን አይችልም፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
10) የራሱን አስተሳሰብ መልቀቅ አይፈልግም

ትውልዳችን በአብዛኛው ከታሪክ መማር አይፈልግም፡፡ ዛሬ ያለትላንት እንዳልኖረች አይገነዘብም፡፡ ታሪክን ወደኀላ መልሶ ማስተካከል ባይቻልም ከታሪክ ግን መማር ይቻላል፡፡ ውድቀትን ከወደቁት ፣ ተሰጥቷቸው ካላወቁበት ዕድለ ቢሶች መማር ትልቅ ነገር ነው፡፡
አንድ የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩ ሰው በወኅኒ ቤት ሲናገሩ "እኛ ሕያዋን መጽሐፍት ነን ፣ የዛሬው ባለስልጣናት ከእኛ ከእድለቢሶቹ መማር አለባቸው" ብለዋል፡፡ ያለፈው ታሪክ ትለልቅ ትምህርተት አለው፡፡ የታሪክ ዓላማ ለትረካ ፣ ጊዜ ለማሳለፊያ ፣ለተረት መተረቻ ሳይሆን ለትምህርት የሚሆን ነው፡፡

ትውልዳችን ከታሪክ ሊይዘው የሚገባውን መልካም ነገር በዜሮ አባዝቶ ትላንትን ያጣጥላል፡፡ ታሪክ ሲወቅስ እርሱም በታሪክ ፊት መሆኑን ይዘነጋል፡፡ ትውልዳችን አሁንም ትልቁ ችግሩ ፣ ችግሩን መፍታት የሚፈልገው ችግሩ በወለደው አስተሳሰብ ነው፡፡ በአዲስ አስተሳሰብ ውስጥ እስካልሆንን ችግሩን መፍታት አይችልም፡፡


ለዚህ መፍትሔው ቆም ማለት ፣ መፀለይ ፣ ሊቃውንትን መጠየቅና የተቀደሱ ፅሁፎችን ማንበብ ያስፈልጋል፡፡

ትውልዳችን ግን ወይ አይጠይቅም ወይ አይጠየቅም፡፡ ራሱን ዝቅ አድርጎ ሊቃውንትን መጠየቅ ቢጠላ እንኳን ዓይኑን ገልጦ መፅሐፍትን ቢያነብ መልካም ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ትውልዳችን ወደማያቀው ግብ እየተጓዘ ፣ መንገድ ሁቹ የሚያደርስ እየመሰለው ወደ ተሰበረ ድልድይ እየነጎደ ነው፡፡

ጠልቆ ባልገባቸው ዘመን ፣ በወለደው ነገር እየተታለሉ ፣ አዲስ ነገር ሁሉ መልካም ነው ብለው የነጎዱ የነቁ ቀን ያዝናሉ፡፡ ስላለፈው እረጅም መንገድ ፣ ስለከንቱ ልፋታቸው ይፀፀታሉ፡፡ ዘመንን ወደሚክሰው አምላክ ካልተመለሱ በቀር ሃዘናቸው ቅጥ የለውም፡፡

ከዓይናማ ሊቃውንትና ከደህና መፅሐፍት የተጣላ ትውልድ ከእውነትና ከእውቀት ብሎም ከእምነት እየራቀ ይመጣል፡፡ የዚያን ጊዜ ሕይወትን አቻችሎ መምራት ያቅተዋል፡፡ የብርሃንና የጨለማን ፈረቃ መታገስ እያቃተው በቶሎ ተስፋ ይቆርጣል፡፡ በአብዛኛው ትውልዳችን ስናየው ምክርን የሚንቅ ፣ በጊዜያዊ ስሜቱ ፣ በገዛ ማስተዋሉ የሚደገፍ ነው፡፡ የራሱን አስተሳሰብ መልቀቅ ስለማይፈልግም ምክርን አይቀበልም፡፡

ከሁለተኛ መፅሐፍ ስምንተኛ ፅሁፍ

ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ

ምን ተሰማቹ ሃሳቡ እውነት ነው ውሸት??

ደራሲው ትውልዳችንን አልታዘበውም ትላላቹ??

ቤታችን እንሁን

አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN


any one ቺብስ ወዳጅ


@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

😊እንዴት አረፈዳችሁ😍

የትውልዳችን 10 ችግሮች ሁላችንንም እንደነካ ሁላችንም ቆም ብለን እንድናስብ እንዳደረገን በሰጣችሁኘ አስተያየት ለማወቅ ችያለሁ፡፡

ካነበብነው በኀላ የሆነ ለውጥ ይኖራል ብዬ አስባለሁ፡፡

እስኪ አሁን ደግም ራዕያችን ላይ ህይወታችን ላይ የሚገጥሙን እንቅፋቶችን እንይ፡፡

እንቅፋት ለምን ይገጥመናል እንቅፋት ጥቅም አለው ወይስ ጉዳት ብቻ ነው??

እንዲህ ይላል

" አዎ ህይወት የምትጥመው በእንቅፋት ውስጥ ነው፡፡ እንቅፋት ቢያምም ቆም ያደርጋል ፣ ለቀጣዩ ጉዞ ጠንቃቃ ያደርጋል፡፡ በሽታ ባይኖር የፈውስ ደስታ ፣ እስር ባይኖር የነፃነት እልልታ ፣ ጦርነት ባይኖር የድል ዝማሬ ፣ እንቅፋት ባይኖር የምንተርከው ገድል አይኖርም ነበር፡፡ ሕይወት የምንጓጓላት መኖርን የሚፈታኑ ነገሮች ሲኖሩ ብቻ ነው፡፡ በተደላደሉ አገሮች የሚኖሩ ዜጎች ከአፍሪካዊያን ይልቅ ራሳቸውን ያጠፋሉ፡፡

መደላደል የኑሮ እርካታ አይደለም፡፡ የታመመው በዳንኩኘ ሲል ጤኔኛው በሞትኩኘ ይላል፡፡ እንዲሁም በራዕይ ውስጥ እንቅፋት አለ፡፡ እንቅፋቱ ግን የራዕይ ፍፃሜ ሳይሆን በጥንካሬ እንዲጓዝ የሚያደርገው ነው፡፡ እንቅፋትን እንደመጨረሻ የሚቆጥር አእምሮ ተገቢ አይደለም፡፡

እንቅፋት ከእንቅልፍ ያድናል፡፡
ማንኛውም ነገር የራሱ እንቅፋት አለው፡፡ ምቹ ነገር ላይ የምንደርሰው የማይመቹ ነገሮችን አልፈን ነው፡፡ እንቅፋት ተፈርቶ የተተወ መንገድ የለም፡፡ መንገደኛ መንገዱ እንዳለ ሁሉ እንቅፋቱም አለ የማይጓዝ ሰው እንቅፋፍ አይገጥመው ይሆናል ግን ፣ አይደርስም አሳብ አርግዞ ፣ አሳብ ይወልዳል፡፡ የሚጓዝ፡ሰው ግን ቢዘገይም ይደርሳል፡፡"


ካነበብኩት በኀላ እንቅፋቶችን ደርምሶ ለማለፍ የተቻለኘን ሁሉ ማድረግ ጀመርኩ አሁንም አደርጋለሁ አሁን ላይ እንቅፋት አይግጠመኘ አልልም ብልም እንደማይሆን አውቃለሁ ግን ያን ጥንካሬ አግኘቻለሁ የሚገጥሙኘን እንቅፋቶች ታግሎ ማሸነፍን፡፡

አንተ አንቺ እናንተም የሆነ ነገር ታተርፉበታላችሁ ብዬ አሰብኩና ላካፍላችሁ ወደድኩ፡፡

እንቀጥላለን🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

ቆዩልኘ፡፡
@jahABP ነኘ አስተያየታችሁ አይለየኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

እንቅፋት

እንቅፋት ያለንን አቅም የምንመዝንበት ነው፡፡ በመንገዱም የዛለው እንቅፋቱ በኃይል ሲያዘልለው ዛሬም ጉልበታም ነኘ ብሎ እንዲያስብ ያደርገዋል፡፡ ብዙ ጊዜ እያለን የለሁም የሚል እንጉሮሮ እናሰማለን፡፡ ያረጀው መንፈሳችነ እንጂ ጉልበታችን አለመሆኑ የምናውቀው እነቅፋቱ መነቃቃት ሲፈጥርልን ነው፡፡

በሰላም ዘመን የተሟሟቱ ሰዎች በመከራ ዘመን ሲታደሱ እናያለን፡፡ ብዙ ተሻዋሚዎቻችንን እግዚአብሔር ማንቂያ አድርጎ እንደ ሰጠን የምንገነዘበው ቆይቶ ነው፡፡ እንቅፋት ያቆስላል፡፡ እንቅፋቱም ስስ የሆነውን የሰውነታችንን ክፍል የሚጎዳ ስለሆነ አእምሮን የሚለውጥ ህመም አለው፡፡ በራዕያችን የሚገጥመን ጋሬጣም የመጀመሪያ አላማው እርምጃችንን መግታት ነው፡፡

በህይወታችን ውስጥ የማንቋቋመው ስር ነገራችንን በመጉዳት ያዘገየናል፡፡ የአንዳዶች ስስ ነገር ስምና ክብራቸው የሌሎች ሀብትና ንብረታቸው ሊሆን ይችላል፡፡ በራዕያቸው ምክንያት ትዳራቸውን ብቻ ሳይሆን አካላቸውንና ጤንነታቸውንም ያጡ ወገኖች ብዙ ናቸው፡፡
ይህ ነገር ሕመሙ ከፍ ያለ ነው፡፡ የራዕይ ሕመም ግን ይነዘንዛል ግን አይገድልም፡፡

ራስ ያሳምማል ግን አያሳብድም፡፡ የቁጣውም ትንታግ ለሌላ በሽታ አሳልፎ አይሰጥም፡፡ እግዚአብሔር በትካዜውና ባለ ራዕዩ መካከል ጣልቃ ይገባል፡፡

እንቅፋት ያዘገያል፡፡ ልብ ወደ ደረሰበት ቦታ እግር መድረስ ያቅተዋል፡፡ የመነሻውና የመዳረሻውርቀቱ እኩል እየሆነ ለመመለስ ሆነ ወደፊት ለማለት ወመወሰን እስኪያቅት ያዘገያል፡፡
እንቅፋት ማሳመም ብቻ ሳይሆን ማመንታትንም ያስከትላል፡፡ በዚህ ዓለም ላይ የተከናወኑ ራዕዮች ሁሉ ፍፃሜአቸው እንጂ ጅማሬአቸው አወዳሽ አላገኘም፡፡

ጉዞ ያልጀመረ ሰው እንቅፋት የለበትም፡፡ ስለዚህ እንቅፋት የመነሳታችንና እልፍ የማለታችን ምስክር ነው፡፡ በመነሻችንና በመድረሻችን መካከልም ያለተግዳሮት ነው፡፡ በወደብ ማዕበል የለም፡፡ ብርቱ ማዕበል ያለው በመሃሉ ላይነው፡፡ ማዕበል ስላለ ግን የመርከብ አገልግሎት አልቆመም፡፡ ቢዘገዩም ይደርሳሉ፡፡

አንድ ወዳጄን አንድ ሰው እንዴት ነህ? ቢለው"ዔሊ አትፈጥንም ግን አታቋርጥም ፣ የዔሊ ጉዞ ብንጓዝም አለን" አለው፡፡

እንቅፋት ቆም እንድንል ያደርጋል፡፡ እንቅፋት ክፉ ብቻ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ቆም እንድንል ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ በስሜት ስንነጉድ ፣ የገዛ ራእያችንን የሚቃወም ምቾት ውስጥ ስንሆን ፣ ነጻነታችን በዝቶ ሌሎችን መጉዳት ሲጀመር ቆም የምንለው በእንቅፋቶች ነው፡፡ የት እንዳለ እንኳን ማወቅ እስኪሳነን በደመ-ነፍስ የምንጓዝ ጊዜ አለ፡፡ እንቅፋት ግን ያለንበትን ቦታ እንድናውቅ ያደርገናል፡፡

እንቅፋት ከእንቅልፍ ያድናል፡፡ በተመቻቹ መንገዶች ላይ በጥበብ የተሰሩ እንቅፋቶች ወይም ማንቂያዎች አሉ፡፡ ከመንገዱ ልስላሴ የተነሳ ሾፌር ሊተኛ ይችላል ፣ እነዚህ ሸካራ መንገዶች ወይም አንስተው የሚያፈርጡ እንቅፋቶች ሾፌሩን ያነቁታል፡፡
ትልልቅ ችግሮች የሚከሰቱት በምቾት ውስጥ ነው፡፡ ምቾት ወደ ሞት ሊወስድ ይችላል፡፡እግዒአብሔር ለሞት እንዳንተኛ ዓይናችንን የሚያበራው በእንቅፋት ነው፡፡

እንቅልፍ መልካም የሚሆነው እየተጓዙ ሳይሆን በአልጋ ላይ ብቻ ነው፡፡ እየተጓዙ መተኛት ወደ ቀለጠው እንቅልፍ ወደ ሞት የሚወስድ ቅርብ መንገድ ነው፡፡ በራዕይ ላይም ማንቀላፋት መደንዘዝ ገዳይ ነው፡፡እንቅፋት ግን ያነቃናል፡፡
የሚተኛመ ሰው የምናነቃው በማችመቹ ነገሮች ነው፡፡ ውሃ በመርጨት ፣ በመነቅነቅ ፣ በመምታት...ነው፡፡ እግዚአብሔርም ከከባድ ችግር በሚያንስ ችግር ያድነናል፡፡

እንቅፋት ለምስጋና ያበቃናል፡፡ ያለፋትን ሰላማዊ ጊዜዎች የምናመሰግነው ፣ እግዚአብሔር ዕረፍትን ሰጥቶን እንደ ነበረ የምንገነዘበው እንቅፋት ሲገጥመን ነው፡፡ የሰላም ጊዜ ቢረዝምም አጭር ነው፡፡ የመከራ ጊዜ አጭር ቢሆንም ከባድ ነው፡፡ የመከራ ዘመን መልሶ መላልሶ ሰላማዊ ዘመን ያሳስባል፡፡ በመከራችን ስንመረር በሰላማችን ጊዜ እንዳላመሰገንን እናስባለን፡፡ በነፃ የተሰጡን ነገሮች ከሄዱ በኀላ በዋጋ እንኳን ለመመለስ እንደሚከብዱ እንገነዘባለን፡፡ እነቅፋት ለምስጋና ያበቃናል፡፡ ያ ምቹ ጊዜ የእኛ እንዳልነበር ይነግረናል፡፡

እንቅፋት የምንከላከለው የመጀመሪያው እንቅፋት እንደሚኖር በመጠበቅ ነው፡፡ ያልተጠበቁ ክፉ ነገር ብቻ ሳይሆን ያልጠበቁት መልካም ነገር ያስደነግጣል፡፡ ለጠበቅነው ነገር ግን የአእምሮ ፣ የአካልና የንብረት ዝግጅት ስለምናደርግ ጉዳቱ ይቀንሳል፡፡ ያልተዘጋጀንበት ነገር ድንጋጤው ብዙ ስለሆነ መፍትሔው ትንሽ ቢሆንም እንኳን ማከናወን ይከብደናል፡፡

ሰው በጉዳት ውስጥ አካሉና ንብረቱን ማጣቱ ትንሽ ጉዳት ነው፡፡ የሚከብደው ጉዳታችን የሚያስከትለው የኅሊና ስብራተት ነው፡፡ ህሊና እንደ አካል በመረቅ የማይጠገን ነው፡፡ የአለም ባህሪይና የሰዎች አካሔድ ፣ የራዕይን እንቅፋት የመንገዱ መሰናክል መጠበቅ ግን ከህሊና ጉዳት ያድናል፡፡ ስለዚህ እንቅፋትን ለመከላከል የመጀመሪያው መፍትሔ እንቅፋት እንዳለ መጠበቅ ነው፡፡

የእንቅፋት ሁለተኛው መፍትሔ እያዩ መሔድ ነው፡፡ አይን ባላየበት እግር ከረገጠ እንቅፋት ፣ ገደልና ወጥመድ ሊገጥመው ይችላል፡፡ የረገጡትን ማየት ሳይሆን የምናየውን መርገጥ ግድ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ከረገጡ በኀላ ስለሚያዩ የሚያዩት ስብራታቸውን ፣ ቆሻሻቸውንና ጠላታቸውን ነው፡፡ በሕይወት ውስጥ የነፃ የትምህርት ዕድልና በዋጋ የሚሰጥ ትምህርት አለ፡፡ የነፃ ትምህርት ዕድሉ እያስተዋሉ መጓዝ ፣ ምክርን ምክርን መጠየቅና መተግበር ፣ እንደ እግዚአብሔር ቃል መኖር ነው፡፡

ለምንቀቀለው መከራ ኅሊናችን የማይመሰክርልን ከሆነ መከራውን ድርብ ያደርገዋል፡፡ ያመንበትን ነገር መቀበል ግን ደስታን ይሰጠል፡፡ እያየን ማንጓዝ ከሆነ ክብር የሌለው መከራን እንቀበላለን፡፡ መከራ ወዳጅን ያሳጣል፡፡ ባለማስተዋል የሚመጣ መከራ ደግሞ ህሊናንም ያሳጣል፡፡ ጠዎ እንቅፋትን ለመከላከል ሁለተኛው መፍትሔው እያዩ መጓዝ ነው፡፡

እንቅፋት የመታው ሰውሰው ሊያደርገው የሚገባው መከላከያ እንቅፋትን ከመንገድ ማስወገድ ነው፡፡ እንቅፋትን ከመንከዱ ያላስወገደ ለዚህ ሲገርመው ለቀጣይ ቁስለትም ራሱን ያዘጋጃል፡፡ እንቅፋትን ከመንገዳችን ካላስወገድን በመዘናጋት እንደገና ልንመታ እንችላለን፡፡ እንደገና በእንቅፋት ስንመታ ከሚያዝንልን የሚነቅፈን ይበዛል፡፡

የትላንቱን ምት የትላንቱን መውደቅና መዘግየት በማሰብ በጥንቃቄ መጓዝ ይገባናል፡፡ ያለፉ ቀኖችን መልሰን መኖር አንችልም ካለፉት ቀኖች መማር ግን መልሰን መኖር ያህል ካሣ ነው፡፡
የተበላሹ ቀኖችን የምንክሰው በመማር ብቻ ነው፡፡

ይቀጥላል

ከሁለተኛ መፅሐፍ ዘጠነኛ ፅሁፍ

እንበርታ እንጠንክር ነገ የተሻለን ይሆናልና፡፡

አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
እነደዚህ ስራህን የሚያደንቅ ወንድም ካለህ አንተ እድለኛ ነህ 😍😍

የማ ወንድሜ አመሰግናለሁ....

ፎቶውን ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

እምየ ምንይልክ...ድንቅ አባት ፣ ግሩም ንጉሥ ፣ ብልህ መሪ ፣ ድንቅ መካሪ የያኔው የፕላኔታችን ጥቁር አንበሳ....የመጨረሻው የሞራል ብቃት ያላቸው የልዕለ ሰብ ባለቤት ከፒያሳ ሰማይ ስር ካለው የክብር ቦታቸው ላይ።

#ወንድሜ #የማነብርሃን እንደገለፃቸው

ትላንት ጠዋት ላይ የተነሳ

አስተያየታችሁን @jahABP
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN


የእኛጋር ፀሀይ


@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN


መልካም ዕለተ ሰንበት ተመኘሁ


@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

አንዳንዴ ብዙ መናገር ትፈልግና ሰሚ ታጣለህ
አንዳንዴ ለማን እንደምትናገርም ይጠፋኻል
አንዳንዴ ችግሮች አንተ ጋር ብቻ ያሉ ይመስላሉ
አንዳንዴ ለችግርህ መፍትሔው ታጣለህ፡፡
አንዳንዴ ምን እንደምትሰራ ግራ ይገባኻል፡፡
አንዳንዴ ትንሹ ነገር ይጋነንብኻል
አንዳንዴ ለምን እንደምትኖር ግራ ይገባኻል፡፡
አንዳንዴ ዝም ብሎ ደስ ይልኻል፡፡
አንዳንዴ ዝም ብሎ ይከፋኻል፡፡
አንዳንዴ ትደክማለህ፡፡
አንዳንዴ ታማራለህ፡፡
አንዳንዴ ታመሰግናለህ፡፡
አንዳንዴ............አንዳንዴ......አንዳንዴ

በዛ በብርድ ጤዛ ውስጥ ቁጭብላ የቧንቧው ውሃ እየጠንጠባጠበባት ሳያት የተሰማኘ ስሜት ነው አንዳንዴ ያልኩት😔
በጣም እኮ ይበርድ ነበር ምን ሆና ይሆን🤔?? ጠጋ ብዬ ልጠይቃትም ፈራሁ ገና ሳያትም ደንግጬ ነበርና፡፡

ፒያሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ፡፡

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD