Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
AB PHOTOGRAPHY

አንዳንዴ ብዙ መናገር ትፈልግና ሰሚ ታጣለህ
አንዳንዴ ለማን እንደምትናገርም ይጠፋኻል
አንዳንዴ ችግሮች አንተ ጋር ብቻ ያሉ ይመስላሉ
አንዳንዴ ለችግርህ መፍትሔው ታጣለህ፡፡
አንዳንዴ ምን እንደምትሰራ ግራ ይገባኻል፡፡
አንዳንዴ ትንሹ ነገር ይጋነንብኻል
አንዳንዴ ለምን እንደምትኖር ግራ ይገባኻል፡፡
አንዳንዴ ዝም ብሎ ደስ ይልኻል፡፡
አንዳንዴ ዝም ብሎ ይከፋኻል፡፡
አንዳንዴ ትደክማለህ፡፡
አንዳንዴ ታማራለህ፡፡
አንዳንዴ ታመሰግናለህ፡፡
አንዳንዴ............አንዳንዴ......አንዳንዴ

በዛ በብርድ ጤዛ ውስጥ ቁጭብላ የቧንቧው ውሃ እየጠንጠባጠበባት ሳያት የተሰማኘ ስሜት ነው አንዳንዴ ያልኩት😔
በጣም እኮ ይበርድ ነበር ምን ሆና ይሆን🤔?? ጠጋ ብዬ ልጠይቃትም ፈራሁ ገና ሳያትም ደንግጬ ነበርና፡፡

ፒያሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ፡፡

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
ሰላም እንዴት ናችሁልኘ😊🙏😍


ከእረፍት መልስ ሁለተኛውን መፅሐፍ እንጨርስ ይህን መፅሐፍ በዚ ባያልቅ ደስ ይለኘ ነበር፡
ሁላችሁም ካለበት አፈላልጋችሁ እንድትገዙት እመክራለሁ፡፡ አሁን ላይ ገበያ ላይ ያለ አይመስለኘም የድሮ መፅሐፍት ቤት የሚገኘ ግን ይመስለኛል፡፡

እኔ ያቀረብኩት ትንሹን ነውና ገዝታችሁ የትልቅ እውቀት ባለቤት እንደምትሆኑ የራሳችሁን ብሎም የሌሎችን ህይወት እንድትለውጡ እምነቴ ነው፡፡

ቤታችን እንሁን እናንብብ

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ


ቆዩልኘ 🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

እንቅፋት 2
እንቅፋትን ከመንገድ ማስወገድ ለቀጣዩ መንገደኛም መንገዱን ማጽዳት ነው፡፡ ባለ ራዕይ ልንሆን የምንችለው ሰው ሁሉ እንደ እኔ ከውድቀቱ ይማር ከሚል አስተሳሰብ ስንወጣ ነው፡፡

ችግሮች በእኛ አልቀው ለቀጣዩ ትውልድ መልካምነት ማቆየት ስንችል ባለ ራዕይ እንሆናለን።

በራዕያችን ውስጥ የሚገጥሙን ብዙ እንቅፋቶች ናቸው፡፡ የገዛ ቤተሰቦቻችን ፍርሃት ይዘሩብናል፡፡ እኛን እየወደዱ ራዕያችንን የሚጠሉ አፍቃሪዎች ይገጥሙናል፡፡ እኛንና ቤተሰቦቻችንን በረሃብ የሚቀጡ ብዙ ክፉ ቀኖች ይደቀኑብናል፡፡ አንዳንዶቹ እንቅፋቶች ልናርቃቸው የምንችላቸው ናቸው፡፡ ተጠንቅቀን የማናልፋቸው እንቅፋቶችም ይገጥሙናል፡፡ በትላንት ስህተቶቻችን ላይ ውሳኔ ካላደረግን መድገማችን የማይቀር ነው፡፡

ስህተትን ትላንት ላይ ብቻ ሳይሆን ነገ ላይ የሚጠብቀን እንቅፋት ነው፡፡ በራዕያችን ላይ የሚገጥመን እንቅፋት የያዝነውን አላማ እንድንጥል የሚያስደነግጠን ነው፡፡ ከዚያም ሲያልፍ ደግሞ ህይወታችንን ለመቅጨት የሚመኝ ነው፡፡ ራዕያችንን አንጥል ስንል ጠላቶቻችን እኛን በማጥፋት ራዕዩን ለማጥፋት ይመኛሉ፡፡ ራዕይ ግን በሰው ሕይወት ላይ ሳይሆን በእውነት ዘላለማዊነት ላይ እንደ ቆመች ባላጋራዎች አያውቁም፡፡

እንቅፋቱ ይበልጥ የሚጎዳው እጆቹን በኪሶቹ ከትቶ የሚሄደውን መንገደኛን ነው፡፡ ሁለቱን እጆቻችን- መቅዘፊያዎች ፣ ስንወድቅ ደግሞ ከአካላችን በፊት የሚዘረጉ ነፍስን አድን ሰራተኞች ናቸው፡፡ በራዕይ ጎዳና ላይ ትዕቢት ትልቅ እንቅፋት ነው፡፡ ትዕቢተኛ በራሱ ኃይል ለመግነን ስለሚፈልግ በሚወድቅ ጊዜ ለመነሳት ረዳት አያገኝም፡፡

ኑሯችን እየተደላደለ ቢመጣም ከማህበረሰቡ በጣም የራቀ ኑሮ ዘይቤ ውስጥ መግባት የለብንም፡፡ ተመልሰን ስንወርድ እንዳንረሳው ወይም ገደሉ እንዳይርቅብን ብዙም መራቅ ተገቢ አይደለም፡፡ በሊፍት የወጣ ሰው በዚያው ፍጥነት በሊፍ ሲወርድ እንደምናየው የዚህ ዘመን ትልቅነትም ከፍታውና ዝቅታው ፈጣን ነው፡፡

ስለዚህ በትሕትና ፣ ትላንትን በማይረሳ ማንነት ፣ ባለጠጎችን በማያመልክ ፣ ድሆችን በማያረክስ ስብእና በመመላለስ ከእንቅፋት ይጠብቃል ፤ በእንቅፋት ወድቆ ከመቅረት ይጋርዳል፡፡

ሁሉም እንቅፋቶች አላሳልፍም የሚሉ አይደሉም፡፡
በራዕያችን ላይም ቀላል የሆኑ እንቅፋቶች ንቀን የምናልፋቸው ሐሜትና ነቀፋዎች አሉ፡፡ ባለራዕይ እንዲህ ተባልኩ እያለ መደነቅ የለበትም፡፡ መባሉ ወደ መሆን እንዳይለወጥ መጸለይ አለበት ሰዎች ብዙ የሚሉት ጥቂት ማድረግ ስላልቻሉ መሆኑን መረዳት አለበት፡፡

አንዳንድ እንቅፋቶች ዞረን የምናልፋቸው በእኛ አቅምም ሊነሱ የማይችሉ ናቸው፡፡ የዘመናት እዳዎች የነገስታት አዋጆች የሚፈጥኑ ደምሳሽ ቀኖችን ባለራዕዩ በጸሎት ማሳለፍ አለበት፡፡
ሞቱን በእግዚአብሔር ፈቃድ ሊያደርግ ይገባዋል፡፡

የማይችለውን በማንሳት ወገቡ እንዳይበጠስ ማሰብ አለበት፡፡ የሚበልጠውን ችግር አስቀምጦ በትንንሽ ችግሮች ዘመኑን እንዳያልቅ አቋሙን መገምገም አለበት፡፡ ባለ ራዕይም ሁሉንም እንዲያከናውን ሳይሆን አንዱን እንዲያከናውን ለሚበልጠውም ቅድሚያ እንዲሰጥ ተልኳል፡፡

እንቅፋት ሲገጥመን ማዘን ፣ መቁሰል ፣ መዘግየት ይገጥመናል፡፡ ብዙዎች እንዳዘኑ ቀርተዋል፡፡ ከሰዎች ጋርም ሲካሰሱ ራዕያቸውን ጥለዋል፡፡ የሳቱ ሰዎች አስተዋቸው፡፡ ሳያስቡት የክፋት ደቀመዝሙር ሆነዋል፡፡ የሚያገኙትን ዕድል ሁሉ የሚጠቅሙት ራሳቸውን ለማስተዋወቅና ሌሎችን ለመንቀፍ ነው፡፡

ስለራሳችን ማንነት መናገር ክፉ ባይሆንም ሥራችን ሲናገር ግን የበለጠ ተአማኒ እንሆናለን። የራዕይ አልባዎች ትልቁ ግብ ራዕይ አልባዎችን ማብዛት መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ ነገር ግን በራዕያችን እኛን የማይፈልጉ ሰዎችን ሳይሆን እኛ የምናስፈልጋቸው ሰዎችን ማየት መቻል አለብን፡፡

ራዕያችንን ከግብ ለማድረስ ስንነሳ የሰዎች ነቀፋ ብቻ ሳይሆን የጤና ፣ የገንዘብ ችግርም ይፈታተነናል፡፡ ሁሉም ከሚሰማና ለሁሉ ለመስጠት ቸር ከሆነው አምላክ እየለመንን ወደፊት መገስገስ ይገባናል፡፡ በራዕያችንም ዝም ብለን ተስፋ የምንቆርጥበት የጠላትን ሹክሹክታ በመስማት ፍሬ አልባ ነኝ የምንልበት የምናየውን እንደ ሕመም የምንቆጥርበት ፣ በደከምንለት ህዝብ የማንረካበት ጊዜ ጥቂት አይደለም፡፡ ሥራችንን በመተው ጥፋት እንዲገዛን የምንፈቅድበት ጊዜ ብዙ ነው፡፡

ለብዙ ጥረቶቻችን ጥቂት ምስጋና እንኳ ስናጣ ፤ ከጊዜ የተነሳ ራዕያችን ሊረከቡ ሲገባቸው ገና ዳዴ የሚሉትን ስናይ ፤ በገንዘብ እጥረት ራዕዩ ለመቆም ሲዳዳ ረጂዎች የሚባሉ ሃሰተኞችን በደስታ ሲረዱ ለእኛ ግን እጃቸው ሲታሰር ስናይ ፤ ከድሆች እየተቀበልን ባለጠጎችን ስናገለግል ሰዎችን ለማሳተፍ ስንነሳ ሁሉም ሲንሸራተቱብን ፤ ስህተታችንን ሲነቅፉ መልካምነታችንን ግን እንዳላየ ሲያልፉብን ፤ በስራው እየጠፉ ለመብሉ የማያራፍዱ ሲገጥሙን ፤ ለአንድነት ጸሎት ብን የሚሉ ለአድማ ሌሊት ሲሰበሰቡብን ፤ ተስፋ ለመቁረጥ እንቃረባለን ለእነዚህ ክፉዎች መልካምነታችንን ለመጣል ማሰብ ትልቅ ውርደት ነው፡፡

ሰይጣን የበጎ ነገር ተቃዋሚ ሆኖ ቆሟል፡፡ የእሱ ጉዳይ አስፈጻሚ የሆኑት ሰዎችም ራዕይን ማሰናከል አይተውም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአገልግሎት ዘመኑ ሰይጣን በአካል የፈተነው አንድ ጊዜ ነው፡፡ በሰዎች ግን ዘመኑን በሙሉ ተፈትኗል፡፡ እርሱ እራሱ እባብና ጊንጡን ትረግጣላቹ በማለት በክፋ ላይ ስልጣን ሲሰጠን ከሰዎች ግን ተጠበቁ በማለት አስጠንቅቆናል፡፡

ሁሉም ነገር ፀጥ ካለ እኛም እየሞትን ነው ማለት ነው፡፡ ከሰራን ግን ጫጫታ አለ፡፡

እነዚህ የህይወት ትግሎች ራዕዩ ግቡን ከመምታቱ በፊት ተሰርተን እንድናልቅ ይረዱናል፡፡
የነጠረ ማንነት የምንቀዳጀው ልንገፋ ባቃተን ነገር ራሳችንን ተሰርተን ስናገኘው ነው፡፡ እግዚአብሔር እንድንገፋው ያስቀመጠው ተራራ ለዘመናት እልፍ የማይል ይሆናል፡፡ ተራራው እንደቀድሞው ቢሆንም እኛ ግን እንደቀድሞ አንሆንም፡፡ ጡንቻችን ይጠነክራል፡፡ ሰውነታችን ይዳብራል፡፡
እግዚአብሔር የለውጥ ስራውን የሚሰራው በሦስት ነገር ነው

★ ችግሩን በመለወጥ

★ እኛ እንድንለወጥ በማድረግ እና

★ ችግሩ እንዳለ እኛን እንዳይጎዳን በማድረግ ነው፡፡
በእነዚህ ሶስት ነገሮች ይሰራል ፣ ጸሎታችንን ይመልሳል፡፡

በመንገዳችን ላይ የሚገጥሙን እንቅፋቶች ምንም ነገር የማይደንቀን ጠንካራ ሰዎች እንድንሆን ያደርጉናል፡፡ እንቅፋቶቹ በራሳቸው አያጠነክሩም ፣ ሰይጣንም እንድንጠነክር ብሎ የሚያመጣው እንቅፋት የለም፡፡ እግዚአብሔር ግን እንቅፋቶችና ፈተናዎቹን እኛን ለማነፅ ይጠቀምባቸዋል፡፡ ችግሮች እንደቀድሞው ቢሆኑም እኛ ግን እንደቀድሞው አንሆንም፡፡

መኖርን የሚያጣፍጡና ሕይወትን እንግዳ የሚያደርጉ ያልተመለሱ ጥያቄዎችና ሩጫዎችን የሚጠይቁ ራዕዮች መቀመጣቸው ነው፡፡
የህይወት ማሳያው ግራፍ ከፍና ዝቅ የሚል ነው፡፡ ቀጥ ብሎ የሚጓዝ በሕይወት ውስጥ ምንም የለም፡፡ በማንኛውም መንገድ እንደትላንቱ አይደለንም።

#ወይ #ከፍ ብለናል ወይም #ወርደናል፡፡

#ቤታችን እንሁን እናንብብ
#አስተሳሰባችንን እናስፋ

እንቅፋቶች ዝም ብለው አይመጡም ከትላንት ችግሮቻችን ተምረን ዛሬን እናሳምር።


ለማንኛውም አስተያየታችሁ @jahABP አድርሱኝ

ዲ/ን አሸናፊ መኮንን
የመጽሐፉ ርዕስ:- ራዕይ ያለው ትውልድ

ሁላችንም ልናነበው የሚገባ መጽሀፍ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN



አቤቱ
"ሰው የራሱን ሀጢያት እየደበቀ የሰውን በሚያወራቀት በዚህ ዘመን ጥፋቴን የመናዘዝ ባህል ስጠኘ፡፡ ሰውን በምፈራበት መጠን እንኳን ብፈራህ እመኛለሁ፡፡
ምንም ባይኖረኘ አንተ አለኸኘ ማለት ኩራቴ ይሁንልኘ፡፡ ብርሃኑ ጨለማ ፣ ጨለማው ብርሃን በሚባልበትና የእውነት መመዘኛ በጠፋበት በዚህ አደናጋሪ ዘመን በእውነትህን ሙላኘ፡፡"

@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ሁለተኛውን መጽሐፍ እንዴት አገኛችሁት??

እንደአስተያየታችሁ ከሆነ እንደወደዳችሁት ተረድቻለሁ አመስግኛለሁ😍🙏😊 ፡፡

ረጃጅም ፅሁፎችን ሳትሰለች አርማ እናንተ ጋር እንዲደርስ ለምታደርገው ትዙዬ😍🙏በእናንተ ስም ላመሰግናት እወዳለሁ፡፡

ሦስተኛውን መጽሐፍ ከመጀመራችን በፊት እረፍት እናደርጋለን፡፡

እስኪ ከዚህም ከዚያም ከአዲስ ሰዎች ጋር ስነጋገር ከጓደኞቼ ጋር ስንከራከር በተለያየ አጋጣሚ ሰዎች ሲመክሩኝ ሌሎቹን ሲያስረዱ ከኔጋርም ባይሆን እርስ በእርስ ሲያወሩ በተለያየ አጋጣሚ መንገድ ላይ ታክሲ ላይ የሰማኋቸውን አባባሎች ወይም ፍልስፍናዎች ማለትም ይቻላል ማስታወሻዬ ላይ(በስልኬ ፣ ደብተር ፣ በጭንቅላቴ አለፍ ሲልም በVOICE RECORD) ካስቀረኋቸው ድንቅ ድንቅ ሃሳቦች ላካፍላችሁ ወደድኩኝ፡፡

እዮባ😍 በዘፈኑ ሲመክረን
"ዝምታ ይከብዳል ከማውራት ማድመጥ ሚዛን ይደፋል" ይለናል ትክክለኛ አባባል ነው፡፡

እኔ መስማት አመሌ ነው፡፡

ሰዎች ሲያወሩ...

እኔ፡- ሚስቶች🙆‍♂ ባሎቻቸውን ስልክ📱 ሲያወሩ እንደሚሆኑት ሁሉ ነገሬ ጆሮ👂 ይሆናል

ለጨዋታው ድምቀት ነው እንዳትቀየሙኝ🙏😜

እና በማድመጤ እነዚህን ላካፍላችሁ ነው፡፡ በህይወትህ በጥሩ ነገር ካሰብነው እንቅፋትም ጠቃሚ እንደሆነ ከላይ ባለው መጽሐፍ በደንብ ተመክረናል ታዲያ ዝም ብለን እያደመጥን በነፃ መመከር ተገኝቶ😊😃 ነው፡፡ እናደምጣለን የሚጠቅመንን እንይዛለን ህይወታችንን ከትላንት የተሻለ እናደርጋለን የተሻለ ብቻ ሳይሆን የበለጠ፡፡

ሳዳምጥ ምንም አልንቅም ሁሉንም አደምጣለሁ አብዛኞቹ ደግሞ ይህ ነገር ከእነሱ መስማት ለኔ ትልቅ ነገር ይሆንብኛል እደነቃለሁ ከህፃናት እስከ አዛውንቶች የሰበሰብኳቸውን እነሆ ልላችሁ እወዳለሁ....ትወዱታላችሁ

🏃‍♂ ቆዩልኝ🏃‍♂

@jahABP ነኝ አስተያየታችሁን አድርሱኝ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

አቤቱ
"እልፍ ዓመታት ሲጠልቁ ፍቅር ብቻ ትኖራለችና አፍቃሪ አድርገኘ፡፡
ይህ ዓለም እንግዲህ ቤት አይሆንምና የሰማይ ተስፋዬ ዘወትር አሳስበኘ፡፡
አፈር ለሆነው ሰው ፍቅር ይበቃዋልና፡፡ እምነቴን ባንተ ብቻ አድርግልኘ፡፡
ሁሉም ቻሉኘ በሚሉበት ዘመን ለሁሉም የትግስትን ፀጋ አድል፡፡"

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
ሁሌም አንድ ነገር አስታውስ

★ እግዚአብሔር አምላክህን ቁርስ ፣ ምሳ ፣ እራት ስጠኝ ብለህ ልትለምነው ትችላለህ ግን መክሰስ ስጠኝ ብለህ ልትጠይቀው አይገባም ይሄ ትልቅ ጥፋት ነው፡፡

★ ወንድሜ አንድ ነገር አስተውል ገመድ ሶስት ሆኖ ይቋጠራል ጠንካራ ይሆናል ዋናው ሚና ሚጫወተው መሐል ላይ ያለው ገመድ ነው፡፡
አንተም ለቤተሰቦችህ እንደዛ ገመድ ሁሉንም ጠንከር አድርገህ ይዘህ ጠንካራ ለማድረግ መጣር አለብህ፡፡


★ የምሬን እኮ ነው ምልህ ምን እንዳልኳት ታቃለህ እኛ ሰዎች እኮ አስጠሊታ ፍጡሮች ነን እስኪ ልብስሽን አወላልቂና መስታወት ፊት ቆመሽ እራስሽን እይው የኡነት አስጠሊታዎች ነን
አስቢው በዛ ላይ እድሜ ሲጨምር ሁሉም ነገር እንደነበረ አይሆንም በውበት ልትመኪ አይገባም፡፡ አልኳት አጠፋሁ??

★ እኔ:- የኔ ቆንጆ😍...የኛ ቤት ድመት እኮ ምንም አይልም አትፍሪው እሺ.....

★ እሷ፡- የኛም ቤት ውሻ እኮ ምንም አይልም አትፍራው እሺ (አታምኑኝም የነሱን ቤት ውሻ ሁሉም የሚፈራው ነው) ስለዚህ የኔ የናንተን ድመት መፍራት አያስገርምህ ነው🤔🤔 የ3አመት ህፃን ልጅ ነች እንዲህ ያለችኝ

★ለመኖር ተጨንቄ አላውቅም ለማወቅ ግን እጨነቃለሁ


★ ቤተክርስቲያን ውስጥ የአዳም ልጆች ሩቅ መስለኃቸው ክፉ መስራታቸው እያለች በተደጋጋሚ ጮክ ብላ ትናገራለች....በግፍ የተነጠቀችውን መልሳ ያገኘች ሴት ጩኸት ነበር፡፡
እውነትም አንተ እሩቅ መስለኸን ስንቱን በድለናል
ስንተ ፍትህ አጓድለናል🤦‍♂🤦‍♂

★ እግዚአብሔር ቅጣቱን ከኛ ቢጀምርስ ኖሮ ካንተ ቢጀምርስ ኖሮ ካንቺስ ቢጀምርስ ኖሮ

★ አንተ እኔን
በፍቅር ሳይሆን በእህትነት ምታስብልኝ ይመስለኝ ነበር.........ትላለች ትንሽ ቆይታ ደሞ እንደዛ አብረን አድረን ስንት ነገር አሳልፈን😂😂😂😂
እህትነት አብሮ ማደር🤔🤔😳

★ዛሬ አላሸክምም እራሴው ነኝ ማመጣው..

★ ሀብታም ነህ ገንዘብህን ለሌሎችም አካፍል እንጂ ሸክምን ስራ አድርገው ስንት ቤተሰብ ሚያስተዳድሩ አሉ እኮ ያንን አትዘንጋ ወዳጄ.....አለው

★በዚህ በኩል ብትሄድ አይሻልም🤔??

★ ሰውዬ ዝም ብለህ ተቀመጥ እንጂ እንዴት ወዴት መሄድ እንዳለብኝ አውቃለው ወይስ መሪውን ለሁለት ነው የያዝነው?😏

★ አስታውስ ንግግርህን በማይረባ ነገር የምትጀምር ከሆነ አዳማጭ ታጣለህ

★ እንዴ አእምሮማ ዝም ብሎ አይወስንም የሆነ ምክንያት ይፈልጋል፡፡

★ አትሸወድ አይን ሁልጊዜም ፈሪ ነው፡፡
ልብነው ደፋር እጨርሰዋለሁ ብለህ ስትጀምረው በጥቂት ደቂቃዎች ታጠናቅቀዋለህ የዛኔ ደስታህን አስበኸዋል.....

★ ወንድሜ ድሮ እኛ ኢትዮያዊያን እኮ ኑሯችን ባያምር ብንጎሳቆልም ማንም ባይረዳንም ቀብራችን ግን የደመቀ ነበር በኮሮና ምክንያት አሁን ላይ ይህም ነው የቀረብን ታዲያ ይህ አያሳዝንም ትላለህ? 🤔

ቆዩልኘ

ሌላጊዜ እንጨምራለን
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

መልካም ዕለተ ሰንበት

ፒያሳ አራዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን😍🙏
🇲🇱🇲🇱🇲🇱🇲🇱
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

የሳምንቱ የመጀሪያ ቀን

የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ለብዙዎቻችን ከዕረፍት ማግስት በመሆኑ የረሳናቸው ጉዳዮች የሚታወሱበት ፀጥ ያሉ ስልኮች የሚጮሁበት ያልተቆጩ ሩጫዎች ድቅን የሚሉበት የሰዓት ተቆጣጣሪዎችና ቁጠኞች አለቆች ትውስ የሚሉበት ነው የረሳናቸው ነገሮች መቀስቀስ የሚጀምሩበት ቀን በመሆኑ የሳምንቱን የመጀመሪያ ቀን "ጨለማው ቀን" እንለዋለን በዚህ የመጀመሪያ ቀን ጌታችንን ካልፈለግን ስሜታችን የጨገገ ነው፡፡

አንድ ሰው በየዕለቱ ሲያገኘኝ፡- "እንኳን አደረሰህ" ይለኘ ነበር፡፡
እንዲህ ሲለኘ ከሰሞኑ ያለፈ በዓል እፈልግ ነበር፡፡ ነገር ግን ዓመት ሙሉ "እንኳን አደረሰህ" የሚለኘ እያንዳንዱ ቀን ልዩ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ ወጣት እግዚአብሔር አስተማረኘ ፡፡

ለካ ትልቁ በዓል መኖር ነው! 🤔😍

አንድ አባት ሲፀልዩ፡- "ሰላማዊ ቀን እዘዝልን" ይሉ ነበር፡፡ ሰላምንና ቀን የሚያዝዝልን እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ሁለቱ የሚገጥሙት በስንት ጊዜ አንዴ ነው፡፡ በፀሎት መንፈስ ግን ሰላማዊ ቀን ይታዘዝልናል፡፡
"ሁሉም ባሪያዎችህ ናቸውና ቀኑ በትዕዛዝህ ይኖራል" መዝ. 118÷91 ይላል፡፡ ቀን እንኳን ሳይቀር የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው፡፡

ዕድሜ ስለተጨመረልን በጣም ልናመሰግን የሚገባን ቀን ቢኖር ፣ የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ነው፡፡ ከዕረፍት አንስቶ ያሰማራን የኑሮ ጉድለት ነው፡፡ ይህ የኑሮ ጉድለት በሥላሴ ጥበብ የጎደለ ነው ሲሆን እኛን የሚያተጋን በመሆኑ ደስ ሊለን ይገባል፡፡ ጉድለት ባይኖር ከቤታችን የምንወጣበት ምክንያትና ኃይል ባልኖረን ነበር፡፡ ባይኖር የመሙላት ደስታ ባልኖረን ነበር፡፡ ሲሞላልን ደስ የሚለን ታላቅ ሐሴት ከጉድለት በኀላ የተገኘ ሲሆን ብቻ ነው፡፡

የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ዘመኑ እየፈጠነ ፣ ወሩ በዓመት ለመተካት እየቸኮለ በመሆኑም ብዙ ጊዜ እናዝንበታለን፡፡ "ቀኑ ይበራል" እንላለን፡፡
ቀኑ አልገፋ ያላቸው ብዙ ወገኖች አሉ፡፡ ለእኛ ቀኑ ሳናስበው የሚሔድ ከሆነ ጣፍጦልናል ማለት ነው፡፡ ያልጣፈጠ ቀን የዓመት ያህል ይረዝማልና፡፡
ሌሊቱ አልፎ ብርሃን ሲመጣ እግዚአብሔር ዛሬን እንድንኖር የዕድሜ ኮንትራቱን አራዝሞልናል አድሶልናል ማለት ነው፡፡

ስለታደሰልን ዕድሜ ልናመሰግን ይገባል፡፡ በህይወት ከሌለን የማንኖረው ለጉድለታችንም ለሙላታችንም ነው፡፡ የሚከብደው የኑሮ ጉዳይ ሳይሆን የሚከብደው እድሜ ነው፡፡
ፍላጎታችን አንድ ባለጠጋ ሊሞላው የሚችል ይሆናል፡፡ ዕድሜ ግን በእርዳታ የምናገኘው ሳይሆን የአምላክ ጸጋ ነው፡፡

ጌታ ሆይ ብዙዎች መኖር እየፈለጉ ይችህን ቀን ሳያዩ አልፈዋል፡፡ ማለፋቸውን በማለዳ ሰምቻለሁ፡፡ እኔ ግን አኑረኘ ብዬ በመፀለዬ ሳይሆን ኑር ብለህ በመፍቀድህ ለዚህ ደርሻለሁና አመሰግንሃለሁ፡፡

ሳምንቱን ከአንተ ጋር እንዳሳልፈው ፣ ያቀድኩት ሳይሆን ያቀድክልኘ እንዲሆን እማፀንሃለሁ፡፡ የማይኖሩበት ቀን እንደተቀበሉ ሰዎች ሳይሆን ካንተ ጋር ዕድሜያቸውን እንደሚያጣፍጡ ሰዎች አድርገኘ፡፡ የምኖር ያልመሰሉኘ የፈተና ቀኖችን አሳልፌያለሁ፡፡ ስታኖረኘ ደግሞ ደስ እንዲለኘ እርዳኘ፡፡ ያለኘን ነገር የማከብረው ከእጄ ሳጣው አይሁንብኘ፡፡ ጌታሆይ! በዚህ ቀን አንተ ቅደም ፣ እኔ በጽድቅ በቅዱስ ፍርሃት ልከተልህ፡፡ ሰላምን በዚህ ቀንና ሳምንት እዘዝልኘ፡፡

ዲ/ን አሸናፊ መኮንን ረቡኒ ከሚለው ትንሽዬ መፅሐፉ ላይ እንዳሰፈረው፡፡

መልካም ቀን መልካም ሳምንት ተመኘሁ

አስተያየታችሁን @jahABP አድርሱኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
ሰላም ውድ AB PHOTOGRAPHY

ተከታታዮች አሁን ሁላችንንም ባማከለ መልኩ ኢንተርኔ ተለቋል

ስልካችሁ ያለኘ በቴሌግራም የተዋወቅን ዕሁድ ዕሁድ በምልከው መልዕክት ለመገናኘት ችለናል እረፍ ባደረግንበት ጥቂት ጊዜ ያከኘኀቸውን ያስተምራሉ ያልኳቸውን ፅሁፎች እንዲሁም በስራ አጋጣሚ ስዘዋወር ያነሳኀቸውን የተለያዩ ፎቶዎች ለማጋራት እሞክራለሁ፡፡

ግን ይህ ሚሆነው ከአንድ ወር በኀላ ነው፡፡ በስራ ምክንያት የጊዜ መጣበብ ስለገጠመኘ ነው፡፡ ካሰብኩት ጊዜ ቀድሜም ልመለስ ምችልበት እድል ይኖር ይሆናል፡፡

በትግስት እንደምትጠብቁኘ ተስፋ አለኘ

የተለያዩ መፅሀፍትን ማንበብ አንርሳ መልካምነት መረዳዳት ይቅርታን አመሰግናለሁ ማለትን ልምዳችን እናድርግ፡፡🤗

🙏መልካም ጊዜ🙏
አሳድገህ ለዚህ አድርሰኸናልና ቅዱስ ዑራኤል ሆይ ሁሌም ከፍ ከፍ በልልን🙏🙏😍😍😍
ትልቁ በዓል መኖር ነው፡፡
ይኸው ስላለን ዛሬ ላይ ደርሰናል
መልካም በዓል ከነመላው ቤተሰቦዎ፡፡
መልካምነትን መረዳዳት ይቅርታ እና አመሰግናለሁ ማለትን ልምዳችን እናድርግ፡፡
በዓሉን ስናከብር በጥንቃቄ ይሁን መርዳት መቻል እድል ነውና ለድሆች ያለንን በማካፈል ነፍሳችንንም እናስደስታት 😊🙏😍

AB photography & graphic design
AB PHOTOGRAPHY

ግድቡ የኔ ያንተ ያንቺ የሁላችንም ነው!!!፡፡
🇲🇱🇲🇱🇲🇱
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

በረሃብ ዘመን የጠገብኩብሽ ምግቤ ከጥም መንከራተት የረካሁብሽ ጥሩ ውሃዬ ሐፍረቴን የሸፈንኩብሽ ነጭ ልብሴ ዞሮ መግቢያዬ እናቴ ሆይ አመሰግንሻለሁ፡፡ እኔ ላንቺ ከማስፈልግ ይልቅ አንቺ ለኔ ታስፈልጊኛለሽ ለበጎ ስራ እንጂ ለሀጢያት እንደማይደክመኘ ራሴን አይቼዋለሁ፡፡

በዚህ ጓጉተን በምንጠብቀው ፆም የምህረት እጅሽን በእኔ፡እና የኔ በሆኑት ላይ ይደር፡፡
እንኳን ለፆመ ፍስለታ አደረሳችሁ፡፡
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

እሱ:-የተቀደደ ወረቀት ነው🤔፡፡

እሷ:- የተሰበረ መስታወት ነው🤔፡፡

እኔ:- መብረቅ ነው፡፡😜😜
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

እመጣለሁ!!!

ሐኪም ቤት ቁጭ ብለናል ዶክተሩ እስኪወጣ እየጠበቅን ነው፡፡ የሐኪም ቤቱ ንፋስ በየት በኩል እንደሚነፍስ አናቀውም እየበረደን ነው......እግሬን ይበርደኛል ጆሮዬን ይበርደኛል...እጄ ወደመደንዘዝ ጀምሯል


"ጠንካራ መሆን አለባችሁ" አለችኘ.....

ከገባሁበት እራሴን የማሞቅ ሰመመን ነቅቼ እ አው...ልክ ነው አልኩኘ፡፡

አንድ ታሪክ ላጫውትህ የአሁን ወጣቶች መጠንከር አለባችሁ በጣም ጠንካራ መሆን አለባችሁ ይህን ስልህ እኔ ከሷ ጠንካራ መሆንን ተምሬያለሁ....እሷን አወካት አይደል አንዴ ምን እንዳደረገች ታውቃለህ.....ሐኪም ቤት ሰው እያስታመመች ነው ለሊት ላይ ሰውየው ሞተባት

እእእ🤦‍♂😱😱😳.....እሺ ቀወጠችው ስል

ወይ አንተ........ብላ.......


"አለማየሁ ዋሴ ሰበዝ በሚለው መፅሐፉ አስገርሞናል....ከሱም እንመዛለን የኔ ፕሮፌሰር ብሎ ይጀምርና ዝም ብለህ ተናገር ይለናል ለሀገራችን ቦለቲካ
እኔ ከሞትኩም ሰርዶ ይብቀል ይለናል
አማርኛ ቋንቋ በክብር አስጨብጭቦ አመጣኘ ይለናል
ብዙ ብዙ ይመክረንና አልጨረስክልኘም ብሎ በቁጭት በንዴት ይዘጋብናል..... "


ከሩቅ ከሬዲዮ ይሁን ከቴሌቪዥን
" ኢትዮፕያ ለዘለዓለም ትኑር" የሚል ድምፅ ይሰማኛል ምን የሚሉት የቂል ወሬ እንደሆነ ሁሌም ይገርመኛል ሁሌም ዘለዓለም ማንም እንደማይኖር እየታወቀ እያወቁት ያውም ኢትዮፕያ....ለዘለዓለም ሃሃሃሃሂሂሂሂሂሂሂ 😂😂😂 በዚ ካልሳኩማ በምን ልስቅ ነው ሃሃሃሃሃ ይሔ ሞኘ ህዝብ መቼ ይሆን ሚነቃው ኤዲያ.............አጭሩ ወግ ይቀጥላል....🏃‍♂


እዚ ማዶ አኔ እና እሱ እያወጋን ነው፡፡ ኡነቴን ነው ምልህ አብያ ይሔ ጨለማ አይንጋልኘ ብሎ ይምልልኛል፡፡

እዛ ማዶ ያለው ደሞ ኧረ ለኛ ሲል ይንጋ.....ይላል

በማስክ የተወራው ወሬ ለኔ በቅጡ ያልተሰማኘ እዛ ማዶ ተሰማ፡፡ መጀመሪያ ሳቄ ነው ያመለጠኘ
ኧረ ለኛ ሲል ይንጋ😂🤔🤔ተፈላሰፈ እንዴ😳 ኡነትም ግን እንደ አንዳዳችን ፍላጎት ቢሆን እኮ ይቺ አለም አትነጋም ማለት ነው🤔🤷‍♂፡፡ ይህንን አዝናኘ ወግ እንመለስበታለን፡፡

ብዙ ሰው እኮ አንተ ጎበዝ ነህ ማለት አይፈልግም ለአንተ ሊልህ አይፈልግም ስራዎችህን አይቶ ድንቅ እንደሆነ እያወቀ ስህተቱን ለማውጣት ይሮጣል ይህ የኔ በምትላቸው ሰዎች ይብሳል ይህንን ሁሌም አትርሳ ምርጥ እንደሆንክ ያቁታል እነሱ ስላሉህ ስላላሉህ ብለህ አንድም ደቂቃ ከአላማህ እንዳታዛነብል....ይሔ የሁል ጊዜ ምክሬ ነው፡፡

PEOPLE ALWAYS GO AWAY DON'T FORGE THAT.👊

ከራሴ ከምለው ሰው ጋር ያደረኩት አስደናቂ ቆይታ.....ቃለምልልስ ልለው እችላለሁ ረጅም ሰዓት አውርተናል እኔም እጠይቃለሁ እሱም አይሰለቸውም ይመልስልኛል.......

እኔ፡- እስኪ ስለሴቶች አውራኘ አብሶ ስለዘመኑ ሴቶች?

እሱ፡- በመጀመሪያ ሁለታችንም ምንስማማው አንድ ነገር አለ ...አይደል🤔

እኔ:- አዎ አዎ በአሁን ሰዓት ሴት ልጅ መውለድ አያስፈልግም የሚል አስተሳሰብ እንዳለን አውቃለሁ፡፡

እሱ፡- በኡነት101% ልክ ነን መቼም መቀየር የለብህም ይህን አስተሳሰብ፡፡

ፈጣሪን እንለምነዋለን ወደፊት ካገባሁ ካገባሁ ነው ያልኩት አግብቼም ከወለድኩ ሴት ልጅ አትስጠኘ ብዬ እማፀነዋለሁ ኧረ ሴትነት ፈተና ውስጥ ገብቷል ወንድሜ ለአብለጭላጩ ዘመን እጃቸውን ሰጥተዋል
የቤተሰብ እልህ አይታያቸውም
ሀሳባቸው ቅንጡነትን ነው ቅንጡ እቃ ነው ቤተሰብ ኖረው አልኖረው ፍቅረኛዬ ኖረው አልኖረው አይታሰብም አንተ ካላመጣህ ስንት ያልኩትን ሚያመጣ ወንድ ሞልቷል ሚሉ ይመስለኛል በልባቸው ደሞም ይላሉም እንጂ ሂሂሂሂሂ በትንሽ ብርም ተገዝቶ የተገዛበትን ማዋደድ ነው ሆኗል ስራቸው ተገላልጦ ለመታየት ጡትና ቂጥን ለማሳየት የሚደረግ ሩጫ ነው መላ ሰውነትን ለማሳየት እከሌን ለመሆን የሚደረግ ሩጫ ነው በአሁን ሰዓት ሴትነት.......እያለ ይቀጥልና ይህን ማድረግ ግን መብታቸው አይደለም አላልኩም ግን ልኩ ምንድነው??
እሱ እራስን መጠየቅ ነው፡፡
ግን ይሔ የኔ የአንድ ተራ ሰው አሳብ ነው ሴቶች ላይ ያለኘ.....ለራሴ ልክ ነኘ እና ደግሞ የኔም ያንተም አብዛኛው ጀለሶቻችን ሴቶች መሆናቸውን መዘንጋት የለበትም፡፡

ግን የአንተን የተወሰኑ ሴት ጓደኞችህን ሳላደንቅ ማለፍ አልፈልግም ከነገርከኘ አንፃር ወይም የዋህ ስለሆንክ እነሱ አሳምነው ነግረውኸም ሊሆን ይችላል፡፡ ማለቴ ዋሽተውህ😂😂👊👊

እኔ፡- አይ ውሸት አይደለም እኔም ምኮራባቸው አሉ እንኳንም አወኳቸው እንኳንም ጓደኞቼ ሆኑ ምላቸው፡፡

እሱ፡- በነገራችን ላይ.............አለች?? አንተ እኮ ምትገርም ሰው ነህ

እኔ፡- አይ እሱን ተወው ሌላ ጥያቄዬን ልቀጥል

እሱ፡- ጎበዝ ወዳጅ ነህ ለማለት እደፍራለሁ አፍቃሪ ለመሆን አትችልም አፍቃሪ ሚባል ነገር የለም፡፡ ይቅርታና አንድ ምኞት ልመኘ??😃

እኔ፡- እሺ

እሱ፡- ሁሌም ለራሴ እንደራሴ አይነት ጓደኛ ባገኘ እመኛለሁ.......ይህን ምኞቴ ላንም ጨምሬ መመኘት ጀምሬያለሁ እንደ አንተ አይነት ሰው እንድታገኘ እመኛለሁ፡፡

እኔ ፡- እሺ አመስግኛለሁ😍🙏

በጋዝ ተከቦ ትንንሽዬ ነጠብጣቦች ከታች ወደ ላይ ከሚፈነዳው ስፕራይቱ ተጎነጨ....
ምንም አይደል የሚል ፈገግታን ለገሰኘ

እኔ፡- ስለ ውሸት እናውራ

እሱ፡- ዛሬ ስለሴቶች ነው እንዴ ልናወራ የመጣነው.................😂😂😂😂😂ረጅም ሳቅ በሁለታችንም መካከል😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂 ha ha ሂሂሂሂሂሂ ሃሃሃሃሃሃ....ኧረ ልታስገድለኘ አይደል ሃሃሃሃሃሃሃ አንተ እራሱ አንድ አባባል እኮ አለህ አይደል......ሂሂሂሂሂሂ ልጀምረው፡ጨርሰው በናትህ.....ሂሂሂሂሂ 😂😂በ ጣቱን ወደኔ እየጠቆመ አይ አንተ ይለኛል


ሴቶች ውሸት ስለሚወዱ.......እ ቀጥለው


እኔ:- ወንዶች ውሸታም ሆኑ ነዋ፡፡

ረጅም ሳቅ😂😂😂😂😂😂😂

ውሸት ስለሚወዱ ወንዶች ቆንጅዬ ውሸቶችን እየፈጠሩ በጠረባ እየጣሏቸው ነው፡፡
እንዲህ እያልን ቀጥለነዋል ሙሉውን እቀጥለዋለሁ...🏃‍♂🏃‍♂



ግራጫ ቃጭሎችን አስታወሳችሁት አዳም ረታ ..........መዝገቡ.........መዝጌ......እሱን እኮ በአካል አገኘሁት🙈 እንዴት? የት? መቼ?...🏃‍♂🏃‍♂ ከመዝገቡ ጋር ያደረኩት አጭር ቆይታ
እኔ እእ እና አባቴን እጠላቸዋለሁ እጠላቸዋለሁ ይለናል.....፡፡



ሌሎችም አሉ እንቀጥላለን

ማንበብ ማንበብ መፅሐፍን ብቻ ሳይሆን ሰዎችንም ተፈጥሮንም ስሜትንም ንግግርንም ፊትንም ሳቅንም ሀዘንንም ድምፅንም ዝምታንም ጫጫታን ሁሉንን ማንበብ..ከዛ ከራስ ስሜት አንፃር መገምገም አንዱን መጣል አንዱን ማንሳት እንደሚጠቅመን አድርገን መስራት ለኛ ብቻ ሳይሆን ለማህበረሰባችን እንዲጠቅም አድርገን ጭምር እንጂ ፡፡

@jahABP ነኘ ማንኛውም አስተያየታችሁን አድርሱኘ፡፡ 🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD