Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
AB PHOTOGRAPHY

ድንግል ሆይ ሞትሽ ሞታችን ትንሳኤሽ ትንሳኤአችን ነው፡፡😍🙏😍

ምህረትሽ ቸርነትሽ የበዛ መዓትሽ የራቀ ትዕግስትሽ የሰፋ የመልካም የአሳቤ ፈፃሚ የምኞቴ መሉላት ስምሽ ድንቅ የሆነ የጌታዬ እናት ሆይ አመሰግንሻለሁ፡፡

በድካሜ ብርታትሽን ትገልጫለሽ በሞኘነቴ ትጠበቢያለሽ ማንነቴ አይገርምሽም አፅድተሽ የክብር ዕቃ ታደርጊኛለሽ፡፡

ይቅርታሽ እንደ ቀስተደመና ከቦኛል፡፡
በኔ ላይ ስራሽ ከትላንት ዛሬ ያስገርመኛል፡፡

የኑሮዬ ድምቀት ፣ የቋንቋዬ ጥራት፣ የመኖሬ ትርፍ የመንገዴ መጨረሻ አንቺ ነሽ፡፡

🙏እንኳን አደረሳችሁ፡፡😍
አብይ አንዷለም(የማርያም ልጅ)
😢😭😭😭💔💔🤦‍♂🙇

አስሳውሳለሁ የዛሬ ሦስት አመት ነው ትውውቃችን ከወንድሜ ጋር አንድ ክፍል ነበሩ የአርት ሰው ስለነበረች ወንድሜ እንድተዋወቃት ጋበዘኘ ገራሚ ገራሚ ግጥሞችን የምትፅፍ ግጥሞቿን አድናቂ እንደሆንኩ እና እንደምናሳትማቸው እምነት ነበረኘ ቃላቶቿ ሃይል ነበራቸው እሷ ስታነባቸው ግጥሞቿ በእውቅ ደራሲ የተፃፉ ይመስላሉ፡፡


ደስ ምትል ሳቂታ ተጫዋች ልጅ ነች ግን ብዙ ሃላፊነት የተሸከመች በብዙ ሃሳቦች የተወጠረች ልጅ ናት ሃሳቧ እሩቅ ህልሟ ትልቅ ነው...ለቤተሰቦቿ ስትል መስራት ያለባትን ብቻ ሳይሆን ከዛም በላይ ሆናለች፡፡ ጥንካሬዋ ይገርመኘ ነበር እራሴን ዞር ብዬ እንዳይ ያደርገኘ ነበር፡፡

ግራፊክስ ዲዛይን ትምርት የጀመርኩበት አመት ነበርና....እንዲህ አልኳት ግራፊክስ ትምህርት ጀምሬያለሁ አልኳት ተደሰተች.....እኔም ቃል እገባልሻለሁ የዛሬ ሦስት አመት ስትመረቂ thank you card እኔ ነኘ ምሰራልሽ አልኳት አብዬ አመሰግናለሁ የዛ ሰው ይበለን አለችኘ አሜን አሜን ተባባልን በትምህርቷ ጠንካራ ነበረች ብዙ ነገሮችን አውርተናል ስለሷ ብዙ አውቃለሁ እንገናኛለን ተባብለን በኔም በሷ የስራና የትምር ውጥረት ሳንገናኘ ቀርተናል ዘንድሮ የዛኔ ያልነው ሦስተኛ አመት ደርሶ ኮሮና አስቀረውና ለመስከረም በተሸጋገረው ምርቃታቸው እንደወንድምነቴ ቃሌን ልፈፅም thank you card እና የፎቶግራፊውንም ስራ ነገር ግዴታዬን ልወጣ ቀናትን ስንጠብቅ፡፡

ትላንት አስደንጋጭ መርዶ ለወንድሜ ደረሰው ፂዮን አርፋለች አሉት ደውለው በጣም አዘነ በጣም ለኔም ነገረኘ በጣም አዘንኩ ከልቤ😱😢😢😢😢😢😭😭💔💔💔
ማርያምን ከልቤ አዘንኩ በዚ ሰዓት መሞት አልነበረባትም ወንድሜ ለማረጋጋት አይ ሁለት ፂዮኖች ነው ያሉት አላጣራሁም አለኘ ቆይቼ አጨናነኩት እሱም እያዘነ እሷ ነች አለኘ ይበልጥ ልቤ ደማ አለም ከንቱ ሁሌም ለለፋላት የማትሆን ወጣቷ በአጭር ተቀጨች ስንት ጠንካራ ራዕይ የነበራት ፂዮን አጣናት ምርጥ ጓደኛዬን አጣኀት በጣም አዘንኩ ሁሌም በልቤ በልባችን ትኖሪያለሽ ፂዮንዬ አምላክ ነፍስሽን በአፀደ ገነት ያኑረው 💔😔😢😢😭😭 የምቶጃት እመብርሃን ከደጋጎቹ ጎን ታኑርሽ የውስጥሽን እሷው ታውቃለችና፡፡

እኔ ግን የልቤ ሀዘን ጥልቅ ነው፡፡

ልቀብራት እንኳን አልቻልኩም ምክንያቱም የተነገረን የሰልስቷ ጊዜ ነው፡፡
ይቅርታሽን እንደምትሰጪኘ እምነቴ ነው፡፡ እወድሻለሁ በኡነት እወድሻለሁ ልቤ ተሰብሯል ማመን አቅቶኛል

የተለየሽን ምክንያቱን ባላቅም

በተደጋጋሚ እንደሚያምሽ ነግረሽኘ ነበር
ያንቺን ህመም መከታተል የኔም የወንድምነቴ ድርሻ ነበር እኔ ግን ከንቱ ከማውራት ውጪ ምንም ላመጣ አልቻልኩም ይቅርታ አድርጊልኘ😢🙏...ፂ ይቅርታ አድርጊልኘ😢😢😢ሃዘኔ ጥልቅ ነው፡፡ ማርያምን ሃዘኔ ጥልቅ ነው፡፡😢😢😢😢😭😭😭😭😭😭😭😭
AB POHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ይህን ታሪክ የሆነ ጊዜ ላይ እንዳነበቡኩት አስታውሳለሁ፡፡

ልጅ እና አባት በባቡር እየሔዱ ነው

ከዛ ልጅ፡- በመስኮት እያየ አባ ያ ምንድ ነው ይላል
አባትም ልጄ ያ ዛፍ ጀው ይለዋል

ልጅ፡- አሁንሞ አባዬ ያምንድ ነው ይላል

አባት፡- ልጄ ያ ፎቅ ነው ይለዋል....

ልጅ፡- አሁንም በድጋሚ አባዬ ያ ምንድነው?

አባት፡- አሁንም ሳይሰለች ያ ምትመለከተው የመንገድ መብራት ነው ይለዋል

ልጅ፡- አሁንም ይጠይቃል....

አባት ያለመሰልቸት ይመልሳል

ከዛ ባቡር ውስጥ ያሉት ሰዎች ደሞ ባክህ ይሔን ልጅ አፉን አሲዘው ምንድነው የማይረቡ ጥያቄዎችን ሚጠይቀው ብለው አባትየው ላይ የስድብ ውርጅብኘ ያወርዱበታል...

አባትየውም፡--------ይቅርታ አድርጉልን ልጄ በደረሰበት አደጋ አይኑ ማየት አይችልም ነበር አሁን ነው ከሆስፒታል ተሽሎት የወጣው ለዛ ነው ይሔን ሁሉ ጥያቄ ሚጠይቀኘ አላቸው፡፡


አንዳንዴ በህይወታችን እንደዚ አይነት ነገሮች ይገጥሙናል ስለ አንድ ሰው ቀርቦ ከማወቅ ይልቅ በሩቁ መጥላት ለምን እንደዚ እንደሆነ ሳናውቅ እከሌ እኮ ተቀየረብነ ምናምን እያልን የሰውን ስሜት እንሰብራለን ግን ምክንያቱን ማወቅ ችግሩን እንድንቀርፍ ያደርገናል፡፡

😊😊😊
@jahABP ነኘ🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

በፈገግታ የተሞላ ቀን ይሁንላቹ መልካም የስራ ቀን
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#ኩርኩም

አዎ አጥፍቻለሁ ለጥፋቴም ቅጣት ይገባኛል፡፡

በአለምና በእጄ ባለው ስኩራራ ስለዚህ አለም ስጨነቅ የላይኛውን ፈጣሪ ስረሳ.....ሀጢያትን ሳበዛ ተስፋ ወደ መቁረጥ ስቃረብ የፀሎትን ዋጋ ስረሳ

ሀይለኛ ኩርኩም ያስፈልገኛል

በእጅ አይደለም ታዲያ ጢኒጢየዋ መፅሐፍ መደርደሪያዬ ላይ የሳቸውን መፅሐፍ አነሳለሁ እገልጣለሁ......እራሴን እወቅስበታለሁ እያነበብኩ ቃላቶቹ በሰውጅ ከምመታው ኩርኩም በላይ ያሙኛል.........ብዙ መፅሐፍትን ፅፈዋል ዕውቀታቸው ጥልቅ ነው ወጣቱን ትውልድ ይታዘቡታል እያንዳንዱ መፅሐፋቸው በተለያየ ቋንቋ ተተርጉሟል ቃላታቸው ሃይል አላቸው ስታነቡት እሳቸው በጆሮ መተው የሚናገሩ ነው ሚመስለው....

በተለይ በዚ ሰዓት እኛ ወጣቶች ኩርኩም ያስፈልገናልና ከሳቸው መፅሐፍ ትንሽ ልቆንጥር🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂


በፊት ብዙ ጊዜ አሁን ደግሞ አንዳንዴ በራሴ እታበያለሁ ሁሉንም እችላለሁ እላለሁ እዚጋም እዛጋም መግባት ያምረኛል፡፡
ነፍስ ገዝቼ የሱን ዘፈኖች ሰምቼ ቀጥሎ አዳምጬ ደጋግሜ አዳምጬ ወይ ጉድ እላለሁ የትአባትክንስና ሰው ሁሉንም ነገር አይችልም ብሎ በኩርኩም ይለኛል፡፡

ሬጌ ምት ነው ለመስማት አይቸግርም የኢትዮፕያው የሬጌው ንጉስ ዘፈኑን ቆንጆ አድርጎ ይጫወተዋል #በእዮባ ድምፅ አድርጎ ገጣሚው ይመክረናል....ይገስፀናል እንዲህም ይለናል.....🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂


እመለሳለሁ አብረን እንኮሮኮማለን🙇🙇

@jahABP ነኘ😊🙏
#ኩርኩም 1

የእግዚአብሔርን ዕርዳታ የረሳን እንደሆነ በእርግጥ እኛ ደካሞች ነን፡፡

እግዚአብሔርን የሚያመልክ ሰው ብቻውን አይደለምና፡፡
ሰው በባህርዩ ደካማ ቢሆንም በእግዚአብሔር እርዳታ የማይችለው ነገር የለም፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ "ሀይልን በሚሰጠኘ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ፡፡" በማለት እንደተናገረው፡፡

የሚፀልይ ሰው ከእግዚአብሔር ሀይልን ለማግኘት ይፀልያልና ደካማ አይደለም :- ፀሎቱም ሃይልን ታደርጋለች፡፡ በህይወቱ ውስጥ በበረከትና በረድኤት ስራውን ይሰራል ይህም በሀጢያት ላይ ኃይልን ይሰጠዋል፡፡

ዳዊት እኔ ደካማ ነኘ- እግዚአብሔር ይረዳኛል ባይል ኖሮ ጎልያድን ባልተዋጋ ነበር፡፡
ጎልያድ ግዙፍ ነው ባለብዙ መሳሪያ ነው ሊፈራው ይችል ነበር፡፡
ዳዊት ማንም እንዲዋጋ አልጠየቀውምየጦር መሪዋች ሳኦልነ ጨምሮ ግልያድን ፈርተውት ነበር፡፡ ስለዚህ ዳዊት እኔ ደካማ እና ትንሽ ነኘ ለማለት በቂ ምክንያት ነበረው፡፡ እግዚአብሔር ግን አደፋፈረው ሁሉም ሰዎች የሁኔታውን ክብደት ተረድተው ነበርዳዊት ግን በእምነት ለድል በቃ፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ልንፈፅመው የማንችለውን እንድም ፈፅም አያዝምና የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ከባድና አስቸጋሪ እንደሆኑ ማሰብ የለብንም፡፡ ፈጣሪያችን ያዘናል የምንፈፅምበት ሀይል ይሰጠናል፡፡

ከትዕዛዛቱ ጋር ደግሞ ፀጋው አለ፡፡
ያለበለዛ ሊውጠን እንደሚያገሳ አንበሳ ሆኖ የመጣውን ሴጣን መቋቋም ባልተቻለ ነበር፡፡

አባታችን አብርሃምም የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ከብዶትየታዘዘውን ከመፈፀም አልገታውም፡፡ በእርጅና ያገኘውን ልጁን ለእግዚአብሔር እንዲሰዋ ሲጠየቅ እምቢ አላለም፡፡ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ለመፈፀም አልችልም ብሎ አላመካኘም፡፡

ይቀጥላሉ.....

ለኃጢያት በምንም መንገድ ቢሆን ሽፋን የሚሆን ስያሜ ሊሰጠው አይገባም፡፡
ኃጢአት በኃጢአትትነቱ ልናውቀውማ ልንሸሸው የሚገባ ጠላታችን ነው እንጂ ለአእምሮአችን እንዲመች የቅድስና ስም እየሰጠነው ራሳችንን የምንሸነግልበት መሆን የለትም፡፡ እውነቱን እንናገር ከተባለ ማንኛውም ኃጢአት በሚሰራው ሰው ዘንድ የመሸፈኛ ሌላ ስያሜ አለው፡፡

በዚህም የተነሳ ኃጢያተኛው ንሰሃ አይገባም በዚህ የመጽናኛና የሽፋን ስያሜ እራሱ እያእያታለለ በኃጢያት ይኖራል እንጂ፡፡

ሲጃራ የሚያጨስ ሰው በማጨሱ የሚደሰትበት መሆኑን እንጂ ኃጢአት እየሰራ መሆኑ ስለማያስብ፡-ማጨስ ደግሞ "የደስታ ምንጭ" የተሰኘ የተሳሳተ ስያሜ ስለጠሰጠው የሚያጨሰው በዚህራሱን እያታለለ ማጨሱን ይቀጥላል እንጂ ንሰሃ አይገባም፡፡ ጭፈራም "ጥበብ" ወይም "አርት" ስለተባለ፡- ዝሙትና ማመንዘር (ፍቅር) ስለተሰኘ፡- የሚፈፅሙት ሁሉም ኃጢያት እንደሰሩ ስለማያስቡ፡ንሰሃ አይገቡም፡፡

ሰዎችን ለማሳሳቅ ብለው አንዳንድ ሰዎች በቀልድ ሽፋን በሌሎች ሰዎች ያሾፋሉ በዚህም የሰው ህሊና ይጎዳሉ ፣ ይዋሻሉ የኃጢአት ቃላትን ይጠቀማሉ በዚህም የተነሳ ብዙ ሰዎች ኃጢአትን ይሰራሉ፡- በእነዚህ ሰዎች አመለካከት በሃሳባቸው እየቀለዱ እንጂ ኃጢያት እየሰሩ ስላልሆነ ንሰሃ አይገቡም፡፡

ከዚህ ሁሉ በተቃራኒ ደግሞ ጭካኔም "የበግ ልምድ ለብሶ" የሚቀርብበት ወቅት አለ፡፡
ለምሳሌ ጨካኘ አባት ልጅን በሥነ-ስርአት እንደአሳደገ ራሱን ይቆጥራል እንጂ ጭካኔው ሀጢያት መሆኑን አያስብም፡፡ በመፅሐፍ እንደተፃፈውም "በቁጡነቱም ጽድቅን የሰራ ይመስለዋል" ነገር ግን ቅዱስ ዳዊት "አቤቱ በቁጣህ በአትቅሰፈኘ "ያለውን ዘንግቶታልና ይህን ስራውን እንደ ኃጢአት ላይቆጥረው ይችላል፡፡

ሰው የሚወደውን ኃጢአት የተቋቋመ እንደሆነ በመንፈሳዊ ሕይወቱ ባለድልና አሸናፊ ይሆናል፡፡
ኃጢአትን መቋቋም አሸናፊ የሚያደርግ ከሆነ ብዙውን አጢአት ተቋቁሞ በአንዱ መውደቅ ረብ የሌለውና የማይጠቅም ስለሆነ በኃጢአት ሁሉ ላይ አሸናፊነትን ለመቀዳጀት መጣር ያስፈልጋል፡፡

ምክንያቱም ጠላታችን ሴይጣን ልንቋቋመው ባልቻልነው ኃጢአት ገብቶ በልቦናችን ግዛቱን ካስፋፋ በኀላ ከፈጣሪያችን ሊለየን ይችላልና ነው፡፡

አንዲት የመርፌ ቀዳዳ በምታክል ቀዳዳ ግዙፉ መርከብ ለመስመጥ ታበቃዋለች ፣ አንዲትም ነቁጣ ዕድፍ ያማረውን ሸማ ታቆሽሸዋለች ፣ አንዲጥ ጠብታ ቀለም ብርጭቆ ውስጥ ያለውን ንፅህ ውኃ እንዳይጠጣ ታደርገዋለች በሌሎች ትምህርቶች ሁሉ ጥሩ ውጤት ያመጣ ተማሪ በአንዱ ቢወድቅ ሊመረቅ አይቸልም በመሆኑም የወደቀበት ትምህርት እስኪያልፍና ጥሩ ውጤት እስኪያመጣ ድረስ መማርና ማጥናት አለበት፡፡

የታመመ ሰው ከመላ አካሉ አንዱ በሽታ ቢሆን የታመመው አካሉን ክፍል ተመርምሮ መታከም አለበት፡፡ ኃጢአትም እንዲሁ ነው መንፈሳዊ በሽታ የነፍስ ደዌ ነውና ትንሽም ቢሆን አንድም ቢሆን መታከም ያስፈልጋል፡፡

ጾመኛ ሰው ምግቦች ሁሉ ቢተው ነገር ግን የሚወደውን ምግብ መመገቡ ባያቆም አልጾመም፡- የሚወደውን እያደረገ ነውና፡፡
መፅሐፍም "ሕግን ሁሉ የሚጠብቅ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከ ልማንም ቢኖር በሁሉ በደለኛ ይሆናል፡፡" በማለት ያስገነዝባል፡፡

ከእግዚአብሔር አብልጠን የምንወደው ነገር መኖር የለበትም፡፡
ለእግዚአብሔር ስላለን ፍቅር ግን ሁሉን መተው ይገባል እንጂ፡፡
ከእግዚአብሔር አብልጠን የምንወደውና ከእግዚአብሔር የምናወዳድረው ነገር ካለ ሀጢአት ነው፡፡

እግዚአብሔር ግን በልባችን ከእርሱ በቀር ማንም እንዳይኖር ስለሚሻ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኘ" ይለናል፡፡ ልባችንን ለእግዚአብሔር የሰጠን እንደሆነ ሀጢአት ከእኛ ይርቃል፡፡

ልባችን ከእግዚአብሔር የራቀ እንደሆነ በእኛና በእርሱ መካከል እንቅፋት የሆነ ፈቃደ ሰይጣን ኃጢአት ይገባል በልባችን ያለውን ፍቅረ እግዚአብሔር ይከፍልብናል ይቀንስብናል ከእግዚአብሔር የበለጠ ኃጢአትን እእድንወድ ያደርገናል ከአምላካችንም ያጣላናል፡፡

የመፅሐፍ ርዕስ :- የንሰሃ ሕይወት

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሸኖዳ ፫ኛ የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ፡፡

ውርስ ትርጉም:- ቀሲስ እሸቱ ታደሰ ወንድም አገኘሁ

ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ፡፡

ታነቡት ዘንድ ግብዣዬ ነው እራሳችንን ቆም ብልን እናይበታለንና እንኮረኮምበታለንና፡፡

ጥፋተኛ እንደሆንን ማመን ጥሩ ነው፡፡ ያንን ካመንን ለይቅርታ እንዘጋጃለን ለጥፋታችንም ቅጣቱን መቀበል የተገባ እንደሆነም እናምናለንና ለጥፋቱም ሌሎችን ሳይሆን እራሳችንን እንወቅሳለንና፡፡

መልካም ቀን😊🙏


@jahABP አስተያየታችሁን አድርሱኘ

እቀጥላለሁ.....🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በሸንጎ ተጀንኘ

ፍቅሬን በግልጥ ፣ በአደባባይ
ደስታየን በድንጋይ ሰሌዳ ላይ

መናዘዜ
ቅሬታዬን በደብዛዛ ርሳስ
መከራየን በለሆሳስ
ጭንቄን በምስጢር መያዜ

ካዘናጋሽ

አንድ ቁምነገር ላውራሽ!

ተከፍቼ

ግና ፊቴ ላይ የብርሃን ዱቄት ነፍቼ
ምድር አትችለው ችዬ ፣ ሆዴን ከጠረፍ አስፍቼ
ከሾህ አክሊሌ በላይ ፣ ያልማዝ ዘውዴን ደፍቼ
በሸንጎ ተጀንኘ ፣ በእልፍኜ ብስለመለም
ህመምን አለማወጅ አልታመምኩም ማለት አይደለም፡፡

በዕውቀቱ ስዩም:- አዳምኤል የግጥም መድብል
ወይ ጉድ 😂😂😂😡😡😡🤔🤔

ስቄያለሁም ተናድጃለሁም ሂሂሂሂ...ሃሃሃ..ዝም

የአንድ የሀገራችንን ማወቅ ያለብንን ታሪክ አስቂኘም ነው አስገራሚም ነው.....ጠቅላላ ዕውቀት ላይ እራሱ ቢጠየቅ አብዛኛው ሰው ያውቀዋል ብዬ አላስብም 😂😂🤔

ፅሁፉን እስክለቀው በመጀመሪያ ለመለሰልኘ ሰው የmb ሽልማት አለኘ፡፡


ፅሁፉን ያገኘሁት ካሱን አወቃችሁት አይደል እሱ ካመጣልን ከአንድ የመፅሔት ቁራጭ ላይ ነው፡፡

በአውሮፕላን አደጋ የሞቱት የጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ማናቸው?? መቼ??

ሰው ያላቸውን ቢሰሙ እኮ አይሞቱም ነበር ምክንያቱም አብረዋቸው ያሉት ሌሎቹ ተርፈዋላ
ፓይለቱንም ጨምሮ ፡፡

ሀበሻ ኩራት እኮ😂😂😂😔😔
ኧረ ወግዱልኘ እንደፈሪ......ቀበቶ ልታጠቅ እንዴ አሉ😂😂😂😂

ከነሙሉው ታሪክ እመለሳለሁ

ጥያቄው ላይ ሩቡ መልስ አለ ትልቅ ሰው እንደሆኑ ሴት ይሁኑ ወንድ ባታቁትም፡፡

መልካም ቀን ተመኘቻለሁ

🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂ነገ ጠብቁኘ

ታሪካችንንማ ማወቅ አለብን 🏃‍♂🏃‍♂

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ
የኔ እይታ #ኩርኩም #2

ማን ያውቃል አልልም

ማን ያውቃል አልልም ሚስጥሯን ጨርሶ
ያለፈው ቢነግረው ከሚያውቀው ጠቃቅሶ
ቢፅፈው ቢነበብ ገብቶት ፊደል ቆጥሮ
እሱ ያላየው አለ ሌላው ያየው ኖሮ፡፡

ኖሮ.....ኖሮ....ኖሮ....ኖሮ...ኖሮ


ስለዚህ እኛ ያላየነው ወይም ለኛ አዲስ የመሰለውን ነገር ሌሎች ደርሶባቸዋል ለኛ ነው አዲስ የመሰለን መልካምም ይሁን ጥሩው፡፡

ዛሬ የቀጠለ እንጂ የጀመረ ምንም ነገር የለም ይህን አንተ የደረሰብህን መከራ አሸንፈው ያለፉ አያሌ ሰዎች አሉ ያገኘኸውንም ደስታ ያገኙ አያሌዎች አሉ በደስታ አትስከር በሀዘንህም በጣም አትጎዳ በልክ አድርገው ሚለኘ ይመስለኛል እዮባ😔🙏

ስንቱን ትልቅ ችግር አሃሃሃ ሲፈታ የኖረ
ከሱ አልፎ ለሌሎች ዘዴን የቀመረ
ቀላል ነገር ገጥሞት ሲከዳው ብልኃቱ
በታናሹ ምክር ከሃሳብ ከጭንቀቱ ሲወጣ ማየቱ

አዎ እውቀት በመልካምነታችን ለሌሎች በገንዘባችን በሀሳባችን በተለያዩ ማቴሪያሎች በጉልበታችን ለሌሎች በመድረስ ችግሮችን እንፈታለን......ግን ሰው መሆንህን አትርሳ አንተ ሁሉንም ማድረግ አትችልም አንተ ትልቅ ነኘ ብለህ ብታስብም በሆነ ነገር ወይም በትንሹ ነገር ትወድቃለህ ብህላቱ ይጠፋኻል አንተ ማድረግ የማትችላቸው ሌሎች ብቁ የሆኑበት ነገሮች አሉ ለነሱ ተውላቸው አለቦታህ ገብተህ ትወጅቃለህ ሞኘ ትባላለህ ከደረጃህ ትወርዳለህ የወደቁትን ተመልከት አትሳሳት በተሰማራህበት ስራ ብቁ ሁን እዛም እዚም አትበል ብዙ ያባረረ አንድም አይዝም ነው ብሂሉ ይልህና....

ኦ....ይገርማል ሰነፉ ብርቱ ነው
ኦ....ይደንቃል በሚያውቀው ሲገኘ
ኦ....ይገርማል ካለቦታው ገብቶ
ኦ....ይገርማል አዋቂው ሲሞኘ
ኦ....ይገርማል ይደንቃል ይገርማማማማልልል

ትንሽ ነኘ ብለህ ደግሞ አትዘን አላስፈልግም አልጠቅምም ምንም ረብ የሌለኘ ነኘ ብለህ ተስፋ አትቁረጥ በቦታህ አንተም አዋቂ ነህ ምታስፈልግበት ጊዜ አለ አንተ ትልቅ አዋቂ ጥበበኛ ምትባልበት ቀን ይመጣል፡፡

አንተ ጋር ያው እውቀት በብዙ ሚሊየኖቾ የሚቆጠር ብር ሊያመጣልህ ይችላል አንተ ጋር ያለው ነገር ሌሎቹ ጋር የለም አንተን ማንመ ማንም አስታውስ ማንም ሊሆን አይችልም ወይ ካንተ ያነሰ አለ ወይም የበለጠ እንጂ አንተን ማንም ሊሆን አይችልም፡፡

አንተ የምትሰራውን ውስጥህ ያለውን ነገር አውጥተህ ተጠቀምበት እንጂ ከማንም በላይ ነህህህህህህ ሞክር ያንተ ጊዜ እስኪመጣ ጣር ትልቅ ደረጃ እስክትደር ተስፋ አትቁረጥ፡፡

ያሰብከው እስኪሳካ ሞክር ሙከራዋች ናቸው ወደትልቅ ደረጃ የሚያደርሱት አንገትህን አትድፋ በኡነት ምታስፈልግበት ቦታ አለ ትልቅ ምትባልበት፡፡

ሚጠበቅብህን እየሰራህ ያን ጊዜ ጠብቅቅቅቅቅቅቅ💪💪💪ጀግና የምትባልበትን፡፡

እዮባን የምወደወው ህይወቱን እራሱን ኑሮውን ስለዘፈነ ነው፡፡ አንድም የምጥልለት ዘፈን የለውም ሁሉንም እወዳቸዋለሁ ስለመጀመሪያ አልበሙ እና ስለ ኤልያስ መልካ በሰፊው እንደምመጣበት ቃል ገብቼ ልሰናበታችሁ፡፡

😊🙏 @jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
ሰዓቱ አልቋል🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂👊👊
#በአውሮፕላን #አደጋ #የሞቱት #የመጀመሪው #ኢትዮፕያዊ #ማናቸው??

የሰው ልጅ ለመገናኛ ከፈጠራቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ከ100 ዓመት በላይ የትራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጥ የኖረው አውሮፕላን ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገራችን ሰማይ የበረረውና በመሬታችን ላይ ያረፈው ነሀሴ 12 1921 ሲሆን ባለፈው 90ኛ ዓመት የልደት ቀኑ ነበር፡፡

ይኸው የመጀመሪያው አውሮፕላን አዲስ አበባ ከደረሰ በኀላ ልዩ ስፍራው :- ገፈርሳ-ሜዳ ከቀኑ ሰባት 7 ሰዓት ከአስር ላይ ያረፈ ሲሆን እለቱ ዕሁድ ነበር፡፡ይሄ አውሮፕላን ወደ ሀገራችን የገባበት አመት የመጀመሪያ የአውሮፕላን ፈጣሪ የሆኑት የዊልቨር ወንድማማቾች የተሳካ በረራ ካደረጉ ከ26 ዓመት በኀላ ነበር፡፡

አውሮፕላኑ በሀገር ቤት:- ንስረ-ተፈሪ የሚል የዳቦ ስም ወጥቶለታል፡፡

ቀጣዩ አውሮፕላን የንሥረ-ተፈሪ አውሮፕላን ከፈረንሳይ ተገዝቶ ከገባ በኀላ በቀጣይነት ወደሀገራችን የገባው አውሮፕላን ደግሞ ከሌላኛዋ አውሮፓዊት ሀገር ጀርመን ሲሆን አውሮፕላኑን የፈበረከው ጂንከር የተባለ ኩባንኛ ነው፡፡

ነሀሴ 30 1921 አመተ-ምህረት ከድሬዳዋ ተነስቶ ጃንሜዳ ላይ ያረፈው ይሔው አውሮፕላን ከድሬዳዋ ጀርመናዊውን ዶክተር ብሩስን እና አስተርጓሚያቸውን የነበሩትን አቶ አስፋው አንዳርጌን አሳፍሮ የመጣ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ፖስታዎችን ጭምር ይዞ ነው፡፡

አብራሪው ኢግል የተባለ ሲሆን አውሮፕላኑ ጃ# ሜዳ በደረሰ ጊዜ ታላቅ አቀባበል ነበር የተደረገለት፡፡ በቦታው ቀዳማዊ ኃይለስላሴን ጨምሮ ሚኒስተሮች መኳንቶችና ጥሪ የተደረገላቸው የውጪ ሀገር ዲፕሎማሶች የተገኙ ሲሆን ኃይለስላሴም በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡

አውርፕላኖቹ ቁጥር በአጭር ጊዜ ያበዛችው ሀገር!

ነሀሴ 12-19-21 የመጀመሪያው አውሮፕላንን ከፈረንሳይ ገበታዋ ይዞታዋ ያደረገችው ኢትዮጵያ ይሄን የቴክኖሎጂ ውጤት በአየርዋ ላይ በስፋት ለማርመስመስ እምብዛም ጊዜ አልፈጀባትም፡፡


የኢጣሊ ፋሽሽት ጦር እስከወረራት 1928 አመተ-ምህረት ባሉት ሰባት አመታት ብቻ የኢትዮፕያ የ16 አውሮፕላኖች ባለንብረት መሆኗ ሲታይ ምን ያህል ለዚህ ቴክኖሎጂ ትኩረት ሰጥታ እንደነበር ያሳያል፡፡ በተለይ ከዚህ የአውሮፕላን መብዛት ጋር ተያይዞ በወቅቱ በሕዝቡ የተገጠመ ግጥሞች ነበሩ፡፡

አውሮፕላን መጣ........ሰማይ ለሰማይ
የተበደለውን...............ድሃውን ሊያይ
ነይ እንሳፈር................ነይ እንሳፈር
በማይነቀነቀው.............በሰማይ ባቡር!


ይቀጥላል🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
ቀጣይ ክፍል

ለመመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮፕያ የተገጣጠመችው አውሮፕላን!

ይህቺው በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተገጣጠመችው አውሮፕላን! ይህቺው በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተገጣጠመችው አውሮፕላን:- በማስተርስ ሊድግ ዌበር አማካኘነት በ1928 ዓመተ-ምህረት ነበር፡፡ በኃይለስላሴ ሴት ልጅ በሆነችው በፀሀይ ስም የተሰየመችው ይህቺው አውሮፕላን ተገጣጥማ ካለቀች በኀላ በረራዋን የጀመረችውን ወደ 150 ሜትር በማኮቦኮቦ ነበር፡፡

ሰባት ነጥብ ሁለት ሜትር ርዝመት ያላትና ሁለት መቀመጫ የነበራት ፀሀይ 149 የፈረስ ጉልበት ሲኖራት በሰዓት አንድ መቶ ሃምሳ ኪሎሜትር የመብረር ብቃት ነበራት፡፡ አውሮፕላኗ ማስተማሪያ የነበረች ሲሆን ፋሽሽት ኢጣልያ ኢትዮጵያን በወረራ እስከያዘበት ጊዜ ድረስ ፀሀይ በአጠቃላይ የበረረችበት ሰዓት 30 ሰዓት ወይም አንድ ቀን ከስድስት ሰዓታት ብቻ ሲሆን፡፡ ሀገሪቱ በሞሶሎኒ ጦር ስር ስትወድቅ፡፡

ፀሀይን ከጃንሜዳከሚገኘ ዛፍ ስር ቆማ አገኟት፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ጥቂት ካበረርዋት በኀላ ወደ ሀገራቸው ጭነው የወሰዷት ሲሆን ዛሬም ድረስ በዚያው በኢጣልያን ሀገር በሚገኘ ቪዲ በሚባል ሙዚየም ውስጥ የንጉሱ አውሮፕላን ተብላ በጎብኚዋች እየታየች ትገኛለች፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ጉዳት ያጋጠማት የሀገራችን አውሮፕላን እና በአደጋው የሞቱት ቀዳሚው ኢትዮፕያዊ!

የመጀመሪያው አውሮፕላን ለጉዳት ስትጋለጥ አውሮፕላን ወደሀገራችን ከገባ አንድ ወር እነኳን አልሞላውም፡፡ መስከረም 5 በ1921 በደሴ አካባቢ "ሀጪ ሓጂ ሙሳ አጃይብ" በተባለ ቦታ በሚኖሩ ማህበረሰቦች መካከል ትንሽ ያለመግባባት ተፈጥሮ ነበር፡፡

ይሔን ግጭት ለማብረድና ለመዳኘት ደጅአዝማች ወልደስላሴ - ወልደሚካኤል ፣ ደጃዝማች አመዴ ፣ ፀሐፊ-ትዕዛዝ አፈወርቅ ሚሴ ሸሚት......ደብሊው 33 በተባለች አውሮፕላን ወደስፍራው ለማምራት ገና ተነስታ 100 ሜትር ከፍታ ብቻ እንደበረረች ሞተርዋ ይጠፋና በአደጋው የኃይለስላሴ አጎት የነበሩት #ወልደስላሴ #ወልደሚካኤል በተከሰከሰችው አውሮፕላን ህይወታቸው ሲያልፍ........ፓይለቱ ጨምሮ ሌሎች ተሳፋሪዎቹ ሊተርፉ ችለዋል፡፡

የወልደስላሴ ሞት መንስኤ የራሳቸውም ጥፋት ነበረበት የተባለው አውሮፕላኗ ለበረራ ከመነሳቷ በፊት የደህንነት መጠበቂያ ቀበቶን ይሰሩ ሲባሉ፡- ኧረ ወይግዱልኘ እኔ እንዴት እንደፈሪ ቀበቶ የምታጠቀው!? ብለው ባለማሰራቸው የተነሳ ነው፡፡

በእምቢተኛነታቸው ነው የሞቱት የሚል ወሬ እንደተሰማ

አልቃሾች......

ከላይ አልጨበጡ........ከታች አልረገጡ
ሓጂ ሙሳ አጃይብ....እንደ እንቧይ ፈረጡ

በማለት ገጥመውላቸዋል፡፡

ቃል አምባ መፅሔት 2ኛ አመት ቁጥር 50 ቅዳሜ መጋቢት 2011 ዓ.ም :: ተገንጥሎ ከተገኘ ገፅ ላይ የሰፈረ፡፡

ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ፡፡

😂😂ያስቃልም ያናዳልም😡😡 ሀበሻ

ተገንጥላ ያገኛትን የመፅሔቷን ገፅ አንብቦት ለኛ ይዞ በመምጣት ፅሁፉን እንድናነብ ታሪክን እንድናውቅ ላደረገን #ለካሱ በእናንተ ስም ትልቁን አክብሮትና😘 ምስጋናን🙏 ላቀርብ እወዳለሁ፡፡

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
"ስለምንም ነገር እርግጠኛ ለመሆን ሰነፍ መሆን ያስፈልጋል" ቮልቴር

ጥበብ ከጲላጦስ ስብስብ ስራዎች ኃይለጊዮርጊስ ማሞ
ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ
@jahABP
አስተያየታችሁን አድርሱኘ
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

"እሳቱ እሳት"

እሱ ይናገራል.........

"አልበሜ አሁን ባይሰማም የሆነ ጊዜ ላይ መሰማቱ አይቀርም፡፡ እኔ በህይወት እስካለሁ ድረስ ስለኤልያስ መልካ ሳላወራ አሉልም ይለናል........እሱ ይቀጥልና ይናገራል............ኢትዮፕያ የነቅዱስ ያሬድ ሀገር ናት.......ኢትዮፕያ የነኤልያስ መልካ ሀገር ናት፡፡

ኤልያስ መልካ ለሁሉም ጥሩ የሆነ ሰው ነው እንደፈጣሪው ቃል የኖረ ሰው ነው....ኤልያስ መልካ ብዙ ነገሮችን አስተምሮኛል ነገሮችን በማውራት ሳይሆን በመሆን አሳይቶኛል፡፡ ለዚህም ህይወቱ ምስክር ነው፡፡
ሁሉም ስራዎቹ ምስክር ናቸው.......፡፡"


ይለናል እሳቱ እሳት የሚለው አልበሙ ሙሉ ለሙሉ በኤልያስ መልካ የተሰራለት ድምፀ መረዋው ልዑል ሀይሉ፡፡

ስለ ኤልያስ መልካ በጣም ብዙ ነገር ነው የሚናገረው ባደረጋቸው ቃለምልልስ ይህን ለመታዘብ ችያለሁ፡፡ ይህ አልበም ሁቻችንም ጋር ሊኖር ይገባል

ነፍሱን በፀደ ገነት ያኑርልንና እኔም ሙዚቃን እንድናውቅ ላደረገን ስለኤልያስ መልካ😍🙏በሰፊው እንደምመለስበት ቃል እገባለሁ፡፡

አልበሙን እንድትሰሙት ስጋብዛቹ አንድም ደቂቃ ከህይወታቹ ላይ እንደማታባክኑ እርግጠኛ ሆኜ ነው፡፡ ሬጌ ምት ነው ግጥም ዜማ ቅንብር ፕሮውዲዩሰር ኤልያስ መልካ ነውና....


በኡነት የግጥሙ ጥልቀት ብስለትና ሀይል አስገርሞኛል ይህን ትውልድ ይታዘባል...ኑርአችንን ይገልፀዋል፡፡

ልዑሌ የኤላን ስራ በብቃት ተጫውቶታል፡፡
ከግጥሞቹ ትንሽ እንቆንጥር.....
“ቀዳሚና ተከታይ”  ሙዚቃ ውስጥ የምንሰማቸው ስንኞች ለዚህ ዋቢ ናቸው፡- 
ፀጥ አልንና ሙት መስልናቸው መርዝ የጣፈጠን
ሊቅ ነን ሊሉ ቃርመው ያመጡትን ያኩትን ውጠን 
……………
ቋንቋ አቡክተው ታሪክ ፈትፍተው ስንቅ
አጥፍተው 
ዋሹን ህግ እያቀለሉ፣ ከጥንት አባቶች እያሉ 

ሰው ባልሰማው ባላወቀው
ባልኖረበት ዘመን በራቀው
ከሚግባባት ቋንቋ አብልጦ
ምን ያድርግ ነው ጥንት አብልጦ......

ኢትዮጵያንም እንዲህ ይላታል

“አንችው ነሽ አካሌ” ላይ የምንሰማት ኢትዮጵያ፤ የኤሊያስን እውነተኛ የሀገር ትርጓሜ የምናገኝበት ይመስለኛል፡፡

አዋሽ ጣናና ዳሎል ትርጉም አልባ መሆናቸውን ይጠቁማል፡፡  ከዛም ኢትዮጵያ ማለት መሬቱና ውኃው አይደለም፤ ሰው እንጂ የሚል ሀሳቡን ይሰነዝራል፡፡
መሬቱ አይደለም ሀገር ጣራው
ነፍስሽ ነው ቤቱ የሀገር ስፍራው
አንችው ነሽ ሀገሬ ኦያ 
ነፍስ ያለሽ ህይወቴ አያ
.......
ነፍስሽ ነች ህይወቴ ሆያ ሆዬ 
ነፍሴ ነች ህይወትሽ ሆያ

ሆዬ
.......
ካንች አይብስ ምንጊዜም 
ዳሎልም ተከዜም 
ለፍቅር እንጂ ማዜም...ለፍቅርሽ ነው ማዜም ይላታል፡፡

ኡነትም እኮ ዋናው ሰው ነው፡፡ እኔ አንተ እሱ ካልኖርን ሁሉም ትርጉም አልባ እኮ ነው፡፡
ኤላ አንተ ትለያለህ 😍👏

ጅል ትዕግስት የማይሰራ
ይልቅ ሲያድር አባሽ ሞት መከራ፡፡
ከአጉል ምኞቱ ሰው ካልጠራ
ጣር ነው ቢታገስም ሞት ንን ቢፀና..........

ይንቃ አለ አታባብሉ ሂድ ፈትሽ በሉት
አታዘናጉት ታገስ አትበሉት............ይለናል

በሌላኛው ዘፈኑ......ለምን ታስፈርድ በራስህ
ማወቅ ሳትፈልግ ለነብስ
ህግ አድምጠህ ምን ባታውቅም
መች ተባልክ አትጠየቅም
ሳያውቅ ላጠፋ አውቆ ለከፋ
ህጉ እንደው ያው ነው አይጠብ አይሰፋ🤦‍♂🤔🤔

አልጠብሽ እንዴት ችዬ
አትስጊብኘ አይዞሽ አንችዬ

...ደጋሽ ነኘ በሏት ትምጣ
ሰው ማየት ናፍቋል እሷን......

ልቤ አላርፍም አለ በናፍቆትሽ ነዶ
ካለሽበት ሔዶ
ተይ አድኚኘ መተሽ አርፌ ልተኛ
ተይ አትቅሪ አረገሽኘ ብቸኛ.....

ያለስጋት መኖራችን ትርፍ አይደል ወይየ ዋዛችን
አዝነን ተደስተን ተዋደንም ተጎድተን
እኔም እርሷም ገባን መኖር የእውነት ህይወት ቀነስኩላት ከምቾቴ ሳይነፍስባት ጥንድ ህይወቴ ክብርን ፍቅር ክሳኘ ከነሚደንቅ ውበቷ የራሴ ሆነች የእቅፌ ሴቴ ንግስቷ....ይላታል

ብቻ ሁሉንም ትወዱታላቹ ኤላ በተግፃፁ በልዑሌ ድምፅ አድርጎ ይመክረናል ያነቃናል፡፡

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ😍🙏😊

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

አንድ ፊልም ልጋብዛችሁ እፈልጋለሁ፡፡

ፌስቡክን ለመልካም ነገር ከሚጠቀሙ ሰዎች አንዱ ነኘ ለማለት እደፍራለሁ እናም አንድ ሀበሻ entertainment የሚል የፌስቡክ ግሩፕ አለ እሱ ላይ ሰዎች የተመቿቸውን የተለያዩ ፊልሞችና አዝናኘአስተማሪ ነገሮች ይለቃሉ እና እዛ ላይ ከተለቀቁት ፊልሞች መካከል ይህን ፊልም አይቼው በጣም ስለወደድኩት ላካፍላችሁ ወደድኩ፡፡

ጊዜያችሁን አታጠፉበትም እራሳችሁን ትፈልጉበታላችሁ እንጂ.....ትገረሙበታላችሁ እንጂ የፍቅርን ሀይል ትመለከቱበታላችሁ እንጂ የጓደኘነትን ጥግ ትመለከቱበታላችሁ እንጂ ጓደኘነት የተለያዩ ችግሮችን አብሮ ማለፍ እንደሆነ ትማሩበታላችሁ እንጂ ፍቅር ላይ ማርፈድ እንደሌለባችሁ ታዩበታላችሁ እንጂ ፍቅር ላይ በኀላ ሚባልነገር እንደሌለ ታዩበታላችሁ እንጂ ምን አይነት መስዋትነት መክፈል እንዳለባችሁ ታዩበታላችሁ እንጂ ጅል የምንላቸው ሰዎች ፍቅር ያላቸው እንደሆነ ታዩበታላችሁ እንጂ.....ሰውን ምን ያህል መንከባከብ አለብን የሚለውን ታዩበታላችሁ እንጂ..............ብቻ ብዙ ብዙ......

ይሔን ፊልም በቀን ውስጥ ሁለቴ አይቼዋለሁ አንዴ ብቻዬን በጣም ስለወደድኩትና ስለተመቸኘ ብዙ ነገር ስለተማርኩበት ለቤተሰቦቼም ጋበዝኳቸው ሰብሰብ ብለን አየነው፡፡ ሁሉም ተመችቷቸዋል፡፡ ለናንተም ልጋብዛችሁፈለኩኘ ብዙ ሽልማቶችንም አሸንፉል፡፡

ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

@jahABP ነኘ 😊🙏😊

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD