Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

አንድ ፊልም ልጋብዛችሁ እፈልጋለሁ፡፡

ፌስቡክን ለመልካም ነገር ከሚጠቀሙ ሰዎች አንዱ ነኘ ለማለት እደፍራለሁ እናም አንድ ሀበሻ entertainment የሚል የፌስቡክ ግሩፕ አለ እሱ ላይ ሰዎች የተመቿቸውን የተለያዩ ፊልሞችና አዝናኘአስተማሪ ነገሮች ይለቃሉ እና እዛ ላይ ከተለቀቁት ፊልሞች መካከል ይህን ፊልም አይቼው በጣም ስለወደድኩት ላካፍላችሁ ወደድኩ፡፡

ጊዜያችሁን አታጠፉበትም እራሳችሁን ትፈልጉበታላችሁ እንጂ.....ትገረሙበታላችሁ እንጂ የፍቅርን ሀይል ትመለከቱበታላችሁ እንጂ የጓደኘነትን ጥግ ትመለከቱበታላችሁ እንጂ ጓደኘነት የተለያዩ ችግሮችን አብሮ ማለፍ እንደሆነ ትማሩበታላችሁ እንጂ ፍቅር ላይ ማርፈድ እንደሌለባችሁ ታዩበታላችሁ እንጂ ፍቅር ላይ በኀላ ሚባልነገር እንደሌለ ታዩበታላችሁ እንጂ ምን አይነት መስዋትነት መክፈል እንዳለባችሁ ታዩበታላችሁ እንጂ ጅል የምንላቸው ሰዎች ፍቅር ያላቸው እንደሆነ ታዩበታላችሁ እንጂ.....ሰውን ምን ያህል መንከባከብ አለብን የሚለውን ታዩበታላችሁ እንጂ..............ብቻ ብዙ ብዙ......

ይሔን ፊልም በቀን ውስጥ ሁለቴ አይቼዋለሁ አንዴ ብቻዬን በጣም ስለወደድኩትና ስለተመቸኘ ብዙ ነገር ስለተማርኩበት ለቤተሰቦቼም ጋበዝኳቸው ሰብሰብ ብለን አየነው፡፡ ሁሉም ተመችቷቸዋል፡፡ ለናንተም ልጋብዛችሁፈለኩኘ ብዙ ሽልማቶችንም አሸንፉል፡፡

ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

@jahABP ነኘ 😊🙏😊

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

BARFI
2012.....የህንድ የኮሜዲ ዘውግ ያለው አዝናኘ ፊልም ነው፡፡ RATING 8.1

አንድ መስማት እና መናገር የተሳነው መርፊ...በራሱ አጠራር ባርፊ የሚባል ልጅ ከሁለት የተለያዩ ሴቶች (ሱርቲ እና ጂልሚል) ጋር የሚያደርገውን የፍቅር ታሪክ በሚገርም አቀራረብ የቀረበ ፊልም ነው፡፡

በ85 አካዳሚክ ኦስካር ሽልማት በምርጥ ከእንግሊዘኛ ውጪ በሌላ ቋንቋ የተሰራ ፊልም በመባል እጩ ሆኗል፡፡

በህንድ የተዘጋጁ የተለያዩ ሽልማቶችን ጠራርጎ የወሰደ ሲሆን በ58 ፊልምፌር ሽልማት
ምርጥ ሴት ፕሪያንካታቾፕራ ተዋንያን ምርጥ እረዳት ሴት ተዋንያን ሌአን ደክሩዝ ምርጥ ፊልም ምርጥ ወንድ ተዋናይ ራንቢር ካፑር....ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሚዲያው በመምጣት ምርጥ ትወናዋን ላሳየችው ደክሱዝ የአመቱን ሽልማት፡፡
በምርጥ ፊልም ሽልማት
በምርጥ ስክሪን ፕሌይ አውራግ ባሱ
በምርጥ ዳይሬክተር አውራግ ባሱ
ብዙ ገቢን ያስገኘ ፊልም

አክተርቹ በግላቸውም ብዙ ሽልማቶችን ጠራርገው ወስደዋል...የበለጠ GOOGLE እንድታረጉ እመክራለሁ አበቃሁ፡፡

በትወና፡- ራንቢር ካፑር😍👏 ፣ ሌአን ደክሩዝ😍👏 ፣ ፕሪያንካታቾፕራ😍👏❤️፣ አሺሽ ቪድሪያሪቲ ፣ ጄሹ ሲንጉፕታር ፣ ሮፓ ጋንጉሊ በብቃት ተጫውተውታል

የፊልሙ ርዝማኔ 2:30.......አትፀፀቱበትም

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

➋➐ አቤቱ ከመቅደስህ አትለየን

መልካም ቀን🙏🙏
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ማን ነው ተያቂው? ህይወት? ሰይጣን? አጋጣሚ? ዕጣፋንታ ወይስ ታላቁ ፈጣሪ? ወይስ ሁሉም ተጠያቂዎች አይደሉም? ወይስ ተጠያቂ የሚባል ነገር የለም? ኤልያስ ከፀሀይ በታች ያለው ሁሉ ከንቱ ንፋስን እንደመከተል ነው የተባለው እውነት ይሆን? እውን ከፀሀይ በታች ያለው ሁሉ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው? የከንቱ ከንቱ ለሆነስ ነገር መጨነቅ አስፈላጊ ነው? የከንቱ ከንቱ ከሆነስ ለምን ከፀሀይ በታች ያለው ሁሉ ተፈጠረ? ለምን የምድር ነዋሪዎች ከእነ ግሳንግሳቸው ተፈጠሩ?

ወይስ ከንቱ መሆን እራሱ ከንቱ አለመሆን ነው? ወይስ መሆን አለመሆን! አለመሆን መሆን! መሆን መሆን! አለመሆን አለመሆን!አለመሆን መሆን ነውን? ለነገሩ አለማሰብ ፣ አለመጨነቅ ፣ አለመብሰልሰል ፣ በዝምታ ያለ አንዳንች ጥያቄ ናዳ መቀመጥስ? ይቻላል ከተቻለስ ይህስ ከንቱ አይደለም? ከንቱ ባይሆን እንኳን ከንቱ አለመሆን ራሱ ከንቱ አይደለም?

ለመሆኑ እኔ ማነኘ? ስለምን ይህን ያህል ስለከንቱ መሆንና አለመሆን ተወጥሬ አስባለሁ?ስለምንስ ብቻዬን እቆዝማለሁ? ለመሆኑ እንደው ለአባባል ካልሆነስ ሰው ብቻውን መቀመጥ ይችላልን? አጠገቡ ሴይጣን የለም? አጠገቡ መላዕክት የሉም? አጠገቡ የሚያብሰለስለውስ ሀሳብ የለም? እንኪያስ እኔ ብቻዬን ተቀምጬ እውን ብቸኛ ነኘ ማለት ይቻላልን? ፈጣሪ እንኳን ብቻውን መሆን ይችላል? ፈጣሪ እንኳን ሰማይና ምድርን ሲፈጥር መች ብቻውን ነበር? እውን ከፀሀይ በታች ይሁን ከፀሀይ በላይ ብቸኘኘት የሚባል ነገር አለን? ስለምንስ ውስጤ በአንዳች የባዶነት ስሜት ይናወጣል? ስለምንስ ዘወትር ቀይና ጥቁር በሆነ በማያልቅ ጥያቄ እናጣለሁ?

ስለምንስ በግዴለሽነት ወንዝ ጠብዝቼ እንቦጫረቃለሁ? ስለምንስ ስለህይወት ከንቱነት አብዝቼ እውጠነጠናለሁ? ስለምንስ ሁሉ ነገር የከንቱ ከንቱ ነፋስ የመከተል ያህል ነው እላለሁ? ስለምንስ በከፍተኛ የተስፋ መቁረጥ ማዕበል ውስጥ እዋዥቃለሁ? ስለምንስ ስለዓለም በግዴለሽነት ማዕበል ተሞልቼ አውጠነጥናለሁ? ስለምንስ የመጀመሪያም የመጨረሻም በሌላቸው የጥያቄ እና ሀሳብ እንቆቅልሾች እያውጠነጠንኩ ራሴን አጀዝባለሁ? ስለምንስ በፍልስፍና መንገድ ለመኳተን እታትራለሁ? እደፋደፋለሁ?

ማነኘ? መጨረሻዬ ምንድነው? ለመሆኑ መጨረሻውን የሚያውቅስ አለ? እንኳን እኔ ያለ ፍላጎታቸው ከፀሀይ በታችም ሳይሆን ወይም ከፀሀይ በላይም ሳይሆን "ገነት" በምትባለው የሀሳብ መንደር የተፈጠሩት ሁለቱ ሚስኪኖች ቀዳማይ አባታችን አዳም ሆነ እናታችን ሔዋን መጨረሻቸውን ያውቁ ነበር? መንገዱን ከፈጣሪ ጋር ያደረገው ሙሴ መጨረሻው ያውቅ ነበር? ታላላቅ የዓለማችን ነገስታት መጨረሻቸውን ያውቁ ነበር? አያውቁም!!! እና እኔ አንዲት ሚስኪን እንዴት መጨረሻዬን ላውቅ እችላለሁ?

እ
ና
ም

ስለ መጨረሻዬ መናገር አልችልም፡፡ አለመቻሌ ከንቱ ነው፡፡ በእርግጥ መጨረሻዬ መናገር ብችልም እንኳን ከንቱ ነው፡፡ በዚች በከንቱ የተወጠረች ዓለም ውስጥ የሰው ልጅ ከአምስት ደቂቃ በኀላ ስለሚሆነው ነገር በእርግጠኘነት መናገር አይችልም፡፡

መገመት መብቱ ነው፡፡ መመኘት መብቱ ነው፡፡ተስፋ ማድረግ መብቱ ነው፡፡ ሂሳባዊ ቀመር መስራት መብቱ ነው፡፡ ይህን ማን ይከለክለዋል? ለማንኛውም ስለመጨረሻዬ መናገር ባልችልም ስለተወለድኩበት ቀን.....አሁን እስካለሁበት ቀን ድረስ ያለውን መናገር እችላለሁ! መተርተር እችላለሁ መቀባጠር እችላለሁ! በእርግጥ ይህም ከንቱ ነው ንፋስን የመጨበት ያህል ነው፡፡

ኤጭ.......! ከሚለው የአዘርግ መፅሐፍ የተቀነጨበ፡፡

ኤጭ...!
(በኢትዮጵያ ምድር የተከናወኑ ዘግናኘ ታሪክ)
አዘርግ 2010 ዓ.ም
አዲስ አበባ

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ😊🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
እግዚአብሔር በድርጊት የሚገለፅ አምላክ ነው፡፡

እማሆይ ትሬዛ😍🙏

መልካም አዳር🤓🤲
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

አንፃር

አባቴ ነው፡፡...

.....ቀና ብለህ ከግድግዳው ላይ የተሰቀለውን ፎቶዬን ተመልከት አለኘ፡፡ አባቴ ከእናቴ ጋር ሲጋቡ የተነሳው ፎቶ ነው፡፡ የአባቴ ፀጉር ከብዛቱ ርዝመቱ ጉድ ያሰኛል፡፡ የገረጣ ጠይም ፊት ነው፡፡ መካከለኛ ቁመና ፣ ሥጋ ያልበዛበት አካል ይታያል፡፡ አባቴ ከሰላሳ አመት በፊት የተነሳው ፎቶ፡፡ ፎቶው ላይ ያለው ምስል የአባቴን ዘመን የአለባበስ ስርዓት ያሳያል ፣ ቬል የረዘመ ሱሪ ፣ ኮሌታው የሰፋ ኮት በነጭ ስፖርት ሸሚዝ ይታያል፡፡ አባቴ በእኔ እድሜ እያለ የተነሳው ፎቶ..

"አየህ አይደል? እኔ በአንተ ዕድሜ ሳለሁ ንፋሱን እጨብጥ ባህሩር እጨልጥ ነበር፡፡ ነገር ግን ንፋሱም ከእጄ የለም ፣ ባህሩም ሆዴን አልሞላም፡፡ ከንቱ የወጣትነት ምኞት ነበርና፡፡
እኔ በአንተ ዕድሜ ሳለሁ ከአባቴ ምክር ይልቅ የራሴን ስሜት የማዳምጥበት ወቅት ነበር፡፡ ከአያትህ መሬትነት ይልቅ የኔን እሳትነት እመካበት ነበር፡፡ እኔ በአንተ ዕድሜ እያለሁ"
አለኘ አባቴ፡፡

ፀጉሬን እየፈተልኩ አባቴ የደረሰባትን የዘመን እውነት በልቤ እያሽሟጠጥኩባት እሰማ ጀመር..

"ታሪክ እራሱን ይደግማል ማለት እንግዲህ ይህ ነው፡፡ የምትመካበት አዲስ ነገር ምንድነው? እኔ ያላደረግሁት አንተ የምታደርገው ምን አለ? ተመልከት ፎቶዬን <ፀጉሬ ጎፈሬ ነበር፡፡ የአንተም ፀጉር አፍሮ ነው፡፡ እኔ ለጎፈሬዬ ከኀላ ኪሴ የእንጨት ሚዶ አይለየኘም ነበር፡፡ አንተም እንደኔው ለአፍሮህ ትጨነቃለህ፡፡ አፍሮህ ሲያድግ ደሞ ትገምደዋለህ፡፡

ሲሻህ ደግሞ ትሾርበዋለህ፡፡ይሔ ሁሉ ግን ከእኔ ከአባትህ የተረፈ ነው፡፡ ከኔ ያላገኘኸው ምንም ነገር የለም፡፡ እኔ በጎፈሬዬ የሀገሬን ጠላት ማጥፋቴን ፣ ማንነቴን መጠበቄን መሰከርኩበት፡፡ አንተ ግን በሹሩባህ መጀመሪያ ራስህን ፣ ቀጥሎ ቆነጃጅቶችኝ ጠለፍክበት፡፡
አንተ በፒያሳ እንደምትሆነው ሁሉ እኔም በውቤ በረኃ ዘምቻለሁ፡፡ <ይኼ ሁሉ የአባቴ ምክር ነበር፡፡

አሁንም እጄ ከፀጉሬ ላይ አልተለየም ÷ ሦስቱ ጣቶቼ ፀጉሬ ላይ ይፈትላሉ አባቴም ያወራል፡፡

<ይሄ ሁሉ ግን ጥላ ነው፡፡ እኔ በአንተ ዕድሜ ሳለሁ የሚዳሰስ አካል ይመስለኘ ነበር፡፡ አይደለም፡፡
ወጣትነት ፍቹ እንደሌለው ህልም ነው፡፡ ታየዋለህ ፣ እንደ ነፋስ ሽውታም ያመልጥኻል፡፡ ወጣትነት ፊደል ነው፡፡ ፣ ቃል ግን አይደለም፡፡
ልጄ ሆይ ምክሬን ስማ ወጣትነትና ሕሊና ባዶ ናቸው፡፡

ሕሊና ፀፀትን እንጂ እርምትን አይወድም፣ ወጣትነት እና ሕሊና አንድ ናቸው፡፡ ሕሊና ፀፀት እንጂ እርምትን አይወድም ፣ ወጣትነትም እንደዚያው ነው፡፡ ብዙ ምኞትና ብዙ ከንቱነት፡፡"
ቀና ብዬ አይኑን አየሁት...ዓይኔን ወደመሬት መለስኩት፡፡ ቢጨርስና ቤቱን ጥዬው ብወጣ ደስታዬ ነበር፡፡ የአባቴ ምክር ወሬውን ቀጠለ...

"እስካሁን ከነገርኩህ በላይ የምነግርህ ቢኖር ዕድሜህ በአንተ ላይ ታዛለች እንጂ ፣አንተ በዕድሜህ ላይ መብት የለህም፡፡ እስካሁን የነገርኩህን ሁሉ ልትቀበለኘ የምትችልበትን ስልጣን በራስህ የለህም ወጣት ነህና፡፡ ወጣትነትህ ደግም እርጅናዬን ታስንቅኃለች ፣ እርጅናዬ ደግሞ ያንተን ወጣትነት በቅናት ትንቀዋለች፡፡

ምናልባት፡- ዛሬ አንተ ከእኔ አባትህ የበለጥክበት ጊዜ እንደሚመስልህ ሁሉ አንተ በተራህ በልጅህ የምትበለጥት ጊዜ ጊዜ ቅርብ ነው፡፡ ልጄ ይበልጠኛል ለማለት አትችልም ÷ ልጅህ ከአባቴ እበልጣለሁ ይላል እንጂ፡፡ ያን ጊዜ የልጄን ልጅ ሰባት እጥፍ እወደዋለሁ ÷ የአያቱ ተበቃይ ነውና፡፡ አባቶች የልጆቻቸውን ልጆች የሚወዱበት ምክንያት ለማወቅ ከፈለግህ ፎቶዬን ተመልከተው ÷ አንተ ስወልድ ዕድሜዬ እንዳንተ ነበር፡፡

አንተ በእኔ ዕድሜ ስትሆን እኔ ወደ አያትህ እየሔድኩ ነው፡፡ ሕይወት ታሳሳለች ÷ አባት ስትሆን ደግሞ ልጅህ እያካለለ ሲያሮጣት ታያለህ ያኔ ለልጅህ ጠላቱ ልጁ ነውና የልጅህን ልጅ ትናፍቃለህ፡፡ የልጅህንም ልጅ ከልጅህ ይልቅ ሰባት እጥፍ ትወደዋለህ፡፡ ተበቃይህ ነውና፡፡" ብሎኘ ሽበት የወረረውን ወጉሩ ላይ ባርኔጣውን ጥሎ ከመቀመጫው ተነስቶ ወጣ፡፡

እኔም አባቴ ከተናገራቸው ብዙ ቁም ነገሮች መካከል ያስገረመችኘና ያስፈገገችኘ እያሰብኩ ወደ ቀጠሮዬ ተነሳሁ......

"አሁን የነገርኩህን ሁሉ ልትቀበለኘ የምትችልበት ስልጣን በራስህ የለህም፡፡ ወጣት ነህና፡፡ ወጣትነትህ ትሰማለች እነንጂ አታስተውልም፡፡ ጉብዝናህ እርጅናዬን ታስንቅኃለች ÷ እርጅናዬ ደግሞ ያንተን ወጣትነት በቅናት ትንቀዋለች፡፡"

የይሁዳ ድልድይ እና ሌሎች ሃሳቦች
ከኤፍሬም ስዩም
ህዳር 2007

በድጋሚ የተፖሰተ

ቤታችንእንሁን ቤተሰቦቻችን የሚሉንን እናዳምጥ

@jahABP ነኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

Wallpaper 😍

ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
INSTAGRAM ላይ FOLLOW በማለት ድጋፋችሁን አሳዩኘ😍🙏😊

@abiy_yemaryam_leje

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
" ፍቅር የሚገኘው በፍቅር ነው

ሰዎች ስንወዳቸው ይወዱናል፡፡ እንዲወዱን ከፈለግን ግን መቼም አይወዱንም፡፡
ፍቅር ሳያዳምጡ መውደድ መቻል ነው፡፡
ፍቅር ዕቁብ ሳይሆን ፍቅር ስጦታ ነው፡፡

ካፈቀርን......

መጠላትንም ለመቀበል መዘጋጀት ያስፈልገናል፡፡
ለመረገምም ለመነቀፍም ዝግጁ መሆን ያስፈልገናል፡፡

ግን አስታውሱ.....

የምንኖረው እግዚአብሔር ስለወደደን እንጂ ሰዎች ስለወደዱን አይደለም፡፡

የህዝብ ፍቅር ሲናፍቀን የአንድ ሰው ፍቅር ሳናገኘ እንቀራለን፡፡

ራሱን መውደድ ካቃተው ሰው እኛን እንዲወደን መፈለግ ተገቢ አይደለም፡፡
የፍቅር ደስታው #ሲሰጡት እንጂ #ሲቀበሉት አይደለም፡፡ ያማለት ሲያፈቅሩት እንጂ ሲፈቀሩ አይደለም፡፡
ልወደድ የሚል ስሜት ያደረባቸው ከንቱ አስተሳሰብ ያደረባቸውና የአእምሮ ድህነት ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡

ሰዎች ፍቅር ብቻ አይደለም ያላቸው፡፡
ጥላቻም የእነርሱ ናት፡፡
ስለዚህ ደስ ሲላቸው ይወዱናል ደስ ሲላቸው ይጠሉናል፡፡

እግዚአብሔር ግን ታምኖ የማይከዳ ፣ ወዶ የማይጠላ ፍቅር ብቻ ነው፡፡

አለሙ ፍቅር አልባ አስፈሪ ሆኗል፡፡

የእግዚአብሔር ፍቅርን ብቻ ስናስብ ያልተሰበረ መንፈስ እናተርፋለን"

አፍቃሪ ልብ❤️ ይስጠን 😍🙏🙏

መልካም ጊዜ

@jahABP 😊🙏 ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ፡፡

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

የአመቱ የመጨረሻ ቅዳሜ.....በፈገግታ

ወዳጄ አንድ ነገር ልምከርህ ልምከርሽ ሁሉም ሚሆነው አንተ ስትኖር ነው አንቺ ስትኖሪ ነው፡፡
ኑርልን😃 ኑሪልን😃 ብዙ ነገር ለዚች አለም ማበርከት ትችላለህና ባንተ የተነሳ ቡዙሀኑ ይደሰታሉ ነገ በቅንነት በታማኘነት ይቺን ሀገር ይጠቅማሉ ከሚባሉት ነህና/ነሽና እባክሽ ጠንክሪልን እባክህ ጠንክርልን፡፡

አንተን ካጣ አንቺን ካጣ ሁሉም ቢያለቅስ ቢያዝን ለጊዜው ነው፡፡

ምክንያቱም መርሳት የሰው የተፈጥሮ ባህሪው ነውና፡፡

ከሔደ ለማይመለሰው ውድ ለሆነው ህይወትሽ ስትይ ስትል

ማስክሽን አድርጊ ሳኒታይዘርህን ተጠቀም ከሰዎች ጋር ያለህን ንኪኪህን ቀንስ፡፡
አስገዳጅ ነገር ካልሆነ አቤት አትውጪ፡፡

ነገ አንተን ማየት ያንተን ደስታ ሚፈልጉ ሰዎች በዙሪያህ አሉና ተጠንቀቅ ለሌላው መጎዳት ምክንያት ላለመሆን ጣሪ፡፡

ታስፈልገናለህና ታስፈልጊናለሽና እባክህህ/ሽ እራሳችንን እንጠብቅ፡፡😷😷🤲

@jahABP ነኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

መልካም ዕለተ ሰንበት ከሰንበት ረድኤት በረከት ይደርብን

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

"ይድረስ ላልተፀነስከው ልጄ"
(በ2 pac "letter to my un born chiled" ሙዚቃ የነቃ ፅሁፍ)


ካሱ ካመጣልን አዲስ አይን መፅሔት ግንጣይ ገፅ ላይ ያገኘሁት ፅሁፍ......

ልጅ ወልደኃል ልጅ ወልደሻል??

ወይስ ገና ሚስት እርጉዝ ነች

ደርሰሻል ጥቂት ሳምንት ነው የቀረሽ??
፡፡
ቤቢ ሻወር ምናምን😊....

እሺ የናንተ ይሁን ስትደግሙ ታስቡበታላችሁ

ፅሁፉ ግን ሚለው ገና ላልተፀነሰው ልጄ ነው አባቱ .......ገና ግንኙነት ሳያደርግ የፃፈለት ፅሁፍ ነው........አንቺ እሱ እኔ እኛ ገና ለመውድ ሀሳቡ ያለን እስኪ እራሳችንን እንይበት ምን አይነት ልጅ ነው ለመውለድ ምናስበው፡፡

ልጅ የፈጣሪ ስጦታ ቢሆንም ምንመኘው ግን ምን አይነት ልጅ ነው?? ከፈጣሪ በታች እራሱን እስኪያቅ የኛን ሀሳብ ነውና እየጫንበት የሚያድገውና እኛኑ መስሎ ነው የሚያድገውና.........



ታዲያ ለዚህ አለም ለዚች ሚስኪን ሀገር ምን አይነት ልጅ ነው ለማውረስ ያቀድሽው ምን አይነት ልጅ ነው ልታበረክትልን ያሰብከው??

ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

@jahABP ነኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

ካህኔ የነፍሴ አገልጋይ እንቅልፍ አትተኛም ወይ
🙏🙏😍🙏🙏

ረጅም እድሜ ለአባቶቻችን
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ይድረስ ላልተፀነስከው ልጄ
(በ2 pac "letter to my un bornchild ሙዚቃ የነቃ ፅሁፍ)


በእናትህ ማህጸን ውውጥ ካለ እንቁላል ፣ ከእኔ አብራክ ውስጥ ካለ ዘረምል ወጥተህ ፅንስ ያልሆንከው ልጄ እንደምን አለህልኘ፡፡ እኔ ካንተ ናፍቆት በስተቀር ደህና ነኘ ያገሬ ሰው ሞኘ ነው "የማያቁት ሀገር አይናፍቅም" የሚል፡ተረት ያምናል፡፡

ይኸው እኔ በማላውቅህ ልጄ ባንተ ናፍቆት እየተብሰለሰልኩ አይደል፡፡ ለነገሩ የማያቁት ሀገር ላዬናፍቅ ይችላል የማያቁት ልጅ ያላፀነሱት ልጅ እንደሚናፍቅ ግን እኔ በአስሩም ጣቴ ፈርሜ እናገራለሁ፡፡ ካስፈለገም ማህተቤን ጨብጬ እምላለሁ፡፡ ማረርያምን፡፡ እናልህ ልጄ እጅጉን ናፍቀኸኛል፡፡

ምን አይነት ሰው ይሆን? ፀባዩ? ባህሪው? መልኩ?? ቁመናው?? እያልኩ እራሴን እጠይቃለሁ፡፡ ግን መልስ የለም፡፡
ደግሞ እንደምታውቀኘ ችኩል ነኘ፡፡ ለነገሩ የትብለህ ታውቀኛለህ፡፡አንተ ገና አልተፈጠርክም! ኧረ መች ተፀነስክና! ብቻ ግን ብታውቀውም አይከፋምና እወቀው እኔ የወደፊት አባትህእጅጉነለ ችኩል ነኘ፡፡

እና ይህ ችኩህነቴ እየገፋፋኘ ቶሎ ላፀንስህና ተወልደህ ላይህ እጓጓለሁ፡፡ ግን ደግሞ ከቀልቤ ሆኜ ሳስበውም #አይሆንም፡፡ ምንም ሳይዘጋጁ ልጅ መውለድ ሃጢያት ነዋ! ይህንን ደሞ ያስተማረኘ አለምን በቃሉ ያፀና ፣ ሰማይን ያለምሶሶ ፣ ምድርን ያለመሰረት ያፀናው ክርስቶስ ነው፡፡

እሱ አዳምን የፈጠረው የሚያስፈልገው ሁሉ ከፈጠረበኀላ አይደል? ሌሎቹ አፈጣጠሮቹንም ተመልከት ሁሉንም የፈጠራቸው መጀመሪያ የሚያስፈልጋቸውን ከፈጠረ በኀላ ነው፡፡
ሰማይን ፈጥሮ ፀሀይን ፣ ፀሀይን ፈጥሮ እፅዋትን ከዛ እንስሳትን ምናምን እያደረገ፡፡

ከፈለክ ጠይቀው ከኔ ይልቅ ላንተ ይቀርብ የለ፡፡
"እኔ የክርስቶስ ተከታይ ነኘ" የሚለው የሀገሬ ህዝብ ግን ምንም ሳይኖረው አንዳች ሳያዘጋጅ ልጅ ያምረዋል፡፡ ልጅ እንዴት ያድጋል? ምን ይበላል? ምን ይጠጣል? ምን ይለብሳል? የት ያድራል?የት ይማራል?የሚሉትን ጥያቄዎች ሳይመልስ ይወልዳል ያስወልዳል፡፡

እሱ ምንጨነቀው "ልጅ በድሉ ያድጋል" የሚል ሰንካላ ተረት አለለት በኩ ይፅናናል፡፡ አን ስንቱ መሰለህቀየመንገዱ ተርቦ ፣ተጠምቶ ፣ ታርዞ...የወደቀው፡፡ ቤቱ ይቁጠረው፡፡ ያልተፀነስከው ልጄ ስንቱን መሰለህ "በክርስቶስ ክርስቲያን የሆናችሁ" ሲባል አቤት እያለ ከዲያቢሎስ የባሰው፡፡

ያልተፀነስከው ልጄ የወደፊት አባትህ መልስ ከሌለው ጥያቄ ከምብሰለሰል ለምን አትነግረኘም ምኅ አይነት ሰው ነህ ልጄ? አባትህ ቀጭንቀት ከምሞት እስኪ ንገረኘ፡፡ ለነገሩ እንኳን ገና ያልተፀነሳችሁት ይቅርና በቅርቡ የሚወለዱትስ መች ላባት ቁብ አላቸው፡፡

እኛስ ቀደም ብለን የተወለድነው #ስላባቶቻችን #አባቶቻችን #ላባቶቻቸው #የሚጨነቁትን ያህል መች ጨንቆን? ልጄ ሁሉንም እንተወው እና አንድ ነገር ልንገርህ፡፡

ስማኘ ተወልደህ ለዚች ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ #ትርፍ ሰው እንዳትሆን፡፡የተሰራ ለመድገም የሚጥር አዲስ ሀሳብ የሚጠላ አልቸገራትም፡፡ ልምራሽ ብሎ ወደ ኀላ የሚወስዳት ፣ አውቅልሽ ብሎ ገደል የሚከታት ተቀያሪ ሳይቀር አላት፡፡ ላልማሽ ብሎ የሚያወድማት ፣ ልሳምሽ ብሎ የሚነክሳት ትርፍ አላት፡፡

ሀገርህ ፣ ሀገሬ ኢትዮጵያ፡፡ የማያውቅ አዋቂ ነኘ ባይ ሞልቷታል፡፡ የማያድን አዳኘነኘ ባይ ተሮፉታል ኧረ ስንቱ .....ኧረ ስንቱ ልጄ....በልቶ ስላደረ ሁቹም የጠገቀ የሚመስለው ገንዘብ በደረቱን አስነፍቶት ሁሉን የሚያውቅ የሚመስለው ስንት አለ መሰለህ እሷም ደግሞ አታውቅበትም፡፡ ለማጀቷ በር አላበጀችም፡፡

ማጀቷን ለሁሉ ከፍታለች፡ የደረሰ ይገባል፡፡ የገባው ግን ደግ አይሰራም፡፡ እሱ ቢወጣም ደግ የሚሰራ አይገባም፡፡ የለማ! ሀገርህ እነዲያ አይነት ሰው አላፈራችም! ሀገሬ በጎ ሰው ጨርሳለች! ኢትዮጵያ....ቢኖሯት እንኳን ጥቂት አረሞች ውጠዋቸዋላ! ተወኘ ባክህ ልጄ ሆድ አታስብሰኘ፡፡ይልቅ ከጭንቄ ገላግለኘ፡፡

አንተ ምን አይነት ሰው ትሆን? ትርፍ? ሃገሬ ያልቸገራትን ሀገርህ የሞላትን? አደራ እንዲህ ከሆንክ አንተን ወደዚህ የማምጣት ጉጉቴ ሁቹ በልቤ ውስጥ ይመክናል፡፡ አንተ ወደምድር እንድትመጣ በማደርገው ጥረት ኮንዶምና መሰሎች እንኳን አያስተማምኑኘም፡፡

ብልቴን ቆርጬእጥለዋለሁ እንጂ፡፡ ስላሴን፡፡
እኔ ለሀገሬ ምንም አልሰራሁላት፡፡
ትርፍ ሰው ሆኜባታለሁ ትርፍ ሰው ግን ልጨምርባት አልፈልግም፡፡ እናም አደርገዋለሁ፡፡
ልጄ ሙት አደርገዋለሁ፡፡ ልጄ ሙት እቆርጠዋለው፡፡

ልጄ እባክህ ምን አይነት ሰው እንደሆንክ ንገረኘ አልጨነቅ? ሀገሬ የቸገራት ፣ ሀገርህ ያጣችው ኢትዮጵያ የሌላት አይነት ሰው ከሆንክ ዛሬውኑ ልሰናዳ ወደምድር የመምጫ ትኬት ልቁረጥልህ በእናትህ ማህፀን ላሳፍርህ የሚያስፈልግህን ላሟላል ወደምድር ላምጣህ፡፡

ኢትዮጵያን ታደጋት፡፡ ልጄ ባዛኘቱ አታስጨንቁኘ ንገረኘ ምን አይነት ሰው ነህ???????????መልስህን እጠብቃለሁ፡፡ ቻው፡፡ ምናልባት

የወደፊት አባትህ እኔ😔😔🤦‍♂🤦‍♂


አዲስ አይን መፅሔት ግንጣይ ገፅ
በደቀ ከፈለኘ ወየሻረግ

ፀሀፊው ለሀገሩ ያለውን ፍቅር ሳላደንቅ አላልፍም
እቆርጠዋለሁ አለ እኮ😜😜😜😳😳👏👏👏

ታዲያ እኔ አንቺ አንተ እኛ ሁላችንም ለዚች ምስኪን ሀገር ምን አይነት ልጅ ነው ልናወርሳት ያሰብነው 🤔🤔🤔 ቆዩልኘ🙏😊🙏

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
#ወጣትነት .............ምንድነው??

ሁላችሁም ይሔን ፅሁፍ እንድታነቡት እፈልጋለሁ

ጠብቁኘ 🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

አይ ከንቱነት! አይ የህይወትን ትርጉም አለማወቅ ! አይ የመዝናናትን ትርጉም አለማወቅ!

ለአብዛኛው ለዘመኑ ወጣት መዝናናት ማለት ዝሙት መፈፀም ፣ ጫት መቃም ፣ መጠጥ መጋት ፣ በስካር መናወዝ ፣ እስከምሽቱ ስድስት ሰዓት መጨፈር ፣ ራስን መርሳት ነው ብለው አብዛኞቹ አምነዋል፡፡

አይ ከንቱነት! ወጣትነት ፋሽን ተከታይ ዘናጭ ተሽቀርቃሪ መሆን ማለት አይደለም! ወጣትነት እራስን በሱሶች ማጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት በምክንያታዊነት ሳይሆን በስሜታዊነት እየተነዱ እራስን እና ሌላውን አደጋ ውስጥ መዝፈቅ ማለት አይደለም! ወጣትነት ብዙ ጃንቦ የጠጣ ጀግና ማነው? መባባል ማለት አይደለም!

ወጣትነት ብረት ገፍቶ ደረትን ማሳበጥ ማለት አይደለም! ወጣትነት ሺሻ ቤት ተቀምጦ ጭስ ማቡነን ማለት አይደለም! ወጣትነት በወሲብ ሱስ ከዚህም ከዚያችም ጋር በዝሙት ተወጥሮ ተወጥሮ መልከስከስ ማለት አይደለም! በወጣትነት በጥላቻ እና በዘረኘነት ተሞልቶ በመታወር ፣ መደባደብ እና መነታረክ ማለት አይደለም!

ወጣትነት ተመልሶ የማይመጣውንተፈጥሮ የሰጠችንን ታላቅ ሀይል በማይረባ ነገር ጊዜን ማቃጠል ማለት አይደለም! ወጣትነት ጊዜያዊ ስሜትን ብቻ እያዳመጡ እንደፈረስ ጋሪ መነዳት ብቻ አይደለም! ወጣትነት በሀሜት ፣ በአሉባልታ ፣ በወሬ ሱስ ፣ በአቃቂር ፣ በተንኳሻነት ፣ በቧልት መሞላት ማለት አይደለም!

ወጣትነት ይሔንንም ያንንም ይቺንም ያቺንም መጀንጀን መጀናጀን ማጀናጀን ማለት አይደለም! ወጣትነት በባዶ ጭንቅላት ምርጥ አልባሳትን ለብሶ አልያም ምርጥ የፀጉር ቁርጥ ተቆርጦ እየተጀነኑ በባዶ ኩራት ተወጥሮ መሬትም ለመርገጥ እየተፀየፉ መራመድ ማለት አይደለም!

ወጣትነት በግዴለሽነት በተስፋ መቁረጥ! ፣ ከነፈሰው ጋር መንፈስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በራስ ወዳድ መንፈስ መወጠር እና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ማለት አይደለም! ወጣትነት በማይረባ በቀበሌኛ አመለካከት መታጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት ቁንጫ የምታክል ዕውቀት በመያዝ ይቺ እውቀት ብቻ ትበቃኛለች እያሉ አጉል መመፃደቅ ማለት አይደለም.......

ወጣትነት ባህር ነው፡፡ ወጣትነት ዕውቂያኖስ ነው፡፡ ወጣትነት ከአድማስ ሰፊነት ነው፡፡ ወጣትነት እውቀትን ለማስፋት የምንጋደልበት ሰዓት ነው፡፡ ወጣትነት በማስተዋል ብርሃን መሞላት ነው፡፡ ወጣትነት ችግር ፈጣሪነት ሳይሆን ችግር ፈቺነት ነው፡፡

ወጣትነት በዘረኘነት ተሞልቶ አማራ ፣ ትግሬ ፣ ኦሮሞ ፣ ወላይታ....ቅብርጥሶ እየተባባሉ ቡድን በመስራት ስለ ቀበሌኛ አስተሳሰብ መስበክ ሳይሆን ወጣትነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ከተቻለም ስለአቀፋዊነት እይታን ማስፋት ነው፡፡ ወጣትነት #ፍቅርና #አንድነት መስበክ ነው፡፡ ወጣትነት በዝሙት ባህር መንቦራጨቅ ሳይሆን ስሜትን የመግዛት ጥበብ ማዳበር ነው፡፡

ወጣትነት አንድን ነገር በአንድ ዓይን ሳይሆን በሶስት ዓይን መመልከት ጥበብን ማዳበር መቻል ነው፡፡ ወጣትነት ብርሃን ነው፡፡ ወጣትነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው፡፡ ወጣትነት በቀናነት መሞላት ነው! ወጣትነት እስከ መጨረሻው ጠብታ ህልምን ለማሳካት መፍጨርጨር ነው፡፡

ወጣትነት ማንበብ ነው፡፡ ወጣትነት መጠየቅ ነው፡፡ ወጣትነት ስለዓለም ፣ ስለ ህይወት ፣ ስለ ጥበብ ፣ ስለ ዕውቀት ብዙ ለማወቅ መጠማት ነው፡፡ ወጣትነት ለሌሎች ለሌሎች መኖር ነው፡፡ወጣትነት ለዚች ምስኪን ኢትዮጵያ ምን ልስራላት ብሎ ራስን መጠየቅ ነው፡፡ ወጣትነት ስለነገ ትልቅ ህልም እና ዕቅድ መሰነቅ ነው፡፡

ወጣትነት እሳት ነው፡፡ ወጣትነት ቤንዚል ነው፡፡ ወጣትነት ቅጠል ነው፡፡ ወጣትነት ጤዛ ነው፡፡ ወጣትነት ታክሲ ነው፡፡ ወጣትነት ምርጫ ነው፡፡ ወጣትነት ባህር ላይ ያለች ጀልባ መሆን ነው፡፡ ወጣትነት ከፍርሃት ፣ አልችልም እና አይሳካልኘም የሚለው እስር በጣጥሶ ማለፍ ነው፡፡ ወጣትነት ለአንዳች ስኬት በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው.....፡፡

ኤጭ...........! ከሚለው የአዘርግ መፅሐፍ የተቀነጨበ፡፡

ኤጭ.....!
(በኢትዮጵያ ምድር የተከናወኑ ዘግናኘ ታሪክ)
አዘርግ....2010 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ጃ!.....ይህን መፅሐፍ እንዳነበው ስለጋበዝከኘ አመሰግናለሁ፡፡😍🙏😊

ወጣትነትን በሚገባ ገልፆታል ብዬ አስባለሁ ሁላችንም እራሳችንን እናይበታለን ብዬ አስባለሁ፡፡

#መልካም #በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ እራሳችንን እየጠበቅ በዓሉን ስናከብር በጥንቃቄ ይሁን
#መልካም_አዲስ_አመት

ወጣትነታችንን ለመልካም ነገሮች እንጠቀምበት
ሆነን መታየት ያለብንን ቦታ እስክንደርስ እሩጫችንን ማቆም የለብንም ሩጫችን ከትላንት ማንነታችን የተሻለመሆን አለበት የተሻለ ብቻ ሳይሆን የበለጠን😍🙏😊፡፡

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

wallpaper 😍😱

አዲስ አመት አዲስ ተስፋ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ለውጡ የአመት ብቻ እንዳይሆን እንጠንቀቅ!!

ከሌለን ያለን ይበልጣል ይህን ስል ሁላችንም ጋር ከሌሎች የተሻለ ነገር አለን እያልኩህ ነው በነገሮች ልክ አትለካው አብሶ በጣኸው ነገር ብቻ አትለካው፡፡
እውቀትም ቢሆን አንፃራዊ ነው፡፡
ሁሉም ሰው አንድ ነገር ከኛ በተሻለ ያውቃል ስለዚህ እኛም ከሰዎች በሆነ ነገር የተሻልንን ነን ማለት ነው፡፡

ይህም ማለት እኛ ጋር ሰዎች ሚፈልጉት ነገር አለ ማለት ነው፡፡
ያ ነገር ደግም ለጥሩ ነገር ስንጠቀምበት ውጤቱ አመርቂ ነው፡፡
ፈገግ በል አንተን ማንም ሊሆኖን አይችልም አንተ የፈጣሪ ስራ ነህ አስበኸዋል አንተን ሰው የሰራህ ቢሆን ያንተ ፊት ስንቴ ሊደገም እንደሚችል😜👊 ስለዚህ በሁሉም ነገር አንተን ሊመስል ሚችል የለምና ቀና ብለህ የላይኛውን አመስግነው፡፡

ያለፈውን ጊዜ ቆም ብለህ አስበው እስኪ በመጀመሪያ ስለራስህ አስብ አንተነትህ ማለቴ ፀባይህ.........እያንዳንዱ የምታደርጋቸው ድርጊቶች ምን ጠቀመህ ምንስ ጎዳህ ቀጥል አብረውህ ያሉትንስ ቤተሰብ ጓደኛ ዘመድ.... ጠቀመ ጎዳ?🤔

ለዚህ መልስ መልሰህ ከዛ ቆም ብለህ እራስህን እየው ምክንያቱም ይህን የሚጎዱህን ፀባዮችህን ካልተውክ የተቀየረው አመተ ምህረቱ እንጂ አንተ አይደለህም ዛሬ 23 ዓመትህ ነበር ቀጣይ ደሞ 24.....ዕድሜ ብቻ ጨመርክ አንተ ግን ያው ነክ እኔ ግን ያው ነኘ አንቺ ግን ያው ነሽ
እኛ ግን ያው ነን ይሔ ያናዳል🤦‍♂🤦‍♂

በአዲስ አመት አዲስ ነገርን ፍለጋ ከመጥፎ ፀባያችን ቢያንስ በግማሽ መቀነስ አለብን.....ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለኛ ብለው ለሚጨነቁ ስንል፡፡
የኛን መለወጥ ለሚናፍቁ ስንል ለውጥን ለምን አንሻው ለምን አንይዘውም ለምንያን ያክል እራስ ወዳደድ እንሆናለን?......

ስለመልካምነታችን ምን መባል አያስፈልገውም ይበል ይጠንክር ይበርታ እንጂ፡፡

አዲስን አዲስ ለማድረግ እንትጋ እንጠንክር እንበርታ ሁሌም ይህን እናስብ ከዛሬ ነገ የተሻለ እንደሚሆን ተስፋ እናድርግ የኛ ህይወት በሰው አልተጀመረምና በሰዎች ወሬና ነቀፋ የሚደናቀፍ እና የሚወድቅ አይደለምና፡፡

ያንተ የህይወት ዘዋሪው #ታላቁ_የድንግል_ልጅ ነው እንጂ፡፡

ሰዎች ስላሉህ አይደለም እንዲህ ሆነ ማለት
የሰዎች ልማዳቸው ነው፡፡

ያንተ ህይወትህ መሪው አንድ #አላህ ነው፡፡

አንተን ሊጥሉህ ሁሌም ጉድጓድ ይቆፍራሉ ግን በቆፈሩት ጉድጓድ መውደቃቸው አይቀርም

ምክንያቱም የአንተ ህይወት መንገድ ጠራጊው #ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው፡፡


ተስፋ አለን እንደርሳለን ተስፋ አለን ለዛሬ ብቻ አይደለም ነገንም ለማየት ነው ከትላንት ያለፍነው፡፡ እንበርታ እንጠንክር እኛ ለሀገራችን እናስፈልጋለን በኡነት እኛ ለኢትዮጵያ እናስፈልጋታለን ለዚህ ኮትኩቶ ያሳደገን ሚስኪን ህዝብ ከኛ ሚጠብቀው ነገር አለ እና እንበርታ፡፡

NOT I LOVE YOU #አፈቅርኃለሁ NOT SORRY #ይቅርታ NO THANK YOU ፅድት ያለው አማርኛ አቻ ትርጉሙን #አመሰግናለሁን..........#እንልመድ...........................#መረዳዳት......#መተሳሰብ.....እንጠቀምባቸው የህይወት መሪያችን እናድርጋቸው ገነትን ማየት ያለብን ሞተን ሳይሆን ገነትን ምድር ላይ እንስራ፡፡

ከመጥፎ እንሽሽ! መጥፎውን! አንናገር!

ግን
"የመጥላት #ጥሩ ነገር አለው ለምሳሌ #መጥፎን ነገር መጥላት"
ብሎ የለ ታላቁ😍👏 #ኤልያስ_መልካ

የተቸገሩትን ረድተን ያስቀየምነውን ይቅር ብለን የተጣላን ታርቀን ቂምን ተንኮልን ጥለን ለተደረገልን ብቻ ሳይይሆን ላልተደረገልንም አመስግነን(ምክንያቱም ሚጠቅመን ቢሆን ለኛ እሱ የላይኛው ያሳካልን ነበርና)....ለሁላችንም

መልካም በዓል መልካም አዲስ አመት እንዲሆን ከልቤ እመኛለሁ፡፡

አብይ አንዱአለም(የማርያም ልጅ ነኘ)
@jahABP 😊🙏😍

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD