Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
ገና አራት አመቷን ዘንድሮ ነው ምትይዘው
እቤት ለበዓል ልትጠይቀን መጣች......


በጨዋታ መሃል ማንን ትመስያለሽ አባትሽን ወይስ እናትሽን ስትባል ምን ብትል ጥሩ ነው.............እኔ ምመስለው #አብይ ነው አለች 😔😔😔😍😍😍😍የኔ ፍቅርርርር፡፡

አባቷ ደግሞ ይናገራል......"እነ አብይ ጋር ልንሔድ ነው ስላት በደስታ ፈነደቀች....ዛሬ ትምርት የለውም አለች......አዎ ዛሬ በዓል ነው የለም...ቶሎ በይ አልኳት ከዛ መልበሷን አቁማ ወረቀት እስራስና ከለሮቿን አወጣች....ምን ልታደርጊ ነው....ለአብይ ስዕል ስዬ ልሰጠው ነው....እንዴ ይኸው ከመጡት ስዕሎች ቆንጅየውን እንወስድለታለን ብላት አይሆንም ሞቼ እገኛለሁ እራሴ የሳልኩት ነው ምወስድለት ብላ ለቅሶ........😢😢😢😔😔......በቃ እሺ እሺ ሳይለት ወይ ጉዴ ብዬ ይኸው በስንት መከራ ጨረሰችው ለዛ ነው ያረፈድኩት አፉ በለኘ ወንድሜ አለኘ"

😂😂😂

ሃኒቾዬዬዬዬ የኔ በጣም እኮ ነው ምወድሽ በጣም ምን አድርጌልሽ እንደምቶጂኘ ባይገባኘም....😍😔😍😢🙏😢

ስዕሉን ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY



ሃኒቾ የኔ እድግ በይልኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY



መልካም ዕለተ ሰንበት ተመኘሁ
ትውልዳችን ታላላቆችን መስማት አይፈልግም አባቶችም ጥጉን ይዘው ትውልዱን ይታዘቡታል
ያዝኑበታልም፡፡

አዲሱ አመት ዝቅ ብለን አባቶችን የምንጠይቅበት ፣ የምንሰማበት ፣ ዕውቀትን የምንቀስምበት እንዲሆንልን እመኛለሁ፡፡🙏😊🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

"እግዚአብሔር በፍቅር ኃይሉ ሰዎችን ወደ ራሱ ይስባል፡፡
ሰዎች ግን ፍቅሩን ካልተጠለሉ የቁጣው እሳት ይበላቸዋል፡፡
እግዚአብሔር ማዳንመ መግደልም ይችላል፡፡
የሚጠቀመው ግኅ የማዳን ሀይሉን ብቻ ነው፡፡
ሰዎች ግን በእንቢተኘነታቸው ሲፀኑ እግብዚአብሔር ይቀጣል፡፡

እግዚአብሔር ፍቅር ብቻ እንዲሆንላቸው የሚመኙ ሰዎችን "ይቀጣል" ሲባሉ አይመስላቸውም፡፡
እግዚአብሔር ግን ፍቅር ነው ፣ ፈራጅም ነው፡፡
ፍቅሩና ፍርዱ አይነጣጠሉም፡፡
ምክንያቱም የፍቅሩም የፍርዱም መሰረቱ እውነት ነውና፡፡

እውነት ደግሞ እራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡
ስለዚህ እግዚአብሔር ባሕሪዩን ስለማይክድ አፍቃሪ ነው፡፡ ፈራጅም ነው፡፡
ፍቅር አካል ነሥታ በመንገድ ብናገኛት ብቻዋን አናገኛትም፡፡ በቀኘና ቀግራ የከበቧት ሁለት ወዳጆች አሏት፡፡
እነርሱም:- #እውነት እና #ፍትህ ናቸው፡፡

እግዚአብሔር ይቆጣል ስንል ትግስት ያጣል ማለታችን አይደለም፡፡
እርሱ ፃድቅ በመሆኑ ኃጢያትን ይቀጣል፡፡
እግዚአብሔር ኃጢያትን ባይቀጣ ኖሮ ጻድቅነቱ ባልታወቀ ነበር፡፡ እግዚአብሔር የሚቀጣው #ኃጢያትን ነው፡፡

#ኃጢያትን_ሲቀጣም_ከኃጢያት_ጋር_የሚያገኘውንም አብሮ ይቀጣል፡፡"

😊 መልካም አዲስ አመት ተመኘሁ 🙏

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ
ከቅጣቱ ይጠብቀን
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ሪፖርተር፡- የሠራሀቸውን ሙዚቃዎች በሙሉ በአንድ መጠቅለል ባይቻልም፣ በተደጋጋሚ ከምታነሳቸው ጽንሰ ሐሳቦች መካከል ሰው መሆንን፣ ፍቅርና ጥላቻን፣ አገርንና መንፈሳዊነትን እንዴት ትገልጻቸዋለህ?


#ኤልያስ፡- "ሰዎች ስለሆንን አንዳንዴ መሳሳታችን አይቀርም የሚለውን አላምንበትም፡፡
#ለኔ_ሰው_መሆን_ጥሩ_መሆን_ብቻ_ነው፡፡
ሰውነት ለኔ ለመስተካከል፣ እግዚአብሔርን ለመፍራት መሄድ ነው፡፡
መሳሳት አይቀርም በሚል ምክንያት ካልተሳሳትክ አትማርም የሚል ነገር በፍፁም የለኝም፡፡
ፍቅር ብዙ ዓይነት ነው፡፡
#መጥፎ_ነገርን_መውደድ_ፍቅር_ስለሆነ_ብቻ_ጤነኛ_አይደለም፡፡
ሰው መውደድ ያለበትን መምረጥ አለበት፡፡
የራሱን ልብ ብቻ እያዳመጠ መሄድ የለበትም፡፡
ከሱ በላይ አስተማሪ #የእግዚአብሔር #ቃል አለለት፡፡
ልቡን ብቻ ወይም ልቡ የማይታመን ሰውን እያዳመጠ ከሄደ እርስ በርስ መጨራረስ ነው፡፡

#ጥላቻ ደግሞ #ጥሩም ነገር አለው፡፡
ለምሳሌ #መጥፎ_ነገርን_መጥላት፡፡

አገር ለኔ #ኢትዮጵያዊ #ሰው ነው፡፡
ቁሳቁስ ያልፋል፡፡
#አገር_ማለት_ከሌላው_ለራስ_ወገን_ማዳላት_አይደለም፡፡
በመሬት የተነጠፈ ነገር አገር ነው ብዬ አላስብም፡፡
#በእግዚአብሔር_ቃልም_ሰው_ይበልጣል፡፡
መንፈሳዊነት የግድ ስለሆነ ሰው መንፈሳዊ ላይሆን አይችልም፡፡
የጥሩ ወይም የመጥፎ መንፈሳዊነት አለ፡፡
መንፈሳዊነት እግዚአብሔርን መፍራት ከሆነ ጥሩ ነው፡፡"

ከሪፖርተር ጋር ያደረገው ቆይታ የዛሬ አራት አመት ህዳር 2009 ቀንጭቤ ያቀረብኩት፡፡

ንግግሩ ሰምተህ ከዛ በፊትም ሆነ በኀላ የሰራቸውን ስራ ስትመለከት ምን ያህል ንግግሩን ህይወቱን በስራዎቹ እንደሚገልጥ ታይበታለህ፡፡

ኤላ አንተ ታላቅ ነህ ሁሌም በልባችን ትኖራለህ

😍😔😢😢😢😍😍😊🙏
ሙዚቃን እንድናውቅ ያደረከን አንተ ትለያለህ፡፡

😢😭😢ፈጣሪ🤦‍♂🙇🤦‍♂🙇

ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን

@jahABP ነኘ😊🙏

የኤላን ራዕይ ለማሳካት አውታርን አፕሊኬሽንን በመጠቀም የኤላ ስራዎችን እንዲሁም የተለያዩ የሀገራችን ድምፃውያንን ዘፈኖች እንድትሰሙት እንድታዳምጡ አደራ እላለሁ፡፡

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY



በመጥፋት ላይ ያለው ባህላችን

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
"በቱሪዝም ሀብቷ ላይ #የተኛች ሀገር

ዛሬ ስለ አንድ ግዙፍ ሰው ኢትዮጽያዊ እናወጋለን፡፡

እኛ ኢትዮፕያዊያን ይህን ታላቅ ስብዕና ለተቀረው አለም ለማስተዋወቅ ቅንጣት ታህል ሙከራ አድርገን አናውቅም ነገር ግን በአሁን ሰዓት ይህን ሰው በትንሹ ሁለት ቢሊዮን ሰዎች ያውቁታል በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ያደንቁታል - ኧረ እንደውም ይናፍቁታል፡፡


ግብፃውያን ያ ሰው የኛ ወገን ቢሆን ኖሮ በ-የአመቱ ቀን ወስነን እንዘክረው ነበር ይሉለታል የሆነ የአለም ክፍል ላይ ተገኘተህ ሀበሻ መሆንህን ሲያውቁ ኦ የዚያ ታላቅ ሰው ልጅ ይሉኃል፡፡

ይህን ስብዕና የማስተዋወቁ መንፈሳዊ ፣ ባህላዊ ፣ ታሪካዊ.....ሌላም ሌላም ፋይዳ ሁሉን ትተን በቁስ ቋንቋ ብናወጋ እንኳን ምናልባት በየአመቱ በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገቢ ይኖረን ነበር፡፡

ይህ ድንቅ ሰው ማነው እናወጋለን........."


ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY

"እግዚአብሔር ዛሬ ወደ እኛ ቢመጣ በደስታ ከሚቀበሉት ወይስ ከኃጢያታቸው የተነሳ ከሚሸሹት ወገን እንሆን?

ሰዎች ሞትና ፍርድን የመጨረሻውንም የፍርድ ቀን ይፈራሉ፡፡

እንዲህ ከሆነ ደግሞ ኃጢአትን መተው ነው፡፡
የኃጢአተኞች የመጨረሻው ዕጣፈንታ ፍርሃትና ሞት ነው፡፡"

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሸኖዳ ፫ኛ የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ
ቅድስት ስላሴ ካቴደራል
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
#መውደድማ_ማፍቀርማ_እንደሷ ነው፡፡

ብዙ ዞሬ ብፈልግም የነሱን ፍቅር የሚያክል ብዙ መስዋትነት ተከፍሎበት የቆየ ፍቅር እስካሁን አላየሁም በኡነት በጣም ነው ደስ ሚሉት ብታዩ ከነጭቅጭቃቸው ከነኩርፊያቸው ከነ ሁሉ ነገራቸው ነው ሚያስቀኑት🔥

ወንድሜ ታድሎ እሷ አለችው😍🕺

እሷ ፍቅረኛ ብቻ አይደለችም ሁሉም ነገር ናት እህትም....ጓደኛምም....ወንድምም.....እናትም.....አስተማሪም.....ፈታኘም.....አራሚም..............ተቆጪም.....ሃሳቦቹን....ደጋፊም.....ተቃዋሚም...........በስኬቱ....ቀድሞ አጨብጫቢ.....በውድቀቱ ሁሌም ከጎኑ.....ብቻ ብዙ ብዙ ለኔ አንቺ ለሁሉም ሴቶች የኡነት #ምሳሌያቸው ነሽ #የአፍቃሪ ሴት ምሳሌ ነሽ፡፡

እኔ እሱን ሁሌ እንዲህ እለዋለሁ ወንድሜ ይህን ስልህ ከልቤ ነው፡፡
አንተ እሷን ማጣት የለብህም እሷ የተሟላች ሰው ነች፡፡ ታውቃለህ ይቺ ልጅ የብዙ ሰው ምኞት ነች ግን ያንተ ነች ያንተ፡፡
በጣም ነው ደስ ሚለው እባክህ አንተ ለሷ እንደሷ አይነት ሰው ሁንላት እለዋለሁ፡፡

ክቡራንና እና ክቡራት ይቺ ልጅ ዛሬ ልደቷ ነው በእናንተ ፊት እንኳን ተወለድሽልን ለማለት እፈልጋለሁ፡፡

ሊዱዬ #የኛ ካንቺ የተማርኳቸው አያሌ ነገሮች አሉ፡፡
አንቺ ለፍቅር የከፈልሽውን መስዋትነት አይቼ እራሴን ሳየው ሁሌም ያንስብኛል፡፡

ወንድሜ አንቺ ስላለሽው እድለኛ ነው፡፡
መልካም ልደት እንኳንም ተወለድሽልን ረጅም እድሜ ከጤና ጋር እመኘልሻለሁ፡፡

ለሚዜነት ያብቃኘ😍🙏😊
🤩🙌👫💑💍🤵👰🤴👸👪👨‍👩‍👧‍👦🌹🥂🥂❤️🎈🎂🎂🎂
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ስሙ #ቢላል_ረባህ ይባላል፡፡
ወላጅ እናቱ ከአረብ ትላልቅ ጎሳዎች መካከል አንዱ የነበረው #የጁመህ ጎሳ አባል የሆነ ግለሰብ ዘንድ ባሪያ ስለነበረች በዘመኑ ስርዓት እና አስተሳሰብ መሰረት ልጇ ቢላልም ያሳዳሪው ንብረት ሆነ፡፡

ባሪያ እንደሰዋዊ ፍጡር አይታይም ነበር፡፡ እናም ቢላል አሳዳሪውን በትጋት እና በታማኘነት ከማገልገል የዘለለ ምንም አይነት ሚና ያልነበረው ፍጡር ነበር፡፡
በህይው ውስጥ አንዳችም መብት የሌለው ስለነገም ምንም ተስፋ የማይታየው ተናጋሪ እቃ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ቢላሌ አሳዳሪውቹ እንደሚያስቡት ፈርጣማ አካል ያለው ታማኘ አገልጋይ ብቻ ሳይሆን ብሩህ አእምሮ የታደለው ሰው ነበር፡፡
አንድ ሰሞን አሳዳሪው #ኡመያህ እና ሌሎች የመካ ሹማምንት አንድ ጉዳይ እረፍት እንደነሳቸው አስተዋለ፡፡

ሙሐመድ ስለተባለ አብዝተው ሲወያዩ አደመጣቸው፡፡ ነቢይ ነኘ ማለታቸውን ያስተባብላሉ ግን ደግሞ እጅግ ያከብሩታል፡፡
አምርረውን ይጠሉታል ግን ስለ እውነተኘነቱ ስለታማኘነቱ ስለደግነቱ ይመሰክሩለታል፡፡
ምን ይሻለናል? እያሉ ይጨነቃሉ፡፡
ውስጣቸው በግጭት ተሞልቶ ይዋልላሉ፡፡

በቃ ከዛሬ ጀምሮ እብድ ነው ብለን እናሶራበታለን የሚሻለን ይኸው ነው ማንም ሰኽ እንዳይሰማው ማድረግ ሲባባሉ ይታዘባቸዋል፡፡ ካጠገባቸው የሚታዘባቸው ሰው እንዳለ አያስቡም ምክንያቱም ቢላል ለእነርሱ ተናጋሪ እቃቸው ነው፡፡ በዚህ መልኩ ስለ ነብዩ መሐመድ የሰማው ቢላል ስለ እርሳቸው የበለጠ ለማወቅ ከፍተኛ ጉጉት አደረበት፡፡

ሙሐመድን ለመከተል የገዳቸው ብቸኛ ምክንያት ኢኮኖሚያዊ ጥቅማችን ይነካል ብለው መስጋተቸው ብቸኛው አመንክዮአቸው ያባቶቻቸን ን አንለቅም የሚል ግትርነት መሆኑን አረጋግጧል፡፡ አንድ ቀን ካሳዳሪዎቹ ተደብቆ ነቢዩን አገኟቸው ሁሉንም ከአንደበታቸው ካዳመጠ በኀላ አመነ፡፡ ነቢዩም እምነቱን በልቡ ይዞ እንዲቀመጥ መከሩት፡፡

ቢላል #ሰው ሆነ

እንደተለመደው የመካ ሹማምንት አባ #ሱፋያን ቤት ተሰብስበዋል፡፡ አማር የሚባል ወጣት ከፊት ለፊታቸው ተንበርክኳል፡፡ ጥፋቱ ደግሞ የነቢዩ ተከታይ መሆኑ ነበር፡፡
ሹማምንቱ ወጣቱን ያዋክቡታል፡፡
ቢላል ከወጣቱ በቅርብ እርቀት ቆሞ ሁሉንም ይታዘባል፡፡
ነቢያችሁ የሰው ልጆች ቀሙሉ እኩል ናቸው እያለ ያስተምሯችኀል አሁን ይሔ ባሪያ ከእኔ ጋር እኩል ነውን? ብሎ አንዱ ሹም ለተያዘው ወጣት ጠየቀ፡፡

ወጣቱም ምንም ሳያመነታ አዎ ብሎ መለሰለት ሰው ከሰው የሚበላለጠው በስነምግባሩ በስራው መሆኑን ነገራቸው፡፡ በሳቅ ፈረሱ ጅሎች ተሳለቁበት እንከፎች ወዲያው የቢላል አሳዳሪ ትዕዛዝ አስተላለፈ ግረፈው!! ቢላል አለንጋውን ጨብጦ ከወጣቱ ፊት ተገተረ፡፡ ግን እጁን ማንሳት አቃተው፡፡


በዚያች ቅፅበት ምን ያስብ እንደነበር ሲነገርም አልሰማሁም ተፅፎም አላነበብኩም ስገምት ግንእንዲህ እያለ ከእራሱ ጋር የተሟገተ ይመስለኛል፡፡ ይህ ወጣት እኔ ክቡር ሰው መሆኔን ተናግሮ የሚደርስበትን ለመቀበል ሲዘጋጅ እኔ እንዴት እርሱን ገርፌ በገዛ እጄ ሰው አለመህኔን አረጋግጥላችኋለሁ?

አይ አላደርገውም የሁሉም አይነቢላል ላይ አረፈ ፡፡ ወጣቱ አማር እንዲገርፈው ተማፀነው፡፡ ቢላል እምቢ አለ ቢላል ሰው ሆነ፡፡ ሹማምንት እየሆነ ያለውን አምነው ለመቀበል አልቻሉም፡፡ በቁጣ ነደዱ፡፡ ተፈጥሮ የተዛባች መሰላቸው፡፡
"ዛሬ እንደ ወትሮዋ ጸሀይ የምትጠልቅ አይመስለኘም" አለ ቢን ኸሊፋ አለም ተዘበራርቃበት፡፡

የህሊና ነፃነት እና ሉዓላዊነት

የመካ ሹማምንት ተፈጥሮ እንደተዛባባቸው እንድትቀጥል አልፈለጉም ነገሮች ሁሉ ወደነበሩበት እንዲመለሱ ለማድረግ ቢላል ላይ ዛቱበት እርሱ በእምቢታው ፀና እናሰቃይኃለን አሉት ያሻችሁን አድርጉ አላቸው፡፡ ዝተው አልቀሩም ያሰቃዩት ጀመር አልተበገረም፡፡ በእምነት የሚጋሩ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የሰው ዘርን በሙሉ የሚያኮራ አቋም ወሰደ፡፡

ሰዎች ሁሉ እኩል ናቸው ሰውነት በቆዳ ቀለም አይለካም ትልቅነት በስራ እንጂ በዘር አይደለም የህሊናነፃነትና ሉዓላዊነት ምድርን ሚሞላ ንዋይ አይለወጥም የሚል ትምህርት አስተማረ በአንደበቱ ሳይሆን በተግባር፡፡

ሹማምንት ቢላልን ወደነበረበት ለመመለስ ራቁቱን ገረፉት አሸዋ ላይ ቀቀሉት ደረቱ ላይ ቋጥኘ ጫኑበት ወይ ፍንክች በጽናቱ አሳፈራቸው፡፡ ቢላል አሁን ሰው እንጂ ተናጋሪ እቃ አይደለም የራሱ ሀሳብ አለው የእራሱ እምነት እና አቋም አለው እናም ያለፍቃዱ ምንም ሊያደርጉት አይችሉም አካሉን እንጂ ህሊናውን ማዘዝ አይችሉም፡፡

ትላንትም ምንም የነበረ ባርያቸው ተናግረው ሆነ አሰቃይተው ማሳመን ባለመቻላቸው በሀፍረት ተሸማቀቁ፡፡ ደብድበው መግደል ይችላሉ ግን ሞቱ ከተሰማቸው ቅሌት አይታደጋቸውም፡፡ የትላንት ንብረታቸው ሰው ሆኖ አሸንፉቸዋል፡፡
ክብራቸውን ለመጠበቅ ሀፍረታቸውን ለመቀነስ ሌላ ዘዴ ዘየዱ በሚስጥር ተደራደሩት፡፡

በቃ ሌላውን ሁሉ ይቅር ስለ አማልክታችን ጥቂት በጎ ቃላትን ተናገር እና እንተውህ አሉት ይህንን እንኳን ሳይቀበላቸው ቀረ፡፡
የትላንትን ተራ አገልጋያችን የእራሱ ሀሳብ ኖሮት ጥንቂ አለን ብለው ተሰቃዩ፡፡ እባክህን መሳቂያ መሳለቂያ አታድርገን ያልንህን አድርግና አንተም ከስቃይ ተገላገል እኛንም ከጉድ አውጣን ብለው ለመኑት፡፡

አልሆነም በዚህ መሐል አቡበክር ደረሱናይህ ባሪያ ከአሁን በኀላ ምንም አይፈይዳችሁም ለእኔ ሽጡልኘ አሏቸው፡፡ ከጥቂት ድርድር በኀላ ተስማምተው ሸጡላቸው፡፡
ወዲያው ነፃ ሰው ሆኖ ነቢዩ ዘንድ በመምጣቱ ትልቅ ደስታ ሆነ ከዚያች እለት ጀምሮ ለአፍታ ከነቢዩ ሳይነጠል ኖረ፡፡

መካ ላይ ጎፉ በዝቶባቸው ወደመዲና ሲሰደዱ አብሮ ተሰደደ፡፡ ነቢዩ የጀነት ሰው ይሉታል እርሱ ግን ሀበሻዊ ባርያ ነኘ ይላል፡፡ የነቢዩ ባልደረባዎች መስዕዋትነቱን በማሰብ ልዑካችን እያሉ ያሞካሹታል እርሱ ግን በትህትና የትላንት ማንነቱን ያስታውሳቸዋል፡፡
መዲና ከተሰደዱ በኀላ ነብዩ '#ሙአዚናቸው' አደረጉት፡፡

ስንቱ ተመኘቶ ያላገኘውን ማዕረግ ለቢላል ተሰጠ፡፡

ዋናው ጉዳይ

ኢትዮጵያ እንደ ዋዛ ከጣለቻቸው ሀብቶች መካከል አንዱ የቱሪዝም ሀብቷ ነው፡፡ እኔ ባለኘ መረጃ መሰረት በንጉስ ነጃሺ እና በቢላል ዙሪያ ከቱሪዝም ጋር በተያያዘ ተገቢ ጥረት ቢደረግ ኖሮ አሁን አገሪቱ በመስኩ የምታገኘውን ገቢ 100% ማሳደግ ይቻል ነበር፡፡ ይሔ ዝም ብሎ ምኞት ብቻ አይደለም፡፡

ነጃሺን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የተለያዩ ጥናቶች መደረጋቸው ይታወቃል ሲምፖዚየሞች ተካሒደዋል የዚህ እንቅስቃሴ ተሳታፊ ከነበረ ሰው ዘንድ ባገኘሁት መረጃ መሰረት ከሆነ ምዕራባውያኑ ትተን ከምዕራብ አፍሪካ እና ቱርክ እና ኤንዶኖዢያ ከመሳሰሉት ኤዢያ አገሮች ብቻ በየአመቱ 300 ,000( ሦስት መቶ ሺህ ) ጎብኚዎችን መሳብ ወይም ማስተናገድ ይቻላል፡፡

ባይሆን ከእኛ ሁለት ስራዎች ይጠበቁብናል
የሐላል ቱሪዝምን ተሞክሮ ከሌሎች ሀገሮች ወስዶ ተግባራዊ ማድረግ እና እንደ ቢላል አይነት የማይዳሰሱ ታኢካዊና ባህላዊ ውርሶችን በፅሁፍ እና በፊልም በቅጡ ማደራጀት እንዲሁም ከተቻለ መቼም ባህልና ሚኒስቴር ለዚህ የሚሆን አቅም የሚያጣ አይመስለኘም 3D ቴክኖሎጂ በመጠቀም ጎብኚዎችን ታሪካዊ ትዕይንቶች እዚያው እቦታው ላይ የተገኙ ያህል እየተሰማቸው እንዲጎበኙ ማድረግ፡፡

ፍትህ መፅሔት ቅፅ 01 ቁጥር 11 ጥር 2011 ዓ.ም
በዐብዱልከሪም ታጁ


ሀበሻዊው ቢላል😍👏😊🙏 እንዴት አገኛችሁት?

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ነገ ቅዳሜ አይደለ ቅዳሜያችንን በአንድ ዘፈን እንጀምራታለን እስኪ አዳምጡት


ሁላችንም እራሳችንን እንፈትሽበት፡፡

አንተም አንቺም እሱም እሷም አዳምጡት ጥሩ መልክት አለው ብዬ አስባለሁ፡፡

የነገ ሰው ይበለን😊😍🙏

ዋናው መኖር ነው ለዛሬ ብቻ አይደለም ነገንም ለማየት ነው ከትላንት ያለፍነው፡፡
ተስፋ አለን እንደርሳለን......ወደ ነገ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂ ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂

@jahABP.......ነኘ 😊🙏
Audio
ተረጋጋሽ ወይ

ጎሳዬ ተስፋዬ

መልካም ቅዳሜ ተመኘሁ😍🙏😊 @jahABP ነኘ
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ወደፊት ከሚስቴ ጋር ምጣለላው የማንቼን ጨዋታ አያለሁ አታይም በሚለው ይመስለኛል😜😜

የአመቱ የመጀመሪያ ጨዋታ በግዙፉ
በምድር ገነት ኦልትራፎርድ😍😘❤️
መልካም ዕድል ለውዱ ክለባችን ማንችስተር ዩናይትድ👌🔥🔥🔥
AB PHOTOGRAPHY


መልካም ዕለተ ሰንበት

የምስጋና ቀን.....🙏🙏🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ለሰኞ😍🙏😊
ወጣቱ ድምፃውያን #ሳሚ_ዳን ሁለቱንም አልበሞቹን በደንብ ሰምቼለታለሁ እወዳቸዋለሁ ብዙ ሰዎች በሱ የመጣ ያበሳጩኛል ያለሙያው ነው የገባው ይሉኛል እኔ ደሞ ያለሙያው ቢሆኖማ እንደዘመኑ ዘፋኞች የመሸታ ቤት ሙዚቃ ብቻ ያወጣ ነበር ይህን ስል ሌሎች የለቀቃቸውን ነጠላ ዜማዎች ልል ፈልጌ አይደለም ስለአልበሙ ነው ማወራው እላቸዋለሁ፡፡
ብቻ እናንተ ሰምታችሁ ትፈርዳላቹ፡፡


ለኔ ግንእራሴን እንድፈልግ ስለሚያግዙኘም ክፍተቶቼን እንድሞላም ያደርጉኛል እና ለሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን በዚህ ሙዚቃ እንድትጀምሩት እጋብዛለሁ፡፡


በሀይልህ ትመካ ይሆናል ባለህ ነገር ሌሎችን ትጨቁን ይሆናል ባለጊዜ ሆነህ ሌሎችን እያሰቃየህ ይሆናል በጣም አስመሳይ ትሆን ይሆናል ማንንም ልትዋሽ ትችላለህ......ማንንም ልትበድል ትችላለህ ሁሉንም መጥፎ ነገሮች ልታደርግ ትችላለህ.........የምታደርገው ነገር አንተን ምንም ላይመስልህ ይችላል የሚነግሩህ ሰዎችን ሁሉንም አልሰማ ብለህ ይሆናል ግን...መጨረሻ........

ህሊና....ሲታመም....በምን.....ይድናል🤔🤔.....ይልኻል

ስለዚህ ቆም ብለህ አስብ፡፡ ያለህበት ነገር ብዙሀንን እየጎዳ እንዳይሆን እራስ ወዳድነት አጥር እንዳትታጠር የጥፋት ደቀመዝሙር እንዳትሆን........ምክንያቱም.......
ህሊና......ሲታመም....በምን.....ይድናል🤔🤔.....ይልኻል፡፡


ተስፋ አለን እንደርሳለን ለዛሬ ብቻ አይደለም ለነገምነው ከትላንት ያለፍነው🙏😍😊....

@jahABP....ነኘ 😊🙏
Track 9
Unknown artist
ሳሚ ዳን ሁለተኛ አልበም "Track 9"

ህሊና ሲታመም በምን ይድናል🤔🤔

"ማንም ቋሚ የለም በምድር ላይ ሁሉም መጨረሻው የሞት ሲሳይ
ፍርዱን የሚጠብቅ ካለው ከበላይ፡፡"

ህሊናህን ልትዋሸው አትችልም ለምን ብሎ ይጠይቅኃላ ሰላምህም አይሰጥህማ ይጮኸብኻል፡፡

ህሊናችን ሳይታመም መልካሙን ምናስብበት ሳምንት ይሁንልን

@jahABP ነኘ😊🙏😍
ጓደኘነት🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY


በቱሪዝም ሀብቷ ላይ የተኛች ሀገር

በትንሹ ፈጠራ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD