Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ስሙ #ቢላል_ረባህ ይባላል፡፡
ወላጅ እናቱ ከአረብ ትላልቅ ጎሳዎች መካከል አንዱ የነበረው #የጁመህ ጎሳ አባል የሆነ ግለሰብ ዘንድ ባሪያ ስለነበረች በዘመኑ ስርዓት እና አስተሳሰብ መሰረት ልጇ ቢላልም ያሳዳሪው ንብረት ሆነ፡፡

ባሪያ እንደሰዋዊ ፍጡር አይታይም ነበር፡፡ እናም ቢላል አሳዳሪውን በትጋት እና በታማኘነት ከማገልገል የዘለለ ምንም አይነት ሚና ያልነበረው ፍጡር ነበር፡፡
በህይው ውስጥ አንዳችም መብት የሌለው ስለነገም ምንም ተስፋ የማይታየው ተናጋሪ እቃ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ቢላሌ አሳዳሪውቹ እንደሚያስቡት ፈርጣማ አካል ያለው ታማኘ አገልጋይ ብቻ ሳይሆን ብሩህ አእምሮ የታደለው ሰው ነበር፡፡
አንድ ሰሞን አሳዳሪው #ኡመያህ እና ሌሎች የመካ ሹማምንት አንድ ጉዳይ እረፍት እንደነሳቸው አስተዋለ፡፡

ሙሐመድ ስለተባለ አብዝተው ሲወያዩ አደመጣቸው፡፡ ነቢይ ነኘ ማለታቸውን ያስተባብላሉ ግን ደግሞ እጅግ ያከብሩታል፡፡
አምርረውን ይጠሉታል ግን ስለ እውነተኘነቱ ስለታማኘነቱ ስለደግነቱ ይመሰክሩለታል፡፡
ምን ይሻለናል? እያሉ ይጨነቃሉ፡፡
ውስጣቸው በግጭት ተሞልቶ ይዋልላሉ፡፡

በቃ ከዛሬ ጀምሮ እብድ ነው ብለን እናሶራበታለን የሚሻለን ይኸው ነው ማንም ሰኽ እንዳይሰማው ማድረግ ሲባባሉ ይታዘባቸዋል፡፡ ካጠገባቸው የሚታዘባቸው ሰው እንዳለ አያስቡም ምክንያቱም ቢላል ለእነርሱ ተናጋሪ እቃቸው ነው፡፡ በዚህ መልኩ ስለ ነብዩ መሐመድ የሰማው ቢላል ስለ እርሳቸው የበለጠ ለማወቅ ከፍተኛ ጉጉት አደረበት፡፡

ሙሐመድን ለመከተል የገዳቸው ብቸኛ ምክንያት ኢኮኖሚያዊ ጥቅማችን ይነካል ብለው መስጋተቸው ብቸኛው አመንክዮአቸው ያባቶቻቸን ን አንለቅም የሚል ግትርነት መሆኑን አረጋግጧል፡፡ አንድ ቀን ካሳዳሪዎቹ ተደብቆ ነቢዩን አገኟቸው ሁሉንም ከአንደበታቸው ካዳመጠ በኀላ አመነ፡፡ ነቢዩም እምነቱን በልቡ ይዞ እንዲቀመጥ መከሩት፡፡

ቢላል #ሰው ሆነ

እንደተለመደው የመካ ሹማምንት አባ #ሱፋያን ቤት ተሰብስበዋል፡፡ አማር የሚባል ወጣት ከፊት ለፊታቸው ተንበርክኳል፡፡ ጥፋቱ ደግሞ የነቢዩ ተከታይ መሆኑ ነበር፡፡
ሹማምንቱ ወጣቱን ያዋክቡታል፡፡
ቢላል ከወጣቱ በቅርብ እርቀት ቆሞ ሁሉንም ይታዘባል፡፡
ነቢያችሁ የሰው ልጆች ቀሙሉ እኩል ናቸው እያለ ያስተምሯችኀል አሁን ይሔ ባሪያ ከእኔ ጋር እኩል ነውን? ብሎ አንዱ ሹም ለተያዘው ወጣት ጠየቀ፡፡

ወጣቱም ምንም ሳያመነታ አዎ ብሎ መለሰለት ሰው ከሰው የሚበላለጠው በስነምግባሩ በስራው መሆኑን ነገራቸው፡፡ በሳቅ ፈረሱ ጅሎች ተሳለቁበት እንከፎች ወዲያው የቢላል አሳዳሪ ትዕዛዝ አስተላለፈ ግረፈው!! ቢላል አለንጋውን ጨብጦ ከወጣቱ ፊት ተገተረ፡፡ ግን እጁን ማንሳት አቃተው፡፡


በዚያች ቅፅበት ምን ያስብ እንደነበር ሲነገርም አልሰማሁም ተፅፎም አላነበብኩም ስገምት ግንእንዲህ እያለ ከእራሱ ጋር የተሟገተ ይመስለኛል፡፡ ይህ ወጣት እኔ ክቡር ሰው መሆኔን ተናግሮ የሚደርስበትን ለመቀበል ሲዘጋጅ እኔ እንዴት እርሱን ገርፌ በገዛ እጄ ሰው አለመህኔን አረጋግጥላችኋለሁ?

አይ አላደርገውም የሁሉም አይነቢላል ላይ አረፈ ፡፡ ወጣቱ አማር እንዲገርፈው ተማፀነው፡፡ ቢላል እምቢ አለ ቢላል ሰው ሆነ፡፡ ሹማምንት እየሆነ ያለውን አምነው ለመቀበል አልቻሉም፡፡ በቁጣ ነደዱ፡፡ ተፈጥሮ የተዛባች መሰላቸው፡፡
"ዛሬ እንደ ወትሮዋ ጸሀይ የምትጠልቅ አይመስለኘም" አለ ቢን ኸሊፋ አለም ተዘበራርቃበት፡፡

የህሊና ነፃነት እና ሉዓላዊነት

የመካ ሹማምንት ተፈጥሮ እንደተዛባባቸው እንድትቀጥል አልፈለጉም ነገሮች ሁሉ ወደነበሩበት እንዲመለሱ ለማድረግ ቢላል ላይ ዛቱበት እርሱ በእምቢታው ፀና እናሰቃይኃለን አሉት ያሻችሁን አድርጉ አላቸው፡፡ ዝተው አልቀሩም ያሰቃዩት ጀመር አልተበገረም፡፡ በእምነት የሚጋሩ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የሰው ዘርን በሙሉ የሚያኮራ አቋም ወሰደ፡፡

ሰዎች ሁሉ እኩል ናቸው ሰውነት በቆዳ ቀለም አይለካም ትልቅነት በስራ እንጂ በዘር አይደለም የህሊናነፃነትና ሉዓላዊነት ምድርን ሚሞላ ንዋይ አይለወጥም የሚል ትምህርት አስተማረ በአንደበቱ ሳይሆን በተግባር፡፡

ሹማምንት ቢላልን ወደነበረበት ለመመለስ ራቁቱን ገረፉት አሸዋ ላይ ቀቀሉት ደረቱ ላይ ቋጥኘ ጫኑበት ወይ ፍንክች በጽናቱ አሳፈራቸው፡፡ ቢላል አሁን ሰው እንጂ ተናጋሪ እቃ አይደለም የራሱ ሀሳብ አለው የእራሱ እምነት እና አቋም አለው እናም ያለፍቃዱ ምንም ሊያደርጉት አይችሉም አካሉን እንጂ ህሊናውን ማዘዝ አይችሉም፡፡

ትላንትም ምንም የነበረ ባርያቸው ተናግረው ሆነ አሰቃይተው ማሳመን ባለመቻላቸው በሀፍረት ተሸማቀቁ፡፡ ደብድበው መግደል ይችላሉ ግን ሞቱ ከተሰማቸው ቅሌት አይታደጋቸውም፡፡ የትላንት ንብረታቸው ሰው ሆኖ አሸንፉቸዋል፡፡
ክብራቸውን ለመጠበቅ ሀፍረታቸውን ለመቀነስ ሌላ ዘዴ ዘየዱ በሚስጥር ተደራደሩት፡፡

በቃ ሌላውን ሁሉ ይቅር ስለ አማልክታችን ጥቂት በጎ ቃላትን ተናገር እና እንተውህ አሉት ይህንን እንኳን ሳይቀበላቸው ቀረ፡፡
የትላንትን ተራ አገልጋያችን የእራሱ ሀሳብ ኖሮት ጥንቂ አለን ብለው ተሰቃዩ፡፡ እባክህን መሳቂያ መሳለቂያ አታድርገን ያልንህን አድርግና አንተም ከስቃይ ተገላገል እኛንም ከጉድ አውጣን ብለው ለመኑት፡፡

አልሆነም በዚህ መሐል አቡበክር ደረሱናይህ ባሪያ ከአሁን በኀላ ምንም አይፈይዳችሁም ለእኔ ሽጡልኘ አሏቸው፡፡ ከጥቂት ድርድር በኀላ ተስማምተው ሸጡላቸው፡፡
ወዲያው ነፃ ሰው ሆኖ ነቢዩ ዘንድ በመምጣቱ ትልቅ ደስታ ሆነ ከዚያች እለት ጀምሮ ለአፍታ ከነቢዩ ሳይነጠል ኖረ፡፡

መካ ላይ ጎፉ በዝቶባቸው ወደመዲና ሲሰደዱ አብሮ ተሰደደ፡፡ ነቢዩ የጀነት ሰው ይሉታል እርሱ ግን ሀበሻዊ ባርያ ነኘ ይላል፡፡ የነቢዩ ባልደረባዎች መስዕዋትነቱን በማሰብ ልዑካችን እያሉ ያሞካሹታል እርሱ ግን በትህትና የትላንት ማንነቱን ያስታውሳቸዋል፡፡
መዲና ከተሰደዱ በኀላ ነብዩ '#ሙአዚናቸው' አደረጉት፡፡

ስንቱ ተመኘቶ ያላገኘውን ማዕረግ ለቢላል ተሰጠ፡፡

ዋናው ጉዳይ

ኢትዮጵያ እንደ ዋዛ ከጣለቻቸው ሀብቶች መካከል አንዱ የቱሪዝም ሀብቷ ነው፡፡ እኔ ባለኘ መረጃ መሰረት በንጉስ ነጃሺ እና በቢላል ዙሪያ ከቱሪዝም ጋር በተያያዘ ተገቢ ጥረት ቢደረግ ኖሮ አሁን አገሪቱ በመስኩ የምታገኘውን ገቢ 100% ማሳደግ ይቻል ነበር፡፡ ይሔ ዝም ብሎ ምኞት ብቻ አይደለም፡፡

ነጃሺን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የተለያዩ ጥናቶች መደረጋቸው ይታወቃል ሲምፖዚየሞች ተካሒደዋል የዚህ እንቅስቃሴ ተሳታፊ ከነበረ ሰው ዘንድ ባገኘሁት መረጃ መሰረት ከሆነ ምዕራባውያኑ ትተን ከምዕራብ አፍሪካ እና ቱርክ እና ኤንዶኖዢያ ከመሳሰሉት ኤዢያ አገሮች ብቻ በየአመቱ 300 ,000( ሦስት መቶ ሺህ ) ጎብኚዎችን መሳብ ወይም ማስተናገድ ይቻላል፡፡

ባይሆን ከእኛ ሁለት ስራዎች ይጠበቁብናል
የሐላል ቱሪዝምን ተሞክሮ ከሌሎች ሀገሮች ወስዶ ተግባራዊ ማድረግ እና እንደ ቢላል አይነት የማይዳሰሱ ታኢካዊና ባህላዊ ውርሶችን በፅሁፍ እና በፊልም በቅጡ ማደራጀት እንዲሁም ከተቻለ መቼም ባህልና ሚኒስቴር ለዚህ የሚሆን አቅም የሚያጣ አይመስለኘም 3D ቴክኖሎጂ በመጠቀም ጎብኚዎችን ታሪካዊ ትዕይንቶች እዚያው እቦታው ላይ የተገኙ ያህል እየተሰማቸው እንዲጎበኙ ማድረግ፡፡

ፍትህ መፅሔት ቅፅ 01 ቁጥር 11 ጥር 2011 ዓ.ም
በዐብዱልከሪም ታጁ


ሀበሻዊው ቢላል😍👏😊🙏 እንዴት አገኛችሁት?

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ነገ ቅዳሜ አይደለ ቅዳሜያችንን በአንድ ዘፈን እንጀምራታለን እስኪ አዳምጡት


ሁላችንም እራሳችንን እንፈትሽበት፡፡

አንተም አንቺም እሱም እሷም አዳምጡት ጥሩ መልክት አለው ብዬ አስባለሁ፡፡

የነገ ሰው ይበለን😊😍🙏

ዋናው መኖር ነው ለዛሬ ብቻ አይደለም ነገንም ለማየት ነው ከትላንት ያለፍነው፡፡
ተስፋ አለን እንደርሳለን......ወደ ነገ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂ ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂

@jahABP.......ነኘ 😊🙏
Audio
ተረጋጋሽ ወይ

ጎሳዬ ተስፋዬ

መልካም ቅዳሜ ተመኘሁ😍🙏😊 @jahABP ነኘ
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ወደፊት ከሚስቴ ጋር ምጣለላው የማንቼን ጨዋታ አያለሁ አታይም በሚለው ይመስለኛል😜😜

የአመቱ የመጀመሪያ ጨዋታ በግዙፉ
በምድር ገነት ኦልትራፎርድ😍😘❤️
መልካም ዕድል ለውዱ ክለባችን ማንችስተር ዩናይትድ👌🔥🔥🔥
AB PHOTOGRAPHY


መልካም ዕለተ ሰንበት

የምስጋና ቀን.....🙏🙏🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ለሰኞ😍🙏😊
ወጣቱ ድምፃውያን #ሳሚ_ዳን ሁለቱንም አልበሞቹን በደንብ ሰምቼለታለሁ እወዳቸዋለሁ ብዙ ሰዎች በሱ የመጣ ያበሳጩኛል ያለሙያው ነው የገባው ይሉኛል እኔ ደሞ ያለሙያው ቢሆኖማ እንደዘመኑ ዘፋኞች የመሸታ ቤት ሙዚቃ ብቻ ያወጣ ነበር ይህን ስል ሌሎች የለቀቃቸውን ነጠላ ዜማዎች ልል ፈልጌ አይደለም ስለአልበሙ ነው ማወራው እላቸዋለሁ፡፡
ብቻ እናንተ ሰምታችሁ ትፈርዳላቹ፡፡


ለኔ ግንእራሴን እንድፈልግ ስለሚያግዙኘም ክፍተቶቼን እንድሞላም ያደርጉኛል እና ለሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን በዚህ ሙዚቃ እንድትጀምሩት እጋብዛለሁ፡፡


በሀይልህ ትመካ ይሆናል ባለህ ነገር ሌሎችን ትጨቁን ይሆናል ባለጊዜ ሆነህ ሌሎችን እያሰቃየህ ይሆናል በጣም አስመሳይ ትሆን ይሆናል ማንንም ልትዋሽ ትችላለህ......ማንንም ልትበድል ትችላለህ ሁሉንም መጥፎ ነገሮች ልታደርግ ትችላለህ.........የምታደርገው ነገር አንተን ምንም ላይመስልህ ይችላል የሚነግሩህ ሰዎችን ሁሉንም አልሰማ ብለህ ይሆናል ግን...መጨረሻ........

ህሊና....ሲታመም....በምን.....ይድናል🤔🤔.....ይልኻል

ስለዚህ ቆም ብለህ አስብ፡፡ ያለህበት ነገር ብዙሀንን እየጎዳ እንዳይሆን እራስ ወዳድነት አጥር እንዳትታጠር የጥፋት ደቀመዝሙር እንዳትሆን........ምክንያቱም.......
ህሊና......ሲታመም....በምን.....ይድናል🤔🤔.....ይልኻል፡፡


ተስፋ አለን እንደርሳለን ለዛሬ ብቻ አይደለም ለነገምነው ከትላንት ያለፍነው🙏😍😊....

@jahABP....ነኘ 😊🙏
Track 9
Unknown artist
ሳሚ ዳን ሁለተኛ አልበም "Track 9"

ህሊና ሲታመም በምን ይድናል🤔🤔

"ማንም ቋሚ የለም በምድር ላይ ሁሉም መጨረሻው የሞት ሲሳይ
ፍርዱን የሚጠብቅ ካለው ከበላይ፡፡"

ህሊናህን ልትዋሸው አትችልም ለምን ብሎ ይጠይቅኃላ ሰላምህም አይሰጥህማ ይጮኸብኻል፡፡

ህሊናችን ሳይታመም መልካሙን ምናስብበት ሳምንት ይሁንልን

@jahABP ነኘ😊🙏😍
ጓደኘነት🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY


በቱሪዝም ሀብቷ ላይ የተኛች ሀገር

በትንሹ ፈጠራ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#ጓደኘነት

ጠራኘ......አብያ ዛሬ ብር የለኘም....ግን ሦስት ቢራ መጠጣት እፈልጋው አለኘ፡፡

ምንም ችግር የለውም እሺ ይደርሳል አልኩት፡፡

አመሰግናለሁ.....አለኘና ተቀመጠ......

ከዛ ቁጭ ብሎ ብሎኘ ጨዋታ ጀመረ በመሀልም ስለጓደኘነት ይህን አጫወተኘ፡፡

አንድ የቴሌግራም ወዳጄም እስኪ ስለጓደኘነት ብፅፍልን ብላኘ ነበርና ከጨዋታችን መሀል ይህ ደስ ስላለኘ ላካፍላችሁ ወደድኩ.....😊😍

ይገርምኻል የሰው ልጅ ስታገኘና ስታጣ በጣም ይለያያል፡፡ ማግኘትና ማጣት እንደሆነ ይፈራረቃሉ አለም ላይ ነውና ምንኖረው ግን ስታጣ ሰው ይቀያየራል ያበላኸው የሰጠኸው እራስህን ጎድተህ የጠቀምካቸው ሁሉ ማጣትህን ሲያዩ ያንን ይረሳሉ አንተን በትላንቱ ሳይሆን በዛሬ ውድቀትህ ያዩኻል ያላቸውን ሁሉ ምትወስድባቸው ይመስላቸዋል፡፡

አብረውህ ከበሉ ሚጠግቡ አይመስላቸውም ያላቸውን ግማሽ ለመስጠት ያማቸዋል አንተን ሲያዩ መንገድ ይቀይራሉ፡፡ አንተ ምትመጣ ከመሰላቸው ከሰፈር ይጠፋሉ ብቻ ስንቱ😔🤦‍♂

ግን ህይወት እንደዛ መሆን አለባት ብዬ አላስብም በኡነት ያውም ለጓደኛህ....🤦‍♂

እኔ.....ኡነት ነው አልኩ

ቀጠለ.....
አንድ ጓደኛዬ አለ ሲቪል ኢንጂነር ነው ግን በፊልዱ ስራ ስለሌለ ሌላ ስራ ነበር ሚሰራው በኮሮና ምክንያት ከስራ ተቀነሰ ሚገርምህ ስራ በማጣቱ እንደድሮው ህይወትን ሊመራ አልቻለም በቃ ሰዎች ደሞ ፀባያቸውን ቅድም እንደነገርኩህ ቀያየሩበት በዛ ላይ ሚስቱ አርግዛለች፡፡

እኔ....ሲያበሳጭ አልኩኘ😔😔

ከዛ...በዚ ምክንያት ሰፈር ቀየረ......

እየተገናኘን እንጫወታለን...አብረን እንዝናናለን...ስራ የለውም እኔ ግን እየሰራሁ ነው ስለዚህ ያለንን በአግባቡ እንጠቀምበታለን፡፡
ያለው ጊዜ ኪሱ ኪሴ ነበር የኔም እንደዛዋ፡፡

ይህን ምነግርህ እራስህን እንድታይበት ነው፡፡
እራስህን እንድትፈትሽበት ነው፡፡
እንዲህ አደረኩ ልልህ አይደለም ብቻ አንተ እንደፈለክ አስበው...🤷‍♂...ሚጠቅምህን አንተ ታውቃለህ አለኘ፡፡

ሚገርምህ አንድ ቀን ደወለ......

የት ነህ አለኘ
ስራ ነኘ ልወጣ ነው አልኩት፡፡
እና ደብሮኛል ቦታችን ደቅ ልል ነው ብር አለህ አለኘ፡፡

ብር ተቀብዬ ነበርና እንዲች ብለህ እንዳታስብ እዛው ጠብቀኘ አልኩት.....

ይመችህ አለኘ...👍

ቆይቼ መጣው ተጫወትን...ሒሳብ ከፋፈልን ወጣን...እና የት እንሒድ ሃቫና እንሒድ አልኩት፡፡

ስንት ብር ይዘህ ነው ቆይ አለኘ

ሁለት ሺህ አንድ መቶ ብር

ከት..ብሎ ሳቀ ረጅም ሳቅ😅😅😅😅😅😅😅😁😁😋🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣 😁😄

ምን ሆነኻል አልኩት

እየሳቀ አምጣው ብሩን አለኘ........😂

እሺ ብዬ ሁሉንም ሰጠሁት......

እንካ መቶ ብር.....ለነገ ለቁርስህ እኔ እርጉዝ ሚስት አስቀምጬ ቤት ኪራይ ደርሶብኛል አንተ እንጠጣ ትለኛለህ....ሃሃሃሃሃ....አባቴ አንተ ቀልደኛ በል ቻው ደና ደር እንገናኛለን አለ አንዳንድ ነገር ገዛዝቼ ልግባ ብሎኘ እየሳቀ ጥሎኘ ሔደ፡፡

ለነገ መቶ ብር ብቻ ነው ያለኘ 😂😂😂...😊😊
ደስም እያለኘ ግዴታዬም ነው እያልኩ ወደቤት መሔድ....ሳለሁ ስልኬ ጠራ እሱ ነው...በቃ የተወሰነ ብር ሊጨምርልኘ ነው ስል......

እሱ.......በል ይቺም ትልቅ ነገር ናት ብለህ ለሰዎች ተናገር ደግሞ አለኘ እየሳቀ😂

ሳቅ ነው ያመለጠኘ😂😂😂🤣🤣😅


ሳስበው ኡነቱን ነው የራሴ ብር ቢሆንም ስጠጣ አስፓልት ላይ ልጅ ይዛ ከተቀመጠች እናት ነጥቄ እንደምጠጣ ነው ማስበው፡፡

ከአንድ ቁርቁስ ብለው ከተቀመጡ ሽማግሌ ነጥቄ እንደምዝናና.......

አንድ ሚበላው አጥቶ ጥጉን ይዞ ከወደቀ ወጣት ምግቡን የነጠኩት ያህል ነው ሚሰማኘ፡፡

ከአንዲት የሞዴስ መግዣ ያጣች እህቴን የራስሽ ጉዳይ .......ብዬ እራሴን አታልዬ እንደምዝናና ነገ እዛው ልሆን በከንቱ አለምን ለመርሳት እንደምሞክር ነው ማስበው፡፡

እና ይህን በማድረጌ ቅንጣት አልተከፋሁም እንደውም እኔ እንደዛ ስላላልኩት እየተፀፀትኩ ወደቤቴ ገባሁ እልኻለሁ፡፡

አየህ ጓደኘነት እንዲህ ነው....መሆን ያለበት አንተ እኔን በውድቀቴ ካልደገፍከኘ የጥቅም ሰው ነህ ማለት ነው፡፡
ጥቅመኛ ከሆንክ ደሞ ቋሚ ነገር አይኖርህም ሁሌም እዛም እዚ እያል እንደባዘንክ መኖር ነው፡፡


ጓደኘነት በኡነት ከዝምድና በላይ ነው፡፡
ጓደኘነት ከወንድም በላይነው፡፡
ጓደኘነት ከእህትነት በላይ ነው፡፡
ጓደኘነት በጣም ውድ ነገር ነው፡፡......

አለኘ፡፡


ምንም ማለት አልፈልግም ብቻ ከተጫወትናቸው ብዙ ነገሮች ይሔ አንዱ ነገር ነው፡፡
ሌሎች ሀሳቦችንሌላ ቀን እቀጥላለው...

ይህን የፃፍኩት እራሳችንን እንድናይበት ነው እራሳችንን እንድንፈትሽበት ነው፡፡
ብቻ እንደፈለጋቹ አስቡት ሚጠቅማቹን እናንተ ታውቃላችሁ🤷‍♂

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ 😊🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ብዙ የራሴ ቀኖችን አከብራለሁ......እንደራሴ ስለማከብራቸው ማንም አይቀናቀነኘም ማንም አያስቀርብኘም ከልካይ የለኘም....መስፈርቱ ቀኑ አንተን ይመለከትኻል ወይ ነው.......ከሆነ መልዕክቱን አደርስሀሃልለሁ.......

ነገ አንድ ማከብረው ቀን አለኘ.......

ይህ ቀን የጠፉ ጓደኞቼን ምፈልግበት ነው........ጠፍታቹብኛል መጥፋታችሁ ያሳስበኛል ላስታውሳቹ የግድ ነውና.....😔🙇

ይህን ቀን ማክበር አለብኘ፡፡

እነማናቹ ነገ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

ተስፋ አለን እንደርሳለን ለዛሬ ብቻ አይደለም ለነገም ነው ከትላንት ያለፍነው.....🙏😊😍

@jahABP .........ነኘ😊🙏
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ፂዮንዬ የኔ ምርጥ ስፈልግሽ እንደማላገኘሽ ሳውቅ ሁሌም ጥልቅ ሀዘኝ ውስጥ እገባለሁ ያለ ቢናፈቅ እና ቢጠፋ ያለበት ይኬዳል አንቺ ጋር መምጣት አልችልም ላገኘሽ አልችልም ያ ሁሌም ያሳምመኛል ባለሽበት ግን የናፍቆቴን መልክት ተቀበይኘ😢😢😢😭😭😭🤦‍♂🤦‍♂

Jo...... egremenged picture ቻናል መስራች 😍🙏 ለዚ ቻናል ማደግ ትልቁ ባለውለታዬ ኧረ በጣም ጠፍተኃል ወንድሜ፡፡

ዞላ BIG BRO ሀብታም ስትሆን ሸመጠጥከን አ ኧረ ደስ አይልም እሺ😜😜👊👊 ፈልገን ኧረ

መቅዲዬ😍😘 ውዷ ምንድነው እንዲ ጥግብ ያደረገሽ ግን እ🤔 ኧረ ተይ አያዋጣሽም አሁን ያኔ 7 ክፍል እያለን የነበረን ፉክክር እንዴት ይረሳል ምታመጪው ምሳ😋😋😋🙆‍♂🙆‍♂🙆‍♂ ወይስ ዩኒቨርስቲ ነው እንዲ የቀየረሽ😡ወይ ጉዴ የኔ ቅን አሳቢዬ ኧረ ጠፍተሽብኛል፡፡

አማኑ ( Makaveil ) ጠፍተሃል እኮ የእንግሊዘኛ ሙዚቃ ግብዣዎችህን ናፍቃቸዋል ስለ ቱፓክ ሻኩር ባንተ ነው ጠልቄ ያወኩት አልሞተም ስትለኘ ይህ ቀልድ ነው ብዬህ ሳምንት የዘጋኸኘን አልረሳውም😂😂😜😜😔😔 ዝምተኛው ፀባይኛው አማኑ😍

ሁላቹም መጥፋታቹ አሳስቦኛልና ካላቹበት ብቅ ብቅ በሉ

@jahABP ነኘ 😊🙏
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

"ወገኔ ልብ በል እነ ቄሳር ፣ እነ እስክንድር ፣ እነ ናፖልዮን ፣ እነ ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ያልኖሩበትን አለም አንተ ምስኪኑ ዘላለም ምትኖርበት ይመስልኃልን??

ዓለሙ ሲያዩት ውበቱ በእየዕለቱ እየጨመረ የሚያሳሳ ይመስላል፡፡ ነገር ግን አበባ ሊረግፍም ሲል ያምራል የሚባለው ለሁሉሞ ይሰራል፡፡
የበረዶ መጥለቅም እንበለው ፣ ሱናሚም እንበለው ፣ ኒውክለርም እንበለው ፣ "ኮሮናም" እንበለው ዓለም እንደምታልፍ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ አሁን እየጎላ ነው፡፡

ስለዚህ፡-

👉በሚያልፍ ዓለም የማያልፍ በጎ ሥራ ሥራበት፡፡

👉በሚያልፍ ዓለም የማያልፍ የነፍስ ውሴኔ ወስንበት፡፡

👉በሚያልፍ ገንዘብ የማያልፍ ዘመድ አፍራበት፡፡
ማለት ድሆችን ጎብኘበት የእግዚአብሔር ስራን ስራበት፡፡

👉በሚያልፍ ዓለም ለሚተካው ትውልድ መሠረት ጣልበት፡፡ "

መልካሙን መልካሙን እናስብ
ገነትን ሞተን ሳይሆን ምድር ላይ እንስራ፡፡

መልካም ቀን ተመኘሁ

@jahABP ነኘ 😊🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

መስቀል ሀይላችን ነው!!!
መስቀል ቤዛችን ነው!!!
መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው!!!

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም በጤና
🙏አደረሰን🙏
የመስቀልን በዓል ስናከብር ለኛ የተደረገልንን ትልቅ ፍቅር እናይበታለን ይህም ለምን ከተባለ ለፍቅር ሲል ነዋ አምላካችን በመስቀል ላይ የተሰቀለልን፡፡

ማዕተባችን መስቀል ብዙ ሚስጥር አለው ለጌጥ አደለም❤️

አልቀረም ተቀብሮ ተገኘ መስቀሉ
➕➕➕➕➕➕➕➕➕

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

"ከመጀመሪያው ሰዎች አንስተን ብንመለከተው የሰው ዕድሜ እደቀነሰ መቷል፡፡
የኑሮ ትግል ግን በርትቷል ዕድሜው ትንሽ ትግሉ ብዙ ሆኗል፡፡ በዚህ አለም ላይ የምናሳልፈው ዕድሜ በሰማይ ከምናሳልፈው ጋር ሲነፃፀር የአይን ጥቅሻ ያህል ነው፡፡

ከዘላለም አንፃር ስናየው የዚህ ዓለም ቆይታችን አንዲት ሰዓት እንኳን አይሞላም፡፡
በዚህ አለም ላይ ያሳለፍነው የዕድሜ ልክ መከራችንን በመንግስተ ሰማያት የአንዲት ሰዓት ደስታ ይካሳል የዚህ አለሞ ኑሮ እንደ መግቢያ ነው፡፡

ቢሆንም ትግል ባይኖር የድል ደስታ በሽታ ባይኖር የጤና ምስጋና አይኖርም ነበር፡፡
ጣፋጭን ያጎላው መራራ ነው፡፡
አንድን ነገር ስንፈልገው ከምናገኘው ዋጋ ከፍለን ስናገኘው ያስደስታል፡፡
አክብረንም እንዘዋለን፡፡

አዎ ትግሎች ሳይቀር ለደስታ ተዋቅረዋል፡፡ የዚዓለም ቆይታ ጊዜያዊ ቢሆንም ዘላለማዊ ውሳኔ የሚደረግበት በመሆኑ እንደቀላል የሚታይ አይደለም፡፡
ይህ ዓለም ቆይታው ትንሽ ቢሆንም በጎ ለመስራትም ሆነ በክፉ ስራችን ለመፀፀት ለድል ያለበት ዓለም ነው፡፡

የወዲያኛው ዓለም ግን #የምርጫችንን_ውጤት_የምንቀበልበት_ነው፡፡

የዚህ ዓለም ኑሮ ተጨማሪ ነው፡፡ የሚቀድመውና የሚከተለው ማወቅ ትልቅ እውቀት ነው፡፡
የብዙ ሰዎች ችግር ቀዳሚውንና ተከታዩን አዘባርቆ መኖር ነው፡፡
ከምሳ ቀጥሎ መክሰስ ወይም የእራት መዳረሻ አለ፡፡
የዚህ ዓለም ኑሮው ዋና ሳይሆን የሰማይ መዳረሻ ነው፡፡

በትልልቅ ሆቴሎች ከዋናው ምግብ በፊት የባለጠጎችን አምሮት የሚከፍቱ ቀላል ምግቦች ይቀርባሉ፡፡
ዋናው ምግብ ገና መሆኑን የማያውቅ እስከ መጨረሻው ይመገባቸውና የዋናው ምግብ ሲመጣ ይጠግባል፡፡

ይህ ዓለም ዋና የመሰለው ሰው በቀላል ነገሮች ጠግቦ ዋናውን ሕይወት ይገፋል፡፡
በዋዜማው ጨርሶ የጠገበ ሰው በዋናው በአል ላይ መቆም ያቅተዋል፡፡

ይህም አለም ለሰማዩ ዋዜማ ነው፡፡

ነጋዴ ዋናውን ይዞ ነው የሚነግደው፡፡ ትርፍ ዋዣቂ ነው፡፡ ዋናውን የማያውቅና የማይጠብቅ ነጋዴ መሆን አይችልም፡፡
ከዚህ ሁሉ በላይ ትርፍና ኪሳራውን አጥርቶ አያውቅም፡፡

ሕይወትም ብዙ የምናተርፍባት ብዙ የምንከስርባት ንግድ ናት፡፡

በህይወታችን ውስጥ ዋናው
#እግዚአብሔር ነው፡፡

#ሌላው_ትርፍ_ነው፡፡

ስለዚህ ዋናውን ላለማስነካት መጠንቀቅ አለብን"

መልካሙን በጎ በጎውን እናስብ እናድርግ በተግባር እንግለጠው.....
መልሶ ስለሚደረግልን ሳይሆን እኛ ስለሆንን አንተ ስለሆንክ አንቺ ስለሆንሽ መገለጫችን:-

#መልካምነት #መተሳሰብ #ፍቅር #ይቅርታ
#ይሁን

@jahABP ነኘ 😍🙏😊

መልካም አዳር ተመኘሁ፡፡
ተስፋ አለን እንደርሳለን ለዛሬ ብቻ አይደለም ነገንም ለማየት ነው ከትላንት ያለፍነው፡፡

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPIC DESIGN

እሌኒ ንግስት መስቀሉን አስገኘች፡፡
ምን አይነት መታደል ነው ባካቹ

እሌኒ ተስፋ መቁረጥ ትችል ነበር፡፡
እሌኒ አይ ይሔን ሚያክል ተራራ ላስቆፍር ኧረ ይቅር አድካሚ ነው ማለት ወጪ ይበዛብኛል ብላ ምክንያት መደርደር ትችል ነበር፡፡

ንግስት ነች ሁሉም በሷ እጅ ነውና!
ግን አላማ ነበራት ዋና አላሟዋም አምላኳ ነበር በቁጭት ነበር የተነሳችሁ ትልቅ ተስፋና እምነት ነበራትና አላማዋን ወጥታ ወርዳ አሳካች፡፡


ለኛም ድህነት የሆነውን መስቀሉ ተገኘልን ስሟም ከዛ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ሲጠራ ይኖራል.......

ከመስቀሉ በጣም ብዙ ነገር መማር እንችላለን

ይህ ትልቅ በዓል ነው፡፡
ይህ የማንነታችን መገለጫ በዓል ነው፡፡
ይህ ለፍቅር ሲባል የተደረገልንን ሁሉ ምናስታውስበት በዓላችን ነው፡፡

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ፡፡

ትልቁን ፍቅር ያየነው #በመስቀሉ ላይ ነው፡፡

@jahABP ነኘ 😊🙏😍

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

ደመራ
Home photography
@jajABP
WALLPAPER
መስቀል ሀይላችን ነው!!
መስቀል ቤዛችን ነው!!
መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው!!
የአመት ሰው ይበለን......🙏😍😊

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
አላህ አለሙን ፈጠራና ቀጥሎ እሷን ለመፍጠር አሰበ ልክ ስትታይ የምታስደነግጥ የምትስብ ሁሉ የተሟላላት አጃኢብ ቱቱቱ ማሻ አላህ ከአይን ያውጣሽ የተባለላት ሴት ለመፍጠር አሰበ

ሲሞክር ሳይሳካለት ሲቀር ሲሞክር ስትበላሽበት ሲሞክር አንዱ ነገሯ ያስጠላ ሲሆንበት ሲሞክር የሆነ ነገር ሲጎላት ሲሞክር እንደፈለገው አልሆን ሲለው ቆንጆ አልሆንም ስትለው እውቀቷ ሲያንስ ሲሞክር......ሲሞክር ሲሞክር ሲሞክር..........

ይሔ ሁሉ ሴት የተፈጠረው እኮ አላህ እሷን ለመፍጠር ባደረገው ሙከራዎች ነው

ከዛ ልክ የዛሬ......21 አመት እሷን ፈጠራት ተሳካለት እሱ እራሱ ወደዳት እጄ ይባረክ አለ......ይቺ ልጅ ሀይማኖቷን አክባሪ ናት የቤተሰቧን የሀገሯን ስም ታስጠራለች እውቀቷ ብዙ ነው አለ፡፡

አብረን ስንማር እብድ
ውጤት ላይ አንደኛ ይሔማ ልትሳሳት ማይገባህ ጥያቄ ነው ባለፈው አስረድቼህ ትለኘ ነበር
ብዙ ተፎካክረን አንደኛ ግን እሷ ናት

አሁንደሞ ሐረማያ ዩኒቨርስቲ አሉኘ ከሚላቸው ተማሪዎች አንዷ ክቡራንና ክቡራት እኔ ደሞ ጓደኛዬ ይቅርታ ጓደኛ ብቻ ሳትሆን እህቴ መካሪዬ ሁሉ ነገሬ በመሆኗ በጣም ምኮራባት ውዷ ራኑ(ሩታዬ) ልደቷ ነው.....

ኧረ ለኔ ስትይ እንኳን ተወለድሽልኘ ሩታዬ መልካም ልደት ከረጅም እድሜና ጤና ጋር
አኩርተሽኛል ወደፊትም እንደምታኮሪኘ አልጠራጠርም፡፡

😘😍😘😘👏👏🤪🤪👑🎂🎂🎂🍩🍩