Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

" "እኔ ለአንተአንተ ለእኔ"

የተለያየ ድርሻ መያዛችን ሕይወትን የተሟላች ያደርጋታል፡፡
ሰዎች እንደ እኛ ካላሰቡ የተሳሳቱ ፣ እንደ እኛ ካልተናገሩ ቋንቋ ያበላሹ ፣ እንደ እኛ ካልኖሩ የሞቱ ፣ እንደ እኛ ካልሰሩ ሥራ የፈቱ አይደሉም፡፡


ሌሎች አስፈላጊያችን የሚሆኑት እኛ የማንችለውን ሲያውቁና ሲያደርጉ ነው፡፡
ሁሉም ሰው ዶክተር ቢሆን ያለገበሬ ምን ይመገባል?? ዶክተሩ በእውቀቱ ተመክቶ ገበሬውን አንተ አታስፈልገኘም ቢለው ይሞኛል፡፡
የላይኛው ከታችኛው የግድ የሚፈላለግ የተለያየ ተሰጦ ተቀብለናል፡፡

ስለዚህ አንዱ አንዱን አታስፈልገኘም ሊለውና ሕይወትን ብቻውን ሊመራ አይቻለውም፡፡

ትልቁ የኑሮ የኑሮ ሚስጢር
" እኔ ለአንተ ፣ አንተ ለእኔ" የሚል ነው፡፡

የጥቁሮች መብት ታጋይ የነበረው ማርቲን ሉተር ኪንግ፡-
"በአላባማ እያለሁ ጫማዩን የሚጠርግልኘ አንዲት ሊስትሮ ነበር፡፡
ይህን ሊስትሮ ስመለከት ወደ አእምሮዬ የሚመጣ ነገር ቢኖር የቱንም ያህል ጫማዬን ብጠርገው እንደእርሱ አድርጌ ላሳምረው አለመቻሌ ነው፡፡
ስለዚህምይህ ልጅ በጫማ ማሳመር የዶክትሬት ዲግሪ አለው ብዬ ተቀበልኩ፡፡
ከኔም የተሻለ ስለሆነ አከበርኩት" ብሏል፡፡

የትኛውም እውቀታችን አዋቂ የሚያሰኘን ላላወቁት በምናደርገው መንገድ ብቻ ነው፡፡
ምክንያቱም እውነተኛ እውቀት የአገልጋይነት እንጂ የጌትነት መንፈስ የለውምና፡፡
የእኛ እውቀት አስፈላጊ የሚሆነው የማያውቁ ስላሉ ነው፡፡
ሁሉም ቢያውቅ እውቀታቸው አለማወቅ ይሆናል
ስለዚህ የማያውቁትን አክብረን ማገልገል ይኖርብናል፡፡

የትኛውም ሀብታችን ባለጠጋ የሚያሰኘን በችግር ለሚያቃስቱት ባፈሰስነው ልክ ነው፡፡
ራሱን የቻለ ባለጠጋ አይባልም፡፡
ለሌሎች የተረፈ ግን ባለጠጋ ይባላል፡፡
ስኬታችን የሚለካው ራሳችንን በረዳንበት መጠን ሳይሆን በሌሎች በተረፍንበት መጠን ነው፡፡

ዛሬ ኑሮአችንንና ሕይወታችንን እንዲገዛው የፈቀድንለት ነገር ቢኖር ንቀት ነው፡፡
ሌሎች እንዲያከብሩን እንፈልጋለን ፣ እኛ ግን ሌሎችን መናቅ እንሻለን፡፡
ሌሎችን መናቅ በአዋጅ የተፈቀደልን ሥልጣን ይመስለናል፡፡
ሌሎችን በንቀት ዝቅ ካላደረግን የተስተካከልናቸው አይመስለንም፡፡

ስለዚህ የበላይነት ስሜታችን የበታችነት መንፈስ የወለደብን ነው፡፡
የምንኖረው ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ለመቀበልም ነውና ሌሎችን...ማክበር ደግሞም ፈጣሪ የምንሰጠውን አስታቅፎ ወደ ዓለም ልኮናልና አደራችንን ማድረስ ይገባናል፡፡


በቤታችን ፣ በሥራ ቦታችን ፣ በአገልግሎታችን እየሰራን ያለን እኛ ብቻ መስሎ ከተሰማን ሌሎች የሠሩት አይታየንም፡፡
ሌሎችን መውደድ ያቅተናል፡፡
ሥራችንም ከጥቅሙ ኩራቱ እየገነነ ይመጣል፡፡
በሌሎች ላይም እምነት እያጣንም የርክክብን ሥርዓት እናፈርሳለን፡፡
ራሳችን አልሚ ሌሎችን አጥፊ ሆነው እየታዩን ነቃፊ ብቻ እንሆናለን፡፡

የዓለማችን ትልቁ የኢኮኖሚ አቅም ፣ የሰላም መሰረት ግብረ ገብነት ወይም የሞራል ሕግ ነው፡፡ የሥነምግባር መሰረቱ ሃይማኖት ነውና ሃይማኖትን መጥላት ተገቢ አይደለም፡፡
ሰዎችን ከሕግ ፣ ከፍልስፍና ይልቅ ሃይማኖት የመግዛት አቅም አለው፡፡


ብዙ ባለ ራዕዯች ነን የሚሉ ሃይማኖትን በቀና መንፈስ አያዩትም፡፡
ሃይማኖት ግን የልምድ ሳይሆን የተፈጥሮ መሻት ነው፡፡
መስራት ፣ መማር ፣ መልፋት ፣ መትጋት ብቻውን በቂ አይደለም ሃይማኖት ያስፈልጋል፡፡

ዓለም ድፍርስ ውሃ ነው፡፡
ስለዚህ ማንነትን አያሳይም፡፡
እንደውም እውነትን የሚሸፍን በመሆኑ ምንመ ያልበራለትን የብርሃናት አለቃ ፣ ሰነፉን የትጉሃን አለቃ እያለ ያሞካሻል፡፡
ዓለሙ የሽንገላ ፣ የመዳለል አለም ነው፡፡
ሰዎች መንፈሳዊ መፅሐፍትን የሚጠሉት እውነት ስላልሆነ ሳይሆን ኃጢአጣቸውን ስለሚነግራቸው ነው፡፡
ዓለሙ የንግግር መክፈቻው "አንተ ለአንተ" ወይም "ሀይልህን አውጣ" የሚል ነው፡፡
ዛሬ የሰው ልጆች ሌላውን እንጂ ራሳቸውን ማየት አልቻሉም፡፡

ተራችንን ጠብቀን መቆም ፣ ቀጥሎ መመልከት ከዚያም መጠየቅ በመጨረሻም መጓዝ ነው፡፡
ካልቆምን መመልከት ፣ ካልተመለከትን መጠየቅ ፣ ካልጠየቅንም መጓዝ አንችልም፡፡

መቆም ለቀጣዩ ጊዜ ያዘጋጃል ፣ ለቀጣዩ ጉዞም ኃይል ይሰጣል፡፡
በክፉ ጎዳና የሚጓዝ መቆም ያስፈልገዋል፡፡
የመጣበትንና የሚሔድበትን የሚያየው በመቆም ብቻ ነው፡፡


በመቆም በፀጥታ ውስጥ ሆኖ ራስን መገምገም ፣ ከዚያም መመልከት ቀጥሎም መጠየቅ በመጨረሻም ዕረፍት ወዳለበት ደሴት መጓዝ፡፡"

ራዕይ ያለው ትውልድ

ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንደቀነጨብኩት

መቆም.... ራስን ማየት ...ከኛ የተሻሉ ሰዎች እንዳሉ ማመን፡፡

ከትላንት የተሻልን ብቻ ሳይሆን የበለጠ ለመሆን መሞከር፡፡

ማርቲን ሉተር ኪንግ ግን ሳሚሻን(DOC SHOESHINE) አስታውሶኛል 11-12 እስካሁንም ድረስ ሚኒልክ ትምህርትቤት ደጅ😍🙏😊 ሳሚሾዬ

ተስፋ አለን እንደርሳለን ለዛሬ ብቻ አይደለም ነገንም ለማየትም ነው ከትላንት ያለፍነው፡፡

😍መልካም አዳር😊

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ያኔ ማስታወሻዬ ላይ እንደዚህ ብዬ ፅፌ ነበር......

በጣም ደስ ይላል ንፋሱ አየሩ መንፈስን ያድሳል ብቻዬን ሆንኩ እንጂ🤦‍♂😔
እዚ ቦታ መምጣት ከምቶዳቸው ጓደኞችህ ጋር ቀጥሎ ከፍቅረኛህ ጋር ከዛ ደሞ ከቤተሰብህ ጋር....በእርግጠኘነት ያበደ ጊዜን ነው ምታሳልፈው ኡፍ AM IN LOP WITH ሃዋሳዬ😍😍😍😘😘 እንግዲህ ካልኳቸው ሰዎች ጋር ለመምጣት እግዚአብሔር ያብቃኘ ደሞ አይቀርም💪💪🙏፡፡
ተፃፈ 10:59 ሃዋሳ ሌዊ ሪዞርት
ጥር 2012
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
የቀጣዩ ፅሁፍ

ፀሀፊው፡- ሙሀዘጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ነው፡፡

እኔ በጣም ተመችቶኛል ወድጄዋለሁ

ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY GRAPHIC DESIGN

🤔መንገድ ያለው ከውጪ አይደለም🤔

ሁለት ወንድማማቾች እናታቸው ስታርፍ በቤት ውስጥ ያገኙት ትልቅ ገመድ ብቻ ነበር፡፡
ታላቁ ልጅ እጅግ በመበሳጨቱ ገመዱን ጠቅልሎ ጣራ ላዬ ወረወረውና ከቤት ወጥቶ ሔደ ፡፡
ታናሹ ግን ምንም ቢሆን ገመዱ የእናቱ ማስታወሻ ቅርስ ነውና እንደምንም ብሎ ጣራ ላይ ወጥቶ አወረደው፡፡

ከባዱ ጥያቄ ግን ከዚህ በኀላ ያለውን ኑሮ እንዴት ነው መግፋት ይችላል? የሚለው ነው ነበር፡፡
ለብዙ ሰዓታት ተቀምጦ አሰበበት ምንም ነገር ግን ሊታየው አልቻለም መንገዱ ሁሉ በግንብ የታጠረነው አስቦ አስቦ ወደ አንድ ጠቢብ ዘንድ ሔደ፡፡

ጠቢቡ ሰው እንዳገኘውም የጠየቀው ጥያቄ "ምን አለህ" የሚል ነበር፡፡
መልሱም ቀላል ሆነ "ምንም"
ጠቢቡም ሰውም "በዓለም ላይ ምንም የሌለው ሰው የለም፡፡ ምናልባት ግን ጥቂት ብቻ ያለው ሰው ሊኖር ይችላል፡፡


ለምሳሌ:- አንተ ከወንድምህ በተለየ ጥበብ አለህ ይህም ጥበብ ነው ወደ ጠቢቡ ያመጣህ አለው"
ልጁ ግን በእርግጠኘነት እየማለ ምንም እንደሌለው ተናገረ፡፡

ጠቢቡም "ይህ ፈፅሞ ሊሆን የማይችል ነው፡፡ ሰው ሆኖ ምንም የሌለው የለም፡፡ ረስተኸው ነው እንጂ አንዳች ነገር አለህ" አለው፡፡
ልጁ ቢያወጣና ቢያወርድ ያለውን ነገር ሊያገኘው አልቻለም፡፡
የሚያውቀው ምንም እንደሌለው ብቻ ነው፡፡

ያን ጊዜ ጠቢቡ ልጁን ይዞት ወደ አንድ ክፍል ገባ፡፡ ክፍሉ ሊዳሰስ በሚችል ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ የተሞላ ነው፡፡
ጨለማው አይን ሊወጋ ይደርሳል፡፡
ከጠቢቡም ጋር በዚያ ክፍል እንደገቡም
"ምን ይታይሃል?"አለና ጠየቀው ልጁም ወዲያውኑ ነው መልሱን ያገኘው "ጨለማ"

ጠቢቡ ግን እንደገና ጠየቀው፡፡ "ሌላነገር አለ ፈልገው" ዘወር ዘወር አለ ምንም ግን ምንም የለም ጠቢቡ እንዲህ አለው "ና አብረን ቁጭ እንበልና ጊዜ ወስደህ ተመልከት"

ተቀመጡም ልጁ በግራና በቀኘ በፊትና በኀላ ማየት ጀመረ፡፡ ለብዙ ደቂቃዎች አየ በመካከልም ላይ "አሃ" የሚል ድምፅ ከልጁ ሲወጣ ተሰማ .............ይቀጥላል

ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂ ገራሚ ታሪክ ነው🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY GRAPHIC DESIGN

ልጁ በግራና በቀኘ በፊትና በኀላ ማየት ጀመረ፡፡ ለብዙ ደቂቃዎች አየ በመካከልም ላይ "አሃ' የሚል ድምፅ ከልጁ ሲወጣ ተሰማ፡፡
ጠቢቡም " እሺ ምን ተገኘ" አለው

"በዚያ በኩል ባለው ቀዳዳ ብርሃን ነገር ይታየኛል" አለው
ጠቢቡም አቀፈው
"አሁን አይምሮህን መጠቀም ጀመርክ፡፡ አእምሮን መጠቀም ማለት ከአይነ ስጋ ይልቅ በዓይነ ልቡና ማየት መቻል ከእዝነ ልቡና መስማት መቻል ማለት ነው፡፡ "ልብ ካላየ አይን አያይም" ሲባል አልሰማህም አእምሮን የሚጠቀም ሰው ሁሉ የሚያየውን ብቻ ሳይሆን የማያየውንም ያያል፡፡

ለዚህ ነው አእምሮ ያለው ሰው ተስፋ የማይቆርጠው፡፡ አእምሮ ያለው ሰው በግንብ መካከል በር ፣ በጨለማ መካከል ብርሃን ፣ በተራራ መካከል ፣ ሕይወት ይታየዋል፡፡

መንገድ ያለው ከውጪ አይደለም፡፡
መንገድ ያለው ከውስጥ ነው፡፡

የውጪው መንገድ እግር ነው የሚሔድበት፡፡
የውስጡ መንገድ ግን ልቡና ነው የሚጓዝበት፡፡
በልቦናቸው የሔዱ ሰዎች ናቸው በእግራቸው ለመሔድ ፈልገው የእግሩን መንገድ የሰሩት፡፡
ከእነርሱ በኀላ ግን ብዙዋች በልቡናቸው ሳያዩ ይጓዙበታል፡፡
መጀመሪያ በልቦናቸው የበረሩ ሰዎች ናቸው አውሮፕላንን የፈጠሩት መጀመሪያ በልቡናቸው የተገናኙ ሰዎች ናቸው ስልክን የሰሩት እናመ መንገድ ያለው ውስጥህ ነው፡፡
አንተ ውስጥ መንገድ አለ፡፡

ምን አልባት ያ መንገድ #አልተጠረገ ከሆነ #ጥረገው #ተጎድቶ ከሆነ #ጠግነው #አርጅቶ ከሆነ #አድሰው ከዚያ በኀላ ሁሉም ነገር ቀላል ነው፡፡
ጊዜ ውሰድ፡፡
ለማየት ጊዜ ውሰድ፡፡
ወሳኙ የጨለማው መጠን አይደለም ወሳኙ አንተ የሰጠኸው ጊዜ መጠን ነው፡፡ ለማሰብ የምትወስደው ጊዜህና የምታስብበት መንገድ ነው፡፡
ጊዜህን ወስደህ ባሰብክ ቁጥር ያለኸው ጨለማ ውስጥ አመሆኑን ታውቀዋለህ፡፡ እስኪ ትንሽ ጊዜ እንውሰድ"

ሁለቱም ጥቂት ጊዜ ተቀመጡ
ያልጅም ማየት ጀመረ....
እስከዚያም በዓለም ላይ ታዋቂ የሆነውን

"የተጠማውን ቁራ ታሪክ" ልንገርህ

ቁራው ውሃ ጠማውና በአካባቢው ወዲያና ወዲህ እያለ መፈለግ ጀመረ፡፡ ግን አላገኘም፡፡ በመጨረሻም በውሃ ጥም ወደቀ፡፡ ነገር ግን ተስፋ ለመቁረጥ አልፈለገምና እንደምንም ብሎ ተነስቶ አካባቢውን ማማተር ጀመረ፡፡በሩቁም አንድ ገንቦ አየ ወድቆ እየተነሳ ገንቦው ጋር ደረሰ ሲያይ ጥቂት ውሃ ውስጡ አለ፡፡

ማንቁርቱን አስገብቶ ሊጠጣ ሲሞክርየገንቦው አንገት ጠባብ ስለነበር አልቻለም፡፡ገንቦውን ሊያዘነብለው ሲገፉውም ዐቅሙ ተዳክሞ ነበርና ያንን ከባድ ገንቦ መግፋት አልተቻለውም፡፡

"ማሰብ ጀመረ፡፡ መንገድ ከውስጥ ነውና ውስጡ መንገድ ፈለገ መንገዱንም አገኘው፡፡
በአካባቢው ያሉትን ጠጠሮች እየለቀመ ወደ ገንቦው ውስጥ መጣል ጀመረ ለብዙ ጊዜ ሲጥል ገንቦው በጠጠር እየተሞላ ውሃውም ወደላይ እየወጣ መጣ፡፡ በመጨረሻም የገንቦውን ታችኛውን ክፍል ሞላውና ውሃው ወደ ገንቦው አፍ ደረሰ ቁራውም ጠጣ፡፡"

በታሪኩ ትረካ መካከል ልጁ አንዳች ቅርፅ ያለው ነገር ተመለከተ፡፡ መሥመር ያለው ነገር ከወለሉ ጀምሮ ወደ ጣራው የተሰመረ፡፡ አይኑን ከታች ወደ ላይ እያንከባለለ ተከተለው፡፡ አንዳች የብርሃን ቀጭን መሥመር ከታች ወደላይ ሄደና እንደገና ወደ ግራ ዞረ ተከተለው፡፡ ከግራ ደግሞ ወደ ታች ተጠመዘዘ አብሮትም ሔደ፡፡ ከዚያም ተመልሶ ወለል ላይ ደረሰ፡፡

"ያ የብርሃን መስመር ምንድነው አለው ጠቢቡን"
"ጠጋ ብለህ እየው"
ፈራ
"አትፍራ ጨለማውን ሳትፈራ እንዴት ብርሃኑን ተፈራለህ፡፡ ምንጊዜም የማያቁት ነገር ያስፈራል ሂድ ተጠጋ፡፡"

ሄደና ተጠጋ፡፡ የጣውላ በር በሚመስለው ነገር ዙሪያ የሚገባ ብርሃን ነው፡፡

"እስኪ ንካው" አለው ጠቢቡ እየፈራ እየደፈረ ነካ አደረገው፡፡ ጣውላ ነገር ነው፡፡

"በምትችለው አቅም ሙሉ ግፋው" አለው ላቡ ጠብ እስኪል ገፋው፡፡ ሲጢጢጢ እያለ በመጨረሻ ያ ጣውላ የመሰለ በር ነገር ወደ ኀላ ወደቀ፡፡ ያን ጊዜ በውጪ ያለው ብርሃን ፏ ብሎ ገባ፡፡ ዓይኑን ጨፈን አድርጎ ሲገልጠው በበሩ ፊት ለፊት ሰፊ መንገድ አለ፡፡

"በሕይወትህ ለመለወጥ ከፈለክ ሦስቱን መሰረታዊ ነገሮች አሁን ተምረሃል" አለው፡፡
ምንድናቸው??

"መጀመሪያ እምነት ነው፡፡ ምንግዜም መንገድ አለ፡፡ ሊዘጋ ሊታጠር የማይችል መንገድ አለ፡፡ እርሱም አንተ ውስጥ ነው፡፡ ጊዜ ስጥ ለማሰብ ጊዜ ይኑርህ ምንጊዜም በፍለጋ ላይ ሁን፡፡
አሁን ያልታየህ ቆይቶ ይታይሃል ነገር ለመቁረጥ እንጂ ተስፋ ለመቁረጥ አትቸኩል፡፡ "ገና አላገኘሁትም እንጂ የለም አትበል"፡፡
አለ ግን አልደረስክበትም፡፡
#መድረስ "ጊዜና "ጥረት ይጠይቃል፡፡


ሦስተኛ ያገኘኸው ነገር ያገኘኸው አጋጣሚን ንካው፡፡
ካልነካኸው በሩ ግድግዳ እንደሆነ ይቀራል፡፡
ከነካኸው ግን በሩ መንገድ ይሆናል፡፡

ብርሃን ማየትህ ብቻ ዋጋ የለውም ብርሃኑ እንዳይገባ ያደረገውን ነገር መንካት አለብህ እክ?ኪወድቅ ብርሃኑ በሚገባ እስኪገባ መንገዱ ወለል እስኪል መግፋት፡፡

"ሳይነኩት በምኞት ብቻ የሚወገድ ችግር የለም የሚከፈትም በር የለም አየህ ማሰብ የብርሃን ጭላንጭልን አሳየህ ጊዜ ሰጥቶ ማስተዋል ይህንን በርገለጠልህ መንካት ደግሞ መንገዱን
አሳየህ፡፡ አሁን አይበቃህም??"

"ይበቃኛል"
"ታዲያስአሁን ምን አለህ"
"ገመድ አለኘ"

ሂድ ጊዜ ሰጥተህ ፣ መጣፍ አገላብጠህ ፣ ዐዋቂ ጠይቀህ ፣ ግራ ቀኙን አስብ፡፡
ይህች ገመድ ህይወትህን የመለወጫ ምክንያት ትሆንሃለች የባለፀጋነት መጀመሪያ የሥልጣን እርከን የሊቅነት ፋና ፣ የጀግንነት መንስኤ ትሆንሃለች፡፡

ያለበለዚያ ደግሞ #የመታነቂያህ መሳሪያ ትሆናለች ሁለቱም በእጅህ ነው፡፡"

ብሎ አሰናበተውና...........ሔደ

ዕንቁ መፅሔት ግንጣይ ገፅ ጥቅምት 2005
ሙሃዘ ጥበባህ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
ማልዋኪ ፣ ዊስኮንሲን

እኛስ ያለን ምንድነው??
ባለን ነገር ምንፈልገው ነገር ማምጣት አንችልም??
በደንብ እንችላለን....

የዛሬ መጨለም አይደለም ጨለማው ላይ መንገድ እንዳለ ማመን ነው💪እምነት ሁሉንም ይፈታዋል፡፡
ተስፋ ማድረግ ነው፡፡

ጊዜ ወስዶ ማሰብ ነው ከራስ ጋር ማውራት ነው
ችግር ላይ ስትሆን ከማማረር መፍትሔ መፈለግ ነው፡፡
ይሔን አስታውሱ አለም ላይ ምንም የሌለው ሰው የለም የሆነ ነገር አለን ዋናው ነገር አውጥቶ መጠቀሙ ላይ ነው፡፡
ፍርሃትን እናሶግድ
ምንግዜም መንገድ አለ......

እንበርታ እንጠንክር ፈጣሪ ወደ አለም አስታቅፎ የላከንን ተሰጦ አውጥተን እራሳችንንም ሌሎችንም እንጥቀም እንርዳ

አእምሮአችንን ለበጎ ነገር እንጠቀምበት

ዛሬ እዚህ ደርሰናል ሩጫችን ነገ ላይ ዛሬን ላለመድገም ይሁን


ጊዜ ሁሉን ይፈታል ከጣርን ሁሉም ይሳካል፡፡

@jahABP ነኘ

መልካም ቀን ተመኘሁ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

ወደ.....መለኮስ
😍😘
special.......uncle

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

የዛኔ አልበሟ እንደወጣ ሊያስጠኑን ልናጠና በሚል ሰበብ እንሰበሰብ ነበር ከዛ በ90ዎቹ ራዲዮ😍ድምፁን ቀንሰን የሷን ዘፈኖች መኮምኮም ነው፡፡

በደንብ ሰምተናታል የዛኔ ትንሽ ልጆች ብኖንም ብዙ ባናስተውልም ዘፈኖቹ ስለማይሰለቹም እስካሁንም ስለምንሰማው መልክቶቹ ሀይል አላቸው........እናም አንዱ ዘፈኗ በዚህ ጊዜ መደመጥ አለበት አልኩና ልጋብዛችሁ ፈለኩ

ወይ ኤልያስ መልካ ያስገርመኛል በኡነት ምን አይነት ሰው ነው ብዬ ሁሌም እራሴን እጠይቃለሁ ብሶታችንን ያወጣዋል መናገር ማለት ምንፈልገውን በድንቅ አእምሮው ወረቀት ላይ ያሰፍረዋል ምርጥ ግጥም አድርጎ ግጥሙን የሚያጎላ ዜማ ፈጥሮለት ከሚገርም ቅንብሩ ጋር እንካቹ ይለናል እኛም እንደነቃለን ውስጣችን ያለው ሀሳብ ነውና ተደስተን እንቀበላለን ኡነቱን እኮ ነው ግን እንላለን እኛም እንፈላሰፋለን ቆም ብለን እንጠይቃለን..........

ታላቁ ኤልያስ መልካ😍😔😢
አንተ ትለያለህ ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን🙏


ከፈጣሪ ጋርም በሷ ድንቅ ድምፅ እንዲህ እያለ ሙግት ይገጥማል

ዘፈን ብቻ ሳይሆን ፍልሰፍና ነው፡፡

ጥያቄ ነው ጥያቄው ለሰው አይደለም ለሱ ለፈጣሪ ነው..........

ምን እያለ??🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

ነገ ጠዋት ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

ተስፋ አለን እንደርሳለን ለዛሬ ብቻ አይደለም ነገንም ለማየት ነው ከትላንት ያለፍነው...... 🏃‍♂

@jahABP ነኘ

😊መልካም አዳር🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Track 7
Zeritu
ዘሪቱ ከበደ😍😘
"Track 7" የእኔም አይን አይቷል


አንዱን ሊያደድነው አንዱን ሊያሞኘው
ከአንዱ በፈሰሰ አንዱን ሊያርሰው
ላዘነው ሰው ምነው ቢያካፍለው ቢያቻችለው
ለዘረፈው ምነው በቃህ ቢለው
ይብቃህ ቢለው

አንዱ በዝቶበቶ ሲቸገር መምረጥ
ሌላው ምንም አጥቶ ላይ ታች ሲሮጥ
ላዘነው ሰው ምነው ቢያካፍለው ቢያቻችለው
ለተረፈው ምነው በቃኸ ቢለው
ይብቃህ ቢለው

ለመኖር ሲጓጓ ለማየት የፊቱን
ግን ሳይወድ ይሔዳል ሳይደርስ ምኞቱ
ሌላው ተዘጋጅቶ ሲጠባበቅ ቀኑን
ከርሞ ይበተናል እያለ በሞትኩኘ

ኦ ምን አለፋኘ መልሱ ከጠፋኘ
እሱ አይሳሳት ሁሉም በምክንያት
የኔም አይን አይቷል እሱ ያበራው
ሰሪ አይበልጥም ወይ ከተሰራው


ሰርቆ ለበላ ይበዛለታል
የታመነ አጥቶ ይንከራተታል
ለሚገባው ምነው ቢሆንለት ቢሳካለት
ለሚያምታታው ምነው ቢታይበት ቢቀጣበት

በፅናት ሲታገል ልልፋ እስኪያልፍ እያለ
ሳያልፍለት ያልፋል እንደተቃጠለ
ሌላው ግን ሳይለፋ ሳይጥር እንደደላው
ተስማምቶት ይኖራል አንድ ቀን ሳይከፋ

ኦ ምንአለፋኘ መልሱ ከጠፋኘ
እሱ አይሳሳት ሁሉም በምክንያት

የእኔም አይን አይቷል እሱ ያበራው
ሰሪው አይበልጥም ወይ ከተሰራው


ግጥም....ዜማ.....ቅንብር ታላቁ ኤልያስ መልካ
😍🙏🙏😘😘😔😢😢😭😭

👏👏👏👏እነቱን እኮ ነው እሱ ፈጣሪ አይሳሳት ሁሉንም በምክንያት ነው ሚያደርገው🤷‍♂🤷‍♂🤷‍♂🤷‍♂🤷‍♂

ኤላ አንተ ትለያለህ🙏🙏🙏


መልካም ዕለተ ቅዳሜ ተመኘሁ @jahABP ነኘ
AB PHOTOGRAPHY
🙏➋➌🙏

ሰማዕቱ ሀገራችንንበምልጃህ ጠብቅልን
ሀዘናችንን ለቅሶአችንን የሆነብንን አስብ

ካባቶቻችን ጋር ሆነህ ያደረከው የአድዋው ገድልህን ማንም አይዘነጋው......

ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
ሁሌም ከፊት ለፊት በኢትዮጽያ ሙዚቃ
ጥበብ እሱ እራሱ ስሙ ኤልያስ መልካ፡፡

ገጠምኩ ወይስ ተቀኘሁ

ኤልያስ መልካን ካጣነው ድፍን አንድ አመት ሞላን 😭😢😭

በከተማ መመነን እንደሚቻል ያሳየ ክፋትን በስራዎቹ የተጠየፈ ፍቅርን የሰበከ ፍቅርን ሆኖ በተግባር ያሳየ ሳይሞት ስለራሱ የዘፈነ ሁሉም ነገር ከፈጣሪ እንደሆነ የሚያምን......በፈጣሪ ትልቅ ዕምነት የነበረው ኤልያስ መልካ፡፡

ነበር ብሎ ማውራት ምንኛ ያማል😔😢😭😭🙇በቀጣይ ስለ ኤላ ከአንድ ታሪክ ጋር ልመለስ

1ኛ አመት መታሰቢያ🙏🙏
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

እሱ አይሳሳት ሁሉም በምክንያት

ስለ ኤልያስ መልካ ህይወት ሳስብ አንድ ታሪክ ትዝ ይለኛል....

አስታውሳለሁ በአባቴ ቤት ካሳንችስ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ፀሎቴን አድርሼ ቦታዬ ላይ ተቀምጫለሁ አንድ አባት እያስተማሩ ነው........ ድምፃቸው በደንብ ይሰማኛል

...........እግዚአብሔር አይሳሳትም ሁሌም ትክክል ነው ይላሉ.........

እኔም እውነት ነው እሱ አይሳሳት ሁሉም በምክንያት እላለሁ.....

ከዛ አንድ ትምህርት ጀመሩ

እኔም በጥሞና ተከታተልኩ......እንዲህ ይላል.....

አንድ ሰውዬ ከብዙ ጊዜያት የንግድ ጉዞ በኀላ ወደ ሀገሩ ይመለሳል...... ከቀዬው እንደደረሰም ድል ያለ ድግስ ያያል....ተገርሞ ምንድነው ብሎ አጠገቡ ያገኘውን ሰው ይጠይቃል......

ሰውዬውም አይ የሀገሩ ንጉስ አርፈው ነው ይላል

እንዴ ይህ ንጉስ ህዝቡን ሲበድል ያለውን ሲቀማ አባቶችን ያለ ክፍያ ሲያስለፋ
እናቶችን ሲያስለቅስ
ወጣቶችን ሲገል....ሲያሳድድ አይደለም እንዴ የኖረው.......ይኸው እኔም በሱ የመጣ አይደል ከሀገሬ ተሰድጄ በሰው ሀገር ስሰቃይ የኖርኩት
እንዴት እንዲህ ድል ተደርጎ ይደገሳል ሰርግም አይደል ሞት ይላል..... በአካባቢውም የነበሩት ጥለውት ይሸሻሉ........እሱም እጅግ እየተበሳጨ

ከራሱ ጋር እያወራ ወደ ቤቱ መንገዱን ይቀጥላል
🤦‍♂🚶‍♂🚶‍♂

ከግማሽ ሰዓት ጉዞ በኀላ ወደ ቤቱ እንደመድረስ ሲል ከሩቅ ከሰፈራቸው ደብር አካባቢ በጫካው ውስጥ የተሰበሰቡ ሰዎች ያያል ምን ሆነ ወይ ጉዴ ማን አረፈ ይሆን ብሎ ርምጃ ሳይሆን እንደ ሩጫ ወደ ቤተክርስቲያኗ ነጎደ.........ሲደርስም ምን ተፈጠረ ማን ምን ሆነ አለ አለ በድንጋጤ ሚሆነውን አቷል

ሰዎችም ለማረጋጋት እየሞከሩ የቤተክርስቲያኑ እጅግ የተወደዱ ቄስ እከሌ ናቸው...... አሉት ኮትኩተው አሳድገውታልና ክፉኛ አለቀሰ ወደሳቸው ወደ ሬሳቸው ቀርቦ ሲመለከት ይባስ ብሎ የሞቱት በጅብ ተበልተው ነው......ከቅድሙ ይቀልጥ እየጮኸ አለቀሰ....
ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ....ወይኔ አባቴን.....አባቴን.....ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ....
ለያዣ አስቸገረ...... ለምን እኮ ለምን እያለ እያለቀሰ እየጮኸ ወደ ቤተክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ
ገባ........

በትልቁ የመድኃኒዓለም ስነስዕል ፊት እየጮኸ ተንበረከከ ለምን ለምን አንተ ኡነተኛ ፈራጅ ሆነህ ሳለ ለምነ ወይስ አይደለኸም??
ለምን እንዲህ ታረጋለህ መልስልኘ ለምን......ለምንንንን???

ስንት ሰው ሲበድል የነበረውን የስንት ሰው ሞት ተጠያቂ የሆነውን የስንት ሰው እንባ ያለበትን ሰውዬ ሞቱን ድል አድርገኸ ደግሰህ ሞቱን እየሸኘህ.........

ለስምህ ሲሉ ደፋ ቀና ያሉ ሌት ተቀን ሲያገለግሉህ ህዝቡን ወደ ንሰሃ እያሉ ከደጀ ሰላሙ እንዳንጠፋ ያደረጉ ህፃናት ሀ...ሁ...አቦጊዳ የመገቡ ስንት ዲያቆናትን ያወጡ ስለስምህ መከራን የተቀበሉ ገደልክ.....እሱስ ይቅር እሱስ ይቅር እንዴት አሟሟታቸውን እንኳን ምናለ ብታሳምረው ይሔ ልክ ነውውውውውውው ይሔሔሔ ልክ ነው መልስልኘ በጅብ በጅብ አስበልተኸ ትገላቸዋለህ ምን አይነት ጨካኘ ነህ ኡኡኡኡሐ ለምን መልስልኘ እያለ ያለማቋረጥ ይጮኻል......


እግዚአብሔርም አምላክም ድምፁን አሰማ እንዲህም አለ.....


ልጄ ሆይ ስማኘ ማዘንህን አይቻለሁ ለቅሶህን ሰምቻለሁ እንባህም እኔ ጋር ደርሷል ግን ልጄ ምክንያቴን ግን ልብ ብለህ አድምጠኘ

ያንጉስ የሰራውን ሀጢያት ረስቼ ወይም ዝም ልል ፈልጌ አይደለም እኛ ካህን ያደረጉትን ፅድቅ ጠፍቶኘ አይደለም እኔ ልብና ኩላሊትን ምመረምር አምላክ መሆኔም አትዘንጋ.....ግን ምክንያቴ ይህ ነው..........

ንጉስ ብዙ ሀጢያቶችን ሰርቷል ይህ ሚደበቅ አይደለም ግን ንጉስ በምድር ህይወቱ የሰራቸው ትንንሽ ደግ ነገሮች ነበሩ እነሱን በማሰብ ሰማይ ቤት ሊቀጣ የሀጢያት መዝገቡ ሲገለጥ ከንቱ የሆነ አስቧቸው ያልሰራቸውን ትንንሽ ደጋግ ስራዎች እንዳያነሳ እዛው ምድር ላይ በትንሹ እየከፈልኩት ነው.........

እኛ ፃድቅ አባትም በምድር ላይ ሲኖሩ የሰሩት ትንሽዬ ክፉ ስራ ነበራቸውና የፅድቅ መዝገባቸው ሲከፈት ጥንት ጠላታችን ዲያቢሎስ ሆን አስበው አቅደው ያልፈፀሙትን ሀጢያት እንዳይናገር እዚሁ ቀጥቻቸው ሰማይ ቤት ነፃ እንዲሆኑ ነው አለው፡፡


ይህን ታሪክ ወደ ታላቁ ኤልያስ መልካ አዙሬ አሰብኩት....

ማቆ ጠቁሮ ከስቶ መልኩ ጠፍቶ የነበረው
አለበት የተባሉት በሽታዎች እንዳለ የምድር ትንንሽ ሀጢያቱ ሰማይ ቤት እንዳይጠየቅበት የተቀበላቸው አይመስላችሁም ለኔ በደንብ ይመስለኛል፡፡

😍ነፍስህን በአፀደገነት ያኑርልን🙏

እሱ አይሳሳት ሁሉም በምክንያት


😢😢😢😢😭😭😭😍🙏🙏🙏

@jahABP ነኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY


🔥🔥🔥
Boooommmmmmm

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

መቁረጥ አለመቻል


" "በጊዜው የሆነ እንቢታ የእሺታ ያህል ነው፡፡" ይባላል፡፡

ሳይፈልጉ እሺ እያሉ ሰውን ሲያሹ ከመኖር እምቢ ብሎ ቁርጡን መንገር የሰዎችን ጊዜና ተስፋ የሚያከብር ነውና ትልቅ ስጦታ ነው፡፡

እንደ ዲፕሎማት እሺ እና እምቢ የሌለው የሚንቀዋለል ሕይወት በጣም አደገኛ ነው፡፡
"ቁርጥ ያጠግባል" ይባላል፡፡ ቁርጥ ስጋውን ሳይሆን ቁርጥ ውሳኔ አርኪ መሆኑን የሚገልፅ፡ነው፡፡

ሕይወት የራሳችንን ውሳኔ የምትጠይቅ ሂደት ናት፡፡ ከሰውነት ክብራችን አንዱ መወሰን መቻላችን ነው፡፡
መወሰን የማይችሉ ሰዎች ሌሎች እንዲወስኑላቸው ይፈልጋሉ፡፡
ሌሎች በብዙ ነገሮች ሊወስኑልን ቢችሉ እንኳን ራዕይና ነፍሳችንን በተመለከተ ግን ሊወሱንልን አይችሉም፡፡

ለውሳኔ የሚያስፈልገንን በመጀመሪያ የእውነት እውቀት ነው፡፡
ቀጥሎ የቅኖችና የአስተዋዮች ምክር ነው፡፡
ከሁሉ በላይ በነገሩ ላይ የእግዚአብሔር ፈቃድ መጠየቅ ነው፡፡
አንዳንድ ጊዜ የእውነትን እውቀት አውቀን ለመወሰን እንቸገራለን፡፡
የህይወት ለውጥ የሚጀምረው ከውሳኔያችን ሰዓት አንስቶ ነው፡፡

በራዕይ ላይ መቁረጥ አለመቻል ትልቅ እንቅፋት ነው፡፡
እውቀቱን ጠግበው ቆይ ዛሬ ፣ ቆይ ነገ የሚሉ ቀን ተሰጥቶአቸው ቀን የሚጠብቁ ውሳኔ የሌላቸው ልፍስፍሶች ዕድር ጡሩንባ ያልነፋባቸው ሙታኖች ብዙ ናቸው፡፡

በዚህ ዓለም ላይ ተመልሰን አንመጣም፡፡
እያለፍን እንጂ እየኖርን አይደለም፡፡
ዓለም የአቋራጭ መንገድ ናት፡፡
በውሳኔ ዓለም ላይ ካልወሰንን የት እንወስናለን?

ሰማይማ የውሳኔአችን ደመወዝ ያለበት ስፍራ ነው፡፡"

@jahABP ነኘ 😊🙏

😍መልካን ቀን ተመኘሁ🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY


ተፈጥሮ አስደሳች
አስደሳችየሆነው ህጉን ስለሚያከብር ነው፡፡

ፀሃዯም ይኸው በምስራቅ ወታ በምዕራብ ትገባለች.......

በውቢቷ ሃዋሳ 😍ላይ ሆነህ ደሞ ይህን ትዕይንት መመልከት ነፍስን በሐሴት ይሞላል

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
ይህንን ፅሁፍ እንዳስታውሰው ያደረገኘ አንድ ጓደኛኜ ነው..........ይሔን እንደምታነበው አውቃለሁ.........


በደንብ አውርተንበት መግባባታችን ደግሞ አስደስቶኛል.....



ሁሌም መልካም መሆን🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂ጠብቁኘ
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

የአገራችን ኑሮ ብድር ነው

የአገራችን ኑሮ ስጦታ ሳይሆን ብድር ነው፡፡
ፍቅር ስጦታ ነው፡፡ ብድር ግን ሲከፋፈሉ መኖር ነውና አድካሚ ነው፡፡
ሰዎች ያመጡልንን እንመዘግባለን፡፡
በደስታ ከመቀበል ቀን እንጠብቃለን፡፡
አሳንሶ ላመጣ አሳንሶ ለመስጠት ስጦታ መሳዩን በቀል መዝግበን እንኖራለን፡፡

ፍቅር ግን ሲያልፍ ነው፡፡ የእኛ ወደዚያ በደንብ ሲያልፍ የሌሎችም ወደ እኛ በደንብ ሲፈስ ነው፡፡
ፍቅር ስጦታውን ሳይሆን ወዳጁን ያያል፡፡
ፍቅር በቁሳቁስ ከተሰፈረ ዋጋው ያንሳል፡፡

ባለ ራዕይ....መልካም ሰው ምን አድርገውልኘ ነበር ብሎ መዝገብ አያገላብጥም፡፡
ላልሰጡት ለመስጠት ፣ ያላስተማሩትን ለማስተማር ይገሰግሳል፡፡
ብድርን ወይም ምላሹን አያገናዝብም እንደውምየሚጠብቀው ስድብን ነው የሚጠብቀው ነቀፋንና ክዳትን ነው፡፡

በቤት ውስጥ ካሉት ቁሳቁስ ይልቅ በር ላይ ያለው፡፡ የእግር መጥረጊያ ምንጣፍ ትልቅ አስተዋፆ አለው፡፡
ባለቤቶቹ እንድንገባ የሚፈቅዱልን በልባቸው ቆሻሻችንን መጥረጊያ ምንጣፉ እንዳለ ስለሚያስቡ ነው፡፡ እኛም ጠርገን በነፃነት እንገባበታለን የፀዳንቀትን እቃ ግን ለማየት እንኳን አንፈልግም፡፡ አገልግሎቱም አይታየንም፡፡

ከዚያም ይልቅ ንፁህ ካልሆንን የማይወደውን አበባ ምንጣፍ እናደንቃለን፡፡

በህይወት ላይም ንፁህ ስለሆንን የሚወዱን እና ከነማንነታችን የሚቀበሉን አሉ፡፡
ከነማንነታችን የሚቀበሉንን ሰዎችን ግን ዋጋቸውን አላወቅንም፡፡ እንደደጅ ምንጣፍ እየረገጥንባቸው እንኳን አናያቸውም፡፡
ዋጋቸውን ለማሰብ እንኳን አንፈቅድም፡፡

ብዙ መልካም ሰዎች እንደሚተክዙ እናውቃለን፡፡
ለራሳቸውምያለቅሳሉ በሚያገለግላቸው ሰዎች ደንዳናነት ውለታ ቢስነት ተስፋ ይቆርጣሉ፡፡
አንዳንድ ጊዜ መልካም ሰዎች እግዚአብሔርን ማየት አቁመው ለራሳቸው እያለቀሱ ይገኛሉ፡፡
ለመልካምነታችን ዋጋውን ከሰው አይጠበቅም፡፡

የመልካምነት ዋጋ ከፋይ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡
ሰዎች ቢከፍሉንም የሰው እጅ ትንሽ ልቡም ስስታም ነውና የእግዚአብሔር ይሻለናል፡፡

እንዳንዴ በኑሮአችን ምናየው ነው ችግራቸውን በገዛ አፋቸው ይነግሩናል ደስታቸውን ግን ከሰው ተነግሮን እንሰማለን፡፡
ችግራቸውን ሲነግሩን ከዘመዶቼ ደብቄ ነው ይሉናል፡፡ ደስታቸውን ግን ከእኛ ደብቀው ለዘመዶቻቸው ይነግራሉ፡፡

በነዚህ ቀላል ሰዎች መገረም እንኳን የለብንም፡፡
ምክንያቱም መገረም ጉልበት ይጨርሳልና፡፡
እኛም ለእግዚአብሔር እንዲህ ነን እያልን ራሳችንን ግን እንይበታለን፡፡

ዋጋችንን ከነዚህ ከጠበቅን ግን መልካምነታችን አደጋ ላይ ይወድቅብናልና ምላሹን ከእሱ ከባለቤቱ ከፈጣሪ እንጠብቅ፡፡

ራዕይ ያለው ትውልድ
ለንባብ እንዲመች አድርጌ የቀነጨብኩት

መልካምነት መልካምነት መልካምነት ይለምልም!!

ባደረግነው መልካም ነገር ብዙ ጊዜ ጥሩ ምላሽ እንደማናገኘ መገመትን ተምሬበታለሁ፡፡🙏😊
የመልካምነት ከፋዩ ፈጣሪ ስለሆነ ደግሞ ደስታዬ ወደር አልባ ነው🙏ተመስገንልኘ

😊 @jahABP ነኘ መልካም አዳር 🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

ለሚያየውም ለማያየውም ለሁሉም ሲል ነጋ

🙏ተመስገንልን🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
በደንብ አንግባባም በሰላምታ እንጂ ከዛ ውጪ አውርቼው እንኳን አላውቅም ደስ ሚል ፍልቅልቅ ሲስቅ በጣም ደስ የሚል የሚያምር😁😍ምግብ ቤት ይመጣል ሰላም ነው ይለኛል የሱ ሰላምታ የኔን ፊት ፈካ ያደርገዋል የታዘዘውን ምግብ ይነግረኘና መጣሁ እሺ እላይ ምገዛው እቃ አለ ይለኛል እሺ ቶሎ ደርሰህና እለዋለሁ ያዘዘውን ምግብ ከሰጠሁት በኀላ እንዳይጥለው እሳቀቃለሁ ቀስ እያልክ እሺ ሒድ እለዋለሁ የሚያምረውን ፈገግታውን ይለግሰኘና በትንንሽዬ እግሮቹ ድክ ድክ ጥሎኘ ይሔዳል፡፡

ታዲያ ትላን ማታ መጣና ሰላም አለኘ እንዴ ምነው ጠፋህ በሰላም ነው አልኩት እየተሽኮረመመ አዎ አለሁ እኮ አለኘ.... አትጥፋ እሺ ብዬው ሔደ ከዛ ሱቅ ደርሶ መጣና ይህን በምስሉ ላይ ያለውን ማስቲካ ለኔና ለወንድሜ አንድ አንድ ገዝቶል መጣ በጣም አሳዘነኘ ማላቀው ስሜት ውስጤን አላወሰው ከልብ አመሰግናለሁ እሺ የኔ ቆንጆ እያልኩት ምስጋናውን ላለመስማት ይመስል ጥሎን እሮጠ

የዛኔ ነው አሳዛኙ ታሪክ ወንድሜ የነገረኘ አብያ ባለፈው ካንሰር ያለበት ህፃን አለ ያልኩህ እኮ እሱን ነው አይለኘም😢😭 በጣም ደነገጥኩ ማርያምን በል አልኩት ማለልኘ አዘንኩ በራሴ በጣም አዘንኩ የሆነ ነገር ለማድረግ ያሰብኩ የነበረ ቢሆንም እስካሁን በመቆየቴ አዘንኩ እሱ በለጠኘ🤦‍♂😢


አንዳንድ ሰዎች ከኛ በጣም ጥለውን ሔደዋል
ለመስጠት መቀበልን መስፈርት የማያደርጉ ዝም ብለው መውደድ ያለምክንያት መልካም መሆን ከኛ ምንም ሳይጠብቁ መውደድ😔🙏 ምንኛ መታደል ነው ከዚ ህፃን ልጅ ብዙ ተምሬያለሁ፡፡


ከዚህ በፊትም የአቅማችንን የተቻለንን ለማድረግ አስበን ስለነበር በዚህ በጎ ተግባር መሳተፍ የምትፈልጉ በውስጥ መስመር ልታናግሩኘ ትችላላቹ፡፡

ፍቅር መልካምነት መረዳዳት

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ
"ፍቅር ማለት በምትወደው ነፍስ ውስጥ ራስን መግደል ነው".............

ማነው ያለው?🤔 ጠብቁኘማ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

"ፍቅር ማለት በምትወደው ነፍስ ውስጥ ራስን መግደል ነው"

ለብዙዎቻችን "ምስጢር" የሆነው ፍቅር ከሰው ልጅ የሕይወት ልምዶች ውስጥ አስደናቂውና አይረሴው ነገር ቢሆንም ሊያጤኑት የወደዱ ግን እጅግ ጥቂቶች ሆነው ተገኘተዋል፡፡
ለፍቅር አመጣጥና ዕድገት በየሰው ሕይወት ውስጥ በሚደንቅ ስነፅሁፋዊ አገላለፅ ሲቀርብና ሲያስደንቀን ኖሯል፡፡

ፍቅር በታላላቅ ደራስያን ብዕር ተፅፉል ፣ በታላላቅ ድራማዎች ላይ ተሰርቷል ፣ ባለቅኔዎች ተቀኘተውበታል.....ነገር ግን ፍቅር ምንድነው?
የሚለው ጥያቄ "መልስ አገኘሁለት" በማለት ለመፃፍም ሆነ ለመናገር የደፈረ "አልተገኘም"

አንድ ወንድ አንዲት ሴት ያፈቅራል ይህን የተለመደና በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ የሚከሰት ስሜት ተራ ክስተት አድርጎ ማለት የፍቅር ሀያልነት እንደማሳነስ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
የፍቅር ሀያልነትን ጠበሉን የተቋደሱ ሁሉ ሲመሰክሩ፡- "ፍቅር ከህይወት ጡት ውስጥ እንደሚፈልቅ ወተት አድርገን እንውሰደው"ይላሉ

የፍልስፍናው ጎራ ሰዎችም በዚያ ይስማማሉ፡፡ ሕፃን ልጅ የእናቱን ጡት ሲመለከት የሚሰማውን ደስታ ያህል በወጣትነት ዘመንም በሴቷ ላይ የሚያየው ቁንጅና እንዲሁ ያደርገዋል፡፡
ዳሩ ቁንጅናዋን የፍቅሩ ምክንያት አድርጎ መውሰድም የሚከብድ ነው፡፡

ምክንያቱም
#ቁንጅና_ፍቅርን_ከሚፈጥረው_በላይ
#ፍቅር_ቁንጅናን_ይፈጥራልና ፡፡

እንደመሰለው እንደመሰላት እንደመሰለን እንፋቀራለን፡፡ በትክክል የፍቅራችንን ክፋይ ያገኘን መስሎን በፍቅር የደከምንባቸው ጊዜያት መለስ ብለን ተመልክተን ደግሞ መሳሳታችንን ስንረዳ መለያየትን በቦታው ተክተን ወደሌላ የፍለጋ ጉዞ እንሰማራለን፡፡

ፍቅርን በባግህዋን ሽሪ ራጅናሽ(ኦሾ) እይታ ደግሞ ለማየት እንሞክር፡፡

#ኦሾ "No Water, No Moon" በተሰኘው መፅሐፉ ፍቅርን እንዲህ አስቀምጦታል:-

"ብዙዋች በፍቅርና በወዳጅነት መካከል ያለው ልዩነት ጠፍቷቸው በጎዳናው ላይ ሲዳክሩ ይስተዋላል፡፡ አንድ መስለው ይታዩዋቸዋል ነገር ግን አንድ አይደሉም፡፡
ይመሳሰሉባቸዋል ነገር ግን በእውነታው አይመሳሰሉም፡፡

እንዲያውም ከወዳጅነት ይልቅ ከፍቅር ጋር የሚመሳሰሉ ጥላቻ ነው፡፡
ጥላቻ ተቃራኒውን ነው - ወዳጅነት የጥላቻን እውነታ ደብቆ የፍቅርን መልክ ይይዛል፡፡
ነገር ግን ፍቅርን እየገደለ ነው፡፡
አንድን ሰው የግል ንብረት አድርጎ ማሰብ(Possessiveness) መርዘኛ ነገር የለም፡፡ ይህን በሚገባ ከተረጃችሁ ወደ ቀጣይ ጉዳይ እንዝለቅ....." ይላል፡፡

"ለብዙዎችእንዲህ ሆኗል ለናንተም እንዳይሆንባችሁ ልንገራችሁ ምክንያቱም በፍቅርና በግንኙነት መካከል ያለው ልዩነት ግራ አጋብቷቸዋል፡፡
በተለይም ከውጪ ሆነው ሲመለከቱ የኖሩ ሰዎች ሰለባው ሲሆኑ ኖረዋል ወዳጅነትና የግል ማድረግን እንደፍቅር ወስደውት አይቻለሁ፡፡
በዚህ መንገድም እውነተኛውን ነገር አጥተውታል

"ሰውን የግል ለማድረግ መሻት የውሸት ፍቅር ነው፡፡ ከእንዲህ ዓይነቱ ስሜት ጥላቻ ይሻላል፡፡
#በጥላቻ_ውስጥ_ውሸት_የለም፡፡
ከዚያ በላይ ደግሞ ጥላቻ አንድ ቀን ፍቅር ሆኖ ሊቀየር ይችላል፡፡
የሰውን ልጅ የግል የማድረግ ፍላጎት ግን ፈፅሞ ወደ ፍቅር ሊቀየር አይችልም፡፡

"ፍቅር ማለት በምትወደው ሰው ነፍስ ውስጥ ራስህን መግደል ነው፡፡"
ፍቅር ማለት ሞት ነው፡፡
የሚቻልህን ያህል ጥልቅ በሆነ ሞት ውስጥ ትገባለህ የምትሞተውም በምትወዳት ሴት ነፍስ ውስጥ ነው፡፡


ዕለት ዕለት ወደ ጥልቅ የነፍሷም ቦታ ትወስዳለህ ፍቅር ወደ ምታፈቅራት ሴት የነፍስ ቦታ የምታደርገው ዘላለማዊ ጉዞ ነው፡፡
ጉዞውም ማቆሚያ የለውም፡፡
አንዲት ሴት ስታፈቅራት አንተ ሕይወት ውስጥ ከአንተ በላይ ዋጋ አላት፡፡
ፍቅር ማለት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መማረክ ማለት ነው፡፡

ምክንያቱም አንዳች ቅድመ ሁኔታ መማረክ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም አንዳች ቅድመ ሁኔታ የምናስቀምጥለት ከሆነ ከምታፈቅረው ሰው በላይ ለራስህ ዋጋ ሰጥተኃል ማለት ነው፡፡

ራስህን ዋነኛ ጉዳይ አድርገህ በፍቅር ውስጥ ስትመለከት ተፈቃሪዋ መጠቀሚያህ ሆነች የፍላጎትህ ማርኪያ አደረግሃት በሌሎች ዘንድ መደነቂያህ ሆነች መነሻውም መድረሻውም አንተ ሆነሃል፡፡
ፍቅር ደግሞ መነሻው አንተ መድረሻው ግን ተፈቃሪው ይሁን ይልሃል፡፡
በተፈቃሪው ውስጥ ትሟሟለህ ትጠፋለህ፡፡
የመሞት ሒደትና ክስተት ነው፡፡

ለዚህም ነው ሰዎች ፍቅር የሚፈሩት፡፡
ስለፍቅር ልታወራ ፣ ልትዘፍን ፣ ትችላለህ ነገር ግን የልብህ ጥልቅ ስሜት ቢመረመር ፍቅርን በመፍራት የተሞላ ነው፡፡

"ስለፍቅር የምትቀኘው ቅኔ የምታዜመው ዜማ ሁሉ የፍቅር የምትክ እንጂ በራሳቸው ፍቅር አይደሉም በአጭሩ የምታፈቅረውን ሳታፈቅር ነው፡፡
ፍቅር ደግሞ ያለእሱ መኖር የማትችለውን እጅግ አስፈላጊህ ነገር ነው፡፡
ፍቅርህን እውነተኛ ካልሆነ ደግሞ ምትክ የሚሆነው ነገር ያስፈልግሃል፡፡

የእሱ ምትክ ደግሞ መሻት ሊሆን ይችላል ቢያንስ በመሻትህ በፍቅር ውስጥ ያለህ አድርጎ እንዲሰማህ ያደርጋል፡፡
የውሸት ፍቅርህን እንኳን ደስታን ይፈጥርልሃል፡፡
ፈጥኖም ሆነ ዘግይቶ ግን የውሸት መሆኑን መረዳትህ አይቀርም፡፡ ያን ጊዜ የውሸት ፍቅርህን ወደ እውነተኛ ፍቅርን መለወጥ አትችልም፡፡
አንድ የምትችለው ነገር ቢኖር "ያፈቀርከውን" ሰው መለወጥ ብቻ ይሆናል፡፡

"ሁለቱ መንገዶች እነዚህ ናቸው፡- ያለህበትን ፍቅር የውሸት መሆኑን ስትረዳ ራስህን መለወጥ ትችላለህ፡፡ ይህንን የውሸት ፍቅር ጥለህ ወደ እውነተኛው አፍቃሪነት ትገባለህ፡፡

ሁለተኛው መንገድ ደግሞ ያፈቀርካትን ሴት መለወጥ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ደግሞ አእምሮህ የሚሰራው እንደምታታልል ሳይሆን እንደተታለልክ ነው፡፡


"በምታፈቅረው ሰው በኩል ችግር አለመኖሩ ብትረዳ እንኳን ወደ እውነተኛ ፍቅር ለመግባት ትፈራለህ፡፡ ፍቅር እንደሞት ያስፈራሃል፡፡
ሞትን የምትፈራ ከሆንክ ደግሞ ፍቅርን መፍራትህ አይቀርም፡፡
በሞት ውስጥ የሚሞተው ስጋህ ብቻ ነው፡፡ ማንነትህ ግን እንደተጠበቀ ይኖራል፡፡

ለአንተ ከምንም ነገር በላይ አስፈላጊ ሆኖ የኖረው አእምሮሆ ወደ ሌላ ሕይወት ይወስዳል፡፡
ውስጣዊ ማንነትህ ግን አይቀየርም፡፡ ሞት የሚለውጠው የላይኛው ሽፋንህን ብቻ ነው፡፡


"ስለዚህም ሞት ይህን ያህል ጥልቅ ነገር አይደለም ፡፡ እንግዲህ ሞትን የምትፈራ ከሆነ እንዴት ወደፍቅር የመግባቱ ድፍረት ይኖርሃል?
ምክንያቱም በፍቅር ውስጥ የሚሞተው የላይኛው ሽፋንህ ብቻ ሳይሆን ውስጥህም ነው፡፡

የሞት ፍርሃት የፍቅር ፍርሃት ሆነ ፣ የፍቅር ፍርሃት ደግሞ የጥልቅ ሀሳብ ወይም የፀሎት ፍርሃትን አመጣ፡፡ እነዚህ ሦስት ነገሮች ተመሳሳይ ናቸው:- ሞት ፣ ፍርሃትና ፣ ጥልቅሃሳብ፡፡
አፍቅረህ የማታውቅ ከሆነ መፀለይ አትችልም ማሰላሰልም አትችልም፡፡
አፍቅረህም ሆነ በጥልቅ ሃሳብ ውስጥ ገብተህ የማታውቅ ከሆነ ደግሞ የሞትን የተዋበ ልምምድ አታውቅም ማለት ነው......."

ጥበብ ከጲላጦስ ስብስብ ስራዎች
(፩ ፪ ፫ ፬)
ከኃይለጊዮርገስ ማሞ

ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንደወሰድኩት

😃እየተፈላሰፋችሁ እደሩ😄

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁ አድርሱኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD