Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
ለሰኞ ጠዋት ሚሆን ሙዚቃ............🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
03 Track 3.wma
3.3 MB
💪🏃‍♂💪🏃‍♂🏃‍♂🤓

ቀና ቀና ቀና ልል እንደአንበሳ
ተራ ሰው መሆን በቃ ደግሞ ኮሳሳ
ዱብ ዱብ ልል እንደአንበሳ
ባሉበት መታሸት የለ በቃ አበሳ

ስንፍናን ታጥዬ በብርቱ ልነሳ
ምክንያት ማመካኘት እኔም ላላበዛ
የእናቴ መቀነት ጠለፈኘ ወቀሳ
ማልቀስ ማለቃቀስ አበቃ ተረሳ
ከፊቴ የቆመ ደንቃራ ደብሳሳ
ወይ የማይራመድ ወይ የማይነሳ
ሊጎትተኘ አለ ሊያስቀረኘ በዋዛ
እሱን አያድርገኘ በቁጣ ሳገሳ....
ኦው እንደአንበሳ

😍 ዘሩባቤል ሞላ

መልካም ሰኞ😊
🙏 ፅድት ያለች ሳምንት ተመኘሁ😍
ይቺን ግጥም ተጋበዙልኘማ

ከበላይ በቀለ ወያ

አዲሱ መፅሐፍ.......🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂ነገ
😊🙏😊
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#ማስታወስን #መርሳት

ከሁሉም ከሁሉም
እሱን በማምለኬ እኔን የሚቆጨኘ
የሰናፍጭ ቅንጣት
ታህል እምነት ሰጥቶኘ ተራራ ሚያጋጨኘ
ቃሌን ሳለሰልስ የሚያነጫንጨኘ
እንባዬ ጨው ሆኖት...
የደጁ እየጠራ እንባ የሚያስረጨኘ
አለ የሆነ አምላክ!
በሴቶች ልብ ላይ ጀማምሮ ማይቋጨኘ፡፡

ጀመረ ልማዱን
ካቻምና ከአንዷ ጋር በፍቅር ዘረረኘ
እሷን እሷን እያልኩ
እሱን ስለረሳሁ አጣልቶ መከረኘ፡፡
ስጣላት ደጁ ሔድኩ
አልቅሼ ልማፀን "አታሳጣኘ" ብዬ
ባይሰማኘም ሰማኘ ደረሰው እንባዬ
"አንድ አለችኘ" ምላት.......
ልቤ ላይ ከሰመች አስረሳኘ አንድዬ፡፡

......

ጀመረ ላይቋጨኘ !
አምናም ከአንዷ ጋር በፍቅር ተሰዋሁ
"እሷን እሷን" እያልኩ የሡን መኖር ረሳሁ፡፡
ስረሳው ትዝ አልኩት እንባዬ ናፈቀው
ልቤን ከልቧ ላይ በደማቁ ፋቀው፡፡
ስፋቅ ደጁ ሔድኩኘ....
እንደለመደብኘ እሱን አስታውሼ
እሷን እረሳኀት
ወጣች ከልቤ ላይ ሸኘኀት አልቅሼ፡፡


ጀመረ ላይቋጨኘ!
ዘንድሮም አፈቀርኩ ላንዷ ሰጠሁ ነፍሴን
እሷን እሷን እያልኩ.....
አምላኬን ረሳሁት ዘነጋሁ እራሴን፡፡
ስረሳሁ ትዝ አልኩት ለእንባ ደጁ ጠራኘ
"መቼም የማይረሱት....
አንድ ነገር አለ" ሲል አንድዬ መራኘ፡፡
እላለሁ "እሷ ናትመቼም የማልረሳት
እኩል እረስቼ እኩል ማስታውሳት

እላለሁ "እሷ ናት!"
በሰፈሯ እንዳላልፍ...
የመረጥኩት መንገድ ደጇ የሚወስደኘ
እረስቻት ስኖር.....
ረስቻት የማላውቅ ልቤ እያስገደደኘ
እሷን ለመርሳት ስል
ከብዙ ሴቶች ጋር ልላመድ ብለፋም

እላለሁ ለራሴ

" #ነፍስ_ላይ_ያተሙት_ልብ_ላይ_አይጠፋም፡፡"
አዎ ነፍሴ ላይነች !
ስትሔድ ነው የሞትኩት ስጋዬ በስብሷል
ህያውነቴ ላይ ትዝታዋ ነግሷል፡፡
እላለሁ ለራሴ.....

"ሰው ገነትን ቢወርስ ፃድቅ ብትሆን ነፍሱ
ካምላኩ ጋር ቆሞ......
#ብቻውን_ከሆነ_ሲኦል_ነው_ለራሱ፡፡"
አዎ ሲኦል ላይ ነኘ ገነትን ወርሼ፡፡
ራሴን በራሴ....
#ሳቃጥል_የምኖር_እሷን_አስታውሼ፡፡
እላለሁ ለራሴ....

"እሷ ራሷ ማናት
ሁሉን ምታስረሳኘ ነፍሴ ላይ ታትማ?
ከረሳሁት ጋራ....
ረስቻታለሁ ትዝ አትለኘማ?

የለም
የለም
የለም
#ረስቻት_እንኳን_አልችልም_ልረሳት
አለ አይደል አንዳንዴ.....
ገነትን ሲወርሱ ሚናፍቁት እሳት
እሷ ማለት ያ ናት!

እሱ ግን ማን ነበር....
በሴት ልጅ ልብ ላይ ጀማምሮ ማይቋጨው
እረስቼዋለሁ መርሳቴ እስኪቆጨው!

ኩል እና ጥላሸት የግጥም መድብል
በላይ በቀለ ወያ


@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

አስታውሳለሁ 2005 ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ወደዚህ ቅዱስ ቦታ እግሬ የረገጠው፡፡

ኧረ እኩዬ ይቺን ነው ይከብዳል ያልከን😂😂 ባንዴ ነው ምኖጣት ብለን ዛትን፡፡

ያን ተራራ መውጣት ተጀመረ ወይኔ እግዚአብሔር ሆይ አያልቅም እንዴ 😔 ላለቅስ ምን ቀረኘ በቃ አለ አደል በተስፋ መጓዝ እደርሳለሁ ብለህ ግን አትደርስም ውሃ ጥሙ ፀሀዩ ድካሙ ውውውውው በቃ በጣም ሚከብድ ቦታ ሰው እንዴት ባልጠፋ ቦታ እዚ ቦታ ላይ ወቶ ቤተክርስቲያን ይሰራሌ😭😭😭😢ብቻ ብዙ ነገሮችን አልኩ.......

ግን አይደረስ የቸ ተደረሰ......ስትደርስ ትገረማለህ ሁሉን አይተህ ድካምህ ይጠፋል ያን ሁሉ ደረቅ መንገድ አሳልፈህ ምን የመሰለ የፀበል ባህር ከላይ ሲጠብቅ በፈጣሪ ስራ ትገረማለህ.....😍😃🙏🙏

አይመሽ የለ መሸ ምሽቱ ግን ንጋትን ፀሀይን የሚያስናፍቅ ለሊት መቼ ነው ሚነጋው ኧረ ሰዎች ሰአት እዚ ቦታ እንደቆመ ነው እንዴ ሚቀረው ውውውውው ንፋሶቹስ ለነገ እዚህ ቦታ ተሰብስበው፡ነው እንዴ ሚበተኑ ወይኔኔኔኔኔ ብርድድድድ ድንግል ሆይ በህይወቴ እንደዛ ቀን በርዶኘ አያውቅም አይበርደኘምም፡፡

እንዲሁ ከጨለማው ጋር እንደተፋጠጥን ነጋ....ሩጫ ወደ ፀሀይ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

ባይሞቀንም እንደምንም ተሟሟቅን

ፀበሉ ቦታ ለመቅዳት ገብቼ ወይኔ ቅዝቃዜዜዜ🤦‍♂በቃላት መግለፅ አልችልም....

ግን በንጋት በውቧ ፀሀይ ታግዘን ሁሉን ጎበኘን ሁሉም ያስገርማል አባቶቻችን እጃቸው ይባረክ🙏😍🙏

ግዙፍን ደን ጠብቀው አቆይተው ይህን የመሰለ ስነምህዳር ስለሰጡን ምስጋና ያንስባቸዋል፡፡
ወርቃማዋ ፀሀይ በረጃጅም ዛፎች መሀል እየተሹለኮለከች ስታልፍ ያለው ድባብ ወደ ገነት የሚደረግ ጉዞ ይመስላል........

ወደቤት ስንመለስ የተለመደው የከሰዓት ፀሀይ ተቀብሎ ተጫውቶብን ለቀቀን....

የናኩት የተራራ እግሬን ስትራፖ በስትራፖ አድርጎ አስታውሳለሁ የትምህርትቤታችንን ደረጃ መወጣት አቅቶኘ እንደህፃን እየቆጠርኩ ስወጣ.....😂😂😂👊 ሲሳቅብኘ😂😂


2005------2013 አንድ ጊዜ ብቻ ነው ወደዚህ ቅዱስ ስፍራ ያልመጣሁት....

ክቡራን እና ክቡራት ይህ ድንቅ ቦታ
#ዝቋላ_አቦ ነው፡፡

ያላያችሁት ሰዎች ግን እዚ ቦታ ሔዳችሁ የአባታችንን በረከት ብትካፈሉ ብዬ እመክራለሁ አትፀፀቱበትም፡፡

በጉዞ መሀል ያነሳኀቸውን ፎቶዎች ስመለስ ጠብቁኘ፡፡

እንኳን አደረሳችሁ
አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ
ለሀገራችን ሰላም ፍቅር አንድነትን ያድሉልን
😍🙏😍
@jahABP ነኘ እንደምንገናኘ ተስፋ አደርጋለሁ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
ከአድካሚው ከአሳዛኙ ጉዞ በኀላ በሰላም ወደ ቤታችን ገብተናል.....

የሆነው ሁሉ ሆኖ
የድንግል ልጅ ተመስገንልን🙏

አቤቱ የሆነብንን አስብ.....ፍርድ ያንተ ነውና

ከረፍት መልስ እንገናኛለን......😔😔😞😔😓😴😴

ተመስገን........🙏🙏🙏🙏
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ይህም ለታሪክ ይቀመጥ

ሁሉም ሰው ይህ ይመጣል ብሎ አላሰበም፡፡
በፀሎት ጀምሮ በጅማሬ እየታጀበ ነበር ጉዞ የተጀመረው......ናዝሬት ላይ ለቁርስ ተወረደ....ሁሉም ያገኘውን ቀማምሶ ለድጋሚ ጉዞ ተነሳ ትንሽ እልፍ እንዳልን መኪኖች መቆም ጀመሩ ምን ተፈጠረ ብለን ወረድን መሔድ
አትችሉም ማለፍ አትችሉም......አሉን ፖሊሶቹ

ለምን?? የኛ የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር
አንዱ ፖሊስም በተንተፋተፈ አማርኛ

ኢኛ ኢሬቻን አዲስኤቤባ አታኬቢሩም ቴቢለን ኢነሱ ሊያኬብሩ አይዲም ቢለዋል

ጥያቄውን ቀጠለ ያሁሉ ወጣት እነማ....
የሀገሬው ሰው...ቄሮው ማለት ነው፡፡

አዎ......የዛኔ ሁሉም ማጉረምረም ጀመረ የተወሰኑ መምህራን ሰብሰብ እንበልና ወደላይ እናመልክት እኛ ምንሞትለት ሃይማኖት እንጂ የምንገድልበት ሃይማኖት የለንም በማለት ተናገሩ

የመጣውን ሰው ሲያዩት ከነበሩት ፖሊሶች ጋር በብዛት በሺህ እጥፍ ይበልጣል ኡነት ለመናገር ፖሊስቹ ፈሩ ልዩ ሀይል ብለውም ተደዋወሉ፡፡

ወጣቱም ተሰበሰበ እኛ ለሀይማኖታችን ስንል እንሞታለን እኛ አንገታችንን አሳልፈን እንሰጣለን እንጂ ይሔ ሁሉ ህዝብ ተመልሰን ሒዱ አንልም ሁላችንም እንሔዳለን.....ከገደሉንም ይግደሉን እዚ ድረስ መተን አንመለስም ይህንን ለሁሉም እንናገር........የፈጀውን ሰዓት ይፍጅ እንጓዛለን እንሔዳለን አለ....በዛም ሁሉም ተስማማ፡፡

እናቶችም 😍😱የጉዞው ጀማሪ ሆኖ አንመለስም የመጣው ይምጣ አሉ........ሁሉም ተበራታ አባቶችም ጥንካሬያችን ሆኑ በሉ ልጆቼ ጉልበት የእግዚአብሔር ነው እንጓዛለን አሉ.....😍💪
ሴቶች ህፃናት ሁሉም ተበራቱ፡፡

እኔም አቤቱ የሆነብንን አስብ አልኩ፡፡(ሰቆ.ኤር 5-1)

ጉዞውንም ጀመርን ጭው ያለ መጠለያ የሌለው በረሃ ነው ፀሃዩ በረታብን እናቶች ላብ ጠምቋቸው ሳይ አዘንኩ አባቶቻችን እነሱ መራመድ አቅቷቸው ሌሎችን ሲያበረቱ ሳይ እንባዬ መጣ የታዘሉ ህፃናት ፀሀዩ ሲቀጠቅጣቸው ሳይ አዘንኩ ጡት እንኳን እንዳይጠቡ በዛ ፀሀይ እንዴት ተደርጎ😢😢እህቶቻቸን መጓዝ አቅቷቸው ደክመው መጓዝ አቃታቸው ሳይ የት ነው ያለነው በቃ መንግስት የለም ለቅድስ ቤተክርስቲያን ምላሿ ይሔ ነው😭😭አልኩ፡፡

እኔም በጣም ደከመኘ ፎቶ እንኳን ማንሳት አቃተኘ ደከመኘ ቦርሳዬን እራሱ መያዝ አቃተኘ ምን አለ ካሜራ ባልይዝ ምግቡስ ባይያዝ አልኩ አብረውኘ ያሉ ሁሉም ደክሟል..............

አምስት ሰዓት መንገድ ነው የምንጓዘው ተራራውን እናየዋለን እንጂ........አንደርስበት አልን....አላልቅ አለ......ዝም ብሎ መጓዝ ብቻ፡፡

ውስጥ መጀመረመያ የገቡት አንድ ሁለት መኪኖች በራሳቸው ፈርደው የደከሙ እናቶችን አባቶች ለመውሰድ መጡ....ስሰማ ለስለት የመጡ አራስ እናቶችም በእግር እንደተጓዙ ሰማው በዛ ጭው ባለ ፀሀይ😭😔፡፡

የታሰበልን ሌላ ቢሆንም ከድንግል ልጅ ጋር ሆነን
በአባታችን ምልጃ እና በረከት ቦታውን ለመርገጥ በቅተናል፡፡ አይደረስ የለ ደርሰናል......የደረስነው ተራራው ጋር ነው ገና ተራራውን ለመውጣት የበረታ 3:00 ይፈጅበታል፡፡

አስቡት የአምስት ሰዓት መንገድ በእግሩ መቶ ድጋሚ ቀጥ ያለ ተራራ የሶስት ሰዓት ይጠብቀዋል ይህ ልብን ይሰብራል በጣም ልብን ይሰብራል
የሰውን የገረጣ የደከመ ፊት ማየት ሌላ ህመም ነበር፡፡
በምሽት ተራራውን ተጉዘናል ከእንቅፋቱ መውደቅ መነሳቱ እንዳለ ሆኖ ወደተራራው ጫፍ ወተናል......ወጣቱም እንዲህ እያለ ዘመረ

አንመካም በጉልበታችን እግዚአብሔር ነው የኛ ሀይላችን🙏💪💪💪አለ......

ተመስገንም አልን
ተስፋ ግን ሁሉን እንዲቻል ያደርጋል ትላንት አልፈን ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡

በሌላው እይታዬ እመለሳለሁ ማለቴ በመንፈሳዊ እይታ ተጠቀምን ወይስ ተጎዳን??


ይህ የሆነው 04/02/2013 ነው፡፡

በአብይ አህመድ የስልጣን ዘመን ነው፡፡
ይህም ለታሪክ ይቀመጥ እላለሁ

ፎቶ በቀጣይ እለቃለሁ ከድካሙ አንፃር ያሰብኩትን ፎቶ ባላነሳም፡፡😊🙏

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

የ5ሰዓት መንገድ እንዲህ በጀርባ ታዝሎ በዛ ፀሀይ....በእውነት በጣም ከባድ ነው፡፡

አቤቱ የሆነብንን አስብ

የሆነው ሆኖ ግን 🙏ተመስገንልን🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

በኡነት ያሳዝናል እናቶች እንዲህ እንዲሆኑ ሲፈረድባቸው ማየት በጣም ያማልልልል😢😢😢

አቤቱ የሆነብንን አስብ

የሆነው ሆኖ ግን 🙏ተመስገንልን🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

በኡነት ያሳዝናል እናቶች እንዲህ እንዲሆኑ ሲፈረድባቸው ማየት በጣም ያማልልልል😢😢😢

አቤቱ የሆነብንን አስብ

የሆነው ሆኖ ግን 🙏ተመስገንልን🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

ምስሉን ተጭነው ይመልከቱ

አቤቱ የሆነብንን አስብ

የሆነው ሆኖ ግን 🙏ተመስገንልን🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

እሷ:- አባ አምጡ ላግዞት

አባ:- አይሆንም ልጄ በፍፁም

ትህትና🙏 ፍቅር😍 አክብሮት🙏

ዝቋላ አቦ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

መልካም ዕለተ ሰንበት ተመኘሁ

የጥቅምት አበባ
ፍክትትትትትትት
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ከትላንት ወዲያ እና ዛሬ በጣም የተበሳጨሁበት ቀን ነው 🤦‍♂🤦‍♂፡፡

ደሞ በሰው አይደለም በራሴ ነው😁😁

ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ.........
ከትላንት ወዲያ በጉዞ ደክሜ አልነበር ቀኑን ሙሉ ቤት ነበር የዋልኩት.....እና ነገ ምጋብዛችሁን ሰኞን ምንጀምርበት ፅድት ያለ ቲቪ ላይ ሙዚቃን ሰማሁት ሰማሁት ብቻ አይደለም መስማትማ ሌላም ጊዜ ሰምቼዋለሁ አላዳመጥኩትም እንጂ ዳውንሎድ አድርገን በደንብ አዳመጥኩት አዳመጥኩት ብቻ ሳይሆን አዳመጥነው እቤት ሰብሰብ ብለን ነበር፡፡

እማ እራሱ እየሰማችው ነበር ቪዲዮውንም እያየች እየተመሰጠች ነበር፡፡ እውነት ነው ትላለች

እንዴት እስካሁን አላደመጥኩትም ቀሽም👊👋 ነህ አብያ አልኩት ለራሴ ሁላችንም ራሳችንን የምፈትሽበትን መሰማት አለበት በቃ እንደዚህ አይነት ዘፈኖች በብዛት መዘፈን አለባቸው ለማህበረሰባችን እንዲህ አይነት ህይወት ቀያሪ ሀሳቦችን እያነሳ ያለበትን ቆም ብሎ አስቦ እራሱን እንዲፈትሽ የሚያደርጉ....

ኤልያስ መልካን በዚህ ተወዳዳሪ የለውም😍🙏

ግን የዚህ ሙዚቃ ግጥሙም ዜማውም የኤላ አይደለም የሌላ ታዋቂ ዘፋኘ ነው.......በጣም ተመችቶኛል ግጥሙ ፣ ዜማው ፣ ቀረፃው ፣ የቀረፃው ቦታም ፣ ቅንብሩም....አንደኛ ነው፡፡👏👏👍

ዘፈኑን ካላችሁኘ ነገ ጠዋት ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

በእርግጠኘነት ትወዱታላችሁ😍

ዛሬ የተበሳጨሁበትን ደግሞ ነገ፡፡

@jahABP ነኘ መልካም አዳር😊🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
Audio
ለሚለዋወጥ ማንነት
መሰረትህን አትሳት
.
.
ሰው ሙሉ አይሆን ያለ ህሊና👌👌🙏
.
ስጋ በምኞት ይነዳል
ክፉ ምኞት ሀጢያት ይወልዳል
.
.አንዷን መስመር መኖር ካቃተህ ሰስተህ
.
እጅህ መስጠትን ካሳተው
ሰብሰብ አርገውና የሌላን መንካት ተው

የጡር ንዋይ ምን ቢካበት
እድሜ አትገዛ ሞት አታስቀርበት👏👏👏

ወንድሙ ጂራ #ከራስ_ጋር
ግጥም እና ዜማ፡- ወንድሙ ጂራ😍🙏😍

😊መልካም ሰኞ🙏
AB PHOTOGRAPHY

ዝቋላ መንገድ.......😔
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
የሱ ልደት በቀላሉ አይደለም ሚከበርለት አላልኳችሁም😃

እንዲህ በሚገርም ሁኔታ አልፉል
😍😍😍 ወንድሜ አክብረኸኘ መተህ ሚገርም ጊዜን ስላሳለፍን በጣም ደስ ብሎኛል፡፡
ስጦታውን እንደምቶደው ገምቼ ነበር፡፡
ያወራንባቸውን ነገሮች ወደተግባር ለመለወጥ እግዚአብሔር ይርዳን😊🙏😍

እቤት ገብቶ ስጦታውን ካየ በኀላ

እንዲህ ብሎኛል:-

"ወንድሜ እንዲህ አክብረህ በጣም የምወደውን እና የተደነኩበት የሚኒልክን ምስል ባንተው እጅ የተነሳ ፎቶ እንዲህ አተልቀህ ሁሌ እንድመለከተው ስላደረክ ፤ እንዲሁም ሀዋሳ ሄደህ ሲታይ መንፈስን የሚያድስን በባህር መሀል የምትጠልቅን ፀሀይ ያነሳኸውን ፎቶ ሳየው መንፈሴ እንዲታደስ እሱንም በትልቁ አሳጥበህ ፤ እኔን አክብረህ ፤ ለልደቴ መልካም ምኞት ተመኝተህ ፤ እነዚህን ድንቅ ፎቶዎችህን አሳጥበህ ስለሰጠኸኝ ፈጣሪ ያክብርልኝ እውነት በጣም ደስ ብሎኛል ከዚህ በላይ ባወራ ደስ ይለኝ ነበር ክበርልኝ ወንድሜ። ከዚህም በላይ ፈጣሪ ጥበቡን ጨማምሮ ሰቶህ ከማይወርድ ከከፍታ ላይ ይስቀልህ 😍😍🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏"

እንዴት ደስ ሚል ምኞት ነው እግዜር ያክብርልኘ ወንድሜ😍🙏🙏
AB PHOTOGRAPHY

ዝቋላ ባህሩ ፀበል
አባቶቻችን ይህን የመሰለ ስነምህዳር እስካሁን ጠብቀው ስላቆዩልን ክብር ይገባቸዋል፡፡
👏👏👏👍👌
መንፈስን ነው ሚያድሰው
ታዲያ ይቺ ቤተክርስቲያን ውለታዋ እንዴት ነው መመለስ ያለበት ይሆን??
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

ይህን ሰብል ከአንበጣ አይን ይጠብቀው
🙏😍🙏
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
እሁድ ዕለት ከተበሳጨሁበት ነገሮች አንዱ ይህን መፅሐፍ እንዴት እስካሁን አላነበብኩትም በሚል ነበር.......ለትሹ ወንድሜ ለልደቱ የሰጠሁት መጽሐፍ ነበር፡፡
የአለማየሁ ገላጋይ😍 የአዳምረታ አፃፃፍ አዳቅሎ ከተፃፈው መፅሐፍ የተወሰነች እንቆጥር........

ወጣቱን ፀሀፊ ቱቱቱቱ እደግልን ሀሳብህን ሀሳቦቻችንን በአስገራሚ እና በተመጠኑ ቃላት አስፍረህ ይህን መፅሐፍ ጀባ ስላልከን ከወገባችን ጎንበስ ብለን አመስግነናል ቀጣዩ ስራህን ከዚህ የተሻለና ሰፋ እንደሚል ባለሙሉ ተስፋ ነኘ፡፡

ቀጣዩን ስራህን በጉጉት እንጠብቃለን ማለት እፈልጋለሁ፡፡

መፅሐፉን ልጨርስ ትንሽ ገፆች ይቀሩኛል ቢሆንም እነዚህን ላካፍላችሁ ወደድኩ ስጨርሰው ደሞ ስለመፅሐፉ የተወሰነ ነገር ለማለት እወዳለሁ...........

በተለይ እሷ ይሔን መፅሐፍ እንድታነብልኘ እፈልጋለሁ ማነች?? እሷ ግን🤔🤔


ጠብቁኘ........🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂