AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
ከትላንት ወዲያ እና ዛሬ በጣም የተበሳጨሁበት ቀን ነው 🤦♂🤦♂፡፡
ደሞ በሰው አይደለም በራሴ ነው😁😁
ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ.........
ከትላንት ወዲያ በጉዞ ደክሜ አልነበር ቀኑን ሙሉ ቤት ነበር የዋልኩት.....እና ነገ ምጋብዛችሁን ሰኞን ምንጀምርበት ፅድት ያለ ቲቪ ላይ ሙዚቃን ሰማሁት ሰማሁት ብቻ አይደለም መስማትማ ሌላም ጊዜ ሰምቼዋለሁ አላዳመጥኩትም እንጂ ዳውንሎድ አድርገን በደንብ አዳመጥኩት አዳመጥኩት ብቻ ሳይሆን አዳመጥነው እቤት ሰብሰብ ብለን ነበር፡፡
እማ እራሱ እየሰማችው ነበር ቪዲዮውንም እያየች እየተመሰጠች ነበር፡፡ እውነት ነው ትላለች
እንዴት እስካሁን አላደመጥኩትም ቀሽም👊👋 ነህ አብያ አልኩት ለራሴ ሁላችንም ራሳችንን የምፈትሽበትን መሰማት አለበት በቃ እንደዚህ አይነት ዘፈኖች በብዛት መዘፈን አለባቸው ለማህበረሰባችን እንዲህ አይነት ህይወት ቀያሪ ሀሳቦችን እያነሳ ያለበትን ቆም ብሎ አስቦ እራሱን እንዲፈትሽ የሚያደርጉ....
ኤልያስ መልካን በዚህ ተወዳዳሪ የለውም😍🙏
ግን የዚህ ሙዚቃ ግጥሙም ዜማውም የኤላ አይደለም የሌላ ታዋቂ ዘፋኘ ነው.......በጣም ተመችቶኛል ግጥሙ ፣ ዜማው ፣ ቀረፃው ፣ የቀረፃው ቦታም ፣ ቅንብሩም....አንደኛ ነው፡፡👏👏👍
ዘፈኑን ካላችሁኘ ነገ ጠዋት ጠብቁኘ🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂
በእርግጠኘነት ትወዱታላችሁ😍
ዛሬ የተበሳጨሁበትን ደግሞ ነገ፡፡
@jahABP ነኘ መልካም አዳር😊🙏
@ABPGD @ABPGD @ABPGD

የሱ ልደት በቀላሉ አይደለም ሚከበርለት አላልኳችሁም😃
እንዲህ በሚገርም ሁኔታ አልፉል
😍😍😍 ወንድሜ አክብረኸኘ መተህ ሚገርም ጊዜን ስላሳለፍን በጣም ደስ ብሎኛል፡፡
ስጦታውን እንደምቶደው ገምቼ ነበር፡፡
ያወራንባቸውን ነገሮች ወደተግባር ለመለወጥ እግዚአብሔር ይርዳን😊🙏😍
እቤት ገብቶ ስጦታውን ካየ በኀላ
እንዲህ ብሎኛል:-
"ወንድሜ እንዲህ አክብረህ በጣም የምወደውን እና የተደነኩበት የሚኒልክን ምስል ባንተው እጅ የተነሳ ፎቶ እንዲህ አተልቀህ ሁሌ እንድመለከተው ስላደረክ ፤ እንዲሁም ሀዋሳ ሄደህ ሲታይ መንፈስን የሚያድስን በባህር መሀል የምትጠልቅን ፀሀይ ያነሳኸውን ፎቶ ሳየው መንፈሴ እንዲታደስ እሱንም በትልቁ አሳጥበህ ፤ እኔን አክብረህ ፤ ለልደቴ መልካም ምኞት ተመኝተህ ፤ እነዚህን ድንቅ ፎቶዎችህን አሳጥበህ ስለሰጠኸኝ ፈጣሪ ያክብርልኝ እውነት በጣም ደስ ብሎኛል ከዚህ በላይ ባወራ ደስ ይለኝ ነበር ክበርልኝ ወንድሜ። ከዚህም በላይ ፈጣሪ ጥበቡን ጨማምሮ ሰቶህ ከማይወርድ ከከፍታ ላይ ይስቀልህ 😍😍🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏"
እንዴት ደስ ሚል ምኞት ነው እግዜር ያክብርልኘ ወንድሜ😍🙏🙏

እሁድ ዕለት ከተበሳጨሁበት ነገሮች አንዱ ይህን መፅሐፍ እንዴት እስካሁን አላነበብኩትም በሚል ነበር.......ለትሹ ወንድሜ ለልደቱ የሰጠሁት መጽሐፍ ነበር፡፡
የአለማየሁ ገላጋይ😍 የአዳምረታ አፃፃፍ አዳቅሎ ከተፃፈው መፅሐፍ የተወሰነች እንቆጥር........
ወጣቱን ፀሀፊ ቱቱቱቱ እደግልን ሀሳብህን ሀሳቦቻችንን በአስገራሚ እና በተመጠኑ ቃላት አስፍረህ ይህን መፅሐፍ ጀባ ስላልከን ከወገባችን ጎንበስ ብለን አመስግነናል ቀጣዩ ስራህን ከዚህ የተሻለና ሰፋ እንደሚል ባለሙሉ ተስፋ ነኘ፡፡
ቀጣዩን ስራህን በጉጉት እንጠብቃለን ማለት እፈልጋለሁ፡፡
መፅሐፉን ልጨርስ ትንሽ ገፆች ይቀሩኛል ቢሆንም እነዚህን ላካፍላችሁ ወደድኩ ስጨርሰው ደሞ ስለመፅሐፉ የተወሰነ ነገር ለማለት እወዳለሁ...........
በተለይ እሷ ይሔን መፅሐፍ እንድታነብልኘ እፈልጋለሁ ማነች?? እሷ ግን🤔🤔
ጠብቁኘ........🏃♂🏃♂🏃♂

ዕድሜ ሁለቴ እንደማይሻገረው የወንዝ ውሃ ይወርዳል፡፡ ዘመኑ ከሸማኔ መወርወሪያ ይልቅ ይፈጥናል፡፡ ቀኖቹ ግን የተደገሙ ያህል ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ሰዎች ልጅ ወልደው ሊጥሉ ፣ ማደጎ ሊያሳድጉ ፣ ቀሚስ ሊገልቡ ፣ የታረዘ ሊያለብሱ ፣ ሕሊና ሊያደሙ ፣ ቁስልን ሊያጠግጉ ፣ የቆመውን ሊዘረጥጡ ፣ የወደቀውን ሊያነሱ ፣
ሊመዘብሩ ፣ ሊመፀውቱ ፣ እምነት ሊያጎድሉ ፣ ባህል ሊጠብቁ ፣ ብሌን ሊያጠፉ ፣ ዓይን ሊለግሱ ፣ ሰው ፊት ላይ አንቅረው ሊተፉ ፣ የተበዳይን እንባ ዝቅ ብለው ሊያብሱ ፣ ሰርተው ሊያገኙ ፣ ዘርፈው ሊከብሩ ፣ ወጥመድ ሊያበጃጁ ፣ ጥርጊያውን ሊያቀናኑ ፣ አሳልፈው ሊሰጡ ፣ ሸሽገው ሊያስመልጡ ፣ ሊያገላግሉ ፣ ሊያቀያይሙ ፣ ከወገብ በላይ ታቦት ፣ ከወገብ በታች ጣዖት ሊሆኑ.......
ከትላንት የቀጠለ ሌላ ዕለት ተጨማሪ ንጋት፡፡ የሸኘነው ቀን ካለንበት ዛሬ በምን ይለያል??
ወግ አይቀርምና ሲነጋ ግን አዲስ ቀን ይባላል፡፡
መሽቶ ሲነጋ የአገሩ ገበሬዎች እጆቻቸውን *አንከርፍፈው ወደሰማይ አንጋጠው ፈጣሪን ያመሰግናሉ፡፡ ካህናት በዜማ የታሸ አኮቴት በቤተመቅደስ ያቀርባሉ፡፡ መስጂዶች አዛን ያሰማሉ፡፡ አማኒያን ውዱህ ያደርጋሉ፡፡ ሶሏት ይሰግዳሉ፡፡ ቁርዓን ይቀራሉ፡፡
መሽቶ ባይነጋ ምን ይፈጠራል??🤔 እንደነጋ ቢቀር? *#የእኛ ሕይወትና ዕድሜ በአንድ ወጥ ዕለት ቢያልፍ? ጊዜውን እንዴት ይከፋፍለዋል?ከትላንት ወዲያ ፣ ትላንት ፣ ነገ የሚባሉ የጊዜ አጥቆች ባይኖሩት?
#የሕይወት_ታሪኩ_በአንድ_ቀን_ቢጠናቀቅ?🤔
ሁሉም ዛሬ ቢሆን ፣ ፅንሰቱ ፣ ውልደቱ ፣ ህፃንነቱ ፣ ጉርምስናው ፣ ወጣትነቱ እርጅናው እና ሞቱ ዛሬ ቢሆኑ ምን ይፈጠራል?🤔
ልቡና ትከሻው እነዚህን ሁሉ አካላዊና ስሜታዊ መለዋወጦች በአንዴ ማስተናገድ ይችላሉ?
መሽቶ መንጋቱ ጥቅም የመቻል ትከሻን ማስፉቱ እንደሆነስ? እንጂማ አዲስ ፀሀይ አወጣጥ ፣ አዲስ ምስራቅ የታለ? ፣ ...እና ይሔ ዑደት የጥንት ነው፡፡ ፀሀይ እንዲህ ስትጠልቅ ስንት ትውልድ አልፉል? ስትወጣስ ስንት ትውልድ መጥቷል? ሁሉ ነገር ዘመን ከተቆጠረለት ጥንታዊ ነው፡፡
ጊዜው የበረረው ያህል የትዝታ ባህር መዝገብም ይደልባል፡፡
*#እኛነታችንን አማሃኘ ስፍራ ላይ ብናቆመው ትላንቱን ፣ ዛሬውን ፣ የነገውን የምናገኛቸው ቀጥ ብሎ በሚጓዝ በአንድ የጊዜ መሥመር ላይ ነው፡፡
እኛ ያለፈውን እንጂ የሚመጣውን አናውቅም፡፡
እኛ ግን እናውቃለን፡፡ 'ያ' እርሱን ሰው ሲያደርገው እኛን ደግሞ ፈጣሪ ያደርገናል፡፡
ያለፈውን በማወቃችን ውስጥ ደግም በክፉውም ትላንትን እያነሳን እንድንኖር ተረግመናል፡፡
ታክተነው ብንረሳም በግድ እንድናስታውሰው እንደረጋለን፡፡ ፈልገን አይደለም፡፡ የትዝታ ድንገተኛነት ልክ እንደ ትንታ በመሆኑ ነው፡፡
ማንነታችን እዚህ ላይ የደረሰው ትላንትን አንድ ብሎ ነው፡፡
እናም ምን ያህል ብንሞክር ትላንትን ፈፅሞ መካድ አይችልም፡፡ እዚህ ስንደርስ - እዚህ ያደረሰን ፣ እንዲህ ስንሰማው - እንዲህ እንዲሰማን - ያደረገው ፣ ሲንኮታኮት - ያሽቀነጠረን ፣ ሳያምን ሲቀር - የከዳው ፣ ሲፈራው - ያስደነግጠናል ፣ ሲያለቅስ - የመታው ፣ ሲስቅ - የኮረከረው አለ፡፡
ውጤት ካለ መንስኤ አለ፡፡
ትላንት የሌለውን ዛሬ ያየ ማን ነው?
ትዝታሽን ፡ ለእኔ
ትዝታዬ ፡ ለአንቺ
እሱባለው አበራ ንጉሴ ሐምሌ 2012 ዓ.ም
ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንደቀነጨብኩት
በመፅሐፉ የአንድ ሰው ታሪክን ነው ለንባብ እንዲመች አድርጌ ወደ #እኛ አድርጌ ያቀረብኩ
በምልክትም *# አድርጌበታለሁ፡፡
ይህን አጃኢብ ያሰኘኝን መፅሐፍ ብታነቡት በብዙ የትዝታ ፈረስ ትጓዛላቹ የሆነ ጊዜ ላይ የምታስቡት የነበረውን ሀሳብ ሸጋ በሆነ ቃላት ተከሽኖ ታገኙበታላችሁ በወጣቱ የብዕር አጣጣል ትደነቃላቹ ትወዱታላችሁ ቀጣይ ስቀነጭብም ታዩታላችሁ፡፡
ትላንት ላይ ስለነበርን እኮ ነው ዛሬን ያየነው እና ደግሞ ከትላንት ያፍነው ለዛሬ ብቻ አይደለም ነገም ለማየት ነው፡፡ @jahABP ነኘ😊
😍መልካም ምሽት🙏

ሕይወት እንደፈጠራ ድርሳን ወጥ ምስልን አትሰጥም፡፡
በሠመረ ምክንያትና በተዋጣለት ድርጊት አትሰናሰልም፡፡ በትርጉም መፋለስ የተላለፈና የተጣጡ ሰዎች በእውነተኛው ዓለም በስተመጨረሻም አይገናኙም፡፡ ወደ አንድ ስመር አይመጡም፡፡ አይገናዘቡም፡፡
አስተያየት የሚያደርግላቸው ሁሉን አወቅ ደራሲ አያገኙም፡፡ ማንንም ለማስደሰትና ለማሳዘን አይደለም፡፡
#ሕይወት_ገለልተኛ_መድረክ_ናት፡፡
የባለወንጭፉን #ዳዊትን ገድል ለማሳመር ብላ የባለ ሰይፉ #ጎልያድን ገድል አታበላሽም፡፡
በተዋናይዎቹ ኢምፕሮቫይዜሽን ይወሰናል፡፡
እስኪ የህይወት መድረክ ላይወጣ ብለህ ስንት ዳዊቶች በአንድ የጎልያድ ሰይፍ እንደተገደሉ ቁጠር?
ሰዎች በሚያነቡት ምንባብ ፣ በሚያዩት ቅርፅ ፣ በሚያደምጡት ድምፀት ውስጥ የማያቋርጥ የትርጉም ኅሰሳን ያደርጋሉ፡፡ ምክንያታዊነት ይጠይቃሉ፡፡
ሕይወት ላይ ግን 'ለምን እንዲህ ሆነ? ለምንስ እንዲህ አልሆነም?' ብለን መጠየቅ አንችልም፡፡
ከአልተመለሱልን ጥያቄዎች ጋር እንጓዛለን፡፡
ምክንያቱም ምድር ላይ የያዝነው ሕይወት እንጂ ተውኔት አይደለም፡፡
የተሰጠን ቃለ ተውኔት የለም፡፡ ወደዚህ ምድር ስንመጣ የሕይወትን ትርጉም የያዘ ክታብ በአንገታችን አስረን አልተወለድንም፡፡
ምስኪኖች ነን፡፡
የገዛ ታሪካችን ፍሰቱ የቱ ጋር እንደሚያበቃ አናውቅም፡፡በዘፈቀደ ከምንኖረው ሕይወት ፣ እንደ ቅሪላም ከምንገፋው ኑረታችን ያማረ ፣ የተመጠነ ፣ ስሜንትን የሚሰጥ ምሉዕ ተረክ አንጠብቅም፡፡ ሕይወት 'ከየት መጣን? ወደ የትስ እንሔዳለን?'
ለሚልብሉይ ጥያቄዎች የተሽሞነሞነ ትርጉም የመስጠት ግዴታ የለባትም፡፡ ምን አልባባት አንዲት ብርቱካናማ ሚኒስከርት የለበሰች ጠይም ፍልቅልቅ ሕፃን በውኃ ውስጥ በጥብጣ በትንፋሷ 'እፍፍ' ባለችው የዐረፋ ኳስ ውስጥ ድንገት የተከሰተን ፍጡራኖች ነን፡፡
የዐረፋ ኳሱ አየር ላይ ሰፍሮ ሲፈነዳ የዘላለማዊነታችንም ተበትኖ ይጠፋል፡፡ እኮ ማን ያውቃል ህላዌያችን እንዲህ ባሉ ትርጉም በማይሰጡ ቅጽበታት እንደ ተከበበ?
ስለህይወት መልክ ወርደን ስንጠይቅ ....ስንት ሻሂ ፣ ስንት ቡና ጠጣን? ስንት ሲጋራ አጢሰን ስንት ቢራ ጨለጥን? ስንቴ በሰዓት ደርሰን ስንቴ አረፈድን? ስንት ሳቆች ስቀን ስንት ፈገግታ ፈገግን? ስንቴ ተደብረን ስንቴ ሀዘን ገባን? ስንት ጨለማ አይተን ስንት እንባ አነባን? ስንት ሰው አወቅን? ስንት ሰው ጠበስን? ስንት ሰው ተኳርፈን ስንት ሰው ታረቅን? ስንት ሰው ጨብጠን ስንት ሰው አቀፍን? ስንት ሰው ሸኘተን ስንት ሰውስ ገፋን? ስንት ሰው ወደድን ስንት ሰውስ ጠላን? ስንት ሰው አፍቅረን ስንት ሰውስ ተኛን? ስንቱን ገላ ዳብሰን ስንቱን ቀዳዳ አየን?
ስንት ሰው ፈውሰን ስንት ሰው ገደልን? ስንት ሰዎች ሰብረን ስንት ሰው ጠገንን? ስንት ሰው አስቀን ስንቱን አስለቀስን? ...ብለን ነው፡፡
ከዚህ ሌላ የምናወራርደው ሒሳቅ የለብንም የሕይወት መልክ ያለው መዘርዝሩ ውስጥ ነው፡፡
አጥብቀን አስረነው የተፈታብን የጫማ ክር የለም ፈቅደን ሳነፈታው እንዴት በራሱ ጊዜ ደጋግሞ ተፈታ? ቆም ብለን የአፈታቱን ሂደት ማወቅ አንፈልግም?
ሕይወት የጫማ ክራችን በተፈታበት መንገድ ቢሆንስ ለእኛም የምትሰራው?
የመፅሐፍ ርዕስ፡- ትዝታሽን ፡ ለእኔ
ትዝታዬ ፡ ለአንቺ
እሱባለው አበራ ንጉሴ
ሐምሌ 2012 ዓ.ም
በአዲስ የአፃፃፍ ስልት ከመምጣቱ አንፃር
አንዴ ሳይሆን ተደግሞ የሚነበብ መፅሐፍ፡፡
አብሶ ለእንደኔ አይነቱ ሰነፍ አንባቢ፡፡
እንድታነቡት ስጋብዝ በደስታ ነው
ቆዩልኘ
@jahABP ነኘ መልካም ቀን

በነገራችን ለይ የባላገሩ ቲቪ የሙዚቃ ግብዣዎች በጣም ይመቹኛል......😍👏👏👏
በዚሁ ይቀጥል ባይ ነኘ...👌👌😘
በዚሁ ይቀጥል ባይ ነኘ...👌👌😘
AB PHOTOGRAPHY &GRAPHIC DESIGN
😔የሰማዕት ያለህ😭
እውነተኛ ጠፍቶ እንጂ ዛሬም ሰማዕት አለ፡፡
ሰማዕትነት ቆሞ አያውቅም፡፡ ሰማዕታትም በጣም ይቀንሱ ይሆናል እንጂ ጠፍተው አያውቁም፡፡ የነፃነት ዘመን የመሰለው ከጽድቅ ነፃ ለሆኑ ለመሰሉ ሰዎች ነው፡፡ በሁለት ወገን በእውቀትና በመንፈሳዊነት ለመከኑት ነው፡፡
ስለፀኑት ስታስብ ትፀናለህ፡፡
ስለሰማዕታት ስታነብ ብዙ እንደቀረህ ታውቃለህ
ስለጻድቃን ስታነብ የገንዘብን ፍቅር ትጠየፈዋለህ
በእያንዳንዱ ቀን ካልወሰንህ ክርስትናን መከተል አትችልም፡፡ በዋጋ የመጣው ሃይማኖት ያለዋጋ አይቀጥልም፡፡ ሃይማኖት ለኛ ከመሰከረች እኛም ለሃይማኖት እንመሰክራለን፡፡
#ያለ_እግዚአብሔር_ከመኖር_ከእግዚአብሔር_ጋር_መሞት_ይሻላል፡፡
የእምነት ጀግኖች #አምነው_የኖሩ ብቻ ሳይሆኑ #አምነው_የሞቱም ናቸው፡፡
#እምነት_ህያው_ነውና_ነበር የሚል ቃል_አይስማማውም፡፡
መንግስተ ሰማያትን ለማግኘት ዓለምን መናቅ ፣ የመንፈስ ቅዱስን መጽናናትን ለመውረስ ስለ ኃጢያት ንስሐ ይገባል፡፡
ዓለም የሚያከብር ዓለምን ስትንቅ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ሰው መሆንህ የሚታወቀው የተጣሉትን ስታስታርቅ ነው፡፡
እግዚአብሔርን ስትክድ ዓለሙ ያምንሃል ዓለሙን ስትክድ እግዚአብሔር ያምንሐል፡፡ አስመሳይነት ዳሩ ገነት ውስጡ እሳት ነው የእውነተኘነት ዳሩ እሳት ውስጡ ገነት ነው፡፡
#እግዚአብሔርን_የከሰርክበት_ማንኛውም_ድል_ሽንፈት_ነው፡፡
መትረፍ ማለት ከመኪና አደጋ ማምለጥ ማምለጥ ሳይሆን የነፍስህነ ቤዛ ማወቅና ማመን ነው፡፡ የዕድር መዝገብ አውቆህ የሕይወት መፅሐፍ ካላወቀህ ከሁቹ ይልቅ ሚስኪን ነህ፡፡
ለራስህ ክብር ካለህ በእምነትህ ፅና፡፡ በሃይማኖት ውስጥ የሚታመነው አንዱ እግዚአብሔር የዘላለሙ አዲስ ነውና ሃይማኖት አትታደስም፡፡
እናድሳለን እያሉ ከሚያቆሽሹ እናምናለን እያሉ የከበሩትን ከሚያዋርዱ ተጠንቀቅ፡፡
ሃይማኖት እራሱ ገንዘብ ነውና በሃይማኖት ገንዘብ አትመኘ፡፡ ስለሰው ሞተኻል ስለእግዚአብሔር ኑር፡፡ ሰዎችን ላለማስቀየም ጠጥተኻል እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ሥጋወደሙን ተቀበል፡፡
እውነቱ እውነት ስለሆነ እንጂ ስለሚያመጣው ውጤት አትከተለው፡፡
እግዚአብሔር ከዛሬው መከራ ያድናል ባያድንም እርሱ እግዚአብሔር ነው፡፡
እውነት በሌለበት ሰማዕትነት የለም፡፡
#እውነተኞች_እንጂ_እውነት_ግን_አትታሰርም፡፡
የምትወደውን ሰው በሰማይ ለማግኝ ከፈለክ ዛሬ ቃለ እግዚአብሔርን ንገረው፡፡
ዛሬ ለወንድምህ የምትነግረው ክርስቶስ በፊትህ ቢቆም የምትናገረውን መሆን አለበት፡፡
ክርስቶስ መንገድ ቢጠይቅህ እንዴት ብለህ ታመላክተዋለህ? መንገድ የጠፋውን ሰው እንዲህ አግዘው፡፡ ለክለሳ ተመልሰህ አትመጣምና ዛሬ በጎ ተግባርህን ፈፅም፡፡
የተዋረደ ሃሳብ ካላቸው ጋስ የተከበረ ሃሳብህን ይዘህ አትከራከር፡፡
ያለአጥር ያደገን ሰው ስነስርአት ማስያዝ አስቸጋሪ ነው፡፡
ሰዎች ሲረግሙህ እግዚአብሔር ይመርቅሃል፡፡
*#እግዚአብሔርን ጠልተህ ተወደህ ከነበረህ በረከት ፣ እግዚአብሔርን ይዘህ ተጠልተህ የምታገኘው በረከት ይበልጣል፡፡
ማንም ሳይመክርህ ሕይወትህ ከታረመ ፣ እግዚአብሔር መምህርህ ነበር *#ማለት ነው፡፡
የደስታ ቋጠሮ
ተፃፈ አዲስ አበባ
ሐምሌ 11 ቀን 2010 ዓ.ም
ዲ/ን አሸናፊ መኮንን
አምላካችን ሆይ እባክህ መከራው በቃችሁ በለን፡፡
ፍቅርን አንድነትን መተሳሰብን ስጠን ከእኔ ከማለት ወደ እኛ ማለትን አስተምረን፡፡
ኧረ ወዴት እየሔድን ነው፡፡
ኧረ ቆም ብለን እናስብ😭😢😭😭
@jahABP ነኘ መልካም አዳር😔😢🙏

አፍቃሪው መልካም ልደት
ስለሱ ሳወራ ሁሌም ትዝ ሚለኘ አንድ ዘፈን አለ
"ልሁን ሞኘ የምወደውን ካገኘሁ
ፍቅርን ያጣ ብልጥ እሰኪ ደስታው ምንድነው
ዝቅ ልበላ ከግምታቸው በብዙ
ምን ጥቅም አለው ከፍታ ፍቅር ካልያዙ"
እዮባ😍 ለኔ ዘፍኖልኛል ይለናል
ወዳጄ የሱን ያህል ትህትና እና ፍቅር እንዲኖረኘ ሁሌም ፈጣሪዬን እለምነዋለሁ፡፡
ለሚወደው ሰው የሚከፍለው መስዋዕትነት ሁሌም ሲያስደንቀኘ ይኖራል ምላሹን አይጠብቅም በቃ አለ አደል ዝም ብሎ መውደድ፡እየተጎዱ መውደድ እየተጎዱ ማፍቀር እየተጎዱ መልካም መሆን ነገ ጥሩ ቀን እንደሚመጣ ተስፋ ማድረግ፡፡
በዙሪያችን የከበበን ሁሉንም ነገር ታግሎ ማሸነፍን......
እንባዎቹ ቅንድቡ ጋር ናቸው ትንሽ ተከፍታችሁ ካያቹ ይዘረግፈዋል😭😭ወንድሜ😍😍
የእውነቴን ነው፡፡
የኔ ቁም ነገረኛ😘
ሁሉንም በእኩል አይን ምታይ ለሰው ብለህ የእራስህን ደስታ ወደጎን ምታደርግ ለሰው ብለህ ሁሌም ዝቅ እንዳልክ አምናለሁ ግን በፈጣሪ ዘንድ ከፍ ከፍ ያልክ እንደሆን ምክንያቱም ባለህ ደስተኛ ነህና ለኛ እንጂ ለኔ ማታቀው ወንድሜ
ስላንተ ብዙ ማለት እችላለሁ ግን ሰዎች ውሸት ይመስላቸዋል....
በተለይ ፍቅርህን ለማቆየት ያደረከው ምታደርጋቸው ነገሮች በሙሉ ለኔ ትምህርትቤቶቼ ናቸው ለምወደው ሰው ስል እኔ ምን አደረኩ ....ያንተ ገድሎች ያስገርሙኛል፡፡
ወደፊት አንተ እና ባልተቤትህ ከፈቀዳቹ እፅፈው ይሆናል ያኔ ሰዎች እንደኔ እንዲህ ይላሉ
ከአንተ አንፃር በዛብህስ ማነው ሮሚዮስ ቢሆን ይሉልኻል፡፡ አትጠራጠር
አብያ ጥሩ ነው አንተ ብቻ አታጥፋ ይሁን ለበጎ ነው ሚል ካንተ ውጪ ማን አለ.....ኧረ ስንቱ....
ድብድብ ግን ቀንሰናል አይደል😂😂😂ድሮ ነበር በአምስት ደቂቃ ውስጥ ፀብ ነበር፡፡
ምክንያት አይታጣም እንጣላለን እኔ ሀይለኛ ነኘ ይቅርታ ምትለው ግን አንተ ነህ ወይ አንተ🤦♂🤦♂
ብዙ አስተምረኸኛል፡፡
መልካምነት እና ፍቅር ፊት ቢኖረው አንተ ነህ፡፡
ሁሌም ደስታህ ብቻ ነው ማየት ምፈልገው፡፡
የእኔ እና ያንተ ሳቅ አንድ ላይ 😂😂😂 ሁሌ ታክሲ ውስጥ እንዳሸበረ መንገደኛ እንዳስደነገጠ ክፍል እንደበጠበጠ....
እኔ ከጎንህ ባልሆንም አንተ ከጎኔ ስለሆንክ አንተን መፈለግ አይጠበቅብኘም
ለሁሉም ነገር ቅድሚያ አድርገህ ሮጠህ ምትመጣው ካንተ የተሻልኩ ሳልሆን አክብረህ ሁሉን ነገር ምታማክረኘ ወንድሜ ....
ተምሳሌቱ ብሩክ ብርሃኑ እንኳንም ተወለድክልን ካንተ የምንማራቸው የተማርናቸው አያሌ የህይወት ተሞክሮዎች አሉ እንኳንም ተወለድክልን አቦ ኑርልን አቦ ለሷም ኑርላት፡፡
ሁሌም ሚቆጨኘ አንተ እንደምትወደኘ ልወድህ አለመቻሌ ነው፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቅህ
ድንግል ማርያም ሁሌም ከጎንህ ትሁንልህ
አምላከ ቅዱስ ዑራኤል ጥበብን ጨማምሮ ይስጥህ፡፡
😍አምናለሁ ትልቁ ቦታ ላይ እንደምንገናኘ🔥
መልካም ልደት አፍቃሪው፡፡