Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
እስኪ ይቺን ፅሁፍ ሁላችንም እናንብባት ከዛ እናውራበት.......

"ከሕሊና መንፃት" ይላል

ከሕሊና🤔🤔🤔🤔🤔 🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIN

#ከሕሊና_መንፃት

#ሕሊና_በውስጣችን_የተቀመጠ_የእግዚአብሔር_ወኪል_ነው፡፡ ክስ የህግ ምክንያት እንደሚፈልግ ሕሊናም ለመውቀስ ሆነ ለመክሰስ የሕግ ምክንያት ይፈልጋል፡፡ እውቀት በሌለበት ሕሊና ትክክለኛውን ሚዛን ሊሰጥ አይችልም፡፡ ሕሊና በሰው ውስጥ መኖሩ ሰው ሳያስብ ላደረገው ስህተትና አውቆ ለፈፀመው በደል እንቅልፍ በመንሳት ለይቅርታ እና ለንሰሐ እንዲበቃ ነው፡፡

እግዚአብሔር ሕሊናን በሰው ውስጥ ያስቀመጠው ሰውን ለማሰቃየት ሳይሆን ሰውን ለማስታወስ ነው፡፡
ይህ ሕሊና ባለቤቱ ላልተፈለገ ነገር ይጠቀምበታል ራሱን በሕሊና ቀማሰቃየት ለበደሉ ራሱ ካሣ መክፈል የሚፈልግ ሰው አለ፡፡

ይህ ግን የክርስቶስ ደም ለእኔ አይመጥነኘም እንደማለት ነው፡፡ ሰው ለበደሉ ዋጋ መክፈል ካለበት ያለበት፡መሞት ነው፡፡ ያውም በስጋ በነፍስና በመንፈስ፡፡ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የሞተው ሰው የበደሉን ዋጋ መክፈል ስለማይችል ነው፡፡

ታዲያ ራሳቸውን በሕሊና ማሰቃየት የሚፈልጉ ብዙ ጊዜ አእምሮአቸውን ይጎዳሉ፡፡

ሰይጣን ሕሊናን ለክፉ ነገር ይጠቀምበታል፡፡ ባህርይው መክሰስ ነው እንደሰይጣን ተከሳሽ የለም ሰይጣን ግን ሌሎችን ይከሳል፡፡ የሚከስ ሁሉ ክስ ያለበት ነው፡፡ ትልቁ ተከሳሽ ትንሹን ተከሳሽ የሚያብጠለጥለው ከራሱ ለመሸሽ ነው፡፡
ክስ የሰይጣን ወይም የጠላት ነው፡፡

#እግዚአብሔር_አምላክ_ህሊናን_የሰጠን_ለማስታወስ_እንጂ_ሰውን_ለማሰቃየት_አይደለም፡፡

ሕሊናችን እንዲሁ ሊወቅሰን ይችላልና ማጣራት ይገባናል በድለን ንሰሐ ግባ ብሎ ከወቀሰን መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ነውና መደሰት ይገባናል፡፡ ክስ ብቻ ከመጣብን ሰይጣን እየሞገተን ነውና መገሰፅ አለብን፡፡
#የወቀሳ_ውጤት_ጴጥሮስን_ለንሰሃ_አበቃው፡፡
#የክስ_ውጤት_ይሁዳን_ታንቆ_እንዲሞት_አደረገው፡፡
ክስ ከሰይጣን ነው፡

በዘመናት ሁሉ ሰዎች ሕሊናን የራሳቸው ማድረግ ፈልገዋል፡፡ ሕሊና ግን የእግዚአብሔር ወኪል ነውና የራሳቸው ሊያደርጉት አልቻሉም፡፡
አዳም እና ሔዋን በበደሉ ጊዜ እንዲተፋፈሩ በገነት ጫካ ውስጥ እንዲደበቁ ምክንያት እንዲፈልጉ ያደረገው ሕሊና ነው፡፡

ሰው ሲበድል ነጸፃነት እንዲያጣ ወይም በራሱ እንዲያፍር መደበቂያ ሱስ እንዲፈልግ አሳማኘ ምክንያት እንዲደረድር የሚያደርገው ከንሰሐ የሸሸው ህሊናው ነው፡፡ የሕሊና ድምፅ ለባለቤቱ እንጂ ለጎረቤት የማይሰማ ከፍ ያለ ድምፅ ነው፡፡
ይህም #እግዚአብሔር_ልጁን_በር_ዘግቶ_እንደሚወቅስ_ያሳያል፡፡
ሰዎች ሁሉ በዙሪያው እየዘፈኑለት ሕሊና ግን ሊቃወም ይችላል፡፡

ታዲያ ሰዎች በዚህ ዓለም ላይ በጣም የሚፈሩት ሕሊናቸውን ነው፡፡ ሕሊናን መፍራት ግን ከክፉ አያድንም፡፡ ሕሊናን መፍራት ለጊዜያዊ ጥንቃቄ እንጂ ለፍፁም መቀደስ አይረዳም፡፡
እግዚአብሔርን መፍራት ግን ደህና ማስተዋል ነው፡፡
እግዚአብሔርን ስንፈራ ሕሊናንና ሰዎችን ከመፍራት እንድናለን፡፡ የውስጥ ሰላም መሠረቱም ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሰላም ነው፡፡

ሰዎች ህሊናቸውን ስለሚፈሩ ከህሊናቸው ጋር ላለመገናኘት በተለያዩ ሱሶች ውስጥ ይደበቃሉ፡፡
ትልቁ ዳኛ ግን እግዚአብሔርን ነውና ወደሱ መቅረብ ይገባል፡፡ ህሊናን ከእግዚአብሔር በላይ ማክበር ፍጡርን ማምለክ ነው፡፡ሰው ሕሊናውን በመሸሹ አይቀደስም በደልን በበደል ለማንፃት እየሞከረ በማያቋርጥ ስህተት ውስጥ ይገባል፡፡

ሕሊና ይቅርታ እንዲያደርግላቸው የሚፈልጉ ሰዎች አሉ፡፡ ሕሊና ይቅርታ መስጠት አይችልም፡፡ ሕሊናን ይቅርታ ብነጠይቅ ቅጣት ያቀል ይሆናል እንጂ ምህረት መስጠት አይችልም፡፡ ባህርይው አይደለም፡፡ እግዚአብሔርን ይቅርታ ስንጠይቅ ግነ ሕሊናም ፀጥ ይላል፡፡

መንግስት ምሕረት ሲያደርግልን የምሕረቱ ደብዳቤ እስከ ግዛቱ ወሰን ይበተናል፡፡ እግዚአብሔርም ምህረት ሲያደርግልን የምህረቱ ደብዳቤ በሰማይና በምድር ይበተናል፡፡

ንሰሐ የማይፈልጉ ሰዎች ሕሊናን በበጎ ሥራቸው ፀጥ ለማድረግ ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን ከምናደርገው በጎ ሥራ በፊት ያደረግነው ኃጢያት ማመን ይበልጣል፡፡ ሕሊናን የሚክስ የክርስቶስ መስዋዕትነት እንጂ የእኛ በጎነት አይደለም፡፡

ሕሊናን የሁልጊዜ ጠቋሚ ማድረግ ያሳስታል፡፡ ሕሊና የሚወቅሰን ባወቀ መጠን ነው፡፡
ይህ ሕሊናንም የሞት ዘመን አለው
#ሕሊና_የሞት_ዘመን_ላይ_ሲደርስ_መውቀስ_ያቆማል፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜ በሕሊና ላይ እነንዳንደገፍ መጠንቀቅ ይገባል፡፡ ሕሊና ዝም አለን ማለት ንፁህ ነን ማለት አይደለም፡፡
የሁል ጊዜ ወቃሽ ቃሉና መንፈሱ ናቸው፡፡

የበደልናቸውን ይቅርታ መጠየቅ ይገባል፡፡ ይቅርታ ጠይቀን ካልተቀቀሉን እነርሱ የእኛን ስህተት ተሸክመዋል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሲሰቃዩ ይኖራሉ፡፡ ይቅርታ ለመጠየቅ ሰውቹ በህይወት የሌሉ ከሆነ እነርሱነ ወክሎ ይቅርታ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነውና ለእግዚአብሔር መንገር ይገባል፡፡

ሰው በበደሉ ሁለት ዓይነት ነገሮች ይፈልጋል፡፡ የመጀመሪየው ልበ ሙሉ የሚያደርገው ካሳና ሁለተኛው ከሕሊና መንፃት ነው፡፡ እነዚህን ሰው ለራሱ ማድረግ አይችልም እነዚህን ነገሮች ሰው ለራሱ ማድረግ ከቻለ ሰው አምላክ ሆኗል፡ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም የህሊና ካሳ የሚገኘው እግዚአብሔሬ ከረካበት ነገር ነው፡፡ የህሊና መንፃት የሚገኘው በአምላካዊ አሰራር ነው፡፡

ጌታችን ወደዚህ አለም የመጣውና በመስቀል ላይ የሞተው እነዚህን ሁለት ነገሮች ሊያስገኘልን ነው፡፡

ብዙ ሰዎች ንሰሐ በገቡበት በደል እንደገና ይጸጸታሉ፡፡ እግዚአብሔርን የተወውን ለማስታወስ ይፈልጋሉ፡፡ እግዚአብሔር በባህርይው የማይወደው ይቅር ያለውን በደል ማስታወስ ነው፡፡ ንሰሐ ገብቶ ምልሶ፡መጨነቅ ኃጢያት ነው፡፡ ምክንያቱም በእግዚአብሔር ምሕረት አለማመን ነውና፡፡ ከክርስቶስ ደም በላይ የሆነ ከባድ ሀጢያት የለም፡፡

መፍርሃት ያለብን የእኔ ኃጢያት ንሰሐ የለውም ብለን ሳይሆን ንሰሐ የማይገባ ልብን ነው፡፡

እኔ ይህን እንዴት አደረኩ? ማለት ንሰሐ ሳይሆን መመፃደቅ ነው፡፡
እግዚአብሔር ባይዘን እኛ የማናደርገው የለም፡፡
ሰው በስህተትም አንዳንዴም ከሕሊና ውጪ በመሆን ሌላ ጊዜም ቅጽበቶችን ማለፍ ባለመቻል የተለያየ ስህተት ውስጥ ይገባል፡፡
የተደረገውን እንዳልተደረገ እንዲሆን መመኘት ጥቅም የለውም፡፡ ዋናው ነገር ግን ወደንስሐ መመለስ ነው ከዛ ከማድረጋችን በፊት ከነበረን ቅድስና በላይ ይቀድሰናል፡፡

ይለናል ባለፈው ስጦታ የተሰጠኘ መፅሐፍ፡፡

ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንዲህ ቀነጨብኩለት

ለሁላችንም ለጥፋታችን ንሰሃ ያስፈልገናል፡፡
አብሶ በዚህ ሰዓት

🙏አቤቱ ለንሰሃ ሞት አብቃን😔

አስተያየታችሁን አድርሱኘ @jahABP ነኘ 😊🙏

🙏መልካም አዳር🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
ይቺን ዘፈን አድምጡልኘማ


ግጥሙ የታላቁ መዝሙረኛው የኤልያስ መልካ ነው😍😍😍😔😢😢🙏🙏 ነው፡፡

ጆሮ ካለን ጥሩ አድማጭ ከሆንን ኤሉ ሁሉን ነግሮን ሔዷል😘🙏 ጆሮ አለን ካልን እና ምክርን ከፈለግን ህይወትን በበጎ ማሸነፍን ራስን ቆም ብሎ ለማሰብ....ብቻ ብዙ ብዙ ለማትረፍ የኤላን ስራዎች እናድምጥ፡፡

እዚህ ዘፈን ላይ በወጣቱ ድምፃዊ እሷን ይሞግታታል እንዲህም ይላታል:-.......

ኤሉ ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን🙏🙏🙏😍😍
🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
05 Track 5.wma
3 MB
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

ግልጡን ስሚኘ

ግልጡን አልኩሽ እንጂ ፈልጊኘ ሳልል ሩቅ ቦታ
ሳላቀርብሽ ሳልደብቅ የልቤን ምንም እውነታ
ዘመዴ የነብሴ ናፍቆት የልቤ ጥም ያይን አምሮቴ
እሩቅ ሔደሽ አትጪኘ ግልፁን ያልኩሽን እሱን አድምጪኘ

ምን ማለቱ ብለሽ አልፈሽ
አትፈልጊኘ ታጪኛለሽ
ምንም ማለቴ አይደል
በቀር ካልኩሽ ቋንቋ ካልኩሽ ፊደል

ዘመዴ የነፍሴ ናፍቆት
የልቤ ጥም ያይን አምሮቴ
ሩቅ ሄደሽ አትጪኘ ግልጡን
ያልኩሽን እሱን አድምጪኘ

ያልኩት እንዳልኩት እንጂ ላንቺ
ምን ብለሽ እሩቅ አትሒጂ
ምንም የለም በቃ ሚስጢር
ግልጡን ካልኩሽ ከሱ በቀር

እውነተኛ ወዳጅ
እኔ ነኘ አፍቃሪሽ
ይህን አውቃለሁ እያልሽ
ቅርብ እያልፈለግሽኘ

ሁሌም አንቺን አላርቅም
ማንም አንቺም ሌላ አታውቂም
ሁሌም በቋንቋሽ ሳወራ
ሁሌም እኔው ካንቺ ጋራ

ዘሩባቤል ሞላ

መልካም ዕረፍት ኤልያስ መልካ
🙏😍🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

እናቶች አዝነው ቁጭ ብለዋል የህፃናትን ልመና ይሰማልና ልጅ እየፀለየ ነው አቤቱ ፀሎታችንን ተቀበል፡፡

ለሀገራችንና ሰላም እና አንድነት ስንል ሁላችንም በሀይማኖታችን ወደ ፈጣሪያችን እንፀልይ🙏🙏🙏🙏🙏🙏


@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

5 OR 1🤔🤔🤔


WALLPAPER 😍

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

የተቻለኘን ለማድረግ እየሞከርኩ ነው፡፡
ከዛ ሰብሰብ ብለን የተቻለንን እናደርጋለን፡፡

ነገ ሚባል ቀን ካለ እኛ ጋር ደግሞ ተስፋ መቁረጥ ሚባል ነገር መኖር የለበትም፡፡
ብቻ መጠንከር ነው፡፡
ፈጣሪን ከፊት አስቀድመን ማድረግ ምንችለው ላይ ትኩረት እናደርጋለን፡፡

ትንሹን ስናደርግ በብዙ እርምጃ ወደ ትልቁ እየተጠጋን እንደሆነም ትልቅ እምነት አለኘ፡፡
እዛ እሩቅ ምንለው ቦታ ላይ ደርሰን መቆም አለብን፡፡ ከሌሎች ሰዎች ጋር ሳይሆን ከእኛ ከትላንት ማንነታችን ምን ያህል ተሽለናል? ብለን እራሳችንን መጠየቅ፡፡ ከትላንት የተሻልን ከሆነ ዛሬያችን ልዩ ነው ማለት ነው፡፡

አይሆንም ሚባል ነገር የለም፡፡

ከጠነከርን ሁሉን ማድረግ እንችላለን፡፡
ምኞቶቻችን መልካም ይሁኑ እንጂ ሁሉም ሰው የኛ ተባባሪዎች ይሆናሉ፡፡ ሰዎች ስላሉን ሳይሆን እኛ እንደምናሳካው ካመንበት ይሆናል ይሳካል፡፡
አትጠራጠሩ

እና አሁን ልላችሁ ምፈልገው የፎቶግራፊ እና የቪዲዮ ተሰጦ ያላችሁ የተማራችሁ ወይም እንደኔ ስለምትወዱት ሞያው ላይ ያላቹ የቻናላችን አባሎች ለእናንተ መልካም ዜና አለኘ፡፡

ብዙ ልጆች በውስጥ መስመር እንዴት እራሳችሁን ማሻሻል እንደምትችሉ ጥሩ ፎቶግራፈር ለመሆን ምን ማድረግ አለብብ የሚል ብዙ ነገሮችን እንደተነጋገርን ከዛም አልፎ ስራ እንድፈልግላችሁ ከነማስረጃችሁ ልካችሁልኘ ነበር እየላካችሁልኘም ነው ፡፡


እና አሁን ከአንድ ወዳጄ ጋር የሆነች እንቅስቃሴ ለማድረግ አስበናል አሁን ሀሳብ ነው...ሀሳቡን፡ደግሞ እኔ እናንተ ብትሳተፉበት ብዬ አሰብኩ፡፡ማለቴ ሰብሰብ ብለን ማድረግ ምንችለውን ምንድነው ብለን እንድናስብ🤔🤔 ነው፡፡

ስራው ላይ ቶሎ ካልገባን ከሙያውም እየሸሸን ስራውም ቴክኒኮቹም እየጠፋብን እንደሚመጣ ግልፅ ነው፡፡ እናም ይህ ያልኳቹ ወዳጄ ቶም የፎቶግራፊ እና ቪዲዮ ትምህርትቤት የተማረ ሲሆን አሁን ከኔጋር አውርተን የተወሰኑ ስራዎችን ሊሞካክር አስቧል የተወሰኑ ቀረፃዎች ለማድረግ የተወሰኑ ኢዲቲንጎችን ፎቶዎችን.......ወዘተ

እና ይህን ፅሁፍ የምታነቡ ማንኛውም የቻናላችን አባሎች በውስጥ መስመር አናግሩኘ እና አንድ እርምጃን እንራመድ እላለሁ፡፡
ለጓደኞቻችሁ አካፍሏቸው

በነፃ ለልምድም የምትሰሩበት ቦታ ለማግኘት፡የተሻለኘን ጥረት እያደረኩኘ ነው፡፡

ለሀገራችኝ ሰላም መፀለይ አይረሳ፡፡

ችግራችሁን ነግራችሁኘ ዝም ያልኩት ምኑንም ሳልጨብጠው ላለመቀባጠር ነው ይቅርታ አድርጉልኘ😊🙏🙏፡፡

@jahABP ነኘ ትላንት እንደዛሬ አልነበረም ነገም እንደዛሬ አይሆንም እንዲሆንም አንፈቅድለትም💪እንበርታ እንጠንክር፡፡

ተፃፈ በአብይ 05-03-2013 ህዳር

😊መልካም አዳር🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

የመከራው ጊዜ አልፏልና ድንግል ሆይ ሀገርሽ ገሊላ ግቢ፡፡

ረሀቡን ጥሙን ስደቱን አሳስቢልን፡፡

ምህረትን አሰጪን እንለምነሻለን😍😍ሁሌም ወደ አንቺ እፀልያለን🙏🙏፡፡

እንኳን አደረሳችሁ

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#መልካም_ልደት_ኢንጂነር

እሱ የኔ ልደት ጊዜ ሁሌ እንደዚህ ይለኛል:-

"አብዬ ለኔ ስትል እንኳን ተወለድክልኘ" 😍😍🙏

እኔ ደግሞ ቆይ ማነው እድለኛው እላለሁ🤔🤔

እንዴት ደስ ሚል አባባል ነው በፈጣሪ እናም እኔም የሱ ልደት ጊዜ ልጠቀመው አንድሽዬ ወንድሜ ማርያምን ለኔ ስትል እንኳን ተወለድክልኘ፡፡ አንተ ለኔ ብዙ ነገሬ ነህ እኔ አንተን እያየሁ ነው ያደኩት ያንተን እርምጃዎች ነው የተራመድኩት ይኸው ጠቅሞኘ እዚጋር ደርሻለሁ ፡፡

ምን እንደምልህ ግራ ገብቶኛል ምክንያቱም ስለራስ መፃፍ ሆኖብኘ ከብዶኛል፡፡
አንተ የጥንካሬ ተስፋ ያለመቁረጥ ምሳሌ በአላማ በመፅናት ምንፈልገው ጋር በፅናት እንዴት መድረስ እንደምንችል በዙሪያችን ያሉትን መሰናክሎች እንዴት በመልካምነት ማለፍ እንደምንችል የዛሬ ዝቅ ማለት ለነገ ከፍታችን መሆኑን

ትልቁንም ትንሹን ሰው በእኩል አይነት ማየቱ ለትዕዛዛቸው እሺ ማለትን ሰውን አለማስቀየምን መጥፎ ነገር አለመናገርን መጥፎ ስድቦችን ከአንደበት አለማውጣትን ሚስጥር መጠበቅ...ኧረ ብዙ ብዙ፡፡

በተለይ ከመስመር ስወጣና ወደ መጥፎው ስጓዝ ግልጥ ግልጡን ስለምትነግረኘ መሆን የለበትም እንዴት ይሔን ታደርጋለህ ብለህ እንደሌሎቹ ደባብሰህ ሳይሆን በጣም ስለምተወቅሰኘ ያ ጥንካሬዬ ሆኗል ደግሜ ላለማጥፋት ያንተ ተግሳፅ እጅጉኑ ነውና ሚጠቅመኘ አብዛኞቻችን ደግሞ ያጣነው እንዳንተ ወደ መጥፎ ስንሔድ ወቃሽ አራሚ ሰው ነው እኔ ግን አንተ አለኸኘ፡፡

ከምንም በላይ ደግሞ እግዚአብሔርን መፍራትን አብዝቶ ወደ ደጀ ሰላሙ መመላለስን ቃሉን መስማት በሱም መንገድ መጓዝን ፍፁም መንፈሳዊ ሰው መሆንን የወሬ ብቻ ሳይሆን የተግባር ክርስቲያን መሆንን እናታችን ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ በህይወታችን ድንቅ እንደሆነች እነዚህን እና ሁሉን ካንተ ተምሬያለሁና እኔ በጣም ደካማ ነበርኩና ስላበረታኸኘ አመሰግግሃለሁ፡፡ አየህ የሰጠኸኘ ብዙ ነው ለዚ ነው ለኔ ስትል እንኳን ተወለድክልኘ የምልህ፡፡

ለሰዎች ሁሌም ነው እንዳንተ አይነት ሰው ምመኘላቸው፡፡


ግን አንደበት ነገር ቅር ብሎኛል ምንድነው ካልከኘ የእኔን ፍቅር ሚቀናቀን ስለመጣብኘ😢😢😢በእውነት ነው የምልህ😢፡፡

ሀይሌ ሩስትስ በአዲሱ አልበሙ:-
ታላቁ ኤልያስ መልካን የታመነ ነው ብሎታል

አብይ ደግሞ:-ለአንድሽ ዘፈኑ አንተን ይገልጥሃል

#ይለያል_በቃሉ_ለመዘነው
#ወዳጁን_ያልዋሸ_የታመነው
#ሳይሸነጋገል_ቀርቦ_እውነቱን
#የሚኖር_ተራርሞ_ገልጦ_የልቡን፡፡

#ያልሸነገለው
#ወዳጅ_የምለው
#ሳይሸሽግ_ውስጡን
#የሚገልጠው_ነው
#የሰመረለት
#ወዳጅ_ላደለው
#ከራስ_ይበልጣል
#ከተወለደው፡፡

ታዲያ እድለኛው ማነው🤔🤔

እኔ ማለት አንተ ነኘ ምክንያቱም አንተ መልካም ነሃ መልካምነት ደግሞ የሁሉን ልብ ያሸንፋል፡፡

መልካም ልደት ምርጡ....

እግዚአብሔር አምላክ ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንዲሰጥህ እመኛለሁ ትላንትም ዛሬም አብራህ ከጎንህ ያለችው ወደፊትም የመንገድህ መሪ የሆነች እመአምላክ ወላዲተ አምላክ ፍፃሜህን ታሳምርልህ፡፡ አሳዳጊያችን መልዐክ ሊቀ መልዐኩ ቅዱስ ዑራኤል ዕውቀትን ሰጥቶ እዚህ አድርሶሃል አሁንም አብዝቶ ይጨምርልህ፡፡

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

እንደዚህ አድርገን ለመጠቀም ለምን የሆነ ዘዴ አንሞክርም ግን🤔🤔🤔🤔

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

እኔም ከመከላከያ ጎን ነኘ

እናቴ ሀገሬ ሁሌም ከፍ ከፍ በይልኘኘኘኘኘኘኘኘኘኘኘኘኘ💚💛♥

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
ለአባቱ ያደላል ከሚባሉት ልጆች መካከል ነኘ መሰለኘ😊😂

ህህህህ😂😂😊

እስኪ ድሮ ልጅ እያለን አባቴ አቶ አንዱአለም ዘሪሁን😍🙏🙏 ካስተማረን አሁንም ድረስ የጠቀመን ወደፊትም ከሚጠቅመን የፀሎትን ሀይል እንድንረዳ ካደረገን ድንቅ ጨዋታ እና ከጨዋታው በኀላ ደግሞ በድንቅ አተራረክ የሚነግረንን አጠር ያለች አስተማሪ በጣም አስተማሪ ለኔ አሁንም ድረስ ታሪኳን እያስታወስኩ መጥፎ ነገሮችን ከማድረግ የምቆጠብበት ታሪክ ጀባ ልበላችሁ......

ጠብቁኘማ ትወዱታላችሁ፡፡🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY
እዮባ ወንድሜ እንኳን ደስ አለህ በጣም ደስ ብሎኛል አምላከ ቅዱስ ዑራኤል የተመሰገነ ይሆን ድንግል ማርያም ቀሪውን ጊዜአችሁን ትባርከው፡፡ 😍😍😘❤️❤️


ልቤ ማን ገፍቶት አንቺን አለ
ያኔ ሳያምነበት መች ማለ
በህልሜም በእውኔም ካንቺጋራ ነኘ
ለዓይኔ ሌላ አለም መች አማረኘ
ፍቅሬን በወረቀት መች ፃፍሺው
እግሬን በፍቅርሽ ነው ያሰርሽው
ነፍሴ አካሌነሽ የጎኔ
ዶሴ ከኔ በላይ ለምኔ

ያመንኩሽ ያኔ ነው ተረጋግጦ
ውል አለኘ ሲል ልቤ ቃልሽኝ ሰምቶ
እርስቴም ፍቅርሽ ነው ውስጤ ገብቶ
በቁሜ አውርሶሻል ልቤን ገዝቶ
እዮባ😍****ታላቁ ኤልያስ መልካ
AB PHOTOGRAPHY

ሰፈራችን

ህዳር 12 ነዋ🔥🔥🔥🔥

እነኳን ለመላዕክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ 💚💛♥

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
ሀይለኛ ድካም🤦‍♂😔😔 አለ እንቅልፍ እንቢ አለ 98.1 ለስለስ ባለ ሙዚቃ ምሽቱን.....

አሁን እዮባን እየሰማሁ ነው

አንደበቴ ተናገር......እውነት የሆነ ነገር

ስሜቱን ኖሮ የከሰረ
ማነው በጭንቀት የተሸበረ....

ይቀጥላል....ጉዞ ወደ 97.1
AB PHOTOGRAPHY


ለዚህ ፎቶ ከ10 ይገባዋል ምትሉትን ስጡት

ቡናችን😍😋😋😋

በልዬ ማዘሯ ለፎቶው አመሰግናለሁ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY


እንደምን አደርሽ ኢትዮጽያዬ💚💛❤️


ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY


እንደምን አረፈድሽ ኢትዮጽያዬ💚💛❤️


ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
ለህፃናት እንደዚህ የተቻለንን በአቅማችን እናድርግ፡፡

ሀገር አንድ እርምጃ እንድትራመድ ህፃናት ላይ ነው መስራት ያለብን ወደጥሩው ወደፍቅር አድርገን እንቅረፃቸው፡፡

😍መልካሙን ሁሉ ለነሱ😍
AB PHOTOGRAPHY


መልካም ዕለተ ሰንበት ተመኘሁ💚💛❤️

አምላካችን መልካሙንሁሉ ያሰማን


ደብረ ሳሌም ቦሌ መድኃኒዓለም ካቴደራል
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD