Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
ኤልያስ መልካ አሁንም የጆሮ ያለህ ይለናል፡፡

ቀጣዩን ፅሁፍ ሳታነቡ ባትተኙ ደስ ይለኛል ጠብቁኘ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂


መልካም ልደት ኤልያስ መልካ፡፡
ሁሌም በልባችን ትኖራለህ፡፡

ቻሌንጁን ይቀላቀሉ የልብ ህመምተኛ ህፃናትን እንርዳ
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#መልካም_ልደት_ታላቁ_ኤልያስ_መልካ

#1970~

ታላቁ የሥነ ጽሁፍ መሲህ #ካሕሊል_ጅብራን ምርጥ "ሙዚቀኛ" የምንለው ይላል?...ምርጥ ሙዚቀኛ የምንለው "ዝምታችንን የሚያዜምንልን ነው"

ይህንን ቃል ተቀብሎ አለማመንና አለመጠቀም አይቻልም፡፡ ምናልባት ከዚህ ንግግር(ሃሳብ) በላይ ባለ እውነት ውስጥ ካልተሰራን አልያም ለኔ? እንደኔ? በሚሉ የስንፍና መሸሸጊያ በሆኑ ሰነፎች በገነቡት...የእውነት መሸሸጊያ ምሽግ መሳይ ግድብ ውስጥ ካልወደቅን በቀር ምርጥ ሙዚቀኛ የምንለው ዝምታችንን ፣ ፀጥ-ያልነውን ፣ ያፈርንበትን ፊደላት መያያዝ መሃል የጋረድነውን ፣ በግንባራችን ተፅፎ የማይነበበውን ፣ አንደበታችንን ያልተወለደውን ፣ ሊወለድ ሲል በስላቅ ሳቅ ያጨነገፈውን ያንን ማንነታችንን ይህን ምንነታችንን የሚያዜምልን የሚያዜምብም እርሱ በእውነት ምርጥ "ሙዚቀኛ" ነው፡፡

"ምርጥ ሙዚቃ ምን ዐይነት ነው" ? እኔም እላለሁ ምርጥ ሙዚቃ ብቻችንን ስንሆን የምናዳምጠው ነው፡፡
በመጀመሪያ ለምን ሙዚቃ ብቻ አያስፈልግም ለምን ምርጥ አስፈለገ የሚል "የዋህ" ጥያቄ ቢነሳ አጭር መልስ "Life is too short to drink cheap wine"(ለርካሽ ወይን ሕይወት አጭር ናት ስለሌለም ምርጡን እመርጣለሁ፡፡ እንደማለት)

ምርጥ የሚያስፈልገው ምንም በሌለበት ነው፡፡ መምረጥ የማያስፈልገው አማራጭ ሲጠፋ ነው ነገሩና ሁኔታው የግድ ሲሆን/ሸንጋይና አስመሳይ ምርጫ ይህን ጽሁፍ አይመለከትም/

ምርጥ ሙዚቃ ከምርጥ ጓደኛችን እኩል ነው፡፡ ምርጥ ሙዚቃ በድራፍትና በቢራ ስሜት ውስጥ የሚሸንጠን አይደለም፡፡ ምርጥ ሙዚቃ በቺቺኒያና በኦሎምፒያ መንገድ ፍርስራሾች ውስጥ የምናዳምጠው አይደለም፡፡ ምርጥ ሙዚቃ በሰርግ ግርግር ለጭፈራ ያስነሸጠን አይደለም፡፡ ምርጥ ሙዚቃ ሁኔታውን የሚያወራ አይደለም፡፡

የዚህ አይነት ሙዚቃ የመልካም ዘመን ጓደኛችን ቢጤ ነው፡፡ የሕይወት ክረምት ሲብት ዕንባ በዓይኖቻችን ሲቋጠር ዓይናችንን ላለማየት ሐዘናችንን ላለመስማት ሠማይ ሠማይ ግራ ቀኘ እንደሚያይ አስመሳይ የምንለው ባልንጀራ አይነት፡፡

የምናውቀውን የዘፈነ እርሱ አልዘፈነም፡፡
ጥበብ አንድም ከልክ ትሰፋለች/ትቀድማለች/ አልያም ጀርባ ሆና ጅራፍ ታነሳለች፡፡ ሕዝቡ በሚመስለው ሕዝቡ በሚፈልገው መንገድ የሚሔድ ጠቢብ እርሱ በሕዝብ የተሠራ ስለሆነ ጥበቡ/ሙዚቃው ፣ ስዕሉ ፣ ግጥሙ ፣ ፊልሙ/ አትረባውም ሕዝብን መስራት ስለማይችል፡፡

#ሕዝብ_ከሰራው_ጠቢብ_ሕዝብን_የሚሰራ_ጠቢብ_እርሱ_ታላቅ_ነው፡፡

ሙዚቃ ስሜትን አትከተልም ስሜትን የምታዝ ሌላ ስሜት ናትና፡፡ ምርጥ ሙዚቃ ምርጥነቷ መስፈርት ሕዝብ አይደለም ገለሰብ እንጂ፡፡
ምርጥ ሙዚቃ ለብቻችን ስንሆን ብቸኘነት ሲሰማን አደባባይ የማይገለጥ ዕንባ በማጀታችን ሲተናነቀን በብዙዎች መሃል ማንም ስንሆን ያኔ ለብቻችን መስማት የምንችላት ሙዚቃ ናት ያውም ምርጥ....

ለብቻችሁ ሥትሆኑ የቱን ሙዚቃ የማንን ሙዚቃ ትሰማላችሁ፡፡? ምርጥ ሙዚቃ ምርጥ ለማለት ሐዘን የግድ ሚዛኑ መሆን አይጠቅበትም ግን ብቻነት ሚዛኑ ነው ምርጥ ሙዚቃ ከምርጥ ጓደኛ እኩል ነውና ምርጥ ጓደኛችን ደግሞ በሽልማታችን ጊዜ የተገኘው አይደለም በሽንፈታችን ጊዜ አብሮን የቆመው እንጂ፡፡ ከዚህ በላይ ሚዜያችሁ ማን ይሆን?

ዓመሻሻችን ላይ ጋደም ስንል የራስጌያችንን መብራት አብርተን የቀኑን ድካማችንን ለማራገፍ ጋደም ሥንል የምንከፍተው ሙዚቃ እርሱ ምርጥ ሙዚቃ ነው? ከፍቅረኛችን ጋር ወይን እየተጎነጨን እደግመዋለሁ ወይን እየተጎነጨን ምን ዓይነት ሙዚቃ ቢከፈትልን ደስ ይለናል?/


ለስላሳ ሙዚቃዎች ሁሉ ምርጥ ናቸው ማለቴ አይደለም/ ግን ብዙ ጩኸት በሌለ ሰዓት ልንሰማቸው የምንችላቸው ሙዚቃዎች መልካሞች ይመስሉኛል ከስሜታዊ ፍቅር የፀዳ የቢራ ብዛት ያልገለጣቸው ወፎች ዝማሬያቸው ማለዳና አመሻሽ ላይ ነው፡፡

ሙዚቃ እንደወይን ነው፡፡ ክብርና ነውርን በሕብር የያዘ፡፡ ወይን እንደ መጠጥ ነው ግን አስካሪ ነውና ሽራፊ ነውርነት አለው ወይን እንደ ድራፍት አይደለም ለጠመቃውም ጊዜና ታላቅ ጥንቃቄ ይጠይቃል፡፡
ወይን የክቡር ነገሮች ሁሉ ተምሳሌት ነው ስለዚህ ወይንን ያለአክብሮት የትም የሚጠጣ እርሱ ወይን አልጠጣም ድራፍት የዕለት መጠጥ ነው ምናልባትም የሰዓታት ውጤት የትምና በማንም ሰው እጅ ያለ፡፡

ክቡር ሙዚቃ ጊዜ ይፈጃል ስድስትና ሰባት ዓመት በጠቢቡ የሕሊና ማድጋ ላይ የተጠመቀውን የሙዚቃ ወይን ጣዕሙ ከቢራና ከድራፍት እኩል ከሆነ አሳላፊው ሳይሆን ጠማቂውን እንዲህ እንለዋለን...
"ከፀዐዳችን ውጣ" ምክንያቱም ሕይወት አጭር ስለሆነች ተራ ወይንህን አንሻም" መልካሙን ለጠመቀው ግን እንላለን......

ምርጥ ሙዚቀኛ ሆይ! እናከብርሃለን እንወደሸሃለን ምክንያቱም ዝም ያልነውን አዚመህልናል ፣ ለብቻችን ስንሆን ሕይወት ስትከብድ ሰው ሲከብድ ኑሮ ሲከብድ መገልገል ሲያምረን ፀጥታ ሲያፍነን የምናዳምጠውን የሙዚቃ ወይነ ጠምቀህልናልና፡፡

ነፃነትን እንሻለን ግን ዝም ብለናል፡፡ ምክንያቱም አናውቀውም ግን ፈርተናል፡፡ እንስቃለን ግን ለእንባችን ቦታ ጠፍቷል፡፡ ጀግናዎች ነን ግን ተሸንፈናል፡፡ ለምለም አለን ግን ደርቀናል፡፡ ተጉዘናል ግን አልደረስንም፡፡ እንፈልገዋለን ግን አናደርገውም፡፡ ጠቢባን ነን ግን አናውቀውም፡፡ አንድነትን እንሻለን አንድ ግን አይደለንም፡፡ ክቡራን ነን ግን አፍረናል፡፡

ይህን እና ያንን የምታዜሙልን የምትጽፉልን እናንተ ለብቻችን ስንሆን የምንይዘውን የምናዳምጠውን ጓደኛ ከጓደኛም ምርጡን ለግሳችሁናልና እንመርጣችኀለን፡፡

እውነታቸውን የሚመስሉ ነገሮች አሉ ነገር ግን እውነተኛ ስላሉ መሳይ አያስፈልገንም፡፡ እውነተኛውን የሚያውቁ አሉ ነገር ግን እውነቱን ካላሳዩን ምርጦቻችን አይደሉም እንደውም ከእነርሱ ይልቅ መሳይ እውነተኛ ይሻለናል /የመሆን ፍላጎት አለውና/ እኛ እውነተኛ የሆኑትን እንመርጣለን "መሆን" ከየትኛውም የስሜት ሁኔታ በላይ ነውና መሆን መሆን ነውና የሆነውን እንመርጣለን የሚመስለውን የማይመስለውን ራሱ እንደወረደ፡፡ ምርጥ ሙዚቃ ፣ ምርጥ መፅሐፍ እንዲሁም ምርጥ ጓደኛ እኒህ አንድም ሶስትም ናቸው፡፡ ምርጥ ሙዚቃ ምርጥ ጓደኛችን እኩል ነው፡፡ ግን ምርጥ ጓደኛችን ማን ነው? ምርጥ ሙዚቃን ለመረዳት ጓደኞቻችንን እንለይ.........

2007 ዓ.ም ከታተመው የይሁዳ ድልድይ እና ሌሎች ሃሳቦች ከሚለው የኤፍሬም ስዩም መፅሐፍ ምርጥ ሙዚቃ እና ምርጥ ሙዚቀኛ ከሚለው ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንደቀነጨብኩት፡፡
የዮቤድም ታሪክ አለ ሙሉ ፅሁፉን እንድታነቡት ስጋብዛችሁ ብዙ እንደምትማሩበት እርግጠኛ ሆኜ ነው፡፡

ይህ ፅሁፍ ኤልያስ መልካን በደንብ ይገልፀዋል ብዬ አስባለሁ እናመሰግንሃለን እንኳን ተወለድክልን በብዙ መክረኸናል ውለታል አለብን
ከፅሁፉ በላይ ምንም ማለት አልፈልግም፡፡
ዝምታችንን ስለተናገርክልን እናመሰግንሃለን፡፡
😍😍🙏🙏👏👏🙏🔥👌

በመጨረሻም መፅሐፉ እንዲህ ይላል

"ከዚህ በተረፈ ከመስመር ውጪ በጥበብ ስም ተሰልፋችሁ እናዜማለን ብላችሁ የምትጫንጩ ሆይ "ከዐፀዳችን ውጡ" ምክንያቱም "ርካሽ ወይን ለመጠጣት ሕይወት አጭር ናትና ጊዜአችንን አትስረቁን፡፡"

02-04-2013 ታህሳስ
@jahABP ነኘ መልካም ጊዜ ተመኘሁ😍

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

40 ሚሊዮን ብር ፈጅቶ ቤቷ እንዲህ አምሮበታል😍😍😍

እናቴ በዓታ ማርያም አንቺስ ለኔ ልዩ ነሽ!!

እንኳን አደረሰን፡፡

#ታዕካ_ነገስት

እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያዬ💚💛❤️


@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#ፈጣሪ_አዳልቶልሻል

ይህን ያለው የባላገሩ ቴሌቭዥን ባለቤት እና የባላገሩ #ምርጥ ዳኛ አብርሃም ወልዴ ነው፡፡
እምትገርሚ ነሽ እንዴት አይነት ጉልበት ያለው ድምፅ ነው፡፡😱 ሚገርም ነገር ነው፡፡

ስንት አመትሽ ነው?

እሷ:- 17

አንቺ አላት አንቺ የድምፅሽ ቀለም ጆሮሽ የሚገርም ነው ዜማውን የሚወጣውን ዳይናሚክሱ የምትቆጣጠሪበት መንገድ በተፈጥሮ...ዝም ብሎ ሚሰጥ መሆኑ ይሔ #አድልኦ ማዳላት ነው፡፡ አንዳንድ ሰው ጋር የሌለ ነገር በዚህ እድሜሽ እንደዚህ አይነት ሙዚቃን መረዳት ሚገርም ነው፡፡
በዚህ ዙር እንዲነው ይሔ ይሔ ነው እንደዚህ ብታደርጊ ምልሽ ልጅ አይደለሽም፡፡
በእውነት አስደንግጠሽኛል ስታወሪ ቀስ ብለሽ ነበር ስትዘፍኚ ደግሞ ሌላ ሰው ቅድም ያወራኀት ልጅ አይደለሽም የሆነ የዘፈን መንፈስ አለ ውስጥሽ፡፡
በጣም ምጠብቅሽ ልጅ ነሽ በዚህ ውድድር ብቻ ሳይሆን በእኛ ሀገር ሙዚቃ በሴቶቹ የራስሽን ነገር ይዘሽ በደንብ ከሰራሽ በጣም ታዋቂ ምትሆኚ ይመስለኛል፡፡

ሶፊ ይቀጥላል:- በጣም አሪፍ ነው በ17 አመት እነደዚህ አይነት ቴክኒክ ከገባሽ እንግዲህ ከፍ እያልሽ ስትመጪ እንግዲህ👏👏👏የጉርምስና ነገር እራሱ አልያዘሽም ጉሮሮሽ ላይ ያለው ነገር በጣም ጥርት ያለ ነው፡፡በጣም በቴክኒክ የበለፀገ በጣም ጉልበት ያለው፡፡
ለዚህ ዘፈን አንድ ስታንዳርድ ያስቀመጥሽ ይመስለኛል፡፡
ከዚህ በኀላ የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች ይሔ ነው የኛ ስታንዳርድ ብለን ምናስበው፡፡
ይህን ዘፈን ይዘው መተው የተወዳደሩ ልጆች አሉ ካንቺ በላይ ይህን ዘፈን የሰራ የለም ሁሉም ያቀረብሽበት መንገድ ፓኬጁ ዳይናሚክሱ ቶኑ
ቴክኒኮቹ በጣም ቆንጆ ነው፡፡
ጎበዝ በጣም አሪፍ ነው በርቺ👍፡፡

አረጋኸኘ እንዲህ አጠቃለለው፡- ሁሉም ገር ተብሏል በጣም ቆንጆ ድምፅ ነው ያለሽ፡፡ በጣም ትልቅ ተስፋ ከባላገሩ አንዲት ትንሽ ልጅ አሳድገን ትልቅ ደረጃ ምደርሺ ትሆኛለሽ ቃላቶቹ አንቺ ላይ ያምራሉ ሌላም ሰው ሰርቶታል ግን አንቺ ላይ ምትፈጥሪያቸው ቃላቶቹ ፊደሎቹ ያምራል ተቆጣጥረሽ ድመፁን ይዘሽ ገብተሽ የላይኛውን ሁሉ ስትሰሪው ምንም እንከን የለውም ላንቺ ምንም ነገር መንገር አያስፈልግ በዚህ ውድድር ትቆያለሽ ሰርተሽ ብዙ ነገር ታመጫለሽ የሚል ግምት አለኘ በርቺ👍፡፡

ስለዚ ዛሬ በሚያስጠርም ሁኔታ ሶስታችንም

አረንጓዴ💚💚💚👏👏

እኔ ዘፈኑን ከዚህ በፊት ሰምቼው አላቅም ግን በሷ ድምፅ ከሰማሁት በኀላ እየኮመኮምኩት ነው ግጥሙ ዜማው በሷ ድምፅ ሌላ ታሪክ ውስጥ ነው ሚከተው፡፡

#እኔ_አና_አንተ

እኔ እናንተ በፍቅር ተዎያይተን ብዙ ታሪክ አይናል
ብዙም ስቀን በደስታ ተከባብረን እስከዛሬ ደርሰናል፡፡
ምኞታችንም ሰምሮ ልጅም ወልደን ለመሳም አብቅቶናል
ኑሮን በፍቅር ስንመራ ለሚያየንም ኧረ እንዴት ደስ ያሰኛል፡፡

ደስታህም ደስታዬ ነው ስቃይህም ስቃይህ ለኔ፡፡
ፍፁም ማንለያይ የክፉ ቀኔ
ብትለየኘ አሎድም ይከፋኛል ቁጭ በል እናውጋ
ጠዋት ሳንልቀን ወይም ቀን ለሊቱ እስኪነጋ፡፡

ደስታህም ደስታዬ ነው ስቃይህም ስቃይህ ለኔ፡፡
ፍፁም ማንለያይ የክፉ ቀኔ
ህይወትክም ህይወቴ ነው አልከዳህም ነህ አለኘታዬ፡፡
ፀባይህም ተስማሚ ፍፁም ለኑሮዬ፡፡

ገራሚ በጣም ገራሚሚሚ ድምፅ
#387 #መስከረም_ኡስማን
በርቺል ባላገሩን ካንቺው ጋር ነኘ😍👏👏🙏🙏❤️😘😘

@jahABP ነኘ
AB PHOTOGRAPHY

በፍቅር😍 በመተሳሰብ🙏 በመረዳዳት💪 ለዘመናት👌👍👌👏
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
እንዲህ ነው እንጂ መጀገን

ምርጥ አምስት አመታትን በጓደኘነት

ፋሲካዬ 😍ማሬ ለዚ ቀን በመድረስሽ በጣም ደስ ብሎኛል በጣም👏የህይወትሽ አንዱ ጉዞ አለቀ ለሌላው ጉዞ ደሞ አንድ ብለሽ መነሳት ልትጀምሪ ነው በርቺልኘ ውዷ😘😘፡፡

የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ካልቆምን ሁሉም ይሳካል፡፡

ካንቺ ብዙ ነገር ነው ምጠብቀው አምላከ ቅዱስ ዑራኤል የተመሰገነ ይሁን፡፡

የኔ የምርጦች ምርጥ😘😍👏👏🔥🔥🔥
በቲክቶክ እና በዩቲዩብ በቅርብ ቀን🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
ሀይለጊዮርጊስ ማሞ

" ሰው " ይለናል

እባካችሁን ይደመጥ🗣⚡️

@jahABP ነኘ
የዘንድሮ ተመራቂዎች ግን ይሔን ፅሁፍ አንብባችሁት ይሆን???

ይህን ፅሁፍ ሳነብ በእውነት የሆነ ደስ የሚል በጣም ደስ የሚል ነገር ነው ሚሰማኘ ሁሉም ሰዎች ሲመረቁ ይህን ፅሁፍ ቢያነቡት ብዬ እመኛለሁ በጣም ተነሳሽነትን ይጨምራል፡፡

ጠብቁኘማ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

ለሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ👏👏😍👏
ተመራቂዎች ዝግጁ ናችሁ😃🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHUC DESIGN

#እንኳን_ደስ_አላችሁ

ዕውቀት ረቂቅ ናት! ላልያዛት ምንም አትመስለውም ለያዛትም ቢሆን ያን ያክል አትደነቅ፡፡ ያላወቃት ስለማያውቃት አይናፍቃትም ያወቃትም በእጁ ስለገባች ተራነገር ትመስለዋለች፡፡ ይህንን አንድ ሊቅ የጠቀሰውን ምሳሌ ወስጄ ላስረዳ፡-

አንድ ሽማግሌ ዓሣ በጠዋት በጎሬው ወጥቶ ህፃናት አሳዎች ዋና ሲለማመዱ ያገኛቸዋል፡፡
"ልጎች እንዴት ናችሁ? ዛሬ ውሃው ሙቅ ነው ወይስ ቀዝቃዛ? አላቸው፡፡ ልጆቹም እርስ በእርሳቸው በአግራሞት ተያይተው:-
"#ውሃ_ምንድነው?" አሉት፡፡ ሽማግሌውም የውሃ ምንነት ማወቅ ይህንን ያህል ትለቅ ነገር ስላልመሰለው ነበር፡፡ ውሃን ላያውቁ ይችላሉ ብሎ ለአፍታ እንኳን አልጠረጠረም፡፡

እውነታው ግን ተራ ነገር የመሰለን ነገር እንኳን የማያውቁ መኖራቸው ነው፡፡ በዚሁም የተነሳ በዚህ ዓለም እውቀትን በመፈለግና ዕውቀትን በማክበር የሚተጋው ውስን በመሆኑ በተለይም በሀገራችን ከዕውቀት አልተጠቀምንም ወይንም በማወቅ አላደግንም፡፡


የዩኒቨርስቲ ዋና ዓላማ ዕውቀትን ሁሉ ለተማሪዎች ማስጨበጥ አይደለም አይቻልምና የዕውቀት ምንነትና ጥቅምን እንጂ፡፡ ስለሆነም እናንተ ተመራቂዎች ለማወቅ የተዘጋጃችሁ የዕውቀትን ጥቅም የምታውቁ የዕውቀትን ሀይል የምትረዱ ሆናችኀል፡፡


በኮምፒውተር ቋንቋ ፎርማትድ(Formated) በኪነጥበብ አነጋገር የተቃኘ ክራር በእናቶቻችን አነጋገር ደግሞ የተሟሸ ምጣድ እንጂ አዋቂዎች አይደላችሁም ማሰብ እንድትጀምሩ እንጂ አስባችሁ ስለጨረሳችሁ ዛሬ አልተመረቃችሁም፡፡

ውድ ተመራቂዎች!
ተመራቂ ስትባሉ አንድ የሙያ መስክ በዓለም ላይ ምን ያክል ዕውቀት እንዳለ ያም ዕውቀት እንዴት ሀብትና ብልፅግና ፣ ድህነትና ሰላም ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ እንደሚሆን ፣ በጥቅሉ ድንጋይ እንዴት ዳቦ እንደሚሆን ፣ ውሃ እንዴት መብራት እንደሚሆን ፣ መርዝ እንዴት መድኃኒት እንደሚሆን ፣ ጊዜ እንዴት ገንዘብ እንደሚሆን ፣ ዕውቀት ካለ ውላን ሽቅብ ማፍሰስ ጉምን መዝገን እንደሚቻል የዕውቀት ብልጭታ በአእምሮአችሁ መፈጠሩን ለማመልከት ነው፡፡

ልክ ክብሪት እንደመጫር ነው፡፡ በርቶ ይጠፋ ይሆናል ወይም ያቀጣጥል ይሆናል፡፡ ብልጭታውን ወደሚቀጣጠል የዕውቀት እሳት መቀየር ከዚህ በኀላ ለእናንተ ዛሬ የተሰጣችሁ ኃላፊነት ነው፡፡

ዛሬ ስውሩ የዕውቀት ዓለም መጋረጃ ለእናንተ የተገለጠ ምስክር ስለመሆኑ የምስክር ቀን ነው፡፡ ለዕውቀት መቅደስ ምስጢር ተካፋይ ለመሆን ብቁ፡እጩ መሆናችሁ የተገለጠበት ዕለት ነው፡፡
ስለሆነም ዋናው የዕውቀት ፍለጋ ዋናው ትምህርት ቤት ከፊት ለፊታችሁ ነው፡፡

እስከዛሬ መምህራን ያስተምራችሁ ነበር ከዚህ በኀላ ግን እራሳችሁን በራሳችሁ ታስተምራላችሁ፡፡ እስከዛሬ በሳምንታዊ ማብቂያ ወይም በሴሚስተር ማለቂያ ላይ መምህራኖቻችሁ ይፈትኗችሁ ነበር ከእንግዲህም ወዲህ ደግሞ ኑሮ በየቀኑ ትፈትናችኀለች፡፡


እስከዛሬ የፈተና ውጤታችሁን መምህራኖቻችሁን መምህራኖታችሁ ያርሙላችሁ ነበር ከዚህ በኀላ ግን ሕይወት ታርምላችኀለች፡፡ የእስከዛሬው ትምህርት ውጤታችሁ A እና B ወይም ቁጥር ነበር ከዚህ በኀላ ግን የፈተና ውጤታችሁ፡-
ብልፅግና ወይም ድህነት ፣ ፍቅር ወይም ጥላቻ ፣ ሹመት ወይም፡ሽረት ክብር ወይም ውርደት ፣ ሕይወት ወይም ሞቶ ሆኖ ይመጣል፡፡

በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ በጥልቀት የማሰብ አቅም የዕውቀትን ጉልበትና ኃይል ተረዳትችኀል፡፡
#የዕውቀት_ድሃ_እንጂ #የገንዘብ_ድሃ_የሚባል ነገር እንደሌለ ከሳይንስ ተምራችኀል፡፡
ማንም ሰው ሲወለድ እርቃኑን ይሁን እንጂ ምጡቅ የብልፅግና ምንጭ የሆነ አእምሮ ከፈጣሪ ዘንድ ይዞ እንደሚመጣ ተረድታችኀል፡፡

#የሰው_ልጅ_እጣ_ፈንታ_በሌሎች_ሰዎች_እጅ_ሳይሆን_በአእምሮው_ውስጥ_እንደተቀመ_አውቃችኀል፡፡

በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ በተደጋጋሚ ትፈተኑ ነበር፡፡ መፈተን ምን እንደሆነ የፈተና ውጤት ምን ሊያስከትል እንደሚችል በአግባቡ ተለማምዳችኀል፡፡ አእምሮአችሁ የጥያቄዎችን መልስ በወረቀት ላይ ማምጣትን ተምሯል፡፡ እንድታብራሩ ከብዙ ምርጫዎች ትክክለኛውን እንድትመርጡ እውነትና ውሸትንእንድትለዩ በየወገኑ እንድታዛምዱ ተጠይቃችሁ አልፋችኀል፡፡

አሁን የልምምድ ጊዜ አብቅቶ እውነተኛው የፈተና ሕይወት ከዚህ በኀላ ይጀመራል፡፡ ሙሉ ትጥቅ ይዛችኀልና ይህንን ነባራዊ ዓለም ለመቀበል ልበሙሉ እንጂ የምትሸበሩ አይደላችሁም፡፡ የችግር ሁቹ መፍቻ ዕውቀት መሆኑን ተረድታችኀል፡፡

በተማራችሁበት የሙያ መስክ በመሰማራት እራሳችሁንና ወገናችሁን አገልግሉ በሚል ምክር ላስራችሁ አልፈልግም፡፡ ይልቁኑም የልባችሁን ፍላጎትና መሻት ተከተሉ(follow your heart) እላችኀለሁ እንጂ፡፡ የሠለጠናችሁበት ሙያ መነሻችሁ እንጂ መድረሻችሁ ለመሆኑ እርግጠኛ መሆን አይቻልምና፡፡ ከዩኒቨርስቲ ያገኛችሁት ሙያ መስፈንጠሪያ(springboard) እንጂ መታሰሪያገመድ አይሁንባችሁ፡፡

#የምትወዱትን_ሥሩ_የምትሰሩትን_ውደዱ፡፡

ውድ ተመራቂዎች !

አንድ ሊቅ እንዳለው መጥፎ ሰው ጥሩ ባለሙያ ሊሆን አይችልም መጥፎ ባለሙያም መልካም ሰው ሊሆን አይችልም፡፡ የተዋጣላችሁ ለሀገር ለወገን መከታ የምትባሉ ምሁር ባለሙያ የምትሆኑት የተስተካከለ ስብዕና ሲኖራችሁ ነው፡፡ ቅንነት ፣ ደግነት ፣ አዛኘነትን ፣ ታታሪነትን ፣ ለመማር ዝግጁነትና

#ፈጣሪን_መፍራትን_ገንዘብ_አድርጉ፡፡
#ብቻችሁን_ሁናችሁ_አስቡ_ስራላይ_ግን_ተባበሩ!

ልብ በሉ! በሀገራችን ብዙ ባለድግሪዎች አሉ ብዙ አዋቂዎች ግን የሉንም ብዙ ባለሙያዎች አሉን ችግር የሚፈቱ ግን ብዙ የሉንም ፣ ብዙ፡የሚናገሩ እንጂ ብዙ የሚሰሩ የሉንም ፣ ብዙ ስሜታውያን እንጂ ብዙ በምክንያትና በጥልቀት የሚያስቡ የሉንም ብዙ የሚወስዱ እንጂ ብዙ የሚሰጡ የሉንም፡፡

#እንግዲህ_እናንተ_የትኛውን_ቁጥር_ትጨምራላችሁ?!

የብዙዎቻችሁ ወላጆች የእናንተን ዕድል አላገኙም፡፡ እነርሱ ያላገኙትን ዕድል ለእናንተ ሰጡ ከዚህ በላይ የፍቅር ዕዳ የለምና ወላጆቻችሁንና ሀገራችሁን ውደዱ ሁሌም ስለደህንነታችሁን አስቡ፡፡ ለታላቅ ሀገራዊ ሐላፊነት እራሳችሁን አዘጋጁ፡፡

ሕይወት_በምዕራፍ_የተከፋፈለች_ናት፡፡

አንድ ምዕራፍ ሲያልቅ ሌላ ይከፈታል፡፡ በሕይወት ዘመናችሁ አንዱንና ወርቃማውን ምዕራፍ ዛሬ በስኬት ዘግታችኀል፡፡
እንኳን ደስ አላችሁ! ነገ ለራሱ ክፋቱ ይበቃዋል እንደተባለ ዛሬ ከወዳጅ፡ዘመዳችሁ ጋር ደስ ይበላችሁ፡፡

ደስታችሁን ቀድሱት፡፡ ያለ ልክ በመብላትና በመጠጣት ሳይሆን በሕሊና እርካታ ወላጆቻችሁን በማመስገን በልዩ ደስታ አክብሩት! ሂዱ ዛሬ ደስ ይበላችሁ!

በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ !
እግዚአብሔር ዘመናችሁን ይባርክ!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

#ሰበዝ ከሚለው
#የአለማየሁ_ዋሴ_እሸቴ መፅሐፍ በአንድ ወቅት ለተመራቂ ተማሪዎች ያደረገው ንግግር፡፡

እናንተስ የትኛው ቁጥር ጥጨምራላችሁ??? ከባድ ጥያቄ

@jahABP ነኘ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!

ከፈጣሪ ጋር ወደፊት🙏🙏🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY

Wallpaper

መልካምዕለተ ሰንበት
repost

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
በማግባቴ ደስተኛ ነኘ ይለኛል

ልንገርህ ወንድሜ የኔ ደስታ አጎት ያደረከኘ ጊዜ ነው፡፡

ህያብዬ አምላከ ቅዱስ ዑራዔል በጥበብ ያሳድግሽ😍😍😘😘😘

#ያአባቷ_ልጅ
AB PHOTOGRAPHY

Wallpaper

መልካምዕለተ ሰንበት


@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
የአሌክስ አብርሃም በጣም አድናቂ ነኘ ይህን ከዕለታት ግማሽ ቀን የሚለውን አዲሱን መፅሐፉን ለመግዛት ሔጄ በብዙ ምክንያት ሳይሳካልኘ ቀርቶ ነበር፡፡

ዛሬ ግን አንድ በጣም ምወደው ወንድሜ መጣና አሁን ከመሸ ይህን ለማንበብ የጓጓሁለትን መፅሐፋ ሰርፕራይዝ አደረገኘ😍😍😍😃😃😃😀😀በእመብርሃን ስም እንዴት ደስ እንዳለኘ አትጠይቁኘ፡፡

የመፅሐፉ የመጀመሪያ ገፅ ላይ እንዲህ ይላል....

"ሰው ለሚወደው ምንም ቢሰጥ ያንስበታል፡፡
አንተ ሁሌም ትለይብኛለህ ባነበብካቸው ስንቱን ቀየርክ፡፡
በዚህም መፅሐፍ ብዙሃንን እንደምትቀይር አምናለሁ፡፡

እወድሃለሁ ልክ አንተ እንደምቶደኘ፡፡
ለ....አብይ የማርያም ልጅ
ከ....ከሚወድህ "

ይላል😍😍🙏🙏

በጣም ደስ ብሎኛል ወንድሜ አመሰግናለሁ እንዲህ እንዳከበርከኘ አምላከ ቅዱስ ዑራኤል ያክብርልኘ፡፡

በመውደድ ግን አንተ ላይ አልደርስም ያንተ ይበልጣል፡፡

ከመፅሐፉ ጀባ እንደምል ቃል እገባለሁ፡፡

አቦ ሁሌም ደስታን ያሰማህ😍😍🙏🙏
ኢትዮጽያዊው ሊቅ ስለ አምላክ ልደት እንዲህ አለ.......🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂


ትላንት ብልቀው ከልብ ሆናችሁ አታነቡትም ብዬ አስቤ ነው....እኔ ሁሌም ደስ ስለሚለኘ በጣም ደስ ስለሚለኘ ላጋራችሁ ፈለኩኘ.....

ሊቁ ምን አለ ጠብቁኘማ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

የአምላክ ልጅ ከአንቺ ሰው ስለመሆኑ በአንቺም የከበርን እኛም ከምድር ወደ አርአያም በአንቺና በልጅሽ ስም የቀረብን ሆንን፡፡

የብርሃን ደመናዎች ከበቡሽ ሊቃነ መላዕክትና የመላዕክት ሠራዊት በመፍራት በመንቀጥቀጥ በፊትሽ ይቆማሉ፡፡
በዚህ ዓለም #ኪሩቤልና_ሱራፌል በሰማይ ካለው ምስጋናቸው አንድም ከቀድሞ ምስጋናቸው ይልቅ እጅግ ከፍ ባለ ምስጋና አመሰገኑሽ፡፡

ፍጥረቱን ኹሉ ሰብስቦ የያዘና ፍጥረቱን ኹሉ የሚመግብ ጌታቸው በእቅፍሽ ተቀምጦ ጡትሽን እንደ ህፃን ሲጠባ ባዩ ጊዜ በአርያም ፈልገውት በዚህ ዓለም እንደ ቀድሞ ከአባቱና ከመንፈስቅዱስ ጋራ አገኙት፡፡

የጌታቸውን ትህትና ባዩ ጊዜም ዐይኖቻቸውን ወደ አርአያም ከፍ ከፍ አደረጉ፡፡ ክንፋቸውንም ዘርግተው ለሁሉ ጌታ አንተ በሰማይ ምስጋና ይገባሃል እያሉ አምላካቸውን አመሰገኑ፡፡

ዳግመኛም በበረት ውስጥ አንቺን ከልጅሽ ጋር አይተው፡፡ "በምድር ላይ ሰላም ኾነ" አሉ፡፡
ከአንቺ የነሳውን የኛን ስጋ ለብሶ ባዩ ጊዜም
.
.
.
#ሰውን_ምንኛ_ወደደው_ብለው_ሰገዱለት፡፡

አንቀፀ ብርሃን ዘደረሰ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ኢትዮጽያዊ በመንፈስ ቅዱስ፡፡😍🙏🙏

መልካም የልደት በዓል

🤔😱🤔ምንኛ ድነቅ ነው ክብርሽ እናታችን

አምላካችን ሆይ በልደትህ የወጣትነት ዘመናችንን ባርክልን፡፡ ሁሉንም ለበጎ ነው ማለትን አስለምደን ያጣነው ነገር ሊጎዳን ይችል ነበርና እንኳንም አልሰጠኸን ስላልሰጠኸን ነገሮች ሁሉ ተመስገንል፡፡😍🙏😍

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD