AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
#ሐኑን
በዚያን ቀን በሰላም ወደቤቴ የተመለስኩት ፈጣሪ ጠባቂ መላዕክቱን ልኮ ጋርዶኘ መሆን አለበት፡፡ እንጂማ ያንን ተራራ የሚያህል ዱሩዬ እንዳይሸእ እንዳይለወጥ አድርጌ አበሻቅጬው እነኳን በሰላም መመለሴ በሕይወት መመለሴም አምር ነበር ግን ሆነ፡፡
ልክ የማደንዘዣ መርፌ እንደወጉት ሰው እኮ ነው ፍዝዝ ብሎ ሲመለከተኘ የነበረው እንኳን እኔ በዚያ ጋን ጋን በሚሸት ትንፉሹ እፍ ቢለኘ ሱሉልታ የምገኘ ላንጌሳ ቀርቶ መሳሪያ ለታጠቀ ፖሊስም የማይመለስ ጉድ ነው፡፡ የዛሬ ዓመት የፍርድቤት መጥሪያ ሊሰጠው የሔደው ፖሊስ አይደለም እንዴ ጆሮ ግንዱን በጥፊ አንድዶት ከነመሣሪያው ካፈር የቀላቀለው?! ቆቡን አንድ ቦታ የክላሽንኮቩ የጥይት መጋዘን ሌላ ቦታ ተበታትኖ ለቃቅመው ነበር በቃሬዛ የወሰዱት፡፡
ማዕረጉ ሳይቀር ከትከሻው ላይ ተነቅሎ በርሮ ትቦ ውስጥ የተገኘው፡፡ ምን እሱ ብቻ ጋሽ አለበልንስ ቢሆን እንዲህ ሁለት የፊት *ጥርሳቸውን በቡጢ አርግፎ የአፋቸውን የጋራዥ በር አስመስሎት የቀረው ማነው? ይኸው ወጠምሻ ዱርዬ ነው!!
የጋሽ አለበል ጥርር ማውለቅ (ማውለቅማ ወግ ነው) አረገፈው እንጂ) ምን እንዳነሳሳው ሲጠየቅ " በቀን አስር ጊዜ ሰላም እያለ አስመርሮኘ ነው!" አለ አሉ እስቲ ለእግዜር ሰላምታ ቡጢ መመለስ ምን የሚሉት እብደት ነው? ...ጋሽ አለበል ሚስኪን የሦስት ልጆች አባት *ናቸው፡፡ ጎረቤት ሁሉ "ሰላምታ ያብቃ ይከተት በጋሽ አለበል" *የሚልላቸው ሰላምተኛ!..ታዲያ አንድ ቀን ለምሳ ወደቤታቸው እየገቡ ይኼን ወመኔ መሃል መንገድ ላይ ቁሞ ያገኙታል፡፡ ባርኔጣቸውን ከራሳቸው ላይ አንስተው በአክብሮት ጎንበስ በማለት "ሰላም ዋልክ?" ብለው አለፉ ሰው መስሏቸው! አለፍ ከማለቱ ዱርየው እንደአንዳች ነገር ተወርውሮ ከኀላ ኮሌታቸውን ጨምድዶ ከያዘ በኀላ በዚያ የግንድ ጉማጅ በሚያክል እጁ በቡጢ ከመሬት ደባለቃቸው ፡፡
ሚስኪኑ ጋሽ አለበል ወደቁና እንደ ትል እጥፍ ዘርጋ እያሉ አፈር ላይ ተንፈራገጡ፡፡ በኀላ ነው ጥርሳቸው መርገፉን ያወቁት፡፡ ደግሞ አያፍሩም ሰው አግኘተው ሙተው ይሔን ዱርዬ ስሙን ኢዮብ አሉት፡፡ ስም አይገዛ! "ስምን መላዕክት ያወጡታል" ቢባልም ቅሉ የአንዳንዱን ሰው ስም ሲወጣ መላዕክት በአካባቢው ዝር እንደማይሉ የገባኘ በዚህ ሰው ነው፡፡
ሌላ ጊዜ ደግሞ እዮብ "ጌታን ተቀብያለሁ ከአሁን በኀላ ወንጌል ሰባኪ ነኘ!" አለና መፅሐፍ ቅዱሱን ይዞ እዚያችው ሁልጊዜ የሚቀመጥባት ድንጋይ ላይ ተቀምጦ አላፊ አግዳሚውን እያስቆመ ስብከት አይሉት ማስፈራሪያ ጀመረ፡፡
( #ሰው_ነፍሱን_ሲቀይር_እንዴት_ወንበሩን_አይቀይርም?)
ትተውው አይሔዱ ነገር ኢዮብ ሆነባቸው፡፡ ከሰማዩ እሳት በፊት የኢዮብ ቡጢ ትዝ እያላቸው ደግሞም ጋሽ አለበልን ያየ ኢዮብን ከኀላው አድርጎ እንዴት በሰላም ይራመዳል ብለው ቁመው ይሰሙት ጀመረ፡፡
መቼም ክርስቶስ ከተሰቀለ ወዲህ ወንጌልን እንዲህ አድርጎ የሰበከ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም! ድንገት አንዱ መንገደኛ ፊት መንገዱን ዘግቶ እንደ ጅብራ ይገተርና የደፈረሰ አይኑን አፍጥጦ "ኢየሱስ ጌታነው!"ሲልማነው ወንዱ የሚቃወም!? ጋሽ ሃምዛ እንኳን ሳይቀሩ ለጁሙዓ ሶላት ወደ መስጅድ እየተጣደፉ ሲሔዱ መንገድ ላይ አስቆማቸውና.....
"ጋሽ ሐምዛ!" አላቸው፡፡
"ለበይክ!"
ኢየሱስ ጌታ ነው! ቢላቸው
"እንግዲህ ከአንተ ጋር ስነዛነዝ ሶላት ከሚያመልጠኘ ይሁና ኢዮብ!" ብለው ወደመስጅዳቸው!! ወዲያው አንድ ወርእንኳን ሳይቆይ ይኼ ወጠምሻ 'ፓስተር' ደብድቦ ታሰረ፡፡ "ለምን ፓስተሩን ደበደብክ?" ቢባል "ክፉ መንፈስ አለብህ ብሎኘ ነው!" አለ፡፡
ከእስር ሲፈታ መፅሐፍ ቅዱሱን ጣጥሎ ወደመጠጥ ቤት ተመለሰ፡፡
#እንዳገረሸበት_ዱርዬነት_አደገኛ_ነገር_የለም ባሰበት! ዓምደ ሚካኤል የሚባለው የሰንበት ትምህርት ቤት ኃላፊ ሳይቀር "ከዚህስ ያንኑ የመናፍቅ ስብከት ቢሰብከን ይሻል ነበር!" እስኺል ድረስ፡፡ ይኸው ሲጠግብና ሲሰክር አላፊ አግዳሚውን እየደበደበ እጁ ላይ ሳንቲም ሲያጣ እየነጠቀ ቦዝኖና ተመችቶ ይኖራል፡፡
ይህንን ጉድ ነው እንግዲህ እንዳይሞት እንዳይሽር አድርጌ በስድብ አጥረግርጌው በሰላም ወደቤቴ የተመለስኩት፡፡ ያውም እቤቱ ሔጄ "እፈልግሃለው ና ውጣ ብዬ፡፡
ምን አገናኛችሁ?! የሚል አይጠፋም መቸስ...ጎዶሎ ቀን ነዋ!
ኢዮብ፡የባለቤቴ ታላቅ ወንድም ነው፡፡ የመጀመሪያ ልጃችንን የወለድን ጊዜ እንደወጉ "ቁርጥ አባቱም!" ከሚለው አራስ ጠያቂው ይልቅ ኢዮብ አጎት ሆነ! ባዩ ይበዛ ነበር፡፡ ሰው፡የመናገር ነፃነትን የሚነፍገው አምባገነን መንግስት ብቻ ይመስለዋል #በየመንደሩ_ስንት_ጥቃቅን_አፋኘ_አለ!
ታዲያ አንድ ቀን ይሔ አፄ በጉልበቱ የማይታለፍ መስመር አለፈ እነኳን፡አንድ የመንደር ዱርዬ ሞቶ እራሱ መጥቶ እፊቴ ቢቆም የማልደራደርበትን ጉዳይ ዘነኮረ....አበድኩ፡፡ እግሮቸ እንደ እግር ሳይሆን እንደ እንፍ አብርረው ወደ ቤቱ ወሰዱኘ ያውም ከስራ እንደወጣሁ ሙሉ ልብሴን ከነከረቫቴ ግምጥም አድርጌ ለብሼ፡፡
ሰው አገሩ ሲነካበት አሮጌ ጠብመንጃ ከሰማይ ከምድር ከገዘፈ ጠላቶቻችን ጋር የሚፉለመው #ከጀግንነት_ይልቅ_በፍቅር_ተገፍቶ_መሆኑን ያወቅኹት በዚያች ቀን ነው፡፡ ኢዮብን እየተንጠራራሁ አንባረኩበት...ማነኘ ነው የምትለው!? አልኩት መንደር ለመንደር እየዞርክ ማንንም ስላስፈራራህ የምፈራህ መሰለህ ወይ? አልኩት ወይ እኔ ወይ አንተ እንሞታለን ኝንጂ ፍርሃትየሚባልየለም አልኩት፡፡
ኢዮብ ቢጨንቀው ብጢውንም ጡጫውንመ እረስቶ...የተወውን ሃይማኖተኘነት አስታወሰና "ኧረ ጌታ ይገስፅህ አለኘ!"፡፡ በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜም አንድ እርምጃ ወደኀላ አፈገፈገ፡፡ እኔም በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጠብና ለጠብና ድብድብ አንድ እርምጃ ወደፊተ ተራመድኩ፡፡ ከዚህ ሁሉ ጩኸት በኀላ ግንየምለው የምናገረው አልቆብኘ በእልህ እየተንቀጠቀጥኩ ማለት የቻልኩት
"#ምን_አደረገቻቹ!" ብቻ ነበር፡፡
ከሁለት ዓመት በፊት መደረግ የማይገባውን አደረግሁ፡፡ ጉዳዩን የሰማ ሰው ሁሉ "ተሳስተኅል" ይለኛል፡፡ መሳሳቴንማ ገና ድሮ ገና ነው፡ያወቅሁት፡፡ ምክር ፈልጌ ስሔድ ፍርድ አሸክመውኘ እመለሳለሁ
#ከመምከር_ይልቅ_መፍረድ_ቀላል_ሳይሆን_አይቀርም፡፡
አገር ምድሩ እኔ ላይ ለመፍረድ የተሰየመ ችሎት እስኪመስል እስትንፋስ ያለው ሁሉ እኔ ላይ ፈረደ፡፡ እግዜር የፈጠረው ሳር ቅጠሉ ሁሉ ጠበቃና ዳኛ ሆነ፡፡ ነገሩ የጀመረው ከቤት፡ነው ሚስቴ ሄራን ገና ከጅምሩ እኔ ላይ ፈረደች፡፡
"ምን ታድርግ እውነት አላት" ብዬ ዝም አልኩ፡፡ ቤተሰቦቼ እኔ ላይ ፈረዱ፡፡
ያው መቼስ #ለልጅ_የሚወረወር_ድንጋይ_ወላጅን_ልብ_መውገሩ_አይቀርምና የወላጅ ፍቅራቸው ነው ያበሳጫቸው ብዬ ቻልኩ፡፡ እንዲያውም አባቴ ቁጣው ገንፍሎ እንዲህ አለኘ.....
"ስማ ይሔ ነገር ወዲያ እልባት አበጅተህ ካላረፍክ እደጄ እንዳትረግጥ አባቴ ብለህም እንዳትጠራኘ አልበዛም እንዴ!? ...ከዛሬ ነገ ልጅነትህህ ሲያልፍ ልብ ትገዛለህ ብለን ዝም አልን፡፡ አንተ ጭራሽ እሰይ! የተባልክ ይመስል አድሮ ቃሪያ ከርሞ ጥጃ ትሆናለህ በዘራችን የሌለ መልከስከስ ከየት አመጣኸው!? ከሌለው ይቅር በሥራ ቦታህ ያለህበት ደረጃ ቀላል ነው እንዴ? እንዴተት ለራስህ አክብሮት አይኖርህም!?
በቃ ውስጤ በአባቴ ተቀየመ...ከወላጆቼ ቤት ቀረሁ፡፡

ጓጀኞቼ እኔ ላይ ፈረዱ፡፡ ሲጀመር "ተው!" ብለው ሲመክሩኘ አልሰማኀቸውም ፍርድና ግሳፄያቸው የሚገፋ ወኔ አልነበረኘም፡፡ እንዲያውም የቅርብ የምላቸው ጓደኞቼ ቀስ እያሉ ከእኔ ራቁ፡፡ የሚስቴ ስሞታ ሰልችቷቸው መሆን አለበት፡፡ ጉዳዩን የሰሙት ሁሉ እኔ ላይ ፈረዱ፡፡ ገና የሚሰሙትም እኔ ላይ ይፈርዳሉ አውቃለሁ፡፡ እኔ ራሴ በየቀኑ በየሰዓቱ ከምተነፍሰው አየር እኩል ጸጸት ከቦኘ እውላለሁ አድራለሁ፡፡
አዎ እኔ ራሴ ራሴን እወቅሳለሁ፡፡
በዚህ ሁሉ ወቃሽ ስዋከብ ያልወቀሰችኘ እንደውም የምታፅናናኘ አንድ ሴት ብቻ ነበረች....... #ሐኑን
"ሐኑን ማለት ምን ማለት ነው?" አልኳት የተዋወቅን ሰሞን፡፡
እሷም፡- *እንዲህ ብላ አብራራች
ይቀጥላል...........
አሌክስ አብርሐም፡-ከዕለታት ግማሽ ቀን
*ምልክት እኔ እንደጨመርኩባቸው ልብ ይሏል
@jahABP ነኘ መልካም አዳር የነገ ሰው ይበለን
😍🙏😊
@ABPGD @ABPGD @ABPGD

"ሐኑን ማለት ምን ማለት ነው አልኳት?" የተዋወቅን ሰሞን፡፡
"በሁለት ቋንቋሁለተ ትርጉም ያለው ስም ነው ይላሉ" ብላ አብራራችልኘ! በሱማሊኛና በአረብኛ
ደግሞ የስሙ ትርጉም መራራቅ፡
ሲላላ #ህመም ጠበቅ ተደርጎ ሲነበብ '#ጣፋጭ' ማለት ነው አሉ፡፡ እኔ ከራሴ ውጣ ውረድ ተነስቼ ሁለቱን ትርጉም አቀላቀልኩት
'#ጣፋጭ_ሕመም!!'
ሐኑን ጣፋጭ ህመሜ ነበረች፡፡ ልክ ሐኪም በእጅ እንዳትነኩት ያለን *ቡግንጅ በእጅ መንካት እያመመ ደስ እንደሚለን ዓይነት የሆነ ቀን ከቡጉሩ ውጪ ሌላ ሰውነት የሌለ እስኪመስለን ድረስ እጃችን አስር ጊዜ ወደዚያው እንደሚሮጠው አይነት፡፡ የነፍስ እጆቼ ወደ ሐኑን እንደተጠራሩ ነበር፡፡
የበደልኳት እሷን ነው እሷን ብቻ፡፡ አንድም ቀን በደሌን አንስታ ወቅሳኘ የማታውቀውምእሷ ብቻ ናት፡፡ እንደው በሰራሁት ሥራ ልክ "ይወገርም ይሰቀልም" ተብሎ ቢፈረድብኘ አንደኛ መውገሪያ ድንጋይ አንስታ ከወጋሪው ሰልፍ ፊት መገኘት የነበረባት እሷ አልነበረችም እንዴ!? የመስቀያ ገመዴን ሸምቀቆ አንገቴ ላይ ማጥለቅ የሷ ሐቅ አልነበረም እንዴ!? ግን ባየችኘ ቁጥር ትልልቅ ዓይኖቿ ሰማይ ከፍቶ ብቅ እንዳለ መልአክ በክብርና በጉጉት እያዩኘ ንፁህና ደግ ፈገግታ ከፊቷ ሳይነጥፍ የምትቀበለኘ እሷ ነበረች እሷ ብቻ!! ይሔ ቻይነቷ ህመሁ አይጣል ነው፡፡
ሳስባት ያመኛል፡፡ በአካል ሳገኛትም ያመኛል፡፡ ከዚህ ህመህ የምፈወስበት አንዳች መድሀኒት ባገኘ ህይወቴን እከፍላለሁ፡፡ ግን ምን ያደርጋል ዚሪያዬን የከበበኘ ሁሉ ስንጥሩን ይዞ ወደ ቁስሌ የሚልክ "የሚያደክም አጽናኘ!" ብቻ ሆነ፡፡
እግዚአብሔር በሚያውቀውከባለቤቴ የደበቅኀት አንድም ነገር አልነበረም፡፡ ሐኑን ከእርሷ በፊት የነበረች ፍቅረኛዬ ነበረች፡፡፡ ከሀ እስከ ፐ ታሪካችንን ለምነ እንደተለያየንም ጭምር ታውቃለች፡፡
#አሁን_ምንም_አይነት_የፍቅር_ግንኙነት_የለንም፡፡ ግን የኔ እርዳታ ስለሚያስፉፍጋት ልርቃት አልችልም፡፡ መደገፍ ስላለብኘ እደግፋታለሁ፡፡ ድጋፌ ብር ያውልሽ እያሉ መወርወር ብቻ አይደለም እንደሰው ከጎና መቆም እንጂ፡፡
ይሔንንም ባለቤቴ ጠንቅቃ ታውቃለች፡፡ ቅንነት #ከጎደለው_እውቀት_አለማወቅ_ይሻላል፡፡
ይህንን የነገርኳት የነገርኳቶ ገና ሳንጋባ በፊት ነበር፡፡ የመለሰችልኘ መልስ እስካሁን ጆሮዬ ላይ ያቃጭላል፡፡
"ምን ነካህ?! ይኼ እክ ምንመ ማለት አይደለም ማንኛችንም ችግር ሊያጋጥመን ይችላል፡፡ ደግሞም አምንሃለሁ አትጨናነቅ! እንዲያውም ዕድሉን ከሰጠኸኘ እኔም ልረዳት እችላለሁ" ቃል በቃል እንዲሁ ነው ያለችኘ፡፡ ንግግሯን ከሴቶች ሁቹ ከፍ ያለች አስተዋይ ደግ አድርጌ እንድመለከታት አድርጎኛል፡፡ ከተጋባን በኀላ ግን ነገሮች በሚያስደነግጥ ፍጥነት ተቀያየሩ ፡፡
ስለ ሐኑን ከእኔና ከሔራን ቤተሰቦች አልፎ ጓደኞቼ ሁሉ ሰሙ፡፡ ሰላም የሚባል ነገር ከቤታችን ጠፋ፡፡ በተለይ ከወለደች በኀላ፡፡ አንድ ቀን "ሐኑንን ሰሌም ብያት ልምጣ በዒያውም የቤት ኪራዩን ብር ላቀብላት" ብዬ ለመሔድ ስነሳ
"ፍቅር!" አለችኘ፡፡ ስትጠራኘ እንዲህ ነው፡፡
"ወይዬ!" አልኩ፡፡ ያው የተለመደውን "ተጠንቅቀህ ንዳ እናእንዳታመሽ!" ምክር ነበር የጠበቅሁት፡፡
እስከመቼ ነው ይችን ልጅ የምንረዳው? ምንድነው መጨረሻው? አትማርም አትሰራም እሺ ይሁን መርዳት ካለብህ እርዳት ለምም የሚያስፈልጋትን ነገር አትልክላትም? በአካል መገናኘቱ ለምን አስፈለገ?" አለችኘ፡፡
ሐኑን ከዛ በፊት "ይቺ ልጅ!" ብላ ጠርታት አታውቅም ነበር፡፡ ልለብስ ያዘጋጀሁትን ኮት፡እንዳንጠለጠልኩ በግርምት ዙሬ ተመለከትኳ፡፡ ፊቷአይቼው በማላውቀው ምሬት ተጥለቅልቋል ዓይኖቿን ከእኔ ላይ ዞር አደረገች፡፡
"እንዴ ከምርሽን ነው?" ብዬ ጠየኳት ተገርሜ፡፡
"ከምርሽን ነው ፤ሐት ምን ማለት ነው? የግድ አፍ አውጥቼ መናገር ነበረብኘ? እንደሌሎቹ ሚስቶች መጨቃጨቅ ነበረብኘ!?
"እንደዛ ማለቴ ሳይሆን...."
እና እንዴት ማለትህ ነ? ምን ማለት ነው 'ከምርሽን ነው ወይ' ማለት? ልክ ተአምር ነገር እንደተናገርኩ የምትገረመው ለምንድነው? ከዚህ በኀላ ባታገኛት ደስ ይለኛል በቃ! ሁሉም ነገር ችክ አለው፡፡ ሥራ መስራት ካለባት ትስራ ማግባት ካለባትም ካለባትም አንዱን ታግባ" ንግግሯ ምሬት የተቀላቀለበት ከጥያቄ ይልቅ ወደ ትዕዛዝ ያዘነበለ ነበር፡፡
ያነሳሁት ኮቶ ሶፋው መደገፊያ ላይ ጣል አድርጌ ከተቀመጠችበት ሶፋ ፊት ለፊት ያለ ክብ፡የመስታወት ጠረቤዛ ጫፍ ላይ ፊት ለፊቷ፡ተቀመጥኩ፡፡ ጉልበታችን ሲነካካ እግሯን ወደኀላ ሰብሰብ አደረገች! በውስጤ "በእርግዝናና በወሊድ ወቅት የሴቶች ሆርሞን መጠነኛ የባህሪ ለውጥ እንደሚያስከትል" ያነበብኩትን እያስታወስኩ ላረጋጋት ሐሳብ ሳሰባስብልክ ያሰብኩትን ቀድማ ያወቀችው ይመስል(አወቀች እንጂ)
"ምነ እንደምታስብ ይገባኛል ሆርሞን ምናምን ብለህ ልላፅናናኘ እንዳትሞክር፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ እዚያው ስለ ወንድነትህ ሆርሞንህ አስብ፡፡ በየትኛውም 'ሎጂክ ቢሆን እያደረከው ያለው ነገር ልክ አይደለም፡፡በቃ! ቤተሰብ ቀልድ አይደለም! ትዳር ነው ይኼ!!"
ግራገባኘ ሐኑን በራሷ በባለቤቴ ጥሪ በሰርጋችን ዕለት አብራን ነበረች፡፡ ቤታችን ውስጥ ዝግጅት ሲኖር ባለቤቴ እየጠራቻት ትመጣና በደስታውም በሀዘኑም አብራነ ስታሳልፍ ቆይታለች፡፡ በእርግጥ ሐኑን ከባለቤቴ ጋር ባትገናኘ ደስ ይለኘ ነበር፡፡ ምክንያቱም ለሳር ለቅጠሉትሁትና የሚመች ፀባይ ያላት ባለቤቴ ሔራን ሐኑን ላይ ሲሆን ትንሽ የሚጫን ባህሪ አላት፡፡
ለእኔ ብቻ የሚገባ ውስብስብ የሆነ ባህሪ ነው፡፡ ግን አንዴ ከተዋወቁ በኀላ ባለቤቴ እራሷ እየደወለች በአካልም እያገኘቻት ልክ እንደጓደኛ ስለተበራረቡ ምንም ማድረግ አልቻልኩም፡፡ ብናገርም ሌላ ጥርጣሬ መፍጠር ነው ብዬ ዝም አልኩ፡፡ ቢሆንም ግን የባለቤቴና የሐኑን ጓደኘነት መቼም ቢሆን ተውጦልኘ አያውቅም! እሳትና ጭድ፡፡
"አምነሽበት? ምኑን ነው የማምንበት? እንዴት ነው የምታስበው?በዚህ በሰለጠነ ክፍለ ዘመን ባሌ እንደድሮ ሰው በትዳሩ ላይ ቅምጥ ማስቀመጡን ነው የማምንበት ይሔን ነው የማምንበት? በቃ! ከዚህ በኀላ ይሔ ነገር መቀጠል የለበትም፡፡ የባንክ አካውንት ከፍተህም ቢሆን፡የምትፈልገውን ብር አስገባላት፡፡
እያወጣች ትጠቀም ጤነኛ ናት! እየሔድክ በማንኪያ አታጎርሳትም፡፡ እንደውም እንደሴቶቹ ሂዳ ትስራ አረብአገር የሚልኩ ሰዎቹ ጋር ላገናኛት እችላለሁ! ከዚህ በኀላ በምንም መንገድ ከእሷ ጋር እንድትገናኘ አልፈልግም፡፡ ሁሉም ነገር ልክ አለው በቃ!"
ጩኸቷና ቃል አባይነቷ ግልፍ አደረገኘ! እናም ኮስተር ብዬ ሶሪ አልችልም አልኳት፡፡
"ምን ማል ነው አልችልም? ይሔ እኮ ጥያቄ ወይም አስተያየት አይደለም! ህጋዊ ባለቤትህ ነኘ! ሳንጋባ በፊት ስለነበረው ነገር አይመለከተኘም ከተጋባን በኀላ ግን አያገባሽም እያልክ ብቻህን መወሰን ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው!?
የበፊት ፍቅረኛህ አዲስ አበባ ድረሰ አምጥተህ ቤት ተከራይተኸ ማኖርህ ' እሽ ይሁን' ብዬ ተቀበልኩ በየወሩ ገንዘብ ተቆራጭ ማድረግህንም ድሁን ብዬ ፈቀድኩ ይሔን ሁሉ የተቀበልኩ መብትህ ስለነበረ አይደለም ከራስህ እንዲመጣ ስለፈለኩ እንጅ! ጭራሽ በየጊዜው እቤቷ እየሔድክ መዋልና ማምሸትህን አቁም ስላልኩህ አፍህን ሞልተህ 'አልችልም' ትለኛለህ እንዴ? እኔን ብትንቅ እንኳን ለልጅህ ስትል ትዳርህን አታከብርም ብላ ቤቱ እስኪናወጥ ጮኸች፡፡

ገና የሁለት ወር ልጅ ምነው ተወልዶ ሰበብ ባደረኩት ብላ የጠበቀችው ነው የሚመስለው፡፡ "ልጅህ" ስትልአቅፋ ጡትየምታጠባውን ልጅ ስለናጠችው መጥባቱን አቁሞ ጭርር ብሎ አለቀሰ፡፡ ለማጥባት ሳይሆን አፉን ለማዘጋት በሚመስል ሁኔታ የጡቷን ጫፍ አፉ ውስጥ በእልህ ወተፈችበት፡፡ ሊያለቅስ የሳበውን አየር ወደ ውጪ እንኳን ሳያወጣ አጉረምርሞ ዝም አለ፡፡ አፍና የገደለችው ነበር የመሰለኘ፡፡ ማመን አልቻልኩም፡፡ ይሔን የተናገረችው ባለቤቴ ሔራን ናት ብዬ ለመቀበል ተሳነኘ፡፡
ዝም ብዬ አየኀት! ዙሪያዋን የተዝረከረከው ማቀፊያ ልብስ ጡጦ እና ምናምን ሁሉ በቁጣ በታትናው ልጃችንን አቅፋ እያለቀሰች ወደመኘታ ቤት ገባችና የቤቱ መሰረት እስኪነቃነቅ በሩን በእግሯ ወደኀላ ወርውራ ዘጋችው፡፡ ጓ....!
ሳሎን መሐል ተገትሬ ቤቱን ቃኘሁት፡፡ ችግር ችግር ሸተተኘ፡፡ አደጋ አደጋ፡፡ ቤታችን ከግድግዳ ሳይሆን ከአራት ቋሚ ችግሮች የተሰራ የመብረቅ ጣሪያ ከላይ የዠደፋብኘ መሰለኘ፡፡
የዘራሁት ሀጢያት ማቆጥቆጥ እንደጀመረ ገባኘ፡፡ ለመቶኑ ሐኑን ብር በባንክ ብልክላትና ሁለተኛ አልመጣም ብላት(አልላትም እንጂ) ም# ይሰማት ይሆን?
ሐኑን.....ሐኑን.....ሐኑን.....የቀጠፍኳት
የቀጠፍኳት አበባ መዓዛዋ አስክሮኘ ውበቷ፡አስክሮኘ ጨብጫት ኖሬ ወደቀልቤ ስመለስ እና የጨበጥኩትን መዳፌን ስዘረጋ እፍኘ ሙሉ እሾህ ተሰክስኮበት ያውም የሚንገበገብ እና የሚመረቅዝ ቁስል ፈጥሮ አገኘሁት፡፡ አላርፍ ያለ መዳፍ፡፡
ይቀጥላል........
አሌክስ አብርሐም፡- ከዕለታት ግማሽ ቀን
@jahABP 😍🙏😊 ነኘ መልካም አዳር ተመኘሁ፡፡

ታዲያ ስለፖለቲኮ ሲወራ በብስጭት ወደ እኔ እየተመለከተ "ፖለቲካ ሸር*ጣ ነው.....! ተመልከት.............
ጠብቁኘማ🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂
ጠብቁኘማ🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
ታዲያ ስለፖለቲኮ ሲወራ በብስጭት ወደ እኔ እየተመለከተ "ፖለቲካ ሸር*ጣ ነው.....! ተመልከት.............
ከንጉሱ ጀምሮየፖለቲካ እሳት ደሃውን እንጂ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉትን መሪዎች አቃጥሎ አያውቅም፡፡ ካላመንክ አንድ በአንድ እያነሳን እንጫወት....እዚህ ሀገር ተምሮና ተንደላቆ፡የሚኖረው ብዙሃኑ 'ግፋ በለው!' ሲል የኖረ ነው፡፡
መንግስቱ ኃይለማርያምን ያንን ሁሉ የድሃ ልጅ ማግዶ እሰሱ ዛሬ የት ነው? 'ዚንቧቡዌ' ተንደላቆ ይኖራል፡፡
የኦነግ መሬዎች ተመልከት ወያኔዎችን ተመልከት...ምን ሆኑ? ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም የእርስ በእርስ ጦርነት ወጣቱ ነው ሚማገደው! ሚስኪን ወጣቶች! በፕሮፖጋንዳ ያበደ አለማስተዋል ነው፡፡ ወጣት አልዋጋም ካለ መሪዎች ሲጨባበጡ ነው የምታገሣቸው! እንዲች ብለው ስንጥር አያነሱም፡፡
ስንት ደም መጣጭ! ስንት ጓደኞቻችን በረኻ ላይ ቀሩ! ስንት 'ጂኒየሶች"'እነኳን ጦርነቱን የፖለቲካ ወሬው ያደነዝዝሃል፡፡ ከዚሀ ከበከተ እንቶፈንቶ ራቅ! ተማር! አሁንም ተማር! ማንም መሀይም መተኮስ ይችላል! መግደል ጀብዱ አይደለም ጅብም ሰው ይገድላል ታይፎድም ወባም ሰው ይገድላሉ!
#ዓላማ_የሌለው_ሞት_አገር_ሸርፎ_ከመሸጥ_እኩል_ነው፡፡
ለምንድነው የምትሞተው? ለምንድ ነው ወጣት የሚሞተው?.....ሊታረድ እንደሚነዳ በሬ የማይረባ ተስፋና ጥቅማጥቅም እንደ እርጥብ ሳር እያሸተቱ ወጣቱን ወደ ቄራ ይወስዱታል፡፡
ወጣቱም ብልጥ የሆነ ከሌላው የተለየ የገባው የረቀቀ የመጠቀ አድርጎ ራሱን ያያል ሲስተሙ ነው እንደዚያ የሚያደርግ፡፡ ከአንተ በላይ አዋቂ የሌለ መስሎ እንዲሰማህ....አለፍ ብለህ እጅህን ስትዘረጋ አረፋ ነው፡፡ ፖለቲካ እንኳን ይዘቱ ቅርፁ ለማንም ገብቶ አያውቅም ፈሳሽ ውሃ ነው ቅርፅ የለውም አንተ ውስጥ ሲገባ አንተን እኔ ውስጥ ሲገባ እኔን....
#ሁላችንም_ብርጭቆዎች_ነን፡፡
በስልጣን ከፍ ያሉት እያጋጩ 'ችርስ' የሚባባሉብን፡፡
አሌክስ አብርሃም፡- ከዕለታት ግማሽ ቀን
@jahABP ነኘ መልካም አዳር
😍🙏😍
ቦለቲካችን

✋ጣቶቹ✋
😔😔😔😔😔😔 ስንት አይነት ሚስኪን ነፍሶች አሉ ይሆን😭😭😭😭😭
ጠብቁኘማ🚶♂🚶♂🚶♂🚶♂😔😔
😔😔😔😔😔😔 ስንት አይነት ሚስኪን ነፍሶች አሉ ይሆን😭😭😭😭😭
ጠብቁኘማ🚶♂🚶♂🚶♂🚶♂😔😔
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
🤚ጣቶቹ🤚
"ቆንጆ ነኘ ወይስ አይደለሁም?" የሚል ጥያቄ ድንገት አእምሮዬ ውስጥብልጭ ያለው ልክ የዛሬ አለመት አካባቢ ነበር፡፡ እስከዛሬም በየቀኑ በየሰዓቱ ጥያቄው በውስጤ ያቃጭላል፡፡ አንዳንዴ እንደውም የሆነ ሰው ጠርቼ "ለመሆኑ ቆንጆ ነኘ ወይስ አይደለሁም?! ብዬ መጠየቅ ያምረኛል፡፡ የራሴን ፊት ማየት ናፍቄያለሁ፡፡
የራሴን ፈገግታ የራሴን ጥርሶች የራሴን ከናፍርት የራሴን አይኖች አፍንጮች ብቻ መልኬን ማየት ክፉኛ ፈልጌያለሁ፡፡ በጣም ፈልጌያለሁ፡፡ በጣም ፈልጌያለሁ፡፡ አንዳንዴ ፊቴን ሳስበው የተጨማደደ ቆዳ ብነካው ለእጄ እንደቆረቆረ የሚሻክር ከንፈርና ግራ ጉንጬ ላይ የሚያዳልጥ ስፋቱ ስሙኒ የሚያህል ጠባሳ የሚኖረው ይመስለኛል፡፡
ግን በቀኘ እጄ ጣቶች ፊቴን ስዳስሰው የሚያጋጥመኘ ሌላ ነው፡፡ እንደተባዘተ ጥጥ የሚለሰልስ ቆዳ!! የቆዳዬ ልስላሴ ለራሴመ ያስደንቀኛል፡፡ የፊቴም ቆዳ የእኔ አይመስለኝም፡፡ እጄ የሌላ ሰው ፊት ላየ ያረፈነው የሚመስለኘ፡፡ ታዲያ ከራሴ ቆዳ ጋር በፍቅር የወደቅሁ ይመስለኛል፡፡ ደጋግሜ የቀኘ እጄን መዳፍ ጉንጬ ላይ በቀስታ አንሸራተዋለሁ ጣፋጭ ደስታ እንደ ማር በውስጤ ሲፈስ ይሰማኛል፡፡
ጣቶቼ ምላስ ሆነው የቆዳዬን ወለላ የቀመሱ ዓይነት፡፡ የዓይነ ኔ ሽፋሽፍት የቅንድቤ ለስላሳ ጸጉር በጣቶቼ ስዳብሳቸው የሚሰማኘ የሐሴት ወደር የለውም፡፡ መልኬን እንደ ብሬል ፅሁፍ በጣቴ ነበር የማነበው፡፡ ከራሴ ጋር ፍቅር የጀመረኘ ልክ የዛሬ ዓመት አካባቢ ነበር፡፡
#ምንም_ይሁን_ምን_መኖር_ጥሩ_ነው!፡፡
"መኖር ምናባቱ!" ብለን በገዛ ፈቃዳችን ነፍሳችንን ከስጋችን ለመለየት ፈራ ተባ ስንል ሕይወት #የተስፋ_ቅንጥብጣቢዋን_በኑሮጎዳናችን_ላይ_እየጣለች እንደ ለማዳ ውሻ ታስከትለናለች፡፡እንጂማ ገና መቼና መቼ የሰው ልጅ እራሱ አጥፍቶ ይችን ዓለም ዳዋ በወረሳት ነበር፡፡
#መኖር_ትልቅ_ሱስ_ነው፡፡
ይኸው ወፈሰማይ ኑሮ ሱሰኛ የዕድሜ ሲጋራውን ለኩሶ የመኖር ሱሱን ሲያሷርፍ በአፍና በአፍንጫው ተስፋን ይምጋታል፡
#አዲስ_ዛሬን_ወደ_ውስጡ_እየሳበ_የተቃጠለ_ትላንቱን_ወደውጭ_ይተነፍሰዋል፡፡
ለዚያ ይሆን እንዴ አየሩ ነበር ነበር የሚሸተው? የሚበዛው ሰው ልክ እንደ ሲጋራ ርጋፊውን የታሪክ ውጭቱ ላይ እየተረኮሰ የነገ ጀምበሩን በጉጉት ሲጠብቅ እጁ ላይ እድሜ ተቃጥላ ትከስማለች፡፡
#ቢሆንም_መኖር_ያሳሳል፡፡
እግዜርን መቼም ከአንደ ዓመት በፊት ግለኘ "ግደለኘ" እያልልኩ ደጋግሜ የፀለይኩትነ ጸሎት ሰምቶ አሁን ከተፍ ቢልና "ልጄ ሆይ ተነሽ እንሒድ" ቢለኘ "ቀልድ አታውቅም እንዴ!?" የምለው ይመስለኛል፡፡ መኖር ያሳሳኘ ከጀመር አንድ ዓመት አካባቢ ሆነኘ፡፡
ከሰኞ እስከ ዓርብ ድረስ በመንደሩ ላይ ከባድ ዝምታ ይረበብበታል፡፡ ሕፃናት ትምህርት ቤት አዋቂዎችም ወደየሥራቸው ይሔዳሉ፡፡ ሥራ የሌላቸው ጠራራውን ሽሽት በየቤታቸው ስለሚከተቱ የሰው ድምዕ አይሰማም፡፡ ከቅርብ እርቀት(ሰፈራችን ካለው ትዝታ ሙዚቃ ቤትየሚባል የተከፈተ) ሱዳንኛ ዘፈን ይሰማኛል፡፡
ሱዳንኛ ዘፈን ስሰማ አገሩ በረሃ የሆነ ነው የሚመስለኘ፡፡ ሁሉም ሰው ትቶኘ ወደሆነ ሀገር የተሰደደ ብቻዬን የቀረሁ እየመሰለኘ እፈራለሁ፡፡ አለ አይደል ሁሉም ሰው እኔ ሳልሰማ በምልክት እና በጥቅሻ ተጠራርቶ ወደ ሱዳን የተሰደደ "ሳትሰማን እንሒድ እሷን ማን ይጎትታታል!" እየተባባለ እግሬ አውጪኘ ያለ፡፡(የሚያወጣ እግር ያላቸው፡፡) ታዲ? እንዲህ ሰፈሩ ጭር ሲል ሁሉም ሰው ትቶኘ ወደ ሆነ ሀገር የሔደ እየመሰለኘ መፍራት ጀመርኩ አንድ ዓመት አካባቢ ሆነኘ፡፡ የሰፈሩን ሰው ሁሉ በስም እየጠራሁ "አላችሁ ወይ" ማለት ያምረኛል፡፡ "እስቲ ካላችሁ...ጣታችሁን አሳዩኘ!"
በፊት በፊት ይኼን ዝምታ አልወደውም ነበር፡፡ ስልችት ነበር የሚለኘ፡፡ አሁን ግን ዝምታው እንደነፍስ ሙዚቃ ከሩቅ እንደሚሰማ ኅብረ-ዜማ ሆኖ ውስጤን በደስታ ያከንፈዋል ተፍነክንኬ ሳላበቃ ደግሞ ውስጤን በድንጋጤ ትርክክ የሚያደርግ ስጋት ይፈጥራል፡፡ ደስታም ሆነ ድንጋጤው የሚነዝር ነገር አለው፡፡(ሰዎች ሲያወሩ ከእግር ጥፍሬ እስከ እራስ ፀጉሬ ነዘረኘ እንደሚሉት) "የደስታሽም ሆነ የድንጋጤሽ መነሻ ምንድነው?" ብባል መልስ የለኘም፡፡ ከመሬት ተነስቼ መደሰትና ከመሬት ተነስቼ መደንገጥ ከጀመርኩ አንድ አመተ አካባቢ ሆነኘ፡፡
አፅናፍ ነው ስሜ አዕናፍ ብሎ ስም ማን ያወጣልኘ ማን እንደሆነ እግዜር ይወቅ፡፡ ምናልባት እናቴ አባቴ ወይም አንዱ መንገደኛ ይሆናል፡፡ ዞሮ ዞሮ ስሜን ያወጣው ሰው በከንቱ ደከመ፡፡ ማንም ሰው በዚህ ሰው ጠርቶኘ አያውቅም፡፡ በስሜ መጠራት ይናፍቀኛል፡፡ "አፅናፍ" ደህና አደርሽ!?" አፅናፍ ሰማም ነው!? " "አፅናፍዬ...." እንዲህ ብባል ብዬ ለራሴ አስባለሁ፡፡ አንዳንዴ ስሜን ሳስበው "አሁን እኔ ምኔ አጽናፍ ይመስላል?" እላለሁ
አፅናፍ ማለት ራሱ ምን መምሰል ነበረበት?ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ስሜ አጽናፍ መሆኑን ያወቅሁት መቼ ይሆን? ማንም ሰው ስሙ የራሱ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያውቀው መቼ ነው? ስም ያወጣልልን ልኛውቅ እንችላለን ግን በስማችን ስንጠራ አቤት ማለት መቼ እንደጀመርን አናስታውስም፡፡
#ሰዎች_እኮ_ሚስኪን_ነን_ስናሳዝን!
ለሁሉም ሰዎች ማዘን ከጀመርኩ አንደበት አመት አካባቢ ሆነኘ፡፡ ለማይታዘንላቸውም ጭምር፡፡
ሃያ አንድ አመቴ ነው፡፡ ታዲያ ላለፉት አሥራ አንድ ዓመታት ከቤት ወጥቼ አላውቅም፡፡
ስወለደ ጀምሮ ሁለቱም እግሮቼ መንቀሳቀስ አይችሉም፡፡ ከወገቤ በታች ሙሉ በሙሉ ሰውነቴን ማንቀሳቀስ ስለማልችል የግድ የሰው ድጋፍ ያስፈልገኛል፡፡ የግራ እጄም ሙሉ በሙሉ አይታዘዝልኘም፡፡ አንዳንዴ አ እንደ ቀኘ እጄ ጠንካራ ባይሆንም ደህና መንቀሳቀስ ጣቶቼን ማጠፍና መዘርጋት ሁሉ እችላለሁ፡፡
ብዙም ሳይቆይ ግን ሙሉ ለሙሉ የማይንቀሳቀስ በድን ይሆናል፡፡ ይኼ ነገር ታዲያ ከግራ እጄ አልፎ እስከ እግሮቼየሚዘልቅ የመዳን ተስፋ ይጭርብኛል፡፡ "ጥሩ ሐኪሙ ቢያገኘኝ እኮ ምናልባት ከባድመና ላይሆን ይችላል" እላለሁ ለራሴ፡፡ ለሰው ተናግሬ ግን አላውቅም፡፡ እዚ# ጎረቤት የአስር ብር መድመኒት መግዣ አጥተው በየቀበሌው የነፃ ህክምና ወረቀት ሲያፅፉየሚንከራተቱ ሚስኪኖች ታሪክ እየሰማሁ እንዴት ነው ሃያአንደኛና አመት *ሙሉ አሳስሮ ቁጭ ላደረገኘ ችግር ሐኪም ፈልጉ የምለው?
ተስቶኘ ብናገር እንኳን "የሞተው ቅድመ አያቴን ከሞት አስነሱልኘ" ያልኳቸው ያህል የሚገረሙ ይመስለኛል፡፡
ማንቀሳቀስ የምችለው ቀኘ እጄን ብቻ ነው፡፡ ቀኘ እጄ ሁሉም ነገሬ ነው፡፡ አንናንዴ በቀኘ እጄ ብቻ የምሰራውን ነገር ሳስብ ራሴን የተለየ ፍጥረት አድርጌ እመለከተዋለሁ፡፡ ልክ በቀኘ እጄ ብቻ ዓለምን መገልበጥ የምችል ኃያል ሰው የሆንኩ እስኪመስለኘ፡፡ ታዲያ እንደፈለኩ መንቀሳቀስ ባልችልም ለዓመታት ከቤቴ ባልወጣም ጥልቅ ብቸኘነቴ ውስጥ ማንም በቁማችን ነገር የማያየው ጥበቃና ፍቅር አለ፡፡
ሕይወቴ በጥበቃ የተሞላ ነው፡፡ ሁል ጊዜ ጧት በናፍቆት ከምጠብቃቸው ነገሮች አንዷ..........
ይቀጥላል🚶♀🚶♀🚶♀
የሚስኪን ነፍስ ህይወት😔😔
አሌክስ አብርሐም፡- ከዕለታት ግማሽ ቀን
@jahABP ነኘ መልካም አዳር 😊🙏😍

ትንሽ ስራ ቢዚ ስላደረገኘ ለተወሰኑ የtelegram ጓደኞቼ ፅሁፎችን ልኬላቸው voice record እንደሚደረጉ ነግሬያቸው ነበር፡፡
እና አሁን ለሀያትዬ😍🙏😊 ልኬላት voicuን ላከችልኘና ግን ድምፄ ይፈጥናል ለትረካ አይሆንም አለችኘ እስኪ ልስማው አልኳት ግን እሷ እንዳካበድችው አይደለም በጣም አሪፍ ድምፅ ከቆንጆ አተራረክ ጋር ነው የሰማሁት😍👏👏
ሐኑን ቀጣይ ክፍል በሀያት
🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂

record20210131195308
<unknown>
ሐኑን ቀጣይ ክፍል
Voice....ሐያት😍👏👏🙏
Voice....ሐያት😍👏👏🙏
እውነት! የምንደርስበት ስህተት
🤔🤔😳😳.............😂😍🙏
ጠብቁኘማ 🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂
🤔🤔😳😳.............😂😍🙏
ጠብቁኘማ 🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
እውነት! የምንደርስበት ስህተት
#ሐሰት_መሆኑን_የምናረጋግጠው_ነገር_እርሱ_እውነት_መሆን_ይጀምራል፡፡
ጋሊሊዮ "መሬት ትዞራለች" አለ፡፡ መሬት በመዞሯ የሃይማኖታቸው ካስማ ተነቅሎ የሚወድቅ የመሰላቸው ሰዎች መሬት እየተሽከረከረች የሥነ ፍጥረት ስርዓት በክብር መጓዙን ከማድነቅ ይልቅ እየተሽከረከረች የስነ ፍጥረት ስርዓተት በክብር መጓዙን ከማድነቅ ይልቅ መሬት ትዞራለች ማለት ሀጢያት ነው፡፡ እዚህ እውቀት ላይ የደረሰውም ሰው ሊቀጣ ይገባዋል አሉ፡፡
ሊቁም #በደረሰበት_የእውቀት_ዕውነት_ተቀጣ፡፡
ለካቶሊክ መነኮሳት በወቅቱ መሬት ትሽከረከራለች (ትዞራለች) ብሎ ማመን ስህተት ለጋሊሊዮ ደግሞ የግል እውነት ነበር፡
አሁን ጋሊሊዮ መሬት ትዞራለች ብሎ ሲያምን የእምነቱ እውነት የሚሆነው መሬት አትዞርም ለሚለው ስህተት ማስረጃው (መግለጫው) መንገድ ነው ማለት ነው፡፡
#ምክንያቱም_እውነት_የምነደርስባት_ስህተት_ናትና፡፡
ይህን ነገር በህልምና በቅዠቶቼ መሃል አሰብኩት፡፡ የማስበውንም ላለማሰብ ፈለግሁ ተመላልሶ ይታሰበኛል የተመለሰውን እደግመዋለሁ የተደገመውን እሰልሰዋለሁ "የሰው ልጅ ከእንስሳት ይለያል የሚባልበት ጉዳይ እውነት ይህ ነውን?" ራሴን እጠይቃለሁ፡፡
#ነገር_ግን_ከሚጠየቀው_ነገር_ይልቅ_የሰው_ልጅ_እንዲ_መጠየቅ_እንዳለ_ማወቁ_እርሱ_ይመስለኛል_ልዩነቱ_ከእንስሳቱ፡፡
በብዙው ጊዜ በባለሰላሳም በባለስልሳም በባለመቶም ጠቢባን መሃል ተመሳሳይ ጥያቄና ተመሳሳይ ፍላጎት ይነሳል፡፡
"#ፍለጋ " የሚባል ነገር፡፡
ውበትን ፍለጋ እውነትን ፍለጋ የሚባል ነገር መዳረሻጠየሌለው ጉዞ ፍቅር......
#እውነት_ፍለጋ_ሳይሆን_መገለጥ_ናት፡፡
እውነት የምትፈለግ የማይደረስባት ስውር የሆነች አይደለችም፡፡ እንዲያ ከሆነ እውነት ራሷ የለችም ማለት ነው፡፡ እውነት የሚገለጥ ልብስ የላትም ራቁቷን ናት-ነውር ግን የላትም፡፡
ጋሊሊይ መሬት ትዞራለች ከማለቱ በፊትም መሬት ትዞር ነበር፡፡ ጋሊሊዮ የመሬት መዞር በመግለጡ መሬት አትዞርም የሚለውን ስህተተኛ እውቀት ውድቅ አደረገው ይህም ማለት እውነት ሁለት ሲደመር ሁለት እኩል ይሆናል አራት ከሚለው ፅንሰ ሀሳብ ይልቅ አራት አሦስት በአንድ ይበልጣል ለሚለው ስሜት ቅርብ ነው፡፡
*2+2=4..............4>3
ጲላጦስም አለ...
"እውነት ምነንድናት???
ይህ ያለፉትና የሚመጡት የትኞቹም ሰዎች በተለያየ አቅጣጫ ሊያነሱት የሚችሉትን ጥያቄ ነው፡፡ ጥያቄው ለተገቢው ሰው ቀርቦ ነበር፡፡
የዘመናት የሰው ልጆች ጥያቄ መልስ ግን የሚነገር አልነበረም፡፡ የሚብራራም አልነበረም፡፡ "እውነት ማለት" ተብሎ መዳፍን ጨብጦ አፍ ላይ አድርጎ ጉሮሮን ጠርጎ "እውነት ማለት?" ብለው የተሞሸረ የቅኔ ለዛ የተላበሰ ስንኘ አድርገው የሚያወሩት ቃል አልነበረም እውነት የሚነገር አልነበረም፡፡
እውነት መሆን ነበረች፡፡ ስለዚህ ሁኔቴዋን ሆነች "ዝም" እኔ እንኳን የእውነት ሁኔታ ለመግለፅ ዝም ብዬ ስፅፍ ያበላሸሁ ይመስለኛል፡፡ ምንም አለማለትን በማለት ለመግለፅ መሞከር በራሱ ስህተት ነውና፡፡
"ዝም"
እዚህች የመሲህ ፀጥታ ውስጥ ነው የአላፊውን፡የመጪውን የሰው ልጆች ጥያቄ የተመለሰው፡፡ ጆሮ ያለው ይህንን ፀጥታ አዳምጧል፡፡
ጆሮ ያለው ይህንን ምላሽ አዳምጧል፡፡ እውነት የሚደርሱባት ውሸት ነበረች ያውም ልብ ብቻ የሚያውቃት የራስ ነውር ነበረች፡፡
#እውነት_በምስክሮች_አንደበት_ውስጥ_የምትፈለግ_ደካማ_ረዳት_የለሽ_አይደለችም _አትሆንም፡፡
"የእውነት ባህሪይ አምላካዊ ነው፡፡" ይላሉ አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ አምላክ በባህርዩ ሞት እንደሌለበት ሁሉ እውነትም እንዲያ ናት፡፡
ነገር ግን እውነቱን በውጪ አትፈልግ እውነቱንማ ልብህ ያውቃል እንዲል ሀበሻ፡፡
#ስህተቱን_ስህተት_ስንል_እውነቱን_እየገለጥን_ነው_ምክንያቱም....
ምሳሌ፩
ከልጅቷ ቦርሳ ውስጥ አስር ብር ተሰረቀ(ጠፋ ከላልኩም)
አሁንስ እውነት የተሰረቀው አስር ብር ማን እንደሰረቀው ማወቅ አይደለም ነገር ግን
#በሰረቀው_ግለሰብ_ልቦና_ውስጥ_ያለችው_ውርደትና_ሀፍረት_እንጂ፡፡
ከልጅቷ ቦርሳ ውስጥ አስር ብሩን ሲሰርቅ አንተ ተመልክተሃል አንተ አስር ብሩን ሲሰርቅ የተመለከትክ የእውነት ምስክር እንጂ እውነቱን አይደለህም፡፡
#እውነቱ_የሌባው_ልብና_መንፈስ_ስር_ያለው_ሁኔታ_ነው፡፡
ምሳሌ፪
ጋሊሊዮ "ምድር ትዞራለች" አለ፡፡ የጋሊሊዮ እነና የእውነት ተቃዋሚ ግለኛ መነኮሳት መሬት አትዞርም ብለው በሃይማኖት ስም ጋሊሊዮን አሠቃዩት፡፡ "ከእነዚሁ ከሁለቱ መሃል እውነትን የሚያውቃት ማነው?" ብትለኘ ጋሊሊዮ አልልህም ፡፡ "መነኮሳቱ ናቸው እልሃለሁ" የጋሊሊዮ እውነት የእነርሱን ስህተት መግለጥ ነውና እውነቱን የሚያሰማውና የሰማው እኩል ናቸው፡፡
" #ዝም_ብለን_አብረን_ዝም_እንበል"
"እውነት የማይወራ ከሆነ አንተስ ስትጽፈውና እያወራህ አይደለም ወይ?" ስትለ የሰማሁህ መሰለኘ፡፡ ይኸው እዚህ ካፍቴሪያ በር ላር ፈገግ እያልክ ቡና እና ማኪያቶህን እየተጎነጨህ "እውነት የማይወራ ከሆነ ለምን ዝም አትልም?" ነው ያልከኘ?
መልስ
ዝም
አንተስ ለምን ዝም አላልክም ኧረ ራሱን እያቄህን ለምን ዝም አላልከውም? ሁላችንም ዝም ያልነው ነን ይሄ ፊደልና ወሬ መሃል ያለው እኛነታችን ጭምብል ነው፡፡ እውነተኛውን መሸፈኛ እንዳይታይ የምንፈልገው መከለያ ማስክ፡፡
አመሻሽ ላይ በጀርባችን ጋደም ብለን ወይምበሌላኛዉ በረንዳ ላይ ጋቢ ደረብ አርገን ከራሳችን ጋር ለመምከር አይኖቻችን ወደ ሰማይ አንስተን ጋደም ካልንም ኮርኒስ ላይ ሰቅለን የምንሰማው ዝም ያልነው እኛን፡፡
ማነው ውርደቱን የማያውቅ? ማንስ ነው ውርደቱን ያወራ? ማነው ያላደፈ? ማንስ ነው በዝምታ ዕንባውን እድፉን ያላጠበ? ማነው ያልተሸፈነ? ማንስ ነው ከሽልማቱ በቀር ሽንፈቱን ያወራ?
እዚህ ዓለም ላይ በተግባር እየተኖረ ባለው ነገር ውስጥ እውነት አልተኖረም ማለት ይቻላል፡፡ ዓለም እውነትን በዝምታዋ ውስጥ ታዳምጣለች፡፡ እውነት ስለክብርም አይደለችም፡፡ ውርደት ናትና፡፡ እውነት ፀጥ ያልካት አመሻሽ ላይ ከሁካታው በኀላ ጋደም ልተትል ስትል አልያም በራስህ የፅሞና ጊዜ ለብቻህ የምትሰማት ማንነትህ(ኩነትህ) ናት፡፡
#እውነትን_አትፈልጋት_ስማት.....
ይሔ ለብቻችን የምንሰማውን ዝም ያልኩት ዝም ያልከውን እርሱን ባውቀው ብታውቀው ምን ይሆናል መሰለህ?......
እስከዛሬ ድረስ የማውቅህ አንተ ምን ሆንክ ማለት ነው? ውሸት! ውሸት ነህ ማለተግባራዊነቱ ነው፡፡ ስለዚህ እኔ የማየው ሳይሆን የአንተ እውነተኛው እውነት ዝም ያልከው ስለሆነ እርሱ ብንደርስበትም ደግሞ ይሔኛው አንተ ውሸት ስለምትሆን እውነት ማለት የምንደርስባት ስህተት ናት እልሃለሁ፡፡
ጲላጦስም ጠየቀ....
እውነት ምንድናት?
ኢየሱስም ዝም አለ
ዝም!!!!........
#የይሁዳ_ድልድይ_እና_ሌሎች_ሀሳቦች
ከኤፍሬም ስዩም
"ዝምታዬ መልሶ እኔው ላይ ይጮኻል
ለምን ዝም አልክ ይለኛል"
አለ ሳሚ ዳን
@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ መልካም #ዝምታ ማለቴ መልካም #አዳር😁😁😁😁😍🙏😍