ታዲያ ስለፖለቲኮ ሲወራ በብስጭት ወደ እኔ እየተመለከተ "ፖለቲካ ሸር*ጣ ነው.....! ተመልከት.............
ጠብቁኘማ🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂
ጠብቁኘማ🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
ታዲያ ስለፖለቲኮ ሲወራ በብስጭት ወደ እኔ እየተመለከተ "ፖለቲካ ሸር*ጣ ነው.....! ተመልከት.............
ከንጉሱ ጀምሮየፖለቲካ እሳት ደሃውን እንጂ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉትን መሪዎች አቃጥሎ አያውቅም፡፡ ካላመንክ አንድ በአንድ እያነሳን እንጫወት....እዚህ ሀገር ተምሮና ተንደላቆ፡የሚኖረው ብዙሃኑ 'ግፋ በለው!' ሲል የኖረ ነው፡፡
መንግስቱ ኃይለማርያምን ያንን ሁሉ የድሃ ልጅ ማግዶ እሰሱ ዛሬ የት ነው? 'ዚንቧቡዌ' ተንደላቆ ይኖራል፡፡
የኦነግ መሬዎች ተመልከት ወያኔዎችን ተመልከት...ምን ሆኑ? ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም የእርስ በእርስ ጦርነት ወጣቱ ነው ሚማገደው! ሚስኪን ወጣቶች! በፕሮፖጋንዳ ያበደ አለማስተዋል ነው፡፡ ወጣት አልዋጋም ካለ መሪዎች ሲጨባበጡ ነው የምታገሣቸው! እንዲች ብለው ስንጥር አያነሱም፡፡
ስንት ደም መጣጭ! ስንት ጓደኞቻችን በረኻ ላይ ቀሩ! ስንት 'ጂኒየሶች"'እነኳን ጦርነቱን የፖለቲካ ወሬው ያደነዝዝሃል፡፡ ከዚሀ ከበከተ እንቶፈንቶ ራቅ! ተማር! አሁንም ተማር! ማንም መሀይም መተኮስ ይችላል! መግደል ጀብዱ አይደለም ጅብም ሰው ይገድላል ታይፎድም ወባም ሰው ይገድላሉ!
#ዓላማ_የሌለው_ሞት_አገር_ሸርፎ_ከመሸጥ_እኩል_ነው፡፡
ለምንድነው የምትሞተው? ለምንድ ነው ወጣት የሚሞተው?.....ሊታረድ እንደሚነዳ በሬ የማይረባ ተስፋና ጥቅማጥቅም እንደ እርጥብ ሳር እያሸተቱ ወጣቱን ወደ ቄራ ይወስዱታል፡፡
ወጣቱም ብልጥ የሆነ ከሌላው የተለየ የገባው የረቀቀ የመጠቀ አድርጎ ራሱን ያያል ሲስተሙ ነው እንደዚያ የሚያደርግ፡፡ ከአንተ በላይ አዋቂ የሌለ መስሎ እንዲሰማህ....አለፍ ብለህ እጅህን ስትዘረጋ አረፋ ነው፡፡ ፖለቲካ እንኳን ይዘቱ ቅርፁ ለማንም ገብቶ አያውቅም ፈሳሽ ውሃ ነው ቅርፅ የለውም አንተ ውስጥ ሲገባ አንተን እኔ ውስጥ ሲገባ እኔን....
#ሁላችንም_ብርጭቆዎች_ነን፡፡
በስልጣን ከፍ ያሉት እያጋጩ 'ችርስ' የሚባባሉብን፡፡
አሌክስ አብርሃም፡- ከዕለታት ግማሽ ቀን
@jahABP ነኘ መልካም አዳር
😍🙏😍
ቦለቲካችን
@ABPGD @ABPGD @ABPGD

✋ጣቶቹ✋
😔😔😔😔😔😔 ስንት አይነት ሚስኪን ነፍሶች አሉ ይሆን😭😭😭😭😭
ጠብቁኘማ🚶♂🚶♂🚶♂🚶♂😔😔
😔😔😔😔😔😔 ስንት አይነት ሚስኪን ነፍሶች አሉ ይሆን😭😭😭😭😭
ጠብቁኘማ🚶♂🚶♂🚶♂🚶♂😔😔
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
🤚ጣቶቹ🤚
"ቆንጆ ነኘ ወይስ አይደለሁም?" የሚል ጥያቄ ድንገት አእምሮዬ ውስጥብልጭ ያለው ልክ የዛሬ አለመት አካባቢ ነበር፡፡ እስከዛሬም በየቀኑ በየሰዓቱ ጥያቄው በውስጤ ያቃጭላል፡፡ አንዳንዴ እንደውም የሆነ ሰው ጠርቼ "ለመሆኑ ቆንጆ ነኘ ወይስ አይደለሁም?! ብዬ መጠየቅ ያምረኛል፡፡ የራሴን ፊት ማየት ናፍቄያለሁ፡፡
የራሴን ፈገግታ የራሴን ጥርሶች የራሴን ከናፍርት የራሴን አይኖች አፍንጮች ብቻ መልኬን ማየት ክፉኛ ፈልጌያለሁ፡፡ በጣም ፈልጌያለሁ፡፡ በጣም ፈልጌያለሁ፡፡ አንዳንዴ ፊቴን ሳስበው የተጨማደደ ቆዳ ብነካው ለእጄ እንደቆረቆረ የሚሻክር ከንፈርና ግራ ጉንጬ ላይ የሚያዳልጥ ስፋቱ ስሙኒ የሚያህል ጠባሳ የሚኖረው ይመስለኛል፡፡
ግን በቀኘ እጄ ጣቶች ፊቴን ስዳስሰው የሚያጋጥመኘ ሌላ ነው፡፡ እንደተባዘተ ጥጥ የሚለሰልስ ቆዳ!! የቆዳዬ ልስላሴ ለራሴመ ያስደንቀኛል፡፡ የፊቴም ቆዳ የእኔ አይመስለኝም፡፡ እጄ የሌላ ሰው ፊት ላየ ያረፈነው የሚመስለኘ፡፡ ታዲያ ከራሴ ቆዳ ጋር በፍቅር የወደቅሁ ይመስለኛል፡፡ ደጋግሜ የቀኘ እጄን መዳፍ ጉንጬ ላይ በቀስታ አንሸራተዋለሁ ጣፋጭ ደስታ እንደ ማር በውስጤ ሲፈስ ይሰማኛል፡፡
ጣቶቼ ምላስ ሆነው የቆዳዬን ወለላ የቀመሱ ዓይነት፡፡ የዓይነ ኔ ሽፋሽፍት የቅንድቤ ለስላሳ ጸጉር በጣቶቼ ስዳብሳቸው የሚሰማኘ የሐሴት ወደር የለውም፡፡ መልኬን እንደ ብሬል ፅሁፍ በጣቴ ነበር የማነበው፡፡ ከራሴ ጋር ፍቅር የጀመረኘ ልክ የዛሬ ዓመት አካባቢ ነበር፡፡
#ምንም_ይሁን_ምን_መኖር_ጥሩ_ነው!፡፡
"መኖር ምናባቱ!" ብለን በገዛ ፈቃዳችን ነፍሳችንን ከስጋችን ለመለየት ፈራ ተባ ስንል ሕይወት #የተስፋ_ቅንጥብጣቢዋን_በኑሮጎዳናችን_ላይ_እየጣለች እንደ ለማዳ ውሻ ታስከትለናለች፡፡እንጂማ ገና መቼና መቼ የሰው ልጅ እራሱ አጥፍቶ ይችን ዓለም ዳዋ በወረሳት ነበር፡፡
#መኖር_ትልቅ_ሱስ_ነው፡፡
ይኸው ወፈሰማይ ኑሮ ሱሰኛ የዕድሜ ሲጋራውን ለኩሶ የመኖር ሱሱን ሲያሷርፍ በአፍና በአፍንጫው ተስፋን ይምጋታል፡
#አዲስ_ዛሬን_ወደ_ውስጡ_እየሳበ_የተቃጠለ_ትላንቱን_ወደውጭ_ይተነፍሰዋል፡፡
ለዚያ ይሆን እንዴ አየሩ ነበር ነበር የሚሸተው? የሚበዛው ሰው ልክ እንደ ሲጋራ ርጋፊውን የታሪክ ውጭቱ ላይ እየተረኮሰ የነገ ጀምበሩን በጉጉት ሲጠብቅ እጁ ላይ እድሜ ተቃጥላ ትከስማለች፡፡
#ቢሆንም_መኖር_ያሳሳል፡፡
እግዜርን መቼም ከአንደ ዓመት በፊት ግለኘ "ግደለኘ" እያልልኩ ደጋግሜ የፀለይኩትነ ጸሎት ሰምቶ አሁን ከተፍ ቢልና "ልጄ ሆይ ተነሽ እንሒድ" ቢለኘ "ቀልድ አታውቅም እንዴ!?" የምለው ይመስለኛል፡፡ መኖር ያሳሳኘ ከጀመር አንድ ዓመት አካባቢ ሆነኘ፡፡
ከሰኞ እስከ ዓርብ ድረስ በመንደሩ ላይ ከባድ ዝምታ ይረበብበታል፡፡ ሕፃናት ትምህርት ቤት አዋቂዎችም ወደየሥራቸው ይሔዳሉ፡፡ ሥራ የሌላቸው ጠራራውን ሽሽት በየቤታቸው ስለሚከተቱ የሰው ድምዕ አይሰማም፡፡ ከቅርብ እርቀት(ሰፈራችን ካለው ትዝታ ሙዚቃ ቤትየሚባል የተከፈተ) ሱዳንኛ ዘፈን ይሰማኛል፡፡
ሱዳንኛ ዘፈን ስሰማ አገሩ በረሃ የሆነ ነው የሚመስለኘ፡፡ ሁሉም ሰው ትቶኘ ወደሆነ ሀገር የተሰደደ ብቻዬን የቀረሁ እየመሰለኘ እፈራለሁ፡፡ አለ አይደል ሁሉም ሰው እኔ ሳልሰማ በምልክት እና በጥቅሻ ተጠራርቶ ወደ ሱዳን የተሰደደ "ሳትሰማን እንሒድ እሷን ማን ይጎትታታል!" እየተባባለ እግሬ አውጪኘ ያለ፡፡(የሚያወጣ እግር ያላቸው፡፡) ታዲ? እንዲህ ሰፈሩ ጭር ሲል ሁሉም ሰው ትቶኘ ወደ ሆነ ሀገር የሔደ እየመሰለኘ መፍራት ጀመርኩ አንድ ዓመት አካባቢ ሆነኘ፡፡ የሰፈሩን ሰው ሁሉ በስም እየጠራሁ "አላችሁ ወይ" ማለት ያምረኛል፡፡ "እስቲ ካላችሁ...ጣታችሁን አሳዩኘ!"
በፊት በፊት ይኼን ዝምታ አልወደውም ነበር፡፡ ስልችት ነበር የሚለኘ፡፡ አሁን ግን ዝምታው እንደነፍስ ሙዚቃ ከሩቅ እንደሚሰማ ኅብረ-ዜማ ሆኖ ውስጤን በደስታ ያከንፈዋል ተፍነክንኬ ሳላበቃ ደግሞ ውስጤን በድንጋጤ ትርክክ የሚያደርግ ስጋት ይፈጥራል፡፡ ደስታም ሆነ ድንጋጤው የሚነዝር ነገር አለው፡፡(ሰዎች ሲያወሩ ከእግር ጥፍሬ እስከ እራስ ፀጉሬ ነዘረኘ እንደሚሉት) "የደስታሽም ሆነ የድንጋጤሽ መነሻ ምንድነው?" ብባል መልስ የለኘም፡፡ ከመሬት ተነስቼ መደሰትና ከመሬት ተነስቼ መደንገጥ ከጀመርኩ አንድ አመተ አካባቢ ሆነኘ፡፡
አፅናፍ ነው ስሜ አዕናፍ ብሎ ስም ማን ያወጣልኘ ማን እንደሆነ እግዜር ይወቅ፡፡ ምናልባት እናቴ አባቴ ወይም አንዱ መንገደኛ ይሆናል፡፡ ዞሮ ዞሮ ስሜን ያወጣው ሰው በከንቱ ደከመ፡፡ ማንም ሰው በዚህ ሰው ጠርቶኘ አያውቅም፡፡ በስሜ መጠራት ይናፍቀኛል፡፡ "አፅናፍ" ደህና አደርሽ!?" አፅናፍ ሰማም ነው!? " "አፅናፍዬ...." እንዲህ ብባል ብዬ ለራሴ አስባለሁ፡፡ አንዳንዴ ስሜን ሳስበው "አሁን እኔ ምኔ አጽናፍ ይመስላል?" እላለሁ
አፅናፍ ማለት ራሱ ምን መምሰል ነበረበት?ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ስሜ አጽናፍ መሆኑን ያወቅሁት መቼ ይሆን? ማንም ሰው ስሙ የራሱ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያውቀው መቼ ነው? ስም ያወጣልልን ልኛውቅ እንችላለን ግን በስማችን ስንጠራ አቤት ማለት መቼ እንደጀመርን አናስታውስም፡፡
#ሰዎች_እኮ_ሚስኪን_ነን_ስናሳዝን!
ለሁሉም ሰዎች ማዘን ከጀመርኩ አንደበት አመት አካባቢ ሆነኘ፡፡ ለማይታዘንላቸውም ጭምር፡፡
ሃያ አንድ አመቴ ነው፡፡ ታዲያ ላለፉት አሥራ አንድ ዓመታት ከቤት ወጥቼ አላውቅም፡፡
ስወለደ ጀምሮ ሁለቱም እግሮቼ መንቀሳቀስ አይችሉም፡፡ ከወገቤ በታች ሙሉ በሙሉ ሰውነቴን ማንቀሳቀስ ስለማልችል የግድ የሰው ድጋፍ ያስፈልገኛል፡፡ የግራ እጄም ሙሉ በሙሉ አይታዘዝልኘም፡፡ አንዳንዴ አ እንደ ቀኘ እጄ ጠንካራ ባይሆንም ደህና መንቀሳቀስ ጣቶቼን ማጠፍና መዘርጋት ሁሉ እችላለሁ፡፡
ብዙም ሳይቆይ ግን ሙሉ ለሙሉ የማይንቀሳቀስ በድን ይሆናል፡፡ ይኼ ነገር ታዲያ ከግራ እጄ አልፎ እስከ እግሮቼየሚዘልቅ የመዳን ተስፋ ይጭርብኛል፡፡ "ጥሩ ሐኪሙ ቢያገኘኝ እኮ ምናልባት ከባድመና ላይሆን ይችላል" እላለሁ ለራሴ፡፡ ለሰው ተናግሬ ግን አላውቅም፡፡ እዚ# ጎረቤት የአስር ብር መድመኒት መግዣ አጥተው በየቀበሌው የነፃ ህክምና ወረቀት ሲያፅፉየሚንከራተቱ ሚስኪኖች ታሪክ እየሰማሁ እንዴት ነው ሃያአንደኛና አመት *ሙሉ አሳስሮ ቁጭ ላደረገኘ ችግር ሐኪም ፈልጉ የምለው?
ተስቶኘ ብናገር እንኳን "የሞተው ቅድመ አያቴን ከሞት አስነሱልኘ" ያልኳቸው ያህል የሚገረሙ ይመስለኛል፡፡
ማንቀሳቀስ የምችለው ቀኘ እጄን ብቻ ነው፡፡ ቀኘ እጄ ሁሉም ነገሬ ነው፡፡ አንናንዴ በቀኘ እጄ ብቻ የምሰራውን ነገር ሳስብ ራሴን የተለየ ፍጥረት አድርጌ እመለከተዋለሁ፡፡ ልክ በቀኘ እጄ ብቻ ዓለምን መገልበጥ የምችል ኃያል ሰው የሆንኩ እስኪመስለኘ፡፡ ታዲያ እንደፈለኩ መንቀሳቀስ ባልችልም ለዓመታት ከቤቴ ባልወጣም ጥልቅ ብቸኘነቴ ውስጥ ማንም በቁማችን ነገር የማያየው ጥበቃና ፍቅር አለ፡፡
ሕይወቴ በጥበቃ የተሞላ ነው፡፡ ሁል ጊዜ ጧት በናፍቆት ከምጠብቃቸው ነገሮች አንዷ..........
ይቀጥላል🚶♀🚶♀🚶♀
የሚስኪን ነፍስ ህይወት😔😔
አሌክስ አብርሐም፡- ከዕለታት ግማሽ ቀን
@jahABP ነኘ መልካም አዳር 😊🙏😍

ትንሽ ስራ ቢዚ ስላደረገኘ ለተወሰኑ የtelegram ጓደኞቼ ፅሁፎችን ልኬላቸው voice record እንደሚደረጉ ነግሬያቸው ነበር፡፡
እና አሁን ለሀያትዬ😍🙏😊 ልኬላት voicuን ላከችልኘና ግን ድምፄ ይፈጥናል ለትረካ አይሆንም አለችኘ እስኪ ልስማው አልኳት ግን እሷ እንዳካበድችው አይደለም በጣም አሪፍ ድምፅ ከቆንጆ አተራረክ ጋር ነው የሰማሁት😍👏👏
ሐኑን ቀጣይ ክፍል በሀያት
🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂

record20210131195308
<unknown>
ሐኑን ቀጣይ ክፍል
Voice....ሐያት😍👏👏🙏
Voice....ሐያት😍👏👏🙏
እውነት! የምንደርስበት ስህተት
🤔🤔😳😳.............😂😍🙏
ጠብቁኘማ 🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂
🤔🤔😳😳.............😂😍🙏
ጠብቁኘማ 🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂🏃♂
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
እውነት! የምንደርስበት ስህተት
#ሐሰት_መሆኑን_የምናረጋግጠው_ነገር_እርሱ_እውነት_መሆን_ይጀምራል፡፡
ጋሊሊዮ "መሬት ትዞራለች" አለ፡፡ መሬት በመዞሯ የሃይማኖታቸው ካስማ ተነቅሎ የሚወድቅ የመሰላቸው ሰዎች መሬት እየተሽከረከረች የሥነ ፍጥረት ስርዓት በክብር መጓዙን ከማድነቅ ይልቅ እየተሽከረከረች የስነ ፍጥረት ስርዓተት በክብር መጓዙን ከማድነቅ ይልቅ መሬት ትዞራለች ማለት ሀጢያት ነው፡፡ እዚህ እውቀት ላይ የደረሰውም ሰው ሊቀጣ ይገባዋል አሉ፡፡
ሊቁም #በደረሰበት_የእውቀት_ዕውነት_ተቀጣ፡፡
ለካቶሊክ መነኮሳት በወቅቱ መሬት ትሽከረከራለች (ትዞራለች) ብሎ ማመን ስህተት ለጋሊሊዮ ደግሞ የግል እውነት ነበር፡
አሁን ጋሊሊዮ መሬት ትዞራለች ብሎ ሲያምን የእምነቱ እውነት የሚሆነው መሬት አትዞርም ለሚለው ስህተት ማስረጃው (መግለጫው) መንገድ ነው ማለት ነው፡፡
#ምክንያቱም_እውነት_የምነደርስባት_ስህተት_ናትና፡፡
ይህን ነገር በህልምና በቅዠቶቼ መሃል አሰብኩት፡፡ የማስበውንም ላለማሰብ ፈለግሁ ተመላልሶ ይታሰበኛል የተመለሰውን እደግመዋለሁ የተደገመውን እሰልሰዋለሁ "የሰው ልጅ ከእንስሳት ይለያል የሚባልበት ጉዳይ እውነት ይህ ነውን?" ራሴን እጠይቃለሁ፡፡
#ነገር_ግን_ከሚጠየቀው_ነገር_ይልቅ_የሰው_ልጅ_እንዲ_መጠየቅ_እንዳለ_ማወቁ_እርሱ_ይመስለኛል_ልዩነቱ_ከእንስሳቱ፡፡
በብዙው ጊዜ በባለሰላሳም በባለስልሳም በባለመቶም ጠቢባን መሃል ተመሳሳይ ጥያቄና ተመሳሳይ ፍላጎት ይነሳል፡፡
"#ፍለጋ " የሚባል ነገር፡፡
ውበትን ፍለጋ እውነትን ፍለጋ የሚባል ነገር መዳረሻጠየሌለው ጉዞ ፍቅር......
#እውነት_ፍለጋ_ሳይሆን_መገለጥ_ናት፡፡
እውነት የምትፈለግ የማይደረስባት ስውር የሆነች አይደለችም፡፡ እንዲያ ከሆነ እውነት ራሷ የለችም ማለት ነው፡፡ እውነት የሚገለጥ ልብስ የላትም ራቁቷን ናት-ነውር ግን የላትም፡፡
ጋሊሊይ መሬት ትዞራለች ከማለቱ በፊትም መሬት ትዞር ነበር፡፡ ጋሊሊዮ የመሬት መዞር በመግለጡ መሬት አትዞርም የሚለውን ስህተተኛ እውቀት ውድቅ አደረገው ይህም ማለት እውነት ሁለት ሲደመር ሁለት እኩል ይሆናል አራት ከሚለው ፅንሰ ሀሳብ ይልቅ አራት አሦስት በአንድ ይበልጣል ለሚለው ስሜት ቅርብ ነው፡፡
*2+2=4..............4>3
ጲላጦስም አለ...
"እውነት ምነንድናት???
ይህ ያለፉትና የሚመጡት የትኞቹም ሰዎች በተለያየ አቅጣጫ ሊያነሱት የሚችሉትን ጥያቄ ነው፡፡ ጥያቄው ለተገቢው ሰው ቀርቦ ነበር፡፡
የዘመናት የሰው ልጆች ጥያቄ መልስ ግን የሚነገር አልነበረም፡፡ የሚብራራም አልነበረም፡፡ "እውነት ማለት" ተብሎ መዳፍን ጨብጦ አፍ ላይ አድርጎ ጉሮሮን ጠርጎ "እውነት ማለት?" ብለው የተሞሸረ የቅኔ ለዛ የተላበሰ ስንኘ አድርገው የሚያወሩት ቃል አልነበረም እውነት የሚነገር አልነበረም፡፡
እውነት መሆን ነበረች፡፡ ስለዚህ ሁኔቴዋን ሆነች "ዝም" እኔ እንኳን የእውነት ሁኔታ ለመግለፅ ዝም ብዬ ስፅፍ ያበላሸሁ ይመስለኛል፡፡ ምንም አለማለትን በማለት ለመግለፅ መሞከር በራሱ ስህተት ነውና፡፡
"ዝም"
እዚህች የመሲህ ፀጥታ ውስጥ ነው የአላፊውን፡የመጪውን የሰው ልጆች ጥያቄ የተመለሰው፡፡ ጆሮ ያለው ይህንን ፀጥታ አዳምጧል፡፡
ጆሮ ያለው ይህንን ምላሽ አዳምጧል፡፡ እውነት የሚደርሱባት ውሸት ነበረች ያውም ልብ ብቻ የሚያውቃት የራስ ነውር ነበረች፡፡
#እውነት_በምስክሮች_አንደበት_ውስጥ_የምትፈለግ_ደካማ_ረዳት_የለሽ_አይደለችም _አትሆንም፡፡
"የእውነት ባህሪይ አምላካዊ ነው፡፡" ይላሉ አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ አምላክ በባህርዩ ሞት እንደሌለበት ሁሉ እውነትም እንዲያ ናት፡፡
ነገር ግን እውነቱን በውጪ አትፈልግ እውነቱንማ ልብህ ያውቃል እንዲል ሀበሻ፡፡
#ስህተቱን_ስህተት_ስንል_እውነቱን_እየገለጥን_ነው_ምክንያቱም....
ምሳሌ፩
ከልጅቷ ቦርሳ ውስጥ አስር ብር ተሰረቀ(ጠፋ ከላልኩም)
አሁንስ እውነት የተሰረቀው አስር ብር ማን እንደሰረቀው ማወቅ አይደለም ነገር ግን
#በሰረቀው_ግለሰብ_ልቦና_ውስጥ_ያለችው_ውርደትና_ሀፍረት_እንጂ፡፡
ከልጅቷ ቦርሳ ውስጥ አስር ብሩን ሲሰርቅ አንተ ተመልክተሃል አንተ አስር ብሩን ሲሰርቅ የተመለከትክ የእውነት ምስክር እንጂ እውነቱን አይደለህም፡፡
#እውነቱ_የሌባው_ልብና_መንፈስ_ስር_ያለው_ሁኔታ_ነው፡፡
ምሳሌ፪
ጋሊሊዮ "ምድር ትዞራለች" አለ፡፡ የጋሊሊዮ እነና የእውነት ተቃዋሚ ግለኛ መነኮሳት መሬት አትዞርም ብለው በሃይማኖት ስም ጋሊሊዮን አሠቃዩት፡፡ "ከእነዚሁ ከሁለቱ መሃል እውነትን የሚያውቃት ማነው?" ብትለኘ ጋሊሊዮ አልልህም ፡፡ "መነኮሳቱ ናቸው እልሃለሁ" የጋሊሊዮ እውነት የእነርሱን ስህተት መግለጥ ነውና እውነቱን የሚያሰማውና የሰማው እኩል ናቸው፡፡
" #ዝም_ብለን_አብረን_ዝም_እንበል"
"እውነት የማይወራ ከሆነ አንተስ ስትጽፈውና እያወራህ አይደለም ወይ?" ስትለ የሰማሁህ መሰለኘ፡፡ ይኸው እዚህ ካፍቴሪያ በር ላር ፈገግ እያልክ ቡና እና ማኪያቶህን እየተጎነጨህ "እውነት የማይወራ ከሆነ ለምን ዝም አትልም?" ነው ያልከኘ?
መልስ
ዝም
አንተስ ለምን ዝም አላልክም ኧረ ራሱን እያቄህን ለምን ዝም አላልከውም? ሁላችንም ዝም ያልነው ነን ይሄ ፊደልና ወሬ መሃል ያለው እኛነታችን ጭምብል ነው፡፡ እውነተኛውን መሸፈኛ እንዳይታይ የምንፈልገው መከለያ ማስክ፡፡
አመሻሽ ላይ በጀርባችን ጋደም ብለን ወይምበሌላኛዉ በረንዳ ላይ ጋቢ ደረብ አርገን ከራሳችን ጋር ለመምከር አይኖቻችን ወደ ሰማይ አንስተን ጋደም ካልንም ኮርኒስ ላይ ሰቅለን የምንሰማው ዝም ያልነው እኛን፡፡
ማነው ውርደቱን የማያውቅ? ማንስ ነው ውርደቱን ያወራ? ማነው ያላደፈ? ማንስ ነው በዝምታ ዕንባውን እድፉን ያላጠበ? ማነው ያልተሸፈነ? ማንስ ነው ከሽልማቱ በቀር ሽንፈቱን ያወራ?
እዚህ ዓለም ላይ በተግባር እየተኖረ ባለው ነገር ውስጥ እውነት አልተኖረም ማለት ይቻላል፡፡ ዓለም እውነትን በዝምታዋ ውስጥ ታዳምጣለች፡፡ እውነት ስለክብርም አይደለችም፡፡ ውርደት ናትና፡፡ እውነት ፀጥ ያልካት አመሻሽ ላይ ከሁካታው በኀላ ጋደም ልተትል ስትል አልያም በራስህ የፅሞና ጊዜ ለብቻህ የምትሰማት ማንነትህ(ኩነትህ) ናት፡፡
#እውነትን_አትፈልጋት_ስማት.....
ይሔ ለብቻችን የምንሰማውን ዝም ያልኩት ዝም ያልከውን እርሱን ባውቀው ብታውቀው ምን ይሆናል መሰለህ?......
እስከዛሬ ድረስ የማውቅህ አንተ ምን ሆንክ ማለት ነው? ውሸት! ውሸት ነህ ማለተግባራዊነቱ ነው፡፡ ስለዚህ እኔ የማየው ሳይሆን የአንተ እውነተኛው እውነት ዝም ያልከው ስለሆነ እርሱ ብንደርስበትም ደግሞ ይሔኛው አንተ ውሸት ስለምትሆን እውነት ማለት የምንደርስባት ስህተት ናት እልሃለሁ፡፡
ጲላጦስም ጠየቀ....
እውነት ምንድናት?
ኢየሱስም ዝም አለ
ዝም!!!!........
#የይሁዳ_ድልድይ_እና_ሌሎች_ሀሳቦች
ከኤፍሬም ስዩም
"ዝምታዬ መልሶ እኔው ላይ ይጮኻል
ለምን ዝም አልክ ይለኛል"
አለ ሳሚ ዳን
@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ መልካም #ዝምታ ማለቴ መልካም #አዳር😁😁😁😁😍🙏😍

#ወደ_ኀላ_በመሔድም_መቅደም_አለ
እናትና አባታችን ይህን በማየታቸው እንደነሱ ተደሳች የለም ደሞ ይገባቸዋል፡፡
እኛ ማለት እነሱ ነንና፡፡
እንደሰዎች ሀሳብ ሳይሆን እንደሱ እንደ #መድሃኒዓለም ጥበቃና እገዛ በምትወዳት እናታችን #ድንግል_ማርያም አማላጅነት፡፡
በአሳደገን መልዓክ #ቅዱስ_ዑራኤል
በፈጥኖ ደራሹ #በሰማዕቱ_መርቆርዮስ አሳድገው ለዚህ ያበቁህ ሁሌም ከፍ ከፍ ይበሉ፡፡🙏🙏🙏🙏
እናትና አባታችን ይህን በማየታቸው እንደነሱ ተደሳች የለም ደሞ ይገባቸዋል፡፡
እኛ ማለት እነሱ ነንና፡፡
እንደሰዎች ሀሳብ ሳይሆን እንደሱ እንደ #መድሃኒዓለም ጥበቃና እገዛ በምትወዳት እናታችን #ድንግል_ማርያም አማላጅነት፡፡
በአሳደገን መልዓክ #ቅዱስ_ዑራኤል
በፈጥኖ ደራሹ #በሰማዕቱ_መርቆርዮስ አሳድገው ለዚህ ያበቁህ ሁሌም ከፍ ከፍ ይበሉ፡፡🙏🙏🙏🙏
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
#ማምሻ
#ሴቶች ይህን የአሌክስ አብርሃም ፅሁፍ አንብቡልኘ......
አስታውሳለሁ አሌክስ አብርሃምን እወደዋለሁ ብዬ ነበር ይህንን መፅሐፍ የጀመርኩት፡፡
ይኸው ብዙ ጊዜ ከሰዎች ጋር የምጣላበትን ቀደም ብዬ መፅሐፉ ከመውጣቱ በፊት እራሴ የፃፍኩትን ፅሁፍ ማንበብ ይቻላል...
አሌክሶ ደግሞ ማምሻ በምትባል ሴት ልጅ መስሎ ሌላ ደግሞ ሎዛ የምትባል ቅመም ጨምሮበት የማህበረሰባችንን ችግር እንዲህ ያስቃኘናል ......
ሴት ልጆች አላችሁ ይህን ፅሁፍ አንብባችሁትስ ይሆን🤔🤔 አው እናንተን ይመለከታል
#ሎዛ በቁጭት እንደዚህ ትላለች(ፍልስፍና ነው ያጠናችው) .....
"በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ 'ሴትነትና ቁንጅና' የሚባል የእስር ፍርግርግታችን እያርዋብን ተሟሙቀን የወንዶች ጭብጨባና አድናቆት እየጠበቅን እንድንኖር ሁነናል፡፡
ሁሉም ሰንሰለቱን ፈቶ አይታይም....እንደውም አንዳንዱ እስራት ለታሳሪው ጭምር አይታይም፡፡
ማህበረሰቡ አንዲት ሴት "የብረት መዝጊያ የሚሆን አማች የምታመጣ እንጂ የብረት መዝጊያ መሆን የምትችል አድርጎ አያስብም! ስለዚህ የእነሱን የምኞት በር የሚዘጋ የብረት መዝጊያ ለማምጣት አንዲት ሴት ዓይኗንም አእምሮዋንም ሳይሆን #እግሯን_እንድትከፍት ከህፃንነቷ ጀምሮ ሲያዘጋጃት ይኖራል"
"እግር የተፈጠረበት የመጀመሪያው ዓላማው መራመድ ነው ለሴት ልጅ ግን ከመራመድ በላይ እግር ውበት እንደሆነ እንድታስብ በሥነ-ፅሁፉ በፊልሙ *በዘፈኑ በእምሮዋ ውስጥ ሲታጨቅባት ኖሯል *እየታጨቀባትም ነው፡፡
ከመራመዷ በላይ አረማመዷን እና የእግሯን ውበት እንድታስብ ስትሰበክ ኖራለች፡፡
ለዚያም ነው ከፊታቸው የተነጠፈውን እሾህም ይሁን ጠጠር ረግጠውና ዋጋ ከፍለው ወዳሰቡበት ከሚራመዱት ሴቶች ይልቅ ከየትም ባገኟት ሳንቲም በየውበት ሳሎኑ ተጎልተው እግራቸውን የጥፍር ቀለም ሲያስቀቡና ተረከዛቸውን ሲያስፈገፍጉ የሚውሉ ዘመነኞች የሚበዙት፡፡ እግራቸው ከለሰለሰ በኀላ አዝሎ የኒያሻግር ወንድ ሲጠብቁ ቁጭ ብለው ይኖራሉ፡፡
እጅ የተፈጠረበት የመጀመሪያው አላማው መስራት ነው፡፡ ብዙ የፋሽንና እና የዘመናዊውን የውበት ሚዛን የሚደፉ 'ዘመናዊ' ሴቶች እጃቸው ከሚበላሽ ስማቸውም ሕይወታቸውም ቢበላሽና እና እጃቸውጠእንደለሰለሰ ቢኖር ይመርጣሉ፡፡
በልስላሴ ሳይሆን በንፅህና እራስን ችሎ በመቆም እንጨባበጥ ከተባለ ማን ናት ደፍራ እጇን የምትዘረጋ?!
ለብዙሃን ወንዶች ጠንካራ የሴት እጅ አገር ያቆመ ሳይሆንጨሴትነትነ የገፉ መስሎ ነው የሚታያቸው፡፡ ለዚያ ነው በስራ ስለደደረ የሴት መዳፍ ዘፋኙም መዝፈን ገጣሚውመ መግጠም የማይወደው፡፡ ድንጋይ ፈልፍሎ እምነበረደ ጠርቦ ውብ የእጅ ጣት ያላት የሴት ሐውልት የሚያሾመው ቀራጺ እጅ ግን ተመልከተው በስራጨየጎለደፈ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡
ከግማሽ በላይ የሚሆነው ህዝብ ሴት በሆነበት ሀገር ሴትች ወንድ በጭናቸው መሀል ካላፈ የሚመስላቸው እጃቸውን አስውበው መደርደሪያ ላይ እንዲያስቀም ጡት በማድረግ ለውጥ ጠብ አይልም እንዲሰሩ.. ማደፋፈር.. እጅ... ወደተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማ እንዲመለስ መሰበክ አለበት!! "
አሌክስ አብርሃም፡- ከዕለታት ግማሽ ቀን
ሴቶች ተጋበዙልኘ.......
@jahABP ነኘ
እኔም እላለሁ ገላዋን አይቶ የመጣ ገላውን አይቶ ይሔዳል እና እህቴ እባክሽን ከዘመንኛ አስተሳሰብ አምልጪ አንቺ ሁሉንም ማድረግ ትቺያለሽ ቁጭ ብለሽ እሱን አትጠብቂ፡፡
በዚ ጊዜ የሴትነት ክብር በጣም የዘቀጠ ሆኖ እያገኘሁት ነው የሰሞንኛ መነጋገሪያዎችንም ጨምሮ ባለፈውም የጋበዝኩት የኀይሌ ሩትስ ዘፈኝ ላይ "ማንነትሽን ገንዘብ ላይተካው ለምን ማንም ክብርሽን ይንካው ይላል" እና እባካችሁን እላለሁ 😔😔😔😔😔
@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ
፡፡ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገንም እያሰብን እንራመድ፡፡
እላለሁ
መልካም ምሽት መልካም አዳር