Phenomenal pictures & graphic design
1.06K subscribers
1.78K photos
8 videos
2 files
16 links
FOR ANY COMMENT
Abiy 09 73 06 89 82
Photographer , travler
MOBOGRAPHER iPhone
traveler
Graphic design
ካነበብኳቸው
ከገጠሙኘ ፣ ከሰማኀቸው....እንቀነጭባለን

@jahABP
Download Telegram
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

የኛ አባት መልዐኩ ቅዱስ ዑራኤል ጥበብ ሰጪው መልዓክ አንተ ከኛ ጋር ሆነህ እኛ ምን ምን ጎሎብን
ሁሌም ከፍ ከፍ በልልን የአንተ መሆን ምንኛ መታደል ነው፡፡
የወጣትነት መናችኝ ይባረክ ዘንድ ስለኛ ልጆችህ ወደ አምላክህ መፀለኘ አታቋርጥ፡፡

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
ትንሽ ስራ ቢዚ ስላደረገኘ ለተወሰኑ የtelegram ጓደኞቼ ፅሁፎችን ልኬላቸው voice record እንደሚደረጉ ነግሬያቸው ነበር፡፡

እና አሁን ለሀያትዬ😍🙏😊 ልኬላት voicuን ላከችልኘና ግን ድምፄ ይፈጥናል ለትረካ አይሆንም አለችኘ እስኪ ልስማው አልኳት ግን እሷ እንዳካበድችው አይደለም በጣም አሪፍ ድምፅ ከቆንጆ አተራረክ ጋር ነው የሰማሁት😍👏👏

ሐኑን ቀጣይ ክፍል በሀያት

🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
record20210131195308
<unknown>
ሐኑን ቀጣይ ክፍል

Voice....ሐያት😍👏👏🙏
እውነት! የምንደርስበት ስህተት

🤔🤔😳😳.............😂😍🙏

ጠብቁኘማ 🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

እውነት! የምንደርስበት ስህተት

#ሐሰት_መሆኑን_የምናረጋግጠው_ነገር_እርሱ_እውነት_መሆን_ይጀምራል፡፡
ጋሊሊዮ "መሬት ትዞራለች" አለ፡፡ መሬት በመዞሯ የሃይማኖታቸው ካስማ ተነቅሎ የሚወድቅ የመሰላቸው ሰዎች መሬት እየተሽከረከረች የሥነ ፍጥረት ስርዓት በክብር መጓዙን ከማድነቅ ይልቅ እየተሽከረከረች የስነ ፍጥረት ስርዓተት በክብር መጓዙን ከማድነቅ ይልቅ መሬት ትዞራለች ማለት ሀጢያት ነው፡፡ እዚህ እውቀት ላይ የደረሰውም ሰው ሊቀጣ ይገባዋል አሉ፡፡

ሊቁም #በደረሰበት_የእውቀት_ዕውነት_ተቀጣ፡፡

ለካቶሊክ መነኮሳት በወቅቱ መሬት ትሽከረከራለች (ትዞራለች) ብሎ ማመን ስህተት ለጋሊሊዮ ደግሞ የግል እውነት ነበር፡
አሁን ጋሊሊዮ መሬት ትዞራለች ብሎ ሲያምን የእምነቱ እውነት የሚሆነው መሬት አትዞርም ለሚለው ስህተት ማስረጃው (መግለጫው) መንገድ ነው ማለት ነው፡፡

#ምክንያቱም_እውነት_የምነደርስባት_ስህተት_ናትና፡፡

ይህን ነገር በህልምና በቅዠቶቼ መሃል አሰብኩት፡፡ የማስበውንም ላለማሰብ ፈለግሁ ተመላልሶ ይታሰበኛል የተመለሰውን እደግመዋለሁ የተደገመውን እሰልሰዋለሁ "የሰው ልጅ ከእንስሳት ይለያል የሚባልበት ጉዳይ እውነት ይህ ነውን?" ራሴን እጠይቃለሁ፡፡

#ነገር_ግን_ከሚጠየቀው_ነገር_ይልቅ_የሰው_ልጅ_እንዲ_መጠየቅ_እንዳለ_ማወቁ_እርሱ_ይመስለኛል_ልዩነቱ_ከእንስሳቱ፡፡

በብዙው ጊዜ በባለሰላሳም በባለስልሳም በባለመቶም ጠቢባን መሃል ተመሳሳይ ጥያቄና ተመሳሳይ ፍላጎት ይነሳል፡፡
"#ፍለጋ " የሚባል ነገር፡፡
ውበትን ፍለጋ እውነትን ፍለጋ የሚባል ነገር መዳረሻጠየሌለው ጉዞ ፍቅር......

#እውነት_ፍለጋ_ሳይሆን_መገለጥ_ናት፡፡

እውነት የምትፈለግ የማይደረስባት ስውር የሆነች አይደለችም፡፡ እንዲያ ከሆነ እውነት ራሷ የለችም ማለት ነው፡፡ እውነት የሚገለጥ ልብስ የላትም ራቁቷን ናት-ነውር ግን የላትም፡፡

ጋሊሊይ መሬት ትዞራለች ከማለቱ በፊትም መሬት ትዞር ነበር፡፡ ጋሊሊዮ የመሬት መዞር በመግለጡ መሬት አትዞርም የሚለውን ስህተተኛ እውቀት ውድቅ አደረገው ይህም ማለት እውነት ሁለት ሲደመር ሁለት እኩል ይሆናል አራት ከሚለው ፅንሰ ሀሳብ ይልቅ አራት አሦስት በአንድ ይበልጣል ለሚለው ስሜት ቅርብ ነው፡፡

*2+2=4..............4>3

ጲላጦስም አለ...
"እውነት ምነንድናት???

ይህ ያለፉትና የሚመጡት የትኞቹም ሰዎች በተለያየ አቅጣጫ ሊያነሱት የሚችሉትን ጥያቄ ነው፡፡ ጥያቄው ለተገቢው ሰው ቀርቦ ነበር፡፡
የዘመናት የሰው ልጆች ጥያቄ መልስ ግን የሚነገር አልነበረም፡፡ የሚብራራም አልነበረም፡፡ "እውነት ማለት" ተብሎ መዳፍን ጨብጦ አፍ ላይ አድርጎ ጉሮሮን ጠርጎ "እውነት ማለት?" ብለው የተሞሸረ የቅኔ ለዛ የተላበሰ ስንኘ አድርገው የሚያወሩት ቃል አልነበረም እውነት የሚነገር አልነበረም፡፡

እውነት መሆን ነበረች፡፡ ስለዚህ ሁኔቴዋን ሆነች "ዝም" እኔ እንኳን የእውነት ሁኔታ ለመግለፅ ዝም ብዬ ስፅፍ ያበላሸሁ ይመስለኛል፡፡ ምንም አለማለትን በማለት ለመግለፅ መሞከር በራሱ ስህተት ነውና፡፡

"ዝም"

እዚህች የመሲህ ፀጥታ ውስጥ ነው የአላፊውን፡የመጪውን የሰው ልጆች ጥያቄ የተመለሰው፡፡ ጆሮ ያለው ይህንን ፀጥታ አዳምጧል፡፡
ጆሮ ያለው ይህንን ምላሽ አዳምጧል፡፡ እውነት የሚደርሱባት ውሸት ነበረች ያውም ልብ ብቻ የሚያውቃት የራስ ነውር ነበረች፡፡

#እውነት_በምስክሮች_አንደበት_ውስጥ_የምትፈለግ_ደካማ_ረዳት_የለሽ_አይደለችም _አትሆንም፡፡

"የእውነት ባህሪይ አምላካዊ ነው፡፡" ይላሉ አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ አምላክ በባህርዩ ሞት እንደሌለበት ሁሉ እውነትም እንዲያ ናት፡፡
ነገር ግን እውነቱን በውጪ አትፈልግ እውነቱንማ ልብህ ያውቃል እንዲል ሀበሻ፡፡

#ስህተቱን_ስህተት_ስንል_እውነቱን_እየገለጥን_ነው_ምክንያቱም....

ምሳሌ፩
ከልጅቷ ቦርሳ ውስጥ አስር ብር ተሰረቀ(ጠፋ ከላልኩም)

አሁንስ እውነት የተሰረቀው አስር ብር ማን እንደሰረቀው ማወቅ አይደለም ነገር ግን

#በሰረቀው_ግለሰብ_ልቦና_ውስጥ_ያለችው_ውርደትና_ሀፍረት_እንጂ፡፡

ከልጅቷ ቦርሳ ውስጥ አስር ብሩን ሲሰርቅ አንተ ተመልክተሃል አንተ አስር ብሩን ሲሰርቅ የተመለከትክ የእውነት ምስክር እንጂ እውነቱን አይደለህም፡፡

#እውነቱ_የሌባው_ልብና_መንፈስ_ስር_ያለው_ሁኔታ_ነው፡፡

ምሳሌ፪

ጋሊሊዮ "ምድር ትዞራለች" አለ፡፡ የጋሊሊዮ እነና የእውነት ተቃዋሚ ግለኛ መነኮሳት መሬት አትዞርም ብለው በሃይማኖት ስም ጋሊሊዮን አሠቃዩት፡፡ "ከእነዚሁ ከሁለቱ መሃል እውነትን የሚያውቃት ማነው?" ብትለኘ ጋሊሊዮ አልልህም ፡፡ "መነኮሳቱ ናቸው እልሃለሁ" የጋሊሊዮ እውነት የእነርሱን ስህተት መግለጥ ነውና እውነቱን የሚያሰማውና የሰማው እኩል ናቸው፡፡

" #ዝም_ብለን_አብረን_ዝም_እንበል"

"እውነት የማይወራ ከሆነ አንተስ ስትጽፈውና እያወራህ አይደለም ወይ?" ስትለ የሰማሁህ መሰለኘ፡፡ ይኸው እዚህ ካፍቴሪያ በር ላር ፈገግ እያልክ ቡና እና ማኪያቶህን እየተጎነጨህ "እውነት የማይወራ ከሆነ ለምን ዝም አትልም?" ነው ያልከኘ?

መልስ

ዝም

አንተስ ለምን ዝም አላልክም ኧረ ራሱን እያቄህን ለምን ዝም አላልከውም? ሁላችንም ዝም ያልነው ነን ይሄ ፊደልና ወሬ መሃል ያለው እኛነታችን ጭምብል ነው፡፡ እውነተኛውን መሸፈኛ እንዳይታይ የምንፈልገው መከለያ ማስክ፡፡

አመሻሽ ላይ በጀርባችን ጋደም ብለን ወይምበሌላኛዉ በረንዳ ላይ ጋቢ ደረብ አርገን ከራሳችን ጋር ለመምከር አይኖቻችን ወደ ሰማይ አንስተን ጋደም ካልንም ኮርኒስ ላይ ሰቅለን የምንሰማው ዝም ያልነው እኛን፡፡

ማነው ውርደቱን የማያውቅ? ማንስ ነው ውርደቱን ያወራ? ማነው ያላደፈ? ማንስ ነው በዝምታ ዕንባውን እድፉን ያላጠበ? ማነው ያልተሸፈነ? ማንስ ነው ከሽልማቱ በቀር ሽንፈቱን ያወራ?

እዚህ ዓለም ላይ በተግባር እየተኖረ ባለው ነገር ውስጥ እውነት አልተኖረም ማለት ይቻላል፡፡ ዓለም እውነትን በዝምታዋ ውስጥ ታዳምጣለች፡፡ እውነት ስለክብርም አይደለችም፡፡ ውርደት ናትና፡፡ እውነት ፀጥ ያልካት አመሻሽ ላይ ከሁካታው በኀላ ጋደም ልተትል ስትል አልያም በራስህ የፅሞና ጊዜ ለብቻህ የምትሰማት ማንነትህ(ኩነትህ) ናት፡፡

#እውነትን_አትፈልጋት_ስማት.....

ይሔ ለብቻችን የምንሰማውን ዝም ያልኩት ዝም ያልከውን እርሱን ባውቀው ብታውቀው ምን ይሆናል መሰለህ?......

እስከዛሬ ድረስ የማውቅህ አንተ ምን ሆንክ ማለት ነው? ውሸት! ውሸት ነህ ማለተግባራዊነቱ ነው፡፡ ስለዚህ እኔ የማየው ሳይሆን የአንተ እውነተኛው እውነት ዝም ያልከው ስለሆነ እርሱ ብንደርስበትም ደግሞ ይሔኛው አንተ ውሸት ስለምትሆን እውነት ማለት የምንደርስባት ስህተት ናት እልሃለሁ፡፡

ጲላጦስም ጠየቀ....

እውነት ምንድናት?

ኢየሱስም ዝም አለ

ዝም!!!!........

#የይሁዳ_ድልድይ_እና_ሌሎች_ሀሳቦች

ከኤፍሬም ስዩም

"ዝምታዬ መልሶ እኔው ላይ ይጮኻል

ለምን ዝም አልክ ይለኛል"
አለ ሳሚ ዳን

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ መልካም #ዝምታ ማለቴ መልካም #አዳር😁😁😁😁😍🙏😍


@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
#ወደ_ኀላ_በመሔድም_መቅደም_አለ

እናትና አባታችን ይህን በማየታቸው እንደነሱ ተደሳች የለም ደሞ ይገባቸዋል፡፡
እኛ ማለት እነሱ ነንና፡፡

እንደሰዎች ሀሳብ ሳይሆን እንደሱ እንደ #መድሃኒዓለም ጥበቃና እገዛ በምትወዳት እናታችን #ድንግል_ማርያም አማላጅነት፡፡
በአሳደገን መልዓክ #ቅዱስ_ዑራኤል
በፈጥኖ ደራሹ #በሰማዕቱ_መርቆርዮስ አሳድገው ለዚህ ያበቁህ ሁሌም ከፍ ከፍ ይበሉ፡፡🙏🙏🙏🙏
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#ማምሻ

#ሴቶች ይህን የአሌክስ አብርሃም ፅሁፍ አንብቡልኘ......

አስታውሳለሁ አሌክስ አብርሃምን እወደዋለሁ ብዬ ነበር ይህንን መፅሐፍ የጀመርኩት፡፡

ይኸው ብዙ ጊዜ ከሰዎች ጋር የምጣላበትን ቀደም ብዬ መፅሐፉ ከመውጣቱ በፊት እራሴ የፃፍኩትን ፅሁፍ ማንበብ ይቻላል...

አሌክሶ ደግሞ ማምሻ በምትባል ሴት ልጅ መስሎ ሌላ ደግሞ ሎዛ የምትባል ቅመም ጨምሮበት የማህበረሰባችንን ችግር እንዲህ ያስቃኘናል ......

ሴት ልጆች አላችሁ ይህን ፅሁፍ አንብባችሁትስ ይሆን🤔🤔 አው እናንተን ይመለከታል

#ሎዛ በቁጭት እንደዚህ ትላለች(ፍልስፍና ነው ያጠናችው) .....

"በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ 'ሴትነትና ቁንጅና' የሚባል የእስር ፍርግርግታችን እያርዋብን ተሟሙቀን የወንዶች ጭብጨባና አድናቆት እየጠበቅን እንድንኖር ሁነናል፡፡
ሁሉም ሰንሰለቱን ፈቶ አይታይም....እንደውም አንዳንዱ እስራት ለታሳሪው ጭምር አይታይም፡፡

ማህበረሰቡ አንዲት ሴት "የብረት መዝጊያ የሚሆን አማች የምታመጣ እንጂ የብረት መዝጊያ መሆን የምትችል አድርጎ አያስብም! ስለዚህ የእነሱን የምኞት በር የሚዘጋ የብረት መዝጊያ ለማምጣት አንዲት ሴት ዓይኗንም አእምሮዋንም ሳይሆን #እግሯን_እንድትከፍት ከህፃንነቷ ጀምሮ ሲያዘጋጃት ይኖራል"

"እግር የተፈጠረበት የመጀመሪያው ዓላማው መራመድ ነው ለሴት ልጅ ግን ከመራመድ በላይ እግር ውበት እንደሆነ እንድታስብ በሥነ-ፅሁፉ በፊልሙ *በዘፈኑ በእምሮዋ ውስጥ ሲታጨቅባት ኖሯል *እየታጨቀባትም ነው፡፡
ከመራመዷ በላይ አረማመዷን እና የእግሯን ውበት እንድታስብ ስትሰበክ ኖራለች፡፡

ለዚያም ነው ከፊታቸው የተነጠፈውን እሾህም ይሁን ጠጠር ረግጠውና ዋጋ ከፍለው ወዳሰቡበት ከሚራመዱት ሴቶች ይልቅ ከየትም ባገኟት ሳንቲም በየውበት ሳሎኑ ተጎልተው እግራቸውን የጥፍር ቀለም ሲያስቀቡና ተረከዛቸውን ሲያስፈገፍጉ የሚውሉ ዘመነኞች የሚበዙት፡፡ እግራቸው ከለሰለሰ በኀላ አዝሎ የኒያሻግር ወንድ ሲጠብቁ ቁጭ ብለው ይኖራሉ፡፡

እጅ የተፈጠረበት የመጀመሪያው አላማው መስራት ነው፡፡ ብዙ የፋሽንና እና የዘመናዊውን የውበት ሚዛን የሚደፉ 'ዘመናዊ' ሴቶች እጃቸው ከሚበላሽ ስማቸውም ሕይወታቸውም ቢበላሽና እና እጃቸውጠእንደለሰለሰ ቢኖር ይመርጣሉ፡፡
በልስላሴ ሳይሆን በንፅህና እራስን ችሎ በመቆም እንጨባበጥ ከተባለ ማን ናት ደፍራ እጇን የምትዘረጋ?!

ለብዙሃን ወንዶች ጠንካራ የሴት እጅ አገር ያቆመ ሳይሆንጨሴትነትነ የገፉ መስሎ ነው የሚታያቸው፡፡ ለዚያ ነው በስራ ስለደደረ የሴት መዳፍ ዘፋኙም መዝፈን ገጣሚውመ መግጠም የማይወደው፡፡ ድንጋይ ፈልፍሎ እምነበረደ ጠርቦ ውብ የእጅ ጣት ያላት የሴት ሐውልት የሚያሾመው ቀራጺ እጅ ግን ተመልከተው በስራጨየጎለደፈ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡

ከግማሽ በላይ የሚሆነው ህዝብ ሴት በሆነበት ሀገር ሴትች ወንድ በጭናቸው መሀል ካላፈ የሚመስላቸው እጃቸውን አስውበው መደርደሪያ ላይ እንዲያስቀም ጡት በማድረግ ለውጥ ጠብ አይልም እንዲሰሩ.. ማደፋፈር.. እጅ... ወደተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማ እንዲመለስ መሰበክ አለበት!! "

አሌክስ አብርሃም፡- ከዕለታት ግማሽ ቀን

ሴቶች ተጋበዙልኘ.......

@jahABP ነኘ

እኔም እላለሁ ገላዋን አይቶ የመጣ ገላውን አይቶ ይሔዳል እና እህቴ እባክሽን ከዘመንኛ አስተሳሰብ አምልጪ አንቺ ሁሉንም ማድረግ ትቺያለሽ ቁጭ ብለሽ እሱን አትጠብቂ፡፡
በዚ ጊዜ የሴትነት ክብር በጣም የዘቀጠ ሆኖ እያገኘሁት ነው የሰሞንኛ መነጋገሪያዎችንም ጨምሮ ባለፈውም የጋበዝኩት የኀይሌ ሩትስ ዘፈኝ ላይ "ማንነትሽን ገንዘብ ላይተካው ለምን ማንም ክብርሽን ይንካው ይላል" እና እባካችሁን እላለሁ 😔😔😔😔😔

@jahABP ነኘ አስተያየታችሁን አድርሱኘ

፡፡ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገንም እያሰብን እንራመድ፡፡
እላለሁ

መልካም ምሽት መልካም አዳር

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
ያን ቀን አስታውሳለሁ🤔🤔🤔😍😍😍😍😍አልረሳውም አይረሳማ..........


🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂
ዘጠኘ አመት ወደ ኀላ....🏃‍♂🏃‍♂
ጠዋት ነው አስታውሳለሁ ትምህርትቤታችን እንደሁል ጊዜው ድምቅ ብሎበት ነበር፡፡ የትምህርትቤታችን ዩኒፎርም ከላይ ቀይ ሹራብ ከታች ደግሞ ሰማያዊ ሱሪ ነው ከላይ ለተመለከተን የሆነ ፍክት ያለ ጽጌሬዳ አበባ ነው ምንመስለው፡፡ በተለይ ጠዋት የሰልፍ ሰዓት፡፡

እኛን ስፖርት አስተማሪን አስታወሳችኀቸው በቦክስ የእጅ ጡንቻችንን ሚማቱት(በጣም ነው ሚያመው በተለይ ለሴቶች😂😂)
እሳቸው ተማሪው ወደ ሰልፍ እንዲገባ ያገኙትን በቦክስ እየተማቱ አስተማሪዎችም ያቺ ነጭ ከሰኞ በኀላ ደግም ወደ ሽሮ ከለር የምትቀየረዋን ጋወናቸውን ለብሰው ተማሪዎችን ከየክፍሉ ያስወጣሉ፡፡ ከሁሉም የሚያስፈራው ኬሚስትሪ አስተማሪ ቲቸር ገመቹ🏃‍♂🏃‍♂ አንቴ ሚን ቲሰራለህ ቶሎ ውጣ እንጂ አንቺ ሚናባሽ ያስገለፍጥሻሊ ፈጠን ኢያልሽ ወዴ ሰልፉ እያለ....እሺ ሚዋከበው ማትስ አስተማሪ ቲቸር ይመርስ
ዝምተኘነቷ እና እርጋታዋ ሚስበን እሷን ብቻ እንድንሰማ እሷን ስናይ ብቻ ሮጥ ሮጥ ምንለዋ ቲቸር ቦንቱ😍

ከሁሉም ደግሞ ሁሉም ሰው ሚደነብረው ፍንዳታ ሚባሉት እራሱ መጣ መጣ ተባብለው ተሽቀዳድመው ሰልፍ ቦታ ላይ ሚገኙት
( እኔ እንኳን አልፈራውም ነበር ለምን እንደሆነ አይገባኘም) በእርግጥ ምንም ነገር አላጠፋም ነበር ለዛ ይሆናል🤷‍♂ ብቻ የትምህርትቤታችን ጠቅላያችን ገዢ አሰናባች የእናቶች ለቅሶ ግድ ማይሰጠው ርዕሰ-መምህራችን #ሰማኸኘ🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

ብቻ የዛኑ ቀን ሁሉንም ተማሪዎች አብዛኛውን ሰብስበው ሰልፍ ላይ ቆምን ዛሬ ለምን እንዲ ሁሉንም ከክፍል ከሜዳ እንደሰበሰቡት እንጃ እየለ ተማሪው ይንሾካሾካል፡፡

ማይክ መጣ ሙከራ አንድ ሁለት ሶስት ተባለ ማይክ የያዘው ሰውዬ ተሽቆጥቁጦ ለርዕሰ መምህራችን ሰጠው እሱ ሲያወራ ማነው ሌላ ወሬ ሚያወራ......ዝም ለምን በተማሪ ፊት ሚማታው ምት😱😱 አስተማሪዎቹም ዩኒትሊደሮችም ከሱ ሙገሳን ለማግኘት በፊቱ ተማሪን ይኮረኩማሉ....ተማሪ ላዬ ይጮኻሉ...

ንግግሩን ጀመረ ስለጥያቄና መልስ ውድድር ነው ወይ ጉዴ አልኩኘ ትላንት ነው ውድድር የጨረስነው እኔም ክፍሌ 7A ወክዬ ተወዳድሬያለሁ ውጤተት አልተነገረንም ነበር ግን እንዲ በዚ ሁሉ ተማሪ ፊት ግን ያደርጉታለ ብዬ አላሰብኩም🤦‍♂🤦‍♂፡፡


እና ተናግሮ ተናግሮ ከሰባተኛ 7 ክፍል አንድኛ የወጣው...የወጣችው.....😳😳😳😳
#ዓባይ_አንዱአለም አላለም አስተማሪዎቼም የክፍለ ጓደኞቼም ምን እነንደነካቸው እግዜር ይወቅ እሱ ሲያወራ ቃል ማይወጣቸው አብይ ነው አብይ ነው አሉ እሱም እንደማፈር ብሎ አብይ እዱአለም ብሎ አስተካከለ ምን ውስጥ ልግባ 🤦‍♂🤦‍♂🙈🙈🙈🙊🙊🙊አፈርኩ እንዴት ብዬ ወጥቼ ነው ሽልማቴን ምቀበለው በጣም ብዙ ተማሪ ነው፡፡ ጓደኞቼም ሌሎች ሚያቁኘም እያደፋፋሩ ሔድኩኘ ሽልማቴን እና የምስክር ወረቀቴን ተቀበልኩ፡፡

ከጠዋት ቤት እስክሔድ የምስከር ወረቀቴን አላየሁትም የክላስ ተማሪዎች ሌላ ክፍሎችን እያበሸቁበት እኔ ጋር አልዋለም ነበር ስቀበለው አዲስ የነበረው ወረቀት ከሆነ ሱቅ ለዳቦ ተብሎ እንደተሰጠ ብጣሽ ወረቀት ሳስቶ እና ተጨማዶ ነበር፡፡
አሁንም የምስክር ወረቀቱ ዓባይ አንዱአለም ነው ሚለው፡፡😂😂😂ትዝታ ነው ብዬ

ይህ ሁሉ ሲሆን እኔ እሷን ነበር ምፈልጋት ከትርምሱ መሃል አየኀት ወዳለችበት ከሰው ጋር እየተጋጨው እንደምንም ደረስኩ ወደ እሷ ጠጋ ብዬ እንዲህ አልኳት ይህን ሽልማት ያገኘሁት አንቺ እዚህ ውድድር ውስጥ ስላልነበርሽ ነው አንቺ ብትኖሪ ማርያምን ሁለተኛ ነበር ምወጣው ይህ ያንቺ ሽልማት ነው አልኳት፡፡ ዝም በል ስለበለጥካቸው ነው ያሸነፍከው አለችኘ በማፈር፡፡አልወዳደርም ስትል አንተ አሸንፍ ብላ የሰጠችኘ እስኪመስለኘ ድረስ ነበር የገረመኘ
ለምን ብዬም ሞግቻታለሁ ድርቅ አለችብኘ እንጂ፡፡


ይኸው የዛሬ ዘጠኘ አመት ያገኘኀት ምርጧ እህቴቴቴ ውዴ የኔ #መቅደስ_ሲሳይ ዲግሪዋን ጭናለች እንኳን ደስ አለሽ መቅዲዬ ይህ ላንቺ ይገባሻል ከዚህም በላይ ነው የሚገባሽ ለጥቂት ያጣሽውን😡😡 ሜዳሊያ በማስተርሱ እንደምታመጪ😊💪💪😍እርግጠኛ ነኘ አንቺ ምርጥ ማርያምን ደስ ብሎኛል ጋዎንሽን ለብሰሽ እንደዛ ሱክ ሱክ ስትይእንዴት ደስ እንዳለኘ ነፍሴ እንዴት ሀሴት እንዳደረገች አታውቂም ከልብ ነበር ደስ ያለኘ፡፡

የጥንካሬ ምሳሌዋ #መቅደስ_ሲሳይ በድጋሚ እንኳን ደስ አለሽ😍😍😘😘😘😘😘🔥🔥🔥

#ምግቦቹ ደግሞ😋😋😋😋እጃቸው ይባረክ

#እግዚአብሔር_አምላክ_ከእነ_እናቱ_ድንግል_ማርያም_ጋር_የተመሰገነ_ይሁን፡፡

👏👏👏 ur bro AB ሁሌም ከጎንሽ💪💪💪
#ትህትና


አቦ ይኼማ ይነበብ.......🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂🏃‍♂

ጠብቁኘማ🏃‍♂🏃‍♂
AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

#ትህትና

ትህትና የትንሽነት ምልክት አይምሰልህ፡፡ ታላቁ መስፍን ሙሴ ታላቁ ጌታ ክርስቶስ ትሁታን ነበሩ፡፡
ባለጠግነትህ ትህትናህን ሊያሳጣህ ሲሞክር ጻድቁ አብርሃምና ጻድቁ ኢዮብን ትሁታን እንደነበሩ አስብ፡፡

ስልጣንህ ልብህን ከፍ ሲያደርግብህ
"ለንጉስ ከቀን በላይ ቀን ትጨምራለህ" በማለት የተናገረውን ዳዊትን አስብ፡፡
ምንም ብትነግስ ለራስህ አንድ ቀን መስጠት አትችልምና፡፡

ደግሞም "ሁሉም ከንቱ ነው" ያለውን ሽቅርቅሩን ንጉስ ሰለሞንን አስብ፡፡ጠቢቡን ንጉሥ "ይዲዲያ" የተባለውን በማሰብ አለባበስንና እውቀትን ናቀው፡፡

ጉልበትህ ሊያስታይብህ ሲሻ ሶምሶምን አስብ፡፡ ኃይል ከኃያላን ሥልጣንህ ከሰለጠኑት እውቀትህ ካወቁት ጋር ቢነፃፀር በጣም ትንሽ ነው፡፡

በምድራዊ ነገር ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊ ጸጋም ልትመካ አይገባህም፡፡
ትምክህት እጄ ሀብትን ጽድቄ ጸጋን አመጣልኘ ማለት በመሆኑን ቁጥሩ ከክህደት ነው፡፡

#በጸጋ_ሳይሆን_በባለጠጋው_መመካት_ግን_ተፈቅዷል፡፡

ኃጢያትህ እየበዛ ሲመጣ የሌሎች ስህተት እየታየህ ይመጣል፡፡ ጽድቅ በውስጥህ እየተስፋፋ ሲመጣ የራስህ ደካማነት ይታይሃል፡፡

ትህትና በአደባባይ እንደ ለበስከው ነጭ ሸማ ነው ታጌጥበታለህ፡፡ ትዕቢት ግን ያዋርድሃል የማያውቅህ ሳይቀር አይቶ ይፀየፍሃል፡፡ የረጅምነት ውበቱ ዝቅ ማለት ነው፡፡
ትዕቢተኛ ስትሆን ሰዎች እንከን እንዲፈልጉብህ መንገድ ትከፍታለህ፡፡

#ትህትና_ራስን_የማወቅ_ውጤት_ነው፡፡

ራሱን በትክክል የሚያውቅ ሊታበይና በሌሎች ሊፈርድ በፍፁም አይችልም፡፡ ትህትና የሌሎችኝ ክብር ማወቅ ነው፡፡ ማክበር መከበር ነውና ሌሎችን ስናከብር ትህትና ታስከብርሃለች፡፡ ትህትና ሁልጊዜ እንደሚማሩ ሆኖ መኖር ነው፡፡

ትህትና በጠፋበት ዘመን ሁሉም አስተማሪ ይሆናል፡፡
ሁሉም ሰው ቅዱስ ነኘ በማለት ሌሎችን ያጣጥላል፡፡
ጆሮ ጠፍቶ አፍ ብቻ የበዛበት ዘመን ዘመነ ትዕቢት ነው፡፡
እገሌ ክፉ ነው ማለት በተዘዋዋሪ እኔ መልካም ነኘ ማለት ነውና ትዕቢት ነው፡፡

ትህትና የሰዎችን ትልቅ ድካም አሳንሶ ትንሽ ብርታታቸውን አጉልቶ ያሳያል፡፡ ትህትና እንዳልኖሩ ሆኖ ከሌሎች ልምድን መቅሰም ነው፡፡

ከፍ ላሉት ዝቅ ማለት ትህትና አይደለም፡፡ ከፍ ያሉትማ ግርማቸው በግድ ያሰግዳል፡፡ ትህትና ዝቅ ላሉት የምናሳየው ፍቅርና ክብር ነው፡፡
ለእግረኛ ቅድሚያ ስትሰጥ አንድ ነገር አስብ:- "መኪና ለሰው እንጂ ሰው ለመኪና አልተፈጠረም ፡፡" እውነተኛ ትህትና የልብ መሰበር ያመጣልና ለንሰሃ ያበቃል፡፡

አበባ ካልታሸ አይሸትም ፍራፍሬ ካልተጨመቀ አይጠጣም ሰውም ትሁት ካልሆነ መልኩ አይወጣም፡፡ ትህትና ያወቁትነ ያለትችት ማስተማር እንጂ አላውቅም ማለት አይደለም፡፡ እያወቁ አላውቅም ማለት ልግመት ሳያውቁ አውቃለሁ ማለት እብደት ነው፡፡ ያወቁትን በትጋት ማስተላለፍ ትሕትና ነው፡፡

የተማርከው ሌሎችን ደንቆሮ ብሎ ለመሳደብ ሳይሆን በጨለማ ላሉት ብርሃን ለማወጅ ነው፡፡
የጋን ውስጥ መብራት ከመሆን የሚያድነው ትህትና ነውና ስናውቅ ትሁት እንሁን፡፡

ፍሬ ያለው ዛፍ ዘንበል ይላል ቀና የሚሉት ፍሬ የሌላቸው ናቸው፡፡ በእውነት ካወቅህ ያላወከው ስለሚበዛብህ ትሑት ትሆናለህ፡፡ በባዶ ቤት የሚያንጎራጉር ድምፁ የሚያምር ይመስለዋል ባዶ አዳራሽም ድምፅን ያስተጋባል ጩኸት ማብዛት የባዶ ቤት ምልክት ነው፡፡

#ባዶሰው_ከቀድሞ_የከፉ_የሰባት_አጋንት_ማደሪያይ_ሆናልና_እባክህ_ባዶ_አትሁን፡፡

ትህትና የልብ ነው፡፡ የልብ ያልሆነ ትሕትና የአንገት መሰበር የጉልበት መሸበር ብቻ ነው፡፡ በልብ እየናቁ በአፍ ማክበር እርሱ ትህትና ማጣት ነው፡፡ ይልቁንም ትልቁን መንግስት መንግስተ አምላክህን እየሰበክህ ትሁት ልትሆን ይገባሃል፡፡ ሐይማኖት ማለት ትህትና ማለት ነው፡፡

ሚስኪኖችና ጦም አዳሪዎችን ኃጢያተኞችና መንገድ የጠፋባቸውን ካላዘንክላቸው ስለሃይማኖትህ አልገባህም ማለት ነው፡፡
የወደቀውን ለማንሳት ዝቅ በል ወደ ሐኪም ቤት ለማድረስ አህያህን እንደደጉ ሳምራዊ ለቀህ እግረኛ ትሆናለህ፡፡

የስድብ አምሮትህን ለመወጣት "ውሾች" ይላል ቃሉ የነቀፉ ጥማትህ "ተኩላ" ይላል ቃሉ እያልክ ከተወጣኸው ሀጢያትና በቅዱስ ነገር መበደልህ ነው፡፡ ውሻ ተኩላ የያለው ጠባያቸውን ለመግለጥ እንጂ ላንተ ስድብ ለማዳበር አይደለም፡፡

ትሀትና ተፈትኜ አልጨረስኩም ብሎ በራሱ በጣም አይመካም፡፡ ገና በፈተና ዓለም ያሉ ሰዎችንም በጣም አያመሰግንም፡፡ እባክህ ወዳጄ ትሁት ሁን፡፡

#የበላይ_የበታች_ሁሉም_ልቡ_ጎረምሳ_ሁኗልና_የሚያስተነፍስ_መዓት_ሳይመጣ_ትህትናን_ገንዘብ_እናድርግ፡፡

#ትህትናን_በማጣት_ያሳዘንከውን_አምላክህን_በብዙ_ትሩፋት_አታስደስተውም፡፡

#ትህትና_የእምነት_መጀመሪያ_ነውና፡፡

የመፅሐፉን ርዕስ ካላችሁኘ ደሞ በውስጥ መስመር አናግሩኘ፡፡

@jahABP ነኘ እንደ ትህትና ምን ደስ የሚል ነገር አለ ግን😍😍መልካሞች ሁሉ ባላችሁበት ፍቅርና አክብሮቴ ይድረሳችሁ ሰላም ሁኑልኘ፡፡

😍😍 መልካም ምሽት ተመኘሁ፡፡🙏🙏

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD