ይህን መፅሐፍ ከመደርደሪያዬ ላይ ሳነሳ እነዚህን ሳላነብ አላልፍም 3:00 ይጠብቁኝ......🏃🏿🏃🏿🏃🏿🏃🏿ከብዙ ቀናት በኃላ ተመልስናል
እውነታው ሰዎች ሊያወድሱህ ከፈለጉ ከፈጣሪ ታናሽ ያደርጉሃል:: ሊዘልፉህ ከፈለጉ ደግሞ ሳጥናኤል የሚቀናበት ክፉ ያደርጉሃል::
ከሰማሃቸው ደግሞ እራስህን የመሆን እድል አይሰጡህም:: ሁሉም በፈለጉት መንገድ ሊቀርፁህ መጥረቢያ ይስላሉ:: ልብህን ከከፈትክላቸው የድርሻቸውን ጠርበው ቅርፅ አልባ ያደርጉሃል::
.
.
.
መስጠት ከመትረፍ አንጀት የሚፈልቅ ወይም ከመብዛት ማዕድ የሚዘገን አልያም ከመበልፀግ ማህፀን የሚወለድ እንዳልሆነ አውቃለሁ::
መስጠት ከመንፈስ እንጂ ከሌጣ እውቀት የተጋባ መክሊት አይመስለኝም::(መክሊት ያልኩት መስጠት ከምግባር ስለሚልቅብኝ ነው::)
.
.
.
ዛር እንዳለበት ባለውቃቢ አብሮኝ እንዳላበደ የሚያደርገኝ ጠፍቶት በስሜት እንዳልሰከረ የሱ እብደት ጎበዝ ሲያስብለው የኔ ያለመሽኮርመም ብዙ ወንድ የምታውቅ ያስብለኛል::
.
.
.
ግልፅነቴ ደንቆት አንቺን ያገኝ ወንድ አፈሰ ባለኝ ቅፅበት ለምን ታዲያ ለምን አንተ አታፍስኝም? ስለው ሴት ልጅ እንዲህ አትልም ይለኛል::
.
.
.
ሀይማኖቴ ፍቅር ነው:: የሰው ልጅ ሁሉ መውደድ:: ራሴን እወዳለሁ:: ለዛ ነው ሌሎችን የሚወድ ልብ ያለኝ:: ለራሱ ፍቅር የሌለው ለሌላው ተርፎ የሚለግሰው መውደድ አለው ብትሉኝ ያንቀኛል:: በሰውኛ ልኬት ሰውን የመውደድ ጣሪያ ራስን ከመውደድ ልክ መሆኑን ለማሳየት ይመስለኛል ክርስቶስ ከህግ ሁሉ የበላይ ህግ የትኛው መሆኑን ሲጠየቅ " ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ" ያለው::
የፈጣሪ ትርጉሙ ለኔ ፍቅር ነው:: የማላየውን ፈጣሪ ማምለክ እና መውደድ በአምሳሉ በፈጠራቸው በሰዎች ሁሉ ውስጥ አለ ብሎ ማመን እነሱን ማክበርና መውደድ ነው::
#ፍቅር_ከክፋት_በብዙ_የራቀ_ነውና_ለክፋት_የሆነ_ልብ_የለኝም::
.
.
.
የሚያውቁኝ የሚመስላቸው ሰዎች ብዙ ሲሉ እሰማለሁ:: ዳሩ እንኳን ሌሎች እራሴም ስለራሴ ነኝ ያልኩትን ላልሆን እችላለሁ::
.
.
.
ሰዎች በየቦታው ፍፁም ትክክል መስሎ ሲታዩ ሰውኛ አይመስለኝም:: ከራሱ እየተቧቀሰ አካባቢው በቀረፀለት የትክክለኛነት ሳጥን ውስጥ የሚንፈራገጥ ሰው ራሱን ያጣ አሳዛኝ ይመስለኛል:: ለእያንዳንዱ ነገር የሚጠነቀቅ ሰው እራሱን እንዳልሆነ ነው የሚገባኝ:: ራስን መሆን እርማት አይጠይቅም:: ጥንቃቄም አያሻም:: መጠኑ ቢለያይም ሁላችንም ጋር ጥቂት እብደት ጥቂትም ስህተት ጥቂትም ፀፀት እና ጥቂትም ውድቀት አለ ብዬ አስባለሁ::
.
.
.
በልጅነቷ አባቷ ሲሞቱ እናቷ ለቅርብ ወዳጃቸው ለአዳዳ እንዲያሳድጟት በአደራ ሰጥተዋት ነው ዛሬ ከእናቷ በላይ የምትወዳቸው አዳዳን ያገኘቻቸው:: ምንም አይነት የደም ትስስር እንደሌላቸው ማውራት አትፈልግም የሴትየዋን ጥሩነት በዝምድና ትስስር ስትለውሰው ግራ ያጋባኛል:: በምን ሒሳብ በደም መቀላቀሉ የሴትየዋን ውለታ እንደሚያከብደው አይገለጥልኝም:: እንደ እኔ እንደውም ያለ ምንም የደም ግምድ ድግ መሆናቸው ዋጋቸውን የሚጨምረው ይመስለኛል::
#ጠበኛ_እውነቶች_በሜሪ_ፈለቀ
ምን አይነት ደስ የሚል አፃፃፍ ነው ቀጣይ ስራሽን በጉጉት እንጠብቃለን::
አብይ የማርያም ልጅ ነኝ @jahABP
ይህን መፅሐፍ ከመደርደሪያዬ ላይ ሳነሳ እነዚህን ሳላነብ እልቀርም .........እንቀጥላለን
@ABPGD @ABPGD @ABPGD

AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN
#ጠንካራ_እምነት_ሊመጣ_የሚችለው_የእምነት_ጀግኖች_አባቶቻችንን_የሠሩትን_አብነት_በማድረግ_ነው::
በአባቶች ዘመን ለእያንዳንዷ የሃይማኖት ነጥብ ብሔራዊም ሆነ ዓለም አቀፋዊ ጉባዔያት ይጠሩ ነበር:: በዚህ ጉዳይ ላይ ቅዱሳን ሃይማኖታቸውን እንዲጠበቅ ትክክለኛውን መሠረታዊ ትምህርት እንዲታወቅ ድንቅ የሆነ ሚና ተጫውተዋል::
የሚያገኙት ግላዊ ጥቅም ሣይኖር በግል የሚጎዱበትም ነገር ሳይኖር ምንቸገርኝ ያሉበት አንድም ጊዜ የለም::
ክርስትና ፍቅር ነውና ቅዱሳንም በፍቅር ውስጥ ሥላሉ ሁሉ ነገር ያሳስባቸዋል:: የሌላው ጭንቀት ጭንቀታቸው ችግሩም ችግራቸው ሆኖ ለአንዲት ቤተክርስቲያን ሲሉ ሕይወታቸውን ለመስዋትነት አቅርበው ያለዕረፍትና ያለመሰልቸት ሠርተዋል::
ቅዱሳን ምን ያህል እንደተጋደሉ ግድ ሊሰጠን ይገባል:: ቤተክርስቲያን በእውነትኛ ሃይማኖት ጥላ ስር የተሰበሰቡና ትክክለኛ ትምህርቷን የሚከተሉ ሰዎች ማህበር እንጂ የወገን ወይንም የወገናዊነት መሰባሰቢያ አይደለችም::
በየዘመናቱ ቅዱሳን ሠማዕታት የተሰቃዩበትን የተገረፉበት የተሰየፉበት ምክንያት ሃይማኖት እንጂ ሌላ እንዳልነበር አስተውል::
ይህን ደግሞ #በየገድሎቻቸው ተፅፎ ምስክር ሆኖ እናገኘዋለን::
ለምሳሌ:- ቅዱስ አትናቲዎስን ብንመለከት አራት ጊዜ ከፓትርያርክነት መንበሩ ተሠዷል በጣም አስፈሪ የነበሩ ክሶችን ሲከሰስ ሲፈረድበት ብሎም "አትናቲዎስ አንተን ዓለም ሁሉ ጠልቶሃል " ሲሉት " #እኔም_ዓለምን_ጠልቼዋለሁ " ብሎነበር የመለሰላቸው::
ዛሬ ግን በጋብቻ ወይም በፍቺ ሃይማኖት በቀላሉ ይቀየራል:: በግድ የለሽነት ወይም ባለማወቅ ከቤተክርስቲያን አገልጋዮችና አባላት ባለመስማማት ብቻ ቤተክርስቲያንን ትምህርቷን ጥሎ የሚወጣው እጅግ ብዙ ነው::
ቅዱሳን ለሃይማኖታቸው ምን ያህል እንደተጋደሉ ለእርሱ ግድ አይሰጠውም:: ምክንያቱም ይህ ሁሉ መስዋትነት የተከፈለበት ሃይማኖቱን የሚመለከተው በግድ የለሽነት ነው ያለፈው ተጋድሎ ረስቶ ስለ እምነት ወይም ስለሃይማኖት ልዩነቶች ምንም ማሰብና መጨነቅ አይፈልግም::
#ቅዱሳንን_የናቀ_ያ_ትውልድም_ሆነ_የዛሬው_የተነቀፈ_ነው::
ቅዱሳን በደግነት በጥሩ ምግባር የደረሱበት ከፍተኛ የመንፈሳዊ እድገት ደረጃ አንተን ዛሬ ባለህበት እንዳትታበይ ለሚበልጠው እንድትጥርና እድገትህ እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው:: በፊትህ ያለው መንገድ እረጅም ነው:: ነገር ግን የሚሰጥህ ጸጋ በእጅህ ልትቀበለው የቀረበ በመሆኑ ቅዱሳንን እግር በእግር እየተከተልክ በመከራ በፈተና ውስጥ እንኳን ቢሆን በቁርጠኝነት ማለፍ እንድትችል ያበረታሃል::
ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! በነፍስህ ጽናትና እምነት ለመትከል እና የማይናወጥ የማይከፋፈል ክርስቲያን ለመሆን የቅዱሳንን ሕይወት የሚናገሩትን ቅዱሳት መጻህፍት ማንበብ ያስፈልግሃል::
#ገዞ_ወደ_እግዚአብሔር
#በብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
ትርጉም #ዲያቆን_ግርማ_ባቱ
ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ
#አብይ_የማርያም_ልጅ ነኝ
መልካም ምሽት
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD

የፍጥረት ናፍቆት
"#እነሆኝ_የጌታ_ባርያ_እንደቃልህ_ይደረግልኝ"
በምድር ላይ ብዙ የማይረሱ ታሪካዊ ንግግሮችን ያደረጉ ታላላቅ ሰዎች አሉ:: ድንግሊቱ የተናገረችውን ይህን አንድ ዐረፍተ ነገር ያህል ግን የሰው ልጅን ታሪክ የለወጠ ቃል የለም::
ይህ ቃል እንደዋዛ ከሌሎች ቃላት ተርታ መፃፍ እንዴት ያስጨንቃል? በዚህ ቃል ምክንያት የሆነልንን ካሰብነው እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ ዐረፍተ ነገር #በወርቅ_ቀለም መፃፍ የሚገባው ቃል ነው:: ይህ ቃል #በብርሃናዊ ብዕር #በቅዱሳን_እጅ ብቻ ሊፃፍ የሚገባው ቃል ነበረ::
ሰማይንና ምድርን ያገናኘ ይሔ ቃል እንዴት እንዲሁ አንብበን እናልፈዋለን?? ይህ ዐረፍተ ነገር በሐዲስ ኪዳን ለተፃፉት ለሌሎች ቃላት ሁሉ መነሻ ነበር:: ይህ ዐረፍተ ነገር የሰው ልጆችም እግዚአብሔርም ተጠባብቀው የሰሙት ድንቅ ቃል ነው::
#የዚህን_ዓረፍተ_ነገር_ያህል_የሰው_ልጅን_ታሪክ_የለወጠ_ቃል_ከፍጡር_እንደበት_ተሰምቶ አይታወቅም::
ብዙ ከማትናገረዋ የዓስራ አምስት ዓመት ብላቴና ድንግል ማርያም አፍ የወጡት እነዚህ ውድ ቃላት በመነገራቸው ያስከተሉት ነገር ፍጥረታትን ሁሉ ለዘመናት ሲናገሩ ውለው ቢያድሩ ሊያመጡት የማይችሉት ነገር ነው::
ይህ ቃል #እግዚአብሔር_ወልድን_ከዙፋኑ_ሰው_ለመሆን የጠራ ቃል ነው::
ይህ ቃል #የገነት_በርን_ያስከፈተ #የኪሩቤልን_ሰይፍ_ያስጣለ_ቃል_ነበር::
ይህ ቃል #የፍጥረትን_ናፍቆት የሆነውን የእግዚአብሔርን ልጅ መገለጥ የወጠነ #የምህረት_ዘመንን ያስጀመረ
#ዘመን_ለማቆጠርለት አምላክ ዘመን እንዲቆጠርለት የማስጀመሪያ ቃል ነበር::
ይህ ቃል 'ብርሃን ይሁን' ብሎ የዓለምን ጨለማ ካበራው የእግዚአብሔር ቃል የሚተያይ የማይጠፋው የዓለም ብርሃን ክርስቶስ እንዲመጣ በጨለማ በሞት ጥላ ለሔደ ሕዝብ እንዲበራ ምክንያት የሆነ ቃል ነው::
ይህ በገሊላዋ ብላቴና የተነገረ ቃል ክርስትናን የመሰረተ ቤተክርስቲያንን የሰራ ቃል ነው::
ድንግል ማርያም የቅዱስ ገብርዔልን ብስራት ከሰማች በኃላ የምትሰጠው መልስ ለአምላክ ሰው መሆንና ለሰው ልጆች መዳን እጅግ ወሳኝ ነው:: እግዚአብሔር ነፃ ፈቃዷን ያከብራልና ድንግሊቱ የፈለግችውን ለመመለስ መብት ነበራት::
ስለዚህ ሕይወቷን መሉ ለሚያስከፍላት ለዚህ የእናትነት አገልግሎት መመረጧን መልአኩ ቅዱስ ገብርዔል አብራርቶ ከነገራት በኃላ መልሷን ቆም ብሎ መጠበቅ ነበረበት::
የእርሷን ምላሽ የሚጠብቀው መልአኩ ብቻ ሳይሆን ገብርኤልን ልኮ ያስነገራት እግዚአብሔርም ነበር::
እኛ የሰው ልጆች ሁላችን መልሷን እየጠበቅን ነበር::
ድንግሊቱ አምላክ ከእርስዋ ሊወለድ እንደመረጣት ስትሰማም 'እነሆኝ' ራሷን አቀረበች::
ሰውነቷን ዙፋን አድርጎ እንዲያድርበት ማህፀኗን ከተማ አድርጎ እንዲያርፍበት ስጋዋን ምን አድርጎ እንዲፈልቅበት እነሆኝ አለች::
እግዚአብሔር ራሱን ለዓለም አሳልፎ እንዲሰጥ ድንግል ማርያም አስቀድማ ራስዋን ለእግዚአብሔር አሳልፋ መስጠት ነበረባት::
ስለዚህ እነሆኝ ብላ ራስዋን ለፈጣሪ አስረከበች:: አንድያ ልጁን ለአለም ይሰጥ ዘንድ የወደደው እግዚአብሔርሔርም ለዓለም ከመስጠቱ አስቀድሞ ለድንግሊቱ ሰጣት::
የሰው ልጆች 'አማኑኤል' 'እግዚአብሔር ከእኛጋር ሆነ' ብለን ደስ እንድንሰኝ አስቀድሞ እግዚአብሔር ከድንግሊቱ ጋር ሆነ'
ድንግሊቱ የተናገረችው ቃል ተከትሎ የሆነው ነገ ከዚያም በኃላ ማንኛውም ፍጡር በአንደበቱ ተናግሮ ከተፈፀመው ነገር ሁሉ እጅግ የከበረ ነው::
#ኤልያስ በፃድቅ ሰው ፀሎቱ ሰማይን ለጉሞ ዝናም እዳይዘንብም እንዲዘንብም አደረገ::
#ኢያሱ 'በገባዖን ላይ ፀሐይ ትቁም በኤሎም ጨረቃ' ብሎ ተናግሮ ፀሐይን አቆመ::
ሐዋርያት 'ተነሣና ተመላለስ' ብለው ሽባውን አስነሱ:: 'ጣቢታ ሆይ ተነሽ' ብለውሬሳ ቀሰቀሱ::
ድንግል ማርያም ግን እግዚአብሔርን ከዙፋኑ ድረስ በቃልዋ የጠራችው:: ይሁንልኝ ብላ እንደኤልያስ ዝናም ከመለጎምና ከማዝነም አልፋ ንጹሑን ዝናም በእርስዋ እንዲያድር አደረገችው:: ይሁንልኝ ብላ እንደ እያሱ ፀሐይን ከማቆም በላይ የፀሐዮችን ፀሐይ በሆድዋ ውስጥ እንዲያበራ በቃልዋ ጠራችው::
በእውነት ይህች ድንግል ስለእርስዋ 'ታማልዳለች ወይ አታማልድም' በሚል ተራ ክርክር ላጠፋነው ጊዜ ይቅ ትበለን:: ወዳጄ የአንተ ጊዜያዊ ችግር ለመፍታት ማንኛውም ተራ ሰው ሊፀልይልህ ይችላል:: ቅዱስ ጳውሎስም 'ለሁላችን ምልጃ ይደረግ' 'ስለእናንተ ሲያማልዱ ይናፍቋችኃል' 'ክፉ ሲናጉሩን እንማልዳለን' ብሎ እርስ በእርሳችን አንዳችን ለሌላችን ልንማልድ እንድምንችል ጽፎአል::
መቼም አብዛኝው ጥያቄያችን ከሥጋ አያልፍምና ደህና ገንዘብ ሥልጣን ያለውም ሰው የአንተን ችግር ለመፍታት አያንስም:: 'ይሁንልኝ' የሚል የእምነት ቃልዋን ተናግራ ሰማይና ምድርን በማሕፀንዋ ያስታረቀችን የእግዚአብሔር ውድ ፍጥረት ድንግል ማርያም አንተን አማልዶ ማስታረቅ ትልቅ ነገር የሚሆንባት ይመስልኃል???
#እመቤቴ_ሆይ የአንቺ 'ይሁንልኝ' የሚል ቃል ተከትሎ እግዚአብሔር ሰው ሆነ::
ሰው ሆኜ ተፈጥሬ ሰው መሆን ያቃተኝን እኔስ #ሰው_የምታደርጊኝ_መች_ይሆን??🥺🥺
አምላክ ሰው እንዲሆን ይሁን ያልሽዋ ሆይ ስለ እኔ ሰው መሆን 'ይሁን' የምትይው መቼ ይሆን? 'በርታ ሰውም ሁን' የሚለው ቃል መጠበቅ አቅቶኝ ኃጢያት ሰልጥኖብኝ 'ሰው ክቡር ሆኖ ሳለ አላወቀም እንድሚጠፋው እንስሳት መሰለ' የሚያሰኝ ሕይወት ለምኖረው ለእኔ እንደቃሉ መሆን ላቃተኝ ለኔ ወደ መሐሪው ልጅሽ...
'ይህ ሐጢያተኛ ባሪያህ እንደቃልህ ይሁንልኝ' ብለሽ እኔንም እንደቃሉ የምታደርጊኝ መቼ ይሆን??
#የብርሃን_እናት
ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ
ምን አይነት ድንቅ ፅሁፍ ነው በድንግል ስም
መምህራችን ድንግል ማርያም ከዚህ በላይ ፀጋህን ታብዛልህ::
እንደው ይህን አንብበው ትንሽ እራሳቸውን ቆም ብለው እንዲያስቡ ይህንን ፅሁፍ ላኩላቸው::
አብይ የማርይም ልጅ ነኝ
ለንባብ እንዲመች አድርጌ አቀረብኩት

AB PHOTOGRAPHY &GRAPHIC DESIGN
#መዓዛ_ምግባር
የክፎች መዓዛ ምግባር እንዳይሸትህ አፍንጫህን ያዝ::
እንዲሁም ክፉ ተናግረው እንዳያናግሩህ አፍህን መዝጋትና ለግፍ ሳቃቸው ተካፋይ እንዳያደጉህ ከንፈርህን መግጠም እግዚአብሔር ላዘጋጀልህ ለዘለዓለም ደስታ ብቁ ሊያደርግልህ ይችላል:: ይህንንም የመሰለ ምግባራዊ ጥንቃቄ በእውነት ደረጃ ላይ ሊያውልህ መቻሉ እርግጥ ነው::
መድኃኒት ያቀማመጥና ያያያዝ ጥንቃቄ ሲጎድልበት መርዝ ይሆናል:: ሰብአዊ ኑሮም ይህን የመሰለው ሕይወታዊ ድርጅት ሳይደረግለት ቢቀር የመጥፎ ዕድል ባልደረባ አድርጎ ያስቀራል::
ሰው በምግባሩ በኩል ቅዱስ ለመሆን ከፈለግ ሰይጣን በበኩሉ ያስወጣቸውን ደንቦች ለመቃወም ሲችል እሱ ከክፋት የራቀውን ያህል ክፋት ከሱ እየራቀ መሔዱ የታወቀ ነው::
የዓለም ክፋት ትዝ እያላቸው ከዓለም የሚሸሹትን ደጋግ ሰዎች እንኳ ሳይቀር ሐተታውን ለመከታተል የማይቻል ፈተና ቢደርስባቸውም በመጨረሻው ድልን ለማግኘት መቻላቸው የታወቀ መሆኑ አይዘነጋም::
ለምሳሌ:- #አባ_መቃርስ የሚባል መንፈሳዊ አርበኛ ሰይጣን ይሠራው ዘንድ ደግ አስመስሎ የሚያመጣውን የክፋት ሥራ ሁሉ እየተቃወመና ዘወትር ዝንባሌው ወደ ደግነት እየሆነ ቢያስቸግረው መቃሪ መቃሪ ብሎ ጠርቶ ዛሬስ በእውነቱ አሸነፍከኝ አለው ይባላል::
የደግነት አርበኞች ሁሉ የመጨረሻ ድላቸው እንደዚህ ነው::
መንፈሳዊ ጦርነት ዘወትር ድልን ማግኘት አለበት:: እንደ ሥጋዊ ጦርነት ድል ብሆንም ከዱር ገብቼ በሽፍንነት እከላከላለሁ ሊባል አይችልም:: ብማረክም በወጆ እለቀቀቃለሁ ተብሎ ተስፋ የሚጥሉበት አይደለም::
በሥነ ምግባር ጠንክሮ ተከላክሎ ጠላትን ከማሸነፍ በቀር በሰይጣን ጥፍር ከተያዙ በኃላ ሌላ ማምለጫ የለም::
እንደ ቆሮንቶስ ፍፁም ብሕትውና የተደረገበት ገዳም የለም:: እንዲሁም ሰይጣን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት የሆነውን ድል በማንም ፊት ሆኖ አያውቅም::
ከሰይጣን ጋር በትሩፋት የሚዋጋ ቶሎ ልብቃ ቶሎ ክንፍ ላውጣ ማለት ገና የወጣኒነትን ደረጃ ሳያልፈው ሰይጣን በምትሃቱ ጠልፎ እንዲወድቅ ያደርገዋል:: ማንኛውም ስራ ይህን በመሰለ ዕንቅፋት መሰናክል ስለምይቀርለት ሁሉን ነገር አስተውሎ ማድረግ ይጠቅማል::
ኃጢያት የዲያቢሎስ አመጽመ ርስት ነው በል በል የሚልህን አሳብ ተዋግተህ ድል ያደረግህ እንደሆነ የጽድቅህ መገለጫ በዚያ ጊዜ ነው::
አሰሪ መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ ሰይጣን አይደለም:: ስለዚህ ከእንደዚህ ያለው አሠሪ ለመለየት አሰናባች የሆነ ክፉ ምግባር አይኑርህ:: ምዝለቂያህና መውጫህን ተመልከት:: መግቢያህንም አስተውል:: ፍፃሜህን አትዘንጋ:: ልብ አለና ልብ የሌለህ አትሁን:: ሰው ነህና ከሰውነት የወጣ ስራ አትስራ:: ነገርህ ሁሉ ጨው ያነሰው ፍትፍት አይሁን:: ምግባርህን ያረረ ዳቦ አታድርገው:: ከከንፈርህም የሬት ልጋግ አይዝነም ::
ወጣት ሆይ ነሆ ለጥበብ ተጠርተኃል:: ጥበብም ዕድመኛ አድርጋሃለች:: አስከትላህ ወዴት እንድምትሔድ መንገዱ የሕይወት ነው:: መድረሻው የክብር ሥፍራ ነው:: ፈሪሃ እግዚአብሔር ለልብህ እንደከንፈር መዓር ይሁነው:: ሰው እንዳይሆን የለምና ንገ የምትሆነውን ዛሬ ለነገ ኑሮ ዋዜማ ነው:: ይህ ሁሉ ሲሆን የምትከተለውም የሚከተልህ የአምላክ ሕግ ነው::
ለሁሉም ነገር ዋና ስራ አስኪያጅ ግብረገብነት ነው:: ግብረ ገብ የሆነ ሰው ትእዛዛት ሁሉ አይከብዱትም:: ግብረ ገብያልሆነ ግን እንኳን ከባዱ ትእዛዛትና አነስተኛውም ቢሆን ስለሚከብደው ሲያዝዙ ይቆልፈዋል:: በግድም ሆነ በውድ የታዘዘውን መፈፀሙ ላይቀር ይፍተለተላል ይተሻሻል::
ስለዚህ በብሩህ ገጽ ትዕዛዝን ተቀብሎ መሥራት ያስመሰግናል:: ያስሾማል ያስሸልማል ይህ እድል ህይወተ ነፍስንም ይከተላል: የዚህም ሁሉ የቅርብና የሩቅ መነጥሩ ሃይማኖትና ምግባር ነው:: በጎ ምግባር ካለህ በፊትህ ዕንቅፋት አያጋጥምህም:: በኃላ አስጊ የለብህም በደስታ የተከበብክ በይባቤ የታጀብክ ሁነህ እግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር ለወዳጆቹ ወዳዘጋጀው ወደ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ትችላለህ::
ጥንት ጠላታችን ዲያቢሎስ እጅ ባይሰጥም ለሚያቀርብልን ክፉ ስራ አለመሸነፍ የማሸነፍ ያህል ነው::
#ሥነ-ምግባር
ተፃፈ #ከወልድ_ጊዮርጊስ_ወልደ_ዮሐንስ
አብይ የማርያም ልጅ ነኝ

AB PHOTOGRAPHY @abiy_yemaryam_lej
#የቤተክርቲያን_ብርሃን_ቅዱስ_ያሬድ
ቅዱስ ያሬድ ዜማውን በሚያዜምበት ጊዜ ጣዕመ ዜማውን ሲሰሙ አዕዋፍ በስማይ ክንፋቸውን ረበው ሲግጟዙ በመሬት እንስሳት አራዊት ይከተሉት ነበር:: የተጠመዱ በሬዎች እንኳን ሳይቀሩ ዜማውን ይከተሉ ነበር::
#ወላዲተ_አምላክ #እመአምላክ #አማላጄ
#ፅጌ_ፀዓዳ
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #ገድለ_ቅዱሳን
#street_photography
#best #awesome #timing
#photoshoot
#our #lovely😍 #Ethiopia

ሃይማኖትህን ያለ ሀገር ሆነህ የትም ልታከብረው ትችል ይሆናል ሀገር ስታጣ ግን ሁሉ ታጣለህ:: ኦርቶዶክስን ግብፅ እስልምናን መካ መዲና ካቶሊክን ቫቲካን ፕሮቴስታንትን ጀርመን ታገኝ ይሆናል:: ኢትዮጵያ ግን የትም የለችም:: ሃይማኖታችን የምኖደው ኢትዮጵያን ቀድሶ ስለሰጠን ነው ኢትዮጵያን የምንወዳት ሃይማኖታችንን እጅግ መንፈሳዊና ከፈጣሪ ጋር የሚያገናኘን ንጹህ መንገድ ስላደረገችልን
4:00 ላይ ይጠብቁኝ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
4:00 ላይ ይጠብቁኝ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
AB PHOTOGRAPHY & graphic design
#ጥበብ
የንጉስ ሰሎሞንን ዝና ሰምታ ከጥበቡ ጥበብ ከእምልኮው አምልኮ ልትቀስም ንግስተ አዜብ ማክዳ ጥበብን ናፈቀች::
የመንገዱን ርዝመትና አስቸጋሪነት በአግባቡ የተረዳችው ቢሆንም ለንግስት ማክዳ ከድካም በላይ ጥበብ በለጠችባት::
አማካሪዎቿም " እመቤታችን ሆይ! ጥበብ እኮ ካንቺም አልታጣም! ጥበብን አጥብቀሽ የምትወጂው በጥበብ ነው:: ጥበብ ትጠራሻለችና:: እኛ ግን አንቺ ብትሔጂ ከአንቺጋር እንሔዳለን:: ሞትም ቢሆን ሞታችን ካንቺ ጋር ይሆናል:: ሕይወትም ቢሆን ሕይወታችን ካንቺ ጋር ይሆናል " አሏት
ንግስተ ሳባ ማክዳ የንግስትነት ክብሯ ሳይከለክላት የሴትነት ጉልበቷ ሳያግዳት ጥበብን ፍለጋ ተራራ ወጥታ ቁልቁለት ወርዳ ጋር ሸንተረር አልፋ ባህር ብረኃ አቋርጣ ተሻግራ ወደ ኢየሩሳሌም ረጅሙን ጉዞ ተጟዙች::
797 ግመል ቁጥሩ በማይትወቅ በቅሎዎችና አጋሰሶች ብዙ ወርቅ ብር የዝሆን ጥርስ ሽቱ የከበሩ ድንጋዮች ለስጦታ ተጭኖ ትልቅ ቅፍለት ይዘው ወደ ቀይባህር ዳርቻ ተጟዙ:: በብዙ መርከቦች ተሻግራ የዐረቢያን በረኃ አቋርጣ ኢየሩሳሌም ደረሰች::
የጥንካራዋ ሴት ልጆች ነን:: የዚች ባለ ብሩህ አእምሮ ንግስት ልጆች ከጥበብ ማዶ ሆነን ከዓለም ስልጣኔ ጭራ ሁነን መገኝታችንን ዛሬ ተነስተን ብታይ ምን ትለን ይሆን? ጥበብን ፍለጋ ሳይሆን ሳንቲም ፍለጋበዓለም ሁሉ እንደ ጨው ዘር የምንበተን ምስኪን ሕዝቦች መሆናችን ብታይ እንዴ ታዝንብን ይሆን??
የንግስት ማክዳ ልጆች ነን የጥበብ ፈላጊዋ የጥበብ አሳሿ መቼ ይሆን ወደ ጥንት ክብራችን እንመለስ ብለን ሆ ብለን የምንነሳው የሞራልና የደግነት የአብሮነት የታታሪነት የጀግንነት የነፃነት ልዕልና የአልፋ ኦሜጋ ጥበብ ባለቤት ለመሆን በቁጭት የምንነሳው?!
ንግሥተ አዜብ ማክዳ ኢየሩሳሌም እንደደረሰች ንጉስ ሰሎሞን በክብር ተቅበላት:: ጥበቡን ሁሉ አካፈላት:: ያቀረበችለትን እንቆቅልሾች ሁሉ ፈትቶ ጥበበኝነቱን አረጋገጠላት:: የአባቶቹን የአብርሃም የይስሐቅ የያዕቆብ አምላክ ሥርዓተ አምልኮና የታቦተ ጽዮንን ቃልኪዳን ሁሉ አስረዳት::
የቤተ መንግስቱን ባለሟሎች ስንዱነት ሁሉን አነሳያት:: ለጉብኝቷ ማስታወሻ ለሀገሯ ስም መጠሪያ ይሆን ዘንድ በኢየሩሳሌምና ባቅራቢያዋ ርዕስት ጉልላት ሰጣት:: ለውበቷ ለንፅህናዋ ልብሩህ አዕምሮዋ አድናቆት ልብ አልቀረለትም ነበርና በፍቅሯ ወደቀ::
ከማህፀኗ ዘር ያስቀር ዘንድ ተጋ:: እናም ሆነ! እርሱም ለእርሷም በኩር የሚሆነውን ልጁን ከሀገሯ ተመልሳ ቀዳማዊ ምኒልክን (እብነ ሀኪም) ውለድች::
ክጉዞዋ መልስም የተመኘችውን ጥበብ የሰሎሞንን ማስተዋን በጥልቅ እንደቀሰመች ተናገረች::
"ወድ ጥበብ በር ዘልቄ ገባሁ:: ወድ ጥልቁ መረዳት ሰመጥሁ:: ወደ ዕውቀት ጮራ አቀናሁ በእኔምልይ ጥበብ ብርሃኗን አበራች:: ጥበብን ጋሻ አደረኳት በራስ መተማመኔ ጠበቅሁ::ደግሞም ለእኔ ብቻ አይደለም ጥበብን ፍለጋ ለተጟዙ ሁሉ ለሀገሬ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ለሀገሬ ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ሁሉ እንጅ::"
ድግሞም አለች:
" ከእንግዲህ ወገኖቼ! እውነትን ውደዱ ሐሰትን ጥሉ:: አዎን! ሽፍጥን ጭቆናን በእናንተ ዘንድ አስወግዱ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ነውና እናንተም በአንድ አምላክ ሥር ቤተሰብ ሆናችኃልና!"
ቀዳማዊ ምንትልክም በጥበብና በሞገ አደገ:: እናቱ ንግስት ማክዳ አባቱን እንዲጎበኝ ወደ ኢየረሳሌም ላከችው:: በጉብኝቱም በአባቱ በንጉስ ሰሎሞን ፊት ሞገስን አገኘ:: አባቱ በእጅጉ ወደደው:: በመንበሩ ሊላስቀምጠው በመንግስቱ ሊሰይመው በልቡ ፈቀደ:: ይህንንም ነገር አለው:-
"እግዚእብሔር ከወደድ እስከ እባቴ ዕድሜ ድረስ ያድርሰኝ:: ወደ አብባቴና አባቶቼ ከተወሰድኩ እንተ በዙፋኔ ላይ ትቅመጣለህ:: በእኔ ፋንታም ትነግሳለህ:: የእስራኤል ሊቃውንት ፍሞ ይወዱሃል:: እኔን ድድካማው በአባቶቼ ዙፋን ታየኛለህ:: ከእኔም በኃላ አንተ እንደኔ ትሆናለህ::"
አባቱ ጥበበኛው ንጉስ ስሎሞን በእስራኤል ሀገር ከእርሱ ዝንድ ቢቀር መንግስትን እንድሚያወርሰው ዙፋኑን እንድሚሰጠው ነገረው:: የከበረችውን ታቦተ ጽዮን መማፀኛው ትህነ ዘንድ ባቅራብያዋ እንድእሚሆን ጥበቡንና ሁብቱን ሁሉ እንደሚሰጠው ቃል ግባለት:: እንደወጣትነቱም ውብ ልዕልት ወዕቁባት እንድሚድርለት ነግሮ አባበለው::
ቀዳማዊ ምንልክ ግን ክዚህ ሁሉ ሥልጣንና ተድል ይልቅ እናቱንና የእናቱን ሀገር ኢትዮጵያ በለጡበት::
እናም:- "ጌታዬ አባቴሆ! እናቴንና ሀገሬን እተው ዘንድ አይቻለኝም:: እናቴ በቶሎ ወደ እርሷ እንድመለስ እንጂ እዚህ እንዳልቀር በጡቶቿ አምላኛለች የእስራኤል አምላክ ታቦትም ባለሁበት ትባርከኝ:: ፊትህን ላይ ቃልህን ልስማ በረከትህንም ልቅበል ወድ እናቴም በድህና እሔድ ዘንድ ሽቻለሁና ጸሎትህ በሄድኩበት ትከተለኝ" አለው ቁርጥ አድርጎ::
ሃይማኖትህን ያለ ሀገር ሆነህ የትም ልታከብረው ትችል ይሆናል ሀገር ስታጣ ግን ሁሉ ታጣለህ:: ኦርቶዶክስን ግብፅ እስልምናን መካ መዲና ካቶሊክን ቫቲካን ፕሮቴስታንትን ጀርመን ታገኝ ይሆናል:: #ኢትዮጵያ_ግን_የትም_የለችም:: #ሃይማኖታችን_የምኖደው_ኢትዮጵያን_ቀድሶ_ስለሰጠን_ነው #ኢትዮጵያን_የምንወዳት_ሃይማኖታችንን_እጅግ_መንፈሳዊና_ከፈጣሪ_ጋር_የሚያገናኘን_ንጹህ_መንገድ_ስላደረገችልን_ነው::
<እኛም የንግስት ማክዳ ልጆች ነን የጥበብ ፈላጊዋ የጥበብ አሳሿ አኦን የቀዳማዊ ምኒል ልጆች ነን እናት ሀገራችንን ፍፁም ወዳጅ ሥልጣን ምቾት የማይለውጠን ታማኝ!> ለማለት መቼ ይሆን የምንደፍረው!
የልጁን ቁርጥ ቃል የሰማው ንጉ ሰሎሞን ልቡ ታወከ:: ልቡ የወደደውን የበኩር ልጁ በእርሱ ዝእንድ እንደማይቆይ ተረዳ:: እናም መንገዱን ሊያሰናክልበት አልፈቀድም:: ሹማምቱና ሽማግሌዎቹን በየነገዳቸው ጠርቶ:
"የአብራኬ ክፋይ የበኩር ልጄ ተመልሶ ወደእናቱና ሀገሩ ሊሔሄድ ነው:: እናም ብቻውን ይሔድ ዝንድ አይገባምና የእስራኤል በኩር ሁሉ አብሮት ይሂድ!" አለ::
<ክብረ ነገስት> የተባለው ጥንታዊ መጽሐፍ እንድሚተርክልን በዚህ ውሳኔ መሠረት ቀዳማዊ ምኒልክ በብዙ እስራኤላውያን በኩራት ታጅቦ ታቦት ጽዮንን በስጢር ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ::
#ሚተራሊዮን
#ዓለማየሁ_ዋሴ_እሸቴ

ለwallpaper ሞክሩት እመቤቴን ሲያምር
#ወላዲተ_አምላክ #እመአምላክ #አማላጄ
#ፅጌ_ፀዓዳ
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #ገድለ_ቅዱሳን
#street_photography
#best #awesome #timing
#photoshoot
#our #lovely😍 #Ethiopia
ለwallpaper ሞክሩት እመቤቴን ሲያምር
#ወላዲተ_አምላክ #እመአምላክ #አማላጄ
#ፅጌ_ፀዓዳ
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #ገድለ_ቅዱሳን
#street_photography
#best #awesome #timing
#photoshoot
#our #lovely😍 #Ethiopia