"የሚፅፋ ሰዎች ያስደስቱኛል ዕውቀትና ሐሳብ ማካፈል በጣም ጥሩ ነው፡፡
አንድ ሰው አእምሮው ካልሰራ በሌሎች ነገሮች ብቻ መኖር አይችልም እኮ፡፡ አእምሮው እንዲሰራ ደግሞ ማሰብ አለበት ፣ እንዲያስብ ደግሞ ዕውቀት የሚያካፍለው ያስፈልጋል፡፡ መብላትና መጠጣት እንድትቆይ እንጂ እንድትኖር አያደርጉህም፡፡
መኖር እና መቆየት ሚለያዩ ይመስለኛል -
መኖር የህሊና መቆየት ግን የአካል ነው፡፡
እየበላህና እየጠጣህ ሳትሞት ብዙ ዘመን መቆየት ትችል ይሆናል፡፡ በመብላትና በመጠጣት ብቻ ግን መኖር አትችልም፡፡ ለመኖር የህሊና ምግብ ያስፈልግሃል፡፡
አንድ የአጎቴ ጓደኛው ሰውን <ለማሰብ የሚበላ> እና <ለመብላትየሚያስብ>ብሎ ሲከፍል ሰምቼዋለሁ፡፡
እንደ እኔ ይቺ ዓለም የሰዎች መኖሪያ እንጂ መቆያ መሆን የለባትም ብዬ አምናለሁ፡፡
ሰዎች እንዲኖሩ ደሞ የኅሊና ምግቦች ያስፈልጓቸዋል፡፡ የሚነበቡ ፣ የሚታዩ ፣ የሚጎበኙ ፣ የሚደመጡ ነገሮች፡፡ ምግብ ስንበላ እኮ ቀጥታ ደም ስራችን ውስጥ አይገባም፡፡ የራሱ የሆነ ሒደት አለው፡፡ በዚያ ሒደት ብዙ አካላት ይሳተፋሉ፡፡ አእምሮም እኮ የሚያላምጠው የሚፈጨው ነገር ይፈልጋል፡፡
ወዲያና ወዲህ የሚያመላልሰው፡፡ ይህንን ከሚሰጡን ሰዎች መካከል መፅሐፍት ናቸው ፡፡ ለዚህ ነው የሚፅፋ ሰዎች የሚያስደስቱኘ፡፡ "
ሙሃዘ-ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
<እኛ የመጨረሻዎቹ> እና ሌሎችም
ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተወሰደ
አስተያየታችሁን @JahABP አድርሱን
ሼር በማድረግ ለጓደኞቻቹ አድርሷቸው
@ABPGD @ABPGD @ABPGD