Addis መረጃ™
35.3K subscribers
9.54K photos
279 videos
27 files
1.11K links
@Addis_Mereja ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹
.
⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬
⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬

መረጃዎችን ለመላክ @Adis_Merejaa_bot
Download Telegram
ጆን መዲድ ከድቶናል-ህወሓት

ህወሓት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጄኔራል ዮሐንስ ወልደጊዮርጊስ በቅፅል ስሙ ጆን መዲድ ከድቶናል፣ከማዕከላዊ የጦር አዛዥነት ተነስቷል ያለ ሲሆን በትግላችን ውስጥ የተከሰቱ እና እየተከሰቱ ያሉ ከዳተኞች እና ከሃዲዎች አሉ ያለ ሲሆን ትግላችን በግለሰብ ከሃዲዎች እና ከዳተኞች አይቃጠልም፣አይሸነፍም ብሏል።

@Addis_Mereja
❤12🔥1👏1🍾1👀1
ኢትዮጵያ 12 አዳዲስ ዘመናዊ
የጦር ጄቶችን ከሩሲያ ተረከበች!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እንዳስታወቁት፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሉዓላዊነቱን ለማስጠበቅና ማንኛውንም ጥቃት ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችለውን አቅም እየገነባ ነው።ከሩሲያ ጋር በነበራቸው ስምምነት መሠረትም ሀገራችን የመጀመሪያዎቹን 12 ዘመናዊ የሱ-35 (Su-35) የጦር ጄቶች ዛሬ በይፋ ተረክባለች፤ በቀጣይም አራት የኤስ-400 (S-400) የአየር መከላከያ ሲስተሞች እንደምትረከብ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስምምነቱ ከተያዘለት ጊዜ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ አውሮፕላኖቹን እንዲረከቡ ላደረጉት ትጋት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

@Addis_Mereja
❤23👍3🔥1🍾1🤝1
ኢትዮጵያ ዘመናዊ የሆኑትን ሱ-35 የጦር ጄቶች በመታጠቅ ከአልጄሪያ ቀጥሎ በአፍሪካ ሁለተኛዋ አገር ናት‼️

ብዙ የተባለለትን ይህን የጦር ጄት በተመለከተ ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቆይታ ያደረጉት አንጋፋው የጦር አውሮፕላን አብራሪ እና አሠልጣኝ ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ፣ ኢትዮጵያ እነዚህን ዘመናዊ ጄቶች መታጠቋ እንዳስደነቃቸው ይገልፃሉ።

"በዚህ ሙያ ውስጥ እንዳለ ሰው እንዲህ አይነት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ አገር ስትታጠቅ የሚያመጣው ጥቅም በቀላሉ ይገባኛል" ይላሉ ካፒቴን ተሾመ።

@Addis_Mereja
❤19👎3🔥3👏1🍾1👨‍💻1😎1
በታሪክ ትልቁ የክሪፕቶከረንሲ ዘረፋ፦
ሰሜን ኮሪያ 6 ቢሊዮን ዶላር ሰረቀች ተባለ!

ጥቅምት 20 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓለም አቀፉ የዲጂታል ገንዘብ ሥርዓት ላይ እስካሁን ከተፈጸሙት ጥቃቶች ሁሉ እጅግ አስከፊው እና ትልቁ የተባለ የ6 ቢሊዮን ዶላር የክሪፕቶከረንሲ ዘረፋ ተፈጸመ።

የብሎክቼይን ደኅንነትና የምርመራ ተቋማት ባወጡት መረጃ፣ ጥቃቱን ያደራጀውና የፈጸመው በሰሜን ኮሪያ መንግሥት የሚደገፈው «ላዛረስ ግሩፕ» (Lazarus Group) የተሰኘው የታወቀ የሳይበር ሃኪንግ ቡድን ነው። ጥቃቱ የተሰነዘረው የዓለማችን ትልቁ የክሪፕቶከረንሲ ልውውጥ መድረክ በሆነው «ባይናንስ» (Binance) ላይ ሲሆን፣ ዘራፊዎቹ ወደ ሥርዓቱ የገቡት የኩባንያውን አንድ የሶፍትዌር ኢንጂነር ኮምፒውተር በመንደፍ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ የተዘረፈው የሀብት መጠን ከዚህ ቀደም በታሪክ ከፍተኛው ተብሎ ከተመዘገበው የ1.5 ቢሊዮን ዶላር ዘረፋ በአራት እጥፍ የሚበልጥ ነው የተባለ ሲሆን፣ እስካሁን ከተሰረቀው ገንዘብ ውስጥ 3 ቢሊዮን ዶላር ያህሉ በዓለም አቀፍ የመርማሪ ቡድኖች እንቅስቃሴ እንዳይንቀሳቀስ ታግዷል።

የባይናንስ ተቋም በበኩሉ በደንበኞቹ ሀብት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማይደርስና አደጋውን ሙሉ በሙሉ በራሱ ፈንድ እንደሚሸፍን ያረጋገጠ ሲሆን፣ የመርማሪ ቡድኖች ደግሞ የተረፈውን ገንዘብ ለማስመለስ የዲጂታል መረቡን አሰሳ ቀጥለውበታል።

የደቡብ ኮሪያና የአሜሪካ የደኅንነት ባለሥልጣናት እንደሚያስረዱት፣ ሰሜን ኮሪያ በከባድ ዓለም አቀፍ ማዕቀቦች ውስጥ ሆና የኑክሌርና የጦር መሣሪያ ፕሮግራሞቿን ለመደገፍ እንዲህ ያሉ ግዙፍ የዲጂታል ዘረፋዎችን እንደ ዋና የገቢ ምንጭ ትጠቀምበታለች።

@Addis_Mereja
❤29😁6👏1🍓1🍾1👀1
“የጽምዶ ኃይሎች” በስድስት ቀበሌዎች ሲንቀሳቀሱ እንደነበረ የኦሮሚያ ክልል አረጋገጠ፤ ከአንድ ሳምንት በፊትም “የግፍ ግድያ” የፈጸሙት እነዚሁ ኃይሎች ናቸው ሲል ወነጀለ!

በሽርካ ወረዳ በንጹሃን ላይ ጥቃት የፈጸሙት የ“ጽምዶ ኃይሎች” መሆናቸውን የገለጸው የኦሮሚያ ክልል፤ ስድስት ቀበሌዎችን የማጽዳት እና ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር የማዋል ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ፡፡
 
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ደቡብ ምስራቅ ዞን ሽርካ ወረዳ ከአንድ ሳምንት በፊት ራሳቸውን መከላከል በማይችሉ ንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ጥቃት ያካሄዱት “የጽንፈኛው ፋኖ እና የሸኔ” ስብስብ የሆኑት “የጽምዶ ኃይሎች” መሆናቸውን የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጥቃቱ ከተፈጸመ አንድ ሳምንት በኋላ አስታውቋል፡፡
 
የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊው ኃይሉ አዱኛ ዛሬ ለመንግስት ቅርበት ላላቸው መገናኛ ብዙኃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት፤ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም በሽርካ ወረዳ የተፈጸመው ድርጊት አገሪቱ የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ለማደናቀፍ “የታሪካዊ ጠላቶችን ተልዕኮ በመቀበል የተፈጸመ” የሽብር ተግባር ነው። እነዚህ ኃይሎች ተናብበው በመንቀሳቀስ ሕብረ ብሔራዊ በሆኑ አካባቢዎች የብሔርና የኃይማኖት ግጭት ለማስነሳት፣ “በንጹሃን ደም ለመነገድና የፖሊቲካ ጥቅም ለማግኘት” ሲሉ የዜጎችን ህይወት ማጠፋታቸውንና ንብረት ማውደማቸውን አብራርተዋልል።
 
ይህን አሰቃቂ የሽብር ድርጊት ተከትሎ የክልሉ መንግሥት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ አካሂዶታል ባሉት የተቀናጀ ኦፕሬሽን እስካሁን 73 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያደረገ ይገኛል። በተጨማሪም “የጽምዶ ኃይሎቹ”  እንቅስቃሴ ያደርጉባቸው የነበሩ ስድስት ቀበሌዎችን ሙሉ በሙሉ የማጽዳት ሥራ የተከናወነ ሲሆን፣ በአካባቢው አስተማማኝ ሰላም እስኪሰፍን ድረስ እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
 
በሌላ በኩል፣ ከጥቃቱ ጋር ተያይዞ ከመኖሪያ ቤታቸው የተፈናቀሉና የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን መልሶ ለማቋቋም ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ኃይሉ ገልጸዋል። በዚህም መሠረት ለተፈናቀሉ ዜጎች አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍና የምግብ አቅርቦት እየተደረገ ሲሆን፣ የሕክምና አገልግሎት ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ቅድሚያ ተሰጥቶ ሕክምና እንዲያገኙ እና ተፈናቃዮችን ወደ ቀደመ ቀያቸው ለመመለስ ከህዝብ ጋር ጥልቅ ውይይቶች መካሄዳቸው ተጠቅሷል።
 
በመጨረሻም የክልሉ መንግሥት ህዝቡ አገራዊ አንድነቱንና ሕብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነቱን በመጠበቅ የጠላቶችን ሴራ እንዲያከሽፍ ጥሪ አቅርቧል። በተለይም በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ፣ ጥላቻን የሚሰብኩና ግጭትን የሚያቀጣጥሉ ሀሰተኛ መረጃዎች “የታሪካዊ ጠላቶች ተላላኪዎች”  አጀንዳ መሆናቸውን ተገንዝቦ፣ ህብረተሰቡ ራሱን ከእንዲህ ዓይነት መረጃዎች እንዲጠብቅና የተመዘገቡ ልማቶችን በማስቀጠል ወደፊት እንዲራመድ አሳስበዋል።

@Addis_Mereja
❤24😁17👎6🔥2👏2🍾1👻1
የህወሓቱ ኮ/ል ሠመረ ተክሉ የ92ኛ አርማ ሎጀስቲክስ አዛዥ በመከላኪያ ሰራዊት በተደረገበት ድንገተኛ ጥቃት ከነ ጠባቂዎቹና ታጣቂው ተደምስሷል::

እንዲሁም በርካታ የቡድንና የነብሰ ወከፍ መሣሪያ 16 የእጅ ሬድዮ 06 ማን ፓክ ሬዲዮ 01 ቱሪያ ስልክ ከህገ ወጡ ህወሃት ተማርኳል።

@Addis_Mereja
❤10👍1🔥1
የኤችአይቪን ስርጭት ይገታል የተባለዉ መድኃኒት ለ120 አገራት ሊቀርብ ነው‼️

የአሜሪካው የምግብና መድኃኒት አስተዳደር በዓመት ሁለት ጊዜ ብቻ በመውጋት የኤችአይቪ/ኤድስን ስርጭት ለመከላከል የሚያስችለውን "ሊናካፓቪር"  የተባለ መድኃኒት አጸደቀ። ይህም መድኃኒቱ በዝቅተኛ የገቢ ደረጃ ላይ ለሚገኙ 120 አገራት በዝቅተኛ ዋጋና በፍጥነት እንዲደርስ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ተጠቁሟል።

የመድኃኒቱ አምራቾችና የጤና ተቋማት እንዳስታወቁት፣ መድኃኒቱ በእነዚህ አገራት ለአንድ ሰው በዓመት 40 ዶላር ገደማ የሚቀርብ ሲሆን፣ ይህም በአሁኑ ወቅት በየቀኑ ከሚወሰዱ የመከላከያ እንክብሎች ዋጋ ጋር እኩል ነው ተብሏል።

በየቀኑ መድኃኒት መውሰድ ለሚረሱ ወይም ለሚቸገሩ ሰዎች ይህ ክትባት ከፍተኛ መፍትሔ እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን፣ ተደርገዋል በተባሉ ጥናቶችም አዳዲስ የኤችአይቪ ኤችአይቪ የመያዝ አጋጣሚዎችን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ማስቀረቱ ተረጋግጧል።

@Addis_Mereja
❤27✍1🤔1💋1
ኢትዮጵያ ስድስት የሱዳን ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች!

ስድስት የሱዳን ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ማዘዟን ሮይተርስ ዘግቧል።እንደዘገባው ከሆነ ዲፕሎማቶቹ ሁለቱ ሀገራት በሚዋሰኑበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መዲና አሶሳ በሚገኘው የሱዳን ቆንስላ ጽህፈት ቤት ይሰሩ የነበሩ ናቸው።

ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በኋላ አዲስ አበባ ከአስመራ እና ካርቱም ጋር ያላት ግንኙነት እየሻከረ መጥቷል።ከአንድ ወር በፊት በተመሳሳይ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ይገኙ የነበሩ 10 የኤርትራ እና አንድ የግብጽ ዲፕሎማቶች መባረራቸው ይታወሳል።

ይህን ውሳኔ ተከትሎ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ስታቋርጥ ግብጽ በበኩሏ በኢትዮጵያ ላይ ተመሳሳይ የአጸፋ እርምጃ መውሰዷን አስታውቃ ነበር።ኢትዮጵያ እና ሱዳን አንዳቸው በአንዳቸው የውስጥ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ መግባታቸውን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።

@Addis_Mereja
❤15💘2💯1
ሱዳን በአሶሳ የሚገኘው ቆንስላዋ መዘጋቱን ተከትሎ በገዳሪፍ የኢትዮጵያን ቆንስላ በመዝጋት ዲፕሎማቶችን አስወጣች

የሱዳን መንግሥት በምሥራቃዊቷ ገዳሪፍ ከተማ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቆንስላ በመዝጋት በዚያ የሚሠሩ ዲፕሎማቶች ከሀገሪቱ እንዲወጡ አዘዘ። ይህ እርምጃ ኢትዮጵያ በአሶሳ የሚገኘውን የሱዳን ቆንስላ ከዘጋችና ስድስት የሱዳን ዲፕሎማቶችን ከሀገሪቱ እንዲወጡ ካዘዘች በኋላ ነው። ሁለቱ ጎረቤት ሀገራት በግዛታቸው ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖችን በመደገፍ በእርስ በርሳቸው መካሰሳቸው የዲፕሎማሲ ውጥረቱን ይበልጥ አባብሶታል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ በመጠየቅ ከሮይተርስ ጋር ቆይታ ያደረጉ ሁለት የሱዳን ባለሥልጣናት፣ ካርቱም የኢትዮጵያን ቆንስላ እንዲዘጋና የዲፕሎማሲ ሠራተኞቹ ከሀገሪቱ እንዲወጡ ማዘዟን አረጋግጠዋል።

@Addis_Mereja
❤7🔥1
በመቐለ ከተማ ማንኛውም ተሽከርካሪ ከዛሬ ጀምሮ ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ እንዳይንቀሳቀስ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ‼️

“ህጋዊ ፍቃድ የሌለው” የጦር መሳሪያ የያዙ አሊያም በቤታቸው የደበቁ የከተማይቱ ነዋሪዎች፤ ለትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲያስረክቡም ከዛሬ ጀምሮ የሶስት ቀናት ቀነ ገደብ ተሰጥቷቸዋል።

የሰዓት እላፊውን እና የጦር መሳሪያ የማስረከቡን ቀነ ገደብ በከተማይቱ መጣሉን ያስታወቀው የመከላከያ ሰራዊት ነው።

በትግራይ ክልል መገናኛ ብዙሃን ምሽቱን በትግርኛ ቋንቋ የተሰራጨው የሰራዊቱ መግለጫ፤ እነዚህ እርምጃዎችን መተግበር ያስፈለገው የመቐለ ከተማን “ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ” እንደሆነ አመልክቷል።

የመቐለ የጸጥታ ሁኔታ “በሂደት መሻሻሎች እያሳየ” መሆኑን የጠቆመው መግለጫው፤ ሆኖም የከተማይቱ ነዋሪዎች “አልፎ አልፎ” ለተለያዩ “የደህንነት ስጋቶች እየተጋለጡ” መሆኑን አስታውቋል። እነዚህ ስጋቶች የመነጩት ከዚህ በፊት በተለያዩ መንገዶች “ከእስር የተፈቱ ግለሰቦች” እና “የተደራጁ የዝርፍያ ቡድኖች” በሚፈጽሟቸው ወንጀሎች ምክንያት እንደሆነም መግለጫው ጠቁሟል።

ከጥቅምት 27 ቀን ጀምሮ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት እስከ ጧቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ማንኛውም ተሽከርካሪ ፣ ነሞተር ሳይክል እንዲሁም ከባድ ተሽከርካሪዎች በከተማዋ ውስጥ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው። ሆኖም በልዩ ምክንያት በምሽት ወደ ከተማዋ የሚገቡ ሀገር አቋራጭ ከበደ ተሽከርካሪዎች በልዩ ሁኔታ ይታያሉ ተብሏል።

@Addis_Mereja
❤10🔥1🙏1
ከ144 ሺህ በላይ ደንበኞች የስማርት ቆጣሪ ተጠቃሚ ሆኑ

ከ144 ሺህ በላይ ደንበኞች የስማርት ቆጣሪ ተጠቃሚ ሆኑ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት በመላ አገሪቱ ለ144 ሺህ 388 ደንበኞች ዘመናዊ የኤስ.ቲ.ኤስ ስማርት ቆጣሪዎችን ማዳረሱን አስታወቀ።

ቆጣሪዎቹ ደንበኞች በተለያዩ የዲጂታል ክፍያ አማራጮች የኤሌክትሪክ ኃይል በማንኛውም ጊዜና ቦታ እንዲገዙ ከማስቻላቸውም በተጨማሪ፣ የቆጣሪ ንክኪን ለመቆጣጠርና የኃይል መቋረጥ ሲያጋጥም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንደሚያግዙ ተገልጿል።

@Addis_Mereja
❤7🔥1👏1👻1
714$ በትሬዲንግ አተረፍኩ

🎉 የመጀመሪያዬን $714 FundedNext Payout! 💰

በዚህ ቪዲዮ የPayout ጥያቄዬን ሂደት እና ለዚህ ውጤት ያበቃኝን Trade Setup አጋርቻለሁ።

▶️ ሙሉ ቪዲዮውን እዚህ ይመልከቱ 👇

https://youtu.be/yxs4Ta882Xw?si=hoa0LxqMvPeatTwu

@Habesha_Fxx
❤3🏆1🍾1🤝1🫡1