ባህሩ ተካ - Bahiru Teka
41.4K subscribers
712 photos
31 videos
118 files
4.19K links
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
قناة رسمية
لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا
(أبو عبيدة) الدعوة السلفية

በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን
እንለቃለን
ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ
ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka
Download Telegram
👉  ወላጅን በመኻደም የተገኘ የአንድ ዲናር በረካ !

ጣውስ ኢብኑ ከይሳን – ረሒመሁላሁ – የአንድ ዲናር በረካ ታሪክን እንዲህ በማለት ይነግረናል :- 

" አራት ልጆች ያሉት አንድ ሰው ነበር ። ታመመ , ከልጆቹ አንዱ ከፈለጋችሁ አባታችንን አስታሙት ከውርሱ ምንም የላችሁም ወይም እኔ ላስታመው ከውርሱ ምንም ይቅርብኝ አላቸው !
እነርሱም አስታመው ከውርሱ ይቅርብህ አሉት ። እሱም አባቱን እስኪሞት ድረስ አስታመመው ። ሞተም በቃሉ መሰረት ከውርሱ ምንም አልፈልግም አለ ! ማታ ሲተኛ በመናሙ እንደዚህ አይነት ቦታ ሂድና መቶ ዲናር ውሰድ ተባለ , እሱም  በረካ አለው ወይ ብሎ ጠየቀ ?
አይ የለውም ተባለ ! አይ አልፈልገውም አለ ,
ጠዋት ለባለቤቱ ያየውን ነገራት ለምን አልወሰድክም በረካው ማለት በሱ ልብስ ገዝተን መልበሳችን ነበር አለችው , እሱም አይደለም አልፈልግም አላት , በሚቀጥለው ቀንም ሲተኛ እንደዚህ ያለ ቦታ ሂድና አስር ዲናር ውሰድ ተባለ, እሱም በረካ አለው ወይ ብሎ ጠየቀ ? የለውም ተባለ , አልፈልግም አለ ። ጠዋት ለባለቤቱ ነገራት , እሷም እንደመጀመሪያው አለችው , እሱም እንደርሱ አይደለም አለ ።
በሚቀጥለው ቀን ሲተኛ እንደዚህ ያለ ቦታ ሂድና አንድ ዲናር ውሰድ ተባለ , እሱም በረካ አለው ወይ ብሎ ጠየቀ ? አው አሉት , አንድ ዲናሩን ሄዶ ወሰደ ። ከዛም በአንዱ ዲናር ያገኘውን ነገር ለመግዛት ወደ ገበያ ወጣ !
ሁለት አሳዎችን የያዘ ሰው አገኘ , ስንት ናቸው ብሎ ጠየቀው ? ሰውየውም ሁለቱ በአንድ ዲናር አለው ከፍሎ ይዟቸው ወደ ቤቱ ሄደ ። ከዛም  በሁለቱም ሆድ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ አይነት አልማዝ አገኘ ! የሀገሩ ንጉስ አልማዝ እንዲፈለግለት አዘዘ ! ሲፈለግ ሲፈለግ እዚህ ሰው ጋር እንዳለ ታወቀ ። እሱም አንዱን በሰላሳ በቅሎ ጭነት ወርቅ ሸጠው ። ንጉሱ ሲያየው ይህ የራሱ አይነት ሌላ ያስፈልገዋል
ካልሆነ አይሆንም በዚህ እጥፍም ቢሆን ፈልጋችሁ ግዙልኝ አለ ! መልእክተኞቹ ተመልሰው መጥተው ንጉሱ የራሱ አይነት ሌላ ያስፈልጋል ብሏል ካለህ በመጀመሪይው እጥፍ እንገዛሃለን አሉት እሱም አለኝ ብሎ በእጥፍ ሸጠላቸው ። እንዲህ ነው ወላጅን የመኻደም በረካ ! አላህ ወላጆቹን ኻድሞ ከበረካ የተገናኘ ባሪያው ያድርገን ።

ሒልየቱል አውሊያእ  ( 4/7 - 8 )

http://t.me/bahruteka
Audio
የያሲን ምእራፍ ክፍል 04

" እኛ እጆቻችን (ኃይሎቻችን) ከሠሩት ለእነርሱ እንስሳዎችን መፍጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ለእርሷ ባለ መብቶች ናቸው ፡፡ የሚለውና ሌሎችም አንቀፆች የተብራሩበት ።
🔷 ለአላህ ዲን የሚከፈል ዋጋ ምንም ቢሆን ቀላል ነው ።

يقول:  عمر بن عبدالعزيز  - رحمه الله تعالى -

" فلو كان كل بدعة يميتها الله على يدي ؛ وكل سنة ينعشها الله على يدي ببضعة من لحمي ؛ حتى يأتي آخر ذلك من نفسي ؛ كان في الله يسيرا "

طبقات ابن سعد ، ( 5/343 )

ዑመር ኢብኑ ዐ/ዐዚዝ  - ረሒመሁላሁ - እንዲህ ይላል :-

" እየአንዳንዱ ቢዳዓ አላህ በእጄ እንዲሞት ቢያደርገው , እየአንዳንዱም ሱና አላህ በእጄ ከፍ ቢያደርገው ( እንዲስፋፋ ቢያደርገው ) ለዚህ ዋጋው የስጋዬ ቁርጥራጭ ሆኖ የዚህ መጨረሻው ነፍሴን መስጠት ቢሆን ለአላህ ከሆነ ቀላል ነበር "

http://t.me/bahruteka
👉 ያለ ስራ ምኞት ቂልነት ነው ።

قال يحيى بن معاذ -رحمه الله - :

أعظمُ الاغترَار: التمادِي في الذنُوبِ
معَ رجَاء العَفْو مِن غير ندامَة ،
وتوقّع القُرب من الله بغير طاعَة ،
وانتظَار زرْع الجنّة بِبَذر النار ،
وطلَبُ دَار المطيعينَ بالمعاصِي ،
وانتظار الجزاء بغير عمَل ،
والتمنّي علَى الله مَعَ الإفرَاط.

تزكية النفوس(١١٤).

🔷  የሕያ ኢብኑ ሙዓዝ የተባሉ ታላቅ ሊቅ እንዲህ ይላሉ :-

" በጣም ትልቁ መታለል በወንጀል መዘውተር ነው ። ያለ ፀፀት የአላህን ምህረት , መከጀል
ትእዛዙን ሳይፈፅሙ ወደ አላህ ለመቃረብ መጠበቅ , የእሳት ዘር እየዘሩ የጀነት ፍሬ መጠባበቅ , ወንጀል እየሰሩ የአላህን ታዛዦች ሀገር መፈለግ , ያለ ሥራ ምንዳ መፈለግ ,
ምንም ሣይሠሩ በአላህ ላይ ተስፋ ማድረግ " ናቸው ።

http://t.me/bahruteka
Audio
ሰኞ ጁሙዓ የሆነበት ሁለተኛ ሚስት ፈላጊ አጠር ያለ ለፈገግታ የሚሆን ገጠመኝ ። ከሱረቱ ሳፋት የቁርኣን ትርጉም ቀንጨብ ተደርጎ የተወሰደ ።

http://t.me/bahruteka
ይህ የሀድያ ዞን ሰለፍይ ወንድሞቻችን የዋትስአፕ ግሩፕ ነው ። በመቀላቀልና ለሌሎች በማጋራት እንተባበራቸው ። ግሩፕ ሲከፍቱ እያጠፉ ሊበትኗቸው ብዙ ይሰራሉ ! ሐቅ የአላህ እርዳታና እገዛ ስላለው ፅናቱን አላህ ይስጠን ማለትና መታገል የግድ ነው ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://chat.whatsapp.com/H81aVjkAD5BLvEDrQeV4r5
Audio
የሷፋት ምእራፍ ክፍል 01

" አምላካችሁ በእርግጥ አንድ ነው "፡፡ የሚለውና ሌሎችም አንቀፆች የተብራሩበት ።
*قال الحافظ ابن حجر رحمه الله :*

*إنَّ الْعَاقِلَ يَـشْـتَـدُّ عَـلَـيْـهِ ،*
*أَنَّ الْأَجْنَبِيَّ يَرَىٰ وَجْهَ زَوْجَتِهِ وَابْنَتِهِ .*

📖 فتح الباري ( 245/12 )
Forwarded from ተውሒድ || 𝐓𝐞𝐰𝐡𝐢𝐝 𝐛𝐨𝐭
🎁 ስጦታ ለእውቀት ፈላጊዎች
      ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
➥ ለጀማሪዎች በሚመች መልኩ፣ እጅግ በጣም ጥሩ በሆነ አቀራረብ፣ በሳቅና ፈገግታ፣ በተግሳፅ፣ በምክሮች በተሞላ መልኩ እና ከመጠነኛና ጠቃሚ ማብራሪያ ጋር ተደርገው በተለያዩ የእውቀት ዘርፎች ላይ የተሰጡ ትምህርቶች እንካችሁ ብለናል።

🎙በውዱ ኡስታዛችን በኡስታዝ አቡ ሙስዐብ (አቡ አብዲላህ) ሰዕድ ኢብኑ አብዲለጢፍ አላህ ይጠብቀው!
          
▪ አላህ ኡስታዙን በመልካም ይመንዳው! እኛም ቀርተን የምንጠበምበት ያድርገን።

📢 ||• ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!
🚫 የወለድ አነስተኛ ደረጃው እናትን እንደመገናኘት ነው እንጠንቀቅ ‼።

عن عبدالله بن مسعود – رضي الله عنه – قال قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم –

" الربا ثلاثةٌ وسبعونَ بابًا ، وأيسرُها مثلُ أنْ ينكِحَ الرجلُ أمَّهُ ، … الحديث "

أخرجه ابن ماجه بسند صحيح

🔹 ዐብዱላሂ ኢብኑ መስዑድ ባወራውና በሶሒሕ ሰነድ ኢብኑ ማጃህ በዘገቡት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ያላሉ : –

" ወለድ ሰባ ሶስት በር ( ደረጃ ) አለው ። መለስተኛው ልክ አንድ ሰው እናቱን እንደማግባት ( መገናኘት) ነው … "።

http://t.me/bahruteka
Audio
የሷፋት ምእራፍ ክፍል 02

« በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ በእርግጥ እንመረመራለን? » (የሚል)፡፡ የሚለውና ሌሎችም አንቀፆች የተብራሩበት ።
👉  ሙሉ የምትሆነው ሐቅን አውቀህ ስትከተለው ነው !

يقول ابن القيم – رحمه الله تعالى– :

" كمال الإنسان مداره على أصلين :
معرفة الحق من الباطل ، وإثار الحق على الباطل ،
وما تفاوتت منازل الخلق عند الله  في الدنيا والآخرة ، إلا بقدر تفاوت منازلهم في هذين الأمرين " .

الجواب الكافي  : ص 99

ኢብኑል ቀይም – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል :-

" የሰው ልጅ ሙሉነቱ የሚሽከረከርበት ነጥብ ሁለት ነገሮች ናቸው :  ሐቅን ከባጢል ለይቶ ማወቅ
ሐቅን ከባጢል ማስቀደም
የፉጡራኖች ደረጃ በዱንያም ሆነ በኣኺራ አላህ ዘንድ አልተለያየም
በእነዚህ ሁለት ነገሮች ባላቸው ደረጃ ቢሆን እንጂ "

http://t.me/bahruteka
👉 የዳዕዋ መጀመሪያው ተውሒድ ነው !

قال الشيخ ربيع بن هادي المدخلي– رحمه الله – :

تأملوا القرآن يا إخوة ! وتدبروه ، القرآن ينمي الإيمان ، والقرآن ينمي التوحيد ، والقرآن – إذا فهمته – صرت من أتباع الرسل في دينهم وعقيدتهم ومنهجهم ،
قال تعالى :
(شَرَعَ لَكُمْ مِنَ الدِّينِ مَا وَصَّى بِهِ نُوحاً وَالَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَى وَعِيسَى أَنْ أَقِيمُوا الدِّينَ وَلا تَتَفَرَّقُوا فِيهِ )
الشورى: (13) ،
الدين : التوحيد ، أقيموا هذا التوحيد ، إذا أقمت التوحيد ؛ استقام لك كل شيء ..

🎙محاضرة : التوحيد أولاً

🎤 ሸኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አል መድኸሊ
ሐፊዘሁላሁ እንዲህ ይላሉ : -

" ወንድሞች ሆይ ቁርኣንን አስተውሉት, አስተንትኑትም, ቁርኣን ኢማንን ያሳድጋል ።
ቁርኣን ተውሒድን እየጨመረ እንዲሄድ ያደርጋል ። ቁርኣን ከተገነዘብከው በዲናቸው ፣ በዐቂዳቸው ፣ በሚንሀጃቸው የነብያቶች ተከታይ ትሆናለህ !።
አላህ እንዲህ ብሏል :–
{ شَرَعَ لَكُم مِّنَ الدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِ نُوحًا وَالَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰ ۖ أَنْ أَقِيمُوا الدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا فِيهِ ۚ… الآية
الشورى (13)
" ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም ወዳንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ በእርሱም አትለያዩ ማለትን (ደነገግን) ።
ዲን ማለት ተውሒድ ነው ። ይህን ተውሒድ ቀጥ አድርጉ ! ተውሒድን ቀጥ ካደረግህ ሁሉ ነገር ቀጥ ይልልሀል "።

" ተውሒድ ነው ( የዳዕዋ) መጀመሪያ" ከሚለው ሙሐደራ የተወሰደ ።

http://t.me/bahruteka
✅ ሙሲባ ማለት...

يق
ول ‏عبد الله بن سليمان– رحمه الله :-

"
ليست المصيبة أن يصاب الإنسان بنفسه أو ماله أو ولده، وإنما المصيبة العظيمة، والكسر الذي لا ينجبر أن يصاب الإنسان بدينه !
فيحل الشك محل اليقين، فيرى الباطل حقًا، والحق باطلاً، والمعروف منكرًا، والمنكر معروفًا ."

  
              الدرر السنية ( ١٥ / ٤٦٦ )

🔷
  ሱለይማን ኢብኑ ዐብደላ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል ፦

"ሙ
ሲባ ማለት አንድ ሰው በራሱ ፣ በንብረቱ ፣ በልጁ የሚደርሰው አይደለም ። ነገር ግን ትልቁ ሙሲባ የማይጠገነው ስብራት ማለት አንድ ሰው በዲኑ ሙሲባ ሲደርስበት ነው ።
(ይህ
ም በሚከተሉት ነጥቦች ማወቅ ይቻላል) ፦
– እርግጠኛ የነበረበት ነገር ሲጠራጠር
– ባጢል ሐቅ, ሐቅ ባጢል ሲመስለው
–
የተጠላ ነገር የተወደደ የተወደደ ነገር የተጠላ ሲመስለው ።"

ht
tps://t.me/bahruteka
👉  ስለ ዱንያ እንጂ ከማያወራ ሰው ጋር እንዳትቀማመጥ !

‏وصية سفيان الثوري رحمه الله :–

" ليكن جليسك مَن يُزَهِّدُكَ في الدنيا ، وَيُرَغِّبُكَ في الآخرة ، وإياك ومجالسة أهل الدنيا الذين يخوضون في حديث الدنيا ؛ فإنهم يفسدون عليك دينك وقلبك ، وأكثر ذكر الموت ، وأكثر الاستغفار مما قد سلف من ذنوبك ، وسل الله السلامة لما بقي من ‏عمرك ".

حلية الأولياء ٨٢ / ٧

ሱፍያን አስ ሰውሪ ኑዛዜ ሲያደርጉ እንዲህ ይላሉ :–

" የምተቀማመጠው ሰው በዱኒያ ጉዳይ ላይ እንድትብቃቃ ከማያስፈልግህ ነገር ችላ እንድትል የሚያደርግህ ይሁን በአኼራ ላይ ጉጉት እንዲኖርህ እነዚያን በተገናኙ ቁጥር ስለ ዱንያ ከሚያወሩ ሰዎች ጋር ከመቀማመጥ ተጠንቀቅ እነዚህ ሰዎች ዱንያህንም ቀልብህን ያበላሹብሀል ሞትን ማሰብን አብዛ ካለፈው ወንጀልህ ምህረት መጠየቅን አብዛ ለቀሪው እድሜህም የአላህን ጥበቃ ለምነው"

https://t.me/bahruteka
Audio
የሷፋት ምእራፍ ክፍል 03

" ኢብራሂምም በእርግጥ ከተከታዮቹ ነው "፡፡ የሚለውና ሌሎችም አንቀፆች የተብራሩበት ።
👉   የነጃሺ ድል !

መካ ላይ በሙስሊሞች ይደርስ  የነበረውን ሰቆቃ ለመቀነስ የአላህ መልእክተኛ - ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - ለሶሓባዎች በሀበሻ ምድር እሱ ዘንድ ሰው የማይበደልበት ፍትሃዊ ንጉስ አለ ወደርሱ ሂዱ ብለው ሀሳብ አቀረቡላቸው ።
የተወሰኑ ሶሃባዎች የመጀመሪያውን ጉዞ አድርገው በሰላም ደርሰው በነጃሺ ተቀባይነት እምነታቸውን በነፃነት እያካሄዱ በሰላም መኖር ጀመሩ ።
በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ የተወሰኑ የነጃሺ ተከታዮች በነጃሺ ላይ ተቃዉሞ ያነሱ ቢሆንም ነጃሺ በመልካም ውይይት እንዲመለሱ አደረገ ።
ይሁን እንጂ  አንድ ግለሰብ ጦርነት አውጆ ከነጃሺ ጋር ለመዋጋት ይወስናል ነጃሺም ተዘጋጀ ። ከዚያም ነጃሺ ለሶሀባዎች መርከብ ያዘጋጅና እዚህ ላይ ሁኑ ከተሸነፍኩ የተመቻችሁ ቦታ ትሄዳላችሁ ካሸነፍኩ ከኔው ጋር ትሆናላችሁ ይላቸዋል ። ከዚያም ወደ ጦርነቱ ይሄዳል
ክስተቱን ኡሙ ሰለማህ እንዲህ በማለት ትነግረናለች :-
" በአላህ ይሁንብኝ እንደዛን ቀን አይነት ጭንቀት ተሰምቶን አያውቅም ያ ሰው ምናልባት ያሸንፍ ይሆናል በሚል , ነጃሺ ጦሩን ይዞ ወደርሱ ሄደ በመካከላቸው የአባይ ምድር አለ ። ሶሃባዎችም እንዲህ አሉ :– ማነው ወደዛ ሄዶ የሚከሰተውን ነገር የሚያመጣልን ?
ዙበይር ኢብኑል ዐዋምም እኔ ይላል ። አዎ አንተ ይሉታል ። በእድሜ ከእነርሱ ትንሹ ነበር ።
የቆዳ ስልቻም ነፉለት ደረቱ ላይ አድርጎ እየዋኘ ሄደ ። ከባህር ዳርቻም ደረሰ ። ከዚያም ወደ ጦር ሜዳው ዘለቀ ።
እኛም ትላለች ። ሁላችንም አላህ የነጃሺን ጠላት አጥፍቶ ለነጃሺ በሀገሩ ድል እንዲሰጠው ዱዓእ አደረግንለት ! በዚህ ሁኔታ ላይ እየተጠባበቅን እያለን ዙበይር ብቅ አለ ።
ልብሱን እያውለበለበ አብሺሩ ! አላ የነጃሺን ጠላት አጥፍቶ ለነጃሺ በሀገሩ ድል ሰጥቶታል አለን ።
በአላህ ይሁንብኝ የዚያን ቀን የተደሰትነው አይነት ደስታ ተደስተን አናውቅም ትላለች ።
ሀበሻ በነበሩበት ጊዜ ለማለት ፈልጋ ይሆናል ። ወላሁ አዕለም ! ከዛም ወደ መካ እስክንመለስ በመልካም ሁኔታ እሱ ጋር ቆየን በማለት ታሪኩን ታጠናቅቃለች ።

ሲራ አንነበዊያህ ሊብኒ ሂሻም
( 1/ 362, 365 )

http://t.me/bahruteka
  🔷 የሙስሊም መሪን መታዘዝ !

ከሸሪዓችን የጠሩ መመሪያወች አንዱና ዋነኛው የሙስሊም መሪዎችን በመልካም መታዘዝ ነው ። ይህን ትልቅ መርህ ለመናድ የኢስላም ጠላቶች ገና ከጠዋቱ ነበር እንቅስቃሴ የጀመሩት !።
ነብዩ - ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም - የአይሁዶች ክህደትና ሴራ ጅብሪል ሲነገራቸው ከመዲና እንዲወጡ ለማድረግ ጊዜ አልወሰዱም ። ቀጥሎ ዑመር - ረዲየላሁ ዓንሁ - ጨርሶ ከአረቢያ ግዛት ካስለቀቃቸው ጊዜ ጀምሮ ለኢስላምና ለሙስሊሞች ጉድጓድ መማሳቸውን በማጠናከር በአብደላህ ኢብኑ ሰበእ አል የሁዲ አማካይነት እንቅስቃሴ ተጀመረ ።
በጀነት የተመሰከረላቸው ሶስተኛው ኸሊፋ ዑስማን - ረዲየላሁ ዐንሁ - እንዲገደሉ አደረጉ ። በኃላም የሙስሊሙ ዓለም እንዳይረጋጋ ሙስሊሞች ከመሪዎቻቸው ጋር እንዳይስማሙ
የሙስሊሞች የበላይነት እንዳይቀጥል ቢያንስ እስልምናና ሙስሊሞችን በማራራቅ ባዶ በማድረግ የተሳካለት ሚና እየተጫወቱ ነው ።
አይሁዶችና ርዝራዦቻቸው ምእራባዊያን ዋነኛ ጠላታቸው እስልምናን በማድረግ  ለመምታት በጣም የረቀቀና የተቀነባበረ ስራ እየሰሩ መሆኑን የሚረዱ ሙስሊሞች ግን ጥቂት ናቸው ።
ከዚህ ስራቸው ውስጥ ዋነኛው ከላይ የተጠቀስው መሪዎችን ከህዝቦች መነጠል , ሰላም እንዳይኖር ማድረግ ነው ።
በዚህ የተንኮል ሴራ ኢስላማዊውን የደውላ ኡስማኒያ አገዛዝ እንዲፈረካከስ አድርገው የሙስሊም ሀገሮችን በታትነው ሁሉም ሀገር በራሱ መሪ እየተመራ ቢሆንም ይህም ቢሆን እንቅልፍ የነሳቸው ምእራባዊያንና አይሁዶች በዘረጉላቸው የጥፋት መረብ ወድቀው እየተፈረካከሱ ይገኛሉ ።
የዚህ የአይሁዶች ሴራ አስፈፃሚዎች ደግሞ የቅርብ ወዳጆቻቸው ኢኽዋኖች ናቸው ። ይወቁም አይወቁም ሙስሊሞች በመሪዎቻቸው ላይ እንዲነሱ የማድረግ እንቅስቃሴ የምእራባዊያን ኢስላምን የማፍረስ ሴራ ውጤት ነው ። ይህን የጥፋት መረብ በመዘርጋትና ኢኽዋኖች ለሙስሊሞች ነፃነት መቆርቆር ነው ብለው በሙስሊም መሪዮች ላይ አመፅ በማስነሳት የሙስሊም ሀገሮችን እንዲፈርሱ እንዲያደርጉ እያደረጉ መሆኑንና ኢኽዋኖችን ደግሞ የምታሰማራው ኢራን መሆኗን እንርሱ በተሽከርካሪ ወንበር ላይ ቁጭ ብለው እንደሚመለከቱ የእስራኤሉ መሪ ኔታኒያሁ ስልጣን በያዘ ባጭር ጊዜ ለፓርላማ ያቀረበውን ሪፖርት በሚቀጥለው ሊንክ ገብተው ይመልከቱ :–
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://drive.google.com/file/d/1KdvbtuOLGUSG4aepRk2eAornLH5Vae44/view?usp=drivesdk
በሚገርም መልኩ አሁን ደግሞ ይህ ሴራ የሌላ ሀገር መሪን መታዘዝ በኔ ላይ ግዴታ አይደለምም በሚል ፈሊጥ ወደ ሰለፍዮች እየገባ መሆኑ ነው ።
አንተ ሰለፍይ ሆይ ልብ በል! የሌላ ሀገር መሪን መታዘዝ ባንተ ላይ ግዴታ ባይሆንም የመሪዎችን ስም በመጥፎ ማንሳትና መሳደብ ነውሩን ባደባባይ መናገር በግልፅ መተቸት በማያሻማ መልኩ ሸሪዓ እርም ያደረገው ተግባር መሆኑን አውቀህ ማመንና መተግበር ግዴታህ መሆኑን አውቀህ ለመሪዎች ዱዓእ ማድረግ ምላስህን መሰብሰብ, በመልካም አደራ መባባል, በመልካም መተባበር, ግዴታ እንደሆነ አውቀህ ዐቂዳህ ማድረግ ይኖርብሀል ።
መሪዎችን በተመለከተ የመጡ ሀዲሶች ባጠቃላይ መታዘዝ የሚለው በየትኛውም ቦታ ያለ ሰለፍይ ( የነብዩንና የሶሓቦችን መንገድ ለሚከተል ሙስሊም) ለመሪዮች ዱዓእ ማድረግ እነርሱን ከመተቸት ምላስን መሰብሰብ እንደሚያስፈልግ አፅኖት ሰጥቶ ያስተምራሉ ! ።
በመሆኑም የኔ ሀገር መሪ ስላልሆነ አይመለከተኝም በሚል በየሚዲያው በየጋዜጣው በየሜንበሩ ላይ መሪዎችን መተቸት ሙስሊሞች በመሪዎች ላይ ልባቸው እንዲሸፍት ማድረግ በምእራባዊያን ተወጥኖ ለኢኽዋኖች የሙስሊሞችን ሀቅ ያላግባብ ከመበዝበዝ ማዳን በሚል እንዲያስፈፅሙት የተሰጠ የቤት ስራ ነው ። አዩሁዶች በሶስተኛ ኸሊፋ በዑስማን ኢብኑ ዐፋን ላይ በዐብዱላህ ኢብኑ ሰበእ አማካይነት የሰሩት ይህ ነበር ።
በዚህ ላይ የሚካፈል ሰው በተካፈለው ልክ እስልምናን ለመናድ በሚሸረበው ሴራ እጁ አለበት !
የኔ ሀገር መሪ ስላልሆነ እሰድበዋለሁ ማለት የዋህነት ነው ። እንኳን ሸሪዓ ጤነኛ አቅልም አይፈቅደውም ።
ምክንያቱም መሪህን የምትታዘዝ ከሆነ ምክንያቱም አንተ የሰደብከው መሪ ህዝብ ያንተን መሪ ስለሚሰድብ በሌላ አባባል መሪህን እየሰደብክ ነው ማለት ። ይህን አስመልክቶ የመጡ የቁርአንና ሀዲስ መረጃዎች ቁጥር ስፍር የላቸውም ። የሰውን እናት የሰደበ እናቱን እንደሰደበ ይቆጠራል የሚሉና ሌሎችም ብዙ ናቸው ።
በመሆኑም ሰለፍዮች በጣም ልትጠነቀቁት የሚገባ አደገኛ አካሄድ ነው ። የዚህ ሰለባ የሆነ ሰው ሰለፍይ ነኝ የሚል ከሆነ ሰለፍይ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የማያውቅ ወይም የሰለፍዮች አቂዳ ያልገባው ስለሆነ ጊዜ ሳይወስድ ሊያውቅ ይገባል ።
የሰለፍያ ዳዕዋ የዚህ አይነትን እንቅስቃሴ ያወግዛል ። ከተግባሩም ራሱን ያጠራል ።
በየሶሻል ሚዲያው በተውሂድ ስም የሙስሊም መሪዎችን የምታንቋሽሹ አክቲቪስቶች ሰለፍያ ዳዓዋ ውስጥ ሰርጋችሁ የገባችሁ ሱሩርይ ወይም ቁጥብይ የምእራባዊያን ተልእኮ አስፈፃሚ መሆናችሁን አውቃችሁ ቶሎ ተውበት አድርጋችሁ ልትመለሱ ይገባችኋል ።
ሰለፍይ እህትና ወንድሞች የዚህ አይነት እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ ሰዎች ራሳችሁን ጠብቁ
በኢኽዋን ላይ የሚጨክን ልብ የሌለው ወደዚህ ቻናል አይቀላቀል እላለሁ ።

አላህ በሀቅ ላይ የምንፀና ያድርገን ።

http://t.me/bahruteka