ባህሩ ተካ - Bahiru Teka
41.3K subscribers
711 photos
30 videos
118 files
4.19K links
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
قناة رسمية
لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا
(أبو عبيدة) الدعوة السلفية

በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን
እንለቃለን
ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ
ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka
Download Telegram
‏صورة من حسين عبد الله
👉 ወጣቶች ከዑለሞች እጅ ሲወጡ ይጠፋሉ !

قال الشيخ ربيع بن هادي المدخلي – رحمه الله –
" لما كان الشباب مرتبطين بالعلماء ويسمعون لنصائحهم كانت الحماية والصيانة من كل أنواع الضلال،
من الكفار والملاحدة والزنادقة وأهل البدع والضلال، ولما فكوا هذا الإرتباط بين العلماء والإلتزام بهذا المنهح جاءت المشاكل وجاء الضياع.
الذريعة ( 1/328 )

ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አል መድኸልይ እንዲህ ይላሉ : –
" ወጣቶች ከዑለሞች ጋር ትስስር በነበራቸውና ምክራቸውን ይሰሙ በነበረ ጊዜ ከጥመት አይነት ሁሉ ከከሀዲያን ፣ ከመላሂዳዎች ፣ ንፍቅናቸው ግልፅ ከሆኑ ሙናፊቆች ፣ ከቢዳዓና የጥመት ባልተቤቶች መጠበቅና ( የዐቂዳ ንፅህና) ነበር ።
በዑለሞችና በዛ ሚንሀጅ ላይ የሙጥኝ ባሉ ( ወጣቶች) መካከል በለዩ ጊዜ ችግሮችና (የወጣቶች) መጥፋት መጣ "!።

http://t.me/bahruteka
👉 የዲን እውቀት ፈላጊ ከሆንክ ስድስቱን ደረጃዎች ጠብቅ !

1 – ንያህን ማጥራት
2 – ሸይኽኽን በጥሞና መስማት
3 – እውቀቱን መገንዘብና መዕናውን ማካበብ
4 – እውቀቱን መሸምደድና ማስረፅ
5 – በእውቀቱ መስራት
6 – እውቀቱን ማሰራጨት
እነዚህ ተርቲቦች በአላህ ፈቃድ እውቀትን ፍሬያማ እንዲሆን ያደርጋሉ ።

http://t.me/bahruteka
Audio
የጛፊር ምእራፍ ክፍል 03

" ፈርዖንም አለ «ሃማን ሆይ! መንገዶችን እደርስ ዘንድ ረዢም ሕንጻን ለእኔ ካብልኝ "፡፡ የሚለውና ሌሎችም አንቀፆች የተብራሩበት ።
Forwarded from أبو سكينة(أمير)
⚪ #የሀራ ሰለፍዮች የመስጅደል ፉርቃን የገቢ ማሰባሰቢያ ግሩፕ።

👉የቴሌግራሙ ሊንክ
https://t.me/haraselefi

ሸር በማድረግ ለሌሎች #ወንድም #እህቶች ተደራሽ እንድሆን የበኩላችንን እንወጣ ባረከሏሁ ፊኩም!!
አስደሳች ልዩ ፕሮግራም ከአልኢስላሕ መድረሳ

እነሆ ዛሬ ዕለተ ረቡዕ ሐምሌ 29/2018 ከመግሪብ እስከ ዒሻእ ድረስ ልዩ የሙሐደራ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡

ተጋባዥ እንግዶች    
1) ሸይኽ ኢስማዒል ዘይኑ ከተንታ ወሎ
 2) ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሐሰን ኢድሪስ ከደሴ
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል፡፡  አልኢስላሕ እንገናኝ፡፡

🕌አልኢስላሕመድረሳ
https://t.me/medresetulislah
👉 ከፊት እውነታን መረዳት !

سئل عبدالله بن سلام – رضي الله عنه – عن سبب إسلامه فقال :

" تأملت وجه النبي – صلى الله عليه وسلم – فأيقنت أنه ليس بوجه كذاب "

أخرجه ابن ماجه بسند صحيح

ዐብዱላሂ ኢብኑ ሰላም ( አዩሁዳዊ የነበረው) በምን ምክንያት እንደሰለመ ሲጠየቅ እንዲህ ብሎ መለሰ : –

" የነብዩን ፊት አስተውዬ አየሁት, ከዛም ( ፊታቸው ) የውሸታም ፊት እንዳልሆነ እርግጠኛ ሆንኩኝ " ።

http://t.me/bahruteka
Forwarded from أبو فوزان السلطي ان شاء الله
​🔖 ታላቅ የምስራች ለሀዋሳና አካባቢዋ የሱና ወዳጆች በሙሉ! 🌟

​السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

~​እነሆ!  መሻኢኾችና ኡስታዞች የሚታደሙበት ፣ ድናችንን የምንተዋወስበት፣ መንፈስን የሚያድስ የዳዕዋና የኮርስ ድግስ በሀዋሳ ከተማ ተዘጋጅቶ ይጠብቆታል።

​"مَنْ دَلَّ عَلَى خَيْرٍ فَلَهُ مِثْلُ أَجْرِ فَاعِلِهِ"
"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ፤ ልክ እንደ ሰሪው አጅር አለው።"
​ያልሰሙትን በማሰማትና በዚህ ታላቅ ፕሮግራም ላይ በአካል በመገኘት የዕውቀት ተካፋይ ይሁኑ!

      ​🛋 የዕለቱ ተጋባዥ እንግዶች፦

● ​🎙️ ሸይኽ ሙሐመድ ዐረብ (ከወለጋ)

●​ 🎙️ ሸይኽ ኢስማኢል ዘይኑ  (ከወሎ)

● ​🎙️ ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሀሰን ኢድሪስ (ከደሴ)

● ​🎙️ ኡስታዝ ዐብዱልሀሚድ   (ከሀዋሳ)

​📍 ፕሮግራሙ የሚካሄድበት ቦታና ጊዜ፦

◦ ​🏢 ​ቦታ፦ በሀዋሳ ከተማ ዳቶ ዑመሩል ፋሩቅ መድረሳ
◦ ​📅 ​ቀን፦ ነሀሴ-1(ጁመዓ) እስከ ነሀሴ-3(እሁድ)
◦ ​🕒 ​ሰዓት፦ ከጁመዓ ኹጥባ ጀምሮ

አዘጋጅ፦ የሀዋሳ ሰለፊዮች ጀመዓ
🕋 አላህ በሰላም ያገናኘን! 🕋


የኮርሱን ኪታቦችና አጠቃላይ ዝርዝር መረጃ በቀጣይ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

​📱 ቀጥታ ስርጭት (Live):
​በአካል መገኘት ለማትችሉ፣ ፕሮግራሙን አላህ ካለ (ኢንሻ አላህ) በሚከተለው የቴሌግራም ግሩፕ መከታተል ትችላላችሁ፦

🔗 ጆይን ኢያላችሁ ሊንኩን ሼር አድርጉት!
https://t.me/hawassajemea
https://t.me/hawassajemea

N.B ሊንኩን አትቁረጡ  بارك الله فيكم
🔷 እድለ ቢስነት ከተሰማህ ምን ማድረግ ነው ያለብህ ⁉️

ወንድሜ ነገሮች ተወሳስበው እድለቢስ ነኝ እንዴ የሚል ስሜት ከተሰማህ ከእናትህ ጋር ያለህን ግንኙነት ፈትሽ !
አላህ በተከበረው ቃሉ ስለ ነብዩላሂ ዒሳ ሲነግረን እናታቸው መርየም እሳቸውን ወልዳ ወደ ህዝቦቿ በመጣች ጊዜ በዝሙት የወለዳቻቸው መስሏቸው በወረፏት ጊዜ በአንቀልባ አዝላው ወደ ነበረው ህፃን እያመላከተች እሱን አናግሩት ስትላቸው እንዴት በአንቀልባ የሚታዘልን ህፃን እናናግራለን ሲሉ አላህ አናግሯቸው መልስ ሲሰጡ : –

" قَالَ إِنِّي عَبْدُ اللَّهِ آتَانِيَ الْكِتَابَ وَجَعَلَنِي نَبِيًّا
(ሕፃኑም) አለ «እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ ፡፡ መጽሐፍን ሰጥቶኛል ነቢይም አድርጎኛል ፡፡»
وَجَعَلَنِي مُبَارَكًا أَيْنَ مَا كُنتُ وَأَوْصَانِي بِالصَّلَاةِ وَالزَّكَاةِ مَا دُمْتُ حَيًّا
«በየትም ስፍራ ብሆን ብሩክ አድርጎኛል ፡፡ በሕይወትም እስካለሁ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል ፡፡»
وَبَرًّا بِوَالِدَتِي وَلَمْ يَجْعَلْنِي جَبَّارًا شَقِيًّا
«ለእናቴም ታዛዥ (አድርጎኛል) ፡፡ ትዕቢተኛ እምቢተኛም አላደረገኝም ፡፡

የመርየም ምእራፍ ከ (30 – 32)

አላህ የዋለላቸውን ውለታና ያዘዛቸውን ነገር ሲናገሩ መጨረሻ ላይ ለእናቴም ታዛዥ ( መልካም የምውል) አድርጎኛል ። ትእቢተኛ እምቢተኛ ( እድለቢስ) አላደረገኝም ማለታቸውን ነገረን ። ይህ ማለት እናትን ( ወላጆችን) ማመፅ እድለቢስ የሚያደርግ መሆኑን ያሳየናል ።

http://t.me/bahruteka
✅ አላህን የመውደድ ምልክቱ !

قال ربيع بن أنس – رحمه الله –

" علامة حب الله كثرة ذكره "

مدارج السالكين (3/162)

ረቢዕ ኢብኑ አነስ የተባለ ዓሊም እንዲህ ይላል : –

" አላህን የመውደድ ምልክቱ እሱን ማውሳት ማብዛት ነው " ።

http://t.me/bahruteka
Forwarded from Abu abdirahman«አብዱልቃዲር ኢብኑ ሐሰን» (أنا المكدي وابن المكدي وهكذا كان أبي وجدي إلى متى يا نفس)
ታላቅ የምስራች በአይነቱ ልዩ እና አጓጊ ታላቅ የሙሓደራ ድግስ በአዳማ ከተማ



    እነሆ የፊታችን እሁድ ነሐሴ 03/2018 በአዳማ ከተማ 01 ቀበሌ በኢብኑ ተይሚየህ መስጂድ የመድረሰቱል ሂጅራ ቦታ ግዢ ባስመለከተ ልዩ የሙሐደራ እና ደማቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል ።

     የእለቱ ተጋባዥ እንግዶች : –

① የተከበሩት ሸይኽ ሸይኽ አ/ሐሚድ (ሀፊዘሁሏህ)

②ተወዳጁ  ኡስታዝ ባህሩ ተካ (ሀፊዘሁሏህ)
  
3 ተወዳጁ  ኡስታዝ አቡ ሐመዊያ ሸምሱ ጉልታ (ሀፊዘሁሏህ)


በአሏህ ፍቃድ ሌሎችም ይኖራሉ

     ፕሮግራሙ በአላህ ፈቃድ ከጠዋቱ 2 : 30 የጀመራል ። 

https://t.me/hijra_masjid
Audio
የጛፊር ምእራፍ ክፍል 04

" በእሳትም ውስጥ የሚከራከሩበትን ጊዜ (አስታውስ) ፡፡ ደካማዎቹም ለእነዚያ ለኮሩት «እኛ ለእናንተ ተከታዮች ነበርንና እናንተ (አሁን) ከእሳት ከፊሉን ከእኛ ላይ ገፍታሪዎች ናችሁን?» ይላሉ "፡፡ የሚለውና ሌሎችም አንቀፆች የተብራሩበት ።
✅ አላህን መገዛት የሚቻለው እሱ ባዘዘበት መንገድ ነው !

يقول ابن القيم – رحمه الله –

" كل عمل بلا إقتداء لا يزيد عامله من الله إلا بعدا. فإن الله تعالى إنما يعبد بأمره لا بالآراء والأهواء ."
مدارج السالكين (1/105)

ኢብኑ ቀይም እንዲህ ይላል : –

" ማንኛውም የነብዩን ፋና ያልተከተለ ዒባዳ ባለቤቱን ከአላህ መራቅን እንጂ አይጨምርለትም ። አላህን ( ባሮቹ) ሊገዙት የሚገባው ባዘዘው መልኩ እንጂ በዝንባሌና በይመስለኛል አይደለም "።

http://t.me/bahruteka
👉 ቂልን መራቅ ወደ አላህ መቃረቢያ ነው !

يقول الحسن البصري – رحمه الله –

" هجران الأحمق قربة إلى الله عز وجل "

كتاب العزلة ص (42)

አል ሐሰኑል በስርይ የተባለው ሊቅ እንዲህ ይላል : –

" ቂልን መራቅ (ማኩረፍ) ወደ አላህ መቃረቢያ ነው " ።

🔹እኔም አልኩኝ ከሙብተዲዕ የባሰ ቂል ይኖራል እንዴ ? ስለዚህ ሙብተዲዕን መራቅ ወደ አላህ መቃረቢያ ነው ።

http://t.me/bahruteka
👉 የኣደም ልጅ ነፍስ በሶስት ፀፀት እንጂ ከዱንያ አትወጣም !

قال الحسن البصري – رحمه الله –

" لا تخرج نفس ابن آدم إلا بحسرات ثلاثة :–
1 – أنه لم يشبع مما جمع
2 – ولم يدرك ما أمل
3 – ولم يحسن الزاد لما قدم عليه "

موسوعة ابن أبي الدنيا (5/132)

አል ሐሰኑል በስርይ የተባለ ታላቅ ሊቅ እንዲህ ይላል : –

" የኣደም ልጅ ነፍስ በሶስት ፀፀት እንጂ ከዱንያ አትወጣም !

1– ከሰበሰበው ነገር አልጠገበም ።
2 – የተመኘውን አላገኘም ( አልደረሰበትም) ።
3 – ለሚሄድበት ሀገር በቂ ስንቅ አላዘጋጀም "።

http://t.me/bahruteka
Audio
የጛፊር ምእራፍ ክፍል 05

" አላህ ያ ለእናንተ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት (ጨለማ) ቀንንም (ልትሠሩበት) የሚያሳይ ያደረገላችሁ ነው ፡፡ አላህ በሰዎች ላይ በእርግጥ የችሮታ ባለቤት ነውና ፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያመሰግኑም "፡፡ የሚለውና ሌሎችም አንቀፆች የተብራሩበት ።
👉 ማንኛውም ሰለፍይ ባህሩን ቢተች ረድ ቢያደርግበት ሁለታችንም አንከስርም !

ሰለፍይ ማለት ፍፁም አይደለም ። ሊያጠፋ ሊሳሳት ይችላል ። በዚህን ጊዜ ከተቻለ መምከር ስህተቱን ራሱ እንዲያርመው ማድረግ ጥሩ ነው ። ግን ግዴታ አይደለም ። ሌላው አካል ስህተት ነው ብሎ ያየውን ሳይመክርም በቀጥታ በመረጃ ሞግቶ ተችቶ ምላሽ ሊሰጥ ይችላል ።
በመሆኑም ፍላጎቱና አላማው ምንም ይሁን ራሱን ወደ ሰለፍያ መዝሀብ ያስጠጋ ሰው በኔ ላይ ረድ ቢያደርግ ፣ ትችት ቢሰነዝር ፣ እኔም እሱም አጅር እናገኛለን ። ግን በአላህ ፈቃድ ሁለታችንም አንከስርም ። ምክንያቱም ያ ሰው ለሱና ተቆርቁሮ የኔን ስህተት በመረጃ ግልፅ አድርጎ ረድ ካደረገና ከተቸ ሱናን በመጠበቁና እኔም ከስህተቴ እንድመለስ በማድረጉ አጅር አለው ።
ምናልባት ያለ አግባብ የተቸና ረድ መስሎት የሰጠው ምላሽ ልክ ባይሆን እኔ አውፍ እለውና አጅር አገኛለሁ ። ትክክል ከሆነ እሱ ለሐቅ ዲፋዕ በማድረጉ አንድ አጅር የሚያገኝ ሲሆን እኔ ወደ ተውበት ከተመለስኩ ሁለት አጅር ያገኛል ። እኔም ተውበት አድርጌ በመመለሴ አጅር አገኛለሁ ። በሁለቱም ሁኔታ ግን ሁለታችንም አንከስርም ።
አላህ ኢኽላስና ሲሳሳቱ መመለስን ይወፍቀን !

http://t.me/bahruteka
ወሳኝ የሆነ ምክር በሸይኻችን
ሸይኽ ሙሐመድ ሀያት አል ወሎዊ (አቡ መንሱር) Sheikh Muhammed Heyat (Abu Mensur)
👉👉 ወሳኝ የሆነ ደዕዋ

☯️ ርዕስ በተውሂድ ላይ አደራ ና ተያያዥ ነጥቦች


🎤 በሸይኽ ሙሀመድ ሀያት

🕌
ሀራ - በመስጂድ አልፉርቃን

ቀን: 1/12/2018 ከመغሪብ — ኢሻ

🥇 በውስጡ በጣም ጠቃሚ ርዕሶች ተዳሰውበታል
ከነዚህም መካከል
— ለተውሂድ መስራት እንዳለብን
— የነብዩ የደዕዋ ሂደት
— ስለ ጥመት አንጃወች
— ስለ ተቅዋ
ና ሌሎቹም ጠቃሚ ርዕሶች ተዳሰውበታል ።

ሸር በማድርግ ይህን ወሳኝ ሙሓደራ ከማህበሰረባችን ለማድረስ እንሞከር ባረከሏሁ ፊኩም

https://t.me/SheikMohmmedHyatHara
https://t.me/SheikMohmmedHyatHara