ባህሩ ተካ - Bahiru Teka
41.4K subscribers
711 photos
30 videos
118 files
4.19K links
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
قناة رسمية
لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا
(أبو عبيدة) الدعوة السلفية

በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን
እንለቃለን
ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ
ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka
Download Telegram
👉  አንተ ሰለፍይ ሆይ ያንተን መካም ስብእና ለሌሎች የከረፋ ማንነት ብለህ አትቀይር

     አላህ ሰዎችን ሲፈጥር የተለያየ ስሜትና ፍላጎት ሰጥቶ ፈጥሯል ። የሱ ሒክማ ባስፈረደው መልኩ ግማሹ ሰላምና ፍቅር ፣ እዝነትና ትህትና ፣ ማክበርና መተናነስ ፣ ለሌሎች ከፍታ የሚጥርና በዚህ የሚረካ ፣ ሰዎች ስኬት ላይ ሲደርሱ የሚደሰት አድርጎ ፈጥሮታል ። በተቃራኒው ደግሞ የሌሎች ሰላምና ፍቅር እረፍት የሚነሳው ፣ እርክሰትና እብሪት የተጠናወተው ፣ ሌሎችን በትንሽ አይን እያየ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ፣ የሰዎች ስኬት እሳት የሚሆንበትና እንቅልፍ የሚነሳው ፣ ህልምና ፍላጎቱ ሰዎች ወድቀው ማየት የሆነ ፣ ይህን ለማሳካት የፈለገውን ዋጋ እንዲከፍል አድርጎ ፈጥሮታል ። ይህ የሱ ጥበብ ያስፈረደው ስለሆነ በምድር ላይ ሁሉም አብረው ይኖራሉ ።
     እዚህ ጋር ጥንቃቄ የሚያስፈልገው አላህ መልካም ስብእና ሰጥቶ የፈጠራቸው ሰዎች የራሳቸውን መልካም ስብእና የሌሎች የተበላሸ ማንነት ሊቀይረው እንደማይገባ ነው ። ሁሉም ለተፈጠረለት ነገር የተገራ ስለሆነ ሁለቱም ስራቸውን አያቆሙምና መልካሙ ስብእና ሊጠበቅ ይገባል ። የበቀሉ አምላክ አለና አንተ ለመበቀል አታስብ ።
     ይህን የሚያሳይ አንድ ክስተት ልንገራችሁ ። አንድ ገበሬ ጫካ ላይ እሶክ መንጥሮ እያቃጠለ እያለ አንድ እባብ እየተሳበ ወደ እሳቱ ሲመጣ አየውና መቃጠል የለበትም ብሎ አንገትና ጅራቱን ይዞ ወደ ጫካ ወስዶ ያስቀምጠዋል ። ይሁን እንጂ በእባቡ ከመነደፍ አላመለጠም ። የነደፈውን ቦታ መድሀኒት አድርጎበት ወደ ስራው ሄደ ። ከጊዜ በኋላ አሁንም እሾክ መንጥሮ እያቃጠለ እያለ ሌላ እባብ እየተሳበ ወደ እሳቱ ሊገባ ሲል እንደ መጀመሪያው አደረገ ። አሁንም ተነደፈ ። የዚህን ጊዜ በሁለቱም ገጠመኝ እያየው የነበረ አንድ ሌላ ገበሬ ባለፈው ተነደፍክ እንዴት አሁንም እባብን አድናለሁ ብለህ ትነደፋለህ አለው ።
    ገበሬውም መናደፍ የእባብ ባህርይ ነው ማዳን ደግሞ የኔ ባህርይ ነው ለእባብ ባህርይ ብዬ የኔን ባህርይ አልቀይርም አለው ይባላል !!! ።
  
https://t.me/bahruteka
👉 ሙሐመድ ሓሚዲን የሰይድ ቁጥብ ጠበቃ !

ክፍል ስድስት

ሰይድ ቁጥብ ወሕደተል ውጁድና ቁርኣን መኽሉቅ ነው ማለቱን በመረጃ ማረጋገጥ ።

ወሕደተል ውጁድ ማለት ወሰን ያለፉ ሱፍዮች ዐቂዳ ሲሆን ከነሷራና አዩሁዶች የባሰ ኩፍር ያለባቸው እንደነ ኢብ ዐረቢ የመሳሰሉ አካላት ዐቂዳ ነው ። ትርጉሙ በፍጥረተ ዐለሙ ያለ ነገር ሁሉ አላህ ነው የሚል ሲሆን አንድ ሰው ድንጋይም ዛፍም አውሬም ቢያመልክ ችግር የለውም እንደማለት ነው ። ምክንያቱም በዚህ አስተሳሰብ በምድር ላይ ያለ ነገር ሁሉ የአላህ መገለጫ ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው ። በመሆኑም አንተ የምትገዛው የትኛውም ነገር አላህ ስለሆነ ምንም ችግር የለውም ነው እነርሱ ዘንድ !!!
ሰይድ ቁጥብ መጀመሪያ አካባቢ ፊ ዚላለል ቁርኣን በሚለው ኪታቡ ላይ ይህን አስተሳሰብ በማውገዝ በሱረቱል በቀራ ላይ የከሀዲያን ዐቂዳ ነው ብሎ አውግዞት ነበር ። ነገር ግን መጨረሻ ላይ የፈላሲፋዎቹን መፅሐፍት አንብቦ ሐቅ ነው ብሎ አምኖበት ይመስላል ይህንን አስተሳሰብ ወይም ዐቂዳ በግልፅ ቋንቋ ብዙ ቦታ ላይ አስፍሯል ። እኔ አንዱን ብቻ ልጥቀስ : –
" إنها أحدية الوجود، فليس هناك حقيقة إلا حقيقته، وليس هناك وجود حقيقي إلا وجوده، وكل موجود آخر؛ فإنما يستمد وجوده من ذلك الوجود الحقيقي، ويستمد حقيقته من تلك الحقيقة الذاتية، وهي من ثم أحدية الفاعلية، فليس سواه فاعلاً لشيء أو فاعلاً في شيء في هذا الوجود أصلاً، وهذه عقيدة في الضمير، وتفسير للوجود أيضاً ".
الظلال - سورة الإخلاص (6/ 4002)

" ነገሩ የግኝት አንድነት ነው ። ከሱ (ከአላህ መገኘት) ውጪ እውነተኛ መገኘት የለም ። የማንኛውም ነገር መገኘት ከዛ ከእውነተኛው መገኘት ነው የሚወሰደው , ከዚህ በመነሳት እሱ የሰሪ አንድነት ነው ። ከውነተኛው ግኝት ውጪ በአንዳች ነገርም ሆነ ለአንዳች ነገር ሰሪ የለም ። ይህ በልብ ውስጥ ያለ ዐቂዳ ነው ። ( ለፍጥረተ ዐለሙም ትንታኔ ነው "።

ፍልስፍና ስለሆነ ብዙ ግልፅ ላይሆን ይችላል ። ምክንያቱም አስተሳሰቡ የተወሰደው ራሱ ከፈላሲፋዎች ስለሆነ ። የዚህ ዐቂዳ ባልተቤቶችን እንደነ ኢብኑ ዐረቢ ፣ ኢኑል ፋሪድና ኢብኑ ሰቢዒን የመሳሰሉትን የሰለፍ ሊቃውንቶች ኩፍራቸው ከነሷራና አዩሁዶች ኩፍር ይብሳል ብለዋቸዋል ።
ሰይድ ቁጥብ በሱረቱል ኢኽላስና አል ሐዲድ ላይ በብዙ ቦታ ነው ይህን የሚያረጋግጠው ። ከላይ እንዳልኩት መጀመሪያ አካባቢ በጣም ሲኮንነው የነበረ አስተሳሰብና ዐቂዳ ነበር ። መጨረሻ ላይ ግን ዋናው የአስተሳሰቡ መሪ ሆኗል ። የዚህ ምክንያት ግብፅ የሱፍዮች መፍለቂያ ስለሆነች በእነርሱ አስተሳሰብ ተፅኖ ስር ወድቆ ካመነበት በኋላ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል ።
— ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ስለዚህ ተጠይቀው ሲመልሱ እንዲህ ብለዋል : –
" مسكين ضايع في التفسير "
" ስለተፍሲር የማያውቅ የጠፋ ምስኪን ነው "

— ሸይኽ አልባኒ ስለዚህ ንግግር ተጠይቀው ሲመልሱ እንዲህ ብለዋል : –
" هذا الكلام كفر ، ولا يجوز إقراره ، ولا يجوز إبقاؤه "
" ይህ ንግግር ኩፍር ነው ። ይህን ማረጋገጥ አይፈቀድም ። ይህን ማቆየትም አይፈቀድም " ( ማጥፋት ያስፈልጋል) እንደማለት ነው ።

— ሸይኽ ሷሊሕ አል ዐሰይሚን ስለሰይድ ቁጥብ ንግግር ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል : –
" قرأتُ تفسيره لسورة الإخلاص وقد قال قولاً عظيماً فيها مخالفاً لما عليه أهل السنة والجماعة؛ حيث أن تفسيره لها يدل على أنه يقول بوحدة الوجود"
" የሱረቱል ኢኽላስን ተፍሲር አንብቤዋለሁ የአህሉ ሱናዎችን ዐቂዳ የሚፃረር ከባድ ንግግር ተናግሯል ። የዚህ ሱራ ተፍሲሩ በወሕደተል ወጁድ እንደሚል ያመላክታል " ።

ሰይድ ቁጥ ስለወሕደተል ውጁድ ከተናገረባቸው ንግግሮች ውስጥ አንዱን ነው የጠቀስኩ እንጂ በጣም ብዙ ነው ። ከዑለሞችም ንግግር ውስጥ የጥቂቶቹን ነው ያመጣሁተረ ። ነገር ግን ሐቅን ለሚፈልግ በቂ ሲሆን ለባጢል ለሚወግንና ለባጢል ለሚከላከል ተውራትና ኢንጂልን ቁርኣንን ጨምረህ ብታመጣለት አይቀበልም ። ለዚህም ነው ሙሐመድ ሓሚዲን ስሌት እየሰራ አጣፍቶ ጥብቅና ቆሞለት ሚዛን በሌለው ሚዛናዊነቱ ሙዋዘና የሰራው ።

አላህ ሐቅን አውቀው ከሚከተሉና ባጢልን አውቀው ከሚርቁ ባሮቹ ያድርገን ።

https://t.me/bahruteka
🔷 ለ2019 በዳሩል ሂጅራ የሒፍዝ ማእከል ለመግባት ያለፉ ተማሪዮች ስም ዝርዝር : –

1 – ቢላል ሻሚል ቃራ ቃራ
2 – ሲማሩ ዲንሰፋ ዲቸ
3 – ካሚል አብደላ ማዞሪያ
4 – ሚዕራጅ ወርቁ ጠረደ
5 – ዩሱፍ ሙከሚል ጋርዳሼ
6 – አብዱል ወዱድ ጉንችሬ
7 – ዒልሙ አበሻ አጋሬ
8 – መዕሩፍ ናስር ገንበናር
9 – አብዱል ሐኪም ኧረንባጥ
10 – አብዱል በር ሙራድ አብርር
11 – ኑር ዘማን ገረመው ኧጂጊሳይ
12 – ቢላል ይሽርጋ ጎንቸቢድ
13 – አንዋር ያሲን አጫወደ
14 – ፉአድ ረጀብ አብሬት
15 – ሙሐመድ ሸምሱ ኧወተሬ
16 – ሳዲቅ ኑሩ ኧሽኩራ
17 – ሙሪዱ ዋቢ ቡባር
18 – አልሐምዱ መካ ሆርበት
19 – ሀይደር ነስሩ ጓንታና
20 – መኑር ሙርጋ አጋታ ናቸው ።

ተማሪዮች ወደ መርከዝ የሚገቡት መስከረም ሰኞ መስከረም 04/2019 ሲሆን ይዘውት መምጣት ያለባቸው : –
— ቢያንስ ሁለት ነጭ ጀለቢያከስር ከሚለበሱ
ቲሸርቶችና ቁምጣዎች ከ2 ነጭ ኮፍያ ጋር
— ጠዋት ለፈጅር የሚለብሱት ፎጣ
— ለውዱእ የሚሆን ነጠላ ጫማ ናቸው ።
ዳሩል ሒጅራ ላለፉት ተማሪዮች በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ እያለ መልካም የሒፍዝ ዘመን እንዲሆንላችሁ ይመኛል ።
🔷 ማስታወሻ

ነባር ተማሪዮች የሚመለሱበት ቀን እሁድ መስከረም 3/2019 ስለሆነ ላልሰሙት በማሰማት ተባበሩ ለማለት እንወዳለን ።
✅ ከአርሽ ጥላ ስር መሆን ስሜትን በመኻለፍ ነው የሚገኘው !

يقول ابن القيم – رحمه الله –

" إذا تأملت السبعة الذين يظلهم الله – عز وجل – في ظل عرشه يوم لا ظل إلا ظله، وجتهم إنما نالوا ذلك الظل بمخالفة الهوى "

روضة المحبين ونزهة المشتاقين ص( 648)

🔹 ኢብኑል ቀይም የተባለው ታላቅ ሊቅ እንዲህ ይላል : –

" እነዚያን ጥላ በሌለበት ቀን አላህ በአርሹ ጥላ ስር የሚያጠላቸውን ካስተዋልካቸው ይህን ( የዐርሹን) ጥላ ያገኙት ስሜታቸውን በመኻለፋቸው ሆኖ ታገኘዋለህ "

https://t.me/bahruteka
👉 ደስታ የሚሞላው መቼ ነው ?

يقول الشيخ ابن باز – رحمه الله –

" فمن صبر عند البلية، وشكر عند النعمة، تمت له السعادة، وصار من الناجين "

مجموع الفتاوى (1/96)

ሸይኽ ኢብኑ ባዝ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላሉ : –

" በፈተና ጊዜ ሶብር ያደረገና ፀጋ ሲያገኝ ያመሰገነ ደስታ ሞልቶለታል ። ከሚድኑትም ይሆናል "።

https://t.me/bahruteka
መስጂድ እና ሙሰላ ይለያያሉን?
ከዑለማዎች ፈታዋ
🟢መስጂድ እና ሙሰላ ይለያያሉን ❓

⏸ፈታዋውን ከሰጡት ዑለማዎችውስጥ፡

አሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን
አሸይኽ ሳሊህ አልኡሰይሚን
አሸይኽ ሰዕድ አልኸስላን

⏸ከፈታዋዎቹ ከሚገኙ ቁምነገሮች ውስጥ

✏️መስጂድ ለአላህ ወቅፍ ነው አይሸጥም አይለወጥም። ሙሰላ ግን ወቅፍ አልተደረገም።የሰው ሀብት ከመሆን አልወጣምና።

✏️በኪራይ መድረሳዎች ውስጥ ጀመዓ ቢሰገድባቸውም እንኳ የመስጂድ ሁክም አይዙም።

✏️ትምህርት ቤቶች ፣ መስሪያ ቤቶች ወዘተ ውስጥ ያሉ መስገጃዎች ሙሰላ ናቸው።

✏️መንግስት ካፊርም ቢሆን ለሙስሊሞች ለመስጂድ በቋሚነት የሰጠው ቦታ ወቅፍ ነው።

✏️በካፊር ሀገሮች የሚሰገድበት የኪራይ ቤትም ሆነ ቦታ ሙሰላ እንጂ መስጂድ አይሆንም።

✏️ኢዕቲካፍ በመስጂድ ውስጥ እንጂ በመድረሳ ወይም በሙሰላ ውስጥ አይሆንም።

✏️ሙሰላ እንደመስጃድ ባይሆንም ግን ሊከበርና ስርዓቱ ሊጠበቅ ይገባል።

ሌሎችም ጠቃሚ ቁምነገሮችን ያቀፈ ስለሆነ በጥሞና አዋቂዎች ሰምታችሁ  ጉዳዩን ላልገባቸው ሁሉ አብራሩላቸው::

https://t.me/FATTAWAS
👉 ሙሐመድ ሓሚዲን የሰይድ ቁጥብ ጠበቃ !

ክፍል ሰባት

ሰይድ ቁጥብ ቁርኣን መኽሉቅ ነው የሚል ለመሆኑ ከራሱ መፅሐፍ በመረጃ ማረጋገጥ !

ውድ ሰለፍዮች ቁርኣን የአላህ ቃል መሆኑ የራሱ የቁርኣን ፣ የነብዩና የሶሓቦች አስተምሮ ነው ። ቁርኣን ፊደሎቹም ንግግሩም መልእክቱም ባጠቃላይ የአላህ ቃል ነው ። አላህ በቀጥታ ተናግሮበት ጅብሪል ሰምቶት ወደ ነብዩ ያደረሰው መለኮታዊ የህይወት መመሪያ ነው ። ንግግር የአላህ ሲፋ ነው ። የአላህ ሲፋ መኽሉቅ (የተፈጠረ) ነው የሚል ይከፍራል ።
ይህ ነጥብ የነብዩን ሱና በተከተሉና በዲን ላይ አዳዲስ ፈጠራ ባመጡ የጥመት አንጃዎች መካከል መሰረታዊ የልዩነት ነጥብ ነው ። ከእነዚህ የጥመት አንጃዎች ዋና ዋናዎቹ ጀህምዮችና ሙዕተዚላዎች ፣ እንዲሁም አሻዒራዎች ይገኙበታል ። በመካከላቸው የአገላለፅ ልዩነት ቢኖርም የአላህ ቃል አይደለም መኽሉቅ ነው የሚለው ያገናኛቸዋል ። በመሆኑም የዚህ አይነት ዐቂዳ ባለቤት የሆነ ሰው እንኳን የዲን መሪ ሊሆን ጉዳዩ ዑለሞች ዘንድ ይከፍራል ወይስ አይከፍርም ነው ።
ሰይድ ቁጥብ ቁርኣን መኽሉቅ ነው የሚል ለመሆኑ ከራሱ መፅሐፍ እንመልከት : –

" إن القرآن ظاهرة كونية كالأرض والسماوات"

الظلال: (4/2328
" ቁርኣን ግልፅ የሆነ ሁን በሚለው የአላህ ትእዛዝ እንደ ሰማይና ምድር የተፈጠረ ነው "።

"والشأن في هذا الإعجاز هو الشأن في خلق الله جميعاً وهو مثل صنع الله في كل شيء وصنع الناس".
الظلال (1/38)
" የዚህ ማሳኛ ( ቁርኣን) ጉዳይ እንዳጠቃላይ የአላህ መፍጠር ነው ። ምሳሌው በሁሉ ነገር ላይ የአላህ መፍጠር አይነት ነው… " ።

وقال عن الحروف المقطعة :

" ولكنهم لا يملكون أن يؤلفوا منها مثل هذا الكتاب, لأنه من صنع الله لا من صنع إنسان".

الظلاله (5/2719)
ሆሄያቶችን ( ምህፃረ ቃላቶችን) አስመልክቶ ሲናገር እንዲህ ይላል : –
" ከሀዲያኖች እንደዚህ አይነት (ቁርኣን) መፃፍ አይችሉም ። ምክንያቱም የሰው ስራ ሳይሆን የአላህ ስራ (መፍር) ስለሆነ ነው " ።

وهذا الحرف "صاد " يقسم به الله سبحانه, كما يقسم بالقرآن ذي الذكر, وهذا الحرف من صُنعة الله فهو موجده, موجده صوتاً في حناجر البشر".
الظلال (5/3006)
የሷድን ምእራፍ ሲያብራራ እንዲህ ይላል : –
" በ" ሷድ " አላህ ጥራት የተገባው ጌታ ይምላል ። በቁርኣን እንደሚምለው ሁሉ ። ይህ ፊደል የአላህ ስራ ነው ። እሱ ነው ያስገኘው (የፈጠረው) በሰዎች ጉሮሮ ውስጥ ድምፅ አድርጎ ያስገኘው ነው "።
የአላህ ቃል ሳይሆን በሰዎች ጉሮሮ ውስጥ ድምፅ ሆኖ የተፈጠረ ነው ይለናል !!!።
ይህ ነው ኢኽዋኖች ከነብያቶችና ከሶሓቦች በላይ ንግግሩን የሚቀበሉትና ለክብሩና ለዝናው ጥብቅና የሚቆሙለት የኢኽዋኖቹ መሪ !!!
ሰይድ ቁጥብ ማለት በአለም ላይ አጥፍቶ የመጥፋትን ሽብር በእስልምና ስም ያሰራጨ የሱን አስተሳሰብ ያልተቀበሉ የሙስሊም መሪዮችና ዑለሞችን እያከፈረ እነርሱን አጥፍቶ መጥፋት ፅድቅ ነው የሚል ትውልድ እየተተካ እንዲሄድ የሚያደርግ መርህ ትቶ የሄደ ግለሰብ ነው ። ንግግሮቹና ተግባሮቹ የሚያከፍሩ ከመሆናቸውም ጋር ንግግሩንና ተግባሩን የሚመዝንበት የሸሪዓ እውቀት ስላልነበረው በወቅቱ ያየው የነበረውን ሁኔታ በሸሪዓ እይታ ከማየት ይልቅ በራሱ ፍልስፍና አይቶ የራሱን ፍርድ የሰጠ ነው በሚል በጅህልና ዑዝር እየሰጡት ነው ዑለሞች ያላከፈሩት ። ይሁን እንጂ የሚመጣው ትውልድ የሱን የአእምሮ ጭማቂ ጠጥቶ እንዳይሰክር ንግግሩንና ተግባሩን በቁርኣንና ሐዲስ በሶሓቦች ግንዛቤ ውድቅ እያደረጉ ከሱ ያስጠነቅቃሉ ። ይህ ነው የነብያቶች ወራሾች ተግባር ።
የሰይድ ቁጥብን የአጥፍቶ መጥፋት አስተምሮ ቀለል እያደረጉ ሚዛን በሌለው ሚዛናዊነት ሙዋዘና ሰርተው ጥብቅና መቆም የስሜት ተከታዮች ተግባር ነው ።
አላህ ሐቅን አውቀው ከሚከተሉና ባጢልን አውቀው ከሚርቁ ባሮቹ ያድርገን ።

https://t.me/bahruteka
አይ ዱሮ! ናፈቀኝ ኢኽዋኖችን ከላይ እስከታች ኹራፋቶቻቸውን በጋራ ስናወግዝ

አሁንማ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰወች ከነ አቡ በክር ከነ ያሲን ኑሩ ከነ አሕመድን ጀበል ጋር ኮትና ሱሪ ቅልና ግጣም ሆኑ

የ አሸዋ ሜዳ ወንድሞችም በየ ክፍለ ሀገር ያሉ ወንድሞቻቸው መሻይኾቻቸውም የመጅሊሱ ዋና ተጠሪዎች ሆኑ

ይባስ ብለው አጠፋቹህ ብሎ የሚመክራቸው የሱና ሸይኽ ጠላታቸው ሆነ የለተሞ መንጋ ብለውም ሰየሙት።

t.me/abumuazhusenedris
👉 ትልቁ እውቀት ኻቲማህ እንዳይበላሽ መፍራት ነው !

يقول ابن القيم – رحمه –

" من أعظم الفقه أن يخاف الرجل أن تخذله ذنوبه عند الموت، تحول بينه وبين الخاتمة الحسنى ".
الداء والدواء ص (167)

ኢብኑል ቀይም – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –

" ትልቁ እውቀት ማለት ሰውየው በሚሞትበት ጊዜ በሱና በጥሩ መጨረሻ ( ሑሱኑል ኻቲማ) መካከል ወንጀሉ ግርዶ መሆኑን መፍራቱ ነው "።

https://t.me/bahruteka
Forwarded from 🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ) ✍ (أبو حموية)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🟢ኡማውን ያቃጠለ ቀይ እሳት ሒዝቢያ (ቡድንተኝነት) ነውና ተጠንቀቁት

🎤አሸይኽ ሙቅቢል አልዋዲዒይ

🤲ሀገራችንን ከሒዝቢያት አላህ ያፅዳልን

https://t.me/Abuhemewiya
Forwarded from 𝚝ĕ𝚠𝚑𝚎𝚎𝚍 & ŝūññã𝚑
📣👍👍👍👍👍👍👍📣

✅የሀገራችንን ሰለፍይ አሊሞች፣ ሸይሆች፣ ኡስታዞችና ዳኢዎች በአንድ መድረክ ማግኘት ይፈልጋሉ❓

📢መልስዎ 100% ❤️‍🔥‘አዎ’ እንደሚሆን ቅንጣት አንጠራጠርም❕፡፡

🗓 ለመስከረም አጋማሽ ቀጠሮ ይያዙ❕

🕐 በሀገራችን በአራቱም አቅጣጫዎች የሚገኙትን ብርቅዬና ተናፋቂ የሰለፍይ አሊሞችን፣ ሸይሆችን፣ ኡስታዞችንና ዳኢዎችን በአንድ የዳእዋ መድረክ ያገኟቸዋል - ኢንሻ  አሏህ❕
ከእውቀት ማእዳቸውና ከምክራቸው ለመጠቀም ጥሩ የአእምሮ ዝግጅት ያድርጉ፡፡

📍በኢትዮጵያ አህለ ሱና ተቋም የሚመሩትን ቻናሎቻችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡
💎💎💎

🏖️
✈️t.me/bilalmesji
(በባህርዳር አባይ ማዶ ሰለፍያ ቢላል መስጅድ ግዥና ግንባታ ማሰባሰቢያ)
✈️t.me/alateriqilhaq
(የባህር ዳር አህለ ሱና መሻይኾች ገፅ)

🔴🕐 ትክክለኛው ቀንና ሰአት በቅርቡ ይፋ ይሆናል፡፡

💡በአሏህ ፈቃድ ሰለፍይነት ያብባል፤ ተውሂድ ይነግሳል፡፡

🌐https://t.me/bilalmesji
🌐https://t.me/bilalmesji
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👉 ሙሐመድ ሓሚዲን የሰይድ ቁጥብ ጠበቃ !

ክፍል ስምንት

ሰይድ ቁጥብ የእስልምና ሸሪዓ ከመሲሒያና ሹዩዒያ ተወስዶ የተጨመረበት ነው ማለቱ ከራሱ መፅሐፍ ማረጋገጥ !

ማንኛውም ሙስሊም ማወቅ ያለበት የእስልምና ሸሪዓ አላህ ከሰባት ሰማይ ከዓርሹ በላይ በጂብሪል አማካይነት በነብዩ ላይ ባወረደው ወሕይ (ቁርኣንና) በሳቸው አስተምሮ ሐዲስ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ነው ። ቁርኣን ከበስተፊቱም ሆነ ከበስተኋላው እከን የማይገኝበት ጥበበኛና አዋቂ ከሆነው አላህ የተወረደ መለኮታዊ ቃል ነው ።
አላህ ቁርኣንን የመጨረሻ መፅሐፍ አድርጎ በነብዩ ላይ ሲያወርደው ከዛ በፊት የነበሩትን ህግጋቶች የሚሽርና የበላይ ተቆጣጣሪ አድርጎ ነው ያወረደው ። በመሆኑም የትኛውም ሸሪዓ ከቁርኣን በኋላ ተቀባይነት የለውም ። የኢስላሙ ሸሪዓ ከሀያሉ አምላካችን አላህ የተወረደ ሙሉ የሆነ ከየትኛውም ጉለት የተጠበቀ ሸሪዓ ነው ።
መሲሒያ ማለት የኩፍር እምነት ሲሆን ሸሪዓውም የተበረዘ የተቀነሰበትና የተጨመረበት በየዘመኑ ለተለያዩ እንከኖች የተጋለጠ ነው ። ኢስላም ከመሲሒያ ነው ሸሪዓውን የወሰደው ወይም ጎደሎ ነበር ያሟላው ከመሲሒያ ሸሪዓ ወስዶ ነው ማለት የሚያከፍር መሆኑኑም ማወቅ በየትኛውም ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው ። ሺዩዒያ ማለት መሰረት የሌለው በፍልስፍና ላይ የተመሰረተ አላህ መኖሩን የማይቀበል የኢልሓድ አስተምሮ ነው ። የእስልምናን ሸሪዓ ወደዚህ ፍልስፍና ማስጠጋት በእስልምና ላይ የተቀጠፈ ትልቅ ቅጥፈት ነው ። ከዚህም በላይ መለኮታዊውን የአላህ ቃል ዋጋ ማሳጣትና የነብዩን ሸሪዓ ከጀርባ መውጋት ነው ። እንዲህ አይነቱ ቅጥፈት ወንጀሉ በጣም የሚከብደው ሙስሊም ነኝ በሚል አካል የሚሰነዘር ሲሆን ነው ።
ለመግቢያ ይህን ያክል ካልን ይህ ቅጥፈት የሰይድ ቁጥብ መሆኑ በሚቀጥለው የራሱ መፅሐፍ እንመልከት : –

" ولا بد للإسلام أن يحكم ، لأنه العقيدة الوحيدة الإيجابية الإنشائية التي تصوغ من المسيحية والشيوعية معا مزيجا كاملا يتضمن أهدافهما جميعا ويزيد عليهما التوازن والتناسق والاعتدال"
معركة الرأسمالية والإسلام ص(61)

" እስልምና ዳኛ ለመሆኑ ቅሮት የለውም ። ምክንያቱም ከመሲሒያና ከሹዩዒያ አንድ ላይ ተደባልቆ ሙሉ ሆኖ ተወስዶ የሁለቱንም አላማ ይዞ (እስልምና) ሚዛናዊነት መስማማትና ፍትሕን ጨምሮበት የሌላውን ዐቂዳ ሳይጥል ግለሰብም ይሁን ማህበረሰብ የሚገነባ ዐቂዳ ባለቤት ስለሆነ ነው " ‼።
ተመልከቱ በዚህ ንግግር ውስጥ የእስልምናን አስተምሮ መርህ የሚንዱ በጣም ብዙ የኩፍር ንግግሮች አሉበት ። ከእነዚህ ውስጥ : –
" العقيدة الوحيدة الإيجابية والإنشائية "
– የሌሎችን ሳይጥል በግለሰብና በማህበረሰብ ደረጃ የሚገነባ ዐቂዳ ስለሆነ ።
ይህ ማለት ኢስላም የኩፍርና የሽርክን ዐቂዳዎች ውድቅ ሳያደርግ አጠናክሮ ስራ ላይ እንዲውሉ ያደረገ ዲን ነው ማለት ነው ‼ አላህ ይጠብቀን ። በሌላ በኩል የሀይማኖት እኩልነትም ሽታ አለው ።
" التي تصوغ من المسحية والشيوعية معا مزيجا كاملا يتضمن أهدافهما جميعا "
— እስልምና ከመሲሒያና ከሹዩዒያ ሙሉ ሆኖ የተደባለቀውን ሸሪዓ የሁለቱንም አላማ ተቀብሎ ሚዛናዊ እንዲሆኑ አድርጎ የሚሰራበት ዲን ነው እንደማለት ነው ። ይህ ማለት የእስልምና ሸሪዓ የሁለቱ ጭማቂ ነው ማለት ነው ። " አላሁመ ሰሊም "!!!
"ويزيد عليهما التوازن والناسق والإعتدال "
— የእስልምና ሸሪዓ የሁለቱ ጭማቂ ሆኖ እስልምና የጨመረው ሚዛናዊነት እንዲሁም እንዲስማሙና ፍትሐዊ እንዲሆኑ ማድረግ ነው ። ይህ ማለት እስልምና ኩፍርና ሽርክን ተቀብሎ እውቅና ከሰጠ በኋላ የተስማሙ ሚዛናዊና ፍትሐዊ አድርጎ በእነርሱ የሚፈርድ ዲን ስለሆነ ነው መፍረድ ያለበት እያለ ነው ።
በጣም የሚገርመው ቁርኣን ተፍሲር ኩቱቡ ሲታ እናስቀራለን ከማንም በላይ እስልምናን ሚዛናዊ በሆነ መልኩ የተረዳነው እኛ ነን የሚለው ሙሐመድ ሓሚድን ለዚህ ግለሰብ ነው ሚዛን በሌለው ሚዛናዊነቱ ሙዋዘናት እየሰራ ያ በዚህ ይጣፋል እያለ ጥብቅና የቆመለት ።
አላህ ሐቅን አውቀው ከሚከተሉና ባጢልን አውቀው ከሚርቁት ያድርገን ።

https://t.me/bahruteka
✅ አላህን በኢማን ላይ ፅናት ሰጥቶህ መጨረሻህን እንዲያሳምርልህ ለምነው !

يقول السعدي – رحمه الله –

" ينبغي للعبدي أن يلح دائما على ربه في تثبيت إيمانه، وأن يحسن له الخاتمة "

تيسير اللطيف المنان ص (286)

" አንድ ባሪያ ኢማኑን አፅንቶለት መጨረሻውን እንዲያሳምርለት ሁሌም መለመን ያስፈልገዋል " ።

https://t.me/bahruteka
👉 ከዒልም አደብ መቅደም አለበት !

يقول الإمام مالك بن أنس – رحمه الله –

" كانت أمي تعممني وتقول لي : اذهب إلى ربيعة فتعلم من أدبه قبل علمه "

ترتيب المدارك وتقريب المسالك (1/130)

ኢማሙ ማሊክ እንዲህ ይላል : –

" እናቴ አመኢማ ታለብሰኝና እንዲህ ትለኝ ነበር ። ረቢዓ ( የኢማሙ ማሊክ ሸይኽ ናቸው) ጋር ሂድና ከዒልሙ በፊት አደብ ተማር " ።

https://t.me/bahruteka
Audio
ሸይኽ ዐ/ሀሚድ አል'ለተሚይ
🔊 አዲስ ሙሐደራ

ርዕስ፦“ስለ ሹክር”

🎙ሸይኽ ዐብዱል ሐሚድ አል ለተሚይ

🕌 ሌራ ኢማሙ አሕመድ መስጂድ

🗓 ረቢዐ'ልአወል 19 (1448)

t.me/abdulham/2852
t.me/abdulham/2852
خمسون_نصيحة_لطلاب_العلم_والوقاية_من_الوقوع_في_الفتن_والبدع_وتجنب.pdf
290.2 KB
هذه الرسالة من أنفع الرسائل التي كتبها الشيخ الفاضل الدكتور حسين بن محمد،حفظه الله تعالى
لما اشتملت عليه من نصحٍ وتوجيهٍ وعلاجٍ لأمراضٍ كثيرةٍ منتشرةٍ بين الشباب في هذا الزمان، وستكون ـ بإذن الله تعالى ـ دواءً نافعًا لكثيرٍ من تلك الآفات ونسأل الله أن يجعلها مباركة ويثبت كاتبهاعلى الصراط المستقيم والمنهج القويم ونسأله تعالى أن يحفظ عقيدةالمسلمين ومنهجهم في كل زمان وفي كل مكان من الانحراف والتضليل عن سبيل الله
የጁሙዐ ኹጥባ ( ምክር )
ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ
♦️| አንገብጋቢ የጁሙዐ ኹጥባ !

« ከሀዲያኖችን በማንኛውም መልኩ መመሳሰል በኢዶቻቸው ላይ ተሳትፎ ማድረግ ሀራም ነው » !
أي نعم ...

— ፂምህን ለራሱ እንደነሱ ጥጥ አስመስለህ አትሒድ ! ሸሪአ በሒና ቀይረህ እንድትኸልፋቸው አዟሀል !

🎙 ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ    - ሐፊዞሁ'ሏህ -

🕌 በ ኮምቦልቻ ከተማ ሰላም መስጂድ

🗓 መስከረም /𝟎𝟏/ 𝟐𝟎𝟏𝟗

|| የቴሌግራም ቻናል፦https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha
በእጅ የያዙት ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል።
◈◈◈

ኢብኑ ተይሚያን መስሊም ነን የሚሉ በርካታ ጭፍራዎች "ካፊር ነው" እና መሰል ትችቶችን እያቀረቡ እሱን ለማዋረድ ጥረት እያደረጉ ባለበት ተጨባጭ የምዕራባውያን ምሁራኖች እና ታላላቅ የአካዳሚክ ተቋማት ስለ ኢብኑ ተይሚያህ ጥናት እያካሄዱ ነው።

አዎ ኢብኑ ተይሚያህ ለአለም ህዝብ የሚጠቅሙ ስራዎች አሉትና ሊጠና ሊመረመርና ደረጃው ሊታወቅ ይገባል።

የዘመናዊ አካዳሚክ ምሁራን ኢብኑ ተይሚያህን እንደ “የሰለፍያ ምሁር” ብቻ ሳይሆን የመካከለኛው ዘመን ታሪክ የተለያዩ ዘርፎች ምሁር አድርገው ያጠኑታል። ከነዚህ የምዕራቡ አለም ምሁራን መካከል፦

1) Jon Hoover — ጆን ሁቨር

በዘመኑ ከኢብኑ ተይሚያህ ጥናት ጋር በጣም የተያያዘ ምሁር ነው።
ዋና የጥናት መስኮቹ፦
የኢብኑ ተይሚያህ የዐቂዳ አስተሳሰብ
የአላህ ባህሪያት
ምክንያትና ወሕይ
የኢብኑ ተይሚያህ ሥራዎች የእጅ ጽሑፍ ምንጮች የኢብኑ ተይሚያህ ቅርስ
በተጨማሪም የኢብኑ ተይሚያህ የአረብኛ የእጅ ጽሑፎችንና የታተሙ እትሞችን ለምርምር የሚጠቅም ሰፊ መመሪያ አዘጋጅቷል።

2) Carl Sharif El-Tobgui — ካርል ሻሪፍ ኤል-ቶብጊ

በተለይ درء تعارض العقل والنقل
በተሰኘው የኢብኑ ተይሚያህ ኪታብ ላይ ጥልቅ ጥናት አድርጓል። ይህ የሸይኹል ኢስላም ኪታብ አቅል ማለትም አእምሮ እና ቁርኣን ወይም አድስ ይጋጫሉን የሚለውን ጉዳይ የዘረዘረበት ነው።

ይህ ምሁር Ibn Taymiyya on Reason and Revelation በማለት ሰፊ ጥናት አስቀምጧል።

3) Yossef Rapoport — ዮሴፍ ራፖፖርት

በኢብኑ ተይሚያህ የፊቅህና የሕግ አስተሳሰብ ላይ ጥናት አድርጓል።

4) Shahab Ahmed — ሻሃብ አህመድ
ከRapoport ጋር በመሆን Ibn Taymiyya and His Times የተባለውን መጽሐፍ አዘጋጅቷል።

ይህ መጽሐፍ ከተለያዩ ምሁራን የተሰበሰቡ ጥናቶችን ይዟል፤ ዐቂዳ፣ ተፍሲር፣ ፊቅህ፣ ሺዓ–ሱኒ ውይይት፣ ክርስትና ጋር ያለው ክርክርና የኢብኑ ተይሚያህ ተፅእኖ ይዳስሳል።

5) Caterina Bori — ካተሪና ቦሪ

የኢብኑ ተይሚያህን የሕይወት ታሪክ፣ ተማሪዎቹንና የእርሱን ምሁራዊ ጥበብ አጥንታለች።

6) Yahya Michot — ያሕያ ሚሾ

ኢብኑ ተይሚያህን በተለይ በፖለቲካ፣ በጂሃድ ፋታዋዎችና በዘመናዊ እንቅስቃሴዎች የተጠቀሰበት መንገድ ላይ አጥንቷል። የኢብኑ ተይሚያህን ጽሑፎች ከኋለኛው ዘመን የጽንፈኝነት ትርጓሜዎች መለየት እንዳለበት ያስረዳል።


7) Rachael Omari

የኢብኑ ተይሚያህን በሱና ዙሪያ ያለውን እይታ "Theology of the Sunna" በሚል ያጠናች ሲሆን በተጨማሪም ከአአሻኢራዎች ጋር ያለውን የክርክር ታሪክ አጥንታለች።

8) David Thomas
በኢብኑ ተይሚያህ ከክርስትና ጋር ያደረገውን የክርክር ሥራ፣ በተለይ
الجواب الصحيح لمن بدل دين المسيح
የተሰኘው ኪታብ ላይ ጥናት አድርጓል።

♻️ አሁን ያሉ በጣም አዳዲስ ጥናቶች

● Mehdi Berriah — መህዲ በሪያህ
እና
● Arjan Post — አርጃን ፖስት

➹ እነዚህ ሁለቱ በ2026 አንድ አዲስ እና ክፍት የሆነ የአካዳሚክ መጽሐፍ አዘጋጅተዋል፦
Ibn Taymiyya’s Thought: Corpus, Reception, and Legacy
ይህ በLeuven University Press የታተመ 282 ገጽ ያለው መጽሐፍ ነው። የኢብኑ ተይሚያህን ጽሑፎች፣ አስተሳሰብ፣ በታሪክ ያለው አቀባበል እና ዘመናዊ ትርጓሜዎች ይመረምራል።

ከዋና ዋና ተቋማት መካከል፦
ኢብኑ ተይሚያህ ጥናት በአንድ ተቋም ብቻ አይካሄድም። በተለይ እነዚህ ቦታዎች ጠንካራ የእስላማዊ ጥናት ሥራ አላቸው

1/ University of Oxford – Islamic Studies

2/ Princeton University – Department of Near Eastern Studies

3/ KU Leuven – Arabic and Islamic Studies

4/ University of Nottingham – Islamic Studies

5/ Leiden University / Brill – Islamic Studies

6/ Cambridge University – Islamic Studies

7/ Harvard University – Islamic Studies

8/ SOAS University of London
French Institute for the Near East (Ifpo)

9/ Leuven University Press

ውዶቼ ለማንኛውም ስለ ምሁራችን በደንብ ለማወቅ በሚቀጥለው ሊንክ ግቡና ታሪኩን አዳምጡ!

https://t.me/AbuImranAselefy/10656