ባህሩ ተካ - Bahiru Teka
41.3K subscribers
711 photos
30 videos
118 files
4.19K links
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
قناة رسمية
لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا
(أبو عبيدة) الدعوة السلفية

በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን
እንለቃለን
ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ
ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka
Download Telegram
አጆ ሜዳ
ሸይኽ ሙሀመድ ሀያት
ወሳኝ ና ወቅታዊ ሙሓደራ


🔑 ርዕስ : “አስታውስ ማስታውስ አማኞችን ይጠቅማልና”

🎙 በሸይኽ ሙሀመድ ሀያት

🕌 በአጆሜዳ መስጂደል ፉርቃን


በውስጡ ከተዳሰሱ ነጥቦች መካከል
👉 ወደ ተውሂድ መጣራት እንዳለብን
👉 ቤተቦቻችንን በሚገባ መልኩ ጥሪ ማድረግ እንዳለብን
👉 አዛኝ መሆን እንዳለብን
👉 በሶላት ዙሪያ
👉 ስለ ሺርክ
👉 ሱናን መያዝ እንግዳ ያደርጋል በአሁኑ ሰዓት
ና ሌሎችም ወሳኝ ነጥቦች ተዳሰውበታል ።

ሸር በማድረግ ለወገኖቻችን እናድረሰው

https://t.me/SheikMohmmedHyatHara
https://t.me/SheikMohmmedHyatHara
وجّه معالي وزير الشؤون الإسلامية والدعوة والإرشاد الشيخ د. عبداللطيف آل الشيخ، خطباء الجوامع في مختلف مناطق المملكة، بتخصيص خطبة الجمعة 21 ربيع الآخر 1448هـ، للحديث عن منزلة الصحابة رضي الله عنهم وفضلهم، وبيان فضل محبتهم والترضي عنهم، والتحذير من الوقيعة فيهم والمساس بمكانتهم.

كما وجه بالتأكيد على منهج أهل السنة والجماعة في توقيرهم وحفظ حقوقهم، وإبراز فضل الخلفاء الراشدين رضي الله عنهم وسابقتهم في نصرة الدين وحفظ جماعة المسلمين ونشر الإسلام.
قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد
وجّه معالي وزير الشؤون الإسلامية والدعوة والإرشاد الشيخ د. عبداللطيف آل الشيخ، خطباء الجوامع في مختلف مناطق المملكة، بتخصيص خطبة الجمعة 21 ربيع الآخر 1448هـ، للحديث عن منزلة الصحابة رضي الله عنهم وفضلهم، وبيان فضل محبتهم والترضي عنهم، والتحذير من الوقيعة فيهم…
የተከበሩ የእስልምና ጉዳዮች የዳዕዋና የኢርሻድ ሚኒስቲር አሽሸይኽ ዶ/ር ዐብዱልለጢፍ ኣሊ ኸይኽ በተለያዩ የሳውዲ ከተማ ያሉ ኸጢቦችን የረቢዓል ኣኺር 21/1448 አመተ ሂጅሪያን የጁሙዓ ኹጥባ ሶሓቦች ያላቸው ደረጃና ለእስልምና ያበረከቱትን ችሮታ በመግለፅና እነርሱን መውደድና ስማቸው ሲነሳ አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው ማለት ያለው ደረጃ ግልፅ ማድረግ እንዲሁም ክብራቸውን ከመንካትና ደረጃቸውን ዝቅ ከማድረግ በማስጠንቀቅ ዙሪያ እንዲሆን አዘዋል ።
በሌላ በኩልም የአህሉ ሱና ወል ጀማዓ አቋም ሶሓቦችን በማላቅና ሐቃቸውን በመጠበቅ የአራቱን ኸሊፋዎች እስልምናን ለመርዳትና የሙስሊሞችን አንድነት ለማስጠበቅና እስልምናን ለዓለም ለማድረስ በተደረገው ትግል ቅድሚያ ያላቸው መሆኑን በማወቅና በማሳወቅ ላይ ምን እንሆነ ትኩረት በመስጠት ላይም እንዲሆን አቅጣጫ ሰጥቷል ።

https://t.me/bahruteka
|| አስደሳች ኸበር

ከነገ (ረቢዐል ኣኺር 22) ጀምሮ ሸይኽ ዐብዱል ሐሚድ አል ለተሚይ መደበኛ ደርሳቸውን የሚሰጡት ሌራ ኢማም አሕመድ ይሆናል _ ኢንሻ አሏህ_ ይህንንም ተከትሎ በሸይኻችን የሚሰጠው ደርስ በቴሌግራም በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል -ቢኢዝኒሏህ-

የሚተላለፍበትም ቻናል ፦
«t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk»
✅ የሰው ልጅ ሆይ አንተ የቀናት ክምችት ነህ !

يقول الحسن البصري – رحمه الله –

" ابن آدم إنما أنت أيام كلما ذهب يوم ذهب بعضك "
سير أعلام النبلاء (4/585)

ሐሰኑል በስርይ የተባለ ሊቅ እንዲህ ይላል : –

" የኣደም ልጅ ሆይ አንተ የቀናት ( ክምችት) ነህ, አንድ ቀን በሄደ ቁጥር ከፊልህ ይሄዳል " ።

https://t.me/bahruteka
👉 አኼራ ላይ የምትፈልገው ነገር ዛሬ ሰርተህ አስቀምጠው !

يقول أبو حازم وهو ( من صغار التابعين) – رحمه الله –

" انظر الذي تحب أن يكون معك في الآخرة فقدمه اليوم، وانظر الذي تكره أن يكون معك هناك فاتركه اليوم " .
حلية الأولياء (23/238)

አቡ ሓዚም የተባለ ከመጨረሻዎቹ ታቢዒኖች የነበረ ዓሊም እንዲህ ይላል : –

" በአኼራ ላይ ካንተ ጋር መሆን የምትፈልገውን ነገር ተመልከትና ዛሬ ሰርተህ አስቀምጠው ። በአኼራ ላይ ካንተ ጋር መሆኑን የምትጠላውን ነገር ተመልከትና ዛሬ ተወው " ።

https://t.me/bahruteka
✅ በአላህ ላይ ተመካ አለም ቢያሴርብህ አይጎዳህም !

يقول ابن القيم – رحمه الله –

" إن المؤمن المتوكل على الله إذا كاده الخلق فإن الله يكيد له وينتصر له بغير حول منه ولا قوة " .
السير ص ( 216)

ኢብኑል ቀይም –ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –

" በአላህ ላይ የተመካ ሰው አለም በሙሉ ቢያሴርበት እሱ መላም ይሁን ሀይል ሳይኖረው አላህ ሴራቸውን ያመክንለታል, ይረዳዋልም " ።

https://t.me/bahruteka
👉   የቢሾፍቱ ኢሬቻ ተግባራት በኢስላም ሚዛን !

     ባህል በሚል ሙስሊሞችን ለማጃጃል የሚሞከርበት ቢሾፍቱ ላይ የሚከበረው ኢሬቻ በዐቅል ባልተቤቶች ስምምነት ጣኦት አምልኮ ነው ። በዚህ በአል ላይ ለዛፍ ይሰገዳል ! ለዛፍ ቅቤ ይቀባል ! ለዛፍ ከተቀባው ቅቤ ላይ መልሰው በረከትና ፈውስ ፍለጋ ይቀቡበታል ! ይህን እውነታ በሚቀጥለው ሊንክ ገብተው ይመልከቱ ! ሊንኩን ስትከፍቱ ድምፁ ከፍተኛ ስለሆነ እንዳይረብሻችሁ መቀነሳችሁን አትርሱ : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://drive.google.com/file/d/1JUPsOCouZBGQV-3IqeUQID-CtBil1iI4/view?usp=drivesdk
     የኢስላምን አስተምሮ ተውት የትኛው አእምሮ ነው ይህ ተግባር ባእድ አምልኮ አይደለም የሚለው ? ሰዎች በ21ኛው ክ/ዘመን ላይ ሆነው እንዴት ይህ አምልኮ አይደለም ይላሉ ?  የሚሰግዱት እምነታችን ነው እያሉ ስለሆነ አይገርምም ። ይህ ተግባር የእነዚህ ለዛፍ ሰጋጆች እምነት መሆኑን ለማረጋገጥ በሚቀጥለው ሊንክ በመግባት  ከራሳቸው አንደበት መስማት ይቻላል ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
     https://drive.google.com/file/d/1O-GiEvNBJtLt-0YXv3T12l-aHiWpVd0U/view?usp=drivesdk
    በመሆኑም እነርሱ መብታቸው ነው ። የሚገርመው የእነርሱ ሳይሆን አምልኮ አይደለም የሚሉ ተምረናል ባዮች ማስተባበያ ነው ። ለማንኛውም የአላህ ባሬያና የነብዩ ተከታይ ሙስሊሞች ሆይ ይህ ተግባር የሽርክና የኩፍር ተግባር ነውና ሸይጣን ከጎኑ አሰልፎ የጀሀነም ማገዶ እንዳያደርጋችሁ ነፍሳችሁን አድኑ ።
አላህ በተከበረው ቃሉ ከአላህ ውጪ ያሉ አካላትን ስለሚያመልኩ አካላት ሲነግረን እንዲህ ይለናል : –
{ يَا أَيُّهَا النَّاسُ ضُرِبَ مَثَلٌ فَاسْتَمِعُوا لَهُ ۚ إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ لَن يَخْلُقُوا ذُبَابًا وَلَوِ اجْتَمَعُوا لَهُ ۖ وَإِن يَسْلُبْهُمُ الذُّبَابُ شَيْئًا لَّا يَسْتَنقِذُوهُ مِنْهُ ۚ ضَعُفَ الطَّالِبُ وَالْمَطْلُوبُ }
الحج ( 73 )
" እናንተ ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምሳሌ ተገለጸላችሁ ፡፡ ለእርሱም አድምጡት ፡፡ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸው (ጣዖታት) ዝንብን ፈጽሞ አይፈጥሩም ፡፡ እርሱን (ለመፍጠር) ቢሰበሰቡም እንኳን (አይችሉም) ፡፡ አንዳችንም ነገር ዝንቡ ቢነጥቃቸው ከእርሱ አያስጥሉትም ፡፡ ፈላጊውም ተፈላጊውም ደከሙ "፡፡

አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ከመራቸው እሱን ብቻ ከሚያመልኩ ባሮቹ ያድርገን ።

http://t.me/bahruteka
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
بشرى سارة
ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎችና ለሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ
ነገ(እሁድ)  የዳዕዋ  ፕሮግራም ስላለ በሰዓቱ ተገኝታችሁ የዳዕዋው ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ ተጋብዛችሗል!!

የዳዕዋ ተጋባዥ 

🎤 ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሀፊዘሑሏህ!!

ሰዓት ✅ ከመጝሪብ -ዒሻ
ቦታ   ✅ አል-ፈትህ የተማሪዎች መድረሳ

አድራሻ =>  በዩኒቨርሲቲው ዋና በር አለፍ ብሎ በስታድየሙ ፊት ለፊት ባለው አስፓልት ገባ ብሎ በሁለተኛው ኮብል - ምስራቅ በር ት/ቤት ፊት ለፊት

👇👇👇👇👇👇
https://t.me/hutemariwochchannel
♦️| ዑለሞችን ተከተል!


"የሱና ዑለማኦችን ትተህ የመንደር ጋዜጠኛ አትስማ !

🎙 ሸይኽ አቡ ዘር ሐሰን ኮምቦልቻ -ሐፊዞሁ'ሏህ-

የድምፅ ፋይሉን ለማግኘት 👇https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha/13177
✅ ከሙብተዲዕ አህያ ይሻላል !

يقول شريك بن عبد الله النخعي الكوفي – رحمه الله– :
" لَئِنْ يَكُونَ فِي كُلِّ قَبِيلَةٍ حِمَارٌ أَحَبُّ إِلَيَّ مِنْ أَنْ يَكُونَ فِيهَا رَجُلٌ مِنَ أَصْحَابِ أَبِي فُلَانٍ " - يعني رجلاً مبتدعاً .
الإبانة (2/496)

ሹረይክ ኢብኑ ዐብዲላሂ አንነኸዕይ የተባለ ዓሊም እንዲህ ይላል : –

" በየጎሳው ሁሉ የእገሌ ( ሙብተዲዕ የሆነ ሰው) ጓደኛ አለ ከሚሉኝ አሕያ አለ ቢሉኝ የበለጠ ደስ ይለኛል " ።

http://t.me/bahruteka
👉 በብዛት አትሸንገል ተከታዩ ቢያንስም የሐቅን መንገድ ተከተል !

  يقول  فضيل بن عياض - رحمه الله تعالى - :

" اتبع طرق الهدى ولا يضرك قلة السالكين ،  وإياك وطرق الضلالة ، ولا تغتر بكثرة الهالكين  "

الإعتصام  1/135

🔷 ታላቁ ሊቅ ፉደይል ኢብኑ ዒያድ -  ረሒመሁላሁ  - እንዲህ ይላል :-

"  ቅኑን መንገድ ተከተል የተከታዮቹ ማነስ አይጎዳህም ። የጥመትን ጎዳና ተጠንቀቅ በሚጠፉ ሰዎች ብዛት አትሸንገል "

http://t.me/bahruteka
✅ ነውር የሌለበት ጓደኛ አትፈልግ !

قال الفضيل بن عياض – رحمه الله –  :

" من طلب أخا بلا عيب، بقي بلا أخ ".

             شعب الإيمان ( 10/574)

   👉  ታላቁ ዓሊም ፉደይል ኢብኑል ዒያድ እንዲህ ይላል :–

     " ነውር የሌለበት ጓደኛ የፈለገ ሰው ያለ ጓደኛ ይቀራል " ።

https://t.me/bahruteka
🔷 የስስት መነሻው በአላህ ላይ መጥፎ ጥርጣሬ ነው !

قال الامام التابعي الحسن البصري -رحمه الله-:

" نظرتُ في السخاء فما وجدتُ له أصلاً ولا فرعًا إلا حسنُ الظن بالله عز وجل، وأصلُ البخلِ وفرعُهُ سوء الظن بالله عز وجل ".

شعب الإيمان (٣٢٠/١٣)


🔹 አል ሐሰኑል በስርይ የተባለ ሊቅ እንዲህ ይላል : –

" በለጋሽነት ላይ ተመለከትኩኝ ግንዱም ይሁን ቅርንጫፍ አላገኘሁለትም በአላህ ላይ መልካምን በመጠርጠር እንጂ ! የስስታምነት ግንዱም ይሁን ቅርንጫፉ ( ደግሞ) ልቅና በተገባው አላህ ላይ መጥፎ ጥርጣሬ ነው "

http://t.me/bahruteka
👉 ሙሐመድ ሓሚዲን የሰይድ ቁጥብ ጠበቃ !

           ክፍል አስራ ሶስት

                  ማጠቃለያ

   ባሳለፍናቸው ክፍሎች ሰይድ ቁጥብ የእስልምናን አስተምሮ እንዳጠቃላይ የሰለፎችን አስተምሮ በተለይ ከኻለፈባቸው መሰረታዊ ነጥቦች ውስጥ ለማሳያ ያክል አቅርቤያለሁ ። ያ ባሆን ኖሮ በሶሓቦች ላይ የዘመተበት ዘመቻ ብቻ ብዙ ሙጀለድ ይወጣው ነበር ።
   በዚህ ዙሪያ የበለጠ ለማወቅ የፈለገ ሰው የሸይኽ ረቢዕን " መጣኢን ሰይድ ቁጥብ ፊ አስሓቢ ረሱሊላሂ " የሚለውን ኪታብ ቢያነብ በጣም ጥሩ ነው ። በአስማእ ወስሲፋት ፣ በኢማን ጉዳይና በነብዩላሂ ሱለይማን ላይ የተናገረውን ሙሪዶቹ በቀጥታ አይደለም ብለው ስለሚያለቅሱ ትቼዋለሁ ።
   የሰይድ ቁጥብ ኪታቦችን ያጠና ሰው ሁሉም በሚባል መልኩ የሚያጠነጥኑት በስልጣን ዙሪያ ነው ። የትችቶቹ መሽከርከሪያ በመንግስትነት ላይ ነው ። የእስልምናን ሸሪዓ በሙሉ በሚባል መልኩ ጠምዝዞ እሱ በምናቡ ወደ ሚያየው ስርኣት ነው የሚወስደው ። የራሱን አስተሳሰብና ሚዛን በእስልምና አስተምሮ ከማነፅ ይልቅ እስልምናን በርሱ ፍልስፍና ልክ ያልተረዳን በሙሉ ከእስልምና ወደ ማውጥት ነው ያዘነበለው ። ፍትሃዊ የሆነ አንባቢ ይህን መንፈስ ከመፅሓፎቹ ያገኛል ።
    እንደሚታወቀው ኢስላም የተወው የህይወት ጎን የለም ። ለሁሉም ስርኣትና ሚዛን ያስቀምጣል ። ሙስሊሞች የኢስላሙ ሸሪዓ እንደሚፈልገው መሆን እንጂ ያለባቸው ሸሪዓውን እነርሱ እንደሚፈልጉት ለማድረግ ሲሞክሩ ከቀጥተኛው መስመር ወጥተው ወደ ጥመት ጎዳና ይገባሉ ። ሰይድ ቁጥብም መርህ የሌለው እንሰሳዊ ህይወት የሚኖረውን  የምእራቡን አለም ስርኣትና አለም እኛ በምንዘረጋው መስመር መሄድ አለበት የሚለውን የፖለቲካ ቅዠት አይቶ ሲመለስ ለእነርሱ ፍልስፍና ምላሽ ነው ያለውን የራሱን ፍልስፍና የኢስላም አስተምሮ አድርጎ በማቅረብ በአለም ሙስሊሞች ላይ ሓኪሚያ የሚል የፖለቲካ ቅዠትን መርህ አድርጎ ሳይቀበሉት ሲቀሩ ከፍረዋል ከእስልምና ወጥተዋል ብሎ ኩፍር በየነባቸው ።
    በሰይድ ቁጥብ ሚዛን እሱ በነበረበት ዘመን የነበሩ ሙኣዚኖች ከሁሉም በላይ የሚቀጡ ካፊሮች ናቸው ። ይህ የሆነው ይላል ካወቁ በኋላ ስለከፈሩ ነው ! ።
    የሰይድ ቁጥብ ደጋፊዮች ከሱ ፍልስፈና ውጪ ለመስማትም ለመቀበልም ፍላጎት የላቸውም ። ለሱ ጥብቅና ለመቆም መታወር ግድ ነው ። ከሀገራችን የኢኽዋን መሪዮች አንዱ የሆነው ሙሓመድ ሓሚዲንም ይህን ተከትሎ ነው ለሱ ጥብቅና የቆመው ። ነፃ የሆናችሁና ለነብዩና ለሶሓቦች ዲን እንቆረቆራለን የምትሉ ከመጀመሪያው ክፍል እስከመጨረሻው አንብባቸው የሰይድ ቁጥብ አስተሳሰብ መመሪያው ከሆነው ኢኽዋንያ ራሳችሁን ነፃ አውጡ እላለሁ ።
   በሚከተሉት ሊንኮች እየገባችሁ ስለሰይድ ቁጥብ ማንነት አንብቡና የጠበቆቹን ማንነት ታውቃላችሁ  : –

ክፍል አንድ
https://t.me/bahruteka/7683
ክፍል ሁለት
https://t.me/bahruteka/7684
ክፍል ሶስት
https://t.me/bahruteka/7695
ክፍል አራት
https://t.me/bahruteka/7702
ክፍል አምስት
https://t.me/bahruteka/7710
ክፍል ስድስት
https://t.me/bahruteka/7716
ክፍል ሰባት
https://t.me/bahruteka/7723
ክፍል ስምት
https://t.me/bahruteka/7728
ክፍል ዘጠኝ
https://t.me/bahruteka/7735
ክፍል አስር
https://t.me/bahruteka/7744
ክፍል አስራ አንድ
https://t.me/bahruteka/7754
ክፍል አስራ ሁለት
https://t.me/bahruteka/7773

አበቃሁ አላህ ሐቅን አውቀው ከሚከተሉትና ባጢልን አውቀው ከሚርቁት ያድርገን ።

http://t.me/bahruteka
✅ ሶስት አይነት ሰዎችን አትከራከር !

አንደኛ – እንቢተኛ አላዋቂን
ምክንያቱም የፈለግኸውን መረጃ ብታቀርብለት አይቀበልምና ።
ሁለተኛ – ምቀኛን
ምክንያቱም የሚከራከረው ለመግባባት ሳይሆን አንተን ለማዋረድ ነውና ።
ሶስተኛ – ኩራተኛን
ሁሌም ራሱን ሐቅ ላይ አድርጎ ስለሚያይ ከሱ ጋር መከራከር ትርፉ ጊዜ ማጥፋት ነውና ።

http://t.me/bahruteka
👉  አላህን ትፈራለህ ወይ ከተባልክ መልስ አትስጥ !

‏قال الفضيل بن عياض – رحمه اللّه –:

" إذا قيل لك هل تخاف اللّه ؟

فاسكت ، فإنّك إن قلت نعم كذبت وإن قلت لا كفرت ! "

           تزكية النفوس ص ( 117 )

      🔹   ፉደይል ኢብኑ ዒያድ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –

" አላህን ትፈራለህ ወይ ከተባልክ ዝም በል ። ( ምክንያቱም )  አው ካልክ ዋሽተሀል ። አይ ካልክ ደግሞ ከፍረሀል ። "

https://t.me/bahruteka
👉  አል ሐሰኑል በስሪ - ረሒመሁላሁ -
  ከታቢዒን ዑለማዎች አንዱ

ንግግሩ የነብያቶች ንግግር ይመስላል ተብሎ የተመሰከረለት ፣ እውቀትን ጠጥቶ በጥበብ የተናገረ ፣ ዛሂድ ፣ ፈቂህ ፣ ለዒባዳ የታጠቀ ለዱንያና ለጌጧ ጀርባውን የሰጠ ነበር ።
ኢማሙ ዘሀብይ ስለሱ ሲናገር እንዲህ ይላል :- በእውቀት መሪ ነበር ሙጅተሂድ
በጣም አንባቢ ፣ በቁርኣንና በተፍሲሩ መሪ የነበር ፣ በግሳፄና በምክርም የሚደርሰው አልነበረም ። በዒባዳና በትእግስት ቁንጮ ላይ የተቀመጠ ነበር ። በዙህድና በእውነተኝነት ቀዳሚ ሲሆን በንግግር ጥልቀት አቻ ያለው አይመስልም ነበር ። በጀግንነትም ግንባር ቀደም ነበር ።
ስሙ - አል ሐሰን ኢብኑ አቢል ሐሰን
ኩንያው  - አቡ ሰዒድ ሲሆን ለዑመር ኢብኑል ኸጣብ - ረዲየላሁ ዐንሁ - ኺላፋነት ሁለት አመት ሲቀረው ነበር የተወለደው ።

🔹 የሰለፍ ዑለሞች ስለሱ ከተናገሩት : –

አል አዋም ኢብኑ ሑሸብ የተባለ ዐሊም የአላህ መልእክተኛን ይመስል ነበር ይላል ።
አቡ ቡርዳህ የተባለ ዓሊም ደግሞ የነብዩ ሶሐባዎችን የሚመስል እንደርሱ አይነት አላየሁም ብሏል ።
አነስ ኢብኑ ማሊክ አል ሐሰንን ጠይቁ እኛ ረስተናል እሱ ሐፍዧል ይል ነበር ።
ቀታዳህ የማንም ሰው እውቀት ከሱ እውቀት አላገናኘሁትም ለእውቀቱ ብልጫ ባገኝለት እንጂ ይል ነበር ። ቁርኣን ሲቀራ እንባው በፂሙ ላይ እስከሚፈስ ያለቅስ ነበር ።
ጃቢር ኢብኑ ዘይድ እንዲህ ይላል :-
አል ሐሰን ሲመጣ ስለ አኼራ በዐይኑ ያየውን የሚናገር ሰው የመጣ ይመስል ነበር ይላል ።
በክር ኢብኑ ዐብዲላህ አልሙዘኒ ካየናቸው ሁሉ አዋቂ የሆነ ሰው ማየት የፈለገ ወደ አልሐሰን ይይ ይል ነበር ።
በሐጃጅ ኢብኑ ዩሱፍ ላይ ኢብኑል አሽዐስ በወጣ ጊዜ ከፉቀሃዎች ውስጥ የተወሰኑት ተሰብስበው ወደርሱ መጥተው አንተ አቡ ሰዒድ ሆይ ይህን ወሰን አላፊ በመጋደል ላይ ምን ትላለህ ?
ክልክል የሆነን ደም የሚያፈስ ፣ ክልክል የሆነን ንብረት የሚዘርፍ ፣ ሶላት የተወ  ------- ወዘተ ብለው የሚሰራውን ወንጀል ዘረዘሩ ።
እሱም እንዲህ አላቸው :-
አትጋደሉት ምክንያቱም ከአላህ የሆነ ቅጣት ከሆነ የአላህን ቅጣት በሰይፋችሁ አትመልሱትም ። በላእ ከሆነ ታገሱ አላህ እስከ ሚፈርድ እሱ መልካም ፈራጅ ነውና ! ከዛም
እንዲህ እያሉ ወጡ : – ይህን ጠማማ አንታዘዝም ። ከተዋጊዎች ጋር ወጡ ሁሉም ተገደሉ ። ከዛም እንዲህ አለ :– ሰዎች በመሪዎቻቸው ሲፈተኑ ቢታገሱ ኖሮ ፈረጀት ሳይመጣላቸው አይቆዩም ነበር ።
ነገር ግን ወደ ሰይፋቸው ይዞራሉ ወደ ሰይፋቸውም ይተዋሉ ( ይወከላሉ ) ምንም መልካም ነገር ይዘው አይመጡም ።
ሂሻም ኢብኑ ሐሳን አልሐሰን እንዲህ ብሎ ሲምል ሰምቼዋለሁ ይላል :–
አንድም ሰው ዲርሀምን አላላቀም አላህ ቢያዋርደው እንጂ ።
ዙረይክ ኢብኑ አቢ ዙረይክ አልሐሰን እንዲህ ሲል ሰምቼዋለሁ ይላል :–
ይህ ፈተና ሲመጣ ዓሊሞች ያውቁታል ከሄደ በኀላ ግን ሁሉም ጃሂል ያውቀዋል ።
በ88 አመቱ በ110ኛው አመተ ሂጅሪያ ወደ አኼራ የሄደ ከሰለፍ ዑለሞች አንዱ ነበር ። ራሕመቱላሂ ዓለይሂ ራሕመተን ዋሲዐን !።

http://t.me/bahruteka