Forwarded from Kelemat Ads
📚 አጠቃላይ የፋይናንስ እና የግብር Online ስልጠና!
🖥 ለመመዝገብ:
1️⃣ ወደ ድህረ-ገፃችን ይግቡ
👉 https://www.apextaxschool.com
2️⃣ “Join Now” የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ
3️⃣ ሙሉ ስምዎን ኢሜልዎን እና Password ፈጥረው ያስገቡ
4️⃣ የሚፈልጉትን የስልጠና ክፍል ይምረጡ
5️⃣ “Enroll Now” በመጫን ከዝያም “Buy Now” በማለት ክፍያዎን ፈፅመው ምዝገባዎትን ያጠናቁ
በ0995958351 በመደወል መመዝገብም ይችላሉ።
📍 አድራሻ: ሃያ ሁለት፣ በየነ ጠበሉ ህንፃ፣ 1ኛ ፎቅ
📞 0995 958 351
#ApexFinancialSolution
#Onlinetraining

❤2
የ2005 ዓ.ም. የ20/80 እና የ40/60 የቤት ተመዝጋቢዎች ያሉባቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንዲፈቱ መጠየቅን ይመለከታል።
በመጀመሪያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነዋሪውን የቤት ባለቤት ለማድረግና የከተማዋን ገጽታ ለመቀየር እያከናወነ ያለውን ሰፊ የልማት ስራዎች እናደንቃለን። በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለቤት ተመዝጋቢዎች ተስፋ የሚሰጡ እንቅስቃሴዎች በመጀመራቸው ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ይሁን እንጂ እኛ የ2005 ዓ.ም. የ20/80 እና የ40/60 የቤት ተመዝጋቢዎች ምዝገባ ካካሄድን ከ13 ዓመታት በላይ አስቆጥረናል። በዚህ ረጅም የጥበቃ ጊዜ ውስጥ ተመዝጋቢው የደረሰበትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች የከተማ አስተዳደሩ ብለን እናምናለን ለምሳሌም
የኑሮ ውድነትና የመኖሪያ ቤት አለመረጋጋት፦ ለረጅም ዓመታት በቤት ኪራይ ውድነት ምክንያት ቤተሰቦቻችን ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገዋል። ተመዝጋቢው ካለው አነስተኛ ገቢ ላይ ለቤት ቁጠባና ለቤት ኪራይ በየወሩ የሚከፍለው ክፍያ ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተዳምሮ ህይወታችንን የተረጋጋ እንዳይሆን አድርጎታል።
የቅድሚያ ተጠቃሚነት ጥያቄ፦ ባለፉት ዓመታት የተገነቡ ቤቶች ለተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች (ለልማት ተነሺዎች፣ ለአቅመ ደካሞችና ለሌሎችም አካላት) ቅድሚያ ተሰጥቶ ሲከፋፈሉ ቆይተዋል። እኛ ተመዝጋቢዎች እንደ ሀገርና እንደ ከተማ የሚነሱ ችግሮችን በመረዳትና ለሰብአዊነት ቅድሚያ በመስጠት በትዕግስት ስንጠባበቅ ቆይተናል። ይሁን እንጂ አሁን ላይ የተመዝጋቢው የመታገስ አቅም ከመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሷል።
ፍትሃዊ ተጠቃሚነት፦ ቤት ለሰው ልጅ መሰረታዊ ፍላጎት መሆኑ እየታወቀ፣ ዓመታትን በቁጠባና በተስፋ ለጠበቀው ተመዝጋቢ ትኩረት ሳይሰጥ ሌሎች አካላት በተለያዩ ምክንያቶች ቅድሚያ ሲያገኙ ማየት በተመዝጋቢው ዘንድ ከፍተኛ የቅሬታ ስሜት ፈጥሯል።
ስለሆነም አስተዳደሩ የሚከተሉትን የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንዲመለከትልን በአክብሮት እንጠይቃለን፦
ለተመዝጋቢው ቅድሚያ መስጠት፦ አሁን ላይ የተገነቡና በመጠናቀቅ ላይ ያሉ ቤቶች ያለ ምንም ተጨማሪ ማዘግየት ለቆጣቢው ህዝብ በፍትሃዊነት እንዲከፋፈሉ፤
ግልጽነት ያለው አሰራር፦ በቀጣይ የሚከናወኑ የቤት እጣዎችና ስርጭቶች የ2005 ተመዝጋቢ ታሳቢ ያደረጉና ግልጽነት የተሞላባቸው እንዲሆኑ፤
እኛ ተመዝጋቢዎች መንግስት የጀመረውን የልማት ስራ እየደገፍን፣ ለጥያቄዎቻችንም አፋጣኝና ፍትሃዊ ምላሽ እንደምናገኝ ሙሉ እምነት አለን።
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር!
የ2005 ዓ.ም. የቤት ተመዝጋቢዎች ተወካዮች

❤17
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
😭3
የመሬት ሊዝ ጨረታ ተራዘመ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 8ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለተጨማሪ 10 ቀናት መራዘሙን የጨረታ ኮሚቴ አሳውቋል፡፡
220 ፕሎቶች በዘጠኝ ክፍለ ከተሞች በተሰናዱበት በዚህ ጨረታ የኦንላይን ሰነድ ሽያጩ ከታህሳስ 25/2018 እስከ ጥር 12/2018 ዓ.ም በተመቻቸው የተቋሙ ድረ-ገፅ ሲሸጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ሆኖም በተለያየ ምክንያት የጨረታ ሰነድ ላልገዙ አካላት ተጨማሪ እድል ለመስጠትና የተሳታፊዎችን ቁጥር ለማሳደግ እንዲያግዝ በደንብ ቁጥር 162/2016 አንቀፅ 20 በተደነገገው መሰረት የሰነድ ሽያጩን ከጥር 13/2018 ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት እንዲራዘም ተደርጓል፡፡
ስለሆነም ፍፁም ፍትሐዊና ግልፅ በሆነው የከተማችን የመሬት ሊዝ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ አካላት የጨረታ ሰነዱን ከጥር 13/2018 እስከ ጥር 26/2018 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ የቴሌ ብር አካውንታችሁን ተጠቅማችሁ ሰነዱን ከተቋሙ ድረ-ገፅ (landlessdocument.aalb.gov.et) በመገዛት እንድትወዳደሩ ቢሮው በድጋሚ ጥሪ እያቀረበ የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ ጥር 26/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 መሆኑን እንገፃለን፡፡
በተጨማሪም ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በወጣው አዲስ ልሣን ጋዜጣ ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የጨረታ ቁጥር አ/ቃ/ክ/ከ/27/18 የቦታ ኮድ LDR-AKI-MIX-00014927 የቦታ ስፋት 992 ካሜ ተብሎ የተጠቀሰው 233 ካ.ሜ በሚል የተስተካከለ ሲሆን በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ለሚኩራ፣ልደታ እና ኮልፌ ቀራኒዬ ክ/ከተማ በድምሩ 82 ቦታዎች ከጨረታ ተሰርዘዋል ።
የተሰረዙ ቦታዎችን ኮድና ዝርዝር መረጃ ነገ ጥር 09/2018 ታትሞ በሚወጣው አዲስ ልሳን ጋዜጣ ላይ ይመልከቱ።