የዳንሴ ቅ/አ/ አ/መ/ደ/ ትምህርት ቤት/Danse preprimery,primery and middle school
94 subscribers
195 photos
2 videos
233 files
26 links
Education for all
Download Telegram
Forwarded from Negese Bekele
👏👏👏👏የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ከዳንሴ ትምህርት ቤት 👏👏👏

​ውድ እና የተከበራችሁ ✅የዳንሴ✅ ትምህርት ቤት ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን እና መላው የትምህርት ቤታችን ሰራተኞች፤
​በመጀመሪያ መላው የእስልምና እምነት ተከታይ ለሆናችሁ የትምህርት ቤታችን ማህበረሰብ አባላት እና ለሕዝበ ሙስሊሙ በሙሉ፣ የዳንሴ ትምህርት ቤቱ የተሰማውን ታላቅ ደስታ እየገለጸ ✅"ለ1447ኛው ✅የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!" ለማለት ይወዳል።
​የኢድ አል አድሀ በዓል ታላቅ መስዋዕትነትን፣ ታማኝነትን፣ አብሮነትን እና ለፈጣሪ ሙሉ በሙሉ መታዘዝን የምንማርበት ታሪካዊ በዓል ነው። ይህ ✅እለት እርስ በርስ በመተሳሰብ፣ ✅የተቸገሩትን በመርዳት እና ፍቅርን በመጋራት የሚከበር በመሆኑ፣ እኛም በትምህርት ቤታችን ውስጥ ለምናሳድጋቸው ልጆቻችን ልናስተላልፍላቸው የሚገባውን ታላቅ የደግነት እና የሞራል እሴት የሚያስታውሰን ነው።
​በትምህርት ቤታችን « ዳንሴ» ውስጥ የምንገነባው አካዳሚያዊ ጥንካሬን ብቻ ሳይሆን፣ ተማሪዎቻችን በባህላቸው እና በሃይማኖታዊ እሴቶቻቸው ኮርተው፣ ሌሎችን አክብረው እና ተከባብረው የሚኖሩበትን መልካም ሰብዕና ጭምር ነው። ይህ በዓል ልጆቻችን የጋራ መረዳዳትንና ትጋትን እንዲለማመዱ መልካም አጋጣሚ እንደሚሆን አንጠራጠርም።
​በመጨረሻም፣ ይህ የ1447ኛው የኢድ በዓል፦
​ለሀገራችንና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሰላም እና የፍቅር፣
​ለቤተሰባችሁ የጤና፣ የበረከት እና የደስታ፣
​ለልጆቻችን ደግሞ የትጋትና የስኬት እንዲሆንላቸው ከልብ እንመኛለን።
​ኢድ ሙባረክ! መልካም የኢድ አል አድሀ በዓል!

✅​የዳንሴ ት/ ቤት✅

✅​Kabajamtoota fi Jaallatamtoota Maatii, Barattoota, Barsiistota fi Hojjattoota Mana Barnootaa Daanse Maraaf;

​Ji’a kabajamaa fi qulqulluu kan ta’e, ayyaana dhiifamaa fi deeggarsaa kan ta’e ayyaana iid-Al-Adhaa (Arafa) 1447ffaa ilaalchisee, hordoftoota amantaa Islaamaa mana barnootaa keenyaa fi hawaasa Muslimaa maraaf gammachuu guddaan "Baga Ayyaana iid-Al-Adhaa (Arafa) 1447ffaan Isiin Gahe!" jechuun barbaada.
​Ayyaanni iid-Al-Adhaa ayyaana aarsaa, amanamummaa, tokkummaa fi uumaaf ajajamuufi. Akkasumas, ayyaanni kun wal gargaaruun, harka qalleeyyiif kenuun fi jaalala waliif qooduun kan kabajamu yoo ta’u, kunis ijoollee keenya boru addunyaa kana jijjiiran biratti miira gara laafinaa fi namoomasaa uumuuf iddoo guddaa qaba.
​Nuti Mana Barnootaa keenya keessatti, barattoonni keenya gama barnootaan qofa utuu hin taane, aadaa fi amantaa isaanii kabajanii, safeeffatanii fi waliif kabaja kennanii akka guddatan gochuuf hojjenna. Ayyaanni kunis ijoolleen keenya waliif yaaduu fi hawaasummaa akka baratan carraa gaarii akka uumu hin shakkamu.
​Xumura irratti, Ayyaanni iid-Al-Adhaa 1447ffaan kun:
​Biyya keenya fi addunyaa maraaf ayyana nageeyyaa fi jaalalaa,
​Maatii keessaniif ayyaana fayyaa, eebbaa fi gammachuu,
​Barattoota keenyaaf immoo ayyaana carraaqqii fi milkaa’inaa akka ta’u hawwina.
​iid Mubaarak! Ayyaana iid-Al-Adhaa Gaarii Ha Ta'u!

✅​M/Barumsaa Daansee✅
Forwarded from Negese Bekele
✅Haa dubbifamu
✅ይነበብ
✔️ለ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተፈተኞች የትምህርት አይነትና ኮድ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
⭐️በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!✅
========================
⭐️ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው::

⭐️ከፈተና በፊት ይህን አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምንችለበት መንገድ:-
------------------------------------------------
✅ ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።

✅ ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡

✅ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ። 

✅ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል እንደሚቻል ማመን።

✅ ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።

✅ የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ  መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል። 
ሰላም እንዴት ናችሁ
👉አስቸኳይ !
ለዳንሴ  መምህራን በሙሉ 
የ1ኛ ሰሚስተር ውጤት ያልገባላቸው ተማሪዎች ስለ ተገኙ እስከ ሐሙስ E_school ላይ እንድትታስገቡ   እናሳስባለን።
                   ት/ቤቱ
Akkam jirtu?
Ariifachiisaa!
Barsiisota hundaaf
Qabxiin sem.1ffaa barattootni hin galleef waan jiraniif hanga kamisaatti akka galchitan beeksifna
Forwarded from Negese Bekele
📚 የተፈታኞች መብትና ግዴታ ✅

📚 ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብና ሥርዓት  አከባበር እንዲሁም የመልስ ወረቀት አጠቋቆርና   ተዛማጅ ሁኔታዎችን አስመልክቶ በሚሰጡ ገለፃዎች ላይ የመሣተፍ ግዴታ አለበት።

📚 ተፈታኙ በገለፃው ላይ ባለመሳተፉ ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለሚያጋጥመው ችግር ኃላፊነቱን ይወስዳል።

📚 ተፈታኙ/ኟ የሰራበትን የመልስ ወረቀት ለፈታኙ በመስጠት  የጥያቄ ወረቀቱን ይዞ መውጣት ይችላል

📚 ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ጥያቄዎቹን መስራት ከመጀመሩ በፊት በፈተና የመልስ መስጫ ወረቀት ላይ የግል መለያ መረጃዎችን በሙሉ ግልፅ በሆነ ሁኔታ በቅደም ተከተል ጽፎ ማጥቆር ይኖርበታል (በተለይ የመለያ ቁጥር እና የትምህርት አይነት ኮድ)።

📚 ማንኛውም ተፈታኝ የራሱን ችሎታና ዕውቀት ተጠቅሞ መስራት ይጠበቅበታል፡፡

📚 የሚሠራባቸው የጥያቄና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ለሌሎች ተፈታኞች ዕይታ የተጋለጡ እንዳይሆኑ ሸፍኖ መስራት ይኖርበታል

📚 ማንኛውም ተፈታኝ ሞባይል፣ ካልኩሌተርና የመሳሰሉ ማንኛውንም ዓይነት  የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ይዞ ወደ ፈተና ክፍል መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው ።

📚 እያንዳንዱ ተፈታኝ ይህንን አውቆ በቅድሚያ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ።

📚 ይህንን ባለማድረጉ ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለሚያጋጥመው ችግር ተፈታኙ  ራሱ ኃላፊነቱን ይወስዳል።

📚 ማንኛውም ተፈታኝ በመፈተን ላይ እያለ ፈተናውን እንዳይሠራ የሚያውኩ ሁኔታዎች ቢያጋጥመው በፈታኙ ሲፈቀደለት ችግሩን በመግለጽ አስፈላጊውን እርዳታ ማግኘት ይችላል ይሁንና በማንኛውም ምክንያት ለባከነ ጊዜ ተጨማሪ ሰዓት አይፈቀድም

📚 ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከሚጀመርበት ጊዜ ተኩል ሰዓት /30 ደቂቃ/ ቀደም ብለው ከመፈታኛው ቦታ በመገኘት መቀመጫቸውን መያዝ አለባቸው።

📚 ፈተናው ከተጀመረ ከ15 ደቂቃ በኋላ የሚመጣ ተፈታኝ ወደ ፈተናው አዳራሽ መግባት አይፈቀድለትም።

📚 ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ፈተናውን ሠርቶ ቢያጠናቅቅም እንዲወጣ አይፈቀድለትም።

📚 ይሁን እንጂ ፈተናው ከተጀመረ ከ45 ደቂቃ በኋላ ከፈተና አዳራሹ ለመውጣት   እንዲፈቀድለት ሲጠይቅ የመልስ ወረቀቱን ለፈታኙ አስረክቦ በጸጥታ እንዲወጣ ይፈቀድለታል።

📚 ፈተናው ሊጠናቀቅ ከ10 ደቂቃ ያነሰ ጊዜ ሲቀረው የሚጨርስ ተፈታኝ የሁሉም ተፈታኞች የመልስ ወረቀቶች እስኪሰበሰቡና ለፈተናው የተፈቀደው የጊዜ ገደብ አብቅቶ እስኪደወል ድረስ በቦታው ተቀምጦ እንዲቆይ ይደረጋል።

📚 ፈተናው በሚሰጥበት ጊዜ ማንኛውም ተፈታኝ ትክክለኛ ያልሆነ የተቀደደ ወይም የተበላሸ የፈተና ጥያቄ ጥራዝ ከገጠመው ወይም የተሰጠው የመልስ ወረቀት የተበላሸ ከሆነ ወይም በራሱ እጅ ቢበላሽበት እጁን አንስቶ በመጠየቅ ሲፈቀድለት ሊያስቀይር ይችላል።

ለተፈታኞች የተፈቀዱ

✅ እርሳስ
✅ የተማሪዎች የደንብ ልብስ (UNIFORM)
✅ ADMISSION CARD
✅ ላጲስ፣ መቅረጫና ማስመሪያ

ለተፈታኞች የተከለከሉ

❌ ስልክ ይዞ መግባት አይቻልም
❌ ካልኩሌተር
❌ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን
❌ ሰዓት
❌ በሀኪም ከታዘዘ ውጪ የሆኑ መነጽሮች
❌ የሚነበቡ ጽሁፎች በሙሉ

#ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ
√ 6ኛ ክፍል ከሰኔ 8- 10 /2018 ዓ/ም
√ 8ኛ ክፍል ሰኔ 11 እና 12/2018 ዓ/ም ይሆናል።
Forwarded from Mebrat Teklu
ቀን 07/10/2018
ለመምህራን
የሰኞ የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም ላይ በተለመደው ሰአት ሳታረፍዱ ትምህርት ቤት እንድትገኙ እናሳስባለን ።
Forwarded from Negese Bekele
✅ራዕይ/Vision
2022 ውጤታማ የመማር ማስተማር ስርአት በማስፈን በእውቀት፣ ክህሎትና ስነምግባር የታነጸ፤ አለማቀፍ ተወዳዳሪ እና የነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ ማፍራት፡፡
✅ተልዕኮ/Mission
የትምህርት ቤቱን ማህበረሰብ እና የአካባቢ ነዋሪ በትምህርት ስራ ላይ በባለቤትነት በማሳተፍ ጥራት ያለውና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት ለአካባቢው ማህበረሰብ ማዳረስ፡፡
✅እሴት/Values
ለትምህርት ጥራት ቅድሚያ እንሰጣለን፤
መልካም ስነ-ምግባር የዜጎቻችን መለያ ነው፤
ጥናትና ምርምር የችግሮቻችን መፍቻ ነው፤
በእውቀትና በእምነት እንመራለን/እንሰራለን፤
በግልጽነት እናገለግላለን፤
የተጠያቂነት ስርዓትን እናሰፍናለን፤
ለለውጥ ዝግጁ ነን፤
የላቀ አገልግሎት እንሰጣለን፤
በጋራ መስራት መገለጫችን ነው፡፡
✔️የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተና በሰላም ተጠናቋል!!
Qormaati kutaa 6ffaafi 8ffaa nagaan xumurameera!!
👏👏👏👏👏👏
Forwarded from Negese Bekele
ለ ዳንሴ መምህራንና ሰራተኞች በሙሉ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተና 
በሰላም እንድጠናቀቅ ለተባበራችሁን አካለትና በሂደቱ ለተሳተፋቹህ
✅የክ/ከተማና የወረዳ የት/ት አመራሮች
✅የፈተና ጣቢያ ሀላፊዎች
✅ ሱፐርቫየዘሮችና ር/መምህራን
✅  መምህራን
✅የፖሊስ አካላትና
✅ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሙሉ በት/ቤቱ ስም ከልብ እያመሰገን ደግም ጥሩ ውጤት እንደምናመጣ ተስፈ እናደርጋለን!!!!!!

📌 ከልብ እናመሰግናለን
👏👏👏👏👏👏
ቀን፡ 16/10/2018
ማስታወቂያ
ለሁሉም መምህራን
መምህራን የተማሪዎችን መረጃ በ“E-school” ላይ አስገብታችሁ ካጸዳችሁ በኋላ፣ እስከ ቀን 20/10/2018 ድረስ ለቢሮው እንድታቀርቡ በጥብቅ እናሳውቃለን።
                        Guyyaa: 16/10/2018
Beeksisa
Barsiisota hundaaf
Barsiisotni ragaa barattootaa  “E-school” keessatti galchuu fi sirreessuu erga xumurtanii booda, hanga gaafa 20/10/2018tti waajjiraatti akka galchitan ciminaan ni beeksifna.
Forwarded from Negese Bekele
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
✨✨ዳንሴ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት⚡️⚡️⚡️
     22/10/2018 ዓ.ም

ለውድ የዳንሴ ትምህርት ቤት
👉መምህራን
👉ተማሪዎች
👉ወላጆችና
👉የትምህርት ቤቱ ማህብረሠቦች
የስምንተኛኛ ክፍል ሚንስትር ካስፈተናቸው

👉 34 ወንድ
👉  60 ሴት
👉 በድምሩ 94 ተማሪዎች መካከል
🙌 94 ተማሪዎችን🙌. ማለትም
🏆 34 ወንድ
🏆 ሴት 60 ተማሪዎች
               100% ተማሪዎችን
50 % እና ከዛ በላይ በማስመዝገብ
ወደ ቀጣይ (9) ክፍል ማሳለፋችንን ስንገልጽ በደስታ ነው።
✨✨❤️ ❤️❤️❤️🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
🏆ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ያላሰለሰ ጥረትና መሥዋዕት ለከፈላችሁ
👉የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች
👉መምህራን
👉ርዕሰ መምህር እና ምክትል ርዕሳነ መምህራን
👉የአስተዳደር ሰራተኞች
👉 የተማሪ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች
👉የወረዳ ት/ት ጽ/ቤት ባለሙያዎች

          እንኳን ደስ ያላችሁ!!
             እንኳን ደስ አለን!
ውድ ተማሪዎች፣ መምህራንና የት/ቤቱ ማህበረሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ
እንኳን ደስ አለን!!🙌🙌🙌🙌
👍1
ቀን: 23/10/2018
ማስታወቂያ
ለሁሉም መምህራን
የ1ኛ እና 2ኛ ሴሚስተር የተማሪዎች ውጤት በE-School ሥርዓት ላይ በመሙላት ላይ ይገኛል። ሆኖም ግን፣ ቀደም ሲል የተሞላው የ1ኛ ሴሚስተር ውጤት አሁን ካለው መረጃ ጋር ልዩነት ስላለው፣
ስለዚህ ሁሉም መምህራን ውጤታቸውን በድጋሚ በጥንቃቄ እንዲያረጋግጡ፣ ስህተት ካገኙም እስከ 24/10/2018 ድረስ እንዲስተካከል በአክብሮት እናሳስባለን።
እናመሰግናለን።
✔️የትምህርት እድል

(ለ8ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች)

✅ለቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት

✅ከት/ቤታቹህ መስፈርቱን የሚያሟሉ 1 ወንድ እና 1ሴት ተማሪ በቅጹ መሰረት አስከ ነገ አርብ 10:00 ድረስ ብቻ በሶፍት