ቀን 06/01/2019 ዓ.ም
ማስታወቅያ
ለመምህራን በሙሉ
በተማሪዎች ዩኒፎርም እና ደብተር ስርጭት ጋር በተያያዘ የክፍለ ግዜ ብክነት እና የተማሪዎች በግቢ ዉስጥ አላስፈላጊ እንቅስቃሴ እየተስተዋለ ይገኛል ፡፡ ስለሆነም ከ07/01/2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚደረገዉ የደብተር እና ዩኒፎርም ስርጭት በስም ጠሪ መምህራን አማካኝነት ስም ጠሪ መምህራን በሚኖራቸዉ ክፍለ ግዜ ብቻ ስለሆነ ሁሉም መምህራን በወጣላችሁ ክፍለ ግዜ ክፍል ዉስጥ በመገኘት የማስተምር ሂደት እንድታስተካክሉ በጥብቅ እናሳዉቃለን ፡፡

Forwarded from Negese Bekele
የአሳታፊና ተማሪ ተኮር የማስተማር ስነ-ዘዴዎች ለአንደኛ ደረጃ 1–8ኛ ክፍል መምህራን አጭር መመሪያ መግቢያ የተማሪ ተኮር ማስተማር ማለት መምህሩ ብቻ የሚናገርበት ሳይሆን ተማሪዎች የሚያስቡበት፣ የሚጠይቁበት፣ የሚወያዩበት፣ የሚሞክሩበት፣ የሚተገብሩበትና የራሳቸውን ግንዛቤ የሚገነቡበት የማስተማር ሂደት ነው። ዋና ዓላማው፦ - የተማሪዎችን ተሳትፎ ማሳደግ፣ - ማሰብና ችግር መፍታትን ማዳበር፣ - ትምህርትን ከተግባር ጋር ማያያዝ፣ - የመግባባትና የቡድን ሥራ ክህሎትን ማዳበር፣ - ተማሪውን የመማር ንቁ ተሳታፊ ማድረግ ነው። የተለመዱና ዋና ዋና የአሳታፊ/ተማሪ ተኮር ስነ-ዘዴ ዓይነቶች ስነ-ዘዴ፣ አጭር የአተገባበር ሂደት፣ በተለይ የሚስማማበት ትምህርት/ይዘት እንደሚከተለው ባጭሩ ቀርቧል። 1. የጥያቄና መልስ ዘዴ -መምህሩ ለማሰብ የሚያነሳሳ ጥያቄ ያቀርባል፣ ተማሪዎች ያስባሉ + መልስ ይሰጣሉ፣ መምህሩ ያብራራል/ያስተካክላል። *ለሁሉም ትምህርቶች፤ በተለይ ቋንቋ፣ ሳይንስ፣ ማህበራዊ ሳይንስ ተመራጭ ነው 2. የቡድን ውይይት/የቡድን ስራ ዘዴ -ተማሪዎችን በቡድን መከፋፈል፣ ርዕስ/ጥያቄ/ተግባር መስጠት፣ የቡድን ውይይት/ሥራ ማከናወን፣ ውጤት ማቅረብ፣ ግብረመልስ፣ የጋራ ድምዳሜ ላይ መድረስና ማጠቃለል፣ *ለሁሉም ዓይነት ትምህርት፤ በተለይ ፕሮጀክት፣ ሳይንስ፣ ቋንቋ ተመራጭ ነው። 3. Think–Pair–Share -ተማሪው በግል ያስባል፣ አጠገቡ ካለው ጓደኛው ጋር ይወያያል ከዛ ለክፍሉ ያካፍላል። *ለቋንቋ፣ ሳይንስ፣ ማህበራዊ ሳይንስና ሂሳብ ተመራጭ ነው። 4. ችግር መሰረት ያደረገ ትምህርት (Problem Based Learning) -እውነተኛ ችግር ማቅረብ፣ ችግሩን መለየት፣ መረጃ መፈለግ፣ መፍትሔ ማቅረብ፣ መፍትሔውን መገምገም። *ለሳይንስ፣ ሂሳብ፣ ማህበራዊ ሳይንስ፣ አካባቢና አጠቃላይ ሳይንስ ተመራጭ ነው። 5. ፕሮጀክት ተኮር ትምህርት -ርዕስ መምረጥ፣ ዕቅድ ማዘጋጀት፣ መረጃ መሰብሰብ፣ ውጤት/ግኝት/ሪፖርት ማዘጋጀትና ማቅረብ። *ለሳይንስ፣ ሶሻል ስተዲ፣ ቋንቋ፣ አካባቢና አጠቃላይ ሳይንስ ተመራጭ ነው። 6. ማሳያ/ሙከራ (Demonstration) -መምህሩ ወይም ተማሪው ያሳያል፣ ተማሪዎች ይመለከታሉ፣ ይጠይቃሉ፣ እራሳቸው ይሞክራሉ። *ለሳይንስ፣ ሂሳብ፣ ሙያ/ተግባራዊ ይዘቶች ተመራጭ ነው። 7. የሚና ጨዋታ (Role Play) -ሁኔታ መፍጠር፣ ሚና መመደብ፣ ተማሪዎች ሚናቸውን መጫወት፣ ውይይትና ግምገማ። *ለቋንቋ፣ ግብረገብ/ዜግነት፣ ሶሻል ስተዲ ተመራጭ ነው። 8. የጨዋታ ተኮር ትምህርት -የትምህርቱን ዓላማ ከጨዋታ ጋር ማያያዝ፣ ሕግ/መመሪያ ማስረዳት፣ ጨዋታ ከትምህርቱ ጋር ማገናኘት። *ከ1–4ኛ ክፍል በተለይ ለሂሳብ፣ ቋንቋ፣ ክወናና እይታ፣ ግብረገብ፣ አካባቢ ሳይንስ ተመራጭ ነው።
9. Brainstorming (የሀሳብ ማዕበል)| -ጥያቄ/ችግር ማቅረብ፣ ተማሪዎች ሀሳብ መስጠት፣ ሀሳቦችን መመዝገብ፣ መደራጀት፣ መገምገም። *ለሁሉም ትምህርቶች በተለይ ቋንቋ፣ ሶሻል ስተዲ፣ አካባቢና አጠቃላይ ሳይንስ ተመራጭ ነው። 10. ጉዳይ ጥናት (Case Study) -እውነተኛ/ምሳሌያዊ ጉዳይ ማቅረብ፣ መረጃ መተንተን፣ አማራጮችን መወያየት፣ ውሳኔ ማቅረብ። *ለሶሻል ስተዲ፣ ዜግነትና ግብረገብ ተመራጭ ነው። 11. Inquiry-Based Learning -ጥያቄ ማንሳት፣ መገመት፣ መረጃ/ማስረጃ መፈለግ፣ መተንተን፣ መደምደም። *ለሳይንስ፣ ሂሳብ፣ ሶሻል ስተዲ ተመራጭ ነው። 12. Peer Teaching/ተማሪዎች አንዱ ለአንዱ ማስተማር/ -ጥያቄ/መልስ ከዛ መምህሩ ማረጋገጥና ማስተካከል። *ለሂሳብ፣ ቋንቋ፣ ሳይንስ ተመራጭ ነው። 13. Flipped Learning -ተማሪው ከክፍል ውጭ መሠረታዊ ይዘት ይመለከታል/ያነባል፣ በክፍል ውስጥ ችግር መፍታትና ተግባር። -በተለይ ከ5–8ኛ ክፍል ለሳይንስ፣ ሂሳብ፣ ቋንቋ ተመራጭ ነው። የስነ-ዘዴ ምርጫ መርሆዎች መምህሩ “ይህ ዘዴ ጥሩ ነው” ብሎ ብቻ መምረጥ የለበትም። የሚመርጠው የስነዘዴ ዓይነት ከሚከተሉት ጋር መጣጣም መቻል አለበት፦ 1. የትምህርቱ ዓላማ ተማሪው በመጨረሻ ምን ማወቅ፣ ምን መረዳት ወይም ምን ማድረግ አለበት? 2. የይዘቱ ባህሪ ይዘቱ እውቀት (cognitive) ነው? ክህሎት (psychomotor)? ስሜት (affective)? ችግር መፍታት (problem solving)? አመለካከት (attitude)? ተግባር (task)? 3. የተማሪዎች ዕድሜና የመማር ደረጃ 1ኛ ክፍል ተማሪና 8ኛ ክፍል ተማሪ በተመሳሳይ መንገድ አይማሩም። 4. የክፍሉ መጠን ብዙ ተማሪዎች ካሉ የቡድን ሥራና Think–Pair–Share ከግለሰብ ውይይት የበለጠ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል። 5. የሚገኙ መርጃዎች መጽሐፍ፣ ምስል፣ የሙከራ ቁሳቁስ፣ ቴክኖሎጂ፣ የአካባቢ ቁሳቁስ ወዘተ። በአንድ ትምህርት ውስጥ ከአንድ በላይ ዘዴ መጠቀም አንድ መምህር በአንድ ክፍለ-ጊዜ አንድ ዘዴ ብቻ መጠቀም ግዴታ የለበትም። ብዙ ጊዜ የተሻለው ውጤታማ አቀራረብ የሚባለው የተለያዩ ዘዴዎችን በተገቢው መንገድ በማቀናጀት መጠቀም መቻል ነው። ምሳሌ — የሳይንስ ትምህርት 1. Brainstorming — “ተክሎች ለምን ያስፈልጉናል?” 2. Inquiry — ተማሪዎች ጥያቄ ያነሳሉ። 3. Group Work — በቡድን መረጃ ይሰበስባሉ። 4. Demonstration/Experiment — የተግባር ሙከራ ያደርጋሉ። 5. Discussion — ውጤታቸውን ይወያያሉ። 6. Assessment — መምህሩ ግንዛቤያቸውን ይመዝናል። የተማሪ ተኮር ትምህርት አጠቃላይ ሂደት የመማር ዓላማ፣ ቅድመ እውቀት፣ ጥያቄ/ችግር፣ የተማሪ ተሳትፎ፣ ትብብር/ምርመራ፣ ማቅረብ፣ ግብረመልስ፣ ግምገማ፣ ፅብረቃ። ይህ ሂደት መምህሩን ከ“ዋና ተናጋሪ” ወደ “የመማር አመቻች (Facilitator)” ያሸጋግረዋል። በአሳታፊ ስነዘዴ አተገባበር ሂደት የመምህሩ ሚና በተማሪ ተኮር ማስተማር ሂደት የመምህሩ ሥራ አይቀንስም፤ በእርግጥ የበለጠ የተዘጋጀ መሆንን ይጠይቃል። መምህሩ፦ - የመማር ዓላማን ያስቀምጣል። - ተገቢውን ዘዴ ይመርጣል። - የመማሪያ አካባቢ ያዘጋጃል። - ጥሩ ጥያቄዎችን ይጠይቃል። - ተማሪዎችን ያበረታታል። - ይመራል፣ ይከታተላል፣ ግብረመልስ ይሰጣል። - የተማሪዎችን መማር ይገመግማል። - በውጤቱ መሠረት ትምህርቱን ያሻሽላል። አስፈላጊ ማስታወሻ (ማጠቃለያ) “ተማሪ ተኮር” ማለት መምህሩ ከክፍል ውስጥ ከጎን ቁጭ ብሎ ተማሪዎችን ብቻ መመልከት አይደለም። ተማሪ ተኮር ማስተማር ማለት “መምህሩ ሁሉንም መልስ ከመስጠት ይልቅ፣ ተማሪው መልሱን እንዲፈልግ መንገዱን ማመቻቸት ነው።” ወርቃማ የማስተማር መርህ “Good teaching is not about how much the teacher says; it is about how much the learner does, thinks and understands.” “ጥሩ ማስተማር መምህሩ ምን ያህል እንደተናገረ ሳይሆን፣ ተማሪው ምን ያህል እንደሠራ፣ እንዳሰበና እንደተረዳ ነው።" ማስታወሻ።፦ አሳታፊ ስነዘዴ ዓይነቶች እነዚህ ብቻ አይደሉም። ለመነሻና ለማስታወስ ያህል ነው። ዕለታዊ ዕቅድ ስናዘጋጅና ስንተገብር በዚህ መልኩ እንዲሆን ለመጠቆም ነው።

👍1
ማስታወቂያ ለቅድመ አንደኛ መምህራን እና ሞግዚቶች
በ 05/01/2019 ዓ.ም ትምህርት በይፋ መጀመሩ ይታወቃል ስለሆነም የተለያዩ ግብዓቶችን ስርጭት እየተደረገ ይገኛል ነገ ማለትም ሐሙስ 07/01/2019 ክፍሎቻችሁን ስለሚደራጅ ሁላችሁም ተገኝታችሁ ክፍላችሁን እንድታደራጁ እና ለመማር ማስተማር ስራ ዝግጁ እንድታደተርጉ እናሳስባለን ት/ቤቱ
ማሳሰቢያ፡-በነገው ዕለት የሚቀር ማንኛውም ሰራተኛ ኃላፊነቱን ሚወስድ ይሆናል፡፡

❤1
ቀን 08/01/2019 ዓ.ም
ለስም ጠሪ መምህራን በሙሉ
ሰኞ ማለትም በ11/01/2019 ዓ.ም ስም ጠሪ በተመደባችሁበት ክፍል እና ሴክሽን የተጣራ የተማሪ መረጃ በተለይ በስም እና በፆታ የተለየ መረጃ እስከ 4፡15 ሰዓት ድረስ ሪፖርት እንድታደርጉ በጥብቅ እናሳዉቃለን ፡፡
ማሳሰብያ ፡- ይህ መረጃ በፍጥነት ስለሚፈለግ መዘግየት የለበትም
- የክፍል አለቃ ያላስመረጣችሁ መምህራን እስከ 3 አለቃ እንድታስመርጡ እና ለተማሪዎች እዉቅና እንዲኖራቸዉ እንድታደርጉ እናሳዉቃለን ፡፡
- ይህ መረጃ ከቅድመ አንደኛ እስከ 8ኛ ክፍል ስም ጠሪ ለሆናችሁ መምህራን ይሆናል ፡፡

ቀን 10/1/2018
ማስታወቂያ ለቅድመ አንደኛ መምህራን በሙሉ
ሰኞ ማለትም 11/1/2019 ፈረቃ የሚጀምረው ከደረጃ 2 ሲሆን ማክሰኞ 12/1/2019 ደረጃ 1 ዕረቡ ደግሞ ጀማሪ 13/1/2019 የሚጀምር ይሆናል ከዚህ ጋር ተያይዞ ሁሉም መምህር በተመደበበት ክፍል እንዲገኝ እና ተማሪዎቹን እንዲቀበል እናሳስባለን
ማሳሰቢያ ማርፈድም ሆነ መቅረት አይቻልም
መልካም የት/ት እና የስራ ዘመን ይሁንላችሁ

Forwarded from Mebrat Teklu
የዛሬ ሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር የመክፈቻ ፕሮግራም ይህንን ሲመስል ያልተገኛችሁ መምህራን በቀጣይ እንድትገኙ እናሳውቃለን ።
Forwarded from FF
የልዩ ፍላጎት መለያ መስፈርት.docx
76.2 KB
🌼እንኳን ለብርሃነ መሰቀሉ በሰላም አደረሰ🌼
🌼በዓሉ 🌼የሠላም 🌼የአንድነት 🌼
🌼የመፋቀር 🌼 የመተሳሰብ፣፣? 🌼
🌼ይሁንልን🌼
🌼 መልካም በዓል🌼
🌼በዓሉ 🌼የሠላም 🌼የአንድነት 🌼
🌼የመፋቀር 🌼 የመተሳሰብ፣፣? 🌼
🌼ይሁንልን🌼
🌼 መልካም በዓል🌼