Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.75K photos
76 videos
20 files
998 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ከጀርመን ምክትል አምባሳደር ጋር ተወያዩ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 11/2019 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 12/148ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ

​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በኢትዮጵያ የጀርመን ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ዶክተር ፈርዲናንድ ቮን ዌይሄን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በውይይቱ ላይ ሰላም ጉዳይ የሀገርና የዜጎች ብቸኛ አማራጭ መሆኑን ጠቁመው ጠቅላይ ምክር ቤቱ እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለሀገር ሰላምና ልማት በጋራ እየሠሩ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።

ፕሬዝደንቱ አክለውም ጠቅላይ ምክር ቤቱ በአዋጅ መቋቋሙ ህዝበ ሙስሊሙ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ለሀገር ልማትና ዕድገት በሙሉ አቅሙ እንዲሰራ ከማድረጉ ባሻገር ለሰላምና ለሕዝቦች አብሮነት ትልቅ እሴት መጨመሩን አስረድተዋል።

​በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ዶክተር ፈርዲናንድ ቮን ዌይሄ በበኩላቸው የጀርመን መንግሥት ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በሰላም፣ በትምህርት፣ በሰብዓዊ እርዳታና በልዩ ልዩ የማኅበራዊ ልማት ዘርፎች በትብብር ለመሥራት ያለውን ጽኑ ፍላጎት ገልጸው ቀደም ሲል የተጀመሩ የጋራ መግባባቶችን በተጠናከረ ሁኔታ ለማስቀጠል እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

​በመጨረሻም ምክትል አምባሳደሩ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለተደረገላቸው ሞቅ ያለ አቀባበል በእራሳቸውና በኤምባሲያቸው ስም ምስጋና አቅርበዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ቨቨዠፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና የክልል መጅሊስ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የስራ አስፈጻሚ አባላት ስብሰባ መካሄድ ጀመረ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 12/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 11/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስፈፃሚ አባላትና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የክልል መጅሊስ አመራሮች፣ የኦዲትና እንስፔክሽን አባላት፣ የዕለማእ ጽህፈት ቤት አባላት እንዲሁም የዘርፍ ሰብሳቢዎች 2ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀመረ።

በቅድመ ​በጉባኤው ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈፃሚ አባላት፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደሮች እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አመራሮችና ስራ አስፈጻሚ አባላት እንዲሁም የኦዲትና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን አመራሮች፣ የዘርፍ ተጠሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እና የዑለማ ጉባዔ ሰብሳቢ የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በጉባዔው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ጉባኤው በሕገ መጅሉሱ አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 2 መሠረት የተጠራ መሆኑን ገልጸዋል።

የተወሰኑ የጉባዔው አባላት በሀገራዊ ምክክሩ ተሳታፊ የነበሩ በመሆናቸው ምክንያት ጉባዔው ከተያዘለት ቀነ ገደብ መዘግየቱንም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

ጉባኤው በዋናነት ምክር ቤቱ ባለፉት ጊዜያት ያከናወናቸውን ተግባራት፣ የኦዲትና ኢንስፔክሽን ሪፖርቶችን፣ እንዲሁም በቀጣይ አቅጣጫዎችና የትኩረት መስኮች ላይ በመመከር ውሳኔዎችን ያስልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

​አዲሱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚ ከጳጉሜ 2 ቀን 2017 ዓ.ል ጀምሮ ኃላፊነቱን ተረክቦ ወደ ሥራ መግባቱ ይታወሳል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1