Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.61K photos
76 videos
20 files
994 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ከእንግሊዝ አምባሳደር ጋር ተወያዩ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 14 /2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 13/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዌልችን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

​ውይይቱ ሁለቱ ወገኖች በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ተቋማዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነው።

አምባሳደር ዳረን ዌልች የእንግሊዝ መንግስት ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በጤና፣ በትምህርት እና በተለያዩ የልማት ዘርፎች በትብብር የመስራት ፍላጎት እንዳለው ገልጸው ጠቅላይ ምክር ቤቱ ላደረገላቸው መልካም አቀባበልም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
ሕዝበ ሙስሊሙ በእሳት አደጋ ጉዳት ለደረሠሰበት ቢላል ኢስላማዊ ፋውንዴሽን ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 14 /2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 13/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

ሕዝበ ሙስሊሙ በእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ የወደመውን
ቢላል ኢስላሚክ ፋውንዴሽን ቁጥር 2 የኡለሞች እና የዱዓቶች ማፍሪያ ኮሌጅ ዳግም ለመገንባት እንዲረባረብና ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርግ የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴው ጥሪ አቀረበ።

በቢላል ኢስላሚክ ፋውንዴሽን የተቋቋመው የሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ምክር ቤተ የስብሰባ አዳራሽ በእሳት አደጋው ምክንያት ስለወደመው ቢላል ቁጥር 2 የዑለማዎች እና የዱዓቶች ማፍሪያ ማዕከል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው ሰብሳቢ ሸይኽ መሀመድዘይን ዘህረዲን በዚሁ ዕለት እንደገለጹት በደቡብ ወሎ ዞን ከላላ ወረዳ የሚገኘው ታዋቂው ኢስላማዊ የትምህርት ማዕከል መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ.ል በደረሰበት ከፍተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ መውደሙን አስታውሰዋል።

​የኮሚቴ ፀሐፊ ዑስታዝ ሰዒድ ዓሊ በንባብ ባቀረቡት መግለጫ በእሳት አደጋው ምክንያት በርካታ ቁርአን፣ የኪታቦች ስብስቦች እና ታሪካዊ ቅርሶች ሙሉ ለሙሉ መቃጠላቸውን ገልጸዋል።

ከአካባቢው መጅሊስ የስራ ኅላፊዎች፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከመንግስት የተውጣጣ ኮሚቴ የአደጋውን መንስኤ እያጣራ መሆኑን የገለጸው መግለጫው በርካታ የኢስላም ሊቃውንትን እና ዱዓቶችን ማፍራት የቻለው የዕውቀት ማዕከሉ ዳግም ተገንብቶ ወደ ቀድሞ ስራው እንዲመለስ ህዝበ ሙስሊሙ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርግም በመግለጫው ጥሪ ቀርቧል።

ህዝበ ሙስሊሙ ድጋፍ ማድረግ እንዲያመቸውም በኮሚቴው እውቅና በተለያዩ ባንኮች አዳዲስ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች ተከፍተው እርዳታ ማሰባሰብ ስለመጀመሩ ተመላክቷል። የቢላል ቁርጥ 2 የኡለሞች እና የዱዓቶች ማፍሪያ ኮሌጅ መልሶ ማቋቋሚያ ሀብት ማሰባሰቢያ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡ 1000798973731
ዳሽን ባንክ፡ 2906011241111
አዋሽ ባንክ፡ 014381541058500
​አቢሲኒያ ባንክ፡ 268676872
ዘምዘም ባንክ፡ 0099178310301
ሂጅራ ባንክ፡ 1006506710003
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1