አራተኛው አህጉር አቀፍ የቁርኣን ውድድር ማጣሪያ በኦንላይን መካሄድ ጀመረ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 15/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 14/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ከሞሮኮው ንጉሥ ሙሐመድ 6ኛ የአፍሪካ ዑለማ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው 4ኛው አህጉር አቀፍ የቁርኣን ውድድር ማጣሪያ በኦን ላይን ተጀመረ።
ኢትዮጵያን ወክለው እየተወዳደሩ የሚገኙት ቃሩእዎች ሚያዚያ 2018 ዓ.ል በአዲስ አበባ በተደረገው ሀገር አቀፍ ውድድር ላይ አሸናፊ የነበሩ ሲሆኑ በሶስት የአቀራር ዘርፎች ከ48 ሀገራት ተወካዮች ጋር ይወዳደራሉ።
በ30 ጁዝ ሂፍዝ በሃፍስ ርዋያ ውድድር ራቢያ ኢስማኢል ሀሰን፣ በ30 ጁዝ በዋርሽ ርዋያ ሂፍዝ አቀራር ሙሀመድ አሚን አብደላ እንዲሁም በአምስት ጁዝ ቁርኣንን አሳምሮ በመቅራት (ቲላዋ) ነጃሺ በሺር አባ ሙካ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዑለማእ ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኅላፊ እንዲሁም የስልጠናና የውድድር ተጠሪ ዶክተር ማህሙድ ሁሴን አብደላ እንደገለጹት ውድድሩ የቁርኣንን ታላቅነት ከፍ ከማድረጉም በላይ የዑለማዎችን ድርሻ ለማጎልበት እና የወጣቶችን አቅም ለመገንባት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።
በዑለማእ ጉባዔ የፈትዋ አባልና የትምህርትና ካሪኩለም ዘርፍ ኅላፊ እንዲሁም የውድድሩ አስተባባሪ ዶክተር አብደላ ኸደር በበኩላቸው ውድድሩ ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት የሚካሄድ ውድድር የዳኝነት ሥራው በዓለም አቀፍ ዳኞች ይከናወናል ብለዋል።
በዚህ የማጣሪያ ውድድር አሸናፊ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች በሞሮኮ በሚዘጋጀው የመዝጊያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ሽልማት የሚቀበሉ ይሆናል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Telegram
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
በጂግጂጋ ከተማ ለ100 ዜጎች ነጻ ከአንገት በለይ ህክምና ተሰጠ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 16/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 15/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጂግጂጋ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የማህበራዊ አገልገሎት ዘርፍ ከሶማሌ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት እና ከጂግጂጋ ዩንቨርስቲ ሸይኽ ሀሰን የበሬ አጠቀላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በመተባበር በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ ሲሰጥ የቆየው ነጻ ከአንገት በላይ ህክምና አገልግሎት በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ።
ለስድስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ በቆየው በዚህ የህክምና ዘመቻ ከ100 በላይ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ነጻ የጆሮ፣ የአፍንጫ እና የጉሮሮ ህክምና ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።
የህክምና አገልግሎቱን መጠናቀቅ አስመልክቶ በተካሄደው የመዝጊያ መርሃ ግብር ላይ የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱረዛቅ ዚያድ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከዳዕዋና ሌሎች ኢስላማዊ ኃላፊነቱ በተጨማሪ ለማህበረሰብ ጤና መሻሻል እያደረገ ያለው ከፍተኛ ጥረት ለሌሎች ተቋማትም አርአያ የሚሆን ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ ዶክተር ኢብራሂም አህመድ በበኩላቸው ጠቅላይ ምክር ቤቱ በማህበረሰብ ጤና፣ በልማት እና በሌሎች የማህበራዊ አገልግሎት ዘርፎች የሚያከናውናቸውን ተግባራት በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እያከናወናቸው ላሉት ተግባራት ከሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ እና ከጂግጂጋ ዩንቨርስቲ ሸይኽ ሀሰን የበሬ አጠቀላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል።
በመዝጊያ ስነ ስርዓቱ ላይ የሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሀሙድ መሀመድ፣ የጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝደንት እና የሸይኽ ሀሰን የበሬ ጠቅላላ ሆስፒታል ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶክተር አብዱላህ ሁሴን እንዲሁም የሶማሌ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዝደንት ሸይኽ ሙሀመድ ዓሊን ጨምሮ በርካታ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው መልዕክት አስተላፍለዋል።

የ1447/2018 የሐጅ አፈጻጸም ግምገማ እና የ1448/2019 የሐጅ መስተንግዶ ስልጠናዊ ግምገማ ተጀመረ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 17/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 16/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
ሶስተኛው ዙር የ1447/2018 የሐጅ አፈፃፀም ግምገማ እና የ1448/2019 የሐጅ መስተንግዶ ለክልል ሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊዎችና የምዝገባ ጣቢያ ሙያተኞች የተዘጋጀ ስልጠናዊ ግምገማ መካሄድ ጀመረ።
በስልጠናዊ ግምገማው የመክፈቻ መርሀ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ዑስታዝ ፈይሰል ዑመር ፤ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከተጣለበት የሰላምና የልማት ስራዎች ጎን ለጎን የሐጅና ዑምራ ጉዞን በበላይነት በማስተዳደር ለሕዝበ ሙስሊሙ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት በትጋት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም በ1447/2018 የሐጅ ወቅት በሳውዲ አረቢያ የሐጅ ሚኒስቴር በተዘጋጀው የ"ለበይቱም አዋርድ" ጠቅላይ ምክር ቤቱ የዳይመንድ ደረጃ ተሸላሚ በመሆን የሕዝባችንንና የሀገራችንን ስም በበጎ ማስጠራት መቻሉን አውስተዋል።
ወርቃማ ውጤቱ ከምዝገባ ማስተባበሪያ ጣቢያ ሰራተኞች ጀምሮ የዑለሞች፣ የክልል መጅሊሶችና የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ጥረት ውጤት መሆኑን በመጠቆም፣ በዘንድሮው ዓመትም ይህንን ስኬት ለማስጠበቅ በትጋት እንዲሰራ የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የተቋማትና ማህበራት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ሐጅ ሽኩር ቃሲም በበኩላቸው፤ ሁጃጆችን ማገልገል፣ መንከባከብና ማስተናገድ እጅግ ከፍተኛ ምንዳ (አጅር) የሚያስገኝ ታላቅ የዒባዳ ዘርፍ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ዘርፍ የክልል ምዝገባ ማዕከላት ኃላፊ ሼይኽ ኢስሀቅ አደም በበኩላቸው ፤ አገልግሎቱን በሰው ኃይልና በግብአት በማዘመናችን ለአል ራህማን እንግዶች የሚሰጠው አገልግሎት በከፍተኛ ደረጃ ማሻሻል ተችሏል ብለዋል።
በ1447/2018 የሐጅ መስተንግዶ ወቅት የታዩ ውስንነቶችን በማረም በዘንድሮው ዓመት የተሻለ አገልግሎት ለሁጃጁ ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት በሙሉ መደረጉን ኅላፊው ገልጸዋል።