Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.61K photos
76 videos
20 files
994 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
የለበይቱም እውቅናና ሽልማት ለ2019/1448 ዓ.ሂ. የሐጅ አገልግሎት ቅድመ ዝግጅት መሠረት ሆኖ ቀጥሏል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 18/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 17/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |

​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሀጅና ዑምራ ዘርፍ በ2018 ዓ.ል /1447 ዓ.ሂ. ባስመዘገበው የላቀ የአፈጻጸም ብቃት ያገኘው የ«ለበይቱም» ሽልማት ለ2019/1448 ዓ.ሂ. የሐጅ አገልግሎት ግብዓት ሆኖ እንዲያገለግል የሚያግዝ የእውቅና መርሐ ግብር በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተካሄደ።

​በመርሐ ግብሩ ላይ በሳዑዲ ዓረቢያና ኦማን የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ዶክተር ሙክታር ኸድር፣ የጠቅላይ ምክር ቤቱ በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ሷሊህ፣ የኤምባሲውና የቆንስላ ጽህፈት ቤቱ አባላት እንዲሁም የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ተወካዮች ተገኝተዋል።

​አምባሳደር ዶክተር ሙክታር ኸድር እና ዶክተር መሀመድ ሷሊህ በዝግጅቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የ«ለበይቱም» ሽልማት የጽሕፈት ቤቱ ብቻ ሳይሆን የተባባሪ ተቋማትና የመላው ኢትዮጵያዊያን የጋራ ጥረት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።

ሽልማቱ የስኬት መደምደሚያ ሳይሆን በቀጣይ ስራዎች ለሑጃጆች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያነሳሳ ምርጥ ተሞክሮ መሆኑንም አክለዋል።

​የ1448 ዓ.ሂ. የሐጅ አገልግሎትና መስተንግዶ ዝግጅትን ውጤታማ ለማድረግ ከቀድሞ ልምዶች በመማር በቅድመ ዝግጅት፣ በተቋማት ቅንጅት፣ በዲጂታል ሥርዓቶችና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ በምዝገባ ማዕከላት አቅም ግንባታ እና ከአገልግሎት አቅራቢዎች ጋር በሚደረግ ትብብር ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራም በመርሃ ግብሩ ላይ ተመላክቷል።

መርሐ ግብሩ የባለፈውን ዓመት ጥንካሬዎች በማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በመፍታት ለ1448 ዓ.ሂ. የሐጅ ተጓዦዥ የተቀናጀና የላቀ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል የጋራ አቋም በመያዝ ተጠናቋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ 100 ኢማሞች እና ኡስታዞች የተሰጠው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቀቀ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 19/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 18/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

​ወላይታ ሶዶ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማዕ ጉባኤ ጽህፈት ቤት ከቡንያን ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚገኙ 50 ኢማሞች እና 50 ኡስታዞች ሲሰጥ የነበረውን የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቋል።

​በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስተባባሪነት በወላይታ ሶዶ ከተማ በተካሄደው በዚህ የስልጠና ማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ የክልሉ የመጅሊስ ኃላፊዎች፣ ዑለሞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

​በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማዕ ጉባዔ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ እና የስልጠናና የውድድር ተጠሪ ዶክተር ማህሙድ ሁሴን አብደላ እንደተናገሩት፣ ሰልጣኞቹ ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር ማህበረሰቡን በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በቀጣይም ስልጠናው ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች ጥናትን መሠረት ያደረጉ ተመሳሳይ የአቅም ማጎልበቻ ፕሮግራሞች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

​ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሀጅ ያሲን ከድር በበኩላቸው ስልጠናውን የሰጡ ተባባሪ አካላትን አመሥግነው በቀጣይም በሚደረጉ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ላይ የክልሉ መጅሊስ ተባብሮ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ዑለሞች ፣ የመጅሊስ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ ስልጠናው ለኡስታዞችና ለኢማሞች የነበራቸውን እውቀት ለማሳደግና የማህበረሰብ አገልግሎታቸውን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ተመልክቷል።

•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1