Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.56K photos
76 videos
20 files
993 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
ሀገር አቀፍ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ላይ ፈትዋ ለመስጠት የሚረዳ ምክክር አውደ ጥናት በአዳማ ተጀምሯል።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 19/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 18/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዳማ |

አውደ ጥናቱ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን የፌደራል፣ የክልልና የከተማ የዑለማ ጉባዔ የፈተዋ ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የጤና ሚኒስቴር እና የኮራህ (CORHA) የሥራ ኅላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በአውደ ጥናቱ መክፈቻ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማ ጉባዔ የፈተዋ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ጀይላን ኸድር ባደረጉት ንግግር ፣ ፈትዋ በኢስላም ህግ እና አስተምህሮ ውስጥ ከፍተኛ እና አስፈላጊ ቦታ ያለው ሃይማኖታዊ ውሳኔ ወይም ብያኔ የሚሠጥበት ሂደት መሆኑን ተናግረዋል።

አዲስ ለተከሰቱ ወይም ግልጽ ያልሆኑ ሃይማኖታዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ግላዊ ጉዳዮች ከቁርኣን እና ከሐዲሥ በመነሳት የሚሰጠው ህጋዊ ማብራሪያ ወይም ውሳኔ በቀጣይ አለማዊ ህግ ሆነው ሊያገልገል እንደሚችሉም ተናግረዋል።
በዚህ አወደ ጥናትላይ የሚቀርቡ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ፅሁፎች በዑለሞቹ ታይተው ፈተዋ ( ሃይማኖታዊ) ብያኔ እንደሚሰጥባቸውም ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥነ የሕዝብ ፈንድ (UNFPA) ተወካይ ሚስተር ቶ ታይዎ ኦሉዮሚ፣ በበኩላቸው የምክክር መድረኩ ከዑለሞቹ ጋር የበለጠ መግባባትን በመፍጠር፣ እምነትን በማጠናክር፣ የቤተሰቦችና የማህበረሰቦች ደህንነትና የአናቶችና የህጻናት ጤና ላይ የሚሰጠውን ሃይማኖታዊ ብያኔ መሠረት በማድረግ መመሪያን ለማዘጋጀት እድል ይፈጥራል ብለዋል።

የኮራህ ተወካይ ወ/ሮ ቤተልሄም በዛብህ በኢስላም አስተምህሮ መሠረት በዑለሞች የሚሠጠውን የቤተሰብ እቅድ አገልግሎትን ብያኔ መሠረት አድርገው በቀጣይ በትብብር ለመሥራት ድርጅታቸው ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
ዛሬ በአዳማ የተጀመረው ሀገር አቀፍ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ፈትዋ ለማዘጋጀት ግብኣት ለማሰባሰብ እንዲቻል ምክክር አውደ ጥናቱ ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎችና ተሞክሮዎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።

•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
#የስራ #ቅጥር #ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የሥራ መደቦች መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።