Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.61K photos
76 videos
20 files
994 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
ሀጅና ዑምራ ዘርፉ ለ2019 (1448 ዓ.ሂ.) ሁጃጆች የምግብ አቅርቦት ውል ስምምነት ተፈራረመ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 27/2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 26/1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መካ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሀጅና ዑምራ ዘርፍ ለ2019 (1448 ዓ.ሂ.) ኢትዮጵያውያን ሁጃጆች የሚቀርበውን የምግብ አገልግሎት ጥራቱን የጠበቀ ማድረግ የሚያስችለውን የውል ስምምነት ከሳዑዲ ዓረቢያ የምግብ አቅራቢ ኩባንያዎች ጋር ተፈራረመ።

​የውል ስምምነቱ በሀጅ ወቅት ለሁጃጆች ምግብ በወቅቱና በጥራት ለማቅረብ እንደሚያስችል የተገለጸ ሲሆን የምግብ አቅርቦቱ የሁጃጆችን ጤና፣ ደኅንነትና ምቾት የጠበቀ ይሆናልም ተብሏል።

​የምግብ አቅራቢ ድርጅቶቹ በየዕለቱ የሚያቀርቡት ምግብና መጠጥ ጥብቅ የንጽህና፣ የጥራትና የደኅንነት መስፈርቶችን ማሟላቱ የሚረጋገጥ ሲሆን አቅርቦቱ ስምምነት በተደረበት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በመካ፣ በመዲና እና የሐጅ ሥርዓት በሚፈጸምባቸው ቦታዎች ሁሉ ያለ ምንም መስተጓጎል ተደራሽ ይሆናል።

በአቅርቦት ሂደት ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ እክሎችን በቅንጅት ለመፍታት የሚያስችል አሠራር ለመዘርጋትም የውል ስምምነቱ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።

​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሀጅና ዑምራ ዘርፍ የሐጅ አገልግሎትና መስተንግዶውን ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ለማጠናቀቅ እያከናወናቸው ያሉትን ተግባራት በቀጣይም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክቷል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1