Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
11.2K subscribers
6.61K photos
76 videos
20 files
994 links
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
Download Telegram
በሦስት ዘርፍ የተካሄደው ሀገር አቀፍ ነቢያዊ የሐዲስ ውድድር ተጠናቀቀ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 28፣ 2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 27 1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ

​በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የዑለማ ጉባኤ እና በሞሮኮ ንጉሥ መሐመድ 6ኛ ፋውንዴሽን ትብብር የተዘጋጀው 3ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የነቢያዊ ሐዲስ የማጣሪያ ውድድር አሸናፊዎች ተለዩ።

በሶስት ደረጃ ተከፍሎ በተደረገው ውድድር ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚ አባልና የመስጂድ ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም የውድድሩ የደኝነት ኮሜቴ አባል ሸይህ እንድሪስ ዓሊ ውድድሩን ያዘጋጁትንና ያስተባበሩትን አካላት በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም አመስግነዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዑለማ ጉባኤ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ እንዲሁም የስልጠናና የውድድር ዘርፍ ተጠሪ እና የውድድሩ ዳኛ ዶክተር ሸይኽ መሐመድ ከማል በበኩላቸው ዑለማ ጉባኤው ከሞሮኮ ንጉሥ መሐመድ 6ኛ ፋውንዴሽን ጋር ያለውን ግንኙነት ከውድድር እና ከአቅም ግንባታ ስልጠና ባሻገር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል።

የማጣሪያ ውድድሩ አሸናፊዎች በጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማ ጉባኤ የትምህርት ካሪኩለም ዘርፍ ኃላፊና የውድድሩ ዋና አስተባባሪ ዶክተር አብደላ ኸድር ይፋ የተደረገ ሲሆን በሦስቱም የውድድር ዘርፎች አንደኛ የወጡት ሦስት አሸናፊዎች በሞሮኮ በሚካሄደውና 48 ሀገራት በሚሳተፉበት ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው እንደሚሳተፉም ገልጸዋል።

የማጣሪያ ውድድሩ አሸናፊዎች፡-
​
40 ሐዲስ በመሀፈዝ

​1ኛ፡ አብዱልጀሊል አሊ ( ከአፋር)
​2ኛ፡ አብዱራህማን ናስር (ከኦሮሚያ)
​3ኛ፡ አብድልበር ድሉ (ከአዲስ አበባ)

30 ሐዲስ ከነማብራሪያው በመሀፈዝ

​1ኛ፡ መሐመድ ኸደር (ከአዲስ አበባ)
​2ኛ፡ ቃሲም ሸምሰዲን (ከአዲስ አበባ)
​3ኛ፡ ሙስጠፋ መሐመድ (ከኦሮሚያ)

​30 ሐዲስ በከነ ህግጋቱ መሀፈዝ
(ሙስጠላሐል ሐዲስ)

​1ኛ፡ አይመን ጀማል (ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ)
​2ኛ፡ ኢብራሂምዓሊ (ከአፋር)
​3ኛ፡ ኢብራሂም መሐመድ (ከአዲስ አበባ)
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ​በአማራጭና በጎልማሶች ትምህርን ዙሪያ ምክክር አካሄደ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መስከረም 30፣ 2019 ዓ.ል| ረቢዑል ሳኒ 29 1448 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ መደበኛ ባልሆነ የትምህርት ፕሮግራም መሠረታዊ የአማራጭ እና የጎልማሶች ትምህርትን ለደረሳዎችና ዑለሞች ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የግንዛቤ ፈጠራና የምክክር መድረክ አካሄደ።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የስራ አስፈጻሚ አባልና የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ ዚያድ ዓልይ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስጀመሩት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ የልማትና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኸ ሐሚድ ሙሣ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ፕሬዝደንቱ ሸይኽ ሀሚድ ሙሳ በዚህ መልዕክታቸው ጠቅላይ ምክር ቤቱ በየጊዜው ተቋማዊ ቁመናውን በማሻሻልና የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን አደራ የሰጠውን ህዝበ ሙስሊም ለማገልገል እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ሸይኽ ሐሚድ ሙሳ አክለውም በትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የሚሠራው ሥራ ለዑማው ዘላቂ ጥቅም የሚያስገኝ በመሆኑ በኢስላማዊ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ ደረሳዎች እና ዑለማዎች ዘመናዊና አማራጭ የጎልማሶች ትምህርት የሚያገኙበት ሁኔታ መመቻቸቱ ሀገራዊ ሚናቸውን ከፍ ያደርጋል ብለዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ የትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አልዩ ሰዒድ ዘርፋ በበኩላቸው የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ በ2019 በአማራጭ መሠረታዊ ትምህርትና በጎልማሶች ትምህርት ፕሮግራም ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ በትኩረት እንደሚሰራ አብራርተዋል።

በትምህርት ዘርፍ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ መፍጠር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ ውይይት ማድረግ በመንፈሳዊና በመደበኛ የትምህርት ዘርፍ ያለውን ቅንጅት ለማሻሻል እንደሚያግዝም አቶ አልዩ ሰዒድ አክለዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶች መሠረታዊ ትምህርት ዴስክ ሃላፊ አቶ ዘላለም አራጋው አማራጭ እና የጎልማሶች ትምህርት አተገባበር እና የፖሊሲ አቅጣጫዎች ዙሪያ ለውይይት መነሻ የሚሆን ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል።

በመጨረሻም በቀጣዩ በጀት ዓመት መሠረታዊ የአማራጭ እና የጎልማሶች ትምህርት ተግባራዊ የሚያደርጋቸውን መርሃ ግብሮች በማጠናከር ዑለማዎችንና ደረሳዎችን በማብቃት ለህዝበ ሙስሊሙ የተሻለ አገልግሎት እንዲችሉ ማድረግ እንደሚገባ የውይይቱ ተሳታፊዎች ሃሳባቸውን አንስተዋል።

በውይይቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የዑለማ ጉባዔ ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ ጁነይድ ሐምዛ፣ ሥራ አስፈጻሚ አባላት፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያን ይከታተሉ | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1